Topics related to cultures, arts, languages, arts such as humor, music, traditional literary genres of poems, ግጥም ፣ ቅኔ ፣ ተረትና ምሳሌ)
by password » Sun Mar 08, 2020 10:01 pm
Last edited by
password on Fri May 08, 2020 7:57 pm, edited 4 times in total.
-
password
- ኮትኳች

-
- Posts: 324
- Joined: Fri Apr 04, 2008 2:02 am
- Location: Europe
-
by password » Fri Apr 24, 2020 5:33 am
445 ግዜ ተጎብኝቷል.. ይህ ፖስት
Google books ጎራ ብለው መጽሐፉን የገዙት ቁጥር እልፍ ሊሆን እንዴት እንደቻለ አልገባኝም...
ምናልባት ሼርና ሸር ይሆን?
ቀልዱን ልተውና የገረመኝን ልንገራችሁ...
ይህ መይሐፍ በብዙ የውጭ ቋንቋዎች ተተርጉሞ በbest seller ነት ረጅም ግዜ የቆየ ነበር... ፊልም ሁላ እንደተሰራበት ይታወቃል።
የኛ ሰው ግን ያገሩ ጉዳይም ሆኖ፣ መጽሐፉን ያዘዘ አንድ አለመኖሩ በጣም ገርሞኛል... ያውም ለሥነጽሑፍ ቅርበት ወይም ዝንባሌ አለው ከሚባል ወገን ውስጥ!
እንደ ተርጓሚ እኔ በግሌ ከመጽሐፍ ሽያጭ የማገኘው ጥቅም እምብዛም ነው... በመተርጎም ብቻ 52 000 kr (ወደ 200 000 ብር ማለት ነው.) ተከፍሎኝ... ሌላም አበል አፍሼበት ዞር ብያለሁ... ምስጋን ለስዊድን መንግስት ባህል ምክር ቤት። ትንሽ ለሚሞጫጭር ሳንቲም ይዶጋግማሉ።
አሳታሚውም ቢሆን የህትመት ወጪውን የምትሸፍን የሆነች ድጎማ አያጣም። ግን ከዚህ በኋላ ለዚህ መጽሐፍ ጠል: ቦልታኪ ትውልድ እንኳን መጽሐፍ አንድ በራሪ ቅጠል ይበጥሳል የሚል እምነት የለኝም...
"ቦርጫም ሁላ ድራፍት መጋትና ሺሻ መንፋት ብቻ ነው... ሌላ ምን ያውቃል" ሲል ሰምቼዋለሁ...
ከዚህ ሃፍረት የምንማረው አንድ ቁምነገር አለ:: ለቦርጫታሙ ትውልድ ብዙ የሚደረግ ነገር ላይኖር ይችላል። ከእንግዲህ አንብብ እያልን በመጽሐፍ ጥራዝ ብንፈነካክተው ያምጽብናል እንጂ አይሰማንም። እሱ ይፖልትክ:: ታዳጊውን ግን ፣ ቀላል ባይሆንም: ማዳን ይቻላል የሚል እምነት አለኝ።
ታዳጊው የዘመኑ ቴክ ባመጣው እንደ ፌስ ቡክ፣ ዩትዩብ፣ ኔትፍሊክስ ወዘተ
ዓይነቶች የመዝናኛ አፖች ተጠምዶ ለመጽሐፍ ማንበቢያ ግዜም ሆነ አቅል ላይኖረው ይችላል ። ይሁን እንጂ መጻሕፍት በገጽ ብዛትና በይዘት በእድሜውና በግንዛቤው ልክ ታቅደውና ተመዝነው ቢዘጋጁለት፣ ወላጅና መምህራን ደግሞ ሳይሰለቹ የበኩላቸውን ሚና ቢጫወቱ ፣ አዲስ አንባቢ ትውልድ መፍጠር ይቻላል ብዪ አገምታለሁ።
እና የሚመለከታችሁ እስኪ አስቡበት።
በሉ ከመጽሐፍ ብቻ ሳይሆን ከክሮናውም ራቅ ለማለት 2 ሜትር ተራራቁ ...
ፓስ.
-
password
- ኮትኳች

-
- Posts: 324
- Joined: Fri Apr 04, 2008 2:02 am
- Location: Europe
-
Return to Warka Culture and Literature - ዋርካ ባህልና ሥነ ጽሑፍ
Who is online
Users browsing this forum: No registered users and 4 guests