መግባቢያ ቋንቋችን

Topics related to cultures, arts, languages, arts such as humor, music, traditional literary genres of poems, ግጥም ፣ ቅኔ ፣ ተረትና ምሳሌ)

መግባቢያ ቋንቋችን

Postby password » Sun Aug 23, 2020 6:37 pm

አማርኛ
ሰሞኑን አንድ ባልሥልጣን አማርኛን አስመልክተው የተናገሩት ገርሞኝ ነው ብቅ ያልኩት። እንዴት ናችሁ ዋርካዊያን? ለመሆኑ አላችሁ?

ባለሥልጣኑ፣ በተለይ አማርኛን የማዳከም ስራ እየተሰራ መሆኑን የሚናገሩት እንደ ጀብድ ነበርና እስኪ የተሰማኝን ላካፍላችሁ።

አንድ ማህበረሰብ ሌላ መግባቢያ መሳሪያ መጨመሩ ብልጠት ነው፣ በእጁ ያለውን መግባቢያ መሳሪያ ማዳከም ግን ሞኝነት በቀር ሌላ ሊሆን አይችልም። አማርኛ እዚህ የደረሰው በዘመናት ውስጥ በልዩ ልዩ ዘርፎች ሲሰራበትና ሲያገለግል በመቆየቱ፣ በሂደትም እንደየዘመኑ ሁኔታ እየተሻሻለ፣ እየጎለበተ፣ እየሰፋ በመሄዱ እንጅ ሌሎች ቋንቋዎች እንዳይዳብሩ በመጫን አይደለም። ቋንቋው የግዜን ፈተናዎች አልፎ ታሪክ ባመጣው አጋጣሚ አገር አቀፍ ሆኗል። አንዴ እዚህ ደረጃ የደረሰ ቋንቋን ቢቻል የበለጠ አስፋፍተህ መቶ ሚሊዮን ሰዎችን ማግባቢያ መሳሪያ አድርገህ ትጠቀምበታለህ እንጁ እሱን አዳክመህ በሌላ ለመተካት መሞከር የቋንቋን ምንነት ከለመገንዘብ የሚፈጠር ስህተት ነው።

በእጅህ ያለ ዶላር የትም ብትሄድ የምትጠቀምበት ገንዘብህ ነው። የአሜሪካኖችን ጉራ ስለጠላህ ዶላርህን አልጠቀምበትም ብትል የምትጎዳው ራስህ ነህ። ቋንቋም ያው ነው። ካወቅከው ያንተ ነው። የአንድ ቋንቋ ባለቤት ተናጋሪው ራሱ ነው። አማርኛ የምትችል ከሆነ አማርኛ አለህ፣ ባለቤቱ ሆነሃል ማለት ነው።

የአፍ መፍቻ ቋንቋቸው አማርኛ ያልሆነ ልጆች ፣ በአማርኛ ተናጋሪ ልጆች የሚበለጡ፣ አማርኛ ተናጋሪዎቹ (advantage) ቅድሚያ እንደሚያገኙ አድርገው አንዳንድ ምሁራን ሲናገሩ ይደመጣሉ። ይሄም ስህተት ነው። ልጆች ከአፍ መፍቻ ቋንቋቸው ሌላ በርካታ ቋንቋዎች በቀላሉ መማር ይችላሉ። አማርኛ ተናጋሪ ካልሆነ ቤተሰብ የሚወለዱ ልጆች በተለይ ከ10 ዓመት በታች ያሉቱ አማርኛ ቢማሩ አፍ መፍቻው አማርኛ ከሆነው ልጅ ባልተናነሰ ቋንቋውን የሚመልኩት መሆኑ በጥናትና በተግባር የተረጋገጠ ሃቅ ነው ። አማርኛ ተናጋሪው ልጅ አማርኛ የማይናገረውን በቋንቋ የሚመራው ለጥቂት ወራት ብቻ ነው። ማራቶን ወይም አስር ሺ ኪሎ ሜትር ሩጫ ላይ ሯጮች ከፊት ስላሉ ሩጫውን በአሸናፊነት ያጠናቅቃሉ ማለት እንዳልሆነ ሁሉ፣ ወላጆቹ አማርኛ የሆነ ልጅ ፣ በሌሎቹ ላይ የቋንቋው ቅድሚያ ይኖረዋል ወይም ይበልጣቸዋል ማለት አይደለም። ለዚህ ነው አፋቸውን በሌላ ቋንቋ የፈቱ ግን አማርኛ በግዜ የተማሩ ሰዎች፣ በንግግርም ሆነ በስነጽሑፍ ከማንም ያላነሰ ሆነው የምናገኛቸው። እነ ፍቅሬ ቶሎሳና ጸጋዬ ገ/መድሕን መጥቀስ ይቻላል።

አማርኛን ማዳከም የሚባል ሃሳብም ሲነገር ሰምቻለሁ። ይህ ቀላል አይደለም። ሊተገበርም አይችልም። ከተሞከረም በርካታ ምዕት ዓመታት ይፈጃል። አማርኛን እንደ ምንም በሌላ መተካት የሚሞክር ከሆነ ደግሞ ከአማርኛ ይበልጥ በሥራና በሥነጽሑፍ የዳበረ ቋንቋ ታመጣ እንደሆነ እንጅ ገና ለገና ብዙ ሰው የሚናገረው አንድ ቋንቋ ስላለ ብቻ እሱ ለአስተዳደራዊ አገልግሎት መዋል ይችላል ማለት አይደለም።

አማርኛን ማዳከም በተግባር የማይሳካ እኩይ ፖለቲካ ስለሆነ ልጆቻችሁን እንዳይማሩ የምትከለክሉ ወላጆች ኋላ ጉድ እንዳትሆኑ፣ የልጆቻችሁን ዕድል ነው የምታበላሹት። ዶ/ር አብይ አማርኛ ባይችል ኖሮ እንኳን ጠቅላይ ሚንስትር የበሻሻ ቀበሌ ሊቀመንበር አይሆንም ነበር። አማርኛ አትማሩ የሚሏችሁ ሁሉ አማርኛን ከአማርኛ ተናጋሪው ባላነሰ ይናገሩታል።

እኔ በመሠረቱ ከአማርኛ ተናጋሪዎች አብራክ የወጣሁ ሰው አይደለሁም፣ የአፍ መፍቻ ቋንቋዬን ብቻ እንዳውቅ ብወሰን ኖሮ ዛሬ የእማርኛ ልቦለዶች በመሞጫጨር እና በውጭ ቋንቋ የተጻፉ መጽሐፍትም ወደ አማርኛ በመተርጎም መጠቀም ባልቻልኩም ነበር። ባለፈው ዓመት ከስዊድንኛ ወደ አማርኛ የተረጎምኩት 438 ቀናት የተሰኘው መጽሐፍ ገና ለገበያ ሳይወጣ፣ ለትርጉንም ሥራ ብቻ 250 000 የኢት ብር ገደማ ( ከመደበኛ ሥራዬ በተጓዳኝ); አፍሼበታለሁ። እንደ ገንዘብ ማግኛ እንኳ ይጠቅማል ማለቴ ነው።

እና ወዳጆቼ፣ የነ ስልጣን በኪሴን ወሬ አትስሙ። አማርኛ ተጭኖብህ ነው ሲሉ “እንኳን ተጫነብኝ። ” ነው መልሱ። ቋንቋ በመጫን የሚገባ ቢሆን ኖሮ ምን ትምህርት ቤት አመላለሰን፣ አስጭነን እንገላገል አልነበር።

በሌላ መጣጥፍ እስክንገናኝ። ሄይ ዶ!
password
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 330
Joined: Fri Apr 04, 2008 2:02 am
Location: Europe

Re: መግባቢያ ቋንቋችን

Postby ዘርዐይ ደረስ » Sun Aug 30, 2020 6:01 pm

password
ሐሳብህ ጥሩ ነበር፡፡ባለስልጣኑ ያሉት ግን ከተጨባጭ ሁኔታው ብዙ የራቀ አይመስለኝም፡፡1983 አማርኛ የነበረውን አቅምና ዘንድሮ ያለውን ለማወዳደርና ክፉኛ መዳከሙን ለመረዳት ምሑራዊ ጥናት አያስፈልገውም፡፡
''ፍምን እፍ ብትላት ትነዳለች ትፍም ብትልባት ትጠፋለች ሁለቱም ሁሉ ከአንድ አፍ ይወጣሉ ::''መጽሐፈ ሲራክ 28:12
ዘርዐይ ደረስ
ውሃ አጠጪ
ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1380
Joined: Sat Oct 23, 2004 3:52 am
Location: ethiopia


Return to Warka Culture and Literature - ዋርካ ባህልና ሥነ ጽሑፍ

Who is online

Users browsing this forum: No registered users and 3 guests