ይድረስ ለልጅ ቅጣው ያየህይራድ

The Love Forum (love, relationship) (የኔ ቆንጆ እንተዋወቅ :-)

ይድረስ ለልጅ ቅጣው ያየህይራድ

Postby ቱሉቦሎ » Thu Oct 17, 2013 6:56 pm

ይድረስ እጅጉን ለማከብርህ ለወዳጄ ለባራምባራስ ያየህይራድ ልጅ ለልጅ ቅጣው ያየህይራድ

አባትህ እጅግ በጣም ወዳጄ ነበሩ : ፈሪሀ እግዚአብሄር ያደረባቸው ሰው የሚወዱና ቸር ሰው ነበሩ :: ዘር ከዛፉ አይርቅም እንዲሉ አንተም ይኸው እግዚአብሄር ባርኮህ ለሁላችን መገልገያ ይህንን ገጽ አቅርበህልን የያየህይራድ ዘር ይባረክ እያልን እየተጠቀምንበት ነው ::

አሁን ግን ችግር አለ :: ችግሩ ወዲህ ነው
እርኩስ መንፈስ ዋርካን በምች ከመታው ወዲህ በግል የተጣጣፍነውን ማየት በግል መጣጣፍ አልተቻልም :: በዚህ በለገስከን ገጥ ተዋውቄ የተዋዳጀኋት ፋጤ ጥሩ ጋደኛዬ ሁናለች :: አሁን ግን ከፋጤ ጋር መጣጣፍ ስላልቻልኩ : ሲከፋኝም ፋጤ የጣፈችልኝን እያወጣሁ ማንበብ ስለተቸገርኩ ይህንን እንድታስተካክልልኝ ልጄን እግርህ ላይ ወድቄ እማጠናለሁ

አደራህን ልጄ የፍቅር ነገር ነውና የፋጤን መልክቶች ሁሉንም እንዳሉ አድርገህ ቸል ሳትል ነገ ዛሬ ሳትል : ሳትውል ሳታድር ይቺን ነገር መላ ታበጅላት ዘንድ እለምናለሁ

እግዚአብሄር በቸርነቱ ይባርክህ
ጠጉርክን አለምልሞ ጎፈሬ ያድርግህ

አክባሪህ

ባላምባራስ ቢተው ተካልኝ ከሸንኮራ ሸዋ
ቱሉቦሎ
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 195
Joined: Tue Sep 04, 2012 8:13 pm

Re: ይድረስ ለልጅ ቅጣው ያየህይራድ

Postby እሰፋ ማሩ » Tue Sep 05, 2017 7:49 pm

የዋርካ አስተዳዳሪዎችና ባለቤቶች
ይህ የቀድሞ ማሳሰቢያ በዚያን ወቅት ተገቢ ስለነበር ስምታችሁ መስተካከል የሚገባውን በማስተካከላችሁ አሁን ፖስት የማድረግ ችግር የለብንም፡፡የወቅቱ ችግር ደግሞ ዋርካን በክፉ ስድብ ዘርን ሳይቀር በተለይ አማራና ኦሮሞውን የሚሰድቡ የወያኔ ጀሌዎች የፖለቲካ አምድ መፈንጫ ሆኖ አሁን መስተካከሉ ደስ ብሎናል ይህ ርምጃ ወደሌቹም አምዶች ይተላለፍ፡፡
ከምስጋና ጋር፡፡
ቱሉቦሎ wrote:ይድረስ እጅጉን ለማከብርህ ለወዳጄ ለባራምባራስ ያየህይራድ ልጅ ለልጅ ቅጣው ያየህይራድ

አባትህ እጅግ በጣም ወዳጄ ነበሩ : ፈሪሀ እግዚአብሄር ያደረባቸው ሰው የሚወዱና ቸር ሰው ነበሩ :: ዘር ከዛፉ አይርቅም እንዲሉ አንተም ይኸው እግዚአብሄር ባርኮህ ለሁላችን መገልገያ ይህንን ገጽ አቅርበህልን የያየህይራድ ዘር ይባረክ እያልን እየተጠቀምንበት ነው ::

አሁን ግን ችግር አለ :: ችግሩ ወዲህ ነው
እርኩስ መንፈስ ዋርካን በምች ከመታው ወዲህ በግል የተጣጣፍነውን ማየት በግል መጣጣፍ አልተቻልም :: በዚህ በለገስከን ገጥ ተዋውቄ የተዋዳጀኋት ፋጤ ጥሩ ጋደኛዬ ሁናለች :: አሁን ግን ከፋጤ ጋር መጣጣፍ ስላልቻልኩ : ሲከፋኝም ፋጤ የጣፈችልኝን እያወጣሁ ማንበብ ስለተቸገርኩ ይህንን እንድታስተካክልልኝ ልጄን እግርህ ላይ ወድቄ እማጠናለሁ

አደራህን ልጄ የፍቅር ነገር ነውና የፋጤን መልክቶች ሁሉንም እንዳሉ አድርገህ ቸል ሳትል ነገ ዛሬ ሳትል : ሳትውል ሳታድር ይቺን ነገር መላ ታበጅላት ዘንድ እለምናለሁ

እግዚአብሄር በቸርነቱ ይባርክህ
ጠጉርክን አለምልሞ ጎፈሬ ያድርግህ

አክባሪህ

ባላምባራስ ቢተው ተካልኝ ከሸንኮራ ሸዋ
እሰፋ ማሩ
ውሃ አጠጪ
ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1229
Joined: Mon Sep 12, 2016 8:47 pm

Return to Warka Intimate - ዋርካ ፍቅር

Who is online

Users browsing this forum: No registered users and 1 guest