ሙዝ1 wrote:አህመዴ ሽኩረን
ምን መሰለህ ሰዉ በህይወት ዘመኑ በቀደደዉ አልያም በተቀደደለት ቦይ ስታልፍ ሁሌም መልካም ብለህ የምታደርጋቸዉን እያደረክ ታልፋለህ:: እኔም ያንን ነበር ሳደርግ የነበረዉ ወደፊትም የማደርገዉ:: በያንዳንዷ ርምጃህ ታዲያ ትናንት መልካም የነበረዉ ዛሬ ፈጽሞ አጥፊ መሆኑን ልትገነዘብ ትችላለህ .... በመርህ አክሮባት ተገለባብጠህ በፊት ሆንኩ ብለህ በጀርባ በጀርባ ሆንኩ ብለህ በፊት ትሆናለህ ....
ይህቺን ልጅ ስቀርባት እንደማንኛዉም ጊዜ ቀድሞ የታየኝ ወይንም የፈለኩት ቆንጆ ሴት መሆኗን ነዉ ... አለቀ:: አቀራረቤም ለምንም አልነበረም .... ጊዜዬን በደስታ ለማሳለፍ ..... አምላክ ለአይኔ አሳምሮ የፈጠረዉን ዉበት ከማየት ባለፌ ... በሌሎች ተጨማሪ የስሜት ህዋሳቶቼ ለማጣጣም ... በቃ!!!!!!!! በህይወትህ ስንት ጊዜ አሃ! ብለህ መስመርህን አጥብቀሀል ወይንም ሰርዘሀል? በቃ!!! አሃ ነበር ያልኩኝ:: መኖርህን ለሌላ ሰዉ አድርግህ አስበህ ታዉቃለህ? እንደዛ ነዉ ... እያንዳንዷ የመራመድ ዉሳኔዬ ዉስጥ እሷም አለችበት .... ትንሽ እየቆዬን ስንሄድ መጀመሪያ እንደማንኛዉም ሴት ለወሲብ መቅረቤ አሳፈረኝ .... ከዛ በላይ ነች ... አብራኝ መሆኗ በራሱ ህይወት ነዉ:: ሳትኖር ስለሷ ማሰቤ ሰዉነቴ ዉስጥ የሚያፈሰዉ ጣፋጭ ሙቀት አለ .... :: ስልኬን ለማንሳት ቀፎዬን ሳየዉ እሷዉ በፈገግታ ሳያት .... ህምምም ዋሌቴን ለክፍያ ስመዠርጠዉ .... ከነ ደማቅ የጥቅምት የተፈጥሮ ፈገግታዋ ጋ ሳያት .... እነሆ ሙዘይድ ከግለሰብ ወደ ብዙሀን ሀብት ተቀይሮ ነበር:: ሁሉም ሴት የኔ ... እኔም የቆነጃጅት የሚለዉ የህይወት መስመሬን ትቼ እኔም የዉዴ .... ዉዴም በራሷ ፍቃድ የኔ ብቻ!!! ይህም ደስ ይላል:: ለራስህ ያለህ ክብርም የዛኑ ያክል ከፍ ይላል:: ንጹህ የመምሰል .... ከንጹህ የምንጭ ዉሀ የመሰራት አይነት ስሜት:: ታሪኬ ያስጠላል:: በተለይ ደግሞ የሷን ታሪክ ሳይ:: የወንድ ከንፈር እነዛ እንቡጥ የፈነዱ አበቦች የሚመስሉ ከናፍርቷ ላይ አላረፉም::: የኔስ? ..... መቁጠር እችል ይሆን? መጀመሪያ ፍቅር ሲያሟዝዘን ... እንዲህ ልቅ ነዉ ሙዘይድ እያልኩ ቆሻሻዉን ህይወቴን እተርክላት ነበር .... ፍቅር የማያጠራዉ ቆሻሻ አለመኖሩን አሳየችኝ ....
ለሁሉም ምክሮችህን ተቀብያለሁ....
ሙዞ አቤት አቤት ፍቅር ላይ ሙዝዝ ያለ ቀደዳሽ ተመቸኝ እዉነትም ሙዝ ነገር ነሽ:lol: :lol: :lol: :lol: :lol:
ያንተ የወቅቱ የፍቅር ስሜትህ እንዴዉ የዛሬ ሶስት አመት ገደማ ጥንቅሽ ከሆነችዋ ፍቅሬ በስስት እንደወለላ ማር ያጣጣምሁትን ፍቅር አስታወስከኝ:: እስካሁንም በርግጥ ጥንቅሽ ቆንጆ ነች: ግን ስሜታችን እንደ ድሮዉ አይደለም: እኔም አይኔ በተለይ እነዚህ ሀያዎቹ መጀመሪያ ላይ ያሉ ችኮች ላይ ከርተት ከርተት ማለት ጀምርዋል :lol: :lol: :lol: :lol: :lol: መጥኔዉን ይስጥህ በሉኝ
እና ይህንንም እየጠበቅህ :wink: :wink: :wink: