አይ ግንቦቴ
የት ነበርሽ
እንደሚያፈቅርሽ ሲነግርሽ
ጓዳ ሆነሽ በመተቸት
ተደብቀሽ በማፌዝ በመፈተን
ስትርቂው በምቀኞች ውሸት
የት ነበርሽ
በየዋህነት እንደመልዓክ ሲቀርብሽ
ጨለማ ቤት ሆነሽ
እውር መልዕክተኛን እየተጠጋሽ
ብርሃን እንዳፈለቅሽ የበላይነት እየተሰማሽ
የት ነበርሽ
ባክሽ ቅረቢኝ አዋሪኝ ስሚኝ ሲልሽ
የሚጎዳሽን ተከትሎ መሄዱን መርጠሽ
መልዓኩን ከሰማይ በገመድ ጎትተሽ
እንደ ንጋት ልጅ ልታወርጂው እየሞከርሽ
የት ነበርሽ
ውድ ጊዜው ሲያልፍ ኑሮው ሲበለሻሽ
እንዳይቀርብሽ በተሰወረ መርዝ እያኮላሸሽ
ሌላው የጎዳውን መፈውስ እያለምሽ
እንዲያው ነገ ነገ ስትይ ጨቅላ ሆነሽ ቀረሽ