by እድል » Mon Nov 14, 2005 12:59 pm
የዋርካ ጉዶች ነጠላ ዜማ
የዋርካ ቀዬ ውበት ሞገሱ
በስድብ ናዳ ሲከሳከሱ
በመረን ጭቃ ሲለዋወሱ
ነገር አቡካክተው ሲበሳበሱ
ሲጨቀይ ነው የሚያምር እሱ ::
የተሟላጩ የእንቶኔፈረስ
የዋርካው እገሌ የስድብ ምላስ
ማንትስዬ እባክህ ድረስ :
እየበዛ ነው ቁም ነገር ዋርካ
ናና ገላግለን አድርገው ቦካ
በስድብ ጸበል ሁሉን ነካካ ::
በገሃዱ አለም የጠላነውን
ማናባቱ ነው የሚጭንብን :
እንትናዬም ና ትፈለጋለህ
እየተሟለጭክ ታጋግላለህ ::
የጨዋ ትምህርት ቀና ምሳሌ
የቁም ነገር ወግ .... - ገለ መሌ :
መጨዋወት ልምድ መካፈል
መመካከር ጂኒ ቁልቋል
ያስፈልገናል ዋርካ ላይ የሚል
ሹጣም ቅማጫም እና ጅላጅል
እስቲ ወንድ ሆኖ እዝች ዝር ይበል::
ውጫጭ ቅርናታም መንጋ ሞላላ
ቅንቅናም ቡሽቲ ኩክኒያም ቅማላም
እከካም ሉጢ ቀሽማዳ ሁላ
ልብ አለኝ ካለ ድርሽ ይበላ ::
እመጣለሁኝ ካለም ተዳፍሮ
ማንትስዬ ያው ተወርውሮ
በመሞላለጭ አደነቋቁሮ
በገልቱ ስድቡ አንኩሮ አንኩሮ
ያስምለዋል ላይመጣ ዞሮ
ከዋርካ ደጃፍ ከዋርካ ጓሮ ::
እድል
P.S.
ግጥሜ በር እንዲያንኳኳ ብዬ አንዳንድ የስድብ ቃላትን ሳላስፈቅድ በመውሰድ የኮፒ ራይት ቫዮሌሽን በመፈጸሜ የሚመለከታቸውን ይቅርታ ጠይቂያለሁ ::
(ግጥሞቹን ለማሰባሰብ ያክል እንጂ ይህ በሌላ ገጽ ቀደም ብሎ ቀርቧል - ስሞችን አውጥቻለሁ as they do not appear to be applicable anymore ... ማለት ሰዎቹ አሁን የሉም ..... )
To handle yourself, use your head. To handle others, use your heart.