የ CYBER ጉዶች!!

The Love Forum (love, relationship) (የኔ ቆንጆ እንተዋወቅ :-)

Postby ጌታ » Thu Mar 02, 2006 3:31 pm

ተወዳጁ እድል እንኳን በደህና ተመለስክ::
ኢትዮጵያ እጆቿን ወደ እግዚአብሄር ትዘረጋለች!!!
ጌታ
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 3118
Joined: Sun Apr 17, 2005 5:35 pm
Location: ዶሮ ተራ

Re: ..

Postby ሜሎ » Thu Mar 02, 2006 7:03 pm

እድል wrote:.. የጻፍኩት ጠፋ....
..እመለሳለሁ...

Welcome EDEL
ሜሎ
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 252
Joined: Fri Feb 11, 2005 12:31 am

Postby Ellenie » Thu Mar 02, 2006 8:10 pm

..
Last edited by Ellenie on Wed Apr 30, 2008 11:52 pm, edited 1 time in total.
Smile
Ellenie
ውሃ አጠጪ
ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1000
Joined: Wed Jul 27, 2005 4:36 am
Location: ethiopia

Postby Ellenie » Fri Mar 03, 2006 5:04 am

[qu
Last edited by Ellenie on Wed Apr 30, 2008 11:53 pm, edited 1 time in total.
Smile
Ellenie
ውሃ አጠጪ
ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1000
Joined: Wed Jul 27, 2005 4:36 am
Location: ethiopia

Postby Ellenie » Fri Mar 03, 2006 6:34 am

[እድል
Last edited by Ellenie on Wed Apr 30, 2008 11:55 pm, edited 1 time in total.
Smile
Ellenie
ውሃ አጠጪ
ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1000
Joined: Wed Jul 27, 2005 4:36 am
Location: ethiopia

Postby ቁም ነገር2 » Fri Mar 03, 2006 7:56 am

እድል እንኳን ደህና መጣህ!
respect yourself and others will respect you
ቁም ነገር2
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 451
Joined: Wed Sep 07, 2005 7:24 am
Location: ethiopia

Re: ለ Profanity ሊቆች!!

Postby ክሪስታል » Fri Mar 03, 2006 8:46 am

እድል wrote:ለዛ ባለው ጠምዛዛ አሽሙር
አውቆ እውነቱን በማሳከር
ጎሸምሸም - ሸንቆጥ በነገር:

ተረብ ጥሎ መፎጋገሩ
ተሞጋግሶ መደራደሩ
ተዘራጥጦ መነጋገሩ
በስላቅ ቧልት መጠጋገሩ:
ማን አለ እኮ ከፋ
ጨዋታነቱ እስካልጠፋ::

በአዝናኝ humor በተሞላ
ጭውውት ቁም ነገር ሲብላላ:
Sarcasmሙን እየተረተሩ
ሲዋዛ ቀደዳው - chatteሩ
አቤት ወጋችን ማማሩ!!!

ክርክሩ በውስጠ-ወይራ
ቅኔ ነክ ቃላት ውርወራ
ተጋግሎ ሲያንሰራራ
ተውቦ ወሬው ሲደራ:
መንፈሳችን በተሃድሶ
ከድካም ጭንቀቱ ተፈውሶ
ዘና ይላል ተመልሶ::

ግና ሁሌም አይሞላማ
ጥልቅ ይላል አንዱ ጠማማ:
ባፈጠጠ ስድብ ዜማ
ወጋችንን እያግማማ
አጨማልቆ ሊያገለማ::
አድፍጦ እያደባ
አለአግባብ እየገባ
ጨዋታን ሊያደፈርስ
አቆርፍዶ ሊያፋርስ::

ሞያው የሱ ነው መራቀቅ
በ profanity መመጻደቅ
በራቁት ብልግና መሞሻለቅ:
'ዝቅ" ባለ ጸያፍ ወሬ
መበርገድ እንደ አቦሬ::

ሸፈንፈን አርጎ በለበጣ
ለመባለግ 'ሳያስጠጣ'
መች ያውቃል ቃላት መረጣ
ማቀርሸት እንጂ እንደመጣ::
የሚያውቀው እሱ ከፍጥረቱ
መለጠፍ ብቻ እንደንፍጡ
መቅዘን ነው Vulgar በጠጡን::

እድልየ ፕሮፋኒቲ ሊቆች :lol: :lol: ..... እቺ ተመቸች !

እንኳን ደህና መጡ ውድ እድል!
"We can do no great things--only small things with great love." -- Mother Teresa
ክሪስታል
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 256
Joined: Sat Sep 03, 2005 3:35 pm
Location: Crawkozia

Re: የዋርካ ጉዶች! - የ Profanity ሊቆች!!

Postby ሜሎ » Tue Mar 07, 2006 10:28 pm

እድልን ያያችሁ እባካችሁ................................!!!!!!

እድል wrote:ዋርካ ፍቅር
ፍቅር ትሆን እውን ከምር?
ወይስ ናት መደበሪያ
የስራ ፈት መናሀሪያ:
አሊያም ናት መናገሻ
የአበሻ ሆደ ባሻ
የልቡን መተንፈሻ::

ያስቀኛል አንዳንዴ
የዋርካ ''ፍቅር'' መንገዴ
እንደው ያሰያየሙ ዘዴ::

የ''ፍቅር'' መድረክ ግብግቡን
መናናቁን ጥላቻውን
ካየሁ ከታዘብኩ በኍላ
Oolala!! እንዲያው ዝም ብዬ Oolala!!

የኔ ቆንጆ እንተዋወቅ
ቅቅ ቅቅ ቅቅቅቅ
ድንቄም የለ መተዋወቅ
ቢሉት ይሻል ነበር ይልቅ
የኔ ፉንጋ እንተናነቅ
ተያይዘን እንተላለቅ::

የሆነውን ቢሆን መድረኩ
መቼም ከመጎብኘት አልቦዘንኩ::

በፍቅር ሰይፍ የተቀላ
የነፈዘ ነሁላላ
አሊያም አታላዩ ሁላ:
ገርል ፍሬንዴ ኮብልላ
ሚስቴ በdollar ተደልላ
አልጠጣ እህል አልበላ:
እ...
የባሌ እቃው እ-ን-ስ ብላ
መሄዴ ነው ወደሌላ
ልብ ከሚያርስ ሸበላ
እያሉ ይጭሩብናላ
መንጋ የሴሰኝነት ንክ ሁላ::

ሚስቴ ሆዴ የኔ ገላ
ባታውቅም እኔን በድላ
ልተዋት ነው ይለናላ:
ምን ላርግ ታዲያ....እቃዋ ቦርቅቋላ
ሞኒካ ወይ ትትና በሉኛ እስቲ መላ
መፍትሄ አምጡ blah blah blah blah

የምክሩ አይነት አበዛዙ
ታጅቦ በንዝንዙ
በስድብ ጥዝጥዙ
አርስት ለቀው እየናወዙ::

ቃላት አክርረው ሊጠመዝዙ
ልጅ ደጉ ሲቅበዘበዙ:

በኩሩሩ እሹሩሩ
ካልተዘነጋው ነገሩ
አይቀር ከቶ ሳያቅራራ
የዋርካው አቶ ቀብራራው
እያለ ''ወንድሜ በል ኮራ""
""ዝም ብለህ አትደንብራ"'

በነ ት(ህ)ትና ትንተና
ባለጉዳይ ሲል ዘና:
የሞኒካን ወግ ጥረቃ
ሲከታተል ብሎ ነቃ:

እንዲያ ቢሆን ደሞ እንደዚ
ስትለው ማድሞዜል? ደብዚ:
ይላታል thank you! now I see!
Oh now I really really see!

ጥያቄክ ከሆነ ከምርክ
አየከው ወንድሜ ምን መሰለክ
እኔ እህትክ የምመክርክ
ብላ ስትገባ sweet ሲትራ
ነገሩን ልታብራራ:

ይመጡና ሴጣኖቹ
አባትና ልጆቹ
እናታቹን ል...ዳላቹ
F--k you! ምን ትሆናላቹ!?
ምንስ ታመጣላቹ?
በስድብ በቅሎ ቹ! ቹ! ቹ! ቹ!

ከች ይልና አስተማማኝ
""አንቺ ለማኝ""! ""አንተ ቂጥኝ""!
አንድ አገር የስድብ ቋጥኝ
ሊያወርድብን ውርጅብኝ
ይላላ ያዙኝ ልቀቁኝ
በገጽ ሙሉ እኝ እኝ እኝ እኝኝኝኝኝኝ::

ያች ፈጣጣ አይነ ደረቅ
ናፍቆት ቆቋ ስትራቀቅ
ነገር ስትፈለቅቅ
ስታደርገው ይህንን ጠቅ ያንንም ጠቅ:
ስትፈትል አማርኛ
ስትጠልፍ ከፈረንጅኛ:
ሲነገር አርስት መክፈቷ
ጎራ ነዋ ወደ ቤቷ
ወዳጇም ሆነ ጠላቷ
እሷም አትቦዝን የታባቷ
ናፍቆት አክሮባቲስቷ
ፊለፊት ከመማታቷ
ይቺን ቷ! ያንንም ቷ!


ወይ መዘባረቅ........ በሉ ቻው!!

እድል
ሜሎ
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 252
Joined: Fri Feb 11, 2005 12:31 am

Postby እድል » Fri Mar 24, 2006 5:38 pm

ሜሎ
ቁም ነገር
ጌታ
እሌኒ

ምስጋናዬ ለሁላችሁም!!!
To handle yourself, use your head. To handle others, use your heart.
እድል
አዲስ
አዲስ
 
Posts: 40
Joined: Thu Feb 17, 2005 11:51 am
Location: ethiopia

Postby እድል » Fri Mar 24, 2006 5:41 pm

edited[/b]
Last edited by እድል on Tue Apr 29, 2008 7:54 pm, edited 1 time in total.
To handle yourself, use your head. To handle others, use your heart.
እድል
አዲስ
አዲስ
 
Posts: 40
Joined: Thu Feb 17, 2005 11:51 am
Location: ethiopia

Postby ባሊጋ » Fri Mar 24, 2006 6:28 pm

ጥሩ ግጥም ንች;;;;መቸም ይሂ የዛሪው የኔ ትዝብት ሞሆን አለበት ኢንስፓየር ያረግህ..ይህንን ግጥም ለምጻፍ;; ጥሩ ትዝብት ነው ለነግሩ;;; ትችቱን ባላንስ ለማድረግ መሞክርህ ጥሩ ነው;;;ክኒ ምሻልህን አስምስክርሀል. ምንም እንክዋ እኒ ብመርም;;;
ባሊጋ
አዲስ
አዲስ
 
Posts: 27
Joined: Sat Mar 11, 2006 12:32 am

Postby እድል » Tue Apr 29, 2008 7:57 pm

የሳይበር ጓደኝነት

ከቶ የማላይሽ የማታይኝ - ጓደኛዬ የ Cybeሯ
ምን አይነት ትሆኝ’ወዳጄ - አንቺ የድንበር ባሻገሯ?

ያምላክን ታምር አስመስካሪ - ገጸ መልአክ ብርሃን ፈንጣቂ
ልዩዩዩዩ ውበት የተላበስሽ - አፍዛዥ ነገር ቀልብን ነጣቂ
ትሆኚ ይሆን ጽጌረዳ - ቆንጆ ፍጥረት ትንፋሽ ሰራቂ?

ከጸጉር - እስከ’ግር ጥፍርሽ - እምታምሪ የውብ ተምሳሌት
ተሽቀርቃሪ ዝንጥ ያልሽው - ዘመናይዋ ሽንቅጥ ወጣት
ነሾ’ይ ከቶ የጥበብ ስራ - ረቂቅ ቅምር ረቂቅ ስሌት?

ወይስ…
ቀይ ነሽ፡ የቀይ-ዳማ፡ ጢንዚዛ፡ ኑግ መሳይ ልጥልጥ
ድቡልቡል እንደኳሷ፡ የከበድሽ፡ ወፍራም ዝርጥርጥ?

ወይ ልምጥምጥ እንዳርጩሜ፡ ቀትረ-ቀላል፡ ላባ፡ ሲምቢሮ
ወስፌ እግር፡ ተስፈንጣሪ ጥላ ቢስ ነገር - ቢራቢሮ?

ጭራሽ ማስጠሎስ እንደሆነ ያ ፉንጋ ፊትሽ መልከ-ጥፉው?
በተብለጭላጭ ጥራዝ ነጠቅ - አስመሳይ ስም ተደግፎ
የ Cyber ሰማይ የተመቸሽ በ fancy nick ለመንሳፈፉ።

አሮጊቴ ነገር ትሆኝ ውልቅልቅ ጥርስ - ገጸ ጨምዳዳ
ቅዝቅዝ ብለሽ የከራረምሽ ድክምክም ያልሽ ሽመድማዳ?


ግን… ግን….
ቆይ እስቲ፡ ምና’ረገው - መልክሽን ለኔ ነገር ጉዳዬ
እስከኖርሽልኝ ሳይበር ሰመጣ - ወግ፡ ጨዋታ፡ ወሬሽን ብዬ፡፡

አንብቤሽ አንብበሽኝ ተለዋውጠን ፍሬ ሃሳቡን
አጧጡፌው እስከተደሰትኩ ካገር ልጅ ጋር ቀደዳውን
ተዝናንተን እስከሄድን ተወራውረን ቧልት ተረቡን
ናፍቆቴን አስታግሼው - ባገሬ ቋንቋ መጻጻፉን፡፡
To handle yourself, use your head. To handle others, use your heart.
እድል
አዲስ
አዲስ
 
Posts: 40
Joined: Thu Feb 17, 2005 11:51 am
Location: ethiopia

Postby መልከጻዲቅ » Tue Apr 29, 2008 9:48 pm

Code: Select all
ያስቀኛል አንዳንዴ
የዋርካ ''ፍቅር '' መንገዴ
እንደው ያሰያየሙ ዘዴ ::

የ ''ፍቅር '' መድረክ ግብግቡን
መናናቁን ጥላቻውን
ካየሁ ከታዘብኩ በኍላ
Oolala!! እንዲያው ዝም ብዬ Oolala!!     
 
የኔ ቆንጆ እንተዋወቅ
ቅቅ ቅቅ ቅቅቅቅ
ድንቄም የለ መተዋወቅ
ቢሉት ይሻል ነበር ይልቅ
የኔ ፉንጋ እንተናነቅ
ተያይዘን እንተላለቅ ::

የሆነውን ቢሆን መድረኩ
መቼም ከመጎብኘት አልቦዘንኩ ::

በፍቅር ሰይፍ የተቀላ
የነፈዘ ነሁላላ
አሊያም አታላዩ ሁላ :
ገርል ፍሬንዴ ኮብልላ
ሚስቴ በ dollar ተደልላ
አልጠጣ እህል አልበላ :
እ ...
የባሌ እቃው እ -ን -ስ ብላ
መሄዴ ነው ወደሌላ
ልብ ከሚያርስ ሸበላ
እያሉ ይጭሩብናላ
መንጋ የሴሰኝነት ንክ ሁላ ::

ሚስቴ ሆዴ የኔ ገላ
ባታውቅም እኔን በድላ
ልተዋት ነው ይለናላ :
ምን ላርግ ታዲያ ....እቃዋ ቦርቅቋላ
ሞኒካ ወይ ትትና በሉኛ እስቲ መላ
መፍትሄ አምጡ blah blah blah blah

 


ዋው... :lol: እድል እያዝናናች የምታስተምር ቆንጆ ግጥም ናት:: :lol: እንዲህ አይነት ቤት መኖሩንም ገና ዛሬ ነው ያየሁት:: እረ ጊዜ ስታገኝ ጨማምርበት:: 8)
የግጥሞችህ አድናቂ:: :idea:
መልከጻዲቅ
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 899
Joined: Wed Aug 08, 2007 11:45 pm

Re: የዋርካ ጉዶች!

Postby Debzi » Thu May 01, 2008 1:43 am

Debzi wrote:
እድል wrote:

እንዲያ ቢሆን ደሞ እንደዚ
ስትለው ማድሞዜል? ደብዚ
ይላታል thank you! now I see!
Oh now I really really see!

እድል


የኔ ስም mentioned የሆነበትን አርስት አይኔ እያየ ወደ ሁለተኛ ገጽ አላስኬደውም መቸም::
በተጨማሪም የእድልን የፈጠራ ስራ ለማመስገን ያህል ነው::


አልኩኝ ያኔ......ሶስት አመት ሊሆነው ነው.......አቤት ጊዜው ሲሮጥ ግን! ጊዜ ሰው ቢሆን ኖሮ ቀነኒሳን እንደሚቀድመው አልጠራጠርም!
የሆኖ ሆኖ....... :shock: አሁንም የእድል ፈጠራ ወደ ሁለተኛ ገጽ እንዳይሄድ እስቲ እዚህ ልሰረው!
Ke akbrot selamta gar!!
Debzi
ዋና ውሃ አጠጪ
ዋና ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1918
Joined: Sun May 02, 2004 12:34 am
Location: Los Angeles, CA

Postby መሰማማት » Thu May 01, 2008 9:47 am

ደብዚዬ የሳይበር ውሽማዬ አለሽልኝ ወይ ?ንፍቅቅቅቅቅቅቅቅ
መሰማማት
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 290
Joined: Mon Aug 20, 2007 6:37 am

PreviousNext

Return to Warka Intimate - ዋርካ ፍቅር

Who is online

Users browsing this forum: Google [Bot] and 4 guests