by እድል » Thu Jul 28, 2005 11:31 am
ሚስቱን ሻጥ 'አርጎ ከጎኑ
ቀልመድ ቀልመድ ይላል ባይኑ:
በፊቱ አለፍ ባለች ቁጥር
ባለቀሚስ የሄዋን ዘር::
ዞር ስትል ባልተቤቱ
ላንዲት ደቂቃ ከፊቱ
ይፈጥናል ለመወስለቱ
ከናኒ ከቤቲ ከቱቱ::
ይንቀዠቀዣል ሊጫወት
ጥድፍ ጥድፍ ይላል ሲያዩት
ከጥቅሻ ገበያ ሊጫረት
At the drop of a hat!
'ኧረ ተው አንተ ሰውዬ '
'ምነው ቢቀርብህ ?' ብዬ
ልመልሰው መክሬ
ገና ከመጀመሬ:
'Please ባክህ አቦ ተዋ "
'እንዲህ አታካብደዋ '
አትስጥ አለኝ ብዙ Attention
"It's just flirtation!'
ይች አመል ስር አብቅላ
መዘዟን አስከትላ
ትዳርህን በክላ
ብታስቀርህ ሜዳ አውላላ
የለሁበትም በኍላ::
አይሆንም ተው እንደሱ
የሴሰኝነት ሱሱ
አመንዝሮ መልከስከሱ
ይሄው ነው አነሳሱ:
ብዬ እንዲገባው ስጣጣር
እንዲመለስ በምክር
የሱ ምላሽ ግን ፈጣን ነበር
ሳያንዛዛ እንዲሁ ባጭር
ይለኛላ 'WHATEVER!"
አንዲት ጣት አላርፍ ብላ
አሉ ወጣች አር ጠንቁላ
እንደተተረተው ተብሎ
የኔው ጉድ ቂላ ቂሎ
በ flirtation ፈረስ በቅሎ
ጥቂት ልሂድ ልጓዝ ብሎ
ጀመረ ጉዞውን ሸልሎ
ባያቆመውም ኍላ ችሎ::
አዎ አላቆመውም ጭራሽ
ዘሩን እንደወፍ ዘራሽ
አስኪያዝረከርከው በብላሽ
እስኪወጣ ተበክሎ
የጠነቆለውን ጠንቁሎ::
የቆጡን በማየቷ
የያዘችውን ከብብቷ
የተወራላት ማጣቷ
የዛች እህታችን እጣ
አንዴ አፍጦበት ሲመጣ
'ምንድነው ምን አይነት ጣጣ ?'
'እንዲህ በከባድ የምቀጣ! '
'እንደዋዛ ሚስቴን የማጣ!'
ይለኛል ይህ የማይማር
ሲመክሩት የማይመከር
ተጸናውቶት የወሲብ ዛር
የሚያሾትል ለማጭበርበር
ለመማገጥ ለማመንዘር
ይህ ቁሌታም Womanizer!
መሰልኩት እንዴ ቂሎ ማሞ
'Flirtatioንንንንን ' ይለኛል ደሞ
እኔም አልኳ ስመልስ
ስማ እሺ ! Flirtation my asssssss!!!!!
እድል እንደጻፈው .....
ቻው !
To handle yourself, use your head. To handle others, use your heart.