ምንትሴ ... ቅብርጥሴ

The Love Forum (love, relationship) (የኔ ቆንጆ እንተዋወቅ :-)

Postby ክሪስታል » Thu Jul 27, 2006 10:33 am

My wife and I were happy for twenty years. Then we met.

-----------------

Two secrets to keep your marriage brimming
1. Whenever you're wrong, admit it
2. Whenever you're right, SHUT UP!
"We can do no great things--only small things with great love." -- Mother Teresa
ክሪስታል
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 256
Joined: Sat Sep 03, 2005 3:35 pm
Location: Crawkozia

Postby ክሪስታል » Sun Jul 30, 2006 1:05 pm

በቅርቡ እኔና የሁለት አመት ፍቅረኛዬ የሆነች ልጅ ልንጋባ ወሰንን... ውሳኔያችንንም ለ ቤተሰቦቻችን አሳወቅን ... የኔ ቤተሰቦች ሀሳቤን በጣም ደገፉት... በብዙ መንገድም ድጋፋቸውን ገለፁልኝ....

ሰርጋችን ቀን እየቀረበ ሲመጣ አንድ አስቸጋሪና እጅግ የሚፈትን ሁኔታ አጋጠመኝ.... እጮኛዬ ታናሽ እህት አለቻት... 22 አመት ቢሆናት ነው... ታምራለች: በጣም ቆንጆና የተስተካከለ ሰውነት ያላት ናት... አስተያየቷ በቃ ልብን የሚሰርቅ ነው.... አለባበሷ ወንድነትን የሚቀሰቅስ ነው... ደግሞም ሆን ብላ እኔ ብቻ እያየሁዋት እንደሆነ ስታውቅ የምታደርጋቸው እንቅስቃሴዎች ልዩ ናቸው ... የፊቷን መስለምለም መተው ነው ... ፈታኝ የሆኑ የሰውነቷን ክፍሎች ለእኔ እይታ ማጋለጥ... ሌላም ሌላም የእኔን ወንድነት የሚፈታተኑ ነገሮችን ሆን ብላ ታደርጋለች....

አንድ ቀን እቤታቸው ስሄድ ማንም ሰው አልነበረም እሷን ብቻዋን አገኘኍት... በጣም ደስ ብሏት .. የሁለታችን ብቻ በዚያ ሁኔታ መገናኘት በጣም ስትፈልገው የነበረው አጋጣሚ መሆኑን ቆንጆ አይኖቿን እኔ ላይ እያንከባለለች ነገረችኝ ... ከዚያም በጣም ተጠግታኝ እስካሁን እጅግ የምገረምበትን ነገር ዘከዘከችው.... ያም ምንድነው በቃ ለኔ ልዩ የሆነ አመለካከት እንዳላት... ሆሌ በህልሟ ውስጥ እንዳለሁ ... እኔን በተመለከተ ያላትን ሴክሹዋል ፋንታሲ ሁሉ ዘከዘከችው.... ክው ነበር ያልኩት.... ሆኖም ቀጠለች.... እየውልህ አሁን የኔን እህት ልታገባት ነው.... አንዴ ካገባህ በሁዋላ ከእህቴ ውጪ የትም ልትሄድ አትችልም ... አሁን ግን አንተ እጅግ ታስፈልገኛለህ ምናምን ምናምን እያለች ወደመኝታ ቤቷ ጎትታ አስገብታ በስሜት ትደባብሰኝና ትስመኝ ገባች ... ልብሷን አወለቀችው ... ልቤ እንዴት እንደመታ ልነግራችሁ አልችልም ... ቀጥላም የውስጥ ሱሪዋን አውልቃ ፊቴ ላይ ወረወረችው... ልቤ በጣም መታች ምንም መናገር አልቻልኩም .... በቃ ፊቴን መልሼ ውጪ ወዳቆምኳት መኪናዬ ስሄድ አባቷ አዚያጋ ቆመው አገኘሁዋቸው.... ፈራ ተባ እያልኩ ስጠጋ ትኩር ብለው እያዩኝ አንባ ተናንቋቸው ወደኔ ቀረብ ብለው እጃቸውን ዘርግተው እንቅ አርገው አቀፉኝ.... ድምጻቸው እየተቆራረጠ ...ልጃቸውን የሚያገባው ሰው ያዘጋጁለትን ፈተና በማለፉና በዚያም ምን ያህል ጠንካራና ታማኝ መሆኑ ማረጋገጥ በመቻላቸው እጅግ መደሰታቸውን ነገሩኝ... አይገርምም....

እና ምን መሰላችሁ ከዚህ ሁሉ ነገር የተማርኩት ትልቅ የሞራል ትምህርት..... ማንም ሰው ቢሆን ኮንዶሞቹ መኪና ውስጥ ማስቀመጥ እንዳለበት ነው::
"We can do no great things--only small things with great love." -- Mother Teresa
ክሪስታል
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 256
Joined: Sat Sep 03, 2005 3:35 pm
Location: Crawkozia

Postby ክሪስታል » Mon Jul 31, 2006 8:31 pm

አንድ ኤሊ ነው - ዛፍ ላይ መውጣት ጀመረ። ከሰአታት ጥረት ብኋላ ጫፍ ላይ ይደርስና ሲያበቃ የፊት እግሮቹን እያርገበገበ ይዘላል። ያው ግን ወርዶ አፈር ድሜ ይግጣል። ትንሽ አገግሞ እንደገና ቀስ እያለ ዛፉን ይወጣና እንደበፊቱ ቢዘልም ድጋሚ ወርዶ ይፈጠፈጣል። ኤሊው ይህንን ነገር ደጋግሞ ይሞክራል። በወቅቱ ከዚያው ዛፍ አንድ ቅርንጫፍ ላይ የተቀመጡ ሁለት ባልና ሚስት ወፎች ኤሊው የሚያደርገውን አሳዛኝ ጥረት ከመጀመሪያው ጀምሮ ይታዘቡ ነበር።
በመጨረሻ ሴቷ ወፍ ወደ ወንዱ (ባሏ) ዞራ፡ - “የኔ ፍቅር፡ በቃ ባክህ ይነገረው”
ወንዱ ወፍ፡ ምኑ ይነገረው?
ሴቷ ወፍ፡ ማለት…. በቃ በጉዲፈቻ ወስደን ያሳደግነው መሆኑን ማወቅ አለበት።”
"We can do no great things--only small things with great love." -- Mother Teresa
ክሪስታል
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 256
Joined: Sat Sep 03, 2005 3:35 pm
Location: Crawkozia

Postby ምርቃና » Tue Aug 01, 2006 8:00 am

ክሪስታል wrote:እና ምን መሰላችሁ ከዚህ ሁሉ ነገር የተማርኩት ትልቅ የሞራል ትምህርት..... ማንም ሰው ቢሆን ኮንዶሞቹ መኪና ውስጥ ማስቀመጥ እንዳለበት ነው::


የምትፅፋቸው ፅሁፎች ለዛ አላቸው በርታ!! ለሰው መሳቅ አይደክም እንዲህ የሚያስቅ ነገር ሲገኝኝኝ ..ቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅ
ቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅ
ቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅ
ቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅ
Just chat, dont consider it>>>> Love 4 all>>
figaww.
ምርቃና
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 211
Joined: Tue Feb 24, 2004 7:23 am

Postby ክሪስታል » Tue Aug 01, 2006 5:55 pm

ደብዚና ምርቃና .... አመሰግናለሁ::
"We can do no great things--only small things with great love." -- Mother Teresa
ክሪስታል
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 256
Joined: Sat Sep 03, 2005 3:35 pm
Location: Crawkozia

Postby ክሪስታል » Tue Aug 01, 2006 5:56 pm

እጅግ ሃይለኛ ዶፍ በሚወርድበት አንድ የተረበሽ ምሽት ላይ መኪናዎን እየነዱ ነበር። በዚያ ሰዓትና ጊዜ በአንድ የአውቶብስ መቆሚያ በኩል ያልፋሉ…. እናም ሶስት ሰዎች አውቶብስ መጠበቂያው ውስጥ ተቀምጠው እየጠበቁ ነበር። አንዷ አውቶብስ ጠባቂ አሮጊት ሴት ናት… የታመመችና ልትሞት የደረሰች ትመስላሰች። ሁለተኛው ጠባቂ ድሮ የሚያውቁትና በአንድ መጥፎ አጋጣሚዎ ደርሶልዎት ህይወትዎን ያተረፈ ሰው ነው። ሶስተኛዋም ደግሞ እጅግ የሚንሰፈሰፉላት፡ ዘወትር የሚያልሙዋትና የራስዎ እንድትሆን የሚመኙዋት ነገር ግን ቀርበው ለማናገር አጋጣሚውን ለረጅም ጊዜ ያላገኙላት ውብ ወጣት ናት።

እና በዚህ ሁኔታ … እርስዎ ለማን ሊፍት ይሰጣሉ? ልብ ይበሉ መኪናዎ ከአንድ ሰው ሌላ ተጨማሪ ተሳፋሪ መጫን አትችልም።

አሮጊቷን ነው በመኪናዎ የሚያሳፍሩት… ማለት ልትሞት ስለሆነ እንዲያድኗት በማሰብ? ወይስ ያንን ዛሬ በህይወት ለመኖርዎ ምክንያት የነበረውን የጥንት የጥዋት ጓደኛዎን… ምክንያቱም ብድርዎን ለመመለስ ይህ የማይገኝ አጋጣሚ ስለሆነ። ከነዚህ ምርጫዎች አንዱን ከወሰዱ ደግሞ ያቺን የህይወትዎን ንግስት ከዚህ በኋላ ለዘለአለም ድጋሚ ላያይዋት ይችላሉ…. ከባድ ምርጫ ነው አይደል … ግን የቱን ይመርጣሉ? እስቲ ቀጥለው ከማንበብዎ በፊት የርስዎን ምርጫ ያሰላስሉ።
..
..
..
..
..
..
..
..
..
..
..
..
..

ብዙ ሰዎች ይህን ጥያቄ ተጠይቀው የተለያየ ምክንያት በመስጠት ከሶስቱ አንዱን መርጠዋል።
በጣም ብልህ መልስ የሰጠው ሰው ግን እንዲህ ነበር ያለው….
“የመኪናዬን ቁልፍ ለዚያ ለድሮ ጓደኛዬ እሰጠውና አሮጊቷን ወደሆስፒታል ይወስዳታል…. እኔ ደግሞ ወርጄ የዘወትር ህልሜ ከሆነችው ቆንጆ ልጅ ጋር አውቶብስ እጠብቃለሁ ... እናም እድሌን እሞክራለሁ::
"We can do no great things--only small things with great love." -- Mother Teresa
ክሪስታል
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 256
Joined: Sat Sep 03, 2005 3:35 pm
Location: Crawkozia

ፍየሊቷ ሚስቴ

Postby ክሪስታል » Sat Sep 09, 2006 4:50 pm

ሱዳን ውስጥ ነው …. ሰውዬው (ሚር. ቶምቤ ይባላል) አንዲትን ፍየል በሚስትነት እንዲጠቀልል ፈረዱበት አሉ። ከፍየሏ ጋር ወሲብ ሲፈጽም ተይዞ ነው ይህ ፍርድ የተፈረደበት። የፍየሏ ባለቤት (ሚር. አፍሊ) ነው ሚር. ቶምቤ ከፍየሏ ጋር አለሙን ሲያይ ደርሶ ወደ ዳኞች የወሰደው። የ ሚር. አፍሊ የካሳ ጥያቄ ምን ነበር መሰላችሁ… አዎ ሚር. ቶምቤ ጥሎሽ እንዲያስገባ … 15 ሺህ የሱዳን ዲናር።

በኋላ ሚር. አፍሊ ተጠይቆ … “ ፍየሏን ሰጥተነዋል…. እስከምናውቀው ድረስ እስካሁን አብረው ናቸው” ነበር ያለው።

እኩለ ለሊት ላይ ጩኸት ሰምቼ ስወጣ … ሚር. ቶምቤን ከፍየሏ ጋር አገኘሁት… ምን እያደረገ እንደሆነ ስጠይቀው ... ከፍየሏ ጀርባ ላይ ወረደ…. ይዤ አሰርኩት… ዳኞቹም ፍየሏን እንደ ሚስትነት ስለተጠቀመባት … ጥሎሽ ይክፈል አሉ….

ምንጭ - ቢቢሲ: እዚህ ይጫኑት
"We can do no great things--only small things with great love." -- Mother Teresa
ክሪስታል
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 256
Joined: Sat Sep 03, 2005 3:35 pm
Location: Crawkozia

Postby THE » Sat Sep 09, 2006 8:51 pm

ክሪስታል wrote:እጅግ ሃይለኛ ዶፍ በሚወርድበት አንድ የተረበሽ ምሽት...


ክሪስታል

I was able to answer your question correctly. I am good :)
THE
መንገደኛ
መንገደኛ
 
Posts: 8
Joined: Fri Aug 25, 2006 1:16 am

Postby ክሪስታል » Sun Oct 15, 2006 4:24 pm

አስተማሪ: በራሪ ሆነው የሚያጠቡ እንሰሳት እነማን ናቸው?

ተማሪ: የለሊት ወፎች ..... እና ደግሞ...እ

አስተማሪ: እ....ና ምን? (በመገረም)

ተማሪ: ሆስተሶች
"We can do no great things--only small things with great love." -- Mother Teresa
ክሪስታል
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 256
Joined: Sat Sep 03, 2005 3:35 pm
Location: Crawkozia

መደበሪያ ነገር....

Postby ክሪስታል » Tue Dec 12, 2006 7:01 pm

ሰውዬው መኪናውን በፍጥነት እያሽከረከረ ባለበት ሰአት ፍሬኑ እንደማይሰራ ይገነዘባል.... ማለት ፍሬን ተበጥሷል.. እናም መታጠፊያ መንገድ ላይ ደርሶ ለማብረድ ቢሞክር እምቢ ይለውና ... ተሰብስበው የቆሙ አንድ 10 ስዎች ጨፈላልቆ ከቋሚ ነገር ጋር ተጋጭቶ ይቆማል... ትራፊክ ፖሊስ ደርሶ ስለጉዳዩ ይጠይቀዋል...

ፖሊስ: እንዴት ልትጋጭ ቻልክ

ሾፌር: ፍሬን አልይዝ ብሎኝ ... ለማቆም የግድ ከአንድ ነገር ጋ ማጋጨት ነበረብኝ

ፖሊስ: ታዲያ እያየህ 10 ሰው ላይ ትወጣለህ... እንደደረሰን መረጃ መሰረት ከተጋጨህበት ቦታ በተቃራኒው በኩል አንድ ሰው ብቻ ነበር የነበረው... ለምን በዚያ በኩል ተጋጭተህ ለመቆም አልሞከርክም... 10 ሰው ከመግደል የተሻለ አማራጭ ነበረህ...

ሾፌር: እሱ እኮ ነው ችግሩ .... አየህ ወንድሜ ... እኔም እኮ ያ አንድ ሰውዬ ወደነበረበት የመንገዱ ዳር ነበር መጀመሪያ መኪናዋን ያዞርኳት ....

ፖሊስ: አልገባኝም..... እ

ሾፌር: ያ ዲቃላ ሰውዬ ነዋ ... ወደሱ :lol: መምጣቴን ሲያይ እሮጦ ተሻግሮ ከ 9ኙ ሰዎች ተደባለቀ አ!
"We can do no great things--only small things with great love." -- Mother Teresa
ክሪስታል
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 256
Joined: Sat Sep 03, 2005 3:35 pm
Location: Crawkozia

Postby ቅመምዬ » Tue Dec 12, 2006 9:56 pm

ክሪስታል
:lol: :lol: :lol: :lol: :lol: :lol: ዲቃላው ሲያሳዝን ሞት ጠርቶት ነው አይደል
GB
ቅመምዬ
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 405
Joined: Tue Jun 06, 2006 8:16 pm

Postby ክሪስታል » Wed Dec 13, 2006 9:31 am

........
Last edited by ክሪስታል on Mon Nov 14, 2016 6:25 pm, edited 2 times in total.
"We can do no great things--only small things with great love." -- Mother Teresa
ክሪስታል
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 256
Joined: Sat Sep 03, 2005 3:35 pm
Location: Crawkozia

Postby SUAVE » Wed Dec 13, 2006 11:39 am

ሁለት ሰዎች ረጅም መንገድ እየተጉዋዙ ሳለ ድንገት አንድ ጫካ መሀል ትልቅ ዝሆን ሞቶ ያገኛሉ:: ዝሆኑን ለመቅበር አስበው የመቃብር ጉድጓድ ለመቆፈር ጥረት ቢያደርጉም ከዝሆኑ ግዙፍነት አንጻር አልቻሉም:: መላ ለማፈላለግ ሁለቱም በየፊናቸው አሰቡና ሟቹን ከመቅበር ይልቅ ቢያቃጥሉት የተሻለ እንደሚሆ ተስማሙ:: እናም ባካባቢው እንጨት ፈልገው ክብሪት ጭረው እሳቱን አያያዙ:: ነገር ግን እሳቱ እንጨትና ቅጠላቅጠሉን ከማቃጠል አልፎ የዝሆኑን ሬሳ ሊያቃጥልና ወደ አመድ ሊለውጥ አልቻለም:: ሁለቱ ሰዎችም ሌላ አማራጭ ስላጡ ዝሆኑን የነበረበት ቦታ ትተው መንገዳቸውን ቀጠሉ!

ይህ የሚያስተምረን አንድ ነገር, ሁላችንም አንድ ቀን ያላሰብነው ነገር እንደሚያጋጥመን ነው!
SUAVE
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 475
Joined: Sat Sep 03, 2005 8:42 am
Location: ethiopia

Postby ክሪስታል » Wed Dec 13, 2006 12:41 pm

ሴትዮዋ … አሮጊት ነገር ናቸው… ዶክተር ጋ ይሄዳሉ።

ዶክተሩም … ምን ልርዳዎት? ሲላቸው
… ‘በርዝ ኮንትሮል ፒልስ እፈልጋለሁ” ይሉታል።

በነገሩ የተገረመው ዶክተር ትንሽ አሰብ አድርጎ…. “ይቅርታ ወይዘሮ ትህትና….እ … እድሜዎን 75 አመት ያሉ መሰለኝ። እና የወሊድ መቆጣጠሪያ ኪኒን ምን ይጠቅመኛል ብለው ነው።

“ጥሩ እንቅልፍ ኖሮኝ እንድተኛ ይረዱኛል”

ዶክተሩ አሁንም አሰብ አድርጎ… “እንዴት ሆኖ ነው ፒልስ .. ማለት.. በርዝ ኮንትሮል ፒልስ ለ እንቅልፍ የሚረዳዎት።”

የማሳድጋት የልጅ ልጄ… የሞኒካ ብርቱካን ጭማቂ ውስጥ እጨምራቸውና… እኔ ምሽቱን የሰላም እንቅልፍ ይወስደኛል።
"We can do no great things--only small things with great love." -- Mother Teresa
ክሪስታል
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 256
Joined: Sat Sep 03, 2005 3:35 pm
Location: Crawkozia

ሴቶች

Postby ክሪስታል » Thu Jan 18, 2007 9:54 pm

Women are important in a man’s life only if they’re beautiful and charming and keep their femininity
... this business of feminism, for instance. What do these feminists want? What do you want? You say equality. Oh! I don’t want to seem rude, but.. you’re equal in the eyes of the law but not, excuse my saying so, in ability ... You've never produced a Michelangelo or a Bach. You've never even produced a great chef. And if you talk to me about opportunity, all I can say is, Are you joking? Have you ever lacked the opportunity to give history a great chef? You've produced nothing great, nothing! … You're schemers, you are evil. All of you.[
"We can do no great things--only small things with great love." -- Mother Teresa
ክሪስታል
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 256
Joined: Sat Sep 03, 2005 3:35 pm
Location: Crawkozia

PreviousNext

Return to Warka Intimate - ዋርካ ፍቅር

Who is online

Users browsing this forum: No registered users and 3 guests

cron