ፋሲል ይትባረክ የሚባል የፃፈው ነው አሉ ....... ሰለ ውሽማዋ አንዷ እንዲህ አለች ብሎ!
ለባሌ እየጋገርኩ እንጀራ ከቤቴ
በእሳት ሲፈተን ወርቁ ሚስትነቴ
አደንግዝ ጠረንህ አድሮ ታከላቴ
የትዝታህ ጅረት ቀዶ ከማጀቴ
የማልጠግብ ገላህን ቢያሳየኝ ከፊቴ
ታስቦኝ ሲቃትት ትንፋሽህ ከአንገቴ
ከሜዳው ደረትህ ተጣብቆ ደረቴ
ለክምክም ጎፈሬህ ሰግዶ ኩሩነቴ
ወዝህን ጎምጅቶ ቢከዳኝ ጎልበቴ
እጡብ ወንድነትህን ቢራብ ሴትነቴ
ቢወድህ ነሁልሎ ከንቱ ሰውነቴ
ምጣዴን አሰስኩት በዚያች በጫጩቴ::