Mo's coffee house!!!

The Love Forum (love, relationship) (የኔ ቆንጆ እንተዋወቅ :-)

Postby ወዲአክሱም » Sat Jun 18, 2011 9:58 pm

ስማ ምን ያናድዳሀል ባክህ? ቆርቆሮ ራስ ረጋ በል
ወዲአክሱም
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 117
Joined: Wed Nov 12, 2003 2:33 am

Postby ወርቅነች » Sun Jun 19, 2011 9:46 am

ቅል ተሸክመህ መዞርህ ነው ያናደደኝ :lol:

ጀሚላ ከቸርችል ጎዳና
ወርቅነች
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 967
Joined: Sun Oct 03, 2010 10:05 am

Postby ቶታአው » Tue Jun 21, 2011 10:54 am

ሞኒዬ የኔ ወርቅ አለሽልኝ? ምነዉ አይንሽም ፈዘዘብኝ ወገብሽም ጎበጠ ባትሽም ለተተ ያ እርጅና የሚሉት ከፉ አገኘብኝ ይሆን::

ደህና ነሽ ግን? ብታረጂም እወድሻለሁ :: አንቺ እኮ......
ቶታአው
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 357
Joined: Mon May 31, 2004 12:39 pm

Postby Monica****** » Mon Mar 19, 2012 3:44 pm

:roll:
Monica******
አዲስ
አዲስ
 
Posts: 11
Joined: Sun Apr 22, 2007 3:01 pm

Postby ገልብጤ » Mon Mar 19, 2012 3:53 pm

Monica****** wrote::roll:

ቅቅቅቅቅ..ሞኒካ ****** ስድስት ኮከብ
ያልበሰለ ፖለቲከኛ ስለቀጣዩ ምርጫ ሲያስብ
የበሰለ ፖለቲከኛ ስለቀጣዩ ትውልድ ያስባል
James freeman clarke
ገልብጤ
ዋና ውሃ አጠጪ
ዋና ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1746
Joined: Sat Jun 26, 2010 11:24 pm

Postby humaidi » Sun Mar 25, 2012 8:20 am

ሰላም ሞኒካ,

ባለሸበት የተመኘሺው ተሳክቶልሸ ተደሰተሽ ሂወትሸን እንደምትመሪ ተሰፋ አለኝ:: ቆርጠሻልና መመለሻ መሰመር ለማበጀትም መሞከሩ ቀርቶ ማሰብሸንም እንኳ እጠራጠራለሁ:: ብልጽግናውን ሁሉ እየተመኘሁልሸ ዋርካን ያወቅኩት በቤትሸ እንደሆነ ኩራት ሲሰማኝ የምሰናበትሸ ላንዴና ለመጨረሻ ከዚሁ ከቤትሸ ነው::

ምንም ጊዜም አክባሪሸ ሁሜዲ

Adious Monica****
humaidi
ዋና ውሃ አጠጪ
ዋና ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1741
Joined: Tue Jan 03, 2006 11:50 am

Postby ENGEDA1967 » Sat Apr 14, 2012 9:55 am

ሰላም ሞኒኩሽ
ዋርካ ብዙ ወገኖችዋን ያጣች ስትሆን ቸት ሩም ከተዘጋ ጀምሮና ነባር ደምበኞችዋ እያረጁ እየተሰላቹና እየተዳከሙ ስለሆነ ከቀን ወደቀን እየቀዘቀዘች ነው ; ድሮ ጥዋት የተጻፈን ከሳአት ማግኘት ገጽ መገልበጥ ግድ ነበር አሁን ወርም ዳፉን ሳይለቅ እናገኘዋለን
ዋርካ በተለይ ውጭ ላሉ ኢትዮፒያውያን በአማርኛ ለመነጋገር ቆንጆ መድረክ እንደነበረች እንድትቆይ ቸቱን መክፈት ግድ ነው በሌላው መድረክ መጨቃጨቅ አቅምና ትዕግስት ያለን አልመሰለኝም ወጣቱ ትውልድ ደግሞ በባዕድ ቋንቋ እያደግን ስለሆነ አማርኛው እንግዳችን ነው እና ዋርካ ለስደተኞች መሆንዋ እያከተመች ይመስለኛል
ዋርካም እንደልጆችዋ እያረጀችና እየቀዘቀዘች ነው
ሞኒካ እኔም ከሚያከብሩሽና ከሚወዱሽ አንዱ ነኝ ባለሽበት ቦታ ይመችሽ ዘንድ የዘወትር ምኞቴ ነው
ሰላም ሞኒካ
እንግዳ ነን ከእየሩሳሌም
ENGEDA1967
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 475
Joined: Fri Aug 27, 2004 11:09 pm
Location: united states

ስላምታ

Postby ኦፕሬተር » Fri Oct 12, 2012 1:24 pm

Hur mar du Monica dear????
ወይ ጊዜ ይሄ ቤት ድሮ እንዴት ሞቅ ያለ እንደንበር ሳስታውስ የጊዜን ሂደት ሳልፈልግ እንዳስበው አድርጎኛል::
ሞኒክ የኔ ሆድ jag har saknat dig!!!! <3
ደምበኞችሽም አንቺ ቤቱን ጥለሽ ስትሄጂ እነሱም ጠፉ!!! ሁሜድና ወርቅነች እንክዋን አይጨክኑም ነበር ባንቺ ቡና....ይሁን መቼም ዋናው ስላምና ጤና ነው:: እስኪ ድንገት ዋርካ ከገባሽ ስላምታ ስጭኝ ካልሆነ እዛው ፌስ ቡክ ላይ እንገናኝ አንዳንዴም ግቢና የልጆቼን ፎቶ ተመልከቺ::
ሞኒክዬ ሁሌም እወድሻላሁ
ስልከኛው ወንድምሽ
ኦፕሬተር
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 281
Joined: Wed May 16, 2007 9:03 pm
Location: who cares?

Re: ስላምታ

Postby ቱሉቦሎ » Fri Oct 12, 2012 6:07 pm

ኦፕሬተር wrote:Hur mar du Monica dear????
ወይ ጊዜ ይሄ ቤት ድሮ እንዴት ሞቅ ያለ እንደንበር ሳስታውስ የጊዜን ሂደት ሳልፈልግ እንዳስበው አድርጎኛል::
ሞኒክ የኔ ሆድ jag har saknat dig!!!! <3
ደምበኞችሽም አንቺ ቤቱን ጥለሽ ስትሄጂ እነሱም ጠፉ!!! ሁሜድና ወርቅነች እንክዋን አይጨክኑም ነበር ባንቺ ቡና....ይሁን መቼም ዋናው ስላምና ጤና ነው:: እስኪ ድንገት ዋርካ ከገባሽ ስላምታ ስጭኝ ካልሆነ እዛው ፌስ ቡክ ላይ እንገናኝ አንዳንዴም ግቢና የልጆቼን ፎቶ ተመልከቺ::
ሞኒክዬ ሁሌም እወድሻላሁ
ስልከኛው ወንድምሽ

ነብሷን ይማረውና ጥሩ ቤት ከፍታ ነበር :: እግዚአብሄር ነብሷን በመንግስተሰማያት ያኑርልን :ለቤተሰቦቿ ጽናቱን ይስጣቸው ::
ቱሉቦሎ
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 195
Joined: Tue Sep 04, 2012 8:13 pm

Re: Mo's coffee house!!!

Postby humaidi » Wed Apr 05, 2017 8:59 am

ሰላም ይድረሰ ለሞኒካ ባለችበት you will remain the Queen of warka ለዘላላም .......................
humaidi
ዋና ውሃ አጠጪ
ዋና ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1741
Joined: Tue Jan 03, 2006 11:50 am

Re: Mo's coffee house!!!

Postby ጌታህ » Thu Jun 22, 2017 8:58 am

humaidi እንደታገደ እኔም ሳልታገድ ሰላም ብዮሸ ልውጣ ልእልት ሞኒካ፡፡
ጌታህ
ውሃ አጠጪ
ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1209
Joined: Sat May 30, 2009 3:05 pm

Re: Mo's coffee house!!!

Postby ጌታህ » Tue Aug 29, 2017 6:24 am

ይህ ዘመን የት ደረሰ...እነ ሞኒካሰ የት ናቸው...የዛሬ 12 አመት ሰው እንዲህ ያሰብ ነበር...ለዚህም ነበር ወርቃማ ዘመን ተብሎ መታወሰ ያለበት...ዋርካዊያን እንዲህ ነበር የሚያሰቡት..."ትልቅ ትንሸ ሳይል በደስታ ያሰተናግዳል"ነበር አሰተሳሰባቸው...ትልቅ ነነ ትንሸ አይደለንም አወቅን ሳይሉ...ያላቸውን ሁሉ ያካፍሉ ነበር ሳይሰሰቱ....የሰውን ልጅ ለመርዳት በተለይ ሓበሻን የማይጏዙት ርቀት አልነበረም...ራቀን ቀረበን ሳይሉ..የሚከፍሉትም አሰተዋጽኦ ቀላላ አልነበረም...የሚያውቁትን ለሁሉም ሲያካፍሉ...ሰው የሚያውቀውን ለመሰማት ና ለመረዳት ለማወቅም ሳይሳናቸው ጠባብ ሃይማኖተኛነት ወይም ብሄርነት ሳያግዳቸው ሁሉንም በሚችሉት ያህል ያሰተናግዱ ነበር...አንደ ጊዜ እንኳ መጠፎ ነገር ሳይወጣችው ቢሰደቡ እንኳ ይቀር ሰላም ይሰፈን ይሉ ነበር...በፖለቲካ ሆነ በአሰተሳሰብ ከማይገናኟችቸው ጋርም ሆነ ከሌላ ማንንም ሳያቆስሉ ከሁሉም ጋር በሰላም ለመኖር ይጥሩ ነበር...እኔ እንጃ አላውቅም ሰው ነው የተቀይረው ወይሰ ዘመኑና ጊዜው...እንደ ሞኒካ ጨዋ የሆነ ሰው ደሰ ካላለው ድምጹን ሳያሰማ ረጋ ብሎ ይሰወራል...ዛሬ ይህን ቤት ያሰታወሰኝ አንዲት ልጅ በግርድና ከኢትዮጵያ ከወጣች በኋላ አሰሪዎቿ እንደ ባሪያ ሊጠቀሟት ሲሞክሩ እምቢ ብላ ሸሸታ ከጠፋች በኋላ ሞኒካ ና ዋርካዊያን እዚሁ ቤት ዋርካ ላይ ባደርጏላት እርዳታ ነጻ ወጥታ የግል ሂወቷን እንድትቀጥል የተደረገች ሰለሆን ቁጭ ብላ ሰታጫውተኝ ብዙ ነገር ትዝ ብሎኝ ነው እዚህ ቤት ብቅ ያልኩት...ዘመን ጊዜ ወይሰ ሰው ይሆን የሚቀየረው ...ሁለቱም ሊቀይሩ ይችላሉ...እንደ ሞኒካ ያሉት ግን በእርግጠኛነት ማእድናቸው አይቀይርም !!!

ጌታህ ከፒያሳ (አራዳ)

Monica**** wrote:Mo's coffee house ሁሉንም የዋርካ ታዳሚዎች ትልቅ ትንሽ ሳይል በደስታ ያስተናግዳል!
ይሄ ቤት በተለይ ይሄ ቤት ጥቅሙ ስዎች who wants to get away from hustle and bustle of their daily lives!!!

ኮፊ ሀውሳችን ቀልዶችን ምክርንና, ራስልምድ ላይ የደረሱ አስቂኝና አሳዛኝ ነገሮች, መወያየት የምንችልበት ባህላዊ ቤት ነውና......ladys and gents. please feel free!!!
Mo's coffee house is helping you to unwind and slacken since you can talk about anything and everything under the sun!!!!(as long as it is refrain from obscene, and racist remarks)

Mo's coffee house ምንም እንክዋን ለቡናችንና ለደስታችሁ ገንዘብ ባናስከፍልም...............አንድ ነገር የምትጠየቁት እዚህ ቤት ለመጀመሪያ ጊዜ ስትገቡ አንድ የሚያስቅ ነገር የደረስባችሁን ወይም የምታውቁት ስው ላይ የደረስውን እንድታጫውቱን ስጠይቅ በደስታ ነው::
እስኪ እኔ የማውቀውን አንድ ልበል

***********

አዲሳበባ ለእረፍት ሄጄ....... አንድ ቅዳሜ ከስአት በህዋላ ለመውጣት ሽር ብትን ስል መልክት ይዤ የመጣሁለት ስው አጉል ስአት ደውሎ እቃውን ልወስድ ነበር ይለኛል..... እኔም እቤት ጥዬልህ እሄዳለሁ ስለው እዛው ቤታችሁ አካባቢ ነኝ ይለኝና ይዘሽው የምትሄጂው መልክትም ስላለኝ የሆነ ኬክ ቤት ይዘሽው ነይ ይለኛል ( literally I live 3 minutes walk from the place and I think it was a new hot spot)
እኔም በአለም ላይ እንደኔ ዘናጭ ያለ የለም የምል እመስላለሁ.....ትንሽ የዘመድ ልጅ ቢጤ አስከትዬ መሬት ለምን ነካኝ ብዬ ቀና ዘርጋ ስል ኬክ ቤቱ ከፊትለፊት ይታየኛል እና ቅዳሜ ስለሆነ መኪናውና ስው ሞልቶታል......እኔም የአገሩ ሁሉ አይንና አቴንሽን እኔ ላይ ነው ብዬ አስቤ በኩራት ስራመድ (የዛ ጊዜ መንገድ እየተስራ ነበር.....) ያው የአገራችን መንገድ ጉድጉዋድ ምናምን አያጣውም አይደል....አንድ ከርካሳ ታክሲ በአጠገቤ ሲያልፍ ትዝ ይለኛል ከዛ በህዋላ የሆነው እንደው ጭንቅላቴን እንደቴፕ slow motion አድርጌ ሳስበው.......ያ የተረገመ ታክሲ ነጂ ጎማው እዛ ditch ውስጥ ገብቶ ለካ የአለም የጭቃ ውሀ ከጸጉር እስከ እግሬ ድረስ አልብሶኛል!!አቤትትትትትትትት ቅሌትትትትትትትትት :evil: :evil: :evil: :evil: ምናለ መሬቱ ተስንጥቆ ቢውጠኝ አምላክ እንደዛ ከሚያዋርደኝ ነበር ያልኩት! እርግጠኛ ነኝ መቼም ስው ጥሩ ነገር ሲሆን አያይም ለመጥፎ ግን ማን ብሎን............. በልቤ የመስለኝ የመንገዱ ትራፊክ አንድ ፕሬዘዳንት እንክዋን ሲመጣ እንደዛ መኪናና ህዝብ አይበዛም( 3 መኪናም ቢሆን እንደዛ አይነት ጊዜ ላይ 30 ሆኖ ነው የሚታየው)!!! ስዉ አንዳንዱ አፍጥጦ ሲያየኝ ግማሹም ታክሲ ነጂውን ሲሳደብ ግማሹም ደህና ነሽ ሲል....... (እንዳላለቅስ አፍሬ ወደቤት ሩጫዬን) ከዛ በህዋላ እዚህ እስክመለስ ድረስ በእግሬ ከቤቴ በራፍ ፍንክች አልልም ነበር!!!
ይባስ ብሎ ያቀሽም ልጅ ሻወር እንክዋን መውስጃ ጊዜ ሳላገኝ እኔ መሆኔን አውቆ ከ2 ቆንጆ ጉዋደኞቹ ጋር እቤት ተከትሎኝ ከች :evil: :evil: :evil: በመጀመሪያ ደረጃ እቤትና ስለው እምቢ ያለው ልጅ አሁን በጭቃ ቦክቼ ሊስቅ ነው የመጣው? :evil: :evil: :evil: :evil: ዳሩ በአመቱ ስመለስ ያስታወስኝም ስው ያለ አይመስለኝም እዛ አካባቢ ካሉት ሊስትሮዎች በቀር.....ከድሮ ጀምሮ ስለማውቃችው :oops: :oops: :oops: መንገዱም ቆንጆ ሆኖ ተስርቷል!

በሉ ቡና ድገሙ እባካችሁ
ጌታህ
ውሃ አጠጪ
ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1209
Joined: Sat May 30, 2009 3:05 pm

Re: Mo's coffee house!!!

Postby እሰፋ ማሩ » Sat Dec 30, 2017 4:33 am

ውዲት ሙኒት የዋርካ ንግስት እስኪ ብቅ በይ እነጌታም ይጠሩ ወያኔ ሊቀበር ደስታችን ሊሰምር በደጅ ነው...

ጌታህ wrote:ይህ ዘመን የት ደረሰ...እነ ሞኒካሰ የት ናቸው...የዛሬ 12 አመት ሰው እንዲህ ያሰብ ነበር...ለዚህም ነበር ወርቃማ ዘመን ተብሎ መታወሰ ያለበት...ዋርካዊያን እንዲህ ነበር የሚያሰቡት..."ትልቅ ትንሸ ሳይል በደስታ ያሰተናግዳል"ነበር አሰተሳሰባቸው...ትልቅ ነነ ትንሸ አይደለንም አወቅን ሳይሉ...ያላቸውን ሁሉ ያካፍሉ ነበር ሳይሰሰቱ....የሰውን ልጅ ለመርዳት በተለይ ሓበሻን የማይጏዙት ርቀት አልነበረም...ራቀን ቀረበን ሳይሉ..የሚከፍሉትም አሰተዋጽኦ ቀላላ አልነበረም...የሚያውቁትን ለሁሉም ሲያካፍሉ...ሰው የሚያውቀውን ለመሰማት ና ለመረዳት ለማወቅም ሳይሳናቸው ጠባብ ሃይማኖተኛነት ወይም ብሄርነት ሳያግዳቸው ሁሉንም በሚችሉት ያህል ያሰተናግዱ ነበር...አንደ ጊዜ እንኳ መጠፎ ነገር ሳይወጣችው ቢሰደቡ እንኳ ይቀር ሰላም ይሰፈን ይሉ ነበር...በፖለቲካ ሆነ በአሰተሳሰብ ከማይገናኟችቸው ጋርም ሆነ ከሌላ ማንንም ሳያቆስሉ ከሁሉም ጋር በሰላም ለመኖር ይጥሩ ነበር...እኔ እንጃ አላውቅም ሰው ነው የተቀይረው ወይሰ ዘመኑና ጊዜው...እንደ ሞኒካ ጨዋ የሆነ ሰው ደሰ ካላለው ድምጹን ሳያሰማ ረጋ ብሎ ይሰወራል...ዛሬ ይህን ቤት ያሰታወሰኝ አንዲት ልጅ በግርድና ከኢትዮጵያ ከወጣች በኋላ አሰሪዎቿ እንደ ባሪያ ሊጠቀሟት ሲሞክሩ እምቢ ብላ ሸሸታ ከጠፋች በኋላ ሞኒካ ና ዋርካዊያን እዚሁ ቤት ዋርካ ላይ ባደርጏላት እርዳታ ነጻ ወጥታ የግል ሂወቷን እንድትቀጥል የተደረገች ሰለሆን ቁጭ ብላ ሰታጫውተኝ ብዙ ነገር ትዝ ብሎኝ ነው እዚህ ቤት ብቅ ያልኩት...ዘመን ጊዜ ወይሰ ሰው ይሆን የሚቀየረው ...ሁለቱም ሊቀይሩ ይችላሉ...እንደ ሞኒካ ያሉት ግን በእርግጠኛነት ማእድናቸው አይቀይርም !!!

ጌታህ ከፒያሳ (አራዳ)

Monica**** wrote:Mo's coffee house ሁሉንም የዋርካ ታዳሚዎች ትልቅ ትንሽ ሳይል በደስታ ያስተናግዳል!
ይሄ ቤት በተለይ ይሄ ቤት ጥቅሙ ስዎች who wants to get away from hustle and bustle of their daily lives!!!

ኮፊ ሀውሳችን ቀልዶችን ምክርንና, ራስልምድ ላይ የደረሱ አስቂኝና አሳዛኝ ነገሮች, መወያየት የምንችልበት ባህላዊ ቤት ነውና......ladys and gents. please feel free!!!
Mo's coffee house is helping you to unwind and slacken since you can talk about anything and everything under the sun!!!!(as long as it is refrain from obscene, and racist remarks)

Mo's coffee house ምንም እንክዋን ለቡናችንና ለደስታችሁ ገንዘብ ባናስከፍልም...............አንድ ነገር የምትጠየቁት እዚህ ቤት ለመጀመሪያ ጊዜ ስትገቡ አንድ የሚያስቅ ነገር የደረስባችሁን ወይም የምታውቁት ስው ላይ የደረስውን እንድታጫውቱን ስጠይቅ በደስታ ነው::
እስኪ እኔ የማውቀውን አንድ ልበል

***********

አዲሳበባ ለእረፍት ሄጄ....... አንድ ቅዳሜ ከስአት በህዋላ ለመውጣት ሽር ብትን ስል መልክት ይዤ የመጣሁለት ስው አጉል ስአት ደውሎ እቃውን ልወስድ ነበር ይለኛል..... እኔም እቤት ጥዬልህ እሄዳለሁ ስለው እዛው ቤታችሁ አካባቢ ነኝ ይለኝና ይዘሽው የምትሄጂው መልክትም ስላለኝ የሆነ ኬክ ቤት ይዘሽው ነይ ይለኛል ( literally I live 3 minutes walk from the place and I think it was a new hot spot)
እኔም በአለም ላይ እንደኔ ዘናጭ ያለ የለም የምል እመስላለሁ.....ትንሽ የዘመድ ልጅ ቢጤ አስከትዬ መሬት ለምን ነካኝ ብዬ ቀና ዘርጋ ስል ኬክ ቤቱ ከፊትለፊት ይታየኛል እና ቅዳሜ ስለሆነ መኪናውና ስው ሞልቶታል......እኔም የአገሩ ሁሉ አይንና አቴንሽን እኔ ላይ ነው ብዬ አስቤ በኩራት ስራመድ (የዛ ጊዜ መንገድ እየተስራ ነበር.....) ያው የአገራችን መንገድ ጉድጉዋድ ምናምን አያጣውም አይደል....አንድ ከርካሳ ታክሲ በአጠገቤ ሲያልፍ ትዝ ይለኛል ከዛ በህዋላ የሆነው እንደው ጭንቅላቴን እንደቴፕ slow motion አድርጌ ሳስበው.......ያ የተረገመ ታክሲ ነጂ ጎማው እዛ ditch ውስጥ ገብቶ ለካ የአለም የጭቃ ውሀ ከጸጉር እስከ እግሬ ድረስ አልብሶኛል!!አቤትትትትትትትት ቅሌትትትትትትትትት :evil: :evil: :evil: :evil: ምናለ መሬቱ ተስንጥቆ ቢውጠኝ አምላክ እንደዛ ከሚያዋርደኝ ነበር ያልኩት! እርግጠኛ ነኝ መቼም ስው ጥሩ ነገር ሲሆን አያይም ለመጥፎ ግን ማን ብሎን............. በልቤ የመስለኝ የመንገዱ ትራፊክ አንድ ፕሬዘዳንት እንክዋን ሲመጣ እንደዛ መኪናና ህዝብ አይበዛም( 3 መኪናም ቢሆን እንደዛ አይነት ጊዜ ላይ 30 ሆኖ ነው የሚታየው)!!! ስዉ አንዳንዱ አፍጥጦ ሲያየኝ ግማሹም ታክሲ ነጂውን ሲሳደብ ግማሹም ደህና ነሽ ሲል....... (እንዳላለቅስ አፍሬ ወደቤት ሩጫዬን) ከዛ በህዋላ እዚህ እስክመለስ ድረስ በእግሬ ከቤቴ በራፍ ፍንክች አልልም ነበር!!!
ይባስ ብሎ ያቀሽም ልጅ ሻወር እንክዋን መውስጃ ጊዜ ሳላገኝ እኔ መሆኔን አውቆ ከ2 ቆንጆ ጉዋደኞቹ ጋር እቤት ተከትሎኝ ከች :evil: :evil: :evil: በመጀመሪያ ደረጃ እቤትና ስለው እምቢ ያለው ልጅ አሁን በጭቃ ቦክቼ ሊስቅ ነው የመጣው? :evil: :evil: :evil: :evil: ዳሩ በአመቱ ስመለስ ያስታወስኝም ስው ያለ አይመስለኝም እዛ አካባቢ ካሉት ሊስትሮዎች በቀር.....ከድሮ ጀምሮ ስለማውቃችው :oops: :oops: :oops: መንገዱም ቆንጆ ሆኖ ተስርቷል!

በሉ ቡና ድገሙ እባካችሁ
እሰፋ ማሩ
ዋና ውሃ አጠጪ
ዋና ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1550
Joined: Mon Sep 12, 2016 8:47 pm

Re: Mo's coffee house!!!

Postby ቢተወደድ1 » Fri Jan 19, 2018 2:13 pm

አለቅላቂው አጠፋ ማሩ
ጦርነት በሌለበት እንዴት ሰለ ምሽግ ታወራለህ???

እሰፋ ማሩ wrote:ውዲት ሙኒት የዋርካ ንግስት እስኪ ብቅ በይ እነጌታም ይጠሩ ወያኔ ሊቀበር ደስታችን ሊሰምር በደጅ ነው...

ቢተወደድ1
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 518
Joined: Thu Sep 01, 2016 8:48 am
Location: Bisheftu

Re: Mo's coffee house!!!

Postby እሰፋ ማሩ » Fri Jan 19, 2018 8:48 pm

ቢትወደድ ወያኔው ዛሬ ምንም እንደተለመደው ትክዳላችሁ? የአለም ማህበር ሃያላን የህዝባችንን ብሶት በሚገባ ተርድተው ጌቶችህን እያስጨነቁ ነው ቅቅቅ
DW.COM IN 30 LANGUAGES DW AKADEMIEABOUT DW
Deutsche Welle
የተባበሩት መንግሥታት በኢትዮጵያ ተጨማሪ የፖለቲካ እስረኞች እንዲፈቱ ጠየቀ
የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ኢትዮጵያ የተቀዋሚ ፓርቲ መሪውን ዶ/ር መረራ ጉዲናን ጨምሮ 115 እስረኞችን መልቀቋን አደነቀ፡፡ ይሁን እንጂ የኢትዮጵያ መንግሥት አሁንም በእስር ላይ የሚገኙ በሺህ የሚቆጠሩ ሰዎችን ሁኔታ ዳግም አጢኖ እንዲለቅ ጠይቋል፡፡
Merara Gudina Vorstizender der OPC (Getty Images/AFP/E. Goujon)
የመንግሥታቱ ድርጅት በዛሬው መግለጫው የኢትዮጵያ መንግሥት የጸረ-ሽብር ሕጉን እንዲያላላ፤ በመብት ተሟጋቾች እና በመገናኛ ብዙሃን ባለሙያዎች ላይ የሚወስደውን እርምጃም እንዲያቆም አሳስቧል፡፡ የተባበሩት መንግሥታት የሰብዓዊ መብት ኮሚሽን ቃል ቃል አቃባይ ሊዝ ትሮሴል፤ “የኢትዮጵያ መንግሥት አሁን የጀመረውን አበረታች እርምጃ በመቀጠል በፖለቲካ አመለካከታቸው እና እምነታቸው ምክንያት የታሰሩ ሌሎች ሰዎችን እንዲለቅቅ እናሳስባለን” ብለዋል፡፡ “ኢትዮጵያ በወሳኝ ጊዜ ላይ እንደምትገኝ እናስባለን፡፡ ለዚህም ነው ኢትዮጵያን ለመርዳት ዝግጁ ነው ነን የምንለው፤” ሲሉ ቃል አቃባይዋ ዛሬ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ አክለው ተናግረዋል፡፡
ኢትዮጵያ ዉስጥ አሁን በእስር ላይ ያሉ ሰዎች ትክክለኛ ቁጥር እንደሌላቸው ነገር ግን በሺህዎች እንደሚቆጠሩ ጠቁመዋል፡፡ “ባለመረጋጋቱ እና በአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ወቅት ከ20 ሺህ በላይ ሰዎች ታስረው እንደነበር የሚያሳዩ ዘገባዎች አሉን፡፡ ከእነዚህ ውስጥ የተወሰኑት ተለቅቀዋል ነገር ግን አሁንም ቁጥራቸው ከፍተኛ የሆነ ሰዎች በእስር ላይ እንዳሉ እናምናለን” ሲሉም አክለዋል፡፡
የፌደራል ጠቅላይ አቃቤ ሕግ አቶ ጌታቸው አምባዬ ባለፈው ሰኞ በሰጡት መግለጫ የኢትዮጵያ መንግሥት በመጀመሪያው ዙር በጥቅሉ 528 እስረኞችን እንደሚለቀቅ አስታውቀው ነበር፡፡ ይቅርታ የመስጠቱ እና ክስ የማቋረጡ ሂደት ለሁለት ወር ያህል እንደሚቀጥል መናገራቸውም አይዘነጋም፡፡
የኢትዮጵያ መንግሥት የጸረ-ሽብር ሕጉን እንደገና እንዲከለስም የጠየቁት ቃል አቃባይዋ፤ ሕጉ “ለትርጉምም ሆነ ለአተገባበር ሰፊ በሆነ መልኩ ጥቅም ላይ ውሎ ሰዎች በስህተት ወይም በዘፈቀደ ለእስር እንዳይዳረጉ እንዲያረጋግጥም፤” አሳስበዋል፡፡ ከዚህ በተጨማሪም የኢትዮጵያ መንግሥት መንግሥታዊ ያልሆኑ ድርጅቶችን እና የመገናኛ ብዙሃን ሥራ ላይ ገደብ የሚጥሉ ሕጎቹን ሊያሻሽል ይገባዋል ማለታቸዉን የሮይተርስ ዘገባ ዘርዝሯል።
ተስፋለም ወልደየስ
ሸዋዬ ለገሠ
እሰፋ ማሩ
ዋና ውሃ አጠጪ
ዋና ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1550
Joined: Mon Sep 12, 2016 8:47 pm

PreviousNext

Return to Warka Intimate - ዋርካ ፍቅር

Who is online

Users browsing this forum: Google [Bot] and 6 guests