Mo's coffee house!!!

The Love Forum (love, relationship) (የኔ ቆንጆ እንተዋወቅ :-)

Postby Monica**** » Thu Dec 29, 2005 5:54 pm

እማማ እርጎየ
ደህና ዋሉልኝ እናቴ? ቅድም ለቅሶ ልደርስ ሄጄ መጥተው አጡኝ አሉ! ዛሬ ማምሻውን እዚሁ ነኝ እባክዎን ኑና እንጫወት!
እማማ እርጎዬ መልክና ቁመናው መጀመሪያ ካላማረ እንዴት አድርጌ ልወደው እችላለሁ?????
በርግጥ ቁመናውን አሳምሮ ጸባይ ከሌለው ልክ ነው እንደዛ አይነት ወንድ ጨጉዋራ ነው የሚልጠው........ግን በእርስዎ አስተያየት አንድን ወንድ መጀመሪያ ለመቅረብ መልክ አስፈላጊ ነው ወይስ ጸባይ?
የጸባዩን ቁንጅና እንዴት ላውቅ እችላለሁ መልኩን ሳልወድ???
ድሮ ወንዱን ሁሉ ያጋድሉ ነበር ሲባል ስምቻለሁ እስኪ ትንሽ አጫውቱኝ!

መሽቷል ብለው አያስቡ ዘቢደሩ ታደርስዎታለች ኢቺ ደንባራ ዳሩ የት እንደምትሄድም አታውቀው......በቃ እዚህ ያድራሉ ጠዋትም ነገ የአመቱ መድሀኒአለም ነው አብረን ሄደን እናስቀድሳለን :wink:
እማማ እርጎየ wrote:
ልጄ ....ወንድም...አሳቢ...መከታ...መኩሪያ የሆነ ባል ይስጥሽ::

ሞኒካዬ እንደዛሬ ልጆች መልክና ቁመና አይማርክሽ ልጄ....የውስጥ ነገር ነው ዋናው....ቁምነገር ..ቁምነገር ልጄ....ቅን ከሆነ...የሚወድሽ ከሆነ...ዘመዶችሽን የሚወድ ከሆነ .....ገንዘብ የማይወድ ከሆነ.....በቃ እሱ ነው ባልሽ...ታዲያ የኔንም ነገር ንግሪው...ይቺን የለመድኩዋትን ቁርስ እንዳይነፍገኝ:: አዎ...ደግ ባል ነው ባል ማለት:: አይይ የኔ ባል.....መሬቱ ይቅለላቸውና...መቸም ባል ብሎ ዝም ነበሩ:: ኤዲያ ትዝታየ ተቀሰቀሰ .. :(

ልሂድ ልጄ..ከቤተክሲያን ስመጣ ብቅ እላለሁ::

ቸር ይግጠመን::
Monica****
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 3195
Joined: Fri Dec 26, 2003 10:24 pm
Location: 999 Total eclipse st. Venus

Postby ባቲ » Thu Dec 29, 2005 10:24 pm

SUAVE:
ጥሩ ጀምረኸው ምነው ባጭሩ አስቀረኸውሳ::
እኔም እንዳንተው የድሮ መርካቶን መርካቶ ፈልጌ አጥቻት ነበር:: አርቤሽት የምንጫወትባቸው ቦታዎች አሁንም ተከብረው አሉ:: ከጉርሻ መሸጫው ማዶ ወንዙን ተሻግረህ:: ምነው ? ምነው? ከቴ ምን በደለችህ? ትምርት ቤት ፎርፈን በአንድ ሽልንግ በህንድ ና በቻይና ሙቪ ተዝናንተን እንደብሩ ስሊ....ያአአአአ! አፍንጫችንን በአውራ ጣትገፋ እያደረግን......., በህንድኛ እየዘፈንን የምንመለስባት:: ከቴ በጀርባችን ላይ ይፈስ የነበረው,ስሙን አልጠራም, ሳስጠይፈኝ አንድ ብር ተሀምሳ ከፍዬ , ኑሮ ተወዷል, አንድ የህንድ ሙቭ አይቻለሁ:: ግን ቴቦ ሲል ድሮ እዚያ በር እንዳትደርሱ የሚሉን የነበሩ አሮጊትና ሽማግሌዎች ከጎኔ በማየቴ.....ከቴ አንቺም ተለወጥሽ ብዬ ነበር የወጣሁት::
SaQ _Be _SaQ.....That's what I wish 4 all of Us
ስምየ ውዕቱ ክንዴ ባቲ
ባቲ
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 942
Joined: Tue Jul 06, 2004 8:18 pm
Location: ethiopia

Postby ዩፎ » Fri Dec 30, 2005 6:14 am

ወዳጄ ቶም:- በጣም ያማምራሉ:: አቦ እግዜር ይባርክህ ቀኔን አብርተሀት ዋልክ:: አሁን ይቺንም ለመናገር ለገባሁዋት 'አንድ ጣል' ማድረግ አለብኝ ማለት ነው? ለነገሩ ከጌታ የተማርኩዋት አንድ ነገር አለች - በክሬዲት ቡና መጠጣት!! ሌላ ጊዜ ተግባራዊ ትሆናለች::

እዚሁ አሜሪካ አንድ ኢትዮጵያዊ የዪኒቨርሲቲ መምህር ላይ የደረሰውን ነገር ነው የማጫውታችሁ:: ሰውየው የክፍሉን ተማሪዎች 'እናንት ቀሽሞች..' ምናምን እያለ ይሳደባል - አገሩ እንደለመደው መሆኑ ነው እኮ:: ከጥቂት ጊዜ ቡሀላ ተማሪዎቹ በትምህርት ቤቱ ጋዜጣ ላይ 'ክፍት የስራ ቦታ ይህንን አይነት ትምህርት ለማስተማር' ብለው ሰውየው የሚያስተምረውን ትምህርት ጠቅሰው 'satire' ይጽፋሉ:: በአጭር ጊዜ ውስጥ የዪኒቨርሲቲው አስተዳደር ተመካክሮ ኢትዮጵያዊውን መምህር ከስራው አሰናበተው::
ዩፎ
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 132
Joined: Sat Dec 25, 2004 10:29 pm
Location: united states

Postby ትትና » Fri Dec 30, 2005 9:29 am

እረ ኮፊ ሀውስ!! እኔ የት ሄጄ ነው ይሄ ሁሉ የሆነው? ቆይ ምርቃት የሚባል ነገር ቀረ አዲስ ቢዝነስ ሲጀመር ነው እኔ አልተጠራሁም? ሞንዮ በጣም ሀሪፍ ቤት ነው ቆይ ወሬ ልፈልግና ልመለስ:: ግን እኮ የዴብዚነትን ጠጅ ቤት ልታከስሪው ነው: :D

ምንግዜም አክባሪሽ!
ትትና
ውሃ አጠጪ
ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1253
Joined: Wed Feb 23, 2005 11:26 am
Location: united states

Postby Monica**** » Fri Dec 30, 2005 11:32 am

መምህር ባቲ
ከመቀመጫዬ ብድግ ብዬ እጅ ነስቻለሁኝ!!!
ስለመርካቶ የምታውቀው ታሪክ ጥሩ ነው! እነ ልብስ ሊስፋልኝ ወይም ሊገዛልኝ ከእናቴ ጋር ዱክ ዱክ እያልኩኝ ነበር የምሄደው እሱም በአመት 2 ጊዘ( ለእንቁጣጣሽና ለጥምቀት ያልሆነ ልብስ ይበጣጠስ ይባል የለ :lol: :lol: :lol: :lol: ) እሱንም ወደቤት ለመመለስ ታክሲ ላይ እስክሳፈር ልቤን ጭንቅ እንዳልኝ ነበር የምመለስው! ይብላኝ ለነእናቴ በየ2ሳምንት ምናምን ለሚሄዱት! አቤት ትርምስ አቤት ጩህት!
አሁን ግን ስሄድ በሌላ አይኔ ስላየሁት ነው መስለኝ የማየው ነገር ግማሽ መግማሽ ቢያሳዝነኝም ruthless የቢዝነስ ስዎች መሆናችውን ሳላደንቅ አላለፍኩም::
ባቲ ይልመድብህ ያገር ልጅ


**************************

ዩፎ የኔ ቆንጆ
አንተማ እዚህ ቤት በገባህ ቁጥር የግድ ገጠመኝ ማጫወት የለብህም!! Senior member እኮ ነህ :wink: :wink: :wink:
እኔ አንተና ቶም አዋሳ ዋርካ ውስጥ ተከታትለን መወለዳችንን አላወቅኩም ነበር :lol: :lol: :lol: በል አንድ ማኪያቶ ላምጣልህ :wink:


**************
ትቴክስ የኔ ቆንጆ
ወይ ጉድ እኔም መቼ እንደምከፍት አወቅኩኝ አንዱ ደግ ነው ገዝቶ የስጠኝ :wink: እንደ SUAVE አባባል ከሆነ ነው ታዲያ
ትትናዬ እረ እኔ ከእህቴ ከደብዚ እንዳያጣላኝ ይሄ ቤት የሷ ማታ ማታ ጠጅ መጠጫ ነው! የኔ ማታ ማታ ደብዚ ቤት ልባችውን በጠጅ ያቃጠለላችውን በትኩስ ቡና ማብረጃ ነው! If there is any conflict of interest, I will be happy to close this coffee House!!!
በይ እስኪ የኔ ቆንጆ ለማንኛውም አንድ ቡና ልበልሽ በሞቴ
Monica****
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 3195
Joined: Fri Dec 26, 2003 10:24 pm
Location: 999 Total eclipse st. Venus

Postby leflafi » Fri Dec 30, 2005 4:13 pm

ሰላም ሞኒካ ለንግዳ ቤቱ ይፈቀድ እንድሆነ አላወኩም ግን በሩ ገርበብ ብሎ የቡናውእና የእጣኑ ሽታ ሲሽተኝ በቡና አልጨክንም እና ለዝያነው ዘው ብየ የገባሁት ፍቃደሽ ከሆነ ለማንኛውም ከበዙ አመት የውጭ አገር ኑሮ በኌላ አዲስ አበባ ለረፍት ሄጀ የደርስብኝን ለንገርሽ አንድ ቀን እኔ ና አበሮኝ የሄደው ጉአደኛየ ከዘመድ በተዋስነው መኪና ምሺቱን ለማየት ወደ ከተማ ብቅ አልን ከብዙ የምሽ ቤት ዙረት በኌላ በዙ መኪና ተደረድሮ ባየንበት አንድ የምሽት ቤት ጥልቅ አልን እዛም ዘፈን እየሰማን እያለ ሁለት እህቶች ፊት ለፊታችን ቁጭ በለው አይናቸወን ለደቂቃ እንኵን ሳይነቅሉ ትኩር ብለው ይመለከቱን ጀመር ጓዋደኛየ በፍርሀት ሹክሹታ ለምን እንደዚህ ትኩር ብለው እንደሚያዩን እየጠየቅኝ እያለ አንደኝኣዋ ምጥታ ሲጋራ እንዳለን ጠየቀችን ሲጋራ እንደማናጨስ ከነገርናት በኌላ ብቻአቸውን ከሆኑና
ከኛ ጋር መቀምጥ እንደሚፈልጉ ጓደኝአየ
ጋበዛቸው እንሱም ለአንድ ደቂቃ እንኵኣን ሳያመነቱ እሽ አሉን የሚጠጡትን ነገር አስትናጋጁ እንዲአመጣአላቸው
ከአስደርገን በሁአላ በስሱ ወሬ ጀመርን ምን እንደሚሰሩም
ስንጠየቃቸው ተማሪ እንድሆኑም ነገሩን እኛም በተባለነው መሰረት ከውጭ የመጣን መሆኑን ላለመናገር በሰፈራችን ያለመስርያቤት ውስጥ እንደምንሰራ ነገርናቸው(እዚህ ላይ እናአንተ ውሽታም እንዳትየን) ምክናይቱም ዘመድ ጉአደኛ ከውጭ መምጣታቺሁን ካውቁ የዘርፉአችኌል ሰለተባለን ነው አትፍረጂብን ወደ ቁም ነገሩ ልግባና ሁላችንም ከደጋገምን በኌላ መጠጡን ሌላ መሄድ የሚፈልጉበት ቦታ ካለ ጠይቀናቸው የዛን ቤት የጠጣንበትን ሂሳብ ከፍለን ወደ
ሚቀጥለው የምሽት ቤት መንዳት ጀመርን
አሁን ሰራ መሄጃየ ደርሰ ተከታዩን 2 ለታኛውን ቡና ለመጠጣት ሰመጣ ኣጫውትሽኣለሁ ከተፍቀደለኝ
leflafi
አዲስ
አዲስ
 
Posts: 27
Joined: Fri Dec 23, 2005 4:45 pm

Postby Estifanos_K » Fri Dec 30, 2005 6:54 pm

ደና አመሻቹ የMCH ወሬኞች እኔ ማውራት አልወድም ስታወሩ ለመስማትና ካፑቺኖ ለመጠጣት ነው የገባሁት:: በሉ እንደ ሰላይ አጠገባቹ ተቀምጨ ወሬ ስለምሰማ ድምጻቹን ከፍ አርጋቹ አውሩ:: እንቢ ካላቹ ግን ወዮላቹ::
Estifanos_K
ጀማሪ ኮትኳች
ጀማሪ ኮትኳች
 
Posts: 89
Joined: Sun Jun 26, 2005 10:46 pm
Location: ethiopia

Postby Monica**** » Sat Dec 31, 2005 12:53 am

leflafi ስላም ያገር ልጅ
ቤቱ ለማንኛውም ኪሱ ውስጥ የቡና መጠጫ ወሬ ይዞ ለሚመጣ ሁሉ ክፍት ነው :lol: :lol: :lol: :lol:
ምናለበት አሁን በአርቡ ምድር በወሬ ልቤን ስቅለህ ባትጠፋ!!! ነገ ብቅ ስትል ሁለት ሶስት ጁሲ የሆነ ወሬ ይዘህ እንድትመጣ ኮፊ ሀውሱ ፈርዶብሀል( በሌለህበት)
በል በጉጉት እየጠበቅኩ ነው መጨረሻውን ለመስማት!
እስከዛው በቸር ይግጠመን
Monica****
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 3195
Joined: Fri Dec 26, 2003 10:24 pm
Location: 999 Total eclipse st. Venus

Postby Monica**** » Sat Dec 31, 2005 12:55 am

Estifanos -k
የኔ ዝምተኛ! አንተ ናና ቡናህን ጠጣልኝ ባታወራም ከታዘብክ ይበቃኛል :wink: :wink: :wink:
በል መልካም አዲሳመት ይሁንልህ የኔ ቆንጆ
Monica****
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 3195
Joined: Fri Dec 26, 2003 10:24 pm
Location: 999 Total eclipse st. Venus

Postby Monica**** » Sat Dec 31, 2005 1:07 am

ስላም ለቡና አጣጮቼ ሁሉ
እስኪ እጣኑም እየጨስ ነው ቡናውም ቆንጆ ሆኖ ቀርቧል...... እማማ እርጎየ ባሉት ነገሮች ላይ ያነሳሁትን የሚመልስ ጀግና ዘራፍ ይበል :lol: :lol: :lol:

Monica**** wrote:እማማ እርጎዬ መልክና ቁመናው መጀመሪያ ካላማረ እንዴት አድርጌ ልወደው እችላለሁ?????
በርግጥ ቁመናውን አሳምሮ ጸባይ ከሌለው ልክ ነው እንደዛ አይነት ወንድ ጨጉዋራ ነው የሚልጠው........ግን በእርስዎ አስተያየት አንድን ወንድ መጀመሪያ ለመቅረብ መልክ አስፈላጊ ነው ወይስ ጸባይ?
የጸባዩን ቁንጅና እንዴት ላውቅ እችላለሁ መልኩን ሳልወድ???
ድሮ ወንዱን ሁሉ ያጋድሉ ነበር ሲባል ስምቻለሁ እስኪ ትንሽ አጫውቱኝ!

መሽቷል ብለው አያስቡ ዘቢደሩ ታደርስዎታለች ኢቺ ደንባራ ዳሩ የት እንደምትሄድም አታውቀው......በቃ እዚህ ያድራሉ ጠዋትም ነገ የአመቱ መድሀኒአለም ነው አብረን ሄደን እናስቀድሳለን :wink:
እማማ እርጎየ wrote:
ልጄ ....ወንድም...አሳቢ...መከታ...መኩሪያ የሆነ ባል ይስጥሽ::

ሞኒካዬ እንደዛሬ ልጆች መልክና ቁመና አይማርክሽ ልጄ....የውስጥ ነገር ነው ዋናው....ቁምነገር ..ቁምነገር ልጄ....ቅን ከሆነ...የሚወድሽ ከሆነ...ዘመዶችሽን የሚወድ ከሆነ .....ገንዘብ የማይወድ ከሆነ.....በቃ እሱ ነው ባልሽ...ታዲያ የኔንም ነገር ንግሪው...ይቺን የለመድኩዋትን ቁርስ እንዳይነፍገኝ:: አዎ...ደግ ባል ነው ባል ማለት:: አይይ የኔ ባል.....መሬቱ ይቅለላቸውና...መቸም ባል ብሎ ዝም ነበሩ:: ኤዲያ ትዝታየ ተቀሰቀሰ .. :(

ልሂድ ልጄ..ከቤተክሲያን ስመጣ ብቅ እላለሁ::

ቸር ይግጠመን::
Monica****
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 3195
Joined: Fri Dec 26, 2003 10:24 pm
Location: 999 Total eclipse st. Venus

እስቲ እኔም አንድ ልበል

Postby የመርካቶው ሰያ » Sat Dec 31, 2005 5:59 am

ሠላም ሞኒካ !እንቅልፍ ባይኔ አልዞር ብሎ ወሬ ስቃርም
ለመጀመሪያ ጊዜ ዋርካ ፍቅር ዘው ስል ቡና ቤትሽን አየሁ::ተመቸኝ::ጨዋው ሰው ይበዛበታል::የመርካቶን ጨዋታ ሳነብ በትዝታ ሄድኩ- አርቤሽት- ሲኒማ አዲስከተማ- ቆጮ ተራ-ዶሮ ተራ .... በነገራችን ላይ ጉርሻ ትክክለኛ ስሙ "ኡፋ"
ነበር :: እንግዲህ ሂሳብ ማለትሽ ስለማይቀር ቦርሳዬን ላውጣ.
ጊዜው ያ መጥፎ ዘመን ነበር:: "ቀይ ሽበር"::ፈድሉ ገና ጀማሪ ጫት ነጋዴ ነበር:: ጫት በጀርባው ተሽክሞ ሲሮጥ ቁም! ይሉታል አብዮት ጠባቂዎች:: አንተ ኢሕአፓ ነህ? ሲሉት እሱ አይደለሁም ማለት! ታዲያ መኢሶን ነህ?ኢዲዩ?
አሱ አደለሁም ማለት! ታዲያ ምንድነህ? እኔ ፈድሉ ነኝ!!
ግራ የገባ ጊዜ ነበር!
መልካም አዲስ አመት ለሁላችሁ
የመርካቶው ሰያ
ጀማሪ ኮትኳች
ጀማሪ ኮትኳች
 
Posts: 54
Joined: Fri Jan 14, 2005 9:13 am
Location: czech republic

አንድ ልጨምር

Postby የመርካቶው ሰያ » Sat Dec 31, 2005 6:15 am

ቦታው አልዩ አምባ ነው
ባልና ሚስት ተኝተው ሌሊቱ ሊነጋ አካባቢ ዘወትር ጎረቤት
ካለው መስጊድ "አላሁ አክበር" የሚለውን የሙአዚኑን ድምጽ
ስትሰማ ሚስት "እኒህ ሰው ድምጣቸው ማማሩ!"ስትል ባል በቅናት ቆሽታቸ አሮ መላ ሲፈልጉ ስንብተው አንድ ቀን ለሚስት መልክተኛ ልከው "ሸሁ ይጠሩሻል" ማለት ::ሚስት ደግሞ የውነት ሼሁ የጠሩዋት መሎዋት ተድብቃ ብትሄድ ባል እንደሸሁ ለብሶ ባለንጋ ገርፎ ወደቤቱዋ ይሰዳታል:
በነጋታው ሊነጋ ሲል "አላሁ አክበር" ሲል ሙአዚኑ ሚስት ዝም አሉ:: ባል ቀበል አድርገው እኒህ ሰው ድምጣቸው ማማሩ! ሲሉ ሚስት ለጥቀው "እጭ እቴ ይማታሉ አሉ! ይባላል
የመርካቶው ሰያ
ጀማሪ ኮትኳች
ጀማሪ ኮትኳች
 
Posts: 54
Joined: Fri Jan 14, 2005 9:13 am
Location: czech republic

Postby Monica**** » Sat Dec 31, 2005 9:34 am

ስላም የመርካቶ ሰያ
አንተን ዋርካ ፍቅር ውስጥ ሊያውም ሞኒካ ካፌ ማግኝት ትልቅ ክብር ነው!!! እረ እነ ዋቆንና ቆቁ የሚባሉትን የዋርካ ፖለቲክስ ብርቅዬዎችን ይዘህልኝና!! መቼም ዱራስንብትና ጥልቁ 1 ፖሊስ ጠርቼ ካላስመጣህዋችው እዚህ አይመጡም ብዬ ነው :lol: :lol: :lol:
ስለ ሼሁና ስለኢህአፓ ያጫወትከን ጥሩ ቀልድ ነው::
እስኪ መቼም ስለመርካቶ ብዙ የምታስታውሳችው ትዝታዎች እንዳሉህ አልጠራጠርምና እባክህ ጊዜ ሲኖርህ አጫውተን!! ይልመድብህ
የመርካቶ ስያ ለጊዜው "መርካቶ ሰፈሬ " የሚለውን የአብዱ ኪያር መስለኝ ስሙ ካልተሳሳትኩኝ! የሱን ዘፈን ላጫውትልህና ቆንጆ ትኩስ ቡና ላቅርብልህ :lol: እሱ ስውዬ ግን እጁን አይደክመውም እንደዛ ሲደንስ????
Monica****
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 3195
Joined: Fri Dec 26, 2003 10:24 pm
Location: 999 Total eclipse st. Venus

Postby Monica**** » Sat Dec 31, 2005 5:57 pm

አቤትትትት ዛሬ ደሞ ይሄ ቤት መጋኛ የመታው መስለ ምነው??? ወይስ ይሄ የፈረንጆች እንቁጣጣሽ ጉዳይ ይሆን ያጠፋችው??? የፈረንጆች እንቁጣጣሽ ነው ብላ ጩኒዬ ታማሪካ ደውላ ነበር......አበስኩ ገበርኩ አለች እትዬ ደብዚ!
አሁን ሁለት ጊዜ እንቁጣጣሽ ምን ይሉታል????
በይ ዘቢደሩ ስኒውን አቀራርቢልኝ, እጣኑንም አጫጭሽ የቡና ሽታ ከሩቅ የጠፉትን ቡና አጣጮቼን ቢያመጣልኝ!
አሁን እማማ እርጎየ ምን ሆንኩ ብለው ነው ሲጠበቁ የውሀ ሽታ የሆኑት???
አይ እሳችው ደሞ ለሁሉ ነገር ለምኑኝ ነው.......በይ እግራችው ላይ ወድቀሽም ቢሆን እማማን አምጭልኝ ጨዋታችውና ምርቃታችው ናፍቆኛል!!!
እማማ እርጎየየየየየየ......ኡ ድምጼ አይስማም መስለኝ
Monica****
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 3195
Joined: Fri Dec 26, 2003 10:24 pm
Location: 999 Total eclipse st. Venus

Postby Debzi » Sat Dec 31, 2005 9:00 pm

አበስኩ ገበርኩ!! እዚህ ቤት ምነው ሰራተኛ ቢቀጥሩ? ይኸው አንድ ሰአት ሆነኝ ቡና ሳይቀርብልኝ:: ምን ልታዘዝ ያለኝ እንኳን የለም:: ኧረንደው የደብዚ ጠጅ ቤት ይግደለኝ!! እዛኮ ሰዉ ገና 'መቀመጫው' ወንበር ሳይነካ ነው አስተናጋጆቹ እንግዳውን የሚያሽሞነሙኑት!! እስቲ ትንሽ ልጠብቅ ባለቤቷ ብቅ እስከሚሉ:: ኦ ኦ ኦ ገባኝ!! ለካ ታሪክ ወይም ጆክ ካላወሩ ሰው አያስተናግዱም:: አፈር በበላሁ! ታዲያ እኔ ጆክም አላውቅ!

እስቲ አስቤበት እመለሳለሁ.....
Ke akbrot selamta gar!!
Debzi
ዋና ውሃ አጠጪ
ዋና ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1918
Joined: Sun May 02, 2004 12:34 am
Location: Los Angeles, CA

PreviousNext

Return to Warka Intimate - ዋርካ ፍቅር

Who is online

Users browsing this forum: Bing [Bot] and 3 guests