Mo's coffee house!!!

The Love Forum (love, relationship) (የኔ ቆንጆ እንተዋወቅ :-)

Postby ባቲ » Sat Dec 31, 2005 9:24 pm

ሞኒካዬ
መነሳት አይገባም, ቁጭ በይ::
በልጅነቴ ብትይ የኔ ልጅነት መርካቶ ውስጥ ነው:: ሁሌ ነግቶ ብቅ ባልሽ ቁጥር መርካቶ አዲስ ነው:- ግርግሩ ጭቃው ቅሚያው ወከባው ዛባው አንከቴው ማሩፍ ያለውና የለለው..........ሁሉም ባንድ ሆኖ ነው መርካቶን ልዩ ያደረጋት:: አንድ የለማኝ ቀብራራ የማውቀው ነበር:: ጠጅቤት እንዳለው የሚነገርለት..... 'በዕለቱ በዋለው ታቦት ስም ይለምንሻል' ካለሽ ነገር ስትሰጪው ካልመሰለው እሱው እራሱ መርጦ አይን የሚገባውን ነው የሚወስደው(ከምትነግጂው ዕቃ):: ሳንቲም ምናምን ፍፁም አይቀበልም:: እምቢ ካልሽ ዕቃሽን አንዱን ከሌላው መለየት እስኪሳንሽ ይቀላቅለዋል:: ጠብ ከመጣ ደግሞ ያራዳው ልጅ በዕንፉቅቅ መንፏቀቁ ይቀርና ብድግ ብሎ ቀጥ ይላል::........ላወራሽ ያሰብኩት ይኽን ሳይሆን አንድ ከበደ ኪሹ ወይም ከቤ የምንለው ነበር, በልጅነቴ ጉድ የሰራኝ:: አለማመኑ ፍፁም ትህትናን የተሞላው ነው:: ሁለት ዕግሮች የሉትም:: የልጅነት ነገር በይው........ብቻ አንድ ቀን እሱ ሲለምን እኔ ከኍላው እንደረዳት የአለማመን ስልቱን እያደነኩ ስከተለው ሳለ ድንገት በቂጡ ሙሉ ለሙሉ ተሽከርክሮ ሁለቱን እግሮቼን ቢመታቸው ዕላዩ ላይ ጠብ አልኩኝ:: እሱና ነገሩን የተመለከቱ በጣም ሳቁ:: ጠረባ ነው ገባሽ? እኔ ግን ለብዙ ቀናት እግሬ የሚቆረጥ የሚቆረጥ እየመሰለኝ በሀሳብ መከራዬን አይቼ ነበር::
ይኽ ሰው የእጅ ፅሁፍ እስካሁን ትዝ ይለኛል:: ማንም እንደሱ የአማርኛ እጅ ፅሁፍ የተዋጣለት ሰው ገጥሞኝ አያውቅም::
መርካቶን ብዙም የማያውቋት በታክሲ ይሻገሯታል:: አንድ ሴትዮ አንገቷ ና እጇን በወርቅ አሸብርቃ መርካቶ ስትጋፋ ያየ አንድ ሰው በሌሊት እየሄዱ ጅብን ነገረኛ ያደርጋሉ አለ:: መስለሽ ከተጠጋሽ በቃ እዚያው ቀረሽ ነው የሚባልው::
ታምሩ የሚባል ዕብድ ነበር ገና ወደማርካቶ ሲግባ በጨርቅ ተራ በኩል ነው መንገዱ.. ቆም ብሎ እጁን ከፍ ያደርግና ' Good morning charq tarra' ሲል ስሙን የማላውቀው ዕብድ ደግሞ የአዲስ ከተማ ተማሪዎች በሚለቀቁበት ሰአት.....ልክ አምባሰል ሙዚቃ ቤት ፊት ለፊት አስፓልቱ ላይ በኖራ ድንጋይ" ZERO MIND.........." ፈልገሽ የምታጪው ምንም የለም......ተራዎችን በተራ በተራ ማዳረስ ብቻ::..............
I love markato

peace out
SaQ _Be _SaQ.....That's what I wish 4 all of Us
ስምየ ውዕቱ ክንዴ ባቲ
ባቲ
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 942
Joined: Tue Jul 06, 2004 8:18 pm
Location: ethiopia

Re: Mo's Coffee House(MCH)

Postby ጭምት » Sun Jan 01, 2006 8:53 am

ጌታ wrote: በትክክለኛው እንግሊዘኛ ከሄድን እኔና አንተ ነን ትክክል:: ቋንቋ ግን አንዳንድ ጊዜ እንዳካባቢው ነዋሪ ስምምነት ስለሚወሰን በዚያ ኅብረተሰብ መሃል እስከኖርን ድረስ ተቀብለን መኖር ነው::


I can't agree more.
ጭምት
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 403
Joined: Sun Jul 31, 2005 7:42 am
Location: ethiopia

እንደምን አደራችሁ?

Postby የመርካቶው ሰያ » Sun Jan 01, 2006 10:03 am

የቡናው ሀራራ/ሱስ/ መሰለኝ በጥዋቱ አዛጋኝ!እስቲ ሞኒካ ጋ ብቅ ብዬ ቡናም ወሬም ይችተተኝ! ባቲ በሳቅ ገደልከኝ
አይ መርካቶ! ላንዱ ሰጥቶ ላንዱ ነስቶ አለ ሎሬት ጸጋዬ

አንድ ጆክ ደግሞ እነሆ::
ትዝ ካላችሁ አንድ ጊዜ "ኢማሌድህ ይጠንክር !!" የሚል መፈከር ነበር:: ይህንን መፈክር የሰሙ የሰፈሬ ሰዎች
ወረ ጉዋድ! ጠንክርስ የኛ ነው ኢማለድህ የማን ነው?
ማለታቸው ይነገራል:: ሲያልፍ ዋዛ አሉ እሜቲቱ ዛሕራ
የመርካቶው ሰያ
ጀማሪ ኮትኳች
ጀማሪ ኮትኳች
 
Posts: 54
Joined: Fri Jan 14, 2005 9:13 am
Location: czech republic

Postby Monica**** » Mon Jan 02, 2006 9:45 am

Debziዬ
ውይ በሞትኩት ቡና ሳትቀምሽ ወጣሽ???? እረ እክሳለሁ አንቺ ብቻ መቼ እንደምትመጭ ንገሪኝ! አዲስ ቡና አፍዪ እቀይራለሁ ያሉኝን አባርሬ!

ባቲ
የመርካቶ ጨዋታ አለፈልኝ አይደል እንዴ?? ባቲዬ በጣም ደስ የሚል ጨዋታ ነው እባክህ ይልመድብህ!!!

የመርካቶ ስያ
በቃ አንተና ባቲ የመርካቶ ጩልሌዎች ናችሁ እስኪ እንዲህ ብቅ እያልክ አጫውተን!

አክባሪያችሁ
ሞኒካ
Monica****
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 3195
Joined: Fri Dec 26, 2003 10:24 pm
Location: 999 Total eclipse st. Venus

Postby Monica**** » Mon Jan 02, 2006 9:58 am

እኔ እምለው ስዎች
አንድ ነርቬን ቁንጥጥ የሚያደርገኝ ነገር እዚህ የምኖርበት አገርና አንዳንድ ይሮፕ ውስጥ በቅርብ ጊዜ የታዘብኩት ነገር mobile phone ring tones በተለይ በተለይ በጣም የሚገርመኝ አልፎ ተርፎም ብስጭት የሚያደርገኝ አይነቱ ...... Crazy frog የሚሉት ነው!!!
መገመሪያ አካባቢ.....I must admit I was very impressed........! የሚያሳፍረው ነገር ግን ሽማግሌውም አሮጊቱም public transports, hospitals እና የመሳስሉ ቦታዎች ding ding ding ding...drrrrrrrrrrr ብሎ ስልካችው ሲደውል ወይ ጉድ ያስብለኛል!!
እሱ አልበቃ ብሏችው በተለያየ መልኩ እያቀረቡ even on the music chart......the crazy frog was number one for a few weeks!! :roll: :roll: :roll:
ምን አስተያየት አላችሁ በአጠቃላይ ስለሞባይል ስልኮች?
እስኪ ቡናውን ፉት እያላችሁ አንዳንድ በሉኝ
Monica****
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 3195
Joined: Fri Dec 26, 2003 10:24 pm
Location: 999 Total eclipse st. Venus

Postby ሜዳ » Mon Jan 02, 2006 9:39 pm

እዚህ ቤቶች አረ ቤቶች ዛሬ ደሞ ማንም የለም እንዴ
ይሄ አመት በአልኮ ወጪ ነው

ቆይ እስኪ ቆይ ቆይ ብድር ምና ምን የለብኝም አደል አዎ ጥግዋ ጋር ብቻ ነው ያለብኝ ቆይ እዚህም ቀስ ብየ ብድር እጀምራለው ወይ አበዳሪ ወይ ተበዳሪ ብሏል -----

እዚህ ቤቶች ጠና ይስጥልኝ


እንደም ነሽ ሞኒካ አመት በአል እንዴት ነው መከራ ኮ ገባን 2 ሁለት አመት በአል እያከበርን

ሞባይል ስትይ ከሰሞኑ ምን ሰማሁ መሰለሽ ለነገሩ ነገር ዘግይቶ ነው ሚደርሰኝ

ቦሌ አሉ እድር,ለቅሶ, ቡና ሲጠራሩ ሜሴጅ በ ሞባይል ነው አሉ ኑ ቡና ጠጡ, እንዴ የኔ ቢጤዎቹ ራሳቸው ሰፈር ላለመበጠበጥ ነው መሰልኝ ይደውሉልሽና ,አሉ ነው, ይደውሉና አሉ ተዘከሩን ነው አሉ ቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅ

እና ቦሌዎች እንዳይሰሙሽ እስቲ በዛ በትልቁ ስኒ ቡናውን ደጋግሚኝ
ሜዳ
አዲስ
አዲስ
 
Posts: 47
Joined: Sun Feb 27, 2005 12:28 am
Location: united states

Postby SUAVE » Tue Jan 03, 2006 7:47 am

ማስታወቂያ

ምርጥ የሀረር, የከፋ, የሲዳሞ ኦርጋኒክ ቡና, በ ሞ ኮፊ ሀውስ በተመጣጣኝ ዋጋ ያገኛሉ:: ቡናዎትን እየተጎነጩ ምርጥ ምርጥ ሀሜቶችንም ከ "ታመኑ ምንጫቸው" አብረው ይኮመኩማሉ:: ለማስታወስ ያክል..... ወ/ሮ ሞኒካ ጥፍት እያሉ ብቅ የሚሉበት ሚስጥር ምንድን ነው?.....የወ/ሮ ደብዚና የወ/ሮ ሞኒካ የንግድ ግንኙነት ምን ይመስላል?.....አቶ ጌታ አገር ቤት ሰሞኑን የሚያሰሩት ፎቅ እውነት በራሳቸው ገንዘብ ነውን?.....አቶ 4ጌት ዚስ "ትንሿ ዋርካ" ብለው በሰየሟት ብሎግ ለአባልነት ማስከፈል ጀምረዋል የሚባለውስ? የወ/ሮ ትህትና 2 የማያልቅ ታሪክ ምንጩ ምንድን ነው?....አቶ ባቲ መርካቶ ውስጥ በምን እንደሚታወቁ ያውቁ ኖሯል?....የመርካቶው ሰያስ ካገር የወጡት ለምን እንደሆነ ሰምተዋል?....አቶ ትምህርት ለምን ጠፉ?.....አቶ ዶማው ቃል የገቡትን የገና ስጦታ በጊዜው ለማድረስ ባይችሉም አሁንም እየተሯሯጡ እንደሆነ ሰምተዋል? ቃል ከተገባሎት ተስፋ አይቁረጡ, ላበሻ ገና ይደርሶታል!......የወ/ሮ ትትናን የፍቅር ታሪክ ያቃሉ?.....የወ/ሮ ምጥኔንስ ሰምተዋል?...አቶ ፓን ሪዚኮ ሰሞኑን የመንግስት ግልበጣ ሴራ ጠንስሰው እንደነበር ያውቃሉ? ውጤቱስ?...የጀኔራል ጃንሜዳ ሚናስ ምን ነበር? አቶ እስጢፋኖስ K ማውራት የማይወዱት ለምን ይመስሎታል? ያቶ ደጉንስ ቀልዶች ምንጫቸውን ሰምተዋል? የወ/ሮ እሌኒን ግጥሞች አስተውለዋልን? መነሻቸው ምንድን ነው? አቶ አእምሮ እውነተኛ የፍቅር ታሪካቸውን ከዘመናት በሁዋላ አሁን መተረክ መጀመራቸው ለምን ይሆን? አቶ ቀብራራው የጠፋችባቸውን የልጅነት ፍቅረኛ አገኙ? መቸ እና እንዴት? የወ/ሮ ሪቾ አወዛጋቢ የፍቅር ታሪክ ምን ይመስላል? አቶ ሜዳ ከፍተኛ ብድር ውስጥ ተዘፍቀዋል ይባላል:: ለምን?!!

ለነዚህና ለሌሎቹም የአእምሮ ረፍት የሚነሱ ጥያቄዎች, ወደ ሞ ኮፊ ሀውስ ብቅ ብለው የማያሻማ "ሙያዊ" ትንታኔ ይሰማሉ!!!
SUAVE
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 475
Joined: Sat Sep 03, 2005 8:42 am
Location: ethiopia

Postby ማይ ገነት » Tue Jan 03, 2006 9:38 am

ይቅርታ ይደረግልኝ በዚ በር ሳልፍ ሳገድም የእጣኑ ሽታ ሳሩ ዘጎዝጉዞ ሰዉ ሲጫወት ሲያሽካካ ስንት ቀን በፍርሀት አለፍኩት
ዛሬስ ይለይልኝ ብዬ ጎራ አልኩ በስማም ልጅ አዋቂው ግጥም ብሎ ሲታይ ደስ ሲል
አስተያየት ለባለቤቲቱ
አስተናጋጆቹ ደንበኛ ይለያሉ ለኔ ቡናው ቅዝቅዝ ካለ በዋላ ነው ያመጡልኝ ግን ቢቀዘቅዝም ጥኡም ቡን የሚያስብል ቡና ነው
ይህን ያክል እግሬን ካስገባው ለሚመጣው ጨዋታ ይዠ እመለሳለው
ይችን ግጥም ግን ባዋቂ አጥፈሽ ግርግዳው ላይ ስቀያት እህት አለም ሞኒካ ለቡና ቤት ተስማሚ ግጥም ናት

ይግቡ ይቀመጡ
የሀሜት ኮፍያዎን እበር ላይ ያስቀምጡ
ስለሰው ያወራሉ
ስለራሶ ምን ያውቃሉ?
ቸር ይመልሰን
loveeeeeeeee
ማይ ገነት
ጀማሪ ኮትኳች
ጀማሪ ኮትኳች
 
Posts: 67
Joined: Sun Dec 11, 2005 10:46 am
Location: ethiopia

Postby ቶም አዋሳ » Tue Jan 03, 2006 1:04 pm

Suave እውነተኛ ቡና ጠጪ አንተን አየው:: ሌላውን ተወው

ና ጥግ ይዘን ጮማ ወሬ እንቁረጥ እስቲ!
ቶም አዋሳ
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 197
Joined: Fri Dec 24, 2004 11:08 am
Location: netherlands

Postby SUAVE » Tue Jan 03, 2006 1:29 pm

ቶምሻ,

ኧረ በል እናውራ! በደረቅ ቡና ኮ ገደሉን! ምን ይወራል ከተማው ውስጥ? ምን ጭምጭምታ አለ? እስኪ ምን ይባላል? እኔ ወሬ ከሚያልፈኝ ምሳ ቢቀርብኝ እመርጣለሁ
SUAVE
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 475
Joined: Sat Sep 03, 2005 8:42 am
Location: ethiopia

Postby Ellenie » Tue Jan 03, 2006 2:44 pm

ሠላም ለሁሉም,

ባቲ በአዲስ አመት እዚህ ምን እያደረክ እንደሆነ ሊገባኝ አልቻለም ኸ! የሰው ነገር.. :oops: ያረረ ቡና ለምን እንደመረጥክ ይገርመኛል ?

SUAVE እንደጻፈው
የወ /ሮ እሌኒን ግጥሞች አስተውለዋልን ? መነሻቸው ምንድን ነው ?

መነሻቸው ምንድነው ትላለህ ?
አንድ ወቅት ግጥሞቼን እንዳልወደድካቸው አይነት ... የሰጠኸው አስተያየት ተቅብዬው ነበር ልበል ?... እናም ከግጥም ይልቅ ስድ ንባብ ቢሆኑ... እንደው ስትል አስታውሳለሁ መሰል... ???
እዚህ ቡና እስከ አራተኛው የሚያንቃርረውስ ምን ይል ይሆን ?
Smile
Ellenie
ውሃ አጠጪ
ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1000
Joined: Wed Jul 27, 2005 4:36 am
Location: ethiopia

Postby ሰምፔር » Tue Jan 03, 2006 5:25 pm

ቤቶች!! ጤና ይስጥልኝ! ከሞኒካ ጀምሮ ደምበኞች በሙሉ መልካም አዲስ አመት ይሁንላቹ! የዚህ ቤት ቡና ጥራትና ጣእም በመላ ከተማው ሲወራ ስምቼ ነው ጎራ ያልኩት እዉነታቸዉን ነው
እስቲ ቡናዬን ፉት እያልኩ ወሬ ጣል አርጉ ስለተባለ እኔን ያሳቀኝ ገጠመኝ እናንተን ያስፈግግ ይሆናል ብዬ ነው

አንድ ጊዜ ዘመዴ ወልዳ ልንጠይቅ ሄድን ከዛ የዘመዴ የ 4አመት ሴት ልጅ አልበም ይዛ መጥታ እየገለጠች ፎቶ ማሳየት ጀመረች:: ከዛ ሁሉንም ፎቶ እኔ ነኝ ስትል ቆየችና አንድ ታላቅ ውንድምዋ ራቁቱን የተነሳዉን ፎቶ እኔ ነን አለች:: ከዛ ታዲያ ይሄ ነገር የታለሽ ስንላት ማሪያምን ነበረኝ ጠፍቶ ነው አለችና አሳቀችን
ሰምፔር
ጀማሪ ኮትኳች
ጀማሪ ኮትኳች
 
Posts: 57
Joined: Mon Jun 20, 2005 3:06 pm
Location: ethiopia

Postby Monica**** » Tue Jan 03, 2006 5:35 pm

Ellenie
ምነው ያገር ልጅ እግርሽ ከመግባቱ ለትችት ቸኮልሽ???
ያረረ ቡና?????
ስው ቤት ሄዶ ስድብማ ነውር ነው! ባይሆን ቡና ይፈላልሽና ከዛ መተቸት ይቻላል....አይመስልሽም?
በነገራችን ላይ እኔ እንክዋን ስራሽን አድናቂ ነኝ.......!
ለነገሩ ከዚህ የከፋም ስድብ ስምቻለሁ አይገርመኝም.......!. አለመምጣትም could be the best option እኮ :wink:
ከአክብሮት ጋር
ሞኒካ

Ellenie wrote:
እዚህ ምን እያደረክ እንደሆነ ሊገባኝ አልቻለም ኸ! የሰው ነገር.. :oops: ያረረ ቡና ለምን እንደመረጥክ ይገርመኛል ?

Last edited by Monica**** on Tue Jan 03, 2006 5:46 pm, edited 1 time in total.
Monica****
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 3195
Joined: Fri Dec 26, 2003 10:24 pm
Location: 999 Total eclipse st. Venus

Postby Monica**** » Tue Jan 03, 2006 5:41 pm

ሌሎቻችሁ በሙሉ ማታ ቤቴ ስገባ አጫውታችህዋለሁ :lol: :lol: የተናደደ ስው ባይ ነው ከስራ ጎራ ያልኩት :wink:
እስከዛ ቡናችሁን እየጠጣችሁ ጠብቁኝ!
Monica****
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 3195
Joined: Fri Dec 26, 2003 10:24 pm
Location: 999 Total eclipse st. Venus

Postby Monica**** » Tue Jan 03, 2006 5:44 pm

:wink:
Monica****
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 3195
Joined: Fri Dec 26, 2003 10:24 pm
Location: 999 Total eclipse st. Venus

PreviousNext

Return to Warka Intimate - ዋርካ ፍቅር

Who is online

Users browsing this forum: Google Adsense [Bot] and 4 guests