ሞኒካዬ
መነሳት አይገባም, ቁጭ በይ::
በልጅነቴ ብትይ የኔ ልጅነት መርካቶ ውስጥ ነው:: ሁሌ ነግቶ ብቅ ባልሽ ቁጥር መርካቶ አዲስ ነው:- ግርግሩ ጭቃው ቅሚያው ወከባው ዛባው አንከቴው ማሩፍ ያለውና የለለው..........ሁሉም ባንድ ሆኖ ነው መርካቶን ልዩ ያደረጋት:: አንድ የለማኝ ቀብራራ የማውቀው ነበር:: ጠጅቤት እንዳለው የሚነገርለት..... 'በዕለቱ በዋለው ታቦት ስም ይለምንሻል' ካለሽ ነገር ስትሰጪው ካልመሰለው እሱው እራሱ መርጦ አይን የሚገባውን ነው የሚወስደው(ከምትነግጂው ዕቃ):: ሳንቲም ምናምን ፍፁም አይቀበልም:: እምቢ ካልሽ ዕቃሽን አንዱን ከሌላው መለየት እስኪሳንሽ ይቀላቅለዋል:: ጠብ ከመጣ ደግሞ ያራዳው ልጅ በዕንፉቅቅ መንፏቀቁ ይቀርና ብድግ ብሎ ቀጥ ይላል::........ላወራሽ ያሰብኩት ይኽን ሳይሆን አንድ ከበደ ኪሹ ወይም ከቤ የምንለው ነበር, በልጅነቴ ጉድ የሰራኝ:: አለማመኑ ፍፁም ትህትናን የተሞላው ነው:: ሁለት ዕግሮች የሉትም:: የልጅነት ነገር በይው........ብቻ አንድ ቀን እሱ ሲለምን እኔ ከኍላው እንደረዳት የአለማመን ስልቱን እያደነኩ ስከተለው ሳለ ድንገት በቂጡ ሙሉ ለሙሉ ተሽከርክሮ ሁለቱን እግሮቼን ቢመታቸው ዕላዩ ላይ ጠብ አልኩኝ:: እሱና ነገሩን የተመለከቱ በጣም ሳቁ:: ጠረባ ነው ገባሽ? እኔ ግን ለብዙ ቀናት እግሬ የሚቆረጥ የሚቆረጥ እየመሰለኝ በሀሳብ መከራዬን አይቼ ነበር::
ይኽ ሰው የእጅ ፅሁፍ እስካሁን ትዝ ይለኛል:: ማንም እንደሱ የአማርኛ እጅ ፅሁፍ የተዋጣለት ሰው ገጥሞኝ አያውቅም::
መርካቶን ብዙም የማያውቋት በታክሲ ይሻገሯታል:: አንድ ሴትዮ አንገቷ ና እጇን በወርቅ አሸብርቃ መርካቶ ስትጋፋ ያየ አንድ ሰው በሌሊት እየሄዱ ጅብን ነገረኛ ያደርጋሉ አለ:: መስለሽ ከተጠጋሽ በቃ እዚያው ቀረሽ ነው የሚባልው::
ታምሩ የሚባል ዕብድ ነበር ገና ወደማርካቶ ሲግባ በጨርቅ ተራ በኩል ነው መንገዱ.. ቆም ብሎ እጁን ከፍ ያደርግና ' Good morning charq tarra' ሲል ስሙን የማላውቀው ዕብድ ደግሞ የአዲስ ከተማ ተማሪዎች በሚለቀቁበት ሰአት.....ልክ አምባሰል ሙዚቃ ቤት ፊት ለፊት አስፓልቱ ላይ በኖራ ድንጋይ" ZERO MIND.........." ፈልገሽ የምታጪው ምንም የለም......ተራዎችን በተራ በተራ ማዳረስ ብቻ::..............
I love markato
peace out