አገባው

The Love Forum (love, relationship) (የኔ ቆንጆ እንተዋወቅ :-)

Postby ወንድም » Fri Sep 01, 2006 8:56 pm

ትትና,ሜሪያንና እድላዊት የኔ ቆንጆዎች በያላቹበት እንደምናላቹልኝ ለማበራታቻ የሞራል ድጋፋቹ በጣም አመሰግናለው አዎ እናት የት ትገኛለች በልቼ ምጠግብ አይመስላትም በጣም እንደምወዳት ያወኩት ከአገር ቤት እንደወጣው ሰሞን ነው ለሊት በእንቅልፍ ልቤ ስምዋን እየጠራው እቃዥ ስለነበር ጉዋደኞቼ ቀን ቀን ይስቁብኝ ነበር ሜሪያን ስለናትሽ ማጣት ከልብ አዝናለው አይዞሽ እግዚአብሔር ካንች ጋር ይሁን
በውሀላ ወደ ታሪኩ እመለሳለው
God bless america and the rest of the world.
ወንድም
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 275
Joined: Thu Jan 13, 2005 3:05 am
Location: united states

Postby እድላዊት » Sat Sep 02, 2006 5:06 am

ሜሪያን wrote:ትትና... እድል... ወንድም... እንዲሁም ለሌሎቻችሁ በሙሉ ልክ ብላችሆል እናትን የመሰለ ማን አለና እኔ እናቴን ካጣሆት 2 አመት ሆነኝ ሁል ግዜ እናቴ በመራብና በመጠማት አለሁት በሰው አገር ላይ እንከራተታለሁ ይህ የዘላለም መጠማት ነው አንዱን ስል አንዱን እያደራረበ የህይወት ጣአምና ሽታው ከኔ ከራቁኝ አመታት ተቆጠሩ አሁን እናንተ ስለእናት ስታወሩ በጣም አስደሰታችሁኝ ባንድ በኩል ደግሞ ቀናሁ ለማለት የምፈልገው በህይወት ያሉትን እናቶችን ከምንም በላይ ከማንም በላይ እነሱን መንከባከብ ሁሉም ሰው አለበት......እስቲ ይሁን

አክባሪ
ሜሪያንሀይ ሜሪ ቆንጆ እንዴት ነሽልኝ

አይዞሽ የኔ ቆንጆ ማንም ስው ቢሆን ወደመጣበት መመለሱ የማይቀር ነው ምን ብንዋደድ ምን ፍቅራችን ቢጸና ይገባኛል የእናት ፍቅር ቀላል አይደለም

ነገር ግን መንፈሳቸው ሁልግዜ ካንቺ ጋር ነው ስጋ ቢሞት እናት መንፈስዋ ከኛ ጋር ነው አንቺ እሳቸውን ሊያስደስት የሚችል ነገር ሁሉ በማድረግ መኖር መቻል ነው የኔ ቆንጆ አንጀቴን ነው የበላሽው ጽሁፍሽን ሳየው ግን አምላክ የወደደውን ይወስዳል

አክባሪሽ እድል

@ወንድም አንተ ተው ተው ቶሎ ቶሎ ጻፈው ቅቅቅቅ
hany
እድላዊት
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 283
Joined: Sat Nov 27, 2004 12:49 pm
Location: united states

Postby ወንድም » Sat Sep 02, 2006 5:07 am

እህቴ ድምጼን ሰምታ ነው መሰለኝ ከጉዋዳ መጥታ ከኛው ጋር ሶፋው ላይ ቁጭ አለችና
""አንተ ሰው ቅድም የሆነች ልጅ ደውላልህ ነበር ማን ነበር ስምዋ እንኩዋን ላስታውስ እ....አዎ ቅድስት የምትባል ልጅ ደውላ ቁጥርዋን ብጠይቃት ግድ የለም ቅድስት አለማየው ደውላ ነበር በይልኝ አለች ነገ ደውላለው አለችኝ''
እናቴ በጥርጣሬ አይን እያየችኝ ''የማን ቅድስት ምትባል ደግሞ አመጣህብኝ ልጄ'' አለች ፊትዋን አቀጭማ.
''እማዬ እኔ ምን አውቃለው እስዋ ደወለች እንጂ እኔ አልደወልኩም'' አልኩኝ እኔም ገርሞኝ ማን እንደሆነች ስላላወኩ
''ተው ባክህ አንተ የዚህን ቤት ቁጥር ባትሰጣት በምን አውቃ ደውላ አንተን ጠየቀች ታድያ. በወግ በማእረግ የአጅሪትን ስም ጠርታ ከስዋ ጋር እንድራሀለን ብለን እቺ ቅድስት ምድስት ምንድነች ታድያ''
አሁን እያመረረች ነው ስትናደድ በአንዴ ነው ግን ቶሎ ትበርዳለች እኔም አንገቴን ደፋው ታድያ ምን ልበል እህቴም እንደወትሮው ልትሸፍንልኝ አልፈለገችም እስዋም ከጎን ሌላ ሴት አልች ብላ አምናለቻ እንደ ማዘር ባይሆንም እስዋም በአዘኔታ አየችኝ
ለደቂቃዎች ቤት ውስጥ ዝምታ ሰፈነ ሁላችንም ወደየአለማችን ሄድን
የሆነ ነገር እንዳስበረገገኝ ነገር ከሶፋው ላይ ተስፈንጥሬ ተነሳውና ወደ ጉዋዳ ገባው የዚን ሰአት ማዘርና እህቴ በግርምታ ይተያዩ ነበር ልጁ ምን ነካው አይነት ነገር ከጉዋዳ ሻንጣየን ከፍቼ ደብዳቤ አውጣው ይድረስ ለቅድስት አለማየው ይላል በረጅሙ ተነፈስኩኝና ተመስገን ብዬ ሄጄ ደብዳቤውን ለማዘር ሰጠዋት.
''አየሽ እማዬ ከአሜሪካ ወንድምዋ ጎረቤቴ ስልሆነ ለእህቴ እሄን ደብዳቤና ሶስት መቶ ዶላር ስጣት ብሎኝ ነበር ነገ ስትደውል የዚህን ቤት አድራሻ ስጫትና አስቀምጭልኝ ካልኩሽ ገንዘብ ላይ ሶስት መቶ ዶላር ከነ ደብዳቤው ስጫት ከዛም ልጁ የሰጠኝን ምልክት ነገርኩዋቸውና ምልክቱን ካልነገረችሽ ገንዘቡን አትስጫት'' አልኩ
''እማዬ እንደ ድሮው ተመልሳ እኔ ደግሞ የማነች ሰላቢ ልጁ የናቱ ጸሎት ተሰምቶለት እቺ የተቀደሰ ነገር ያደርጋል ብል አስናካይ ደሞ በየት መጣች ብዬ አናድደህኝ ነበር አለች በደስታ አነጋገር
ከዛም ማዘር እራት አመጣችልን የጾም ቀን ስለነበር ደስ የሚል የጾም ሽሮ በላን አንድ የናፈቀኝ ነገር የቤቴ ምግብ ስለነበረ በተቻለኝ መጠን ውጭ ላለመብላት እሞክራለው እየተጎራረስን እስከምንጠግብ በላን ከአራት በውሀላ እህቴ ሻይ አፍልታ እየጠጣን ስለ ድሮ ጨዋታ ጀመርን በብዛት ስለዘመዶቻችን ነበር የምናወራው ስለ አንዱ ዘመዳችን እጠይቃቸውና ስልሱይነግሩኝና ወደሌላው ደግሞ እንዘላለን እ እከሊትማ አግብታ እንትናም እንደዚ እያሉ ሲነግሩኝ ጨዋታው በጣም ይጥማል. ከሶፋው ጠረፔዛ ስር መጫወቻ ካርታ አገኘው ሳይታወቀኝ ካርታውን እፐውዘው ነበር.
ይቀጥላል
God bless america and the rest of the world.
ወንድም
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 275
Joined: Thu Jan 13, 2005 3:05 am
Location: united states

Postby ወንድም » Sat Sep 02, 2006 7:01 am

እድላዊት አይዞሽ መጣውልሽ የንጀራ ነገር ስራ የሚሉት ነገር
ሰሞኑን እሄም እንደ ሁለተኛ ስራ ሆኖብኛል part time job ወደ ታሪኩ ልሂድ
እህቴ ካርታውን ይዤ አየችኝና
''ካርታ ትጫወታለህ የምትጫወት ከሆነ ማዘርም ስለምትችል ሁላችንም እንጫወታለን አለችኝ በዚህ ሰአት መዘር ደሞ
''ማዘርም ትችላለች ከመቻልም አልፌ አንቺንና የ አጅሪትን ስም ጠርታ በየጊዜው አይደል እንዴ የምገርፋቹ
እከከ የቀልድዋን እየፎከረች
'' እኔስ ይቅርብኝ ዝም ብለን እናውጋ ስላት የአጅሪትን ስም ጠርታ''
''እስዋም ትጫወታለችኮ''
ስትለኝ በሆዴ አሀ ነው እንዴ another aportunity to know her better
''ምንም እንዳልመሰለኝ
''እሺ ካላቹ እንጫወት''
በሆዴ ግን አጅሪት እስክትመጣ ጉዋጉቻለው
እህቴ ልጥራት ብላ ልትወጣ ስትሄድ ከናቴ ጋር የሆነ አስተያየት ተያዩ ስንተዋወቅ አንተናነቅ ነገር እኔም አየር ለመቀበል እህቴን ተከትዬ ወጣው ነይ ብላት ውጭ ከወጡ በውሀላ
''ወንድምሽ ቤት ገብትዋል?''
''አዎ ምነው?''
''ምንም እኔኮ እማየን አግዛታለው''
''የምን ማገዝ ቁጭ ብለሽ ቲቪ ስታይ አልነበረም ደሞ ወንድሜ ይባላል ይናከሳል!''
''አይ እንደዛ ማለቴ እንኩዋን አይደለም''
''ታድያ ምንድነው ካርታ እንጫወት ነው ያልኩሽ ትራራ እንግፋ አላልኩሽ ባክሽ አንሂድ ብላ በአንገትዋ አቅፋ አመጣቻት
እኔን ጨለማ ስለነበር አላዩኝም በር ጋር ሳይደርሱ ቶሎ ብዬ ገባው
እህቴ አደገኛ ደላላ(pimp) ወጥትዋታል ምን ታድርግ ታድያ ወንድምዋ እንደስዋ ያለጥንድ እንዳይቀር ብላ ይሆናላ
አጅሪት ስትመጣ የሆነ ደስታ ተሰማኝ እኔ ልደብቀው እሞክራለው እሱ ግን ያጋልጠኛል እህቴ ሆነ ብላ የአንድ ሰው መቀመጫ ሶፋ ላይ ሳትቀደም ተቀመጠች አንድ የቀረው ቦታ አጠገቤ ነው እኔ የተቀመጥኩበት ባለ ሁለት ሰው ማስቀመጫ ነው ላቭ ሲት ይሉታል እዚ አማትራ ሌላ ቦታ ስለሌለ ሰላምታ ተለዋውጠን አጠገቤ ተቀመጠች
""ተጠንቀቅ እህትህ ሌባ ነች አብረን እንጠብቃትካርታ ትሰርቃለች አልች በፈገግታ''
'' እረ እቺ ደሞ አንድ ቀን ቸግሮኝ ብሰርቅ ሁሌ እጠረጠራለው'' አለች እህቴም በፈገግታ
'' እኛ የሳውዲ መንግስት አይደለንም ሌባን እጁን አንቆርጠውም ግን አንድ ብርጭቆ ውሀ እናስጠጣለን በዛ እንስማማለን'' ስል
ሁሉም እጅ በማውጣት ተስማሙ
የተሽነፈ እንደ አህያ ልያናፋ እንደ ውሻ ሊጮህ ወይም እንደ አውራ ዶሮ ኩኩሉሉ ልል ተስማማን
መጀመርያ ስትቀመጥ ጭንዋ ከጭኔ እንዳይነካካ በጣም ትጥር ነበር እኔ ቢነካካ ባልጠላው ግን በተልካሻነት እንዳትገምተኝ ሴትዮ እዚያው ነገ ደሞ ምክንያት ፈልጋ እዛው እንደፍጥርጥርህ ብላ ከሀሳቤ እንዳታሰናክለኝ ስለፈራው እግሬን ገጥሜ ነበር የምጫወተው ከግማሽ ሳአት በውሀላ አካባቢ ግን ዘና ማለት ጀመረች እየተቀላለድን እየተሳሳቅን እንጫወት ስለነበር
ሆነ ብዬ እሽነፍላቸው ነበርና አጅሪት እንደ አውራ ዶሮ ጩህልን ትለኛለች እቆምና እጄን አጥፌ በታጠፈው እጄ እንደ ዶሮ ሽንጤን መታና ሆነ ብዬ በሚያስቅ ሁኔታ ኩኩሉሉ ስል በተለይ አጅሪት በሳቅ ትሞታለች እስዋን ደስ ሲላት እኔም ደስ አለኝ አልፎ አልፎ ያ ቆንጆ ባትዋና ጭንዋ እየነኩኝ ይፈታተኑኝ ነበር
God bless america and the rest of the world.
ወንድም
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 275
Joined: Thu Jan 13, 2005 3:05 am
Location: united states

Postby ሜዳ » Sat Sep 02, 2006 5:25 pm

ሰላም ወንደም

አሪፍ ታሪክ ነው እኔም እንደነእደል እየተከታተልኩት ነው

ቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅ አቦ ይመችህ በሳቅ ገደልከኝ እንደ ዶሮ ሰትል ቅቅቅቅቅቅቅቅቅ

በባሌም በቦሌም ብለህ ዋናው አጅሪትን ነው
ምን እንተን ይባል የለ "የትም ፍጭው ዱቄቱን አምጭው ቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅ ዋናው

በል አሪፍ ነው አታጉዋግዋን እዚህ ቤት ደሞ አሪክ ይጀመራል ግን አያልቅም አንተም እንዳይጋባብህ

አክባሪህ
ሜዳ
አዲስ
አዲስ
 
Posts: 47
Joined: Sun Feb 27, 2005 12:28 am
Location: united states

Postby ወንድም » Sat Sep 02, 2006 9:14 pm

ሜዳ ወንድ ነህ ብዬ ገምታለው አንተ ልበልህ እንጂ እንዳልከው የትም የትም ፍጪው .... ለመጀመርያ ጊዜ እንደዚህ አይነት ረጅም ታሪክ ስጽፍ እኔ ራሴ ገርሞኛል እንደዚ ችሎታ እንዳለኝ ባውቅ ችስታው ደራሲ እሆን ነበር ታውቃለህ ብዙ ደራሲዎች ምንም የላቸውም በተለይ ያገራችን አያሳዝኑም ብዙ ሚያነብ ስለሌለ ነውኮ በዛ ላይ ደሞ ውና አትራፊዎች አሳታሚዎች ናቸው ከላይ እንዳልኩት ታሪኩ እውነት ሆኖ ትንሽ ግን ለማጣፈጫ ቅመም ጨማምሬበታለው based on true story
መጣው
God bless america and the rest of the world.
ወንድም
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 275
Joined: Thu Jan 13, 2005 3:05 am
Location: united states

Postby ወንድም » Sat Sep 02, 2006 9:55 pm

አግሬ ገእግርዋ ጋር ሲነካካ እንደ ኤሌክርሪክም መንዘርም ያደርገኛል ወይ ጣጣ እላለው አጅሪት የቀልድ አይደለሽም አታውቂውም እንጂ በጣም ሀያል ነሽ እኔን እያንበረከክሽ ነው. እንኩዋንም ከጫማሽ ስር እንዳስገባሽኝ አላወቅሽ እኔ ያላንቺ ዋጋ የለኝም አልሚዬ ነሽ በየቀኑ ማለዳ ገጎንሽ ከእንቅልፌ ስንቃ እንዴት ያምር ይሆን አያቴ ድሮ ጥሩ ሚስትና ጥሩ ባል የት ይገኛል ጥሩ ሚስት እግርህ እስኪነቃ ዞረህም አታገኛትም ያለው ዛሬ ለኔ ገሀድ እየሆነልኝ ነው
''ጣል እንጂ ያንተ ተራ ነውኮ ምነው ዝም አልክ'' አለችኝ አይን አይኔን እያየች
የምፈዘው በስዋ እንደሆነ ማን በነገራት
አሁን እህቴ ተሽነፈች እንደ አህያ አናፊ አልናት እህቴም እንደ አህያ አይሉት እንደ ጅብ ጮህች ከምር አሳቀችን በተለይ አጅሪት ካካካካካ እያለች ሳታስበው ወደኔ ፊትዋን አዙራ ጡትዋ ደረቴን ነካው ያ እንደ ብርትኩዋን ጠጠር ብሎ ቁጭ ቁጭ ያለው ጡትዋ የነካኝ ከሰከንድ ያነሰ ቢሆንም ለቀናቶች ትዝታ የሚሰጥ ነበር
ይቀጥላል
God bless america and the rest of the world.
ወንድም
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 275
Joined: Thu Jan 13, 2005 3:05 am
Location: united states

ዋውውውውውውውው....

Postby zizu » Sat Sep 02, 2006 11:50 pm

ዋውው ወንድም በጣም አሪፍ ታሪክ አጓጊ እኔ መጨረሻውን ናፍቂያለሁ ከምር ቶሎ ቶሎ ጻፈው እንጂ
zizu
ጀማሪ ኮትኳች
ጀማሪ ኮትኳች
 
Posts: 98
Joined: Sat Aug 21, 2004 7:46 am
Location: saudi arabia

Postby ወንድም » Sat Sep 02, 2006 11:57 pm

ማዘር እንቅልፍዋ መጣ መሰለኝ ደጋግማ ካዛጋች ብውሀላ
''እኔ ልተኛ እናንተ ተጫወቱ'' ብላን ልትተኛ ሄደች
እኛም ካርታው ሰለቸን ምሰለኝ መጫወቱን አቆምንና ወሬ ጀመርን
''አጅሪት እየለመድክ'' ነው አለች
''አዎ ደህና እየለመድኩኝ ነው
''አንቺስ እየለመድሽ ነው'' አልኩዋት
''ምኑን ነው የምለምደው ድሞ''
''አገሩን ነዋ ሌላ ምኑን
''የትኛውን አገር''
''እሄን አገር ሆ......'' ብላ አንገትዋን ከትካሻዋ እንደሆነ ነገር ነቀነቅችውና
''አታሹፍ ባክህ ከመልመድም አልፎ አስለምዳሀለው
ኦኦ ቀልድ አበዛው መሰለኝ ደሞ እሄ ቁም ነገር የሌለው ፌዘኛ ነው እንዳትል ፈርቼ
''አይ ስቀልድሽ ነው አንቺ ደግሞ ቀልድ አታውቂም እንዴ ስል''
''እኔ ምን ላርግ ብለህ ነው ባለውበት አገር ለመድሽ ወይ ስትለኝ''
እህቴም ተቀብላ ''አየሽ እነዚ ከዛ ከደግ አገር ብሉልኝ ጠጡልኝ ከሚባልበት አገር እየመጡ የኛን ቁስል ይነካሉ አይገርምሽም''
እህቴ ለምን እንደዛ እንዳለች ገብቶኛል ባገኘችው አጋጣሚ ተጠቅማ አጅሪትን አጉዋጉታ እያሻሻጠቻት ነው ሌባ የኔ ሌባ ተባረኪ ድሮስ የኔው አይደለሽም አልኩኝ በሆዴ እህቴን
እመለሳለው
God bless america and the rest of the world.
ወንድም
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 275
Joined: Thu Jan 13, 2005 3:05 am
Location: united states

Postby ወንድም » Sun Sep 03, 2006 10:56 am

''እዛ እንደዚህ አበሾች ለመገናኘት እድል አላቹ''አጅሪት አንዳንዴ ስትናገር እንደ ህንዶች ጭንቅላትዋን ትነቀንቀዋለች ''አዎ እንደዚህ ባዮሆንም አልፎ አልፎ መገናኘታችን አይቀርም በተለይ እኔ ያበሻ ነገር ስለማይሆንልኝ የግድ እነሱን ፍለጋ ሄዳለው
''ፈረንጆቹስ ይደብሩሀል''
''መደበርስ አይደብሩኝም ምን መሰለሽ እኔ ሙዴ ከነሱ ጋር አይገጥምም በብዛት ስራ ቦታ ላይ እነሱ ናቸው ግን እንከባበራለን በነገራችን ላይ እኛ አሜሪካ ፈረንጅ አንላቸውም ነጭ ነው የምንላቸው አዲስ የመጣ አበሻ ነው እስኪለምድ ፈረንጅ ፈረንጅ እያለ ልባችንን የሚያደርቀው''
''ጓደኛ አለህ?''
''አሉኝ ሶስት አራት የሚሆኑ''ብዬ ዝም ካልኩ በውሀላ የአጅሪት አማርኛዋ ገባኝ
''ጥያቄሽ የሴት ጓደኛ ከሆነ የሴት ጓደኛ የለኝም''
''እረ እኔ አልወጣኝም ''
ያን ካልኩዋት በውሀላ ፊትዋ ላይ እርካታ ያየውባት መሰለኝ. ስትናገር ደስ ትለኛለች ለዚች ልጅ ያለኝ መውደድ በየ ጊዜው እየጨመረ ነው ልበል የኔን ሁኔታ የማያውቅ አጃጅላዋለች ይላል አትፍረዱ ይፈረድባችዋል ነው
ሰአቱ እየሄደ ስለነበር ተንስታ መሽኮ ልሂድ አለች
''አትቆዪም ለምን አትጫወቺም'' አለቻት
''አይ ልሂድ ጠዋት ተነሺ ነኝ ደህና እደሩ ብላን ከበሩ ልትወጣ ስትል እህቴ ቃል ሳታወጣ ክንፈርዋን በማነቃነቅ ብቻ ''ሂድ ተከተላት!'' ብላ ወደ አጅሪት በእጅዋ አመለከተች አጅሪት ፊትዋ ወደ በሩ አዙራ ስለነበር አላየቻትም
እውነትሽን ነውኮ ብዬ ከበሩ እንደወጣች ደረስኩባትና ""ልሽኝሽ'' ስላት
''እዚው ሰፈር ነው የምኖረውኮ ምን ሸኚ አስፈለገኝ ብለህ ነው''እይሄደች ነው የምታወራው
''አይ ቢሆንም ቆጥሮ የተረከበ ቆጥሮ ማስረከብ አለበት''
''ስለዚህ አንተም ለቤተሰቦቼ እሄው ተረከቡኝ ልትላቸው ነው''
''ታድያ እሄው ልጃችሁን ብዬ ደረሰኝ እጠይቃለው እንዳውም''
ኪርኪር ብላ ከሆድዋ ሳቀችና
''ደረሰኝ እጠይቃለው ነው ያልከው አባቴ ይሙት አንተ ልጅ ግን በጣም ሲበዛ ቀልደኛ ተጫዋች ነህ''ስትለኝ
ቤትዋ አጥር በራፍ ላይ ደርሰን ነበርና ቆምን
እኔም የቀኝ እጅዋን በሁለት እጄ አንስቼ የእጅዋን መዳፍ ጀርባ ሳምኩትና እጅዋን እንደያዝኩኝ
''አንቺ ደሞ የቆንጆዎች ቆንጆ ነሽ ከጸባይ ጸባይ ከመልክ መልክ ያደለሽ እንከን የማይወጣልሽ ጽጌረዳ አበባ ነሽ
ይቀጥላል
God bless america and the rest of the world.
ወንድም
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 275
Joined: Thu Jan 13, 2005 3:05 am
Location: united states

Postby ወንድም » Sun Sep 03, 2006 1:47 pm

''ተው እንጂ''
''ለምን እተዋለው እውነቴን ነውኮ እንደምወድሽ ሳይገባሽ አይቀርም አንቺን ከመውደድም አልፎ በጣም አፈቅርሻለው ድሮ ፍቅር ፍቅር ሲሉ አይገባኝም ነበር. ያለፈው ከመጣው ጀምሮ ልቤ ውስጥ ሰርጸሽ ገብተሽ ከልቤ ላስወጣሽ አልቻልኩም በተለይ አሁንማ በደንብ በተረዳውሽ መጠን ላንቺ ያለኝ ፍቅር እያየለ መጣ ማንንም ሴት አፍቅሬ አላውቅም እባክሽ ነብሴ ፍቅሬን ተረጅልኝ''
ከአይንዋ ከየት መጣ ሳይባል ዘለላ እንባዎች ዱብ ዱብ አሉ
''የኔ ፍቅር አታልቅሺ እኔ ላስለቅስሽ ፈልጌ አይደለምኮ''
ብዬ በሁለት አውራ ጣቴ እንባዋን ከያንዳንዱ አይንዋ ጠራረኩላት እኔም እንባዬ መጥትዋል ጠንካራ መሆን ስለነበረብኝ ችየዋለው
ሳላስበው ከንፈርዋ ከከንፈሬ ጋር ተገናኘ እንደ ማግኔት ስበት መሆን አለበት እንጂ ለዛሬ አላሰብኩትም ነበር የአጥራቸው በራፍ ላይ የተሰቀለችው አንፖል የሚያይ ሰው ቢኖር ወለል ብሎ ባሳየው እኛ ጉዳያችንም አልነበረም ለትንሽ ጊዜም ቢሆን በከንፈር ተጣብቀን ወደ ሌላ አለም ሄደን ነበር ወደ ቆንጆ ፍቅር አለም ምን ያደርጋል ተመልሰን መጣን አሁን ሳያት ቁና ቁና ትተነፍሳለች እቅፍ አድርጌ ስይዛት አስዋም አቀፈችኝና ከተላቀቅንና
''ደህና እደሪ ማሬ ብዬ ጉንጭዋን ስሜ ግቢ አስገባሁዋት የቤታቸውን በር በር ከፍታ እስክትገባ ድረስ በአይኔ እከተላት ነበር ቤትዋ ገብታ በሩን ከውስጥ ከመዝጋትዋ በፊት እጅዋን አውለብልባ ቻው ስትለኝ እኔም አጸፋውን መለስኩላት
ወደቤት ስመለስ እኔ ወንዱ ጀግናው የቆንጆዋን ቆንጆ ልብ ያሙዋማው ምን ይሳነኛል እንደኔ እድለኛ ውንድ አለም ላይ የለም እያልኩ በሆዴ ለራሴው ጉራ ነዛለው ፊቴ ሁሉ ጥርስ ነበር ከሂደቱ አንዱ ክፍል እንደተጠናቀቀ ሳስበው ረካው
God bless america and the rest of the world.
ወንድም
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 275
Joined: Thu Jan 13, 2005 3:05 am
Location: united states

Postby እድላዊት » Mon Sep 04, 2006 8:03 am

ሰላም ላንተ ይሁን ወንድም

ሰሞኑን በቃ እንደጻፍክ ቢገባኝም ጥርቅም ሲል ላንበው ብዬ አስችሎኝ ትንሽ ከበፊቱ ጠርቀም ያለ ስላነበብኩ ደስ ብሎኛል
የውነት አሁን ደሞ የበለጠ ልቤን ጥልጥል አረካት የባሰ ደሞ ልብ ጢል የሚያረገው ርእሱ ነው አገባው ስለሚል በቃ ብዙ ጠብቃለው ብቻ እስቲ ግዜ ይስጥህ እና ቀጥልልን አቦ
ቤተሰባቹ ግን ደስ ሲል ስትተርከው በፍቅር የተሞላ እንደሆነ አተራረክህ ይገልጸዋል

አክባሪህ እድል
hany
እድላዊት
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 283
Joined: Sat Nov 27, 2004 12:49 pm
Location: united states

Postby ወንድም » Mon Sep 04, 2006 10:26 am

zizu ለጥሩ ለአስተያየትህ ከልብ አመሰግናለው

እድል ሰሞኑን ብዙ የጻፍኩት የቅዳሜና እሁድ እረፍት ስለነበረኝ ነው አንቺ ተዝናንተሽ አንብቢ እኔ ደግሞ ያለኝን ጌዜ ሰውቼ ተጨንቄ እጽፋለው የምር ግን ሰዉ ስራዬ ብሎ የኔን ጽሁፍ ሲከታተል በጣም ደስ አለኝ ገረመኝም
God bless america and the rest of the world.
ወንድም
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 275
Joined: Thu Jan 13, 2005 3:05 am
Location: united states

Postby ቆንጂዬው » Mon Sep 04, 2006 11:22 am

አይ ወንድም እሺ ባክህ እኔን ራሴን እንደጉድ አመላለስከኝ :D :D ቀጥል በናትህ ከዛስ?
God is Good, all the time.
ቆንጂዬው
አዲስ
አዲስ
 
Posts: 23
Joined: Tue Aug 15, 2006 6:33 pm
Location: Halifax

Postby ወንድም » Mon Sep 04, 2006 11:54 am

ካገር ቤትከወጣው ጀምሮ ያላገኘውት የድሮ የትምርት ቤት ጓደኛዬ የት እንደሚሰራ ነገሩኝ ሲመቸኝ በታክሲ ሚኒ ባስ ከለገሀር ወደ ንፋስ ስልክ ተሳፈርኩኝ ታክሲው መነሻው ለገሀር ስለነበር ቆሞ ወያላው ታክሲ ውስጥ ሁለት ሰው ብቻ ቢሆንም ''የሞላ የሞላ ጎተራ ንፋስ ስልክ የቸኮለ የቸኮለ'' እያለ ላንቃው እስኪሰነጥቅ ደጋግሞ ይጮሀል.
ለገሀር አካባቢ ሰዎች በጣም ይርመሰመሳል አንዳንዶቹ ከጥግ እግር መሄጃ ምንገድ ወርደው በመኪና መሄጃ የሚሄዱም አልታጡም ሊስትሮው ማስቲካ ቆሎ ሶፍት ሲጋራ የተለያዩ ነገሮች አዝዋሪዎች ቁጥር የላቸውም ሁሉም የለት ጉርሳቸውን ለመዝጋት በሚያደርጉት ጥረት በጣም አደነኳቸው.
ታክሲዋ እንደምንም ሞላችና ጉዞ ጀመርን ወያላው ማስከፈል ጀመረ ቢበዛ የአስራ አራት አመት የሚሆን ታዳጊ ወጣት ነገር ነው.
እጁ ላይ ያለውን ሳንቲም እያንጫጫ
''ሂሳብ ሂሳብ''
ከፊለፊት ጀምሮ ወደሁዋላ ማስከፈል ጀመረ
''አባት ፈጠን ይበሉ እንጂ''ገና ኪሳቸውን ለሚበረብሩ ሽማግሌ ሳንቲሙን ፊታቸው ላይ እያንጫጫ
''ሲገቡ ጋሼ በላቸው ሲወርዱ ቼላ ተቀበላቸው ሲባል አልሰሙም እንዴ''
''አትተርትብኝ! ያ ውልህ ዮሴፍ ነው የምወርደው ብለው ሂሳቡን ሰጡት
መንገድ ተዘግቶበት ይሁን እንጃ ታክሲው በጣም ቀስ እያለ መሄድ ጀመረ አንዱ ከወደሁዋላ
''እኛ የተሳፈርነው ልንተኛ ሳይሆን ወደፈለግንበት ልንጉዋዝ ነው'' አለ ሌሎችን ተሳፋሪዎች እያየ ለድጋፍ
''እኛ ደሞ መኪናችን ለሌላም ጊዜ ስለሚያስፈልገን ሾፌር ቀስ ብለህ ንዳ ወያላውም ወደ ቅድሙ ሰውዬ እያየ ለአጸፋው.
ከጎኔ የተቀመጠችው አንድ በጣም ቀጭን ነገረኛ ቢጤ
ነገር ስታሙዋሙቅ
''እንዴ ምን ለማለት ፈልገህ ነው መኪናችን የምትለው የኛስ ህይወት''
በዚህ ሰአት ያችን ነገረኛ ሴትዮ ተከትለው ወያላው ላይ ውርዥብኝ
እኔ ለራሴ እዚህ ነገር ላይ መግባት አለብኝ ብዬ
''እዛ ከውሀላ ቁጭ ያለው ስውዬ መኪናውን እንዲያጋጨው ወይም እንዲገለብጠው ቀጥታ ትእዛዝ ለሾፌሩ ሲሰጥ የዛኔ ተው ህይወታችንን እንፈልጋለን በሚያውቀው መንገድ በተመቸው ይንዳ ማለት ነበረብሽ አልኩዋት ድምጼን ከፍ አድርጌ
ከውሀላ የነበረው ሰውዬ ''መቸ ነው አንተ አጋጨው ገልብጠው ያልኩት ለመሆኑ ምንነቴን ታውቃለህ'' ብሎ አፈጠጠብኝ.
አናዶኝ ስለነበር እስከ አፍንጫው ላስታጥቀው ብዬ ዞር ብዬ አተኩሬ አየሁትና አንተማ ኪስ አውላቂው ተድላ አይደለህም?''
አንተስ ከትምርትቤት መልስ ጠብቀህ ህጻናቶችን የምሳ ገንዘብ የምትዘርፈው ብሎ ስሜን ጠርቶ አይደለህም?''
ይቀጥላል
God bless america and the rest of the world.
ወንድም
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 275
Joined: Thu Jan 13, 2005 3:05 am
Location: united states

PreviousNext

Return to Warka Intimate - ዋርካ ፍቅር

Who is online

Users browsing this forum: Google Adsense [Bot] and 3 guests