አገባው

The Love Forum (love, relationship) (የኔ ቆንጆ እንተዋወቅ :-)

Postby ገላጋይ-1 » Mon Sep 04, 2006 12:26 pm

ወንድም
መልካም ትዳር እመኝልሀለሁ........ነገር ግን ብዙም አፈቀርኩሽ ሞትኩልሽ አትበላት.........የሀበሻን ሴት ናቅ ስታደርጋት ነው የምትወድህ.....ብትወዳት እንኩአን አትንገራት....እነሱ የሚወዱት ሲገባ ሲወጣ የሚረግጣቸውን ነው
ገላጋይ-1
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 500
Joined: Fri Aug 25, 2006 5:43 pm

Postby Debzi » Mon Sep 04, 2006 5:32 pm

እኔም በጥሞና እየተከታተልኩት ነበር ምንም እንኳን የዋርካ ትረካ ማንበብ ካቆምኩ ብቆይም:: ሰው ታሪክ ጀምሮ ልብ አንጠልጥሎ ጥፍት ስለሚል ትንሽዬ ልብዬ እንዳትንጠለጠልብኝ ብዬ አልጀምርም:: አንዳንዶቹ ደሞ ጀምረው በጥሞና ይቀጥሉበታል ታዲያ እኔ አይ መቋረጡ አይቀርም ብዬ ትቸው አስራ ምናምን ገጽ ይደርሳሉ ከዛ በሰንፍና ተወዋለሁ:: ምንድነው እምለፈልፈው?? ባጭሩ የሚያዝናና ነው ለማለት ፈልጌ ነው::

አመሰግናለሁ
Ke akbrot selamta gar!!
Debzi
ዋና ውሃ አጠጪ
ዋና ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1918
Joined: Sun May 02, 2004 12:34 am
Location: Los Angeles, CA

Postby ወንድም » Tue Sep 05, 2006 5:12 am

ቆንጅየው ከዛማ እየቀጠለ ነው የአጅሪት ነገር መቸ ያልቅና

ገላጋይ አትሳሳት ሴቶች ሲወጣ ሲገባ የሚደበድባቸውን አይወዱም አንተም ብትሆን ከደበደብካት ትጠላታለህ ማለት ነው ከምትጠላት ሴት ጋር ምን ታደርጋለህ አተካራ አልፈልግም ባክህ ተወኝ

ደብዚ ተሙዋሙቼም ቢሆን ጨርሳታለው በዛ አትጠራጠሪ ስላዝናናሽ ደስ ብሎኛል የምትለፈልፊውኮ ያንቺ ጠጅ ቤት መስሎሽ ነው just kidding
God bless america and the rest of the world.
ወንድም
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 275
Joined: Thu Jan 13, 2005 3:05 am
Location: united states

Postby እድላዊት » Tue Sep 05, 2006 6:44 am

እኔም እንደደብዚ እስኪጠራቀም ድርሽ አልልም

በቃ እንዴ ልቤ በፍቅር እስከመቃብር እንኩዋን ያን ያህል አልተንጠለጠለም እኮ

አክባሪያቹ እድል
hany
እድላዊት
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 283
Joined: Sat Nov 27, 2004 12:49 pm
Location: united states

Postby ትትና » Tue Sep 05, 2006 8:27 am

:D :D አይ ወንድም! አደገኛ ነህ ግን ልሸኝ ብለህ ወጥተህ? ሆ! እስቲ ይሁን!

አንተ ገላጋይ! ስምህና የተናገርከው በጣም አይሄዱም:: ቆይ እንዴት ነው ሰው ገላጋይ ተብሎ ስለጸብ የሚያወራው:: አደራ ስራህ እንደ ስምህ ይሁን!

ወንድም እጅህ ይባረክ ብያለሁ!
ትትና
ውሃ አጠጪ
ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1253
Joined: Wed Feb 23, 2005 11:26 am
Location: united states

Postby ገላጋይ-1 » Tue Sep 05, 2006 12:54 pm

ወንድም

ፈዛዛ አትሁን እኔ ምክሬን ነው የሰጠሁህ ለሀበሻ ሴት ክብር አትስጥ ራስህ ላይ ትወጣለች እነሱን ንቀህ ስትረሳቸው ነው የሚከተሉህ አንዳንደም በጥፊ ብትመታት ደስ ይላታል የበለጠ ትወድሀለች......የሀበሻ ሴት የሚያከበራትን ሴት አትወድም


ትትና

ደህና ነሽ ግን ?
ገላጋይ-1
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 500
Joined: Fri Aug 25, 2006 5:43 pm

Postby ወንድም » Tue Sep 05, 2006 5:40 pm

እድል ፍቅር እስከመቃብር አራቴ ያህል እንዳነበብኩት ከዛ ማታ ማታ አሪፉን ክፍል ነካ ነካ አደርገው ነበር ማለትም እንደ ዳዊት ደግመው ነበር
ትትና ልሸኝ ብለህ ወጥተህ ትላለች አውሎ ንፋስ ወይም ሱናሜ ይታገዳል እንደዛ ነውኮ ሆኖብኝ የነበረው
ገላጋይ አይዞህ በሌላ አርእስት ስለ ቦክስና ጥፊ እንማማራለን i am a lover boy not a heater
ይቀጥላል


''ሹፌር ታክሲውን አቁመው እንደ አመሌ ጥርስ ማውለቅ አምሮኛል!!'' ሲል
''እኔም ሰው መዘረር ናፍቄያለው ጥዬ ሱሪዬን አሳየዋለው እንዲ መደፋፈር አቁም አንተ!!''
መኪናው ውስጥ የነበሩ ሰዎች ጉድ ይላሉ አንድዋ አሮጊት ከውሀላዬ ''እረ ባካቹ ጎበዝ ዝም ትላላቹ ሊጨራረሱ ነውኮ ወደ ወንዶች ተሳፋሪዎች እያማተሩ የትኛው ወንድ ነው እኛን የሚያገላግለው ሁሉም ፈርተዋል
ታክሲዋ ቆመች እኔ መጀመርያ ዘልዬ ወረድኩና ቦክስ ጨብጬ ስጠብቀው ተድላም ወረደና ዛሬ ወይ እኔ ወይ አንተ ብሎ እሱም ቦክስ ጨብጦ በጥላቻ መተያየት ከዛ ሁለታችንም ሳቅ በሳቅ በውሀላ የብዙ አመት ናፍቆታችንን ተቃቀፍን ሹፌሩ ''ከአማንኤል ነው ያመለጣቹት'' ብሎ ጎማውን አስጭሶ ተፈተለከ
ተድላና እኔ ሽመልስ ህብቴ ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት ከዘጠነኛ እስከ አስራ ሁለተኛ አብረን ነው የጨረስነው እሱ ረባሽ ተንኮለኛ ለፍላፊ ሆኖ ጭንቅላቱ ብሩህ ስለሆነ ከክፍሉ ከአንድ እስከ ሶስት ወርዶ አያቅም ማትሪክም ተፈትነን እሱ በድግሪ አልፎ አዲስ አበባ ዩንፈርስቲ ሲገባ እኔ ቀሽሙ ወደ ሱዳን አቀናው
ዛሬ እሱን ፍለጋ እየሄድኩኝ ነው እሱም ወደ ስራው ስሄድ የተገናኘነው
ድሮ ሳንከፍል አውቶብስ ውስጥ እንገባና ትኬት ተቆጣጣሪው ሲደርስብን እንደዛሬው እንደምንጣላ ስንሆን እሱም አውቶብሱን አስቁሞ ከፈለጋቹ ወርዳቹ ተጣሉ ይሉን ነበር
በደንብ ሰላምታ ተለዋወጥንና የበለጠ እንድንጫወት ፊት ለፊት ወደ ነበረችው ቡና ቤት ገብተን ቢራ ቢራችን ያዝን ውስኪ ጠጣ ብለው በጠላት ገንዝብ ነው ውስኪ ምጠጣው ያንተ ኪስና የኔ ፊት እንዲጠራ አልፈልግም አለኝ.
'' የከተማውን ቆንጅየዎችን እንዴት አየሀቸው'' ሲለኝ
''በአይነ ቁራኛ'' አልኩት
ተጠንቀቅ የዚ አገር ሴቶች በክትፎ ላይ ክትፎ በኬክ ላይ ኬክ አዘው አንጎል ነው የሚያረጉህ.ሁለተኛ አመት ችስታ የዩንፈርስቲ ተማሪ እያለው አንድዋን ለአፌ ልጋብዝሽ ብላት እስዋ ድመት ይመስል ወተት አታዝም መሰለህ እኔ ያለኝ ገንዘብ ለሁለት ሻይ አስተናጋጁ ላንተስ ሲለኝ ለኔ ንጹህ ውህ ልክ እንደምትከፍል ለምን ሌላ ነገር አታዝም አትለኝ መሰለሕ መድሀኒት እየወስድኩኝ ነው አልኩዋት''
ብሎ አሳቀኝ ብልጥ መለኛ ነው
'' የመስርያ ቤትህ የሂሳብ ክፍል ሀላፊ ነህ ሰማው ጎበዝ ነህኮ አንተ''
''ተው ባክህ የአመቱ ኮከብ ሰራተኛ ብለው ምን እንደሸለሙኝ ታውቃለህ የምስክር ወረቀትና በሚያምር ወረቀት የተጠቀለለ ትልቅ ድፎ ዳቦ ይቀልዱብናል ያሉት ሳትወድ በግድህ ያልፈለከውን ጉቦ እንድትበላ ይገፋፉሀል
ስለኔም የመጣሁበትን ጉዳይ ነገርኩትና በጣም እርግጠኛ እንድሆን መከረሮኝ ስልክ ቁጥር ተቀያይረን እሱ ወደስራው እኔ መርካቶ አመራው የሆነ እቃ ልገዛ.
God bless america and the rest of the world.
ወንድም
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 275
Joined: Thu Jan 13, 2005 3:05 am
Location: united states

Postby ሜሪያን » Tue Sep 05, 2006 8:37 pm

ውድ ወንድም በጣም ልብ የሚሰቅል ነው በጣም በርታ እኔም እንደሌሎቹ በርከት ሲል ነው የማነበው ስል አያስችለኝም ለማንኛውም በተገኘው አጋጣሚ ጣል ጣል አድርግልን በተረፈ ያንዳንድ እብድ ሰው ምክር አትስማ ክብር አትስጥ እያለ የሚመክርህን አትስማ እሱ እዛው ያስለመዳቸውን ይጠፍጥፍ መስሎት ነው ወይ ሲሉ ሰምቶ ለማንኛውም እጅህን ይባርክልን አሜን

እድልዬ ስለ ጣፍሽልኝ ማጥናናት አመሰግናለሁ ተባረኪ
ሜሪያን
ጀማሪ ኮትኳች
ጀማሪ ኮትኳች
 
Posts: 68
Joined: Thu Jun 29, 2006 6:09 pm
Location: ethiopia

Postby ndave » Wed Sep 06, 2006 5:25 am

አገባሁኝ ብለህ ስላልክ መልካም እድል ሳይሆን መልካም የትዳር ዘመን ይሆንልህ ዘንድ የልብ ምኞቴ ነው :: በዚህች አጋጣሚ የአመቱ ኮከብ ሰራተኛ በድፎ ዳቦ ከምር አስቀከኛል :: ቆንጆ ነው እስካሁን በርታ ::
ndave
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 256
Joined: Mon Sep 22, 2003 10:29 am

Postby ወንድም » Wed Sep 06, 2006 6:40 am

ሜሪያን ልብሽን ሰቀልኩት አይዞሽ አወርደዋለው ያንተ እጅ ይባረክ እንዳልሽኝ ያንችም ይባረክ ዳይመንድና ወርቅ ይሙላው


አልፎ አልፎ እህቴ የከፈተችው ጸጉር ቤት ውላለው ሲደብረኝም አጠገቡ ካለው ኬክ ቤት ሄዳለው.ጸጉር ቤቱ አዲስ ስለሆነ ነው መሰለኝ ለወረት ብዙ ደንበኛ አላቸው ባለ ትዳሮች ያላገቡ ኮረዶች አልፎ አልፎም አልሞት ባይ ተጋዳይ አሮጊቶችም ጸጉራቸውን ይሰራሉ ሰራተኞችዋ ሁሉ ሴቶች ናቸው ከአንዱ ወንድ በስተቀር
አንዳንዶቹ ጸጉራቸውን ሊሰሩ ሳይሆን የኑሮ ብሶታቸውን ለማሰማት ሌሎችም ሀሜት የሌላ ሴት ሚስጢር ለመናገር እንጂ እውነት ጸጉር ሊሰሩ የመጡ አይመስሉም ወንዱም ቢሆን ምላሰኛነቱን ስለሚያውቅ ነው መሰለኝ እነዚ ያለጸባይህ ተናጋሪ ያደርጉሀል አለኝ.
አንዳንዴ እኔ ያን ብርድልብስ የሚያክለውን አዲስ ዘመን ጋዜጣ የማነብ መስዬ ፊቴ ላይ በመከለል ጉዳቸውን እየሰማው ድምጼን ሳላሰማ ስቃለው
የነዚ ሁለት ወረኛ ሴቶች ሀሜት ቢጣፍጠኝም መቀመጡ ስለሰለቸኝ የማነበውን ጋዜጣ እጣጥፌ ላስቀምጠው ስል አጅሪት ረጅሙ ወንበር ላይ ቁጭ ብላ ጸጉርዋን ያን ዞማ ጸጉርዋን ወንዱ ሲሰራት አየዋት ልጁ ያበጥራል ይጠቀልላል ሄጄ ሰላም አልኩዋት
ሰላምታ ከተለዋወጥን በውሀላ
''መቸ ነው እንዴ የገባሽው''?
''እኔጃ አንድ አምስት ደቂቃ አድርጌያለው''
''እንዴት ታድያ አላየውሽም''
''ጋዜጣ እያነበብክ ነበራ''
ጸጉር ሰሪው አበጣጠሩን አልወደድኩትም ብዙ መነካካት ያበዛ ሆኖ ተሰማኝ ማበጠርያውን ቀምተህ እነቀው እነቀው ተሰማኝ ወድያው ደሞ ምን ነካኝ እኔ በስመአም ምስኪን ልጅ ስራውን በሰራ እኔ ምን እንደዚህ በቅናት አላወሰኝ ብዬ.
''በይ እዛጋ ቁጭ ብያለው ስትጨርሺ አናግርሻለው''
''እሺ ጠብቀኝ''
ወደ ነበርኩበት ወንበር ተመልሼ ከሩቁ አያት ነበር ጸጉር ሰሪው የሆነ ወሬ ይነግራትና እስዋም ትስቃለች እስዋም በተራዋ የሆነ ወሬ ታወራና እሱም ሳቀ ትንሽ ራቅ ስላለ ምን ምን እንደሚባባሉ አይሰማኝም ግን ልጁ ቀዳጅ ስለሆነ ተራ ወሬ ነው ለኔ ግን ቅናት ሲያበግነኝ ይሰማኛል ጌታው ሲበላ ፍርፋሪ እንደሚጠብቅ የተራበ ድመት ነው አስተያየቴ ሚያው ማለት ነበር የቀረኝ እውነት እሄ ሁሉ ለኔ እላለው ተሰርታ እስክትጨርስ አመት ሆኖብኛል ሰከንዶቹ ቁአ ቁአ ቁአ ስልሳ እንደቆጠሩ ያ ፈዛዛ ደቂቃ ደሞ የግድ ስልሳ ደቂቃ ካልሞላ አንድ ሰአት አይሆንም ይላሉ እንደምንም ተሰርታ ጨረሰች
ጎረቤት ወዳለው ኬክ ቤት ሄድን ሻይዋን ፉት እያለች
''ትላንት የት አመሽህ''
''ቤት ኦ... አንድ ምጠይቃት አክስታችን ስለነበረች እስዋ ጋር አመሸው ግንኮ በጊዜ ነውኮ ቤት የገባውት
''ሶስት ሳአት በጊዜ ነው?'' (በኢትዮፕያ ሰአት አቆጣጠር ማለትዋ ነበር) ፈገግ እያለች
''አይ አንቺ ደሞ ምን ላርግ ብለሽ ነው አክስቴ አለቅ ብላኝ ነውኮ''
በሆዴ አጅሪት አንቺም እንደኔ መቅናት ጀመርሽ አይ ያ የመውደድ ምልክት ሳይሆን አይቀርም ብዬ ገመገምኩኝ.
ከጎኔ ሽጉጬ እንደዛ ሸቃቢ ልጅ ሳይሆን እኔ በፍቅር ያ ደስ የሚለውን ጸጉርዋን እየዳበስኩ እንቡጥ ከንፈርዋን ለምሳ ብበላው ደስ ባለኝ ግን ምን ያደርጋል እንደ አገሩ እንደ ባህሉ መሆን አለብኝ ከታገስኩ ገንዘብ ሊገዛው የማይችል እጹብ ድንቅ ፍጥረት የግሌ ይሆናል በመልስ እኔም የስዋ.
ፈተናም ስላለብኝ ልሂድ አለች
''አትጫወቺም ለምን አትቆዪም?''
''እንዳይረፍድብኝ ሰአት የለኝም ብላ ተነሳች ኮንትራት ታክሲ አሳፈርኩዋትና ሹፌሩ ያላየን መስሎን አንደ ነገሩ ከንፈር ለከንፈር ተሳስመን ለነጂው ሂሳቡን ከፍዬ ታክሲው ፍቅሬን ይዞብኝ ጠፋ
God bless america and the rest of the world.
ወንድም
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 275
Joined: Thu Jan 13, 2005 3:05 am
Location: united states

Postby ህይወት » Wed Sep 06, 2006 8:53 am

ሰላም ወንድም!!

ታሪክህን በጣም ነው የወደድኩልህ... አብሶማ አንዳንዴ ጣል የምታረጋቸው ነገሮች በሳቅ ይገላሉ..... ታየህኝ እኮ የውበት ሳሎን ቁጭ ብለህ እንደድመት ስትቁለጨለጭ ቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅ
በተረፈ ታሪክህን በጉጉት ነው የማነበው.....ጌታ መጨረሻችሁን ያሳምርላችሁ... ማፍቀርንና መፈቀርን የምያክል ስጦታ የለም
ህይወት
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 167
Joined: Mon Dec 15, 2003 5:11 pm

Postby ወንድም » Wed Sep 06, 2006 10:07 pm

ndave ለምኞትህ አመሰግናለው ድፎ ዳቦ አሳቀህ አየህ
ልክ ነኝኮ አንዳንዴ የተማሩት በደንብ አልተያዙም

ህይወት ታሪኬን በመውደድሽ አመሰግናለው ልክ ብለሻል መወደድንና መውደድ የመሰለ ነገር የለም አንዴ ማዘር ትሬሳ ምን አልች መሰለሽ every body have the right to love and loved.
God bless america and the rest of the world.
ወንድም
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 275
Joined: Thu Jan 13, 2005 3:05 am
Location: united states

Postby ወንድም » Thu Sep 07, 2006 2:56 am

መሽትሽት ሲል ወደ ቤት አመራው ከትክሲ ወርጄ ወደ ቤት ሳሰግም የሰፈር ተሰብስበው የሚያወሩ ይርሰፈር ጎረምሶች አየውና
''እንደምናቹ ፍንዳታዎች'' ስል ለተረብም ጭምር
ከመሀላቸው አንዱ
''እኔ ውሸት ነው ብያለው ጠላት ግን አንተ ከአብዮቱ ጋር ነው አብረህ የፈነዳሀው ይባላል ብሎ ትልቁን ጣለብኝ ትልቅ ትልቅ ነህ ሊለኝ ፈልጎ.
አልፎ አልፎ ፌስታልም ይሁን የሆነ ነገር በጄ ስይዝ ካላገዝንህ ይላሉ እኔም አልፎ አልፎ ወጥቼ ሳዋራቸው ደስ ይለኛል ብዙ ማላውቃቸው አዳዲስ ያራዳ ቃላቶችንም አስተምረውኛል እኔ የድሮን ያራዳ አነጋገር ስነግራቸው እሱማ ድሮ የቀረ ፋራ እንዳይሉህ ብለውም ያስጠነቁቅኛል.
ቤት ገብቼ እኔ እህቴና ማዘር ቲቪ እያየን ሳለ እናቴ ያለወትሮዋ ቲቪውን ከልብዋ እንደማታየው ተረዳው አልፎ አልፎም በቆረጣ ታየኛለች.
''እማዬ ምን ሆነሻል እንዴ ልብሽ ላይ ምን አለ'' ብላት
'' ምን አለ ሆዴ ላይ? ሆዴ ላይማ ቅሬታ አለ ባለፈው አጎትህ ሽማግሌ ልላክ ቢልህ አሻፈረኝ መጀመርያ እኔው ራሴው ከስዋ ጋር ልጨርስ አልከ እኛ ደሞ እውነት መስሎን ብንጠብቅ ምንም የለም እንደ ሰዉ ወልደህ መክበድ አትፈልግም ዘላለምህን አንድ ፍሬ ሆነህ ነው የምትኖረው እኔንስ የአያትነት ማእረጌን እንዳላገኝ ነው ምንድነው ችግርህ ልጄ. ለምን እንደ ዘመኑ ወንዶች የሚባለውን አትላትም ሰነፍክ''
ሴትዮ ምን ትላለች ልጅዋ የአጅሪት ልብዋ እስኪጠፋ እንደደከም አንፖል አይንዋ እስኪጭለመለም ከንፈርዋን እንደለብጥኩዋት ማን በነገራት. ለህቴ ግን ጫፍጫፉንም ቢሆን ነግሬያታለው
''ምን መሰለሽ ማዘር እሔ በሆይሆይታ የሚደረግ ነገር አይደለም በሂደት የሚደረግ ነው ሳትወደኝ አትቀርም ከሰሞኑ ነግርሻለው ብዬ እጅዋን መትቼ ማልኩላት
''አጎትህም ልጁ ከምን ደረሰ ብሎ ደውሎልኝ ነበርና ለሱም ደውለህ አስረዳው አለችኝ
''እሺ እማዬ ነገ ደውልለታለው''
አሁን ትንሽ ዘና አለች
God bless america and the rest of the world.
ወንድም
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 275
Joined: Thu Jan 13, 2005 3:05 am
Location: united states

ወንድምምምምምምምም

Postby zizu » Thu Sep 07, 2006 3:57 am

መጀመርያ ሰላም ብያለሁ ወንድም
ታሪኩ በጣም አርፊ ነው ግን ግን አጻጻፍህ አንባቢዎችህን በስጩ እያስያዘን(እያበሳጨን) ነው ወይ ቶሎ ቶሎ ጻፈው ወይ ደግሞ ቆይተህ አንዴ ስትጽፍ በዛ አርገህ ጻፈው::
ከትህትና ጋር ::
zizu
ጀማሪ ኮትኳች
ጀማሪ ኮትኳች
 
Posts: 98
Joined: Sat Aug 21, 2004 7:46 am
Location: saudi arabia

Postby ወንድም » Thu Sep 07, 2006 4:53 am

ዚዙ ታሪኩን እንኩዋን ወደድከው ግን ተረዳልኝ ስራ አለብኝ በዛ ላይ ደሞ ሌላም ማደርጋቸው ነገሮች አለብኝ ስትተርክ ዝም ብለህ ከዘረገፍከው እንክራድዱም ያልፍና አይጣፍጥም አትበሳጭ አይዞህ.

ማዘር ዞር ስትል ለህቴ አጅሪትን ነገ እኩለ ቀን ላይ ቦታ ነገርኩዋትና እዛ ይዛት እንድትመጣ ነገርኩዋት ምንም
''ለምን እኔ እንዳመጣት ፈልክ''
''እንዳይደብራት ነዋ''
''ተው አትቀልድ እውነቱን ንገረኝ''
''እሺ እንድታላምኝኝ''
''ነገ ለትዳር ልጠይቃት ወስኛለው''
''ጎበዝ የኔ ወንድም ትዳር ከፈለክ ከዚች የተሻለ ሌላ ሴት አላውቅም እኔ ወንድ ብሆንኮ እስካሁን ሁለት አስወልጄ ሶስተኛ ባስረገዝኩ''አለችኝ ነቃ ነቃ እንድል ደካማነቴን አሳይታ እየሳቀችብኝ
''ግን እሺ ምትለኝ ይመስልሻል''
''አንዳንዴ ሳስበውኮ ትበዛብኛለች እላለው
''ትቀልዳለህ መሰለኝ ዘንድሮ እንዴት ባል እንደተወደደ ታውቃለህ ደረጃ ከአንድ እስከ አስር ስጥ ብባል ዘጠኝ ወይ አስር እሰጥሀለው ወንድሜ ስለሆንክ አይደለም ብላ
ለሞራሌ አሞጋገሰችኝ.
''እኔ ደሞ ላንቺ አስር ነው የምሰጥሽ አስራ አንድ ስለማይቻል ነው እንጂ አስራአንድም ባሽከምኩሽ ነበስ ነገር እንደሆንሽ ታውቂያለሽ
''አንተ እንደምትለው ከሆነማ የታለ ታድያ ልጁ?''
''ማነው ልጁ''
''ጠፍቶህ ነው የወደፊት የልጆቼ አባት ፍቅሬ እድሜ ላንተ ሁሉ ተሙዋልቶልኛል እናታችንም ከጎኔ አለች ግን አሁን እድሜየም እየገፋ ነው የዚ አገር ወንዶች ታውቃቸዋለህ ህጻን ልጅ ነው የሚፈልጉት
እንደዚህ እንደተሰማት አላውቅም ነበር አይዞሽ አንቺ ደሞ አንድ ቀን ያንቺም ባል በነጭ ፈረስ እየጋለበ መጥቶ ይወስድሻል ሆድ አይባስሽ አንቺም ከሰው ጋር ተቀላቀይ''
'''እይ ነገርን ነገር አንስቶት ነው እንጂ ወንድማ መች ጠፋ ሰካራም ኤድስ የሚያመጣ ሴሰኛ ስራፈት ኩታራ ባል ስላልፈለኩኝ ነው እንጂ
''አይዞሽ ነብሴ እኔ ሳገባ አገባው ብዬ ባንችም በማዘርም ጀርባየን አላዞርም ሁልጊዜ ከጎናቹ እንደሆንኩኝ አትጠራጠሪ.
''አደራህን እንደአንዳንድ ወንዶች ሲያገቡ የሚስታቸውን ወሬ ሰምተው ቤተሰቦቻቸውን እንደሚረሱ እንዳትሆን
God bless america and the rest of the world.
ወንድም
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 275
Joined: Thu Jan 13, 2005 3:05 am
Location: united states

PreviousNext

Return to Warka Intimate - ዋርካ ፍቅር

Who is online

Users browsing this forum: Google [Bot] and 4 guests