by የጁ » Thu Sep 28, 2006 8:49 pm
ሠላም እሪኩም እንዲሁም ከርታታው 88
ውድ እሪኩም በሰዕል አስደግፈህ ፖስት ያደረግከውን የድልብ ተራራ ሳይ በእውነት ውልብ የሚል ትዝታ ነው ያሳደረብኝ በጣም አመሰግናለሁ :: ቤቱ ቤትህ ነው አትጥፋብን ::
ወዳጄ ከርታታው 88 በግጥም ስንኞች ያቀረብካት ውዳሴ ተመችታኛለች በል እስቲ ወደ የጁ ዘልቀህ ግባና አንዳንድ ትዝታዎጭን አጋራን ይልመድብህ ::
እስቲ ስለ ወልድያ ትንሽ ልበላችሁ :: ወልድያ ከኢትዮጵያ መዲና አዲስ አበባ 520 ኪሎ ሜትር እርቃ የምትገኝ በተራራዎች ዙሪያዋን የተከበበች አንጋፋ ውብ ከተማ ነች ይሁን እንጅ በአሁኑ ሳአት እኔ ከማውቃት በሶስት እጥፍ አድጋ ትገኛለች :: እረጅም ኪሎ ሜትር ተጉዘው የየጁ አውራች የመጀመሪያ ክልል የሆነችዋን ምናልባት ባልሳሳት ወርጌሳን አይተው የሊብሶን ጠመዝማዛ መንገድ በአልክሮት እያስተዋሉ ተንጣሎ በተኛው ሜዳ ላይ የተቆረቆረችው መርሳ ከተማ ይገባሉ ይች አናሳ ከተማ በከርሰ ምድሯ ብዙ ፍራፍሬዎችን የምታበቅል ሲሆን ኬነዚህም ውስጥ ምናልባትም በሌላ ቦታዎች እምብዛም የማይታወቀውን "ትርንጎ" የሚባለው ፍሩት በብዛት ይመረትባታል :: ከዝች ከተማ በኋላ ትናንሽ መንደሮች እንደ ገንቦ በር ቀርጨም በር አልፈን ስሪንቃ የምትባል ለም ይተላበሳት ትንሽየ ከተማ እንገባለን,እነዚህን መንደሮች ከትላላቅ ከተማዎች የሚለያቸው ነገር ቢኖር በመኪናዎች መሯሯጥ ፈንታ የአህያና በቅሎዎች ትርምስ ነበር ስለ ስሪንቃ ብዙ አቀንቃኞች ዘካክረዋል ከዚህም ጋር የዝች ትንሽ ከተማ መታወቂያ በዘመነ ሃይለስላሴ ከመሳፍንት ቤተሰብ የተወለዱ እንደ አባተ ሃይሉ ባጎራባች ጎርፉ ተሰማ ራስ ጀበና ደጃዝማች ጎበና በሚባሉ እውቅናን ማግኘቷ ነው ::
በከፍተኛ ቦታ ላይ የተሰራውን ሞላጊወርጊስ ቤተክርስቲያን ከማዶ እያየን ጀነቶበርን አቆራርጠን ወልድያ ከተማን እናገኛለን "ወልድያ" የሚለው ስያሜ ከኦሮሞኛ የተወሰደ ነው የሚባል ነገር ብሰማም ትክክለኛውን ትርጓሜ ጠይቄ እስክመለስ የምታውቁ ሰዎች ካላችሁ ብታሳውቁኝ ምስጋናየ የላቀ ይሆናል ::
ወልድያ እና ውስጣ ውስጧን በሚቀጥለው.......
ከታላቅ አክብሮትና ፍቅር ጋር