***የየጁ ኩማንዳ ጠባ ልጆች***

The Love Forum (love, relationship) (የኔ ቆንጆ እንተዋወቅ :-)

***የየጁ ኩማንዳ ጠባ ልጆች***

Postby የጁ » Thu Sep 28, 2006 11:33 am

እንጀራው መርሳ ላይ እየተጋገረ !
ወጡ ጉባላፍቶ ሲሼተኝ አደረ :

ሰላም ያገር ልጆች ! ፍቅርና ሰላም ከናንተ አይጥፋ እያልኩ ""ወልድያ"" ጣይቱ ብጡል መልካ ቆሌ እና ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት የተማራችሁ እስቲ እዝች ጋ አለን በሉን :: አምዱ ሁሉንም ያሳትፋል ::

ከታላቅ አክብሮትና ፍቅር ጋር
Last edited by የጁ on Mon Dec 14, 2009 3:03 pm, edited 1 time in total.
Diqaw Ke Kumandateba
የጁ
ጀማሪ ኮትኳች
ጀማሪ ኮትኳች
 
Posts: 82
Joined: Thu Sep 28, 2006 10:59 am

የጁ

Postby እሪኩም » Thu Sep 28, 2006 12:02 pm

ሠላም የጁ!

እንዴምነህ ጃል?
ሓብሩ እና ጉባላፍቶ (ውርጌሳ - ሊብሶ - መርሳ - ስሪንቃ - ወልዲያ - ሳንቃ - ሃራ - ዶሮ ግብር ወዘተ) ትዝታቸው አይረሳም:: የመቻሬ እሽት ጥንቅሽ እና ሸንኮራ አገዳስ?
እቴነሽ ብቅ ብላ ስለ ወ/ሮ ጣይቱ ብጡል ት/ቤት እና ውድበን ታጫውተን አለች::
Image
ለጊዜው ከሳንቃ ወደ ላል-ይበላ ስንጓዝ - ወረታ መንገድ ላይ - ድልብን ተመልከቱ::

አብሽር
እሪኩም
እሪኩም
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 853
Joined: Fri Apr 01, 2005 1:20 am
Location: ወሎ

Postby ከርታታው88 » Thu Sep 28, 2006 4:47 pm

"ወረባቡን አይቶ አበደ ሰውየው
ኮምቦልቻንም አይቶ አበደ ሰውየው
መቼ እመለሳለሁ የጁን ሳላሳየው"
ከርታታው88
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 530
Joined: Tue Jan 10, 2006 7:43 pm

Postby የጁ » Thu Sep 28, 2006 8:49 pm

ሠላም እሪኩም እንዲሁም ከርታታው 88

ውድ እሪኩም በሰዕል አስደግፈህ ፖስት ያደረግከውን የድልብ ተራራ ሳይ በእውነት ውልብ የሚል ትዝታ ነው ያሳደረብኝ በጣም አመሰግናለሁ :: ቤቱ ቤትህ ነው አትጥፋብን ::

ወዳጄ ከርታታው 88 በግጥም ስንኞች ያቀረብካት ውዳሴ ተመችታኛለች በል እስቲ ወደ የጁ ዘልቀህ ግባና አንዳንድ ትዝታዎጭን አጋራን ይልመድብህ ::

እስቲ ስለ ወልድያ ትንሽ ልበላችሁ :: ወልድያ ከኢትዮጵያ መዲና አዲስ አበባ 520 ኪሎ ሜትር እርቃ የምትገኝ በተራራዎች ዙሪያዋን የተከበበች አንጋፋ ውብ ከተማ ነች ይሁን እንጅ በአሁኑ ሳአት እኔ ከማውቃት በሶስት እጥፍ አድጋ ትገኛለች :: እረጅም ኪሎ ሜትር ተጉዘው የየጁ አውራች የመጀመሪያ ክልል የሆነችዋን ምናልባት ባልሳሳት ወርጌሳን አይተው የሊብሶን ጠመዝማዛ መንገድ በአልክሮት እያስተዋሉ ተንጣሎ በተኛው ሜዳ ላይ የተቆረቆረችው መርሳ ከተማ ይገባሉ ይች አናሳ ከተማ በከርሰ ምድሯ ብዙ ፍራፍሬዎችን የምታበቅል ሲሆን ኬነዚህም ውስጥ ምናልባትም በሌላ ቦታዎች እምብዛም የማይታወቀውን "ትርንጎ" የሚባለው ፍሩት በብዛት ይመረትባታል :: ከዝች ከተማ በኋላ ትናንሽ መንደሮች እንደ ገንቦ በር ቀርጨም በር አልፈን ስሪንቃ የምትባል ለም ይተላበሳት ትንሽየ ከተማ እንገባለን,እነዚህን መንደሮች ከትላላቅ ከተማዎች የሚለያቸው ነገር ቢኖር በመኪናዎች መሯሯጥ ፈንታ የአህያና በቅሎዎች ትርምስ ነበር ስለ ስሪንቃ ብዙ አቀንቃኞች ዘካክረዋል ከዚህም ጋር የዝች ትንሽ ከተማ መታወቂያ በዘመነ ሃይለስላሴ ከመሳፍንት ቤተሰብ የተወለዱ እንደ አባተ ሃይሉ ባጎራባች ጎርፉ ተሰማ ራስ ጀበና ደጃዝማች ጎበና በሚባሉ እውቅናን ማግኘቷ ነው ::

በከፍተኛ ቦታ ላይ የተሰራውን ሞላጊወርጊስ ቤተክርስቲያን ከማዶ እያየን ጀነቶበርን አቆራርጠን ወልድያ ከተማን እናገኛለን "ወልድያ" የሚለው ስያሜ ከኦሮሞኛ የተወሰደ ነው የሚባል ነገር ብሰማም ትክክለኛውን ትርጓሜ ጠይቄ እስክመለስ የምታውቁ ሰዎች ካላችሁ ብታሳውቁኝ ምስጋናየ የላቀ ይሆናል ::

ወልድያ እና ውስጣ ውስጧን በሚቀጥለው.......

ከታላቅ አክብሮትና ፍቅር ጋር
የጁ
ጀማሪ ኮትኳች
ጀማሪ ኮትኳች
 
Posts: 82
Joined: Thu Sep 28, 2006 10:59 am

Postby ቂሉ » Thu Sep 28, 2006 9:17 pm

ኧረ የጁ የጁ ውድ መን ውድ መን
እህል እየበሉ ሰው ወዶ መመንመን
ቂሉ
ጀማሪ ኮትኳች
ጀማሪ ኮትኳች
 
Posts: 76
Joined: Tue Jun 06, 2006 10:22 pm

ወሎመጀን

Postby ወሎመጀን » Fri Sep 29, 2006 9:07 am

ወሎ የኮነጆዎች አገር
ወሎመጀን
አዲስ
አዲስ
 
Posts: 13
Joined: Fri Jul 09, 2004 9:23 pm

Postby ወሎመጀን » Fri Sep 29, 2006 9:12 am

ላስታ ላሊበላ/ ቡገና/ ትዝታው ጥሩ
ወሎመጀን
አዲስ
አዲስ
 
Posts: 13
Joined: Fri Jul 09, 2004 9:23 pm

Postby ቂሉ » Fri Sep 29, 2006 8:48 pm

እረ ወሎ ወሎ ያላየ ያየ ለት
ቆሞ ይሂድ እንጂ ልብንስ እንጃለት
የወሎ ልጅ ነሽ ወይ የየጁ ልጅ ነሽ ወይ
ትፍቅጂልኝ እንደው ልምጣ ላጫውትሽ ወይ
እረ ወሎ ወሎ እረ መርሳ መርሳ
ሰውነቴ አለቀ ባንቺ የተነሳ
ወሎን ለማሞገስም ሆነ ለማድንቅ ወሎዬ መሆን ግድ አይልም ጥሎብኝ ደስ ይሉኛል
ቂሉ
ጀማሪ ኮትኳች
ጀማሪ ኮትኳች
 
Posts: 76
Joined: Tue Jun 06, 2006 10:22 pm

Postby የጁ » Fri Sep 29, 2006 9:15 pm

ሠላም ውድ አንባቢያን ! እንዲሁም ወሎ መጀን እና ቂሉ አርሂቡልን ::

ባለፈው ቃል በገባሁት መሰረት "ወልድያ" ለሚለው ትርጓሜ የኦሮሞኛ ቃል ትርጉሙ መገናኛ መሆኑን ጠይቄ ለመረዳት ችያለሁ ከዚሁ ጋር ለማስታወስ የምወደው የወልድያ ቀደምት ስሟ ገነቴ መሆኑን ካገኘሁት ምንጭ ተረድቻለሁ ወልድያን ከሚያካብቧት ታሪካዊ አካባቢዎች የነ እቴጌ ጣይቱ ብጡል የነራስ ወሌ ብጡል አገር መርጦ ይገኝበታል ከዚህም በመነሳት እቴጌ ጣይቱ ብጡል ት/ቤት እና የራስ ወሌ ብጡል ሆስፒታል ስያሜውን አግኝቶ በወልድያ ከተማ ይገኛል :: እንዲሁም ታዋቂው የጋላጊወርጊስ ጠበል ከመቻሬ ጎን በውድመንና በአማየሜጫ ሥር የሚገኘው ቦታ ብዙዎች ከተለያዩ ቦታዎች መጥተው ይፈወሱበታል ::

ከታላቅ አክብሮትና ፍቅር ::
የጁ
ጀማሪ ኮትኳች
ጀማሪ ኮትኳች
 
Posts: 82
Joined: Thu Sep 28, 2006 10:59 am

Postby መንዜው** » Fri Sep 29, 2006 9:32 pm

ቂሉ wrote:እረ ወሎ ወሎ ያላየ ያየ ለት
ቆሞ ይሂድ እንጂ ልብንስ እንጃለት
የወሎ ልጅ ነሽ ወይ የየጁ ልጅ ነሽ ወይ
ትፍቅጂልኝ እንደው ልምጣ ላጫውትሽ ወይ
እረ ወሎ ወሎ እረ መርሳ መርሳ
ሰውነቴ አለቀ ባንቺ የተነሳ
ወሎን ለማሞገስም ሆነ ለማድንቅ ወሎዬ መሆን ግድ አይልም ጥሎብኝ ደስ ይሉኛል
ቂሉ እኔ ራሴ ከሸዋ ቀጥሎ እንደወሎዎች የምወደው የለኝም:: በርግጥ የዋሆቹን ኦሮሞዎችና ጉራጌዎች እወዳቸዋለሁ::
One Ethiopia with melted people
መንዜው**
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 164
Joined: Sun Aug 20, 2006 2:26 am
Location: USA

Postby ቂሉ » Fri Sep 29, 2006 9:48 pm

የጁ
ስለምትሰጠን ጠቅላላ እውቀት ስለወልድያና አካባቢው ማለቴ ነው ላመሰግንህ እወዳለሁ
መንዜው
እኔም ጉራጌዎች በጣም ደስ ይሉኛል ግን ግን የወሎ ሴቶቹ
ዋው በነሱ አትምጣብኝ
እኒህ ወለዬዎች አበላል ያውቃሉ
በጤፍ እንጀራ ላይ ሳም/ሳማ/ አርጉ ይላሉ
ቂሉ
ጀማሪ ኮትኳች
ጀማሪ ኮትኳች
 
Posts: 76
Joined: Tue Jun 06, 2006 10:22 pm

Postby እለፈው » Sat Sep 30, 2006 1:13 pm

ወሎ ገራገሩ የቤተሰቦቼ አገር እንዴት ነው ባካችሁ እስቲ ስለላሊበላ አጫውቱኝ?

ወለዬው ነኝ
klklklklk
እለፈው
ጀማሪ ኮትኳች
ጀማሪ ኮትኳች
 
Posts: 62
Joined: Thu Aug 17, 2006 10:34 pm
Location: All over the world

Postby ጦሳው » Sat Sep 30, 2006 2:04 pm

ለመላው አረዳ ሰላምታዬን በማድረስ ስለ ወልዲያ ሲነሳ ትዝ የሚለኝ አንድ ወልዲያ አካባቢ ካለ ተራራ ላይ ተቀምጠው ስለነበሩ በጣም የታወቁ ሸህ --- ስማቸውን ማስታወስ አልቻልኩም በደርግ መገደላቸውን ግን ትዝ ይለኛል : የበለጠ ማብራሪያ ያለው ይጣጥፍ ::
ጦሳው :
ከጦሳ
ጦሳው
አዲስ
አዲስ
 
Posts: 29
Joined: Sat Jan 28, 2006 1:24 pm

Postby እለፈው » Sat Sep 30, 2006 4:21 pm

እናንተ ስለወሎ አጫውቱኝ ስትባሉ አትሰሙም እንዴ? ወሎዬ ብሆንም ስለወሎ ከስም ያለፈ እውቀት የለኝምና ንገሩኝ::

ወሎገራገሩ
እንካንስ ሰዎቹ ይማርካል ሳሩ በላ ያገሬ ልጅ::
klklklklk
እለፈው
ጀማሪ ኮትኳች
ጀማሪ ኮትኳች
 
Posts: 62
Joined: Thu Aug 17, 2006 10:34 pm
Location: All over the world

Postby የጁ » Sat Sep 30, 2006 8:14 pm

ሠላም ያገር ልጆች ! ውድ እለፈው አብሽር አንተን ማዳመጥ እንዳይሰለችህ እንጅ ስለወሎስ ተወርቶም አያልቅ :wink:

ወዳጄ ጦሳው እንደምናለህ ? ተራራ ላይ ሰፍረው የነበሩት ሼህ ታዬ (የአሩሲው ሼህ) በመባል ይታወቁ ነበር የነበሩበትም ቦታ ውድመን ይባል ነበር ::

ከታላቅ አክብሮትና ፍቅር ::
የጁ
ጀማሪ ኮትኳች
ጀማሪ ኮትኳች
 
Posts: 82
Joined: Thu Sep 28, 2006 10:59 am

Next

Return to Warka Intimate - ዋርካ ፍቅር

Who is online

Users browsing this forum: No registered users and 3 guests