***የየጁ ኩማንዳ ጠባ ልጆች***

The Love Forum (love, relationship) (የኔ ቆንጆ እንተዋወቅ :-)

Postby ሾተል » Fri May 18, 2007 10:34 am

የዕትብቴ ቁፋሮ ቅብረት
የስራስር ግንዴ ትክለት
የሽንታሽንት የጅረት ፍሰት
የዘራዘሬ ቁርሾ ውልደት
የኔነቴ የአሁኑ ግኝት ኩራት
የመሆኔ ሆኖ መገኘት
መጠሮ ወለዬነት

በምዕናብ ጨረሬ ጨርሬ
በጥማት እይታዬ ሰክሬ
ከምኞት አለሜ ጋ ዳክሬ
እንዳላያት በኑሮ ህግ ተሳስሬ
ይኸው አላዝናለሁ -
መሄድ በናፈቀው እግሬ

ከዕምባየ ጋ ሳለቅስ እውላለሁ
መምጫየን በማለም ጉጉት ሠልያለሁ

ውልደቴን ብቻ በማወቅ ተረት
አፍ ሞልቶ ለመናገር በሚያንሰኝ ድፍረት
እቆጥራለሁ የሽንት ውርደቴን ወለየ ነኝ በማለት

ምን አውቄ ምን ቢሉኝ
ውልደቴን ለማየት ያልታደልኩኝ
ከተሜ መጤ ሆኜ ያደኩኝ

አይ የኔ ወለየነት
ሽንት ወረድ የጁነት
የተረገምኩ ለስደት እድገት
የተነደፍኩ በእፉኝት ግዞት

እንደ እፉዬ ገላ በራሪ
በጮርቃነት አገር ዟሪ
በንፋስ ጉልበት ተመታሪ
በባእድ ህግ ተዳዳሪ

ከቁርሾ የተጋባች ትንሽ ስጋ
ይሉ ነበር አሳምማ እንደመርፌ ትዋጋ
ታድያ ሲያማቸው እኔንም እያመመኝ
ማጀታቸው ሰሎ ሲርባቸው እየራበኝ
እንስራቸው አፍስሶ ሲጠማቸው እየጠማኝ
መኖር አቅቶዋቸው ሲሰደዱ እያየሁኝ
ቅባቱ ከፊታቸው ተኖ ሲገረጡ እያዘንኩኝ
እንጀራ ውሀ እያሉ ሲሞቱብኝ እምባ ውጦኝ
በሀዘን ለቅሶ ከሌላ አደኩ ስሜታቸው እየተሰማኝ

ዝናብ ጨክኖ ድርቅ መጥጦ ሲተፋቸው
እክለ ሰውነታቸው ሙዋሾ ሲቀሩ ባጥንታቸው
ጨካኙ ተስቦ እየሳበ ወደ ሞት ስቃይ ሲስባቸው
ኮሌራው መድሀኒት አጥቶ እንደማዕበል ሲጠርጋቸው

ወግዱ ተብለው ተሰፈሩ ከትብት ቅባሮ ቀያቸው
በንዳድ ምች አረሩ አንጀት ጠፍቶ ሚያዝንላቸው
መንግስት ኖሮ ሳያያቸው ተሳልቅ በሞታቸው
ይሄው አደኩ እኔም- እያመመኝ ህመማቸው.........


ሾተል.........ትንሽ ስጋ እንደመርፌ ትዋጋ አሉ...
ሾተል
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 9653
Joined: Thu Jan 13, 2005 9:42 pm
Location: Vienna-Austria

አልፈልግ ጠበቃ

Postby ወልዲያ » Fri May 18, 2007 5:19 pm

ሠላም ሾተል!

እንደዚህ ነው ቅደም ተከተል ተከትሎ መግጠሙ:: ደስ የሚል ነው::
Image
ወልዲያ መቻሬ ደረስኩኝ ሣንቃ:
ቆንጅትን ሳላገኝ ተመለስኩ ስሪንቃ:
ማንዣበቤ አይቀርም ነገሩ አላበቃ:
ውሳኔው የእኔ ነው አልፈልግ ጠበቃ::መልካም ጁማ
ወልዲያ


ወልዲያ
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 679
Joined: Tue Apr 17, 2007 11:55 am
Location: የጁ - ወሎ

ይሻል እንደሆነ?

Postby ወልዲያ » Tue May 22, 2007 8:38 am

ሠላም!


ማህቡብ ዬት አለ ወይንም የጁ:
ሚጢ ገንዳ የለ ወደ ዬት ፈረጁ?
Image
ብቅ ብቅ በሉ ምን ታደባላችሁ:
ሾትል እንደሆነ ሣንቃ ነው ቤታችሁ::

መንደራው ተነሥቶ ጠራው ጣዕምን:
ጠጅ እንዳንጠጣ አናውቃት ደብዚን:
ሸሁ ቤት እንግባ ይሻል እንደሆን::መልካም ማክሰኞ
ወልዲያ
ወልዲያ
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 679
Joined: Tue Apr 17, 2007 11:55 am
Location: የጁ - ወሎ

Postby የጁ » Tue May 22, 2007 9:48 am

ቼ ቢሉት ቼ ቢሉት እማይሰማ ፈረስ

አለንጋው ተሰማ ጉባላፍቶ ድረስ

ደሳለኝ ዛሬም ወልዲያን ሲያሞግስ

በሦሥቱ ሥላሴ ባርባው መካኒሳ

በጋላው ጊወርጊስ እንዳንረሳሳ


አላ ገዶ በታች ካለችው ግራር

ተደግፌ ብቆም ተኛሁኝ አዳር

ምን እርቀው ቢኖሩም አይረሳ አገር

ስሪንቃና መርሳ ሊብሶና ውርጌሳ

አሉባት ትዝታ ከቶ እማይረሳ

ማክሰኞ ገበያው ወንዲያ ይውላል

አሪቲና አሽኩቲ አደስም ይሸጣል

እኔንስ እሚያምረኝ እሪኩም እንስላል
Diqaw Ke Kumandateba
የጁ
ጀማሪ ኮትኳች
ጀማሪ ኮትኳች
 
Posts: 82
Joined: Thu Sep 28, 2006 10:59 am

ነፍስ ይማር

Postby ወልዲያ » Tue May 22, 2007 10:22 am

ሠላም የጁ!የጁ ተወልዶ የጁ ያደገው:
በአጭር ምንሽር ያስደገደገው::

Image

እንኳን ዴህና መጣህ የጁ ወንድሜ ሆይ:
ኑሩን ሳላገኘው ብዙ ጊዜ ስቆይ:
ውርጌሣ ብቅ አልኩኝ ፋጡማን ላወያይ::

አህመድ የለ ከፋጡማ ጋራ:
አላህ ነፍስ ይማር በቃ ይበል መከራ::

ደብረገሊላ ላይ ዬት አሉ ሸሁ:
ሙጋድ እንሻገር እኔ ጠረጠርኩ::

ቲንፋዝ ቤቴ ነው እስላም ቀበሌ:
እሌና እና ማርታ ነበሩ ሸበሌ:
እንጠጣ ነበር በሠባራ ፎሌ:
ትምህርቱን ሥቃኝ ትዝ አለኝ ወገኔ::ነፍስ ይማር ለጀግኖች ወንድሞቼ እና እህቶቼ መሰለ ሙሉጌታ ደረጀ ጥላሁን አምባቸው ፈንታው ወዘተ (ያልታደለው ትውልድ)
ወልዲያ
ወልዲያ
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 679
Joined: Tue Apr 17, 2007 11:55 am
Location: የጁ - ወሎ

Postby የጁ » Tue May 22, 2007 3:45 pm

ሠላም ጤና ይስጥልኝ ወልዲያ የወንዜው

እስቲ ትንሽ ላውራህ ድሮ ስላለፈው

ያ ዘመን ዛሬ አልፎ ትዝታ ቢሆንም

ፍጹም አይሰለችም ሲዘከር ቢኖርም

ጎይቶኦም ገብረአምላክ አማሪካ ሊሄድ

እኛም ጓደኞቹ ድግስ ደገስንና

ስንጨፍር ልናድር ተሰባሰብንና

አባ ስድስቶ ቤት ሆነና አዳራችን

እሮም ሠው በጫዎታው እንዲያ ሲያስፈግገን

በሳቅ ሲንከተከት ንጉሴ በሪሁን

አንድ የተረገመ ነበር ጥበቃ ጓድ

አጉል አቢዮተኛ ወጣትን የማይወድ

ስልጣን ለማግኜት ልቡ በጣም ጓጉቶ

እኛ ስንጫዎት ድምጻችንን ሰምቶ

ባላሰብነው መንገድ አድብቶ አድብቶ

እማኝ እንዲሆኑት ወታደሮች ጠርቶ

እጅ ከፈንጅ ያዝናቼው ብሎ ተደስቶ

ኢሀፓዎች ናቼው ብሎ ስም ሰጥቶ

በዛ ደረቅ ሌሊት ዘብጥያ አወረደን

አልሆነለትም እንጅ ቢሆንለትማ

እንደነ መሠለ እኛም ሟቾች ነበርን

ሙች ያላላት ነፍስ አትሞትምና

ሁሉንም አየነው መኖር ደግ ነውና
Diqaw Ke Kumandateba
የጁ
ጀማሪ ኮትኳች
ጀማሪ ኮትኳች
 
Posts: 82
Joined: Thu Sep 28, 2006 10:59 am

Postby የመንደራው » Tue May 22, 2007 8:40 pm

ሰላም የጁ እንኳን በድህና መጣህ ከጠፋህበት

በእውነት እዴት ደስ ይላል ግጥማችሁ እኔም ብችል አዥጎደጉደው ነበር ታድያ ምን ያደርጋል አልችልም ሰላም ሁኑልኝ ባላችሁበት

የናንተው የመንደራው ከሙጋድ
የመንደራው
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 190
Joined: Thu Oct 05, 2006 1:01 pm

እርግብ

Postby ወልዲያ » Wed May 23, 2007 5:16 am

ሠላም የጁ!ምን ታደርገዋለህ ጊዜው ተበላሽቶ:
ይሸት ነበረ እንደ ሕንድ ሽቶ::

በሪሁን ሥትለኝ ትዝ አለኝ ደገኛው:
ትልቁን መኪና እንደዚህ ሲነዳው::

ንጉሡ ዘገዬ አህያው ዳምጠው:
ሰው ይገሉ ነበር እኛ ሳናውቀው::

ኑሩ ጋር ለማጥናት እኔ ሥሯሯጥ:
ዛሬ ጊዜ የለም እጅህን አምልጥ:
ብሎ ምክር ሠጠኝ ነበር እና ብልጥ:
ተቀብዬ ጠፋሁ ብዙም ዛልንበላጠጥ::

ተመራጭ ተብለው ሰውን ሲገሉ:
ጊዜውን ጠብቆ ይኼው ተጋለጡ::

የሓድሽን እህት ታውቃት አልነበረ:
በንጉሥ ዘገዬ ልጁ ተባረረ::

--------------------------

ኧረ የጁ የጁ ውድበን ውድበን........

የኩኩ ስብስቤን ዘፈን መርጨልሃለሁ........

_____________________

በዕለቱ የመሥፍን አበበን ዘፈን ስናዳምጥ ይነሽጠን ነበር:: የድሮው ባይኖርም ለትዝታ ያህል ይችን ጀባ ልበላችሁ::
Image
እርግብ
http://www.youtube.com/watch?v=PIHfXnSP ... ed&search=
_______________________


አክባሪ ወንድምህ
ወልዲያ
ወልዲያ
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 679
Joined: Tue Apr 17, 2007 11:55 am
Location: የጁ - ወሎ

Postby የጁ » Wed May 23, 2007 7:41 am

ሠላም ለዚህ ቤት!!

ቆርኬና ውላጋ አንተ የመንደራው

ደፈርጌ ሳትደርስ ሙጋድ ላይ ያለህው

ከቶ እንደምናለህ እንዴነህ ባያሌው

ሰላሜ ይድረስህ ከኩማንዳ ጠባውወልዲያ ዘመዴ የጥንቱ የጥዋቱ

ሠላምታ አቀርባለሁ በጣሙን በብርቱ

በሪሁን ደገኛ ያ ባለዘጋንባው

በየአመቱ ገብሬል ሠው የሚያመላልሰው

ደሞ የሃድሽ እህት ትበርህ ስድስቶ

እንዴትስ ልረሳት አብሮ ጠጥቶ በልቶ

ትዝ ይሉህ ይሆን? ጫልቱና አቻምየለሽ

ስንጫዎት ውለን አብረን ስናመሻሽ

ሶፊያ ኑርሁሴን ቆንጆ ልጅ ነበረች

አንድ ፍሬ አፍርታ በሞት ተቀሰፈች

ሊዛ ሃሰንና ልጅ አዲሱ ዋሴ

ድንቡክቡክ ትል ነበር ያች አበባ ካሴ

የት ይሆን ያሉቱ የት ይሆን ኑሯቼው

እንዴት መልካም ነበር አንዴ እንኳ ባያቼው
Diqaw Ke Kumandateba
የጁ
ጀማሪ ኮትኳች
ጀማሪ ኮትኳች
 
Posts: 82
Joined: Thu Sep 28, 2006 10:59 am

አብዶዬ

Postby ወልዲያ » Wed May 23, 2007 8:04 am

ሠላም የጁ!

መንደራው ሙጋድ ላይ አገኘሁትና:
ሞኒካ ቤት ገባን ልንጠጣ ቡና::

መንደራው ጀግና ነው ሁሉን ሲያስታውስ:
በቆንጆ ልጅ ፍቅር እንደዚህ ሲጠብስ:
ፈረንሳይ ገባ እንበለው ቢስ::
Image
የጁ ተው እባክህ ሶፊያን አታንሳት:
በሷ ፍቅር ብቻ አለኝ ቀለበት:
ነፍሷን ይማር እንጅ - ከእኛ ተሰወረች እኛ ስንወዳት::

ሮመዳን ሲቀልድ ጨዋታው ሲዳራ:
ክብ ሠርተን ነበር እየጠጣን ቢራ::

ትዝ አለኝ የጧቱ የጥንቱ:
መፋቅር ድንቁ ኧረ ሥንቱ ሥንቱ::

መላካም አብዶዬ
ወልዲያ
Last edited by ወልዲያ on Wed May 23, 2007 8:07 am, edited 1 time in total.
ወልዲያ
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 679
Joined: Tue Apr 17, 2007 11:55 am
Location: የጁ - ወሎ

Postby ሚጢገንዳ » Wed May 23, 2007 10:06 am

ሰላም እንደምን ከርማችኋል?

አረዳው አንድ ላይ እንዲህ ተሰብስቦ

ስሜን ሲያስታውሰኝ ልቤ ብዙ አስቦ

ከዝች የፍቅር ቤት ባብዶዬው ብቅ ብል

ጄምአው ተሰብስቦ ልቡ የጁ ዘልቋል

የጁ ጉባላፍቶ ሲደቦሩ ወንዙ

መርሳና ጊራና ቆንጆ አፍርቷል ብዙ

ወልዲያና እሪኩም መሪ ወንዝ ጎርፉ

የጁ ታይቷል ዛሬ ምንድነው ማኩረፉ

Monicaምትጠራ ትበል አቦል ጄባ

የመንደራው ዳና ቤታችን እንዲገባ
ሚጢገንዳ
አዲስ
አዲስ
 
Posts: 11
Joined: Sat Oct 28, 2006 3:25 pm

ባንቺው መጀን [ደርብ ዘነበ]

Postby ወልዲያ » Thu May 24, 2007 7:53 am

ሠላም ለቤቱ!

ሚጢገንዳ እንደምነህ?

በጣም ደስ የሚል ግጥም ነው:: ብቅ ብቅ እያልክ አጫውተን::

የጁ መንደራው ሾተል እና ሌሎችም መልካም መልካም ጽሁፎቻቸውን ይዘው ብቅ እንደሚሉ ነው::

ጣዕም እና ሞኒካ ከሸፈቱ ወራት አስቆጥረዋል:: እንሱን ያዬ ወዲህ በለኝ::


***********
በአንቺው መጀን [ደርብ ዘነበ]
http://www.youtube.com/watch?v=tVEz6_VEGrU&NR=1
***********
ሠላም እና ፍቅር ለኢትዮጵያ
ወልዲያ
ወልዲያ
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 679
Joined: Tue Apr 17, 2007 11:55 am
Location: የጁ - ወሎ

Postby የመንደራው » Thu May 24, 2007 10:03 pm

እረ አሁንስ ደስታው ፍርርርርርርርርርርርርርርርርርጥ አድርጎ ነው ያስገባኝ የጠፋው ሁሉ ብቅ ማለት ጀመረ አይደል በሉ እስኪ ሞቅ ሞቅ አደርጉት ሚጢገንዳ እንኳን ከጠፋህበት በሰላም መጣህ

ወልዲያ የነበሪሁን ደገኛ መኪናን ብታነሳ እዴት እደሳኩኝ ይህ መኪና በእውነት ነው የምልህ በእግዚቢት መልክ መቀመጥ አለበት እኔ ከሀገር እስክወጣ ድረስ ይስራ ነበር ድምጹ ራሱ ከሌሎች መኪና ይለያል የሚገርም መኪና ነው ታድያ የዛሬ አመት አካባቢ ወልድያ ሄጄ ከቤታቸው በር ላይ ቆሞል ሰው ስጠይቅ እደማይሰራ ነገሩኝ ይህን ሁሉ ያወራሁት እደው መኪናው በጣም ነው የሚገርመኝ

እስኪ የድሮውን እያነሳችሁ አጫውቱን በጣም ደስ የሚል ታሪክ ነው

የናንተው የመንደራው ሙጋድ ካባድንሳ በታች
የመንደራው
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 190
Joined: Thu Oct 05, 2006 1:01 pm

መልካም ጁማ

Postby ወልዲያ » Fri May 25, 2007 8:06 pm

ሠላም ለቤቱ!

የበሪሁን ደገኛው የጭነት መኪና ለብዙ ነገሮች ያገለግል ነበር:: ጥሩ ሰው ነበሩ:: በእውነት በሕይወት አሉ ወይ?

ቲንፋዝ እና በሪሁን ደገኛው

ከተማው ወደ መቻሬ እየሰፋ እንድሚሄድ ነው:: ወይንም ከእስላም ቀበሌ ወደ ልብስ ማጠቢያ ወንዛችን ስንወርድ ባለው ጫካ አካባቢ ወይንም በእነ መፋቅር ድንቁ ሠፈር ብሎም ከአ/ሁ/ደረጃ ት/ቤታችን ጀርባ ወይንም ቆቦ መሥመር ወይንም አውራ ጎዳና ይዘን ወደ ሥሪንቃ አቅጣጫ::

ለማንኛውም ስለሁሉም ሁኔታ በአጭሩ ብታሰፍርልን ደስ ይለኛል (መነደራው) ---- ሌሎችም የቅርብ ትዝታ እና ምስላዊ ገጽታዎች የምታስታዉሱትን ጀባ በሉን::


Image
ከሞኒካ ቡና ልጋብዛችሁ ብቅ በሉ

መልካም ጁማ
ወልዲያ
ወልዲያ
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 679
Joined: Tue Apr 17, 2007 11:55 am
Location: የጁ - ወሎ

ባላገር - ባላገሩ

Postby ወልዲያ » Wed May 30, 2007 4:09 pm

ሠላም ለቤቱ!

ባላገሩ - [ምርጥ ባህላዊ ዘፈን] - ባላገር
http://www.youtube.com/watch?v=Dy1ULW-6w4s

Image


መልካም አብዶዬ
ወልዲያ
ወልዲያ
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 679
Joined: Tue Apr 17, 2007 11:55 am
Location: የጁ - ወሎ

PreviousNext

Return to Warka Intimate - ዋርካ ፍቅር

Who is online

Users browsing this forum: No registered users and 8 guests