***የየጁ ኩማንዳ ጠባ ልጆች***

The Love Forum (love, relationship) (የኔ ቆንጆ እንተዋወቅ :-)

ድፍንፍን

Postby ወልዲያ » Fri Jun 01, 2007 12:15 am

ሠላም!


ለምን ድፍንፍን ታደርጋላችሁ::
Image

አትታለሉ::

በጣም ግን አዘንኩ::

ለሰው ብላችሁ ማደሩ ይበጃል?


መንደራው እንኳን ብሎት ብሎት ወደ ሙጋድ ተሸጋግሯል::


ምን ችግር አለው ----- የሰው ልጅ አፉ እንጅ ልቡ አይገኝም::


ታዲያ ምን ያስጭንቀናል?


ወንድም እና እህቶች ሳይውቁት በነአስረሽው ምችው እና በቆልማሚት ፋይዳ የለሽ ፖለቲካ ተመተዋል::


ከዚህ ምን እንረዳለን?ምንም!


ለምን?

ምክንያቱም ታሪክ ጨማሪ ሳይሆን ቀናሽ ነውና!


ከመናገር እና ከመተቸት አንቆጠብ - ዘረኝነት ትተን
ወልዲያ
ወልዲያ
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 679
Joined: Tue Apr 17, 2007 11:55 am
Location: የጁ - ወሎ

ታሪክን በልኩ

Postby ወልዲያ » Tue Jun 05, 2007 1:39 am

ሠላም!

Image


ታሪክን በልኩ - ሣናውቅ - እንደፈጥጣለን:
ጊዜው ሢያልፍ - ግን - ማነው የሚያወጣን???

አብረን መፍታት ሥንችል ችግሩን አብረን:
ለምን እንናናቅ ፍቅር ሥይጐለን::መልካም ማክሰኞ
ወልዲያ
ወልዲያ
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 679
Joined: Tue Apr 17, 2007 11:55 am
Location: የጁ - ወሎ

Postby የመንደራው » Wed Jun 06, 2007 9:40 pm

ሰላም የጁወች እዴት ናችሁ ዛሬ ብቅ ያልኩት አንድ ወሎየ ነኝ ባይ በጎሮ በኩል ስለሰደበኝ ነው ግን ስም አልገልጽም ራሱ ያውቀዋልና

ስማ ወዳጄ አልልህም ወዳጄ ስላላደለህ ጭቃ ብለህ ከመሳደብህ በፊት የራስህን ጭቃነት አረጋገጥክልኝ እሽ አንተን ለመሳደብም ሆነ ሌላ ሰው አልፈልግም ግን ከሰደብከኝ ልክ ልክህን እነግርህ ነበር ታድያ ምን ያደርጋል ያገሬ ልጆች እዳይቀየሙ ስል ዝም ማለትን መርጫለሁ

እየውልህ አንድ ነገር ልንገርህ ሰውን አክብር እንድትከበር ካልሆነ በራስህ ግዜ ትዋረዳለህ አታቀኝ አላውቅህ ስድቡ ምንም አያደርግልኝም እሽ ደግሞ እፈለኩበት ቤት ገብቼ መጻፍ መብቴ ነው እዚህ ጻፍ እዛ አትጻፍ እያልክ ልትመራኝ አትችልም እሽ

ካሁን ቡኌላ ብትሰድበኝ ግንባርክን ነው የምልህ እደሴት ልጅ አልንጣጣም እሽ ማን ጋ መሰልህ የምታወራው ጨቅላ

የመንደራው ነኝ
የመንደራው
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 190
Joined: Thu Oct 05, 2006 1:01 pm

አፄ ቴዎድሮስ እና ልዑል ዓለማየሁ

Postby ወልዲያ » Sat Jun 09, 2007 1:24 pm

ሠላም!

Image
አፄ ቴዎድሮስ በ1818 ቋራ ተወልደው ሚያዚያ 13ቀን 1868 ዓ.ም ለኢትዮጵያ አንድነት እና ሠንደቅ ዓላማ ብለው መቅደላ (ዐምባ ማርያም) - ወሎ ላይ አረፉ:: ከአንድ ወር በፊት 139ኛ ዓመታቸውን አብብረዋል:: ሥለዚህ ሁላችንም ከማሰብ እና ከማስታወስ ወደ ኍላ አንበል::

**********************
http://www2.dw-world.de/amharic/avwindo ... 38816.html
**********************

Image
የአፄ ቴዎድሮስ ጋሻ ማክሰኞ ሚያዚያ 18 ቀን 2004 ተመልሷል::

Image

የአፄ ቴዎድሮስ ልጅ ዓለማየሁ ቴዎድሮስ ከአባቱ ሞት በኍላ በእንግሊዞች ተይዞ ወደ ሩቅ ምሥራቅ ብሎም ወደ እንግሊዝ ተጓዘ:: በዚያ ወቅት 7 ዓመቱ ነበር:: የእናት እና የአባት ፍቅሩን ያልጨረሰው ልዑል ዓለማየሁ በ18 ዓመቱ በሳንባ ምች ምክንያት በ1879 ዐረፈ:: አፅሙ በቅዱስ ጊዎርጊስ ቤተክርስቲያን (WINDSOR CASTLE) ሲገኝ ወደ ኢትዮጵያ ተመልሶ በክብር የሚያርፍበትን ቀን ይጠብቃል::

ከታሪክ ማህደር
ወልዲያ
ወልዲያ
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 679
Joined: Tue Apr 17, 2007 11:55 am
Location: የጁ - ወሎ

I SHOT THE SHERIFF

Postby ወልዲያ » Sat Jun 09, 2007 1:29 pm

ሠላም ለቤቱ!

I SHOT THE SHERIFF [BOB MARLEY]
Image
I shot the sheriff, but I didn't shoot no deputy
Oh, no, oh
I shot the sheriff, but I didn't shoot no deputy
Ooh, ooh, ooh Yeah

All around in my hometown
They're tryin' to track me down, yeah
They say they want to bring me in guilty
For the killing of a deputy, for the life of a deputy
But I say, oh, now, now...

Oh, I shot the sheriff, but I swear it was in self defense
Ooh, ooh, ooh
I said, I shot the sheriff, Oh Lord
And they say it is a capital offense
Ooh, ooh, ooh
Hear this

Sheriff John Brown always hated me
For what I don't know
Ev'ry time I plant a seed
He said, "Kill it before it grows."
He said, "Kill them before they grow."

And so, oh, now, now,
Read it in the news

I shot the sheriff, but I swear it was in self defense
Ooh, ooh, ooh
Where was the deputy?
I said I shot the sheriff but I swear it was in self defense

Freedom came my way one day
And I started out of town, yeah!
All of a sudden I saw Sheriff John Brown
Aiming to shoot me down
So I shot, I shot, I shot him down
And I say, if I am guilty I will pay

I shot the sheriff, but I say, but I didn't shoot no deputy
Ooh, no, oh
I shot the sheriff, but I didn't shoot no deputy
Ooo, ooo, ooh

Reflexes had the better of me
And what is to be must be
Ev'ry day the bucket a-go-a well
One day the bottom a-go drop out
One day the bottom a-go drop out
I say, I, I, ...

I, I shot the sheriff, but I didn't shoot the deputy, no
(Repeat)


መልካም ቅዳሜ
ወልዲያ
ወልዲያ
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 679
Joined: Tue Apr 17, 2007 11:55 am
Location: የጁ - ወሎ

ባላገር - ባላገሩ

Postby ወልዲያ » Fri Jun 15, 2007 12:47 am

ሠላም ለቤቱ!

ባላገሩ - [ምርጥ ባህላዊ ዘፈን] - ባላገር
http://www.youtube.com/watch?v=Dy1ULW-6w4s

Image


መልካም ጁማ
ወልዲያ
ወልዲያ
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 679
Joined: Tue Apr 17, 2007 11:55 am
Location: የጁ - ወሎ

ሠላም

Postby ወልዲያ » Mon Jun 25, 2007 7:30 am

ሠላም ለሁሉም!


ከየጁ:

ሠላም ለዚህ ቤት!!

ቆርኬና ውላጋ አንተ የመንደራው

ደፈርጌ ሳትደርስ ሙጋድ ላይ ያለህው

ከቶ እንደምናለህ እንዴነህ ባያሌው

ሰላሜ ይድረስህ ከኩማንዳ ጠባውወልዲያ ዘመዴ የጥንቱ የጥዋቱ

ሠላምታ አቀርባለሁ በጣሙን በብርቱ

በሪሁን ደገኛ ያ ባለዘጋንባው

በየአመቱ ገብሬል ሠው የሚያመላልሰው

ደሞ የሃድሽ እህት ትበርህ ስድስቶ

እንዴትስ ልረሳት አብሮ ጠጥቶ በልቶ

ትዝ ይሉህ ይሆን? ጫልቱና አቻምየለሽ

ስንጫዎት ውለን አብረን ስናመሻሽ

ሶፊያ ኑርሁሴን ቆንጆ ልጅ ነበረች

አንድ ፍሬ አፍርታ በሞት ተቀሰፈች

ሊዛ ሃሰንና ልጅ አዲሱ ዋሴ

ድንቡክቡክ ትል ነበር ያች አበባ ካሴ

የት ይሆን ያሉቱ የት ይሆን ኑሯቼው

እንዴት መልካም ነበር አንዴ እንኳ ባያቼው

Imageመልካም ቀን
ወልዲያ
ወልዲያ
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 679
Joined: Tue Apr 17, 2007 11:55 am
Location: የጁ - ወሎ

Postby የጁ » Mon Jun 25, 2007 9:38 am

ሠላም ደሞ ዛሬ በለቱ ቀን ሰኞ

ሁሉም መልካም ይሁን እሮብም ማክሰኞ

ያገር ልጅ ወልድያ እሪኩም መሪ ወንዝ

አንተም ጠጁን ይዘህ እኔም ይዥ ብርዝ

እንጨዋወተው ያን ያለፈ ጊዜ ያንን ባለ ወዝ

ተወርቶ አያልቅ መቼስ የየጁ ትዝታ

አለፍ አለፍ አርገው ካላዩት በተርታ

እስቲ ልጠይቅህ አንዴ ስጠኝ መልስ

አንድ ልጅ ነበረ ስሙ እሚባል ዘውዱ

ሃብሩ ወረዳ ውርጌሳ ከተማ ነበረ ትውልዱ

ትሁት ሠው አክባሪ ጨዋ ልጅ ነበረ

ደርጉ ብቅ እንዳለ ድንገት ተሰወረ

አሁን የት ይሆን ያለው እንደው ካስታወስከው

ዴስ ይለኝ ነበረ አድራሻውን ባውቀው
Diqaw Ke Kumandateba
የጁ
ጀማሪ ኮትኳች
ጀማሪ ኮትኳች
 
Posts: 82
Joined: Thu Sep 28, 2006 10:59 am

ያ ጎበዝ ሥዐሊ

Postby ወልዲያ » Tue Jun 26, 2007 7:58 am

ሠላም የጁ!

ብቅ ብለህ ጨዋታ ስትጀማምር:
በጣሙን ደስ ይላል ኩራት በሃገር::
Image
ደብረ ገሊላ ላይ አዚዚ ምግብ ቤት:
እንደምን ናፈቀኝ አብረን ስንጫዎት::

በደርግ ብትር ብቻ ወንድሞች ሲያልቁ:
በደርግ ብትር ብቻ እህቶች ሲያልቁ:
አንገት መድፋት ነበር የሰው ልጅ ማወቁ::

ጊዜው ባይሻልም አሁንም ተደግሞ:
ማለፉ አይቀርም እስቲ እንጠብቅ ከርሞ::

ዘውዱ መኮነን ያ ጎበዝ ሥዐሊ:
ውርጌሣ ቁጭ ብሏል ሥራ ግን ፈላጊ?

መልካም ማክሰኞ
ወልዲያ
ወልዲያ
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 679
Joined: Tue Apr 17, 2007 11:55 am
Location: የጁ - ወሎ

አብዶዬ

Postby ወልዲያ » Wed Jun 27, 2007 6:12 am

እንደምናችሁ!እጣኑ ይጭስ - አብዶዬ ናቸው እና::


Image


ፍቅር ለሁላችን
ወልዲያ
ወልዲያ
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 679
Joined: Tue Apr 17, 2007 11:55 am
Location: የጁ - ወሎ

የጁ

Postby ወልዲያ » Tue Jul 03, 2007 9:43 am

ሠላም ለቤቱ!ከሚጢገንዳ

ሠላም የጁና ታዳሚዎቹ እኔም ስለየጁ ትንሽ የምለው አለኝ::
Image
የጁ የግዜር መሃል እጁ
እረ የጁ የጁ ውድመን ውድመን
እህል እየበሉ ሰው ወዶ መመንመን

በወልድያ ሼማ በቃሊም እንዶድ
እንዴት አርገው ቢያጥቡት ይለቃል መውደድ

የጁ በጉባላፍቶ እና በሃብሩ ወረዳዎች የታቀፈች እናት ሃገር ናት የጁ የበርካታ ጀግኖች, የብዙ ምሁሮች, የብዙ ሼኮችና ቀሳውስቶች እንዲሁም ቆነጃጅቶች አገር ከመሆኗም በላይ የአትክልትና ፍራፍሬ የቅባትና የምግብ እህሎች የሚበቅልባት ናት :: በተለይ ኢትዮጵያ ውስጥ በብዛት በየጁ ብቻ የሚገኙ ትርንጎ እና ደጋሌት ማሽላ ተጠቃሾች ናቸው እንዲሁም በታላላቅ ቅርሶች ከቀደምት ታሪካዊነቷ በተያያዘ የጁ ወረሴዎች የሚገኙባት አገር መሆኗ ሲገለጽ ወረሴዎች በአሁኑ ሳአትም በወልድያ በጉባላፍቶ እና በስሪንቃ አካባቢዎች ይገኛሉ,ሆኖም የደርግ ስርአተ ማህበር ባላባት በማለት እንዳዳከማቼው ይታወቃል :: ከብዙ በጥቂቱ ለመግለጽ ያክል ከየጁ ሀብቶች እነ መርሳ አባጌትዬ የዳና ሼሆችና መስጊድ እንዲሁም የመርጦ ስላሴ አቢያተ ክርስቲያናት ይዘከራሉ ::

ስለ የጁ ሲነሳ የጥንቷን ገነቴን የአሁኗን ወልድያ ከተማን እናስታውሳለን እንጀራው ወልድያ እየተጋገረ.....ወጡ ጉባላፍቶ ሰሼተኝ አደረ ይባል የለ :: ወልድያ በ1780 እንደኢትዮጵያዋኑ አቆጣጠር በታላቁ ራስ አሊ እንደተቆረቆረች ሲነገር ከባህር ወለል በላይ 2000 ሜትር ከፍታ ላይ የምትገኝ እና ከ200 አመት በላይ ያላት በአሁኑ ሳአት 55 ሽህ ህዝብ የሚኖርባት አገር ስትሆን ከአዲስ አበባ በ520 እርቀት ከባህር ዳር በ360 ኪሎሜትር እርቀት የምትገኝ እስትራጀቲካዊ ጠቀሜታዋ የጎላ ከተማ ናት :: ከ1959 እንደ ኢትዮጵያ አቆጣጠር በፊት በእቴጌ ጣይቱ ብጡል ት/ቤት ከ1ኛ እስከ 12ኛ ክፍል ትምህርት ይሰጥ እንደነበና ከዚያም መድሀኔ አለም 2ኛ ደረጃ ት/ቤት በመከፈቱ በርካት ተማሪዎች ከተለያየ ቦታ ከቦረና,ወረኢሉ,ደላንታ,ኩታበር,ሩጋ,ሀይቅ,ውርጌሳ,መርሳ,
ሰቆጣ,ከረም,አላማጣ,ቆቦ,ሮቢት,ጎብዬ,ላስታ,ቡግና ወዘተ ከመሳሰሉት እየመጡ ይማሩ እንደነበር ሲታወቅ ከጥንት መምህራን በከፊል እንደነ አባ ፈንታው ገብሬ እንደነ አባ ወረደ አበበ አባ ትኩዬ አቶ አስረስ ሲጠቀሱ አንጋፋው የመልካ ቆሌ ት/ቤትም አብሮ ይታወሳል :: በወቅቱ ይማሩ የነበሩት ተማሪዎች የማይረሱት ትልቅ ትውስታ ቢኖር የብዙ ደሃዎች አባት የነበሩትን አባሼሁን ነው በአባ ሼሁ ሻይ ቤት የነበረውን ዶልች ፓስትኒ አሳንቡሳ ያልበላ ያለ አይመስለኝም ለበላበትም ያዘነ እና ፈጣሪውን የፈራ ሂሳብ ሲከፍል የሌለውም እንደሌለው ነግሮ እንዲያም ያለ በጉልበት ወይንም በሽወዳ ሳይከፍል በመውጣት በዚህ መልክ እየተመገቡ ትምህርታቸውን በሰላም የጨረሱና ለቁምነገር የደረሱ በአሁኑ ሳአት በተለያዩ የአለማችን ክፍል ተበታትነው በተለያዩ ሞያ ያሉ ምስክሮች ናቸው :: የአባሸሁን ውለታ ውለታ ለመክፈል በልቡ የማያስብና የማይመኝ በወቅቱም ስህተት የፈጸመ የማይጸጸት እና ቢያገኛቼው ይቅርታ ለመጠየቅ የማያስብ የለም ግን እሳቼው በአሁኑ ሳአት የሉም ነብሳቼውን ይማረውና :: ከዚህም ጋር በተያያዘ እነ አሊ ጎብዬ እነ ፈልቃ ሰፈር ይርዳው ሰፈር የመሃሪ ዳገት የጓሉ ጠጅ ቤት ትንፋዝ ንጥፍ ድንጋይ ሚዳቆ ገደል መንደቅ ሼሌ ጫንጮ ሲደቦሩ ጀነቶበር የጉባርጃና የገብሪኤል ተራራ አሬሮ ኮሬ አዳጎ ሙጋር ሙጋድ መቻሬ እንዲሁም የጋላጊወርጊስ ጠበል እና የራስ ወሌ ብጡል ሆስፒታልን ስናስታውስ የወልድያ ውበትና ጌጦች መሆናቼውን እንረዳለን ::**አንድ ገበሬ ሁለት እረኞች የሚወጣውን*** አንድ አርጎ ፈጠረው አማረ አምባውን እየተባለ የተገጠመላቼው አቶ አማረ አምባውን በቁመት እርዝመት የሚስተካከል አልነበረም ይህንን ስናስብም በአንጻሩም ሃይሌ ኩንኩንን እናስታውሳለን ከነዚህ የወልድያ ሀብቶች በተጨማሪ የኪዳነምህረት ቤተክህነት ሊቅ እና አገልጋይ የነበሩ ጨዋታ ለዛቸው የማይረሱ አለቃ ድንቁን ከልጆቻቸው የሥም አሰያየም ጋር ይታወሳሉ :: የወልድያ ታላቁ የገበያ ቀን ማክሰኞ በመሆኑ ከከተማዋ አራቱም አቅጣጫ በርካታ ገበሬዎች ወደ ገበያ ቦታ ይመጣሉ በተለይ ከቆላው አካባቢ በሃገር ባህላቸው አልባሳት ተውበውና ደምቀው የሚመጡትን ኮበሌዎችና ኮረዳዎች መመልከት የወልድያን ውበት ለማድነቅ በቂ ማስረጃ ነው :: ወልድያ በተፈጥሮ አቀማመጥዋ ወይና ደጋ በመሆኗ የደጋ የወይናደጋ የቆላ የአየር ንብረትን ታስተናግዳለች እንግዲህ ወልድያን ስናነሳ የጥቁር ውሀን 200 ሜትር እርዝመት ያለውን ድልድይ እና የሳንቃ የሼንኮር አገዳ አይዘነጉንም ከዚሁም ጋር አንጋፋው አርቲስት አያሌው መስፍን እናን አሰፋ አባተን እናስታውሳለን መለል መለል ያሉ እንደ ምስሮች***አሁን ገና መጡ የየጁ ልጆች ብሏል አቀንቃኙ :: ምስሮች ለጥርስ መፋቂያነት የሚያገለግል አበቃቀሉም ቀጥ ብሎ የወጣ ነው በተለይ በጫንጮ ወንዝ በብዛት የሚገኝ ተክል ነው ::

ከዕውቁ ተወዳጅ አርቲስት እና መምህር አባ ትኩዬ ግ/እየሱስ ጋር ሰአሊ በላይ ጎርፉ የሚረሳ አይደለም በተለይ በወልድያ እና በተለያዩ የእስልምና እና የክርስትና ሀይማኖት የበአል አከባበር ለየት እና ሞቅ ደመቅ ያለ በመሆኑ ከህሊናችን የሚጠፋ አይደለም በተለይ በቡሄ በአል ለጅራፍ ግርፊያ ወደ ሲደቦሩ ሜዳ መሄዱ የተለመደ ነበር እንዲሁም ለልብስ አጠባም ይሁን ለመዝናናት ሼሌ ወንዝ ጫንጮ ወንዝ ንጥፍ ድንጋ ወንዝ የሚጓዘው ህዝብ ቁጥር ቀላል አልነበረም በጳግሜ ቅዱስ ዩሃንስ ንጋት ወደ ንጥፍ ድንጋ ገላ ለመታጠብ በሚሄዱት ወጣቶች ይሰማ የነበረው የጉዞ ዘፈንና ጭፈራ ልዩ ውበት ይሰጥ ነበር በኢድ ፈጥር እና በአረፋ በዐል በገጠር እና በከተማ የሚገኘው ሙስሊም ህብረተሰብ ጭፈራ ሁሌም የሚታወስ ነው እንዲሁም በጥምቀት በአል ታቦት ለመሼኘት የሚወጣው ህዝበ ክርስቲያን የተለያዩ ባህሎች ጭፈራ ፍጹም የሚረሳ አይደለም ::

በተጨማሪ ከታላላቅ የአገር ሽማግሌዎችም እነ አቶ ደምሴ አፍራሳ አባ ግራዝማች መሀመድ ተጠቃሾች ናቸው ከዛ ባሻገር እሪኩም እሪኩም ይሼታል ገላህ እንዴውም በመላ የየጁ ልጅ ነህ ተብሏል ::

ከሁሉም በላይ ሠላም ለኢትዮጵያችን ::ፍቅር በመሃላችን ይሥፈን
ወልዲያ
ወልዲያ
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 679
Joined: Tue Apr 17, 2007 11:55 am
Location: የጁ - ወሎ

Postby ልምጩ » Fri Jul 06, 2007 6:51 pm

ፍቅር ፍቅር ብቻ የሚሸት ቤት! እንዴት ደስ ይላል !? እዚህ ቤት ማንን አመስግኖ ማንን መተው ይቻላል? እንዲያው በደፈና ፍቅሮች ናችሁ ማለቱ የሚቀል መሰለኝ :D :D :D :D :D
ልምጩ
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 536
Joined: Mon Jul 17, 2006 6:22 pm

Postby የመንደራው » Sat Jul 07, 2007 10:52 pm

ፍርርርርርርርርርርርርርርርርርርጥ

እዴት ናችሁ የጁወች ወልድያ: የጁ : ሚጢገንዳ :እዲሁም ሌሎቻችሁ ሰላም ናችሁ ባላችሁበት ሰላሙን እመኝላችኃለሁ የናንተው ከሙጋድ

የመንደራው
የመንደራው
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 190
Joined: Thu Oct 05, 2006 1:01 pm

ፍትህ

Postby ወልዲያ » Sun Jul 08, 2007 10:51 am

ሠላም ለሁሉም!


Image
ለፍቅር እና ለፍትህ ሁላችንም አብረን እንጓዝ

መልካም ሠንበት
ወልዲያ
ወልዲያ
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 679
Joined: Tue Apr 17, 2007 11:55 am
Location: የጁ - ወሎ

Postby አስራር » Sun Jul 08, 2007 6:08 pm

ስለመርሳ የሚያውቅ ካለ ሙሉ ዘገባ እፈልጋለሁ
አስራር
አዲስ
አዲስ
 
Posts: 32
Joined: Sun Oct 17, 2004 9:25 am
Location: united states

PreviousNext

Return to Warka Intimate - ዋርካ ፍቅር

Who is online

Users browsing this forum: Google [Bot] and 8 guests