***የየጁ ኩማንዳ ጠባ ልጆች***

The Love Forum (love, relationship) (የኔ ቆንጆ እንተዋወቅ :-)

የጁ እና ቁንጅና

Postby እሪኩም » Sun Oct 01, 2006 11:35 am

ሠላም የጁ እና ታዳሚዎች!

የጁ እና ቁንጅና

ውጫሌን አልፌ ውርጌሳ ስገባ:
አለባቸው ተካ ነበር የተቀባ::
Image
ሊብሶ ሱዳን ሰፈር ደረስኩኝ መርሳ:
ውበት ማድነቅ ብቻ ተፈሪ አይረሳ::

ስሪንቃን አድንቄ ስወጣ አቀበቱን:
በስተ ግራ በኩል አየሁ ኃይሉ አባተን:
በክብር ተኝቶል ተማርኩ ጀግንነትን::
Image
አፋፉ ላይ ሁኜ ሳይ ወልዲያን:
ጨዋታ ለማዬት እንደዚህ ልሁን::

ቲንፋዝ ውስጥ ስገባ ጐዳናን አልፌ
ሸሁ ታዬ አሉ ልፈወስ አርፌ:
ችግርን ሲፈቱ - ሞቱ - በደርግ መርፌ::

.............ይቀጥላልመልካም ጊዜ
እሪኩም ከቦሩ ሜዳ
እሪኩም
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 853
Joined: Fri Apr 01, 2005 1:20 am
Location: ወሎ

Postby የጁ » Sun Oct 01, 2006 8:44 pm

ሠላም ያገር ልጆች !!

ወንድሜ እሪኩም "አለቤ" ቢሞትም ሥራዎቹ ህያው ሆነው ይኖራሉ የጁ አሁንም ቢሆን እንደነ መፋቅር ድንቁ የመሳሰሉትን ኮትኩታለች ::

ከታላቅ አክብሮትና ፍቅር ጋር ::
የጁ
ጀማሪ ኮትኳች
ጀማሪ ኮትኳች
 
Posts: 82
Joined: Thu Sep 28, 2006 10:59 am

Postby ሽማግሌው » Mon Oct 02, 2006 2:26 am

ኦነግ ወሎ የኦሮሞ ሀገር ነው : ሀበሻው ወራሪ ነው ይላል ::
ማፓቸውን ብታዩት ወሎን ይጨምራል :: ወሎዬዎች ምን ትላላችሁ ለዚህ ምላሽ ? እውነት ወሎ የኦሮሞ ሀገር ነው ?
አንድ ወሎዬ ሲያጫውተኝ ወሎ አማራ ነው : ያሉት ኦሮሞዎችና የኦሮሞ ስም ለከተሞች የሰጡት የወራሪው የግራኝ አህመድ ጀሌዎች ናቸው ብሎኝ ነበር :: እውነቱ የትኛው ነው ?
ሽማግሌው
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 649
Joined: Sat Nov 08, 2003 11:42 pm

አንድ ኢትዮጵያ

Postby እሪኩም » Mon Oct 02, 2006 8:36 am

ሠላም ሽማግሌው!

[quote="ሽማግሌው"]ኦነግ ወሎ የኦሮሞ ሀገር ነው : ሀበሻው ወራሪ ነው ይላል ::

ጨዋታውን አደበላለከው ጃል:: ፍየል ወዲያ ቁዝምዝም ወዲህ እንደ ማለት ነው:: ለማንኝውም ካለቦታው የሰነዘርከውን ሃሳብም ሆነ አሉባልታ ዋርካ ፖለቲካ ውስጥ ብታስቀምጠው እና ብትወያይበት ይሻላል::
Image
ኦሮሞ አማራ ትግሬ ጉራጌ ወላይታ ሲዳማ አፋር ጋምቤላ ሶማሌ ወዘተረፈ - ሁሉም የኢትዮጵያ ልጆች - ኢትዮጵያ ከዳር እስከ ዳር አገራቸው ነው:: ማንም ሊከለክላቸው አይችልም:: እደፈለጋቸው መንቀሳቀስ መኖር መውለድ እና መክበድ ይችላሉ::

ሽማግሌው - እንደ ስምህ ምራቅህን የዋጥክ መስሎኝ ነበር:: ነገር ባትጭር ጥሩ ነው::


ከአክብሮት ጋር
እሪኩም ከቦሩ ሜዳ
እሪኩም
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 853
Joined: Fri Apr 01, 2005 1:20 am
Location: ወሎ

Postby ሽማግሌው » Mon Oct 02, 2006 7:54 pm

እሪኩም ምነው ነገር ነገር አለህ ልጄ ? ጥያቄ መጠየቅ ነገር መጫር የሆነው ከመቼ ጀምሮ ነው ?
እስኪ ደሴ የት እንደተቀመጠች ማፑን እይና ንገረኝ
Image
ሽማግሌው
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 649
Joined: Sat Nov 08, 2003 11:42 pm

ሠላም ለኢትዮጵያ

Postby እሪኩም » Mon Oct 02, 2006 9:25 pm

ሠላም ሽማግሌው!

የነበረው የኢትዮጵያ ካርታ እና ክፍላተ ሃገራት:
Image
በአሁኑ ሰአት የኢትዮጵያ ካርታ እና ክልሎች:
Image

አሁንም ቢሆን ያልተረዳኽው ነገር አለ:: የኦነግን ካርታ አምጥተህ ከምታሳያኝ እና ከምትለጥፍ - ዓለማም - ዐጠፋም - የወቅቱን የኢትዮጵያ መንግሥት ካርታ ብታስቀምጥልኝ ደስ ይለኝ ነበር:: ለማንኛውም ቸር ይግጠምህ::

የፖለቲካ መድረክ አናድርገው:: በዚህ የተነሳ ብዙ ማውራት አልፈልግም::


ከአክብሮት ጋር
እሪኩም ከቦሩ ሜዳ
እሪኩም
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 853
Joined: Fri Apr 01, 2005 1:20 am
Location: ወሎ

Postby እሪኩም » Tue Oct 03, 2006 8:03 am

ሠላም የጁ!

ለመሆኑ መፋቅር ድንቁ እና ሮመዳን እንዲሁም ሌሎች ነባር ከያኒዎች አሉ ወይ? በመጠኑም ቢሆን አጫውተኝ::

መልካም ቀን
እሪኩም ከቦሩ ሜዳ
እሪኩም
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 853
Joined: Fri Apr 01, 2005 1:20 am
Location: ወሎ

Postby የዜናዊ ልጅ » Tue Oct 03, 2006 9:53 am

ሠላም ውድ እሪኩም !

ከረጅም አመታት በፊት የወልድያ ከተማ የኪነት ጓድ ጋር ይሰሩ የነበሩት መፋቅር ድንቁና ሮመዳን አሁንም በህይዎት አሉ :: መፋቅር ድንቁ ባሁኑ ሳአት የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቴአትር ውስጥ ሲሰራ ሮሜ ለጊዜው አዲስ አበባ እንደሚኖር አስታውሳለሁ ከዚሁ ከወልድያ የኪነት ጓድ ጋር የማልረሳቼው ሰዎች ሲሳይ አሰፌ,ነጋሽ ፈለቀ,ግርማ ከበደ,ጫልቱ ዘውዴ,አቻምየለሽ ጫኔ,አለማየሁ አስረስ,ንጉሴ በሪሁን ወዘተ የወልድያ እንቁ ልጆች ነበሩ ::

ከታላቅ አክብሮትና ፍቅር ጋር ::
የዜናዊ ልጅ
ጀማሪ ኮትኳች
ጀማሪ ኮትኳች
 
Posts: 56
Joined: Sun Aug 27, 2006 6:15 pm

Postby እሪኩም » Tue Oct 03, 2006 10:03 am

ሠላም የዜናዊ ልጅ!

በጣም አመሰግናለሁ:: በትዝታ ወደ የጁ - ወልዲያ - ወሰድከኝ ጃል::

መልካም ቀን
እሪኩም ከቦሩ ሜዳ
እሪኩም
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 853
Joined: Fri Apr 01, 2005 1:20 am
Location: ወሎ

Postby ሀዱድ » Tue Oct 03, 2006 11:23 am

ቅቅቅቅ እሪኩም እንዳትቆጣኝ እንጂ የጁ እሳት ይዞዋል በእጁ ማለት ምን ማለት ነው?

ደሴ ዳውዶ ሆጤ አይጠየፍ ቤቴ
ገራዶ ኮምቦልቻ የጁ ጎረቤቴ
በፍቅር ልሞት ነው ደከመ ጉልበቴ

አንተ የወሎልጅ ጠንበለል ሸበላ
ቆዳህ ለስለስ ያለ ከንፈርህ ወለላ
እኔ ካንተ እርቄ እህልም አልበላ

ልታጠን በሪኩም ልታጠን ባደስ
ልቀባ ልኩዋኩዋል የክቴን ልልበስ
ወደቤት ሲመጣ ልቡ እንዲለው ደስ

አምባሰል ገራዶ ቆንጆ እያፈለቀ
የጁ እራያ ቆቦ በቂቤ በአደስ እየተጠመቀ
ልቤ ማለፍ ሳይችል ሀይቅ ላይ ወደቀ

አንተ የሀይቅ ልጂ ልቤን እዋኝተህ አምጣ
በአንገትህ ማተብ ባጠለቅከው ቁምጣ
ያሳ መረቅ ይዘህ በህልሜ እንዳትመጣ

ያለማጣው ጉብል ጊሊ የታጠቀው
ጉራማይሌ ጥርሱን ፈገግ ቢያደርገው
ልቤን ህሊናየን የሱ ምርኮ አረገው

ወይ የወሎ ልጆች እውዳችሁዋለሁሁሁሁሁሁሁሁሁ
ሀዱድ
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 196
Joined: Thu Jan 08, 2004 9:05 pm
Location: uk

እየመጣሽ ቃኚን

Postby እሪኩም » Tue Oct 03, 2006 12:07 pm

ሠላም ሀዱድ!

የጁ እሳት ይዟል በእጁ - ለሚለው ሰፋ ያሉ መግለጫዎች ከየጁ እና ከሌሎች ታዳሚዎች እስከሚገኝ ድረስ በአጭሩ እንደዚህ ለመመለስ እሞክራለሁ::

የጁ አውራጃ ሁለት ወረዳዎች አሏት:: ሓብሩ እና ጉባላፍቶ::

ለቀዳማዊ ኃ/ስላሴ መንግስት አገዛዝ አመች ያልሆኑ መሳፍንት መኳንንት እና ነፍጠኞች የፈለቁባት አውራጃ ስለነበረች በጥቅሉ ህዝቡን መዋጋት እና ማስተዳደር ስላልተቻለ "የጁ እሳት ይዟል በእጁ" በማለት ኃይለ ስላሴ እና መሰሎቻቸው ተናገሩ - ተነበዩ:: የጁ ለሠላም እንጂ ለጠብ አይመችም::

አንቺን እኔ አይቼ መቼ እለቅሻለሁ:
አሸን ክታብሽን ሃራ አስጥልሻልሁ::

ብቅ ብለሽ አጫውችኝ ለምን ትፈሪአለሽ:
መጎንተል አልችልም እስቲ ልጠቃቅስሽ:
መርሳ አባ ጌትዬ - አሉልሽ አይዞሽ::


በይ አትጥፊ - እየመጣሽ - ቃኚን
እሪኩም ከቦሩ ሜዳ
እሪኩም
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 853
Joined: Fri Apr 01, 2005 1:20 am
Location: ወሎ

Postby የጁ » Tue Oct 03, 2006 2:50 pm

ሠላም ያገር ልጆች ! ከላይ እሪኩምን ሀዱድ በጠየቀችው መሰረት የጁ እሳት ይዟል በዕጁ ለሚለው በሚቀጥለው ጠይቄ እስክመለስ በእሪኩም ሃሳብ እንቆይ :: በዚህ አጋጣሚ ሀዱድ እንኳን ደህና መጣሽ እኛም የየጁ ልጆች እንወድሻለን!! አምባሰል ለገደል ምን ያሽሟጥጡታል ፈረስ ባይወጣበት ልጅ ይወጣበታል ::

ወዳጄ የሮያል ልጅ :)...... ከላይ የጠቀስካቼው ሰዎች እንዳልከው የወልድያ ብርቅዬ ልጆች ናቸው መምህር ሲሳይ አሰፌ የወልድያ የኪነት ጓድ አስተዋዋቂ ነበር :: ንጉሴ በሪሁን (አባቱ በሪሁን ደገኛ) የተባሉት ግን ወደ ደጋው ስለሚኖሩ ይሆን ? በነገራችን ላይ ደገኛ የሚባሉት ሳንቃ ቀበሮ ሜዳ ጃርሳ እና አካባቢው የሚኖሩትን ህብረተሰብ ነው አካባቢው በጣም ቀዝቃዛ ነው ::

እስቲ ዛሬ ደግሞ "ሀራ" ስለምትባለው አገር ትንሽ ልበል ሀራ ከወልድያ 30 ኪሎ ሜትር አካባቢ እርቃ የምትገኝ ከተማ ናት ሞቃት የአየር ጸባይ ያላት ቆላማ ቦታ ናት ባለፈው ስራተ ማህበራት እምብዛም ያልበለጸገች ብትሆንም አሁን ግን በንግዱ አለም የወደፊት ታላቅ ተስፋ የተጣለባት ከተማ ሆናለች..... ምናልባትም ጅቡቲን የሚያገናኘው የባቡር መስመር ከተከፈተ ባካባቢዋ ላሉት መንደሮች አስማት ትርጓሜ ባውቅ ምንኛ ደስ ባለኝ ቆርኬ, ቂላዳሜ, አላሌ ሱቡላ, ጎመጅ, እና ሌሎች :: የሀራ ልጆች ቡርሽጥ የሚባለውን የውበት ማድመቂያ እጃቼውን እና እግራቼውን በመሞቅ ይዋባሉ :: ከዚሁ ጋር እዚሁ ወሎ ክፍለሃገር ቃሉ አውራጃ ውስጥ ባቲ አካባቢ የሚገኙ ሴቶች ቦሎቂያ ሰውነታቸውን ይታጠናሉ ይህም ጥሩ መአዛን እንደሚሰጥ ይነገራል እንዲሁም አንቻሮ አካባቢ ብርጉድ የሚባለው ጢስ መልካም ጠረን እንዳለው ይነገራል እስቲ ስለዚህ ዕውቀቱ ያላችሁ አሳውቁኝ :: ሀራ አካባቢ ከሚበቅሉ ፍራፍሬዎች በደና እና እንኮይ የማይረሱኝ ጣፋጭ ፍሬዎች ናቼው ::

ከታላቅ አክብሮትና ፍቅር ጋር ::
የጁ
ጀማሪ ኮትኳች
ጀማሪ ኮትኳች
 
Posts: 82
Joined: Thu Sep 28, 2006 10:59 am

Re: ***የየጁ ልጆች ብቅ ብቅ በሉ***

Postby ዶኑ » Tue Oct 03, 2006 9:39 pm

የጁ wrote:እንጀራው መርሳ ላይ እየተጋገረ !
ወጡ ጉባላፍቶ ሲሼተኝ አደረ :

ሰላም ያገር ልጆች ! ፍቅርና ሰላም ከናንተ አይጥፋ እያልኩ ""ወልድያ"" ጣይቱ ብጡል መልካ ቆሌ እና ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት የተማራችሁ እስቲ እዝች ጋ አለን በሉን :: አምዱ ሁሉንም ያሳትፋል ::

ከታላቅ አክብሮትና ፍቅር ጋር

ሰላም የጁዬ

'ወሎ ሲገቡ ለቅሶ ሲወጡም ለቅሶ" ........ትክክል!
ትዝታዬን ቀሰቀስክብኝ.......ወይ ደብረ ገሊላ! ወይ አዳጎ! እረ ስንቱ እረ ምኑ?
የወሌ ብጡል ሀገር ! ወይ ነዶ!!

ወሌ ...ወሌ ወሌ ቢሏችሁ:
የውረባቦ እንዳይመስሏችሁ!
የእሳቱ ጉማጅ መርጦ አለላችሁ..

መርጦ ኢየሱስ የጁን በየጁንትዋ ይጠብቃት!

አሜን!!
TO DOUBLE YOUR JOY DIVIDE IT BY TWO
ዶኑ
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 411
Joined: Fri Apr 01, 2005 5:31 am

Postby ሀዱድ » Wed Oct 04, 2006 12:57 pm

ሰላም እሪኩም ጥያቄየን ስለመለስክልኝ አመሰግናለሁ
ያው የጊዜ ነገር ታውቃለህ አይደል
በርቱ ተበራቱ እንደገና ብቅ እላለሁ
ሀዱድ
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 196
Joined: Thu Jan 08, 2004 9:05 pm
Location: uk

Postby የመንደራው » Fri Oct 06, 2006 11:24 am

ያገሬ ልጆች እንዴት ናችሁ? ጨው ሪጋ ሙጋድ አባዲንሳ እስላም ቀበሌ መልካ ቆሌ ሜዳ መቻሬ ሜዳ ወልዲያ ውስጥ የሚገኙ የሰፈር ስሞች ናቸው::

እነ ብሮቤን ንጉሴ ታከለ ወሎ ሀብተማሪም ከስፖርቱ የሚያውቅ ሰው ይኖር ይሆን?

ስለቦለቅያ ለጠየቅከው ልጅ

ቦለቅያ በቤት ውስጥ ጉድጓድ ይቆፈርና በጭቃ ትንሽ ቤት ነገር ይሰራል:: ወይራ ሰበንሳ ቆራስማ የመሳሰሉ ጥሩ ሽታ ያላቸው እንጨቶች (እርጥቡ) ጉድጓዱ ውስጥ ይገባል:: ከዛ ፉም እሳት ይጨመርበታል:: እንጨቱ መጨስ ሲጀምር ሴቷ ከወገቧ በታች ያለውን ሰውነቷን ጉድጓዱ ውስጥ ትከተዋልች እሙሙዋ በጭሱ ትክክል መሆን አለበት:: ራቁቷን ሆና በብርድልብስ ነው የምትጠቀለለው:: ከዛ ላብ በላብ ስትሆን ትወጣለች::

እሙሙው ጠበቅ እንዲል ያደርገዋል ወዲያው ያገኘው ምን ብየ ልንገርህ

አንተ አሹለህ ስትለቅበት እሱ እየጠበቀ እንቅ ነው:: እንተ ምንጭቅ እያደረግክ የተፈጠረበትን እስኪጠላ ድረስ አሳሩን ማሳየት ነው::

ብዙ ጊዜ አዲስ ያገቡ ሴቶች ይጠቀሙበታል::
የመንደራው
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 190
Joined: Thu Oct 05, 2006 1:01 pm

PreviousNext

Return to Warka Intimate - ዋርካ ፍቅር

Who is online

Users browsing this forum: Google Adsense [Bot] and 3 guests