***የየጁ ኩማንዳ ጠባ ልጆች***

The Love Forum (love, relationship) (የኔ ቆንጆ እንተዋወቅ :-)

Postby መንዜው** » Fri Oct 06, 2006 9:53 pm

ወሎ እሳት ይዟል በእጁ ቢባልም አይደንቀኝም:: X ገርል ፍሬንዴ ወለዬ ነበረች በቃ እሳት ነችችችችችችችችች ከምር:: ምን ያላደረግነው ነበረ መሰላችሁ ግን ምን ያደርጋል በቃ ወደሌላ እስቴት ሙቭ አደረገች:: አሁን ምናለበት ትዝታዬን ባትቀሰቅሱት?

ከጠበሱ አይቀር ይጥበሱ ወለዬ

ፍቅር ያሳያሉ አሳሳም ላላየ::

ሲነኩዋት ሽቁጥቁጥ ትላለች እንጠጥ

ሲከቱባት ደግሞ ትፈትላለች ጥጥ::

እረ እሷስ እናት ነች ለሶስተኛው እግሬ

ሲያት ደሙ ይፈላል ይነሳል አጅሬ::

በጣም ይወዳታል ከሁሉም አብልጦ

ቢኖርም ይመርጣል በሷ ቤት ተውጦ::

መታሰቢያነቱ ለወለዬዋ X ገርል ፍሬንዴ ይሁንልኝ::
One Ethiopia with melted people
መንዜው**
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 164
Joined: Sun Aug 20, 2006 2:26 am
Location: USA

Postby የጁ » Sat Oct 07, 2006 3:02 pm

ሠላም ያገር ልጆች !

ውድ ዶኑ እንዴነህ የወንዜ ልጅ ? መርጦ ለየሱስ ያን የቆመ ተራራ አይተህልኛል :) ታዲያ ከዛ ሁሉ ድካም በኋላ ተራራ ጫፍ ላይ ጉብ ያለው መርጦ ማራኪ ቦታ ነው :: የራስ ወሌ ቤተመንግስት ውስጥ የራስ ወሌ አልጋ እራሱ በዛ ጊዜ ከነበረው ስልጣኔ ጋር የአሰራር ይዘቱ ይስባል ::
በል እስቲ ሲያመችህ ብቅ እያልክ ጠይቀን ::

ውድ መንዜው ! አቤት አንተ ልጅ መቼም በደንብ ነው የታዘብካቼው የወሎን ልጆች :wink: ለካስ እንዲህ ፍቅር ያስይዛሉ :: አመሰግናለሁ ሃቁን በመናገርህ

የመንደራው እንዴነህ ነፍሴ ? በጣም አመሰግናለሁ "ቦለቅያን" በተመለከተ ያብራራሃውን ለካስ እንዲህ ኖሯር የዚህ ጉደኛ ጭስ ጥቅሙ ሳላውቅ በመቅረቴ :oops:
ትንሽ መለስ ብለህ ስለ የጁ አውራጃ የእግር ኳስ ቡድን አስታወስከኝ ብሮቤ የ03 ቀበሌ ተጫዋች ነበር ንጉሴ ደግሞ የ02 ቀበሌ ወሎ የ04 እንዴት ይረሳኛል ይህማ እስቲ እኔ ደግሞ ትንሽ ላስታውስህ........ ደገፋ አብዲ, ሂደጎ,ደሱ,መላኩ ከበደ,ሃይለማሪያም አሊ,ዮሃንስ አስፋው,ሙሴ መኮነን,እዮብ ሻኖ,ሰለሞን በርሄ,ዮርዳኖስ አራያ,ዳኜ አባተ, በርግጥ ሁሉን ብዘረዝር ይህ አምድ አይበቃኝም :: ብዙ ነገር ስላስታወስከኝ ከልብ አመሰግናለሁ

ከታላቅ አክብሮትና ፍቅር ጋር ::
Diqaw Ke Kumandateba
የጁ
ጀማሪ ኮትኳች
ጀማሪ ኮትኳች
 
Posts: 82
Joined: Thu Sep 28, 2006 10:59 am

Postby የመንደራው » Sat Oct 07, 2006 8:50 pm

የጁ ሰላም ነህ ያገር ልጅ ካወራርህ የወልድያ ልጅ ትመስላለህ እኔ የወልድያ ልጅ ነኝ04 ቀበሌ አባድንሳ እስኪ እንጫወት?
የመንደራው
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 190
Joined: Thu Oct 05, 2006 1:01 pm

Postby የጁ » Sat Oct 07, 2006 9:40 pm

ወዳጄ የመንደራው ሠላም ባለህበት !!

እኔም ከደብረገሊላ ነኝ እንደዛሬ ናፍቆት ሳያጠቃኝ ስደቶች በዝተው :: እስቲ እነዚህን ሰዎች እሰባቼው ወንዳያ ሰማው,ደጉ,ኮካኮላ,ክብሪት ቀደም ካሉት ደግሞ ሞላ ተሰማ,ትምቧለል,ኩና መላኩ,ኤ ሦስቱ ኤ ::

ከታላቅ አክብሮትና ፍቅር ::
Diqaw Ke Kumandateba
የጁ
ጀማሪ ኮትኳች
ጀማሪ ኮትኳች
 
Posts: 82
Joined: Thu Sep 28, 2006 10:59 am

Postby የመንደራው » Sat Oct 07, 2006 11:05 pm

የጅ ለመልስህ በጣም አመሰግናለሁ የጠቀስካቸውን ሰወች አስታውሳቸዋለሁ በተለይ ወዳያናደጉ,ክብሪት,እርጎየን የማይረሱ ናቸው አክየ እጀራን ታውቀዋለህ ያው እግድህ በቅርቡ የወጣህ ክሆንክ ማለቴ ነው:: ያገርህ ልጅ የመንደራው::
የመንደራው
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 190
Joined: Thu Oct 05, 2006 1:01 pm

Postby እቴነሽ » Sun Oct 08, 2006 7:09 am

የመንደራው wrote:የጅ ለመልስህ በጣም አመሰግናለሁ የጠቀስካቸውን ሰወች አስታውሳቸዋለሁ በተለይ ወዳያናደጉ,ክብሪት,እርጎየን የማይረሱ ናቸው አክየ እጀራን ታውቀዋለህ ያው እግድህ በቅርቡ የወጣህ ክሆንክ ማለቴ ነው:: ያገርህ ልጅ የመንደራው::


እናንተ? እነዚህን ስሞች አይቼ ማለፍ አልቻልኩም :lol: :lol: :lol: :lol: እውነትም የወልድያ ሰዉ ናፍቆችኋል አሁን ማ ይሙት ክብሪት? ወንዳያና ደጉ? :lol:

በሉ መልካም መልካሙን ሁሉ ለእናንተ ይሁን

እቴነሽ
እቴነሽ
ጀማሪ ኮትኳች
ጀማሪ ኮትኳች
 
Posts: 91
Joined: Thu Mar 17, 2005 4:19 am

Postby የጁ » Sun Oct 08, 2006 9:04 am

ሠላም ያገር ልጆች !
እህታችን እቴነሽ :- እንኳን በሠላም ገባሽ ወደዚህ ቤት ሠው በጣም እኮ ነው የሚናፍቀው እርቆ ላለ ዜጋ እስቲ አንችን ደግሞ አንድ ሠው ላስታውስሽ መምሬ አምባዬን ታስታውሽው ነበር ? :lol: በይ መልካም ቀን ከትውስታዎች ጋር ::

ያገር ልጅ የመንደራው ሠላም ላንተ በውነቱ አክየን አላስታውሰውም ለነገሩ ሁለት አስርታት ስላስቆጠርኩ በስደቱ አለም አዲስ ከሆነ አላውቀውም በል አብሽርልኝ ዘመዴ ::

ከታላቅ አክብሮትና ፍቅር ጋር ::
Diqaw Ke Kumandateba
የጁ
ጀማሪ ኮትኳች
ጀማሪ ኮትኳች
 
Posts: 82
Joined: Thu Sep 28, 2006 10:59 am

Postby የመንደራው » Sun Oct 08, 2006 9:42 pm

እቴነሽየ ምን እናድርግ ብለሽነው ያገርሰው ሲገናኝ ቢሆንብኝ ነው ለማንኛውም ሰላም ነሽልኝ?

ያገሬ ልጆች ሰላም ሁኑ ባላችሁበት::
የመንደራው
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 190
Joined: Thu Oct 05, 2006 1:01 pm

መለሠ እና ደረጀ

Postby እሪኩም » Wed Oct 11, 2006 5:31 am

ሠላም ለሁሉም!


ካለፈው የቀጠለ:
Image

ቲንፋዝ የነበሩት መሠለ እና ሙሉ:
ጌታ እና ደረጀ - ደረጀ የታሉ:
እንደው በመታለል በሥም ተቃጠሉ::

የት አለ ጥላሁን - አምባቸው መቻሬ:
ተቃጥለው ቀሩ በነ-ሰው አይምሬ::

ሁሉም በማለፉ እኛ ብናውቀውም:
ታሪክ ለማቆሸሽ መዝለል አንችልም::

ጉባ ላፍቶ ውለን ውድበን ለማደር:
እስከ መቼ ድረስ እኛ እንወዳደር::

አንድ ነው ልባችን አንወላውልም:
ሳስቅን ውለን በከንቱ አንገልም::

ማማት መጥፎ ነገር ሰውን የሚያበላሽ:
ጣል ጣል አድርገን ለምን እንቆሽሽ::

ንጉሡ ዘገዬ ዳምጠው ሰው አራጁ:
ወይ አለማፈራቸው በሰው ሲቀልዱ::


ይቀጥላል

መልካም ቀን
እሪኩም ከቦሩ ሜዳ
እሪኩም
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 853
Joined: Fri Apr 01, 2005 1:20 am
Location: ወሎ

Postby የጁ » Wed Oct 11, 2006 11:53 am

[color=blue][/color] ሠላም ያገር ልጆች !

ውድ እሪኩም :- ገና ባፍላ ዕድሜያቼው ለፍሬ ሳይበቁ ላለፉት የለውጥ ሰማዕታት የህሊና ጸሎት እናድርስ ::

* መሠለ አራደ

* ደረጄ ፈንታው

* ጥላሁን ጉግሳ

* መሠረት በላይ

* ሙልጌታ ወርቅነህ (ከአሬሮ)

* ማሞ ይርዳው (ከመርጦ)

* ስጦት አባተ

* አበበ ቢተው

* ተሻገር አያሌው

* ሙሃመድ ታደሰ

* ሙሉ ዓለም አለሜ

እንዲሁም ብዙ ሰቆቃ ደርሶባቼው የአካል ጉዳተኛ እስከመሆን የደረሱት ::

* መጣባቼው

* ሃይሌ ኩን ኩን

* ወሰኔ አሊጋዝ

* ፍሰሃ ሃብተወልድ

ሁሌም በትውስታችን የሚኖሩ ምርጥ የየጁ ልጆች ነበሩ ::


ከታላቅ አክብሮትና ፍቅር ጋር ::
Diqaw Ke Kumandateba
የጁ
ጀማሪ ኮትኳች
ጀማሪ ኮትኳች
 
Posts: 82
Joined: Thu Sep 28, 2006 10:59 am

Postby ጣዕም » Thu Oct 12, 2006 4:36 am

የጁ;
* መሠለ አራደ
* ደረጄ ፈንታው
* ጥላሁን ጉግሳ
* መሠረት በላይ
* ሙልጌታ ወርቅነህ (ከአሬሮ )
* ማሞ ይርዳው (ከመርጦ )
* ስጦት አባተ
* አበበ ቢተው
* ተሻገር አያሌው
* ሙሃመድ ታደሰ
* ሙሉ ዓለም አለሜ
እንዲሁም ብዙ ሰቆቃ ደርሶባቼው የአካል ጉዳተኛ እስከመሆን የደረሱት ::
* መጣባቼው
* ሃይሌ ኩን ኩን
* ወሰኔ አሊጋዝ
* ፍሰሃ ሃብተወልድ

ከላይ የጠቀስካቸውን ውድ ወጣቶች ስም ሳይ ልዩ ትውስታን ጫርክብኝ:: እምባም ተናነቀኝ:: አይ! ያ ዘመን!! እግዚአብሄር ነፍሳቸውን ይማር:: አጋጣሚ ታጋይ ሀይሌ ኩንኩንን ሱዳን እያለሁ ተገናኝተን ለተወሰነ አመት ያህል እንጠያየቅ ነበር; ከተወሰነ ጊዜ በኍላ ግን ላገኘው አልቻልኩም:: አሁን የት እንዳለ አላውቅም:: እስቲ የሆነ ሰው እጠይቃለሁ::
በርቱ የአገር ልጆች::
If there is a book that you want to read, but it hasn't been written yet, you must be the one to write it.
--Toni Morrison
ጣዕም
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 231
Joined: Sat May 01, 2004 2:02 am
Location: canada

Postby ጣዕም » Thu Oct 12, 2006 5:03 am

ሮመዳን አንድ ምሽት ወልዲያ ውስጥ ያደረገውን የሚያስታውስ አለ? ላጫውታችሁ:
ሮመዳን አንድ ቀን ከጓደኞቹ ጋር ከጫት ምርቃና በኍላ የደንቡን ለማድረስ ወደ መጠጥ ቤት ጎራ ብሎ ጠጁን አረቂውን ሲጨልጥ መከረኛ ስአት እላፊ ይደርሳል:: ታዲያ አቶ ስካር እያደፋፈረው ደረቱን ወጥሮ እነኛን ጭፍጋግ አብዮት ጥበቃ ጓዶች ንቆ ወደ መሀል መንገድ ጉዞ ሲጀመር; ቁም ማነህ? እንዳትንቀሳቀስ? የሚል ድምፅ ሲሰማ እግሬ አውጪኝ ብሎ መሮጥ: እንደተከታተሉት ሲያውቅ ዜዴ ፈለገ; ጨለማ ወዳለበት በመጠጋት በእጁ የያዛትን የሲጋራ ቁራጭ ከግንብ አጥር ላይ ሰክቶ ሮጠ; ጥበቃ ጓዶቹም በርቀት የሚያዩትን የሲጃራ ቁራጭ በማየት ሮመዳን የቆመ መስሏቸው ተጠጋ ወዲህ! እንዳትንቀሳቀስ! ተንበርከክ! በደረትህ እየተሳብክ ወደኛ ተጠጋ! ወዲህ ና ነው የምንልህ! እያሉ ሲጯጯሁ ቆይተው ወደ ቁራጭ ሲጃራዋ ቢጠጉ የሲጃራ ቁሮ ሆና ተገኘ:: አይ ሮመዳን ስንት ትዝታ ነበር::
ሰላም ሁኑ
If there is a book that you want to read, but it hasn't been written yet, you must be the one to write it.
--Toni Morrison
ጣዕም
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 231
Joined: Sat May 01, 2004 2:02 am
Location: canada

Postby የጁ » Thu Oct 12, 2006 11:30 am

ሠላም ያገር ልጆች !

ወዳጄ ጣዕሜ :- ሠላም ባለህበት የሃይሌ ኩን ኩንን አድራሻ ካገኘህ በፕራይቬት ብትጽፍልኝ ምስጋናዬ እጅግ የቀ ይሆናል ከላይ እንደጠቀስከው ያ ዘመን ተመልሶ የማይመጣ ሆነ እንጅ እንዴት አሳዛኝም አስደሳችም ወቅት ነበር,ያለፈውን በነበር እያስታወስን መጭውን ደግሞ በተስፋ ከመጠበቅ የተሻለ ነገር የለምና..... ስለ ሮሜ የጻፍከው ከልብ ነው ያሳቀኝ ሮመዳን መሃመድ አሪፍ የኮሜዲ ሠው ሆኖ ሳለ ነገር ግን በሙያው ሳይገፋበት በመቅረቱ እነ መፋቅር ድንቁ የደረሱበት ቦታ ላይ መድረስ ሳይችል ቀርቷል ::

እኔን ትዝ ከሚለኝ ባንድ ወቅት የወልድያ ከተማ የኪነት ጓድ ጋር በሚሰራበት ሳዐት "የመረረው ሲነሳ" የሚለውን ድራማ ሲሰሩ ሮሜ በተሰጠው ገጸ ባህሪ ላይ ሆኖ እየሰራ እያለ ባንጻሩ ደግሞ የለውጥ ፈላጊ ሆኖ ከሚሰራው ልጅ አንደበት "የመረረው ሲነሳ" የሚለውን መፈክር አንግቦ ሲፎክር ሮሜ ከአረእስቱ ውጭ የራሱን ፈጠራ በመጠቀም "የጣፈጠው ቁጭ አለ" ሲል አብረው እየሰሩ ያሉት ሰዎች የተናገረው ከተሰጠው አርዕስት ውጭ በመናገሩ ትንሽ ቢደናገሩም በዋና አዘጋጅው ግን ከፍተኛ አድናቆት ተበርክቶለት ነበር ::

ወልድያ ዛሬ ምን ላይ እንዳለች ሄጄ የማየት እድሉን እየጠበቅኩ ነው :: ሌላው ወልድያ ውስጥ ከነበሩት እንስቶች በጣም የሚገርመኝ ዙሪያሽ አሰፋ,ፈትለወርቅ ተሾመ,አቻንየለሽ ጫኔ ሊዛ ሃሰን ሁሌም ወጣት እየሆኑ የሚሄዱ ሴቶች ነበሩ እነዚህን ሴቶች እኮ እኔ ሳውቃቼው ስንት አስቆጥረዋል እኔ በጣም አርጅቻለሁ በነሱ አይን ስታይ እንዲያው ይገርማል አሁንስ አርጅተው ይሆን ?


ከታላቅ አክብሮትና ፍቅር ጋር ::
Diqaw Ke Kumandateba
የጁ
ጀማሪ ኮትኳች
ጀማሪ ኮትኳች
 
Posts: 82
Joined: Thu Sep 28, 2006 10:59 am

Postby ዶኑ » Thu Oct 12, 2006 5:01 pm

ውዱ የጁ!

ሰላሙን እመኝልሀለሁ! ቤትህን እንዴት እንደወደድኩት

ልነግርህ አልችልም:;ወገን! የየጁ ትዝታ መች እንዲህ

በዋዛ የሚረሳ ሆነ: አየር ላይ ተንሳፍፌ ቀረሁ እኮ!!

ክረምት ክረምቱን ውንድሜ ጋ ለማሳለፍ ወልድያ

እየመጣሁ አገኘው የነበረውን ደስታ የሀብታሞች ቁንጮ

የቢልጌትን አካውንት ለኔ ቢያዞሩልኝ ሊተካልኝ አይችልም::

እነ ወንዳያና ደጉን ባላውቃቸውም በጣም የሚዋደዱና

የማይለያዩ ጓደኛሞችን የሚያይ ሰው "ወንዳያና ደጉ" ብሎ

እንደሚጠራቸው አስታውሳለሁ:: ትዝ ከሚሉኝ ብዙ

ነገርች ውስጥ አንዱ ደግሞ የ10 አለቃ አባዲ መንገሻ

ጉዳይ ነው:: የየጁ አስተዳዳሪ ተብሎ ሰዉ እንዴት

ይፈራው እንደነበረ ሳስበው ይገርመኛል:: አሁንስ ምን

ተደርጎ ሆን? በተረፈ ወልዲያ ተምረው ውለው ወደ

እየአቅጣጫው በተለይም ወደ ስሪንቃ አቅጣጫ የሚመለሱ

ቆንጅዬ ተማሪዎችን እድሉ ሲቀናን ማስተናገድ ሳይቀናን

አጫውተን መሸኘታችን የማይረሳኝ ውብ ትዝታዬ ነው:

እዚያ አከባቢ ሁል ጊዜ የማይጠፋና ያስፈራራርን የነበረ

አንድ ጥቁር ጥንዝዛ የመሰለ የትንፋዝ ልጅ አስማረ

የሚባል አይረሳኝም : ስለ እርሱ የሚያውቅ ካለ ትንሽ

ቢያጫውተኝእንዴት ደስ ባለኝ: በተረፈ ሌሎች ብዙ

ትዝታዎቼን ይዤ እንደምመለስ ተስፋ ተስፋ አደርጋለሁ:

የጁዬን በድጋሜ አመሰግንሀለሁ:
TO DOUBLE YOUR JOY DIVIDE IT BY TWO
ዶኑ
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 411
Joined: Fri Apr 01, 2005 5:31 am

Postby የጁ » Thu Oct 12, 2006 8:53 pm

ወንድም ዶኑ !

ባለህበት ሠላም እና ፍቅር ካንተ አይለዩ እያልኩ በቅድሚያ አመሰግንሃለሁ:: ያገር ልጅ :- እኔም እዚች ደሳሳ ጎጆዬ ብቅ ብቅ እያሉ ስለ የጁ ያላቼውን ትዝታ ጨለፍ አድርገው በሚያጫውቱኝ ሰዎች እጅግ በጣም ደስተኛ ነኝ :: ወንዳያና ደጉን የሚያውቁ ሰዎች የመልካም ጓደኛሞች ተምሳሌት ያደርጋቼው ነበር በርግጥ የማይለያዩ ሁለት ያንድ ሳንቲም ግልባጭ ነበሩ ብል የተሳሳትኩ አይመስለኝም ነፍስ ይማር ::

ካለሁበት ሀገር የወንዝ ልጆች አንዳንድ ጊዜ ተሰባስበን ስላገር ስናወራ "አስማረን" አንዳችንም አስታውሰነው አናውቅም ነበር አሁን ግን አንተ ስትጠቅሰው ጥቁረቱ መልኩ እንዳለ ፊቴ ላይ መጥቶ ምስሉ ተገተረ :: አስማረ ቄራ(የጥቁር አልማዝ) ይሉት ነበር የማይረሳኝ ልጅ ነበር,ግን እኮ እሱ ልጅ ብዙም ጉልቤ አልነበረም ይልቅስ "አባተ" የሚባል ካስታወስከው ቲንፋዝ ነበር ቤቱ ታዲያ ስታየው እራሱ ፊቱ ያስፈራሃል በጣም ተደባዳቢ ነበር ሴቶችን በተለይ በደፈጣ ነበር የሚጠብቃቼው ሁለት ቦዲ ጋርድ ያላስከተለች ሴት አለቀላት ነው :: ከማስታውሰው ዘውዴ ወርቁ የምትባል ልጅ ብቻዋን በዛ ስታልፍ አግኝቷት ተሼክሞ ወደ ሼሌ ወንዝ ወስዶ ያደረጋት አድራጎት የከተማው መነጋገሪያ ሆኖ ነበር ::

ከስሪንቃ የሚመጡ አልክ....... በውነቱ የማልዘነጋት ልጅ አቻምየለሽ አባተ የዛች ልጅ ቁንጅና ለየት ያለ ነበር አሁን ስቴት ውስጥ ነው የምትኖረው ብቻ ባጠቃላይ ከስሪንቃ የሚመጡ እጅግ በጣም ውበትን የተላበሱ ነበሩ::

አሁንም በድጋሚ አመሰግንሃለሁ ወንድም ዶኑ መልካሙ ሁሉ አይለይህ ::

ከታላቅ አክብሮትና ፍቅር ጋር ::
Diqaw Ke Kumandateba
የጁ
ጀማሪ ኮትኳች
ጀማሪ ኮትኳች
 
Posts: 82
Joined: Thu Sep 28, 2006 10:59 am

PreviousNext

Return to Warka Intimate - ዋርካ ፍቅር

Who is online

Users browsing this forum: Google Adsense [Bot] and 12 guests