***የየጁ ኩማንዳ ጠባ ልጆች***

The Love Forum (love, relationship) (የኔ ቆንጆ እንተዋወቅ :-)

Postby ዶኑ » Thu Oct 12, 2006 9:45 pm

በውነቱ የማልዘነጋት ልጅ አቻምየለሽ አባተ የዛች ልጅ ቁንጅና ለየት ያለ ነበር አሁን ስቴት ውስጥ ነው የምትኖረውአቤት የጁዑዑዑዑዑ!..................ምን ጉድ ነው የምታሰማኝ? አቻም የለሽንማ በደንብ ነበር የምቀርባት: አባቷ እኮ በጣም የተከበሩና ታዋቂ የነበሩ ከሌላ ባላንጣቸው ጋር ተዋግተው የሞቱ አባተ ህይሉ የሚባሉ ናቸው ሲባል ሰምቼአለሁ:: ለመሆኑ ልጅቱ የትኛው ስቴት ውስጥ ይሆን የምትኖረው? አድራሻዋን አውቄ ሰላም ባልኳትና በተሳሳቅን ! ለማንኛውም የጁ በጣም በጣም አመሰግንሀለሁ! እወድሀለሁ ቻውውውውውውውው!
TO DOUBLE YOUR JOY DIVIDE IT BY TWO
ዶኑ
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 411
Joined: Fri Apr 01, 2005 5:31 am

Postby ጣዕም » Fri Oct 13, 2006 4:26 am

ሰላም የአገር ልጅ የጁ
የሀይሌ ኩንኩንን አድራሻ እንዳገኘሁ ያው ሹክ እልሀለሁ:: በብዛት ስለወልዲያ ከተማና ልጆች ትዝታ ይኑረኝ እንጂ ከአምባሰል እየተንደረደርኩ ነበር ወልዲያን የማወቀው:: ኑሬበታለሁም:: ሲሪንቃና መርሳ ደግሞ የዘመዶቸ አገር ነው:: እንደውም የሆነች የሲሪንቃ ልጅ ስምና ውበት ስታነሳ ልቤ ተርከክ አለ:: ቅቅቅቅ ብቻ እንዳላውቃት::
ከአንድ ከስድስት አመት በፊት አቻንየለሽ ጫኔ ካናዳ መጥታ ነበር:: የምትኖረውም አውስትራሊያ መሰለኝ ካልተሳሳትኩ:: ሳቋ ፈገግታዋ ውበትዋና ኪነጥበባዊ ችሎታዋ እንዳለ ነው:: የአካባቢዋ ልጆች ተሰባስበን የካናዳን የገብስ ጠላ እየኮመኮምን ከእሪኩም እስከ አማሬዋ እያዜመች ስታዝናናን አመሽች እልሀለሁ:: መቸስ ምድር ቃጤ! ሆነች ነው የምልህ:: ምነው ይህ ሁሉ ተሰባስበን አገር ላይ ቢሆን? አንድ ቀን አይቀርምምም
እንደው ለመሆኑ አጀብነሽ አድማሱንስ የሚያስታውስ አለ: ስፖርትትት ድምፅ ተስፋየስ? እረ ስንቱ
"እረ ምንይሻለኝ ወዳጄ; እረ ምንይሻለኝ ወዳጄ
ወዴት ጠፋሺብኝ ገንዘብ ሳጣ በጄ::"
የሚለውን ዘፈን ማን ነበር የዘፈነው? ከድሮ ኪነት አባሎች ካስታወሳቸሁ? ምልክቱ መነጸር የሚያደርግ ነበር::
እስከዛው መልካም ጊዜ
If there is a book that you want to read, but it hasn't been written yet, you must be the one to write it.
--Toni Morrison
ጣዕም
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 231
Joined: Sat May 01, 2004 2:02 am
Location: canada

Postby የመንደራው » Fri Oct 13, 2006 10:39 pm

የጁ,ጣዕም,እዲሁም ዶን ሰላም ሁኑ ባላችሁበት
ጨዋታችሁ በጣም ይጥማል በአብዛኛው የእናንተ ትዝታ በጣም አሪፍ ነው::

የጁ ወልድያ በቅርቡ እዳየሁት ከሆን በአሁኑ ወቅትበጣም እየተለወጠች ነው ያው እግዲህ እደምታውቀው ደብረገሊላ በአብዛኛው የዱሮ ቤቶች ነበሩ እነሱ እየፈረሱ በህንዻ እየተለወጡ ነው ትልልቅ ሆቴሎችም ተሰርተዋል ሰላም ሆቴል ላል ሆቴል እዲሁም መቻሬ ሆቴል የማስታውሳቸው ናቸው::
የጁ የወልድያ የመጀመርያ ሆቴል ታስታውሰዋለህ ? ከቶታል ጎን ያለው ኢትዮዽያ ሆቴል እዳለ ነው ምንም ለውጥ የለውም ::

ከታላቅ አክብሮት ጋር የመንደራው
የመንደራው
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 190
Joined: Thu Oct 05, 2006 1:01 pm

Postby ሲሞሎ » Fri Oct 13, 2006 10:53 pm

የጁ እሳት ይዙዋል በጁ የተባለውን : አብራሩልኝ የጁዎች :
ENTEYAYALEN
ሲሞሎ
ጀማሪ ኮትኳች
ጀማሪ ኮትኳች
 
Posts: 55
Joined: Tue Oct 10, 2006 10:18 pm
Location: baku

Postby የጁ » Sat Oct 14, 2006 11:56 am

ሠላም ያገር ልጆች !

ወንድም ዶኑ :- የቀኛዝማች አባተ ሀይሉ ልጅ አቻምየለሽ ከስድስት አመት በፊት ሳውዲ አረቢያ ጀዳ እንደነበረች አስታውሳለሁ ከዛ በኋላ ወደ ስቴት መሄዷን የሰማሁ ቢሆንም በየትኛው ስቴት እንደምትኖር አላወቅኩም ነገር ግን ወደፊት ባጋጣሚ ካወቅኩ ልጠቁምህ እፈቅዳለሁ ያገር ወሬ እንድትኮመኩሙ :: እነ ደስታን ጽጌን.... ታስታውሳቼዋለህ ? ውድ ዶኑ እኔም በጣም እወድሃለሁ

ውድ ጣዕም :- በጣም ነው የማመሰግንህ :: አቻምየለሽ ጫኔ ሆላንድ እንደምትኖር እሰማ ነበር በርግጥ ይህ ከረጅም ጊዜ በፊት ነበር ከዛ አድራሻ መቀየሯን ሰማሁ በጣም ተቻዋች ልጅ እንደነበረች ይነገራል ወንድሟ ጳውሎስም እንደዚሁ ተጫዋች ነበር :: ድምጹ ተስፋየ በጊዜው ታዋቂ የእግር ኳስ ተጫዋች ነበር ከላስታ ከሰቆጣ አካባቢ መጥተው ወልድያ ተምረው እዛው በሥራ መስክ ተሰማርተው የሚኖሩ ድምጹን ጨምሮ ንጉሴ ታከለ,ደባሹ,ቢንያም ሃይሌ,ወርቃፈስ አስፋው,ኪሮስ ደስታ,...የሚባሉ ነበሩ :: እረ ምን ይሻለኝ ወዳጄ** ወዴት ጠፋሽብኝ ገንዘብ ሳጣ በጄ የሚለውን ያንጎራጎረው መምህር እሼቱ ባለ መነጠሩ ነበር ባልሳሳት ከወልድያ ኪነት ጓድ ጋር :: ነጋሽ ፈለቀንና ታምሩን ካስታወስክ እርግጠኛ ነኝ እነ ዘገዬ ጎርፌ,አምታታው,ማርቆስ ከበደ,መርጌታ ጌጡ (አባ),መምህር ህሩይ,አሰፋ አባተ (ማሲንቆ) ታስታውሳቼው ይሆናል :: ከውርጌሳ እየመጡ ይማሩ ከነበሩ ልጆች ዘውዱ ታደሰ,እጅጋዬሁ,ዘውራ አሊና ወንድሟ አሁን እንኳ በህይዎት የሉም ይታወሱህ ይሆን ?
ሀይቅ,ውጫሌ,ጢስ አባሊማ የፍራፍሬው መንደር ከአእምሮዬ አይጠፉም ::

ወዳጄ የመንደራው :- የወልድያን ያሁኑ ገጽታዋን ስላሳወቅከኝ እጅግ በጣም አመሰግናለሁ :: እርግጠኛ ነኝ ከዚህም በላይ ታድጋለች ያች ከተማ,የላል ሆቴል ባለቤት የላሊበላ ልጅ ተዋበ ፋንታ ነበር አሁንም በሱ ሥር የሚተዳደር ከሆነ በውነቱ ብዙ ገንዘብ አፍስሶ እንደዛ አይነት ሆቴል ለከተማችን ውበት መስራቱ በጣም የሚያስመሰግነው ነው :: ማን ያውቃል አንድ ቀን ሄጄ አየው ይሆናል ኢትዮጵያ ሆቴል ባለቤቱ አቶ ግርማይ አባዲ ነበሩ ባብዛኛው ጊዜ ውሎዬ እዛ ነበር እዛ ሆቴል ውስጥ በአርቲስት በላይ ጎርፉ የተሳሉ ድንቅዬ ሰእሎች ነበሩ :: እንደው በዚህ አጋጣሚ "ይርዳው ሰፈር" ፈርሶ ይሆን ? አይ ያ ቀውጢ ቦታ,, ንጥፍ ድንጋይ አሁን ካልደረቀ በክረምት ጊዜ ከገብርኤል ተንደርድሮ የሚወርደው ውሃ ከተማዋን የሚያጥለቀልቅ ነበር የሚመስለው :: በተቀራኒው ደግሞ የኮሬ እና የጉባርጃ ተራራዎች አረንጓዴ ለብሰው ከተማዋን አስውበው ይታዩ ነበር :: አንድ ጊዜ ጉባርጃ ማሪያም የሚከበርበት ቀን ከአንድ ጓደኛየ ጋር ያንን ተራራ እንዴት እንደወጣነው አሁን ሳስታውስ ምን ያክል ጠንካራ ቢሆኑ ነው የአካባቢው ሰዎች ጥዋት ተነስተው ወልድያ ውለው ማታ መመለስ የሚችሉት ::

ያገር ልጅ ሲሞሎ :- ሠላም ላንተ ይሁን :: የጁ እሳት ይዟል በእጁ ለሚለው እሪኩም ከላይ መጠነኛ ማብራሪያ ሰጥቶበት ነበር እስቲ ከፍ ብለህ በገጽ ሁለት ያለውን አንብበው በተረፈ መልካም ቀን ይሁንልህ ::

ከታላቅ አክብሮትና ፍቅር ጋር ::
Diqaw Ke Kumandateba
የጁ
ጀማሪ ኮትኳች
ጀማሪ ኮትኳች
 
Posts: 82
Joined: Thu Sep 28, 2006 10:59 am

ትዝታ

Postby እሪኩም » Mon Oct 16, 2006 7:22 am

ሠላም የጁ!

ስለ የጁ - እና - አካባቢዋ ቆንጆ ነው የምትተርከው:: በጣም ደስ ይላል::

ስለ ተለያዩ ሰዎች ስም ስትጠቅስ ትዝታዬ ጨመረ:: እንደ አሰፋፈርህ ከሆነ የአንድ ዓመት ምርቆች መስለከኝ:: እስቲ ወደፊት ብዙ እንጫዎታለን::

ዘቡራ ዐሊ የአህመድ እና የፋጡማ እህት - ታሪከኛ ቆንጆ ውብ ልጅ ነበረች:: ፋጡማ የኑሩ ዐብድል ዐለም ባለቤት አትረሳኝም:: ኑሩ ዐብድል ዐለም ፎቶ ቤት እና መለስተኛ ሱቅ ነበረው:: ዐብረን ስንማር በብዙ መልኩ የማስታውሰው እና ጥሩ ሥነ ምግባር ያለው ልጅ ነው:: የዐባቱ ሻይ እና ቁርስ ቤት - ከሳምቡሳ ጀምሮ መስተንግዶው አሁንም ከዐእምሮዬ አይጠፋም::

ወንድሙ እና ንጉሴ ግሮሰሪዎች ምን ይመስሉ ይሆን? ፀሐይነሽ እና አበበ አስቴላን ታስታውሳቸዋለህ?

መፋቅር እና ሮመዳን ደስ የሚሉ ከያኔዎች ናቸው:: ወገኔ እና አዋሽ - የጂኦ ግራፊ ሸዋዬ ተካ የዐማርኛ ጎድፍ ዐለሙ የእንግሊዘኛ የመሳሰሉት መምህራን ይታወሱኛል:: ዐበበ ቢተውን እና ጎድፍን ጥይት በላቸው::

ተሻገር ዐያሌው - ጥላሁን እና ዐምባቸው የታወቁ የወጣቶች መሪ እና አስተዋይ አርቲስቶች ነበሩ:: ለእኛ ብለው ቁመና እና ውበት ይዘው ተሰዉ::

የውርጌሳው ሽፈራው አበበ ስምንት እና በላይ ዐመታት ታስሮ እና ተሰቃይቶ ወጣ:: የጥቁር ኮከብ የእግር ኳስ ቡድን አይረሳኝም::

አስር ዐለቃ አባዲ መንገሻ ግንፍልተኛ ይሁን እንጂ የሃብሩ ወረዳ ወጣቶችን አንድም ለጥይት አልዳረገም:: ከካድሬዎች ጋር ሲዋጋ እና ሲፋለም ደስ የሚል አባት ነበር:: ነውም:: የየጁ አውራጃ አስተዳዳሪም ሁኗል:: ታሪኩን ሥራ እና ህዝቡ ይመስክራል::

ወይ ጣዕም በዬት በኩል ከተፍ አልክ ጃል? ይልመድብህ::

መልካም ጊዜ ለሁላችሁ
እሪኩም ከቦሩ ሜዳ
እሪኩም
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 853
Joined: Fri Apr 01, 2005 1:20 am
Location: ወሎ

Re: እየመጣሽ ቃኚን

Postby ሾተል » Tue Oct 17, 2006 3:28 pm

እሪኩም wrote:ሠላም ሀዱድ!

የጁ እሳት ይዟል በእጁ - ለሚለው ሰፋ ያሉ መግለጫዎች ከየጁ እና ከሌሎች ታዳሚዎች እስከሚገኝ ድረስ በአጭሩ እንደዚህ ለመመለስ እሞክራለሁ::

የጁ አውራጃ ሁለት ወረዳዎች አሏት:: ሓብሩ እና ጉባላፍቶ::

ለቀዳማዊ ኃ/ስላሴ መንግስት አገዛዝ አመች ያልሆኑ መሳፍንት መኳንንት እና ነፍጠኞች የፈለቁባት አውራጃ ስለነበረች በጥቅሉ ህዝቡን መዋጋት እና ማስተዳደር ስላልተቻለ "የጁ እሳት ይዟል በእጁ" በማለት ኃይለ ስላሴ እና መሰሎቻቸው ተናገሩ - ተነበዩ:: የጁ ለሠላም እንጂ ለጠብ አይመችም::

አንቺን እኔ አይቼ መቼ እለቅሻለሁ:
አሸን ክታብሽን ሃራ አስጥልሻልሁ::

ብቅ ብለሽ አጫውችኝ ለምን ትፈሪአለሽ:
መጎንተል አልችልም እስቲ ልጠቃቅስሽ:
መርሳ አባ ጌትዬ - አሉልሽ አይዞሽ::


በይ አትጥፊ - እየመጣሽ - ቃኚን
እሪኩም ከቦሩ ሜዳየየጁ አንዱ አውራጃ ጉባላፍቱ ነው ነው ያልከው???እስቲ በጉባላፍቱ ውስጥ ስለሳንቃ ዘወር ጎተራ ሚካዬልና ስለ ጠዶት ማርያም እሪኩም ሆንክ ለሎች ንገሩኝ?ያቺ ቦታ እትብቴ ሳይቀበርባት ቀርቶ ይሆን ምንም ባላውቃትም?አደራ የምታውቁትን ጣል ጣል አድርጉና ስለአመጣጤ ንገሩኝ...
ሾተል
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 9653
Joined: Thu Jan 13, 2005 9:42 pm
Location: Vienna-Austria

Postby ሾተል » Tue Oct 17, 2006 3:54 pm

ወልደያ ሰጥዋ በለውን የሚያውቅ አለ?
ሾተል
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 9653
Joined: Thu Jan 13, 2005 9:42 pm
Location: Vienna-Austria

Postby ዶኑ » Tue Oct 17, 2006 7:00 pm


ንድም ዶኑ :- የቀኛዝማች አባተ ሀይሉ ልጅ አቻምየለሽ ከስድስት አመት በፊት ሳውዲ አረቢያ ጀዳ እንደነበረች አስታውሳለሁ ከዛ በኋላ ወደ ስቴት መሄዷን የሰማሁ ቢሆንም በየትኛው ስቴት እንደምትኖር አላወቅኩም ነገር ግን ወደፊት ባጋጣሚ ካወቅኩ ልጠቁምህ እፈቅዳለሁ ያገር ወሬ እንድትኮመኩሙ :: እነ ደስታን ጽጌን .... ታስታውሳቼዋለህ ? ውድ ዶኑ እኔም በጣም እወድሃለሁ


የጁ! ሠላምታዬ ይረስህ:

ቤትህ ትዝታ ቀስቃሽ ክመሆን አልፎ አዝናኝ ሆኖ አግኝቼዋለሁ:: በጣም ደስ ይላል:: የየጁ ጥንቅሾች አንድ ላይ ተሳባስበው ሲጫወቱ መስማትን ያህል የሚያስደስት ምን ነገር አለ? ወልድያን ባላድግበትም በጣም እወደዋለሁ: ዘመድ ለመጠየቅ እየመጣሁ የማሳልፋቸው ጊዜያት በሙሉ ጥሩ የደስታና የእርካታ ጊዜያቶቼ ነበሩ ብል ማጋነን አይሆንብኝም :: እነአቻምየለሽ መሰሎች ጋር ጊዜ ማሳለፍ ምን አይነት ደስታ ሊሰጥ እንድሚችል ላንተ ምኑ ይነገራል?... እንዲያው ዝም እንጂ!

አቻምየለሽ ብዙ ጊዜ ከብዙ የሴት ጓደኞቿ ጋር ስለማያት የጠቀስካቸውን ልጆች በስማቸው ለይቼ ለማስታወስ ባልችልም አውቃቸው ይሆናል :: እኛ አከባቢ የሆነ ዘመድ ብጤ የሆኑ ሰዎች ስለነበሩአት ብዙ ጊዜ ወደዚያው ትመጣ ነበር: አንዳንዴም ወንድሜ ነው የምትለው ወጣት ልጅ ያጅባት ነበር:: እርሱ በሌለበት ሰአት በደንብ ነበር የምንጫወተው::ከጓደኞችዋ በተለይ አንዲት ከውካዋ የሆነች ምቀኛ (አባይነሽ/አልማዝ) ? እንደ ወንድ ጓደኛ እየቀናችባት ብዙ እንድናወራ እንኳ እድል አትሰጠንም ነበር::ልጅ ስለሆነ ሌላ ነገር አያስብም እያለች እንደሆነ እንጃ እንጂ ፍሪ ሆና ነበር ትቀርበኝ የነበረው:: ብቻ ምንም ይሁን ምን ባለችበት ሁሉ መልካሙን እመኝላታለሁ::

የጁዬ መቼም ብዙ ለፈለፍኩኝ አይደል? :lol: የየጁ ት.......ዝ......ታ መች እንዲህ በዋዛ!

ቻው የጁዬ!


ሌሎቻችሁም እስቲ እንዴ እኔ ትዝታችሁን አሰሙልን
TO DOUBLE YOUR JOY DIVIDE IT BY TWO
ዶኑ
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 411
Joined: Fri Apr 01, 2005 5:31 am

Postby የጁ » Wed Oct 18, 2006 12:44 pm

ሠላም ያገር ልጆች !

ሠላም እሪኩም :- አበበ አስቴላን በጣም አስታውሰዋለሁ የጀሪካን ጠጅ ቤት ባለቤት ምኑ ነበረች ?

የአባ ሼሁን ባስትኒና ዶልች በልቶ ያላደገ የለም አይ ያ ዘመን....

መምህር ደመቀ (ወገኔ) የደምቄን ፈተና የማይደፍን ተማሪ አልነበረም በፈተና ሳአት ታዲያ ጋሼ ሁለተኛውን ጥያቄ ቢያነቡልኝ ብለህ ከጠየቅከው ደመቀ ውሼት አያውቅም ብሎ ነበር የሚመልሰው ታዲያ ተማሪው ስለሚያውቅ የጥያቄውን መልስ እውነት እያልክ መመለስ ነው :: የደመቀ ፈተና እውነት ወይንም ውሼት ብለህ መልስ ብቻ ነው ደረቅ ጥያቄ የሚባል አያመጣም ነበር :: ታዲያ አንዴ ወይዘሮ ማናህሎሽ የቅዱስ ሚካኤል ቡና ቤት ባለቤት ምስሏን በትልቁ እንዲስል በጠየቀችው መሰረት በጣም ቆንጆ አድርጎ ሰርቶ ሄዶ ሲሰጣት የሃብታም ነገር አቶ ደመቀ እዚህ አፍንጫየ አካባቢ ትንሽ ቢያስተካክሉት ማለት ለነገሩ የሚስተካከል ነገር ኖሮት ሳይሆን እንደው እንደዚሁ ልናገር ብላ ነበር እንደዛ ያለችው ታዲያ ደምቄ እንደዛ ተጨንቆና ተጠቦ የሰራውን ሰእል ከፊቷ ቀዶ ደመቀ የሰራውን ማፍረስ መብቱ ነው ብሏት ሄደ መቼም ደመቀን የሚያውቅ ያውቀዋል ::

ወንድሜ ሾተል ሣንቃና የሼንኮር አገዳው አብረው የሚታወሱ ሁሌም የሚዘከሩ ናቸው :: ያን ስንቱን ቻይና የበላውን የድልብን ተራራ ሳንቃ ላይ ሆነው ሲያዩት ማራኪ ነው :: ሰጥዋ በለውን ላስታውሳት አልቻልኩም እስካሁን እስቲ እኔም ሰው ልጠይቅህ ከፍ ዝቅን ታውቃት ነበር ?

ወዳጄ ዶኑ :- እንዳልከው አቻምየለሽ ጋሻና ጃግሬዋ ብዙ ነበሩ ቅቅ ለነገሩማ የቀኛዝማች ልጅ እንደዛ አይነት ውበት ታክሎበት /አልማዝን አስታወስኳት ግን ያች ልጅ ከቅላቷ በስተቀር ፊቷ የወንድ ፊት ነበር የሚመለው እጢ መነፈላ ሆና አስቼግራህ ነበር አይደል ቅቅ መርሳም ቆንጆዎች ነበሩ ወላንሳ እሼቴ የምትባል እንዲሁም ሃዋ ጎበዜ ከውርጌሳ አንድ ሰሞን ወጣቱን አነሁልለውት ነበር::


ከታላቅ አክብሮትና ፍቅር ጋር ::
Diqaw Ke Kumandateba
የጁ
ጀማሪ ኮትኳች
ጀማሪ ኮትኳች
 
Posts: 82
Joined: Thu Sep 28, 2006 10:59 am

ጉባላፍቶ - ሓብሩ

Postby እሪኩም » Sun Oct 22, 2006 12:30 am

ሠላም የጁ!

የጠጅ ቤቱ ባለቤት - የአበበ አስቴላ እናት ናቸው:: ካልተሳሳትኩኝ በስተቀር:: ሁሉንም እንደ ነበረ ስታስቀምጠው - ትዝታው ይመጣና ያንዣብባል:: ደስ ይላል:: ያለፈውን ማስታወስ ለወደፊቱ እርምጃ አስተዋጽኦ ያደርጋል::

መቶ አለቃ አራጋው - የአውራጃው አስተዳዳሪ - ትዝ ይሉሃል:: ወ/ሮ ጣይቱ ብጡል ት/ቤት ግቢ ውስጥ ጠቅላላ ወጣቱ ተሰብስቦ የሰጡት ታላቅ እና የየዋህ አንደበታቸው ይታወሰኛል:: "ልጆቼ እናንተ ይቺ ወፍ ያለባትን ብር እያያችሁ ብር ስትሉ ብር ብላችሁ እንዳትቀሩ - ብሯን ከነወፏ እኛ ማጥፋት አለብን - አትሳሳቱ - አትወናበዱ" አሉ:: ብለዋለም::

የኮሎኔል ተፈራ ውብ ቆነጃጅት ልጆች "እሌኒ እና ማርታ" በአይኔ ይመጣሉ::

Image
የየጁን ውበት ማዬቱ ይበቃል::

ሠላም ሾተል!
የጁ ውስጥ ሁለት ወረዳዎች ነበሩ:: የዛሬውን በውል ባላውቀውም:: ጉባላፍቶ እና ሃብሩ የታወቁ የጀግና አካባቢዎች ናቸው:: ሳንቃ የሸንኮራ አገዳ እና ለምለም የማምረቻ ትንሽ ከተማ ናት:: ጥቁር ውኃ (ወንዝ) አቆርጧት ያልፋል:: ሳንቃ እና አካባቢዋ ለኑሮ አመች ስለሆነ ሁሉም ይመኟታል:: እስቲ ብቅ ብለህ ቃኛት ጃል::

መልካም ቀን
እሪኩም ከቦሩ ሜዳ
እሪኩም
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 853
Joined: Fri Apr 01, 2005 1:20 am
Location: ወሎ

Postby ችክላቨር » Sun Oct 22, 2006 2:43 am

የኮሎኔል ተፈራ ውብ ቆነጃጅት ልጆች "እሌኒ እና ማርታ " በአይኔ ይመጣሉ
እሪኩም! አንተ አመዳም እና ምን ልታደርግ ነው ቢያምሩህ?? ዋ ብላለች አሞራ እየው ነገርኩህ በእጄ እንዳትሞት:: ይሄንን መንቀልቀልህን ብታቆም ደህና ይመስለኛል:: ደግሞ ልጆቹ ካንተ ጋር አይመጣጠኑም :lol: :lol: :lol: :lol: :lol: :lol: :lol: :lol: :lol:
I love habesha women
ችክላቨር
አዲስ
አዲስ
 
Posts: 44
Joined: Fri Oct 20, 2006 9:10 pm

Postby የጁ » Sun Oct 22, 2006 9:17 pm

ሠላም ያገር ልጆች !

ወዳጄ እሪኩም :- አሁን አስታወስኩ እኔም ወይዘሮ እናኑ ጀሪካን ለካስ እናቱ ኖረዋል ::

የኮሎኔል ተፈራ ልጆች አዜብ, ኢሌኒና እርብቃ ቆንጆዎች ነበሩ እነሱስ እንደኛ ስደት ላይ ይሆኑ ?

ወድ ችክላቨር :- ከምር በጣም ቆንጆዎች ነበሩ ::


ከታላቅ አክብሮትና ፍቅር ጋር ::
Diqaw Ke Kumandateba
የጁ
ጀማሪ ኮትኳች
ጀማሪ ኮትኳች
 
Posts: 82
Joined: Thu Sep 28, 2006 10:59 am

ባንቺው መጀን እና እያለ መጋሎ

Postby እሪኩም » Sun Oct 22, 2006 10:57 pm

ሠላም ለሁሉም!

ችክላቨር - ምን ታስፈራራኝ አለህ---:-) ዘወር ብለህ ብትቃኘው - ታሪኩ የቆየ ነው --- ካሰኙህ ፈልገህ አግኛቸው!----ቢሆንም ሩጫ እና ዝላይ ካልቻልክ ዋጋ የለውም ---- ብዙም አትልፋ:: ቆንጃጅት ተይዘዋል:: ለማንኛውም ሞክር---:-)

ሠላም የጁ!

ስለ እሌና እና ማርታ + እህቶቻቸው - በእውነቱ ከሆነ ምንም ፍንጭ የለኝም:: ለመፈላለግ እሞክራለሁ::

ጣዕም - ወ/ሮ ስህን ት/ቤት ዐምድ ውስጥ ካሰፈራቸው ውብ ሙዚቃዎች ውስጥ:
1. ባንቺው መጀን
http://shegervideo1.googlepages.com/derebezenebe.htm

2. እያለ መጋሎ
http://shegervideo.googlepages.com/kebebushnegash.htm

የሚሉትን ወደ የጁ በትውስት መልክ ለሁሉም አቅርቤአለሁ:: እንደምትደሰቱም እተማመናለሁ::

መልካም ጊዜ ለሁላችሁ
እሪኩም ከቦሩ ሜዳ
እሪኩም
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 853
Joined: Fri Apr 01, 2005 1:20 am
Location: ወሎ

Postby ጣዕም » Mon Oct 23, 2006 4:10 am

እሪኩም ያቀረብካት የአገር ልጅ እስክስታዋን ስታስነካው እስቲ ተመልከት
Image
If there is a book that you want to read, but it hasn't been written yet, you must be the one to write it.
--Toni Morrison
ጣዕም
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 231
Joined: Sat May 01, 2004 2:02 am
Location: canada

PreviousNext

Return to Warka Intimate - ዋርካ ፍቅር

Who is online

Users browsing this forum: No registered users and 4 guests