***የየጁ ኩማንዳ ጠባ ልጆች***

The Love Forum (love, relationship) (የኔ ቆንጆ እንተዋወቅ :-)

የጁ ውርጌሳ ላይ መሃመድ ዐሊ

Postby እሪኩም » Wed Oct 25, 2006 12:41 am

ሠላም ጣዕም!

ቆንጆ ቅንብር ነው:: አመሰግናለሁ::
ይልመድብህ ጃል - ወሎ መጀን:: አንዳንድ ትዝታዎችን እስቲ አጫውተን ወንድሜ ሆይ!

አበት ላይ ሁኖ ይታያል ውጫሌ:
ጨዋታ እንደዚህ ነው ጠጅ በብርሌ::

አምባሰልን ስቃኝ ማርዬ ማራኪ:
የጁ ውርጌሳ ነው መሃመድ ዐሊ::

ጊዜው ይለፍ እንጂ ማን አለ መርማሪ:
ቀና ብለህ አውራ ፈንታው ተፈሪ::

መርሳ አባ ጌትዬ ስሪንቃና ሳንቃ:
መፋቀር ድንቁ መቼ ያውቃል በቃ::
Image
እስክስታ ለመምታት ለመጨዋዎት:
ደብረ ገሊላ ላይ አብረን በህብረት:
ሁሉም ነገር ያልፋል አለመሰልቸት::

መልካም ጊዜ
እሪኩም ከቦሩ ሜዳ
እሪኩም
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 853
Joined: Fri Apr 01, 2005 1:20 am
Location: ወሎ

Postby ሚጢገንዳ » Sat Oct 28, 2006 5:43 pm

ሰላም የጁና ታዳሚዎቹ እኔም ስለየጁ ትንሽ የምለው አለኝ::

የጁ የግዜር መሃል እጁ
እረ የጁ የጁ ውድመን ውድመን
እህል እየበሉ ሰው ወዶ መመንመን

በወልድያ ሼማ በቃሊም እንዶድ
እንዴት አርገው ቢያጥቡት ይለቃል መውደድ

የጁ በጉባላፍቶ እና በሃብሩ ወረዳዎች የታቀፈች እናት ሃገር ናት የጁ የበርካታ ጀግኖች, የብዙ ምሁሮች, የብዙ ሼኮችና ቀሳውስቶች እንዲሁም ቆነጃጅቶች አገር ከመሆኗም በላይ የአትክልትና ፍራፍሬ የቅባትና የምግብ እህሎች የሚበቅልባት ናት :: በተለይ ኢትዮጵያ ውስጥ በብዛት በየጁ ብቻ የሚገኙ ትርንጎ እና ደጋሌት ማሽላ ተጠቃሾች ናቸው እንዲሁም በታላላቅ ቅርሶች ከቀደምት ታሪካዊነቷ በተያያዘ የጁ ወረሴዎች የሚገኙባት አገር መሆኗ ሲገለጽ ወረሴዎች በአሁኑ ሳአትም በወልድያ በጉባላፍቶ እና በስሪንቃ አካባቢዎች ይገኛሉ,ሆኖም የደርግ ስርአተ ማህበር ባላባት በማለት እንዳዳከማቼው ይታወቃል :: ከብዙ በጥቂቱ ለመግለጽ ያክል ከየጁ ሀብቶች እነ መርሳ አባጌትዬ የዳና ሼሆችና መስጊድ እንዲሁም የመርጦ ስላሴ አቢያተ ክርስቲያናት ይዘከራሉ ::

ስለ የጁ ሲነሳ የጥንቷን ገነቴን የአሁኗን ወልድያ ከተማን እናስታውሳለን እንጀራው ወልድያ እየተጋገረ.....ወጡ ጉባላፍቶ ሰሼተኝ አደረ ይባል የለ :: ወልድያ በ1780 እንደኢትዮጵያዋኑ አቆጣጠር በታላቁ ራስ አሊ እንደተቆረቆረች ሲነገር ከባህር ወለል በላይ 2000 ሜትር ከፍታ ላይ የምትገኝ እና ከ200 አመት በላይ ያላት በአሁኑ ሳአት 55 ሽህ ህዝብ የሚኖርባት አገር ስትሆን ከአዲስ አበባ በ520 እርቀት ከባህር ዳር በ360 ኪሎሜትር እርቀት የምትገኝ እስትራጀቲካዊ ጠቀሜታዋ የጎላ ከተማ ናት :: ከ1959 እንደ ኢትዮጵያ አቆጣጠር በፊት በእቴጌ ጣይቱ ብጡል ት/ቤት ከ1ኛ እስከ 12ኛ ክፍል ትምህርት ይሰጥ እንደነበና ከዚያም መድሀኔ አለም 2ኛ ደረጃ ት/ቤት በመከፈቱ በርካት ተማሪዎች ከተለያየ ቦታ ከቦረና,ወረኢሉ,ደላንታ,ኩታበር,ሩጋ,ሀይቅ,ውርጌሳ,መርሳ,
ሰቆጣ,ከረም,አላማጣ,ቆቦ,ሮቢት,ጎብዬ,ላስታ,ቡግና ወዘተ ከመሳሰሉት እየመጡ ይማሩ እንደነበር ሲታወቅ ከጥንት መምህራን በከፊል እንደነ አባ ፈንታው ገብሬ እንደነ አባ ወረደ አበበ አባ ትኩዬ አቶ አስረስ ሲጠቀሱ አንጋፋው የመልካ ቆሌ ት/ቤትም አብሮ ይታወሳል :: በወቅቱ ይማሩ የነበሩት ተማሪዎች የማይረሱት ትልቅ ትውስታ ቢኖር የብዙ ደሃዎች አባት የነበሩትን አባሼሁን ነው በአባ ሼሁ ሻይ ቤት የነበረውን ዶልች ፓስትኒ አሳንቡሳ ያልበላ ያለ አይመስለኝም ለበላበትም ያዘነ እና ፈጣሪውን የፈራ ሂሳብ ሲከፍል የሌለውም እንደሌለው ነግሮ እንዲያም ያለ በጉልበት ወይንም በሽወዳ ሳይከፍል በመውጣት በዚህ መልክ እየተመገቡ ትምህርታቸውን በሰላም የጨረሱና ለቁምነገር የደረሱ በአሁኑ ሳአት በተለያዩ የአለማችን ክፍል ተበታትነው በተለያዩ ሞያ ያሉ ምስክሮች ናቸው :: የአባሸሁን ውለታ ውለታ ለመክፈል በልቡ የማያስብና የማይመኝ በወቅቱም ስህተት የፈጸመ የማይጸጸት እና ቢያገኛቼው ይቅርታ ለመጠየቅ የማያስብ የለም ግን እሳቼው በአሁኑ ሳአት የሉም ነብሳቼውን ይማረውና :: ከዚህም ጋር በተያያዘ እነ አሊ ጎብዬ እነ ፈልቃ ሰፈር ይርዳው ሰፈር የመሃሪ ዳገት የጓሉ ጠጅ ቤት ትንፋዝ ንጥፍ ድንጋይ ሚዳቆ ገደል መንደቅ ሼሌ ጫንጮ ሲደቦሩ ጀነቶበር የጉባርጃና የገብሪኤል ተራራ አሬሮ ኮሬ አዳጎ ሙጋር ሙጋድ መቻሬ እንዲሁም የጋላጊወርጊስ ጠበል እና የራስ ወሌ ብጡል ሆስፒታልን ስናስታውስ የወልድያ ውበትና ጌጦች መሆናቼውን እንረዳለን ::**አንድ ገበሬ ሁለት እረኞች የሚወጣውን*** አንድ አርጎ ፈጠረው አማረ አምባውን እየተባለ የተገጠመላቼው አቶ አማረ አምባውን በቁመት እርዝመት የሚስተካከል አልነበረም ይህንን ስናስብም በአንጻሩም ሃይሌ ኩንኩንን እናስታውሳለን ከነዚህ የወልድያ ሀብቶች በተጨማሪ የኪዳነምህረት ቤተክህነት ሊቅ እና አገልጋይ የነበሩ ጨዋታ ለዛቸው የማይረሱ አለቃ ድንቁን ከልጆቻቸው የሥም አሰያየም ጋር ይታወሳሉ :: የወልድያ ታላቁ የገበያ ቀን ማክሰኞ በመሆኑ ከከተማዋ አራቱም አቅጣጫ በርካታ ገበሬዎች ወደ ገበያ ቦታ ይመጣሉ በተለይ ከቆላው አካባቢ በሃገር ባህላቸው አልባሳት ተውበውና ደምቀው የሚመጡትን ኮበሌዎችና ኮረዳዎች መመልከት የወልድያን ውበት ለማድነቅ በቂ ማስረጃ ነው :: ወልድያ በተፈጥሮ አቀማመጥዋ ወይና ደጋ በመሆኗ የደጋ የወይናደጋ የቆላ የአየር ንብረትን ታስተናግዳለች እንግዲህ ወልድያን ስናነሳ የጥቁር ውሀን 200 ሜትር እርዝመት ያለውን ድልድይ እና የሳንቃ የሼንኮር አገዳ አይዘነጉንም ከዚሁም ጋር አንጋፋው አርቲስት አያሌው መስፍን እናን አሰፋ አባተን እናስታውሳለን መለል መለል ያሉ እንደ ምስሮች***አሁን ገና መጡ የየጁ ልጆች ብሏል አቀንቃኙ :: ምስሮች ለጥርስ መፋቂያነት የሚያገለግል አበቃቀሉም ቀጥ ብሎ የወጣ ነው በተለይ በጫንጮ ወንዝ በብዛት የሚገኝ ተክል ነው ::

ከዕውቁ ተወዳጅ አርቲስት እና መምህር አባ ትኩዬ ግ/እየሱስ ጋር ሰአሊ በላይ ጎርፉ የሚረሳ አይደለም በተለይ በወልድያ እና በተለያዩ የእስልምና እና የክርስትና ሀይማኖት የበአል አከባበር ለየት እና ሞቅ ደመቅ ያለ በመሆኑ ከህሊናችን የሚጠፋ አይደለም በተለይ በቡሄ በአል ለጅራፍ ግርፊያ ወደ ሲደቦሩ ሜዳ መሄዱ የተለመደ ነበር እንዲሁም ለልብስ አጠባም ይሁን ለመዝናናት ሼሌ ወንዝ ጫንጮ ወንዝ ንጥፍ ድንጋ ወንዝ የሚጓዘው ህዝብ ቁጥር ቀላል አልነበረም በጳግሜ ቅዱስ ዩሃንስ ንጋት ወደ ንጥፍ ድንጋ ገላ ለመታጠብ በሚሄዱት ወጣቶች ይሰማ የነበረው የጉዞ ዘፈንና ጭፈራ ልዩ ውበት ይሰጥ ነበር በኢድ ፈጥር እና በአረፋ በዐል በገጠር እና በከተማ የሚገኘው ሙስሊም ህብረተሰብ ጭፈራ ሁሌም የሚታወስ ነው እንዲሁም በጥምቀት በአል ታቦት ለመሼኘት የሚወጣው ህዝበ ክርስቲያን የተለያዩ ባህሎች ጭፈራ ፍጹም የሚረሳ አይደለም ::

በተጨማሪ ከታላላቅ የአገር ሽማግሌዎችም እነ አቶ ደምሴ አፍራሳ አባ ግራዝማች መሀመድ ተጠቃሾች ናቸው ከዛ ባሻገር እሪኩም እሪኩም ይሼታል ገላህ እንዴውም በመላ የየጁ ልጅ ነህ ተብሏል ::

ከሁሉም በላይ ሠላም ለኢትዮጵያችን ::
ሚጢገንዳ
አዲስ
አዲስ
 
Posts: 11
Joined: Sat Oct 28, 2006 3:25 pm

Postby የመንደራው » Sun Oct 29, 2006 7:14 pm

ወይ ጉድ ነው ነግሩ ሚጢ ገንዳ የምትገርም ሰው ነህ እኔ ወልድያ ተወልጄ ባድግም እዲህ እዳንተ ልቅም አድርጌ ሰውችን አላውቅም ለማንኛውም አበጀህ ተባረክ ነው የምለው
ግን ዘፍኞችን ስትጠቅስ ያዳጎውን ጎረምሳ ጋሻው አዳልን ምነው እረሳህው

እስኪ ጥያቄ ልጠይቅህ ሚጢ ገንዳ ማለት ምን ማለት እደሆነ ታውቃለህ?
የመንደራው
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 190
Joined: Thu Oct 05, 2006 1:01 pm

Postby Monica**** » Mon Oct 30, 2006 11:34 am

ስላም ያገር ልጆች
ዋርካ ቅድም የጻፍኩላችሁን በላብኝ :evil: :evil: :evil:
ወሬ ላስጥርና ምንም እንክዋን ወሎን ባላቀውም እና ማኒፋክቸርድ የተደረግኩት አዲሳበባ ቢሆንም ዘር በአባት ነው የሚቆጠረውና ወሎዬ ነኝ ማለት ነው :D :D ደሞ ቆንጆ ነኝ ለማለት አይደለም መቼም ሲፈርድብን ውበቱን በባሊ ሞልቶ ነው ያፈስስብን :lol: :lol: :lol:
በቁምነገር ግን የጁ ሚጢገንዳ መሪወንዝ እና ሌሎችም የምትጽፉት በጣም ደስ ይለኛል በተለይ ሚጢገንዳ ኦክቶበር 28 ስለየጁ የጻፍከው በጣም ነው ደስ ያለኝ የጁን በአይነህሊናዬ እንድቃኛትና አባቴ የሚተርክልኝን በተጨማሪ ግልጽ ስላደረግክልኝ ሳላመስግንህ አላልፍም!!!
ከዛ በተረፈ ጨዋታችሁን ቀጥሉበት ግን ከመስናበቴ በፊት አንድ ጥያቄ መጠየቅ ይፈቀድልኛል? ባይፈቀድልኝም መጠየቄን አልተውም :lol: :lol:
መቅደላ አጼ ቴዲ የሞቱባት አገር ወሎ ውስጥ ነው የሚል የት እንደስማሁ እንጃ እኔ ጎንደር ውስጥ ነው ባይ ነኝ እውነት መቅደላ ወሎ ውስጥ ነው?
በተረፈ መልካም ጨዋታ
አክባሪያችሁ
ሞኒካ ከሊማ ሊሞ:-)
Monica****
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 3195
Joined: Fri Dec 26, 2003 10:24 pm
Location: 999 Total eclipse st. Venus

Postby ልጁነኝ1 » Mon Oct 30, 2006 12:41 pm

ሚጢገንዳ!
በመሠረቱ ሥለምትወዳት የጁ ያቀረብከው የአገላለጽ ችታህን ጭምር ከፍተኛ አድናቆት አለኝ:: ይገርምሃል የጁ
ብዙ የኢትዮጵያን ህዝብ የያዘች ናት ቅድም ሞኒካ እንዳለችው ከወሎ የማይወለድ የለም:: ትክክል ነች::

ታስታውስ እንደሆነ ስትጽፍ "ገነቴ" ብለኃል:: ገነቴ ደግሞ የሚል ስም በአርሲ ክፍለ ህእገር በአርባጉጉ አውራጃ በጉና ወረዳ ውስጥ እዚያው ጉና አካባቢ ገነቴ የምትባል አገር አለች:: ያንንስም ማን ሰጣት? የአሩሲዋ እመቤት የሚባሉት የመጡት ከየጁ ነው:: ታዲያ እሳቸው ይሆኑ ገነቴ ያሉዋት ውኃ በአካባቢዋ የሚገኝ ሲሆን በጽድና በጫካ የታጠረች አገር ናት::

ልክ አንተ እንደጻፍከው ዓይነት ነው እኔም ተወልጄ ያደግሁባት አካባቢዬ ይደረግ የነበረው:: በጣም ልብን የሚያፈካ የሚያስደስት አጻጻፍ ነው::

የረሣኸው ሰው አሉ!
ስማቸው ቀኛማች አባተ ሐይሉን! ዛሬ የሉም የየጁው መስፍን:: ጀግናው ኢትዮጵያዊ ታስታውሳቸዋለሁ በሚል እገምታለሁ:: በትምህርት ቤት በዓል ግዜ በተለይ ደሴና ወልደያ ለተማሪው ሁሉ በመኪና ኮካኮላ በማቅረብ እንዲዝናኑ ያደርጉም ነበር::

መንግሥት ሊገለብጥ ነው እየተባለ ብዙውን ግዜ እስር ከዚያም ግዞት ይጓዙ ነበር:: አልጋወራሽ ነበሩ ዘወትር እየለመኑ ያሚያስለቅቋቸው:: እሳቸው ግን ተመልሰው መታሰራቸውን አይተውም ነበር:: በመጨረሻም ጀግናን የሚገድለው ትንሽና ፈሪ ሰው በመሆኑ በሰው እጅ ሞቱ::

የአካባቢውን ሁኔታ እንዲሁም ትርንጎ ስትል በአርሲ ክፍለ ኃገር ውስጥ ከላይ ስም በገለጽኩልህ አካባቢ እኛም ቤት ትርንጎ በብዛት ይገኝ ነበር:: ጠንካራ ነው ትርንጎ እሲጣፍጥ ለጉድ ነው:: ደስ ይልኃል እሱን ስትመገብ::

የጁውስጥ ከአዝር ዕቶቹ የሚበዛው ጥንቅሽ መሆኑንም አትዘንጋው እጅግ የሚጣፍጡ:: በተለይ እንዳልከው ለገበያ በአራቱም በሮች በኩል ባላገሮቹ ዕቃቸውን ጭነው በመደዳ እየተከታተሉ ሲሄዱ ለሚያቸው መላኮች በእምድር በግራቸው ወደ አንድ ቦታ ተከታትለው የሚሄዱ ይመስሉኃል:: ምክንያቱ የነኛ ሴቶቹ ልጅ አገረዶቹ ማማርና ቅርጻቸውን ሲመለከቱት ዓለም የምትገኘው ቤቱዋ እዚያ የጁ ነው ያስብልኃል:: ታይተው የማይጠገቡ ናቸውና::

አክባሪህ

ልጁነኝ1

ሚጢገንዳ wrote:ሰላም የጁና ታዳሚዎቹ እኔም ስለየጁ ትንሽ የምለው አለኝ::

የጁ የግዜር መሃል እጁ
እረ የጁ የጁ ውድመን ውድመን
እህል እየበሉ ሰው ወዶ መመንመን

በወልድያ ሼማ በቃሊም እንዶድ
እንዴት አርገው ቢያጥቡት ይለቃል መውደድ

የጁ በጉባላፍቶ እና በሃብሩ ወረዳዎች የታቀፈች እናት ሃገር ናት የጁ የበርካታ ጀግኖች, የብዙ ምሁሮች, የብዙ ሼኮችና ቀሳውስቶች እንዲሁም ቆነጃጅቶች አገር ከመሆኗም በላይ የአትክልትና ፍራፍሬ የቅባትና የምግብ እህሎች የሚበቅልባት ናት :: በተለይ ኢትዮጵያ ውስጥ በብዛት በየጁ ብቻ የሚገኙ ትርንጎ እና ደጋሌት ማሽላ ተጠቃሾች ናቸው እንዲሁም በታላላቅ ቅርሶች ከቀደምት ታሪካዊነቷ በተያያዘ የጁ ወረሴዎች የሚገኙባት አገር መሆኗ ሲገለጽ ወረሴዎች በአሁኑ ሳአትም በወልድያ በጉባላፍቶ እና በስሪንቃ አካባቢዎች ይገኛሉ,ሆኖም የደርግ ስርአተ ማህበር ባላባት በማለት እንዳዳከማቼው ይታወቃል :: ከብዙ በጥቂቱ ለመግለጽ ያክል ከየጁ ሀብቶች እነ መርሳ አባጌትዬ የዳና ሼሆችና መስጊድ እንዲሁም የመርጦ ስላሴ አቢያተ ክርስቲያናት ይዘከራሉ ::

ስለ የጁ ሲነሳ የጥንቷን ገነቴን የአሁኗን ወልድያ ከተማን እናስታውሳለን እንጀራው ወልድያ እየተጋገረ.....ወጡ ጉባላፍቶ ሰሼተኝ አደረ ይባል የለ :: ወልድያ በ1780 እንደኢትዮጵያዋኑ አቆጣጠር በታላቁ ራስ አሊ እንደተቆረቆረች ሲነገር ከባህር ወለል በላይ 2000 ሜትር ከፍታ ላይ የምትገኝ እና ከ200 አመት በላይ ያላት በአሁኑ ሳአት 55 ሽህ ህዝብ የሚኖርባት አገር ስትሆን ከአዲስ አበባ በ520 እርቀት ከባህር ዳር በ360 ኪሎሜትር እርቀት የምትገኝ እስትራጀቲካዊ ጠቀሜታዋ የጎላ ከተማ ናት :: ከ1959 እንደ ኢትዮጵያ አቆጣጠር በፊት በእቴጌ ጣይቱ ብጡል ት/ቤት ከ1ኛ እስከ 12ኛ ክፍል ትምህርት ይሰጥ እንደነበና ከዚያም መድሀኔ አለም 2ኛ ደረጃ ት/ቤት በመከፈቱ በርካት ተማሪዎች ከተለያየ ቦታ ከቦረና,ወረኢሉ,ደላንታ,ኩታበር,ሩጋ,ሀይቅ,ውርጌሳ,መርሳ,
ሰቆጣ,ከረም,አላማጣ,ቆቦ,ሮቢት,ጎብዬ,ላስታ,ቡግና ወዘተ ከመሳሰሉት እየመጡ ይማሩ እንደነበር ሲታወቅ ከጥንት መምህራን በከፊል እንደነ አባ ፈንታው ገብሬ እንደነ አባ ወረደ አበበ አባ ትኩዬ አቶ አስረስ ሲጠቀሱ አንጋፋው የመልካ ቆሌ ት/ቤትም አብሮ ይታወሳል :: በወቅቱ ይማሩ የነበሩት ተማሪዎች የማይረሱት ትልቅ ትውስታ ቢኖር የብዙ ደሃዎች አባት የነበሩትን አባሼሁን ነው በአባ ሼሁ ሻይ ቤት የነበረውን ዶልች ፓስትኒ አሳንቡሳ ያልበላ ያለ አይመስለኝም ለበላበትም ያዘነ እና ፈጣሪውን የፈራ ሂሳብ ሲከፍል የሌለውም እንደሌለው ነግሮ እንዲያም ያለ በጉልበት ወይንም በሽወዳ ሳይከፍል በመውጣት በዚህ መልክ እየተመገቡ ትምህርታቸውን በሰላም የጨረሱና ለቁምነገር የደረሱ በአሁኑ ሳአት በተለያዩ የአለማችን ክፍል ተበታትነው በተለያዩ ሞያ ያሉ ምስክሮች ናቸው :: የአባሸሁን ውለታ ውለታ ለመክፈል በልቡ የማያስብና የማይመኝ በወቅቱም ስህተት የፈጸመ የማይጸጸት እና ቢያገኛቼው ይቅርታ ለመጠየቅ የማያስብ የለም ግን እሳቼው በአሁኑ ሳአት የሉም ነብሳቼውን ይማረውና :: ከዚህም ጋር በተያያዘ እነ አሊ ጎብዬ እነ ፈልቃ ሰፈር ይርዳው ሰፈር የመሃሪ ዳገት የጓሉ ጠጅ ቤት ትንፋዝ ንጥፍ ድንጋይ ሚዳቆ ገደል መንደቅ ሼሌ ጫንጮ ሲደቦሩ ጀነቶበር የጉባርጃና የገብሪኤል ተራራ አሬሮ ኮሬ አዳጎ ሙጋር ሙጋድ መቻሬ እንዲሁም የጋላጊወርጊስ ጠበል እና የራስ ወሌ ብጡል ሆስፒታልን ስናስታውስ የወልድያ ውበትና ጌጦች መሆናቼውን እንረዳለን ::**አንድ ገበሬ ሁለት እረኞች የሚወጣውን*** አንድ አርጎ ፈጠረው አማረ አምባውን እየተባለ የተገጠመላቼው አቶ አማረ አምባውን በቁመት እርዝመት የሚስተካከል አልነበረም ይህንን ስናስብም በአንጻሩም ሃይሌ ኩንኩንን እናስታውሳለን ከነዚህ የወልድያ ሀብቶች በተጨማሪ የኪዳነምህረት ቤተክህነት ሊቅ እና አገልጋይ የነበሩ ጨዋታ ለዛቸው የማይረሱ አለቃ ድንቁን ከልጆቻቸው የሥም አሰያየም ጋር ይታወሳሉ :: የወልድያ ታላቁ የገበያ ቀን ማክሰኞ በመሆኑ ከከተማዋ አራቱም አቅጣጫ በርካታ ገበሬዎች ወደ ገበያ ቦታ ይመጣሉ በተለይ ከቆላው አካባቢ በሃገር ባህላቸው አልባሳት ተውበውና ደምቀው የሚመጡትን ኮበሌዎችና ኮረዳዎች መመልከት የወልድያን ውበት ለማድነቅ በቂ ማስረጃ ነው :: ወልድያ በተፈጥሮ አቀማመጥዋ ወይና ደጋ በመሆኗ የደጋ የወይናደጋ የቆላ የአየር ንብረትን ታስተናግዳለች እንግዲህ ወልድያን ስናነሳ የጥቁር ውሀን 200 ሜትር እርዝመት ያለውን ድልድይ እና የሳንቃ የሼንኮር አገዳ አይዘነጉንም ከዚሁም ጋር አንጋፋው አርቲስት አያሌው መስፍን እናን አሰፋ አባተን እናስታውሳለን መለል መለል ያሉ እንደ ምስሮች***አሁን ገና መጡ የየጁ ልጆች ብሏል አቀንቃኙ :: ምስሮች ለጥርስ መፋቂያነት የሚያገለግል አበቃቀሉም ቀጥ ብሎ የወጣ ነው በተለይ በጫንጮ ወንዝ በብዛት የሚገኝ ተክል ነው ::

ከዕውቁ ተወዳጅ አርቲስት እና መምህር አባ ትኩዬ ግ/እየሱስ ጋር ሰአሊ በላይ ጎርፉ የሚረሳ አይደለም በተለይ በወልድያ እና በተለያዩ የእስልምና እና የክርስትና ሀይማኖት የበአል አከባበር ለየት እና ሞቅ ደመቅ ያለ በመሆኑ ከህሊናችን የሚጠፋ አይደለም በተለይ በቡሄ በአል ለጅራፍ ግርፊያ ወደ ሲደቦሩ ሜዳ መሄዱ የተለመደ ነበር እንዲሁም ለልብስ አጠባም ይሁን ለመዝናናት ሼሌ ወንዝ ጫንጮ ወንዝ ንጥፍ ድንጋ ወንዝ የሚጓዘው ህዝብ ቁጥር ቀላል አልነበረም በጳግሜ ቅዱስ ዩሃንስ ንጋት ወደ ንጥፍ ድንጋ ገላ ለመታጠብ በሚሄዱት ወጣቶች ይሰማ የነበረው የጉዞ ዘፈንና ጭፈራ ልዩ ውበት ይሰጥ ነበር በኢድ ፈጥር እና በአረፋ በዐል በገጠር እና በከተማ የሚገኘው ሙስሊም ህብረተሰብ ጭፈራ ሁሌም የሚታወስ ነው እንዲሁም በጥምቀት በአል ታቦት ለመሼኘት የሚወጣው ህዝበ ክርስቲያን የተለያዩ ባህሎች ጭፈራ ፍጹም የሚረሳ አይደለም ::

በተጨማሪ ከታላላቅ የአገር ሽማግሌዎችም እነ አቶ ደምሴ አፍራሳ አባ ግራዝማች መሀመድ ተጠቃሾች ናቸው ከዛ ባሻገር እሪኩም እሪኩም ይሼታል ገላህ እንዴውም በመላ የየጁ ልጅ ነህ ተብሏል ::

ከሁሉም በላይ ሠላም ለኢትዮጵያችን ::
ልጁነኝ1
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 641
Joined: Tue Dec 30, 2003 2:17 pm
Location: united states

Postby ሚጢገንዳ » Mon Oct 30, 2006 4:41 pm

ሰላም የቤቱ ባለቤት የጁ እና ታዳሚዎቹ ::

ከላይ አንድ ወዳጃችን በጠየቀው መሰረት ሚጢገንዳ.....ወልድያ ከተማ ውስጥ የሚገኝ አንድ ሰፈር ሥም ሲሆን ስያሜውን ያገኘው በወቅቱ የዛች ሰፈር ነዋሪ ከነበሩ አዛውንት ነበር :: እንግዲህ ታሪክ እንደሚለው በዛ አመተምህረት የሰፈሯ እናቶች ባብዛኛው በተመሳሳይ ወቅት ያረገዙበት ጊዜ ነበር ታዲያ የሚወልዱበት ቀን በደረሰ ጊዜ አዛውንቱ እነዚህን ሴቶች ማሪያም በሰላም ትገላግላቼው ቦታው የምጥ ገንዳ ሆንዋል ብለው ጸሎት ሲያደርሱ ከዛ በመነሳት ሰዎች ሚጢገንዳ አሏት እንደ አዛውንቱ አባባል የምጥ ቀበሌ ማለት ነበር :: ከዚሁም ጋር አርቲስት ጋሻው አዳልን ስላስታወስከኝ ሳላመሰግን አላልፍም ::

እህታችን ሞኒካ ደግሞ ቆንጆ አይደለሁም ብለሽ እንዳትከራከሪኝ ቁንጅናሽን እኔ እና የሚያውቁሽ ያውቁታል ይልቅስ ያባትሽን አገር የጁን መቼ ነው የምታይው ?

ልጁነኝ 1
ሰላሜ ይድረስህ ባለህበት ቦታ በርግጥ ቀኛዝማች አባተ ሃይሉን እረስቻቼው ሳይሆን ከላይ ወንድም የጁ ከነ ልጃቼው አቻምየለሽ ስለጠቀሳቼው ድግግሞሽ እንዳይሆን ብዬ ነው ጀግንነት እንደ አባተ ነው እንጅ ::

ውድ ልጁነኝ 1....... "ጥንቅሽን" የቀመሰው ነው የሚያውቀው ይህ ጣፋጭ ተክል በብዛት የሚበቅለው ያለማጋነን በየጁ ብቻ ነበር :: በተረፈ እርግጠኛ ነኝ አንተም ሰፋ ባለ መልኩ ስለ የጁ እንደምትዘካክርልን ::
በመጨረሻም እግዜር ያክብርልኝ ::

ከሁሉም በላይ ሠላም ለኢትዮጵያችን ::
ሚጢገንዳ
አዲስ
አዲስ
 
Posts: 11
Joined: Sat Oct 28, 2006 3:25 pm

Postby የጁ » Mon Oct 30, 2006 4:50 pm

ሠላም ያገር ልጆች !

ወንድሜ ሚጢገንዳ :- በመጀመሪያ እንኳን ወደዚህ ቤት በሰላም መጣህልን እያልኩ ያጻጻፍ ዘይቤህ በጣም ማራኪና ከልብ የመነጨ በመሆኑ በጣም ላመሰገንህ እወዳለሁ መልካሙ ሁሉ ላንተ ይሁን እጅ ይባርክ ::

ከታላቅ አክብሮትና ፍቅር ጋር ::
Diqaw Ke Kumandateba
የጁ
ጀማሪ ኮትኳች
ጀማሪ ኮትኳች
 
Posts: 82
Joined: Thu Sep 28, 2006 10:59 am

ይቺ ናት መንደሬ

Postby እሪኩም » Sat Nov 04, 2006 12:50 am

ሠላም ለሁሉም!

ስለ የጁ ብዙ መጫዎት እና ማለት ይቻላል:: ፍቅር እና ቁንጅና ብሎም ቁምነገር አብሮ ነው የነበረው - ያለው - የሚኖረው::

ቆንጂት ሞኒካ - ስለ ወሎ - የጁ - ከምታውቂያቸው በጥቂቱ ሰንዝረሽ ብታልፊ እና ከቡናሽም ጀባ ብትዪኝ ደስ ይለኛል:: ስለምወድሽ ለገና በዓል ያሰራሁልሽን ጥልፍ ቀሚስ እንድትላበሽ እና ሽር ጉድ እንደምትይ ከወዲሁ ይታየኛል:: ወይ የከንፈር ወዳጅ---:-)

Image
ይቺ ናት መንደሬ - መወለድ ቋንቋ ነው እና

መልካም የፍቅር ጭውውት
እሪኩም ከቦሩ ሜዳ
እሪኩም
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 853
Joined: Fri Apr 01, 2005 1:20 am
Location: ወሎ

Postby Zerish » Sat Nov 04, 2006 3:43 am

እሪኩም,
ፎቶው ላይ ያወጣከው ሰውዬ ወሎዬ ነው እንዴ? :lol: :lol: :lol: :lol:
Just do your best!
Zerish
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 236
Joined: Sun Nov 13, 2005 8:31 am
Location: Bay Area

Postby እሪኩም » Mon Nov 06, 2006 4:06 pm

ሠላም Zerish!

ብለህ ነው?----:-)
ቤተስቤን ለመጠየቅ እና አገር ለመጎብኘት የተጓዘ አውሮፒያዊ የሥራ ባልደረባዬ ነው::

መልካም ጊዜ
እሪኩም ከቦሩ ሜዳ
እሪኩም
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 853
Joined: Fri Apr 01, 2005 1:20 am
Location: ወሎ

Postby ሾተል » Mon Nov 06, 2006 6:56 pm

ሚጢገንዳ wrote:ሰላም የጁና ታዳሚዎቹ እኔም ስለየጁ ትንሽ የምለው አለኝ::

የጁ የግዜር መሃል እጁ
እረ የጁ የጁ ውድመን ውድመን
እህል እየበሉ ሰው ወዶ መመንመን

በወልድያ ሼማ በቃሊም እንዶድ
እንዴት አርገው ቢያጥቡት ይለቃል መውደድ

የጁ በጉባላፍቶ እና በሃብሩ ወረዳዎች የታቀፈች እናት ሃገር ናት የጁ የበርካታ ጀግኖች, የብዙ ምሁሮች, የብዙ ሼኮችና ቀሳውስቶች እንዲሁም ቆነጃጅቶች አገር ከመሆኗም በላይ የአትክልትና ፍራፍሬ የቅባትና የምግብ እህሎች የሚበቅልባት ናት :: በተለይ ኢትዮጵያ ውስጥ በብዛት በየጁ ብቻ የሚገኙ ትርንጎ እና ደጋሌት ማሽላ ተጠቃሾች ናቸው እንዲሁም በታላላቅ ቅርሶች ከቀደምት ታሪካዊነቷ በተያያዘ የጁ ወረሴዎች የሚገኙባት አገር መሆኗ ሲገለጽ ወረሴዎች በአሁኑ ሳአትም በወልድያ በጉባላፍቶ እና በስሪንቃ አካባቢዎች ይገኛሉ,ሆኖም የደርግ ስርአተ ማህበር ባላባት በማለት እንዳዳከማቼው ይታወቃል :: ከብዙ በጥቂቱ ለመግለጽ ያክል ከየጁ ሀብቶች እነ መርሳ አባጌትዬ የዳና ሼሆችና መስጊድ እንዲሁም የመርጦ ስላሴ አቢያተ ክርስቲያናት ይዘከራሉ ::

ስለ የጁ ሲነሳ የጥንቷን ገነቴን የአሁኗን ወልድያ ከተማን እናስታውሳለን እንጀራው ወልድያ እየተጋገረ.....ወጡ ጉባላፍቶ ሰሼተኝ አደረ ይባል የለ :: ወልድያ በ1780 እንደኢትዮጵያዋኑ አቆጣጠር በታላቁ ራስ አሊ እንደተቆረቆረች ሲነገር ከባህር ወለል በላይ 2000 ሜትር ከፍታ ላይ የምትገኝ እና ከ200 አመት በላይ ያላት በአሁኑ ሳአት 55 ሽህ ህዝብ የሚኖርባት አገር ስትሆን ከአዲስ አበባ በ520 እርቀት ከባህር ዳር በ360 ኪሎሜትር እርቀት የምትገኝ እስትራጀቲካዊ ጠቀሜታዋ የጎላ ከተማ ናት :: ከ1959 እንደ ኢትዮጵያ አቆጣጠር በፊት በእቴጌ ጣይቱ ብጡል ት/ቤት ከ1ኛ እስከ 12ኛ ክፍል ትምህርት ይሰጥ እንደነበና ከዚያም መድሀኔ አለም 2ኛ ደረጃ ት/ቤት በመከፈቱ በርካት ተማሪዎች ከተለያየ ቦታ ከቦረና,ወረኢሉ,ደላንታ,ኩታበር,ሩጋ,ሀይቅ,ውርጌሳ,መርሳ,
ሰቆጣ,ከረም,አላማጣ,ቆቦ,ሮቢት,ጎብዬ,ላስታ,ቡግና ወዘተ ከመሳሰሉት እየመጡ ይማሩ እንደነበር ሲታወቅ ከጥንት መምህራን በከፊል እንደነ አባ ፈንታው ገብሬ እንደነ አባ ወረደ አበበ አባ ትኩዬ አቶ አስረስ ሲጠቀሱ አንጋፋው የመልካ ቆሌ ት/ቤትም አብሮ ይታወሳል :: በወቅቱ ይማሩ የነበሩት ተማሪዎች የማይረሱት ትልቅ ትውስታ ቢኖር የብዙ ደሃዎች አባት የነበሩትን አባሼሁን ነው በአባ ሼሁ ሻይ ቤት የነበረውን ዶልች ፓስትኒ አሳንቡሳ ያልበላ ያለ አይመስለኝም ለበላበትም ያዘነ እና ፈጣሪውን የፈራ ሂሳብ ሲከፍል የሌለውም እንደሌለው ነግሮ እንዲያም ያለ በጉልበት ወይንም በሽወዳ ሳይከፍል በመውጣት በዚህ መልክ እየተመገቡ ትምህርታቸውን በሰላም የጨረሱና ለቁምነገር የደረሱ በአሁኑ ሳአት በተለያዩ የአለማችን ክፍል ተበታትነው በተለያዩ ሞያ ያሉ ምስክሮች ናቸው :: የአባሸሁን ውለታ ውለታ ለመክፈል በልቡ የማያስብና የማይመኝ በወቅቱም ስህተት የፈጸመ የማይጸጸት እና ቢያገኛቼው ይቅርታ ለመጠየቅ የማያስብ የለም ግን እሳቼው በአሁኑ ሳአት የሉም ነብሳቼውን ይማረውና :: ከዚህም ጋር በተያያዘ እነ አሊ ጎብዬ እነ ፈልቃ ሰፈር ይርዳው ሰፈር የመሃሪ ዳገት የጓሉ ጠጅ ቤት ትንፋዝ ንጥፍ ድንጋይ ሚዳቆ ገደል መንደቅ ሼሌ ጫንጮ ሲደቦሩ ጀነቶበር የጉባርጃና የገብሪኤል ተራራ አሬሮ ኮሬ አዳጎ ሙጋር ሙጋድ መቻሬ እንዲሁም የጋላጊወርጊስ ጠበል እና የራስ ወሌ ብጡል ሆስፒታልን ስናስታውስ የወልድያ ውበትና ጌጦች መሆናቼውን እንረዳለን ::**አንድ ገበሬ ሁለት እረኞች የሚወጣውን*** አንድ አርጎ ፈጠረው አማረ አምባውን እየተባለ የተገጠመላቼው አቶ አማረ አምባውን በቁመት እርዝመት የሚስተካከል አልነበረም ይህንን ስናስብም በአንጻሩም ሃይሌ ኩንኩንን እናስታውሳለን ከነዚህ የወልድያ ሀብቶች በተጨማሪ የኪዳነምህረት ቤተክህነት ሊቅ እና አገልጋይ የነበሩ ጨዋታ ለዛቸው የማይረሱ አለቃ ድንቁን ከልጆቻቸው የሥም አሰያየም ጋር ይታወሳሉ :: የወልድያ ታላቁ የገበያ ቀን ማክሰኞ በመሆኑ ከከተማዋ አራቱም አቅጣጫ በርካታ ገበሬዎች ወደ ገበያ ቦታ ይመጣሉ በተለይ ከቆላው አካባቢ በሃገር ባህላቸው አልባሳት ተውበውና ደምቀው የሚመጡትን ኮበሌዎችና ኮረዳዎች መመልከት የወልድያን ውበት ለማድነቅ በቂ ማስረጃ ነው :: ወልድያ በተፈጥሮ አቀማመጥዋ ወይና ደጋ በመሆኗ የደጋ የወይናደጋ የቆላ የአየር ንብረትን ታስተናግዳለች እንግዲህ ወልድያን ስናነሳ የጥቁር ውሀን 200 ሜትር እርዝመት ያለውን ድልድይ እና የሳንቃ የሼንኮር አገዳ አይዘነጉንም ከዚሁም ጋር አንጋፋው አርቲስት አያሌው መስፍን እናን አሰፋ አባተን እናስታውሳለን መለል መለል ያሉ እንደ ምስሮች***አሁን ገና መጡ የየጁ ልጆች ብሏል አቀንቃኙ :: ምስሮች ለጥርስ መፋቂያነት የሚያገለግል አበቃቀሉም ቀጥ ብሎ የወጣ ነው በተለይ በጫንጮ ወንዝ በብዛት የሚገኝ ተክል ነው ::

ከዕውቁ ተወዳጅ አርቲስት እና መምህር አባ ትኩዬ ግ/እየሱስ ጋር ሰአሊ በላይ ጎርፉ የሚረሳ አይደለም በተለይ በወልድያ እና በተለያዩ የእስልምና እና የክርስትና ሀይማኖት የበአል አከባበር ለየት እና ሞቅ ደመቅ ያለ በመሆኑ ከህሊናችን የሚጠፋ አይደለም በተለይ በቡሄ በአል ለጅራፍ ግርፊያ ወደ ሲደቦሩ ሜዳ መሄዱ የተለመደ ነበር እንዲሁም ለልብስ አጠባም ይሁን ለመዝናናት ሼሌ ወንዝ ጫንጮ ወንዝ ንጥፍ ድንጋ ወንዝ የሚጓዘው ህዝብ ቁጥር ቀላል አልነበረም በጳግሜ ቅዱስ ዩሃንስ ንጋት ወደ ንጥፍ ድንጋ ገላ ለመታጠብ በሚሄዱት ወጣቶች ይሰማ የነበረው የጉዞ ዘፈንና ጭፈራ ልዩ ውበት ይሰጥ ነበር በኢድ ፈጥር እና በአረፋ በዐል በገጠር እና በከተማ የሚገኘው ሙስሊም ህብረተሰብ ጭፈራ ሁሌም የሚታወስ ነው እንዲሁም በጥምቀት በአል ታቦት ለመሼኘት የሚወጣው ህዝበ ክርስቲያን የተለያዩ ባህሎች ጭፈራ ፍጹም የሚረሳ አይደለም ::

በተጨማሪ ከታላላቅ የአገር ሽማግሌዎችም እነ አቶ ደምሴ አፍራሳ አባ ግራዝማች መሀመድ ተጠቃሾች ናቸው ከዛ ባሻገር እሪኩም እሪኩም ይሼታል ገላህ እንዴውም በመላ የየጁ ልጅ ነህ ተብሏል ::

ከሁሉም በላይ ሠላም ለኢትዮጵያችን ::
ይመችህ ወንድምዬ......ሂድና የማላውቀው ነገር ግን እትብቴ የተቀበረበትን ቦታ እይ አሰኘሄኝ.......ምነው የጁን(ወሎን)ዛሬውኑ ብርር ብዬ ባየሁት?እኔም ለሞኒካ አባትዋ እንደተረኩላት እናቴ ልጅ እያለሁ ትተርክልኝ ነበር....መቼም ከአኡሮፓ የበረርኩ ጊዜ እዛው ተዱዬ የገጠሩንና የከተማውን ህይወት ሳላየው አልቀር ለዛ ያድርሰን እንጂ......

እግዚአብህእር ይስጥህ ስንቱን ነገር አሳወቅከኝ...እስቲ በዚሁ ቀጥሉ አደራ....አመጣጣችንን አሳውቁን....

ፍቅር ለአገሬ ኢትዮጵያ ህዝብ.......
ሾተል ነኝ ከየጁዬ የደም ጠብታ ጽስር
ሾተል
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 9653
Joined: Thu Jan 13, 2005 9:42 pm
Location: Vienna-Austria

ሾተል ነኝ ከየጁዬ የደም ጠብታ ትስስር
ሾተል
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 9653
Joined: Thu Jan 13, 2005 9:42 pm
Location: Vienna-Austria

Postby Monica**** » Wed Nov 08, 2006 11:41 pm

ስላም ያገር ልጆች
እንዴት ከርማችህዋል?
ምነው ሚጢ ገንዳ ያ የሞቀ የደመቀህ ጨዋታህ ባንድ ቆመ? እረ በጉጉት ነው የምንጠብቅህ!
ስለቁንጅና ላልከው መቼም ወሎዬ ከሆነች የቁንጅና ፍንጥርጣሪውን አታጣም ብለህ ነው አይደል? :lol: :lol: ልክ ነህ ቆንጅዬ ወሎዬ ፒካሶ ሲስል እኔ ማስደገፊያ ነበርኩኝ ትንሽ ቀለሙ ነክቶኛል :lol: :lol: :lol: :lol:

ዘርሽ
እግዜር ይይልህ አሁን ምኑ ወሎዬ መስለህ ያ ፈረንጅ? ተንኮለኛ የኒው ካስትል ደጋፊ :lol: :lol: :lol: :lol: :lol:

እሪኩም
ያገር ልጅ ያስራህልኝ አበሻ ቀሚስ ውብ ነው ሹሩባዬን ተስርቼ ብቅ እላለሁ አንተም ከመከም አፍሮህን ሚዶ ሻጥ አድርገህ ከች ነው :lol: :lol: :lol:

ሾተል
አጻጻፍህ አንጀት ይበላል....አይዞህ አንድ ቀን የአባት እናቶቻችንን አገር የመጎብኝት እድሉ ይኖረናል!
Monica****
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 3195
Joined: Fri Dec 26, 2003 10:24 pm
Location: 999 Total eclipse st. Venus

Postby የጁ » Thu Nov 09, 2006 11:06 am

ሠላም ያገር ልጆች !

ወሎ ሲገቡብሽ ለቅሶ....ሲወጡብሽም ለቅሶ ብዙዎች የሚሉት ነው :: ከረጅም አመታት በፊት ወልድያ እያለሁ ከአዲስ አበባ በመምህርነት ተመርቆ የመጣው ጓደኛየ ሲያጫውተኝ የምደባውን ድልድል ሄጄ ሳዬው ይላል ከስሜ በታች የምድብ ቦታ ወሎ ክፍለሃገር የጁ አውራጃ ወልድያ ከተማ የሚለውን ሳይ ሃገር ምድሩ ነው የጨለመብኝ ብሎ ታሪኩን የሚነግረኝ ወዳጄ በመቀጠል የግዴታ ሆነ እና እንጀራ ፍለጋ ወደ ወሎ መጣሁ አለኝ ያን ያክል አድካሚ ጉዞዎችን በአውቶብስ ተጉዘን ወልድያ በገባን ባጭር ጊዜ ውስጥ ያ ሁሉ ጽልመት በብርሀናማ ጊዜያቶች ተቀየሩ ይል እና ወሎ ገራ ገሩ የሚለውን የቃል ፍች እዚህ መጥቼ ነው እውነታውን ያረጋገጥኩት የጁ የፍቅር አምባ የሚለው ወዳጄ እዛው ወልድያ አግብቶ እስከተለያየንበት ጊዜ ድረስ የሁለት ልጆች አባት ሆኖ ነበር ::

የጥምቀት በአል በሚከበርበት ጊዜ ቆነጃጅትን ማየት ልዩ ደስታን ይሰጣል :: ይህ ባአል የሚከበርበት ቦታ (ታቦት ማደሪያ) የተለያዩ አቢያተ ክርስቲያናት ታቦቶች በእልልታ እና በጭፈራ ታጅበው እዚህ ታቦት ማደሪያው ይመጣሉ የኪዳነ ምህረት የሞላ ጊወርጊስ የመድሃኔ አለም ወዘተ የተለያዩ ብሄረሰቦች የየራሳቼውን ዘፈን እና ጭፈራ በዚሁ ቦታ ያሳያሉ በዚህ ሁኔታ ሲጨፈር ይውል እና ከሚካኤል በስተቀር ሁሉም ታጅቦ ወደየ ቦታው ይመለሳል እዛው ያደረውን ሚካኤል ለመሼኘት እና ባአሉንም ለማክበር ቀሳውስቱ በተለያየ አልባሳት ህዝበ ክርስቲያኑ ከትላንቱ በበለጠ አምሮ ልጃገረዶች ተኳኩለው እና ተውበው ወጣት ወንዶች ልጃገርዶችን ለማጥመድ ዘንጠው ወደ ታቦት ማደሪያው ይተማሉ ::

ይቀጥላል
Diqaw Ke Kumandateba
የጁ
ጀማሪ ኮትኳች
ጀማሪ ኮትኳች
 
Posts: 82
Joined: Thu Sep 28, 2006 10:59 am

Postby የጁ » Thu Nov 09, 2006 11:21 am

.....ቀጣይ

የጁ ውስጥ የጥምቀትን እና የሚካኤልን ባአል ደስ በሚል አኳኋን ነው የሚከበረው :: ከላይ እንደጠቀስኩት ሚካኤልን ለመሸኔት የተሰበሰበው ህዝብ አምሮ እና ደምቆ በተለያዩ ጣእመ ዜማ ይደምቃል ሆኖም አንዳንዶች እንደሚሉት ሚካኤል ካልደመቀ አይንቀሳቀስም ስለሚባል ከዚህ በመነሳት በየአቅጣጫው ጫዎታው በእጥፍ ይደምቃል ከታቦት ማደሪያው እስከ ሚካኤል ቤተክርስቲያን ያለው እርቀት በጣም እረጅም ሆኖ ሳይሆን ከላይ የተባለውን ለመተግበር ይመስላል ከጥዋቱ አራት ሳአት የተነሳ ከቀትር በኋላ ስምንት ሳአት ነበር እቦታው የሚደርሰው ::

ታዲያ ይህንን አጋጣሚ በመጠቀም ወጣት ወንዶች ወደ ልጃገረዶች ሎሚ የመወርወር ተግባራቼውን ያጥዋጡፉታል ሎሚውን ተቀብላ አሽትታ ከላጠችው ለወርዋሪው በለስ ቀንቶታል ማለት ነው :: ታዲያ በዚህ መልኩ ቤተክርስቲያኑ ይደረስ እና ሲጫዎቱ ሲዘፍኑ አምሽተው ታቦቱን ቤቱ አስገብተው ጸሃይ ማሽቆልቆል ስትጀምር ሁሉም ወደ ቤቱ ይመለሳል ::
Diqaw Ke Kumandateba
የጁ
ጀማሪ ኮትኳች
ጀማሪ ኮትኳች
 
Posts: 82
Joined: Thu Sep 28, 2006 10:59 am

PreviousNext

Return to Warka Intimate - ዋርካ ፍቅር

Who is online

Users browsing this forum: No registered users and 5 guests