ሠላም ፍቅረ-ዋርካዊያን እና ዋርካዊያት
እዚህ ሠፈር ሠሞኑን ስመላለስ የተከፈቱት ጠጅ ቤትና ካፌዎች ገበያቸው ቀዝቀዘብኝ ልበል.....? አሀይ እስቲ ሞቅ ሞቅ እናርጋቸው:
ይሄው እኔም አልበላም አልጠጣም እያልኩኝ እዚህ ዋርካ ውስጥ ሦስት ዓመታት የቋጠርኳትን ገንዘብ ከሁለት ዓመት በፊት እዚህ ዋርካ ፍቅር ውስጥ ግሮሠሪ መክፈት መፈለጌን አመልክቼ አይደርስ የለ በሊዝ የተሠጠኝ መሬት ደረሠኝ::
እነሆ ዛሬም ግሮሠሪ ሰርቼ ከፈትኩበት ስሙንም '' ባልቻና መዶሻው ግሮሠሪ'' አልኩት በሡ ስም መሠየሜ መታሠቢያ ይሆነው ዘንድ ብዬ ነው::
ይህንንም ራዒ ታይቶኝ ነው::ቅቅቅ
ውድ ዋርካ ዘ-ፍቅራዊያን
በዚህ ግሮሠሪ የፈለጉትን ማዘዝ ይችላሉ የፈለጉትንም መወያየት ይችላሉ__ ለተወሠኑ ጊዜያትም ዱቤ መፍቀዳችንን ከታላቅ አክብሮት ጋር እነገልጻለን::
ግሮሠሪው የሚሠጣቸው ተጨማሪ አገልግሎቶች
__ለፍቅረኞች ደብዳቤ እንዴት እንደሚፃፍ ነፃ የምክር አገልግሎት ይሠጣል::
__የተኳረፉና የተደባበሩ ፍቅረኞችን አማላጅ ልኮ ነፃ የማስታረቅና የማስማማት አገልግሎት ይሰጣል::
ማሣሠቢያ
ሰክሮም ሆነ ሳይሠክሩ ክፉ መነጋገር የተከለከለ ነው ::
ባልቻና መዶሻው ግሮሠሪ ኃሙስ በ21:00 ሠሃት (በግሪንዊች አቆጣጠር) ቻት ሩም ውስጥ መጠነኛ ዳስ ጥሎ ይመረቃል:: በስፍራው መጥታችሁ ትመርቁ ዘንድም ተጋብዛቹዋል::
አድራሻው
ከደብዚ ጠጅ ቤት 11 ሜትር ከፍ ብሎ ከ ሞ' ካፌ ፊትለፊት ከጉዱ ካሳ ሥጋቤት አጠገብ ነው::
አደራ ሸላይ ግሮሠሪ ናት እና ጎራ ይበሉ
ማስታወቂያ
አስተናጋጅ እንቀጥራለን
ዋናው_______________________________________::