ባልቻና መዶሻው ግሮሠር=> ተጠፋፋን

The Love Forum (love, relationship) (የኔ ቆንጆ እንተዋወቅ :-)

Postby ጦምኔው » Tue Jul 31, 2012 2:11 am

እዚህ ቤት በቃ ሀብታም ብቻ ነው የሚገባው?? ባለ ስጋ ቤት (ጉድሽካ), ባለ አኒሜሽን ቤት (ዋንቾ)? እኛ ፍንዳታዎቹስ ምን ይዘን ከች እንበል??

ሻይ ቦይ ሰላምከ አባ:: ምነው ሚሪንዳ አባቱ? ጠሀይ ከጠለቀች በሀላ እኮ...በይ ማነሽ አንቺ የግል እስኪ ቡትሌ አምጪለት

ዋንቾ ዌልካም አባ:: እስኪ በል የገቢ አንድ ቢራ ልቀቅብኝ:: የአዲስ (አበባ እና ከተማ) ጭውቴ በጉጉት እየጠበቅን ነው

ውቅሽ አካም አካም ኦቦሌ አባ ቡቁሻ :lol: በል ቢራ ልቀቅብኝ

ጌቾ ኧረ አባቱ ተቀፈለን....በል ዴች ገፍትር.....ሀፒ አወር 3 ሄኒከን

ይህቺ ሪቾ እዚህ ቤት ማስተናገድ ከጀመረች የአስቴር አወቀ ዘፈን በዝቷል..... :lol:

ሁላቹም ሰላም ሰላም......
ጦምኔው
ዋና ውሃ አጠጪ
ዋና ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1529
Joined: Sun Jan 14, 2007 10:40 pm
Location: Right here

Postby እንሰት » Tue Jul 31, 2012 4:31 pm

ታንክዩ ዋናው
አዲስን በርግጥ አየናት:: ጥሩ ምልከታ ነበር::

ዋናው wrote:ከበርካታ ዓመታት በፊት ከእዚች ገራገር ሃገር ጋር ብቻችንን ሆነን ስንማማል ትዝ ይለኛል እንደትላንትና ሁሉ ቅርብ ሆኖ እስካሁን ይታየኛል:: ግን ዓመታት ነጎዱ...

የመጀመሪያ ቀን ሰላምታ ልውውጤ ውስጥ ሁሉ "...ተቀየርክ አረጀህ አረጅሽ ትልቅ ሰው ሆንክ ሆንሽ..." የመባባሉ ጉዳይ የዕድሜዬን ዘለላዎች እርከን ላይ እንዳፈጥ ጋብዞኛል: በርግጥም ገመድ ሲዘሉ ትተናቸው የወጣናቸው ሕንስቶች ዛሬ በትዳር ውስጥ የራሳቸዉን የኑሮ ገመድ ይዘዋሉ
አዲሳባ ትልቅ የኮንስትራክሽን መንደር ሆና ጠብቃኛለች አስፓልት ይታረሳል ቤት ይፈርሳል አዋራ ከመኪና ጪስ እኩል ይጨሳል የአዲሱ ቤንዚል ሽታ የአዱገነትን ጠረን ቀይሮባታል... በርካታ ፎቆች በቅለዋሉ ቁመታቸው ተመዞ መስተዋት ለብሰው ከማዶና ማዶ ሆነው እርስ በርሳቸው ይተያያሉ አዋራ ለብሰዉም ከፈካችው ፀሃይ ብረሐን ወስደው ሙቀት ይተፋሉ...
ሁሉ ነገር እንግዳ ሆኖብኛል ... አዳዲስ ሰፈሮች አዳዲስ መንገዶች አዳዲስ ብራንድ ተሽከርካሪዎች እንዲሁም አዲስ ትውልድ... የቆመ ቀለጠ የሮጠ አመለጠ ምትለዋ አባባል እንጭጭ እንደሆነች ነበርና አዱገነትን ትቺያት የወጣዉት አሁን ያ ቃል እሁን ሆኖ ሁሉም ይሮጣል... "በጣም ቢዚ ነኝ!" የሚል የኔ ቢጤ ሁሉ ልታገኙ ትችላላችሁ:: ብቻ ሁሉም በፊናው ደፋ ቀና ይላል አላውቅም አልችልም የሚል ቃል ከአፉ የሚወጣ ሰው ማግኘት ይከብዳል ሁሉም ሁሉንም ነገር ይሰራል ይሞክራል::
አዲሳባ ተ'ምቦርቅቃለች ድሮ እምቧይና ሾላ ይብቅልባት የነበረ ጥጋጥጓ ዛሬ በኮንደሚኒየም ቤቶች ጫካ ተውጧላ አዳዲስ ጎረቤቶች አዳዲስ ማሕበረሰብ አዲስ ቀበሌ ውስጥ ትጎራብተው ብራንድ ኒው ጄኔሬሽን ተፈጥሮዋል:: እነኚህ ቀበሌ ውስጥ አዳዲስ ቃላትና አዳዲስ ስራዎች ተፈጥረዋል::
እነኚህ ሰፈሮች ውስጥ ባጃጅ በሶስት እግሯ እየተፈናጠጠች ከመንገድ ዳር እበር ዳር ታደርሳለች እየተገለበጠች ትዘወራለች እየተነዳች ትገለበጣለች ፍንግል ስትል ትንሽ ብረቶቿ እና ነጭ ሸሚዟ አፈር ከመቃሙ ውጪ ምንም አትሆንም:: ጥቂት ከዞርኳቸው ኮንደሚኒየም... ለቡ... ሚኪሊላንድ... ጀሞ... መብራት ኃይል ጥቂቶች ናቸው እነኚህ መንደሮች እንደጥንቱ ጂኦግራፊካል የጥቅም ትሥስር የላቸውም ነዋሪው አፈር ከለበሰ የትላንትና የአፈር ቤቶች ይዞ የመጣው ማንነቱ በዛሬ ፎቅ ውስጥ አልጠቀመዉም:: ግን አዲስ ሕይወት ሀ! ብሎ ጀምሯል
የእርሪ በከንቱዋ ሴተኛ አዳሪ ኮንደሚኒየሞች ውስጥ ወንደኛ አዳሪ ማግኘት አትችልም: የሰንጋተራው እንስራና ጋን ጠጋኝ ዛሬ 'ሚጠግነው ገል አይኖርም... አንዱ አገልጋይ ሌላው ተገልጋይ ሆኖ መንደርን የመጋራት ጉዳይ አሁን የለም ግን ሲሚንቶ ግድግዳ ተጋርተው ይኖራሉ::

ሌሎች አዳዲስ ነግሮች
ድሮ ድሮ አዲሳባ ውስጥ ብዙ ነግሮች አይኖሩም'ንጂ ፌክ ነገር የለም ነበር ለምሳሌ ድሮ መኪና እምብዛም የለም'ንጂ ፌክ መኪና የሚባል ነገር አይታወቅም ዛሬ ስማቸው እንደዓይነታቸው የበዙ መኪናዎች በመዲናይቱ ይታያሉ:: ሴሜትሪካል ያልሆነ መኪና ልታዩ ትችላላችሁ ከኋላው በ BMW ተጀምሮ ከፊትለፊቱ በMERCEDES የሚያልቅ መኪና ታያላችሁ ከሁለቱ አንዱን ስም ስትፈልጉ መኪናው ኋላ ላይ የወንድማችሁን ወይም የእሕታችሁን ስም ልታገኙበት ትችላላችሁ:: ግን ይሄዳሉ ያገለግላሉ ምንም ያገልግሎት አቅማቸው 'ሚፈተሽበት የራሳቸው ዕድሜ ክልል ደርሰው ለመወደስና ለመወቀስ ባይበቁም ክንድ አውጥቶ በቄንት ሚዘውራቸው ጩፌሮች እንዳሸን ናቸው::
ከውጪው መልኩ ያማረ ፎቅ አይታችሁ ውስጡ ስትገቡ ግር ሊላችሁ ይችላል መጠኑ እኩል ያልሆኑ ድረጃዎች ሊያወላክፋችሁ ይችላል... የፀሐይን መውጪያና መግቢያ ያላተኮረ የመስኮት አቅጣጫ ሕንጻ ውስጥ ያልተለመደ አየርና ጠረን ፈጥሮ "ምነው መልክ ብቻ ሆነ" ብላችሁ አሜት ልትጀምሩ ትችላላችሁ... አናቱ ላይ ትኩስ ሲሚንቶ እየፈሰሰበት ምድርቤት ያለው ባንክ ስራዉን ሲያቀላጥፍ በርካታ ቦታ ታያላችሁ:: ሲሚንቶ ጠብ ቢልባችሁ ሚስማር ቂው ብሎ ቢያስደነግጣችሁ ትራንስፎርሜሽን ምትለዋን ቃል እያስታወሳችሁ ታልፋላችሁ... መቼም ኤልሚት(መከላከያ ቆብ) አትጠይቁም::
አንድ ጊዜ የቀለበት መንገድ ሲሰራ ያጋጠመኝ ቻይናው አንጸባራቂ ሰደርያዉን, ብረት ጫማና ኤልሚቱን አድርጎ ሲቆጣጠር የድልድዩን ፌሮ በሽቦ የሚቋጥሩና በዙሪያው ደፋ ቀና የሚሉ ምስኪኑ ያገሬ ባተሌዎች ደግሞ በሲልፐር ጫማና መላጣ ራሳቸዉን አጋልጠው በነተበ ካናቴራ አስተውያቸዋለሁ:: ይህ ግርምቴ የኢትዮጵያን እና የቻይናን አዲስ ፍቅር ምን ይሆን ወደሚለው አሻግሮኝ ከባልንጀሮቼ ጋር ብዙ ተወያየንበት::

አዎ ለውጥ ፈላጊ ነን እና አዲስ ለውጥ በርካሽ ለማግኘት እንዳቅማችን ቻይና ጋር መሄድ (ግድ ብሎናል) <= /የዘመኑ አባባል/ አቅም ኖሮን ወደምሕራቡ ብናቀና ጣጣው ብዙ ነው ኪስም ይጎዳል ቻይና ግን "ስንት ይዘሻል?" ብላ ነውን'ጂ ምትጠይቀው ስለአካባቢ ደሕንነት ስለ ሕዝቦች ምቾት ስለወደፊት ጉዳትና ጥቅም ግድ የላትም::
አሁን አሁን አብሮ የመጣ አንዳንድ ነገር መስተዋል የተጀመረ ይመስለኛል ግን ስሙ "ለውጥ" ይባላል አፍሪካ ውስጥ የራስን ምሶ የሌላዉን ምሶሶ አድርጎ መኖር ለውጥ ተብሎ መነገር ከተጀመረ ቆይቷል... እና አዲሳባም የዛሬ 10 እና 15 ዓመታት የነበረን የራሳችን ስልጣኔ ዛሬ በሌላ ተቀይሯል አንተ ቅደም አንቺ እለፊ ይሄን ልርዳህ ይሄን ላግዝሽ ተባብሎ ችግርን ተናቦ የመፍታቱ ባህላችን ቀርቷል የራስህ ደም አምሳያ የሆነው ዛሬን ጥቅም ካገኘ ደሙን ቀርቶ ሰብህናዉን ሁሉ ይረሳል:: ሃብታሙና ደሃው ተፋጦ ይኖራል ድሮ ባለጸጋው በመስጠቱ እንደሚደሰት ሁሉ ተመጽዋቹም ለባለጸጋው ዕድሜና ጤንነት ይመኝ ነበር... አሁን አሁን ግን ከላይ ያለዉም የታቹን ላለማየት ፊቱን በመኪና መስታወት ጋርዶ ሲሄድ የታቹም "ይድፋው!" ይላል::

ካስደሰቱኝ ለውጦች አንዱ የሬዲዮ ጉዳይ ነው: አዲሳባ ውስጥ ብዙ ዓይነት ኤፍ ኤም ራዲዮዎች አዳምጪያለሁ: ትርካው, ትምሕርታዊ ውይይቱ, ቀልዱ, ሙዚቃው በርካታ ነው እንደድሮው ለፍላፊና አድማጭ ብቻ ሳይሆን ዛሬ ሁለቱም ባንድ መንፈስ ሆነው የማየቱ ዕድል አጋትሞናል:: በርግጥ በርካቶች ቀኑ ሙሉ ስለስፖርት ብቻ ሲዘክሩ ይውላሉ:: እኔም ከንግሊዝ በመምጣቴ ብቻ ስለበርካታ ኳስ ተጫዋቾች ሕይወትና ቤቶቻቸው ተጠይቂያለሁ... ዕድሜያቸው አስራዎቹ ውስጥ ያሉ ወጣቶች ባብዛኛው በምንፈስ እንግሊዝ ሃገር ውስጥ ይኖራሉ ብል ማጋነን አይሆንም ራዲዮ ቀኑን ሙሉ ስለስፖርት ሳይሆን ስለስፖርተኞቹ የግል ሕይወት ሲሰብክ ይውላል... እናም ላንድ አዲሳባዊ ወጣት ሩኒ... ሚስቱ ምን ዓይነት መኪና እንደምትነዳ ለልደቷ ሩኒ ምን እንዳደረገላት ቤታቸዉን በስንት ብር እንደገዙት ለሆሊዴይ ምን ያህል ፓውንድ እንደሚያጠፉ... ማውቀ ራስን ከዘመኑጋ እንደማራመድ ስልጣኔ ይቆጠራል :: የዳኛቸው ወርቁን አደፍርስ መጽሓፍ አፋልጉኝ ያልኳቸው ወጣቶች አደፍርስ በሚለው ስም ተሳልቀዉብኛል::

እናም ቅኝቴን ልቀጥልና አዲሳባ የአፍርካን ቀንድ አየር እየተነፈሰች በሩቅምስራቅ ጨርቅና ማቅ እያጌጠች እና እያዘነች በዱባይ መስታወት ራሷን እየፎተተች በምሕራባዊ ሕልም ውስጥ ራሷን እየቃኘች ኑሮዋን እየገፋች ነው:: don't mind the dust የሚል ጥቅስ ለጥፋ ውስጥ ድረስ ከርሷን እንዳይ ስትጋብዘኝ የናፍቀኝ ወዟን ለማየት ባለኝ ጊዜ ውር ውርታዬን ቀጠልኩኝ::

እንደ እነአባቱ ልጅ ትላልቅ የ villa ብረትበሮቿ እና ጥርብ ድንጋይ ቤቶቿ ወይም ሃመርና ካዲላክ መኪናዎች ሳይሆን እነሙዘይድ የሚያሽኮረሙሟቸው እንስቶች ዓይኖቼን ሞሉት:: ውበትና ደምግባት ተሸክማ በሴትነቷ ተሽኮርምማ አንገቷን የምትደፋ ሴት ሳይሆን ዛሬ ያለችው ያላትንም የሌላትንም ውበት ለማሳየት አንገቷን ሰግጋ ደረቷን ምትነፋ ናት... አንድ ሁለት ቦታ "ካት ወክ እናሰለጥናንለን" የሚለው ማስታወቂያ ምንኛ ገቢያ እንደቀናው በአስትውሎቴ ታዝቢያለሁ:: አዱገነት ድሮም የቆንጆዎች መነሃሪያ ናት ዛሬም ብሶባታል:: የምሽት ክለቦች ውስጥ በቡድን ሆነው የሚጠጡ የሴት ጎረምሶች አይቶ መደነቅ ፋራ ሊያስብል ይችላል ባንድ መዳፍ ጣት የሚቆጠሩ እንስቶች አንድ ጠርሙስ ስቶልችኒያ ወይም ሺቫስ አውርደው ቢደንሱ ብርቅ አይደለም

አንድ ምሽት ከ H2O የምሽት ክለብ ቆይታዬ ስወጣ ቺቺኒያ 'ሚባለዉን ሰፈር ለመጀመሪያ ጊዜ አየዉት:: የሃምቡርጉን ሴንት ፖውል ወሲባዊ መንደር ነው ያስታወሰኝ:: በመብራት ገመድ ራሳቸዉን የተበተቡ ትናንሽ ቡና ቤቶች ውስጥ ውር ውር የሚሉ ጭኖች ሙሉ ቅያሱን ሞልቶታል ከየበራፉ በርካታ ጠረኖችና ሙዚቃዎች ወጥተው ቺቺኒያን አድምቀዉታል... የሰራተኛ ሰፈር, የሰባተኛና የድሮዉን ውቤ በረሃ የስራ ልምድና ጸባይ ባንድ አቀናጅቶ ባሕር ማዶ ተሻግሮ ፈጣጣነትን የወረሰ አዲስ የተፈጠረ ሰፈር ነው:: እሙሙ ለተለያየ ሃገር ዜጋ በተለያዩ ሃገራት ቋንቋ ይሸጣል ቋንቋ እንደወረደ ይነገራል ገጠመኝ እንደወረደ ይደሰኮራል እንጭጭ እሙሙም እንደወረደ ለአረብና ሌላ አፍሪካ ወንዶች ይሸጣል::

ከውጭ ምንዛሪ ጋር ባለመስታወት ፎቅ ስር በኒዮን መብራት ባናየዉም የእሙሙ ምንዛሪ በየቦታው እንደትንግርት ይወራል:: ወቅቱ የአፍሪካ መሪዎች ስብሰባ ነበር ታዲያ ምሽት ላይም ኮንኮርድ, ሜሞ እና ጋዝላይት የራሳቸዉን ስብሰባ ጀምበርን አስተኝተው ይቀጥላሉ እናም የውጪ ምንዛሪው ግብይት ይቀጥላል:: እነኚያ የጸሓይ ነጸብራቅ የጨረቃ ፍልቃቂ የመሰሉ የምሽት ንግስቶች እንደገቢያው ይመነዘራሉ::

አዲሳባ እንደበፊቱ ሁሉ ዘንድሮም ምሽቷ አቅፎ ያባብላል ጥሩ ጥሩ ክለቦች ተከፍተዋል በርካታ ላውንጅም እንደዚሁ ሄጄ ከወደድኳቸው ጥቂቶቹ
ላውንጅ እና ባር=> ሱባ (አንደኛ ነው) ላዩም ታቹም ያምራል /የመደብ ልዩነት አለው/ የተም, ብላክ ሮዝ, MKS እና ፋራናይት ሲሆን.... ከክለብ ደግሞ=> H2O, እና ኢሉዥን ምርጥ ቤቶች ናቸው
ምርጥ ክራውድ (ጥሩ ታዳሚ) በኔ ዕይታ 1ኛ ብላክ ሮዝ ሲሆን ይቅርታና ዲቄት የሆነ ታዳሚ ያለው ደግሞ ኢሉዥን ነው:: ከጃዝ ባር ካቡን ብዙም አልወደድኩትም ጣይቱ ጃዝ አምባ ግን አንደኛ ነው ከሸበሌዉም ይበልጣል what a wonderful poetic jazz ብዬ 6 የሞኒካን 6 ኳክብት ደርድሬላቸዋለሁ::

እስቲ ደግሞ ብሬክ እውስድና እመለሳለሁ ገና ብዙ ያልተዳሰሱ አሉ

እንሰት
ውሃ አጠጪ
ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1213
Joined: Sun Jan 30, 2005 1:14 am
Location: united states

Postby ጉዱ ካሳ » Wed Aug 01, 2012 2:49 pm

....ሻይቦያችን እንኳን በደህና ተከሰትክልን! ዋርካችን ውስጥ ስላየሁ ደስ ብሎኛል! ውቅሽ እንዴት ነህ አባ? ግን አዱ ገነት መቼ ነው የምትጭርለት? አንድ የሰፈራችን ዕብድ ምን አለ መሠለህ "በአሜሪካ ፈረንካ ልቤ ተነካ'
ዋንሽ ስለ ሸገር በፃፈው ነገር....በተለይ ስለሰፈርህ ቺቺንያ እምሙ እንዴት በተለያየ ቋንቋ እንደሚሸጥ ሲገልፅ በአይነ-ህሊናዬ ስትቋምጥ ታየኸኝና እኔም ልቤ ተነካልህ! አሳዘንከኝ- አንጀቴን በላኸው! አይዞኝ ወንድማለም አዱ ገነት ትሄድላታለህ! ካልሆነም እኛው እንልክሀለን! :)

ዋንሽ - አዱገነትን በመጠኑ ስላስቀኘኸን ምስጋናዬን አቅርቤአለሁ! እንደገናም ሌላ ገጠመኞችህን ታካፍለናህ ብዬ ተስፋ አደርጋለሁ!

ጦምናችን እንዴት ነህ ጃል? የኢንቨስተሮች ቤት ብቻ አንዳይመስልህ! ሁሉን ያካትታል አባ :) እንደሱማ ባይሆን ጌትሽና ውቃው.......መደባቸው ሌላ ቦታ ነበር :)
ጉዱሻ
____________________________________
የምንወደውን ብንጠላ የምንጠላውን ብንወድ በራሳችን ላይ ከፍተኛ የሆነ የባህሪ ለውጥ አመጣን ማለት ነው!
ጉዱ ካሳ
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 356
Joined: Wed Oct 22, 2003 6:22 pm

Postby ShyBoy » Wed Aug 01, 2012 7:42 pm

ጌታ: ጦሜክስ እንዲሁም ጉዱ እንዴት ናችሁ? እኔ ከዘንድሮው ሙቀት በስተቀር ይመስገነው በጣም ደህና ነኝ::

እዚህ ቤት ግን ጠላ ማስመጣት አይቻልም? ዋናው እና ዘጌው መጠው እስኪያጫውቱን ድረስ እስኪ አንድ ማድጋ ጠላ ላስመጣና እየጠጣችሁ አቧልቱ::
ShyBoy
ውሃ አጠጪ
ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1118
Joined: Tue Apr 04, 2006 10:36 pm
Location: Gojjam

Postby ፓን ሪዚኮ » Fri Aug 03, 2012 7:12 am

ባልቻ ...እንኳን ደህና መጣህ::
ፓኑ
Imageኢትዮጲያ ትቅደም
ፓን ሪዚኮ
አለቃ
አለቃ
 
Posts: 2044
Joined: Tue Aug 03, 2004 3:35 am
Location: ጎሃ ጽዮን

Postby ዉቃው » Tue Aug 28, 2012 1:46 am

በጠ/ሚ/ር ሞት ከባልቻና መዶሻው ግሮሰሪ ደንበኞች የተሰጠ የአቋም መግለጫ

አገሪቱ እንደምታውቀው...የግሮሰሪው ደምበኞች በተለያየ የስራ ዘርፍ ተሰማርተው ደከመን ሰለቸን ሳይሉ ሳይማር ያስተማራቸውን ህዝብ በትጋት እያገለገሉ ይገኛሉ :: ይህ በቀን ውሏቸው ነው :: አመሻሹ ላይ ደግሞ ባልቹን በማበልጸግ ልማታዊ ጠጪዎች መሆናቸውን በተለያየ ጊዜ አስመስክረዋል :: በርግጥ ደምበኞቹ ከጅማሮው የተለያየ የፖለቲካ አመለካከት ስላላቸው ..በአጀንዳው ላይ አንድ ዓይነት አቋም ላይ መድረስ እጅግ አስቸጋሪ የነበረ ክርክርና ውይይት አስከትሎ ነበር :: ይሁንና አንጋፋ ጠጪ ፓኑ ከልምድ በመነሳት ጥቂት እንዲጠጣ አስተያየት በመስጠታቸው ሁኔታው ቀስ በቀስ ሊረግብ ችሏል ::

በክርከሩ ወቅት
1- የጠ/ሚ/ር መኖሪያ ቤት ወይስ ታላቁ ቤተ-መንግስት ወይም የምኒሊክ ቤተ-መንግስት የሚለው አከራካሪ ነበር ::
2- አካለ ስንኩላን : ሕመምተኞች እና ጎዳና ተዳዳሪዎች አቋማቸውን ሲገልጹ እኛስ በምን እናንሳለን የሚል የቁጭት ክርክርም ተካሂዷል ::
3- ኛው ርዕስ ጠ/ሚ/ር እና መንግስታቸው በመጠጥ እና መጠጥ ነክ ጉዳዮች ላይ ያላቸውን አቋም በተመለተ ሲሆን ...ቤቱ በሙሉ ድምጽ ጠ/ሚ/ር ቢራ እና ዋይን መጥመቂያዎችን ወደግል ባለሐብትነት በማስተላለፍ ለዘረፉ ከፍተኛ አስተዋዕጾ በማድረጋቸው አመስግኗቸዋል ::
4- በዚህ ርዕስ የተነሱት ..ልማት : መንገድ : ጠላት ድህነትን እና ድሃን ማጥፋት : ትምህርት : ዴሞክረሲ እና የስብዓዊ መብት አያያዝ ጉዳዮች ተነስተው ....ከባልቻና መዶሻው ብሄራዊ ጥቅም አንጻር የማይመለከትን ነው ተብሎ አጀንዳው በአብላጫ ድምጽ ውድቅ ሆኗል ::

5- የሴቶችን ጉዳይ በተመለከተ ይሄው ስብሰባ ተወያይቶበታል :: በተለይም ሴቶች ግሮሰሪውን በቡድን እየሆኑ ማዘውተራቸው በጠ/ሚ/ር የራዕይ ዘመን የተፈጸመ መሆኑን ከቀድሞው ዘመን ጋር በማነጻጸር ቤቱ በአንድ ድምጽ ደስተኛነቱን ገልጿል :: ይህንን ጅምር ቀጣዩ ጠ/ሚ/ር ወደተናጠል የሴቶች አዘውታሪነት በማሳደግ እንትን ቀለል እንዲል እንድሚያደርጉ በተስፋ የሚጠበቅ ነውም ተብሏል ::

6 - ከዚህ ሌላ አንድ ለየት ያለ የውይይት አጀንዳ ያቀረበም ደምበኛ ነበር :: ይሄውም ምንድን ነው ...አሁን ሞቅ ብሎናልና [አንዳንዶቻችንም ሰክረናል ] በቃ ...ጠ/ሚ/ሩን ሄደን አንሰናበትም የሚል ነበር :: ይህ ሃሳብ ቤቱን እኩል ለሁለት ከፈለ :: እንዳንዶቻቸን... እኔን ጨምሮ እንሂድ እያልን በከፍተኛ መጯጯህ ስንፎክር ..በሙዝ የሚመራው ቡድን ደግሞ ተቃውሞውን አሰምቷል :: ይሁንና ጠ/ሚ/ሩን መሰናበት አለብን ያለን ቁርጠኞች ወደ ታላቁ ቤተ-መንግስት ያቀናን ቢሆንም ..መንገድ ላይ 'ቤተ መንግስቲ ተዝግቷል' ያሉንን ሰዎች በማመን ከመንገድ ተመልሰን ስብሰባውን ቀጥለናል :: ይህ ነገ በሚወጡ የውጭ አገር ጋዜጦች " ግሮሰሪው ለሁለት ተሰነጠቀ " እንደሚያስብል አላጣነውም :: ይሁንና

በመጨረሻም ወይይቱ በሰላም እየተካሄደ ባለበት ወቅት በቆሎ አዟሪዎች በወጣ መረጃ መስረት ...ስብስባችን በመንግስት ኃይሎች ህገወጥ ነው ተብሎ ተበትኗል ::

በዚህ አጋጣሚ የባልቻና መዶቻው ግሮሰሪ ..በራስ አነሳሽነት ያደረገው በጎ ምግባር የሚበርታታ ሆኖ ሳለ ..አንድ አቋም ላይ መድረስ ሳይችል ቀርቶ የአቋም መግለጫ አለማውጣቱ አሳዝኖናል :: ይሁንና ለሚቀጥለው ጠ/ሚ/ር ግን ከወዲሁ ተዘጋጅቶ የበኩሉን ለማድረግ በዚህ አጋጣሚ ቃል ይገባል ::

ግሮሰሪያችን ለዘላለም ይኑር !
ዉቃው
ውሃ አጠጪ
ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1038
Joined: Sun Jan 07, 2007 2:48 am

Postby እምቢ ለሀገር » Wed Aug 29, 2012 5:36 am

ሰላም ጋሽ ዋናው እንኳን በደህና ተመለስክ :!:
እንኳን ከሞት-ጉባዔ አምልጠህ መጣህ :!:

እስኪ በል ያችን ቃል የገባህልኝ የግብጦ አረቄ በትልቁ ፍንጃል ወዲህ በል! ማነሽ አንች...ደንባራ! አምጭው!...ይሄኔ ወቃው ቢሆን....ውቃቤ ቢስ!

ጋሽ ዋናው! እኔ ምለው የሰሞኑ ወቅቱን ያልጠበቀ እንባ ሳያጥልቀልቀን...መጠጣት አለብን!!...ድገሚኝ!!

ኖር! ኖር! ውቃቸው!(አድሀሪ)

ወቃው...የአቋም መግለጫው..የእኔን ስሜት ስላላካተተ እንደገና!!

በመጨረሻ...አ..አ..ምነው ጋሽ ዋናው..ይኸ የግብጦ አረቂ በእንባ ነው እንዴ የተጠመቀው..እንዴ!..ወይኔ!..ህ.ህ.ህ ጠቅላዬ!...ወይኔ!..አንበሳ ሀወይ!!..////

ሻሂ ቦይ..ለካ አንተም ወደህ አይደለም...እዛ ፖለቲካ ቤት እናባ እንባ ያለህ...አይ! ጠቅላያችን..ተጠቀለሉ..እኔ ልዘርጋ!..እኔ ልኑርልዎት!! እርስዎ ጡርግ...

እምብቾ ነኝ :!:...አደፍርስን የመሳሰሉ መጻህፎች ካልወደሙ
ትራንስፎርሜሽናችን ይፈነዳል :!:
ETHIOPIA ETHIOPIA ETHIOPIA
እምቢ ለሀገር
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 262
Joined: Mon Feb 13, 2012 5:08 pm

Postby ዉቃው » Fri Aug 31, 2012 2:13 am

ቀዝቃዛ ሻወር : ቀዝቅዛ ቢራ : ፓ ..እንዴት ደስ ይላል :: ምን ይሄ ብቻ ! ሌበር ዴይ ዊክኤንድ ደሞ ከች አለኧ !

GOD BLESS AMERICA ! የተባረከ ምድር !
በአጭር የተቀጨው ረጅሙ ጉዟችን !!!!
ዉቃው
ውሃ አጠጪ
ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1038
Joined: Sun Jan 07, 2007 2:48 am

Postby ፓን ሪዚኮ » Sat Sep 01, 2012 9:39 am

ባለ ሙሉ ስልጣኑን እንደራሴ ማን ገደላቸው???
Imageኢትዮጲያ ትቅደም
ፓን ሪዚኮ
አለቃ
አለቃ
 
Posts: 2044
Joined: Tue Aug 03, 2004 3:35 am
Location: ጎሃ ጽዮን

Postby sarandem » Mon Sep 03, 2012 6:07 am

ሰላም ለባልቻ እና ደንበኞች:: ዋናው አዲስ እንደምትሄድ ሳትናገር የመረሽከው የወጪ ላለመጋብዝ ነው :?: ለማንኛውም ብንታዘብም ስለ አዲስ የጻፍከው ክሽን ያለ ሪፖርት አሪፍ ነው:: ስትሄድ ተናግረህ ከሆነም ይቅርታ/ከዋርካ ርቄ ስለነበር/:: ባውቅ ኖሮ አዲስ ስለነበርኩ ባገኝህ ደስ ይለኝ ነበር::

የFM ሬዲዮዎች ዝግጅት ጥሩም መጥፎም ገፅታ አለው:: በእኔ እይታ 24/7 ሚወራው ስለ እግር ኳስ ነው:: ስፖርት ሲባል እግር ኳስ ብቻ ነው የተባሉ ይመስል:: ሁሉንም ሬድዮ ጣቢያዎች ስትቀያይር ምትሰማው ስለ አውሮፓ እግር ኳስ ብቻ:: ለዛውም በተመሳሳይ ሰአት:: ይህ የፓለቲካ ማደንዘዣ መሆኑን ሰው በብዛት አያርፈውም:: ቢያውቅም አማራጭ መዝናኛ እጦት ሳየወድ በግድ ሶከር ተከታታይ ሆኗል:: አስገራሚው ነገር የዚህ የስፖርት ተንታኞች ጥራዝ ነጠቅ አዋቂነት እና ተንታኞች መበራከት ና ከመረጃ መረብ እየሸመደዱ ሚያቀረሹት ነገር ነው:: አዲስ ላይ ስለ ኢትዮጵያ ድህነት ሳይሆን አርሴናል መሸነፍ ሚያንገበግበው ትውልድ ቢበራከት አይገርምም:: ሌሎችም አንፍር ጋዜጠኛ ተብዬዎች አሉ...እንደ ሰይፉ ፋንታሁን ያሉ...ብቻ ሆድ ይፍጀው:: አልፎ አልፎ ማህበራዊ ውይይቶች ፓለቲካን ሳይነኩ ይካሄዳሉ ...ከድሮ ሲታይ መልካም ጅምር ነው:: ሌላው ያስተዋልኩት ነገር የሀገር ውስጥ ፊልሞች እንደ አሸን መፍላት ነው:: አብዛኛው ቆሽት ሚያደብኑ ቢሆንም አልፎ አልፎ ደህናዎችም ተመልክቻለሁ:: በደረቁ ቢበቃኝሥ :?:
sarandem
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 674
Joined: Tue Jul 11, 2006 8:59 am
Location: Nomad Cafe

Postby ዉቃው » Tue Sep 04, 2012 8:19 pm

ሳራንደም ፍሬንድ ....እንኳን ደህና መጣክ :: ይቀጥል ብያለሁ ...ይቀጥል ....:: ዛሬ በኔ ጣለው :: እየጠጣህ አጫውተንማ !

እምቢ ለሀገር ...አድሃሪ አልከኝ ? እኔ አድሃሪ ለመባል ከብቶች አሉኝ አላልኩ : እኛ እያልኩ ራሴን አልጠራሁኝ :: ለራሴ ምስኪን ! ብቻ ይሁንልህ :: ቀምቅመህ የሌላውን ብሶት እኔ ላይ ተወጣህ :: ቆይ ትንሽ ልወሳስድና እኔም እጨፍርብሀለሁ ::
በአጭር የተቀጨው ረጅሙ ጉዟችን !!!!
ዉቃው
ውሃ አጠጪ
ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1038
Joined: Sun Jan 07, 2007 2:48 am

Postby sarandem » Wed Sep 05, 2012 8:18 am

ዋው ሻይ ቦይ የጠፋ ሰው እና ውቃው አማን ነቹ:: ተጠፋፋን ነው ሚባለው::
ከኤርፓርት ብንጀምር እንደዛ የተወራለት አዲስ የተሰራው ተርሚናል ደንበኞችን የማስተናገድ አቅሙ በጣም ውስን ነው:: በተለይ ከሀገር ለመውጣት ኤርፖርት ላይ አራት ጊዜ መሰለፍ ይኖርብናል:: 1. ገና ሲገባ በር ላይ 2. ቼክ ኢን ለመሆን ያለው የሰልፍ ርዝመት የድሮ ቀበሌ ህብረት ሱቅ ተመልሶ መጣ ያስብላል 3. ቪዛ ቼክ ሚደረግብት እንደገና ረዥም ሰልፍ 4. ፎቅ ላይ በየ በሮች ላይ ለመግባት ሌላ የሴኩሪቲ ፍተሻ:: እንደገና :wink:
ሰልፍ መኖሩ ማይቀር ቢባልም የሚታክት እና ከ 3 እስከ አራት ሰአት ሚፈጅ መሆኑ ግን በድህነት ብቻ መሳበብ የለበትም:: ያሉት ካውንተሮች ውስን ቢሆኑም ሁሉም ግን በሙሉ አቅማቸው አገልግሎት እንዲሰጡ ማድረግ አይቻልም :?: ሌላው የአየር መንገድ አስተባባሪዎች እና የተወሰኑ ሰዎች ሰልፍ አለማክበር ሚያበሳጭ ነገር ነው:: ለምሳሌ እኛ 4 ሰአት እየጠበቅን ወደ ፓሪስ ሚበሩ እና ናይሮቢ ሚበሩ በቅድሚያ /ያለምንም ሰልፍ /ሲስተናገዱ ነበር:: ይህንን ያበሳጫቸው የሌላ ሀገር መንገደኞች/እኛ ሀገር ኮምፕሌን ማድረግ ከፀር ልማት ስለሚያስፈርጅ/ ለአስተባባሪዎች እያደረጉት ያለው አሰራር ትክክል እንዳልሆነ ሲነገራቸው የመለሰላቸው መልስ '' የእነርሱ በረራ ከ 20 ደቂቃ በኃላ ስለሚዘጋ ለዛ ብለን ነው የሚል ነበር/:: ሆኖም ይህ ነገር 1 ሰአት ተራዝሞ የእነሱ ሲጠናቀቅ ...ጅዳ ... የጅዳ መንገደኞች... የሚል ቀጠለ..አቤት ወደዚያ ሚሄደው ተሳፋሪ ብዛት...ያም ሆነ ይህ በረራዎችን በየ ካውንተሩ እየከፋፋሉ እንደመስራት ሁሉም የበረራ መስመሮች ሰለሜ ሰለሜ በሆነ ሰልፍ ነው እየተስተናገደ የነበረው::

ኢትዮጵያ አየር መንገድ ቦይንግ 787 ድሪምላይነር ባለፈው ወር አስገብቶ ነበር:: ያው በፈረደበት FM ራድዮ ብዙ ተባለለት:: ቦይንግ 787 በመግዛት በአፍሪካ የመጀመርያው ካአለም ደግሞ ሁለተኛ ከጃፓን ቀጥሎ ተባለ.... 20% ነዳጅ ይቆጥባል.(ከ767 ሲነፃፀር/...አዲስ አበባ እንደገባ ከሰማይ ላይ እንዳለ ፎቶ አንስቶ ወደ አየር መንገዱ የላከ በከባዱ ሽልማት አለው.....አየር መንገዱን ከሌሎች አፍሪካ : መካከለኛ ምስራቅ እና ሩቅ ምስራቅ አየር መንገዶች ተመራጭ ያደርገዋል... ብዙ ተባለ...ብዙ ተጋነነ:: እኛም አሞራ በሰማይ ሲያይሽ ዋለ አልን --አስባልን... ወይ አባይን ያላየ ...ሄዶ ይይ ነው የተባለው :!: የኢትዮጵያን አየር መንገድን ከኳታር ለማነፃፀር መሞከር ኤሊን ከጥንቸል እንደማወዳደር ነው:: ኢምሬትማ አይወራ የ አንድ በረራ ካውንተር አዲስ አበባ ያለው ይሆናል:: ማልክደው ሀቅ በረራዎች እንደድሮ ብዙም አይዘገዩም:: ሆስተሶች መስተንግዶ ጥሩ ነበር:: በተረፈ ኤርፖርት ላይ ያለው መስተንግዶ በትኬት ቢሮዎች ፒያሳም .. ጣና በጣም ኃላ ቀር...ባትፈልግ አትሳፈር ሚመስል /ብሄራዊ ትያትር ይሻላል/:: እንደኔ አየር መንገዳችን ከአንድ ነገር በቀር ተመራጭ ሚያደርገው ነገር አጣሁብት:: ብዙ ኪሌ መፍቀዱ:: ከዛ ውጭ በፍላይት ላይ ማዝናናት ቦሪንግ...
በዋጋው ሰማይ ጠቀስ...መቀመጫ ወንበርማ አይወራ አይሱዙ ቅጥቅጥ ስታይል ..እንደኔ ረጅም እግር ላለው መዘርጊያ ይቸገራል ...ሲያቀብጠኝ አስተናጋጇን የጥርስ ሳሙና አና የጥርስ ብሩሽ አትሰጡም እንዴ :?: ስላት ለ ኢኮኖሚ ክላስ መስጠት ካቆምን ቆይተናል አለችኝ:: በጣም ያሳፍራል:: በኢንተርናሽናል በረራዎች የጥርስ ሳሙናዎች ይዞ መግባት ተከልክሎ እንዲህ አይነት መልስ ማግኘት.. ያሳዝናል:: በሉ ቀጣጥሉበት አድዮስ
sarandem
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 674
Joined: Tue Jul 11, 2006 8:59 am
Location: Nomad Cafe

Postby ዋናው » Sun Sep 09, 2012 12:31 pm

ዛሬ በጥቁር ነው ምፅፈው :wink:

ውቅሽ የአቋም መግለጫዉን ለቅሶው በርዶ የዘን ተበልቶ የእድር ዕቃ ከተመለሰ በኋላ ስለሆነ ያየዉት ይቅርታ አንቀጽ 5ን ግን ውድድ አድርጌያታለሁ ከለቅሶዉም በኋላ ተግባራዊ ይሆን ዘንድ አብዮታዊ ትግላችን መቀጠል ይኖርበታል ባይ ነኝ በተረፈ ሁሉንም ኬፍ ብያለሁ እምቢ ለሃገር የግብጦ አረቄ ለሻይ ቦይ ነበር ያመጣዉት ፈቃደኛ ከሆነ ያካፍልሃል የሞላማሩ ኡዞ ከተስማማ እሱን በሻይ'ም ቢሆን ልስጥህ : ሰረንደም በስንት ዘመኔ ስምህን አየውት ባክህ ... ስማ ይሄኔ እዛ ተላልፈናል ማለት ነው: ለነገሩ ዳያስፖራ ላለመምሰል አንድ ሳምንት ቤቴ ተለማምጄ ነበር: ሰዉ ዳያስፖራ በጣም ጠልቷል ሁሉም ዳያስፖራ ጉረኛ ትእምክተኛ ፖለቲከኛ ምናምን ይመስላቸዋል... ፎቅና ሕዝብ በዛ ብለህ ወሬ ከጀመርክ ሙድ ይያዝብሃል...

እስቲ እንቅደድ ደግሞ


በአንድ ወር ከምናምን ብቅ ብዬ እናማ'ላችሁ ብዬ ልጅመር... አይደብራችሁም አይደል?
ስሙኝማ ምን ይሄ ኦሎምፒክ ቢዚ አድርጎኝ'ኮ ነው በዚህ ላይ እሱ ባለቀ በሳምንቱ ሃዘን ነበረብን... አንዱ በቀደም አግኝቼው ምን ቢለኝ ጥሩ ነው?
"አንተ...ሃገር ቤት መርዝ አርከፍክፈህ ነው እንዴ የመጣከው? ደርሰህ ከመምጣትህ ሞት ፈጃቸው'ኮ"
አለኝ... ለማንኛዉም ነፍስ ይማር! ብያለሁ ሃዘኑ ለከበዳቸው መጽናናትን በሃዘኑ ለሳቁትም ለተሳለቁትም ልብ መግዛትን እመኛለሁ!

እኔ'ምለው... ትዝታዬን ያ ሾካካ በልግ መጥቶ በጉሙ እንዳይውጥብኝ ወደ አዱገነት ልሩጥማ... መቼም ያን ሁሉ ስዘበዝብ ስለዋጋ ሳላነሳ ዝም ስል "እንዴት ነው ዋንቾ በስፖንሰር ነው'ንዴ ይሄደው?" ሳትሉኝ አልቀራችሁም:: በገባው በስንተኛው ቀን ባለንጀሮቼ ግሪክ ክለብ የሚባል ቤት ጋበዙኝ ይሄ የመጀመሪያዬ ግብዣ ነበር እናም ጥሩ የፈረንጅ ምግብ ከጥሩ የሃበሻ ቢራ ጋር ተስተናገድንና ቢሉ ሲመጣ አስደነገጠኝ 9መቶ ምናምን ነበር: የፈለገ ተጋኖ ቢነገረኝ የዚህን ያህል አልጠበቅኩም ነበር::
ግን 'ሚገርመው የትም ቢሄዱ ሙሉ ነው ሰዉ ተወደደም አልተወደደም ይበላል:: በሬ 25 እና 30 ሺህ ብር ተገዝቶ ዘንድሮም ሰርግ ይደገሳል:: አንድ የሰርግ ፎቶግራፈር ከ30 እስከ 40 ሺህ ብር ይጠይቃል:: የበሬን ዋጋ ሲነግሩኝ "መቼም በሬዎቹ ሚሸጡት 'ንደድሮ ሜዳ ላይ ሳይሆን ሾው ሩም ውስጥ መሆን አለበት" አልኩኝ የወተት ላሞችማ ሊብሬ ሁሉ ሳያስፈልጋቸው ይቀራል:: ላንድ ምሽት መዝናናት ሺ ብሮች መያዝ ግድ ነው:: ድሮ ጥቂት መቶዎች በየግላችን አዋጥተን ላንጋኖ 4 እና 5 ቀናት ተዝናንተን እንመጣ ነበር ዛሬ ያ ብር ነዳጅ ከቀዳም ጥሩ ነው:: አብዛኞቹ ላንጋኖ ዙሪያ የተሰሩ መዝናኛዎች (ሪዞርት) የሚያስከፍሉት በዶላር ሂሳብ ነው:: ላንድ ቀን አዳር ከ150 ዶላር በላይ ያስከፍላሉ
በዚህ አጋጣሚ በጣም ጥሩ ጥሩ ሪዞርቶች ተከፍተዋሉ:: ቢሻንጋሪ Xትርምሊ ጃንግል ነው ግን ያምራል ያስፈራልም:: ሳባና እጅግ በጣም ያምራል ሚስተር ፌራሪ ጥሩ አድርጎ ነው የሳራው (ስፖትለስ):: አቅሙ ቢኖረኝ ዘላለሜን እዛው ብሞነክስ ደስ ይለኛል::

ወደ አዋሳ መሄዱን ልተወዉና እስቲ ወደአዱገነት ልመለስ

ሰኞ ረፋዱ በኢ.ሰ.አቆጣጠር 5 ሰኣት አካባቢ ነው:: ፒያሳዬን ላያት ወደ ቼንትሮ አቀናው:: ሲኒማ ኢትዮጵያ ዘንድሮም ሽሮ ቀለም ግድግዳዉን እንመነቸከ ከስሩ ሊስትሮዎችን እና ጃብሎዎችን ያሰማራል (በዚህ አጋጣሚ ዘንድሮ ከሊስትሮ ድሮ ምናውቀዉን የጉራጌ አክሰንት መጠበቅ ብርቅ ነው ሁሉም ማለት ይቻላል የሌላ ብሔር ደቡብ ሕዝቦች ናቸው)
ቼንትሮ ዛሬም ልብ አርስ ማኪያቶ ከቆንጆ ፀሓይ ጋር አለ:: ልብ አውልቅ ሎተሪ አዟሪዎች... ጨቀጫቃ ጋዜጣ ሻጮች... ከበዙ የኔቢጤዎች ጋር ቼንትሮን ይጋሯታል:: ማኪያቶዬን በስስት ጨርሺያት ወደመኮንን ባቅላባ ቤት አቀናው ወደውስጥ ባልገባም ከውጪው ገርመም አደረግኩት ያው እንደድሮው ነው ገና ብዙ ዘመን ሁሉ ሊኖር የዛተብኝ መሰለኝ:: ድፍን አዲሳባ ልብሷንም ሙዷንም ስትቀይር ፒያሳ ብቻዋን ኦልዲስ ጉዲስ ብላ ሙጢኝ ያለች ይመስላል::
የቱራኮ ላዛኛ የማስተርሰን ጉላሽ የኤንሪኮ ቦክሰኛ ኬክ የቶሞካ ቡና የኦሮስኮፕ ኮተሌት የዋጋቸው ዜሮ ዜሮዎች ጨመሩ'ንጂ ያው እንዳሉ ነው:: ፒያሳን ስልጣኔ የዘለላት ይመስላል ማዘጋጃ ፎቅ ቁልቁል በሰማያዊ ቆርቆሮ አጥር የታጠረው ሜዳ ዛሬም ሰማይ ጠቀስ ፎቅ ይቆምበታል ተብሎ ይፎከራል ሰውዬው አጥረው ላሽ በማለት እየመሩ ነው ተብለው ይታማሉ:: 'ሚገርመው ያ ሜዳ እስከዛሬ ክፍት ቢሆን ስንት ስፖርተኞች'ን ታፈራ ነበር::

አንድ ቀን ወደ አዲሳባ ዩኒቨርስቲ/ ስ/ጥበብና ዲዛይን ትምሕርት ቤት ወይም በድሮው አርት ስኩል አቀናው:: የተማሪዎች መመረቂያ ስራ ለአውደ-ርዕይ /ኤግዚቢሽን/ ቀርቦ ነበር:: ገብቼ ከጀርባ ጋሽ ታደሰ ቆርቁረው ካቆሙት ሃውልት ስር ሆኜ በትዝታ ወደውኃላ ላጥ አልኩኝ:: አርትስኩል ዛሬ ተቀይሯል ጊቢው ሆዱ ሰፍቷል ይቅርታና ከወደአናቱ ጠቧል ብል ፎታች ወይም አሜተኛ አታድርጉኝ:: ስራዎቻቸውን አይቼ ትንሽ አዘንኩኝ ይህንን ስል ግን አሁንም ቢሆን የአርትስኩል የነበቄ መንፈስ በአያሉ ተማሪዎቹ ውስጥ ይታያል (እንደድሮው ባይሆንም)
የዲዛይን የኮምፒውተር አኒሜሽን ወ.ዘ.ተ ተብለው የተቀጸሉትን ኮርስ የወሰዱት ተማሪዎች ስራዎች በሙሉ የማየቱ ዕድል ባይገጥመኝም እዛ የቀረቡትን አይቼ ዝም ማለትን መረጥኩኝ /ሰው ሃገር ሆኜ ቀጠነ ወፈረ ማለቱ አግባብ አይደለምና/ ለአርትስኩላችን ግን ሁሌም ምመኘው ያ የጥንቱ መንፈስ እንደጉም በኖ እንዳይጠፋ ብቻ ነው::

በተረፈ አዲሳባ ውስጥ ያለው የሥዕል እንቅስቃሴ ከምንም በላይ ያስደሰተኝ ነገር ነው... ድሮ እኛ እዛ ሳለን "ሠዓሊ ለቢራና ለቀለም ካገኝ ምንም አይፈልግም" እያልን ነበር 'ምንኖረው ዛሬ ግን ሠዓሊዎች ቢያንስ ስራዎቻቸዉን ሸጠው ከቀለምና ቢራ አልፈው ያንን ውድ ኑሮ ይገፉበታል:: በዚህ ላይ ሃገር ውስጥ ያለ ባለሃብትም ብሩን ቆጥሩ ካገሩ ሠዓሊ ሥዕልን መሸመት ጀምሯል ድሮ አንድ ትልቅ ፔንቲንግ 3 ሺህ ብር ተለጥፎበት ሲታይ ሰዓሊው እንደእብድ ስዕሉ እንደተአምር ይታይ ነበር አሁን ግን እኔ እዛ በነበርኩበት ቆይታዬ ፊትለፊቴ የ40ሺህ ብር ፔንቲንግ ሲከፈልበት የማየት ዕድሉ ገጥሞኛል /ከዛ በላይም አለ/
ድሮ 'ማውቃቸው ጓደኞቼ ያሉበትን የዘመን እርከናቸዉን በረቀቀ ጥበብ ባደገ ችሎታ በብሩሽ ሲያሳዩኝ ፈገግታዬ ገንፍሎ ነበር:: በዚህ ላይ እንደድሮው በጣት ሚቆጠሩ ጋለሪዎች ብቻ አይደለም ዛሬ ስዕል የሚሰቀለው በየሬስቶራንቱም ተሰቅሎ ይሸጣል:: ፓናል ዲስከሽኖች ይኪያሄዳሉ የልምድ ልውውጥ ይደረጋል:: ገ/ክርሶስ ደስታ በስሙ ጋለሪ ተከፍቶለታል ምርጥ ጋለሪ... ጎት ኢንስቲቲዩት ከሮሚና ፎቅ ላይ ወጥቶ ከገብረክርስቶስ ጎን ተሰርቷል:: ብሔራዊ ሙዚየም የአዳዲስ እና ነባሪ ሠዓሊያን ስራዎች ተቀብሎ ለሕዝብ ያሳያል ለዛዉም በነጻ... ብቻ በስዕል በኩል ያለው እንቅስቃሴ ጥሩ ነው ይህንን ስል ምን የታዘብከው ደካማ ጎን አለ ካላችሁኝ ኦፍኮርስ አለ ጥሩ የስዕል ሸማቾች ከውጪ ሲገቡ በደላላ ወሬውን ተቀብለው ማታ ለቅልቀው ጠዋት ላይ በጸጉር ብሎው ድራየር ሸራ 'ሚያሞቁትን ከየትኛው እንደምፈርጃቸው ግራ ገብቶኝ ነው የመጣዉት:: ሌላው አንድ ሁለት ቦታ ካየዋቸው አውደ-ርዕይዎች ላይ ያገኘዋቸው ሰዓሊያን ላዋራቸው ስሞክር ከቀለሙና መስመሩ ጀርባ ያላቸው ብስለት ማነስ ከየት እንደጀመሩና ማን እንደጀመራቸው /ጥበቡ ወይስ እነርሱ/ ብዬ እንዳስብ አድርጎኛል::

በሚቀጥለው ቅኝቴ ደግሞ የኢትዮጵያ ሲኒማ ግስጋሴ ሊደፋ ወይስ ሊሰፋ? በሚል ርዕስ ላይ እዛ ሳለው ከነበረኝ የልምድ ልውውጥ ጋር ሰፋ አድርጌ አቀርብላችዋለሁ::

ሰላም ቆዩልኝ ..... እረ እስቲ አፌ ደረቀ ካቲካላ ስጡኝ::
ጥበብ ከእኔ የበለጠ ጠንካራ ናት እኔ እንደምፈልገው ሳይሆን እሷ እንደፈለገችው ታደርገኛለች::
ዋናው
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 2806
Joined: Tue Dec 16, 2003 5:29 pm
Location: ሕልም ዓለም

Postby sarandem » Mon Sep 10, 2012 8:27 am

:lol: :lol: :lol: አባ ውቃው ያራዳ ልጅ ታንክስ ለግብዛው ::
ዋናው ...ስለ ዋጋ ግለት ሳታወራ ምነው ዘገየህ :?: ውነትም በስፓንሰር የሄድ አስመስልከው:: :) አንተ ግን ከመች ጀምሮ ነው ካቲካል መጠጣት የጀምርከው :?: ያው ፓውንዱ እንደ ፈንድሻ በሀያ ምናምን ስታባዛ ስታፈነዳ ቆይተህ ካቲካላ አጠጣጥህ ከከባድ ሚዛን ወደ ቀላል ሳትንሸራተት አንዳልቀረህ መገመት ይቻላል:: ባንዴ ውስኪ ላይ ጉብ ባለማለትህ አድናቆቴ ከፍ ያለ ነው:: አቤት በውስኪ እና በካቲካል መሀል ስንትና ስንት መጠጥ አለ :?:

:arrow: በየሰፈሩ የድራፍት ሀውስ መበራከት በጣም ሚያስደምም ነገር ነው:: ሜታ ድራፍት ሀውስ የሚል አይታቹ ሳትጨርሱ ጊዮርጊስ ድራፍት ሀውስ አዛው አጠገቡ ታገኛላቹ::የድራፍት 11 % እድገት መመስከር እንችላለን :twisted:
አዲስ ውስጥ ሌላው የተገነዘብኩት ነገር በጣም ብዙ መንገዶች ውስጥ ለውስጥ የኮብል ስቶን ንጣፍ ማግኘት ነው:: ስንትና ስንት ተስፋ የተቆረጠባቸው መንገዶች ኮብል ስቶን ተነጥፎላቸው ማየት ሚያስደስት ነገር ሆኖ አግኝቼዋለሁ::(ልማታዊ ሪፖርተር ሆንክ እንዴ ? :wink: )
የመቶ ብሩ ነገር ያው ፌስ ቡክ ላይ አይታቹታል እንደ ኡሴን ቦልት በአስር ሰክንድ ነው ሚጠናቀቀው:: ያው እኛ በዛ ከተባለ ከማዘር ቤቶች አልፈን ቁርጥ ቤት ብንከሰት በፕላንን እና በፕሮግራም ነው:: አንድ ቀን ያለ አቅሜ ሶስት የወዳጅ አገር እንግዶችን እጋብዛለሁ ብዬ ዮድ አቢሲኒያ(ቦሌ ጫፍ) ተከሰትኩኝ አምስት ሆነን ገብተን 1800 ተፈለጥኩኝ:: ባህላዊ ጭፈራ... ከባህላዊ ምግብ ጋር...መጨረሻ ላይ በሞቀ ውሀ እጅህን አስታጥበው እጅህንን ይቆርጡሀል:: ያው ከዛ በኃላ መንገድ ላይ ብቻህን እያወራህ መሄድ ነው:: በነገራችን ላይ መርካቶ(ጎጃም በረንዳ አከባቢ) ቼልሲ ሚባል ምግብ ቤት አለ:: ቅቅል ድሮግባ በዛ ያለበት... ክትፎ ቴሪ የሌለው ...ብሎ ሰው ሲያዝ መደነቅ አይገባም :: ዱለት ገባ ያለ.... ክትፎ ገባ ያለ...ብሎ ማዘዝ ኖርማል እና ስፔሻል ከሚሉ ቃላት ለጥቀው የተጨመሩ ግሳንግሶች መሆናቸው ነው::
ሰዉ:- ያለቀለት../...ቀጭን/ ወፍራም/ግማሽ... ሻይ::...
ነጭ../ጠቆር ያለ/.. እንደወረደ(ማክያቶ) ብሎ ካልሆነ በቀር ያለ ግሳንግስ ምንም ነገር አያዝም...አንድ አስተናጋጅ 5 የተዘበራረቀ ማኪያቶ አዘነው ስናበቃ አምስቱንም አንድ አይነት አሰርቶ መጥቶ ....ማነው ጠቆር ያለ ብሎ ያዘዘው.?..ጠቆር ያለ የመሰለውን ይሰጠዋል... ማነው ነጣ ያለ ያዘዘው.?.. ደስ ያለውን መርጦ ያስቀምጣል:: እንዲ እያረገ ሲያስቀምጥ ፍርስ ነው ያደረገኝ:: ወይ :!: የአዲስ አበባ ሰው ውሀ ቀጠነ ትዛዝ ይገርመኛል:: ይህ አባዜ መጽሀፍ ላይ ታዩታላቹ...የስብሀት ገ/እግዚአብሄር 'ሌቱም አይነጋልኝ እንደወረደ ' ተብሎ ድጋሚ ታትሟል ::
:arrow: ፒያሳ አሁንም የቱሪስት መስህብ በሆኑ ብርቅዬ አገር በቀል ኬክ ቤቶች እና በወርቅ ቤቶች እንደኮራች እና እንደ ዘነጠች ነው:: መኮንን ባቅላቫ ቤት... አራዳ ባር......ቼንትሮ ..ካስቲሊ....ቶሞካ(የቤቱ ጣራ አሁንም በቡና እንደጠቆረ ነው ) :lol: ያው እንደ ጥንቱ ናቸው:: ትሪያኖ ታድሶ ከዘመኑ ጋር ለመዘመን ሙከራ ለማድረግ ሞክሯል(ሌሎቹም ይልመድባቹ ጥሪ አቅርቧል:/: ፕያሳ ከሄዳቹ የህዝብ ሽንት ቤቱን መጎብኘት ግድ ነው:: እንደ ድሮ በነጻ መጠቀም የለም ... ተሰልፋቹ ወረፋ ሲደርሳቹ ለውሀ ሽንት25 ሳንቲም (?) ትከፍላቹ ለከባዱ ዋጋውን አልጠየቅኩም... ከክፍያ በኃላ ደስ ሚለው ነገር ብጫቂ ሶፍት ይሰጣቹዋል ::

ባለችን አጭር ጊዜ ሶደሬ ለመሄድ ተሞክራል... ሶደሬ መግቢያውን 39 ከማድረግ ውጭ ምንም የተቀየረ ነገር የለም .መዋኛው ገንዳው ብትሉ...ዙርያውን...አባድር...ያው እንደ ጥንቱ የጠዋቱ..ነባር ጦጣዎቹ ባቅማቸው አሰራረቁን ዘመናዊ እና ኮምፒተራይዝድ ባደረጉበት ዘመን ሶደሬ ያደራ እቃነቱ እንደተጠበቀ ነው::ሩም ለመያዝ ሞክሬ ነበር አልጋው በጣም አሳፋሪ እና ቆሻሻ ነው ከነሙሉ ግማቱ:: ዋጋው ለአንድ አዳር 600 ብር ባላይ ነው(?) ዋጋው ከንጽህናው ጋር አብሮ አይሄድም:: እንደዛ ሚገማ ከሆነ 1000 ማስገባት ነበረባቸው::ይብላኝ ለእነርሱ እንጂ መኪና የያዘ ሰው ናዝሬት ሄዶ ማደር ይሻለዋል:: አዲስ አበባ 500 ሚከራይ አልጋ ናዝሬት በ 200 ማግኘት ይቻላል :: በመቶ ኪሎ ሜትር ይህንን ያህል ዋጋ ልዩነት በጣም ይገርማል ::
ከሪዞርት ሆቴሎች የማየት እድሉን የደረሰኝ ከሁለት አመት በፊት ደብረዘይት ሚገኘውን ኩሪፍቱ ነበር:: በጣም የወደድኩት ቦታ ነው:: ሁለት ነገር ብቻ ደብሮኛል:: መንገዱ ከዋናው መንገድ ራቅ ከማለቱ ብዙ ኮርኮንች መሆኑ:: ሌላው ማሳጅ ሚያደረገው ለወንድ ወንድ መሆኑ አልተመቸኝም:: ወንድን ወንድ ማሳጅ ሲያረግ ኮምፎርት አይሰጠኝም :: ለሴቶችም ማሳጅ ሚያስደርጉት በሴት ነው:: ምንድነው ነገሩ? አበሻዊ ይሉኝታ እና ወግ አጥባቂነት::እስቲ ሳንረገጥ ይህንን ያህል ካወራን አይበቃም :?: ችርስ
sarandem
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 674
Joined: Tue Jul 11, 2006 8:59 am
Location: Nomad Cafe

Postby ፓን ሪዚኮ » Sun Sep 23, 2012 9:17 am

ሰላም ቤቶች እንደምኑን ከረማችሁ?

እኔ ፈረሴም እጅጉን በጣም ደህና ነን:: ያው ኢኮኖሚው ከ11 ወደ 0 መግባቱ ቢያስደንቀንም ማለቴ ነው ::
ፓኑ አባ ፈርዳ
Imageኢትዮጲያ ትቅደም
ፓን ሪዚኮ
አለቃ
አለቃ
 
Posts: 2044
Joined: Tue Aug 03, 2004 3:35 am
Location: ጎሃ ጽዮን

PreviousNext

Return to Warka Intimate - ዋርካ ፍቅር

Who is online

Users browsing this forum: No registered users and 4 guests