ባልቻና መዶሻው ግሮሠር=> ተጠፋፋን

The Love Forum (love, relationship) (የኔ ቆንጆ እንተዋወቅ :-)

Postby ያባቱልጅ » Mon Oct 01, 2012 5:56 pm

የተከበሩ ዋናው ከሁሉ አስቀድሜ እንኩዋን ሰላም መጡ እላለሁ

የመዘግየቴ ምንክናያቱ ኮምፒተራችን ከአገልግሎት ውጪ በመሆኑ ነው......በተለይ ሳይበር ሎግ ማድረግ አሻረኝ ብሎ ነው::

ጨዋታው ተመችቶናል.....100 ጊዜም የተመላለሱት እንዲህ አዲስ አባን አገላብጠው አላዮዋትም.....አላስተረፍካትም ቅቅቅቅቅ

እንግዲህ ታሁን ወዲያ 12 ወር መቁጠርህ ነው ቅቅቅቅ የሚያቆምህ የለም

የሆነች ቦታ ላይ እንደአባቱ ልጅ ያልካት አልገባችኝም እና እሲት አብራራት እና እንጨዋወትባት
ያባቱልጅ
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 363
Joined: Tue Oct 31, 2006 6:29 pm

Postby ዋናው » Thu Dec 27, 2012 8:44 pm

ለመላው ዋርካዊያን/ያት እንኳን ለፈርንጆቹ ገና እና አዲስ ዓመት በሠላም አደረሳችሁ?

2013 የሠላምና የፍቅር ይሆንላችሁን ዘንድ ምኞቴ ነው::
ጥበብ ከእኔ የበለጠ ጠንካራ ናት እኔ እንደምፈልገው ሳይሆን እሷ እንደፈለገችው ታደርገኛለች::
ዋናው
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 2806
Joined: Tue Dec 16, 2003 5:29 pm
Location: ሕልም ዓለም

Postby ጌታ » Thu Dec 27, 2012 9:58 pm

ዋንቾ እንኳን አብሮ አደረሰን! እንዲህ የጠፋኸው በላጲስ ነው በሰላም? ኧረ አልፎ አልፎም ቢሆን ተከሰት......
ኢትዮጵያ እጆቿን ወደ እግዚአብሄር ትዘረጋለች!!!
ጌታ
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 3120
Joined: Sun Apr 17, 2005 5:35 pm
Location: ዶሮ ተራ

Postby ዋናው » Thu Dec 27, 2012 10:41 pm

ጌትሽ... ከምር ባለሰማያዊ እና ቀዩ የድሮ ላጲስ ሳይሆን አይቀርም ፈዘዝ ብዬ እንኳን እንዳልታይ የጠፋሁት... እስቲ በ2013 ፈጣሪ ጊዜን አብርክቶ ፊቴን ወደዋርካ ይመልሰኝ ዘንድ ልፀልይ... ዘጠኝ ዓመታት ሙሉ ከደጁ የገለፍጥኩበትን ቤት ጀርባዬን ሰጥቼማ አልቀርም ሚገርምህ ግን እስካሁን ድረስ የብራውዘሮቼ ቱል ባር ላይ መጀመሪያ ያለው ሊንክ የዋርካ ኢንዴክስ ነው:: አዳዲስ ርዕሶችም ሳይ በግርድፉ ሳላነብ ሰንብቼ አላውቅም መቼም የድሮዎች ዋርካዊያን ሰው ትመርጣላችሁ ተብለን ታምተናልና እውነት ለመናገር ያንተን... የፓኑን... የውቅሽን.... የሙዝን... የሪቾን... የጦሜክስን... የደጉን... እና የሌሎችንም አንጋፋ ዋርካዊያን ስም ኢንዴኢክሱ ጥግ ተንጠልጥሎ እያየሁት አልፌ አላውቅም... ግን ያው ሕይወት... ውሎ... ትምሕርት... ሥራ... ሲያራውጠኝ... ሎግኢን ማድረግ እየሰንፍኩኝ ነው....
ለነግሩ ሁሉም'ኮ ነው የጠፋው
ጥበብ ከእኔ የበለጠ ጠንካራ ናት እኔ እንደምፈልገው ሳይሆን እሷ እንደፈለገችው ታደርገኛለች::
ዋናው
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 2806
Joined: Tue Dec 16, 2003 5:29 pm
Location: ሕልም ዓለም

(-:

Postby ደጉ » Thu Dec 27, 2012 11:11 pm

...ሰላም ዋናው ወንድማችን እንዲሁም ሌሎች ጠጪዎች...መልካም የፈርንጆች አዲስ አመት ይሁንላችሁ...እኔ በኑሮ ውድነት ምክንያት ሁለት ገና ሁለት አዲስ አመት ማክበር ስላልቻልኩ አንድ አንድ ብቻ ማክበር ይዣለሁ... :D
...ዋናው ደሮ ትምህርት ያልቅ ነበር ያሁኑ አያልቅም ማለት ነው...? እኔ የአለም ፍጻሜ ሆኖ አቁዋርጣለሁ ብዬ ፈርቼ አልተመዘገብኩም ነበር...;) በቃ አሁን እጅመራለሁ...:)
"STUPID IS AS STUPID DOES " :D
ደጉ
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 4552
Joined: Mon Dec 15, 2003 10:39 am
Location: afghanistan

Postby ፓን ሪዚኮ » Thu Jan 10, 2013 11:01 pm

ሰላም ጎበዝ...የገና ጠላ እንዳለቀ አውቃለሁ...ቅራሪ ብጤ ካላቹሁ ....በጥንቱ የዋርካ አምላክ ወዲህ በሉ!!!
ፓኑ አባ ፈርዳ
Imageኢትዮጲያ ትቅደም
ፓን ሪዚኮ
አለቃ
አለቃ
 
Posts: 2044
Joined: Tue Aug 03, 2004 3:35 am
Location: ጎሃ ጽዮን

Postby ዋናው » Fri Aug 23, 2013 1:11 am

እና ዋርካ ውስጥ አስር ዓመት ሞላን ማለት ነው... ጊዜ ግን እንዴት ቀልቃላ ነው አሁን እስቲ ምን አስሮጠው ... ሊደፋ...?

ሠላም ብያለሁ ለሁሉም ዋርካ ሎግ ኢን ማድረግ በስንት ጊዜ እሺ ብላኝ የብርቅ ሁሉ ነው ምፅፈው ይሄን ግሮሰሪ ለውቃውና ለ አባፈረዳ በአደራ እንዲያስተዳድሩ ብሰጣቸው ውቃው የአብዮት መቀልበሻ ፓኑ ደግሞ የጥቁር ፈረሱ ፋንድያ ማራገፊያ አደረጉት... ምን ላድርግ እሺ ለምስክርነት ሚበቁ ዋርካዊያን ሁሉ ዓለም በቃኝ ብለው ምንኩስናና ምናኔን መርጠው ትዝታቸው ብቻ ቀርቶ የውሃ ሽታ ሆነው ቀርተዋል...

የዛሬ ምንትስ ዓመት ወይም ወራት ነው መሰለኝ አንድ የሆነ ቤት ገብቼ ስለ ድሮ ቀደምት ዋርካዊያን እያነሳው በቁጭት ሳወራ አንዱ በንዴት አቦ ሼባዎች እየመጣችሁ ዋርካ ድሮ ቀረ ምናምን እያላችሁ አትነጅሱን ዋርካ ዛሬም አለች ይሄው እኛም እየኖርንባት ነው ብሎ ብሶቱን ፃፈ...

ድብልቅ ያለው ዕውነት ማለት ይሄ ነው ከምር... ሁሉም በዘመኑ ያሻዉን እያደረገ ይኖራል በዘመን ግስጋሴ ንፅፅርን እያመጡ የኖሩበትን ዘመን አውድሶ የቆሙበት መውቀሱ ቂልነት ነው ... ሁሌም 'ማምነው አንድ ነገር አለ ትላንትና ደብዛዛ ነው ነገም ጭላምጭል ነው ዛሬ ግን ስላለንበት ደማቅ ነው::

አሁን 'ስቲ የኔ ባዶ ቤት ገብቶ እንደዚህ ባቻ ማውራት ምን ይሉታል...?

እኔ 'ምለው ግን (ያ ልጅ እንዳይሰማኝ) ... የድሮ ዋርካዊያን አላችሁ...?ጥበብ ከእኔ የበለጠ ጠንካራ ናት እኔ እንደምፈልገው ሳይሆን እሷ እንደፈለገችው ታደርገኛለች::
ዋናው
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 2806
Joined: Tue Dec 16, 2003 5:29 pm
Location: ሕልም ዓለም

Postby ሾተል » Fri Aug 23, 2013 7:15 am

ሰላም ጤና ይስጥልን ወንድማችን ዋናው ::ምን ሆኖ ጠፋ በሰላም ይሆን ብለን ስናስብ ሰንብተን ስናበቃ መኖርህን ከላይ በከተብከው ጽሁፍ ስላረጋገጥክልን በጣሙን ደስ ብሎናል ::

እርግጠኛ ነን ህይወት ባንተ በኩል እንደ አይስክሬምና ቆንጆ ቺክ ከንፈር ጥፍጥ እንዳለልህና መቼም ዘንድሮ ውጥር ያለየቺክ ጡት ባይኖር (እረ አለ....የልጅ ነገር ሆኖ አንዴ በራሷ ጊዜ ሲቆላት አምብዬ እያለች የምትመጣው ወይም ሲመጣባት ደግሞ እያግደረደረች በዚህም በዚያም ብዬ በእትት የማመጣት ከምተኛቸው ያንዷ ጡት እንደ ክሩዝ ሚሳዬል የተወጠረ አይደለም እንዴ?የበላበትን ወጪት ሰባሪ ይሏል እኛን ነው::) እንደ ሰገሌ ጊዜ ቺካኔዎች ጡት አመልማሎ መስሎ እንደሚጎመጥና ሚጎረስ ትርንጎ መሳይ ጡት እምር እንዳለልህ ተስፋ በማድረግ አሁንም እየጻፍክና የምትደነቅበትን ስእል እየሳልክ እንደሆነ ተስፋ በማድረግ ሲሆን የምትወዳቸውን ነገሮች መቼም ከመተግበር እንደማትተው በእርግጠኝነት በክብርነታችን ሆነን ባንተ በመተማመን ነው ::

እኛም በጣሞን ደህና ነን .....አሁንም እንሰዳደባለን ::ስድብ ጨምረናል ::ወደ ገሀዱ አለም ስንመጣ ደግሞ አሁንም እየዞርን ከሴቶች ጋር ወጥረን እንተኛለን ::ጅንጀናም ጨምረናል ::ለዛውም በስታይል ነው ::ፍቅር መስራቱንማ ባይነገር ይሻላል ::የፕሮፊ ሰርተፊኬት የሚሰጠን ጠፋ እንጂ ምናለ በብድ ዶክተሬት ዲግሪ የሚመርቀን ቢኖርና ያቺን ዲግሪ የሆነች ቤት ተከራይተን ባማረ ፍሬም ግርግዳ ላይ ለጥፈን የልብዳችሁ ቢዝነስ ከፍተን ቢሆን ኖሮ ምናለበት ነበር ?ሰው ለሰው ሁሉ ዲግሪ ያድላል ለእኛ ግን የኮሚኒቲ ኮሌጅ የብድ ዲግሪ እንኩዋን የሚሰጠን ይጥፋ ?

ወንድማችን ዋኖስንስ አልፎ አልፎ አየዋለሁ :: ወንድማችን የሚሚ ባል ግን የት ጠፋ ?

ኖ ማተር ዋት በት አይ ሚስ ኤንድ ሎቭ ያ ጋይስ ::

ከፍቅርና ታላቅ አክብሮት ጋር ::

ፊርማ የተከተለው ::


ሾተል ነን .............የጠፋን ሰው ሰላም ሆኖ ሲያገኙት እንዴት ደስ ይላል ?ደስ ብሎናልና ደስ ይበላችሁ ::
እሰይ ተመስጌን አምላኬ ለካስ በክብርነቴ እራሴን ሆኜ እኔነቴን ፈልጌ አግኝቼዋለሁ !?
ሾተል
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 9658
Joined: Thu Jan 13, 2005 9:42 pm
Location: Vienna-Austria

Re: ባልቻና መዶሻው ግሮሠር=> ተጠፋፋን

Postby ዉቃው » Thu Apr 05, 2018 3:12 am

ቀላል ተጠፋፋን ! ቂቂቂቂቂ
በአጭር የተቀጨው ረጅሙ ጉዟችን !!!!
ዉቃው
ውሃ አጠጪ
ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1038
Joined: Sun Jan 07, 2007 2:48 am

Re: ባልቻና መዶሻው ግሮሠር=> ተጠፋፋን

Postby ጦምኔው » Thu May 03, 2018 11:04 pm

ሪፖርቲንግ ፍሮም ዲሲ...... ባለግሮሰሪው የት ጠፉ? ውቅሽ ሰላምከ እባ

ሾተል ጉልበት ስመናል
ጦምኔው
ዋና ውሃ አጠጪ
ዋና ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1529
Joined: Sun Jan 14, 2007 10:40 pm
Location: Right here

Re: ባልቻና መዶሻው ግሮሠር=> ተጠፋፋን

Postby ዋናው » Wed Jun 13, 2018 10:27 pm

ሰላም ጦምናችን
ይህንን ድረ፡ገጽኮ የድሮ ወዳጆች በስህተት'ንኳን ሚደነቁሉት ስለማይመስለኝ ነው.... ውቅሽ ስላየሁ ደስ ብሎኛል ሁለታችንም ወጣት ሆነን የተለያየን ነው አይደል...

የዛሬን ኣያርገውና የዚህ ግሮሰሪ ጫጫታ'ኮ
ጥበብ ከእኔ የበለጠ ጠንካራ ናት እኔ እንደምፈልገው ሳይሆን እሷ እንደፈለገችው ታደርገኛለች::
ዋናው
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 2806
Joined: Tue Dec 16, 2003 5:29 pm
Location: ሕልም ዓለም

Re: ባልቻና መዶሻው ግሮሠር=> ተጠፋፋን

Postby ሩኒ » Wed Jul 11, 2018 9:33 am

ቀላል ተጠፋፋን እንዴ?
ግሮሰሪዋ ግን ተደመረች? ቫት ምናምን ማለቴ ነው፡፡
ዋናው እንዴት ነህ?
ሩኒ
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 108
Joined: Sat Oct 22, 2005 1:56 pm
Location: Wales

Re: ባልቻና መዶሻው ግሮሠር=> ተጠፋፋን

Postby ዉቃው » Sun Jul 15, 2018 2:52 pm

ጦምን ና ዋንች

አለን በዚያው በድሮ አዲዳስና ራንግለር ጂንስ !
ዋንች እርሱ ታለው አርጅተንም ቢሆን እንገናኛለን ...የዋርከኞች ጠበል ጠዲቅ አበጅተን ፣ የተጣላ እናስታርቃለን ፤ የታመመን እንጠይቃለን ፤ ምን ቅጡ
ምን ይሳነዋል ...ለአንድዬ !
በአጭር የተቀጨው ረጅሙ ጉዟችን !!!!
ዉቃው
ውሃ አጠጪ
ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1038
Joined: Sun Jan 07, 2007 2:48 am

Re: ባልቻና መዶሻው ግሮሠር=> ተጠፋፋን

Postby ጦምኔው » Wed Aug 01, 2018 11:19 pm

ተደምረን ከች ብለናል፡፡ ባልታ እስኪ ሁለት ቁንዱፍቱ ወዲህ ል ወዳጄን ውቅሽን ልደምረው፡፡
ዋርክዬን ሸገር ላይ ተበረገደችህ ተባለ......ተባለ እንዴ.....
ሪቾን ይዞ ለመጣ እንድ ጠርሙስ መንገደኛው ዮሃንስ በኔ......
ጦምኔው
ዋና ውሃ አጠጪ
ዋና ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1529
Joined: Sun Jan 14, 2007 10:40 pm
Location: Right here

Re: ባልቻና መዶሻው ግሮሠር=> ተጠፋፋን

Postby ሪች » Wed Aug 08, 2018 11:44 pm

ጦምኔው wrote:ሪቾን ይዞ ለመጣ እንድ ጠርሙስ መንገደኛው ዮሃንስ በኔ......

ስቅ አለኝ ማን አነሳኝ ደግሞ ዲን ዲሪን ዲሪን ቅቅቅ እንግዲህ በንግሊዝ አፍ የነበረው ስሜ ቢጠፋም ለክፋቀን ብዬ ባስቀመጥኩት ባማርኛው ተደምሬ( ተደምሬ ሳይሉ ማውራት ዘንድሮ የድሮ ስርአት ናፋቂ ስለሚያስብል እንደምንም ተቸግሬ በጨዋታ መሀል ማስገባቴ አይዘንጋ) መጥቻለሁ.... ጣምናኔው አረቄዋን ወዲህ በል
ሪች
መንገደኛ
መንገደኛ
 
Posts: 5
Joined: Wed Nov 02, 2005 7:12 am
Location: ethiopia

PreviousNext

Return to Warka Intimate - ዋርካ ፍቅር

Who is online

Users browsing this forum: No registered users and 4 guests