ባልቻና መዶሻው ግሮሠር=> ተጠፋፋን

The Love Forum (love, relationship) (የኔ ቆንጆ እንተዋወቅ :-)

Postby ፓን ሪዚኮ » Sun Jun 12, 2011 2:56 am

ሰናይት25 wrote:
ፓን ሪዚኮ wrote:http://www.mereb.com.et/?mpid=5339593819

ጓዶች እስቲ በዚች ተዝናኑ

ፓኑ አባ ፈርዳ
የሀበሻ ጀምብዱ የሚባለውን መፅሀፍ ካነበብኩት 3 ሳምንታት አለፉ:: ተርጉዋሚው "ድርሳነ ሰላሌ" ቢለው ይቀላል :lol: ይሄንን መፅሀፍ ለማመን በጣም ይከብደኛል:: የመፅሀፉ አላማ የሰላሌ ሰዎች ብቻቸውን :lol: ጣሊያንን አርበደበዱ የሚል ነው:: ተርጉዋሚው የሰላሌ ሰው መሆኑን ስረዳም ግምቴ ግምት ብቻ ሳይሆን 100% ትክክል መሆኑን ተረዳሁ:: ሰላሌን የሚያውቅ ያውቀዋል :lol: ደም በዞረበት የማይዞረው ሰላሌ ጣሊያንን አርበደበደው :lol: :lol: ይለናል የሀበሻ ጀምዱ የሚባለው የትርጉም ስራ:: የሚገርመው ደሞ በዚያን ግዜ የሰላሌ ህዝብ ብዛት ራሱ በመፅሀፉ ላይ ከተጠቀሰው ቁጥር ለማነሱ ምንም ጥርጥር የለውም:: ለማንኛውም ያላነበባችሁት አንብቡትና ያልኩትን ለማየት ያብቃችሁ:: ጎንደር: ጎጃም: ወሎ: ሸዋ: አሩሲ: ወለጋ: ጉራጌ: ጋምቤላ: ሌላውም ሌላውም በኢትዩ-ኢጣሊያ ጦርነት ግዜ እቤቱ ቁጭ ብሎ ፀሎት እያረገ ነበር :lol: :lol: ጥሩ የተረት መፅሀፍ ናት ወድጃታለሁ :roll:
እናመሰግናለን ...እስቲ በቅጡ እንደገና ያንብቡት ....የዚህ መጽሀፍ ተርጓሚ ...ያቀረበው በተንቤን የራስ ካሳን የጦርሜዳ ውሎና ፍጻሜውን ነው ...ጥሩ አንባቢና ጠባብ ባይሆኑ ኖሮ ይህን ለማለት ባልበቁ ነበር

ለመንኛውም ስለ አስተያየቶ ሳላመሰግን አላልፍ
ጳኑ አባ ፈርዳ
ተርጓሚው
Imageኢትዮጲያ ትቅደም
ፓን ሪዚኮ
አለቃ
አለቃ
 
Posts: 2044
Joined: Tue Aug 03, 2004 3:35 am
Location: ጎሃ ጽዮን

Postby ዉቃው » Sun Jun 26, 2011 4:42 am

ዛሬ በጣም ደስ የሚል ቀነ ነበር ያሳለፍኩት :: የቀምቃሚዎችም ቀን እንዲሁ ቢሆን ደስ እሰኛለሁ :: ከእሙሙ ባለሀብቴ ጋር አላስፈላጊ ሰነዶችን ስናስወግድ በ18/3/89 አዲስ አበባ Sinarline Notebooኬ ላይ የጻፍኩትን አገኘሁና እየሳቅኩ ላካፍላችሁ ወደድኩ :: :lol: :lol: እንደወረደ እንዲህ ይነበባል ::

18/3/89
- የሚገርም ጥቅስ " እስክትደርስ ሚስትህ አዝግም በገረድህ
-ዛሬ በቃ በገንዘብ ችግር ስሰቃይ ዋልኩኝ :: ሳምንት እህቴ መቶ ብር ስጠችኝ እሷም አለቀች :: ዛሬ ግን ሙሉ ቀን ቤቴ ዋልኩኝ ..ቤት ውስጥ ..9 ዓመት የኖርኩበት...እስኪ ይታሰብ :: ማታ ለማመሻሸት ወጣ አልኩ :: ወደ 8 ድራፍት ጠጥቼ 9ኛውን ልድገም/ አልድገም እያልኩ በመጠራጠር ላይ ሆኜ ሂሳብ ጠየኩት :: ያለኝ ልጁ 14 ብር ነበር :: ኪሴ ውስጥ የነበረው ባጠቃላይ 14.35 ነበረ ..ከፍዬ ወጣሁ " ድንቅ ቀን" :: ድህነት ይሄ ነው :: በእውነት ::

ይላል :: በጣም ሞቅ ብሎኝ እንድጻፍኩት የእጅ ጽሁፌ ያሳብቃል :: እዚህ በጣም ሳቅንበት :: ያኔ በጠጠሁበት ቤት ድራፍት 1ብር ታምሳ እንድነበረ ትዝ ይለኛል :: አራዳው አስተናጋጅ ሁለት ብር እንደበላኝ አሁን ከ14 ዓመታት በኋላ ድረስኩበት :: እናቱንና ::

ያኔ ስክሬ የማስበበት አንጎል ....አሁን በጤና ሳልስከር ክማስበበት አንጎል ሲነጻጸር እንዴት ድንቅ ነበር !

ኖት ቡኩ ላይ ከጻፍኳቸው አንዳዶቹ ነገሮች ..በጣም ጨቅላ እና እንጭጭ ነገሮች ነበሩ :: ሲበዛ ያሳፍራሉ :: አንዱን ግን በሞቅታ አውትላየኑን ጽፌው ነበርና እና አሁን አስፋፍቼ ቀደዋለሁ ::

መልካም የስካር እና የተቀደሰ አባቡና እሙሙ የሚዋሀዱበት ምሽት ይሁንላችሁ ::


የዓባይነሽን ድንግል መለስነሽ ትውሰደው !
ዓባይን በጭልፋ ይቅር ..ዓባይን በቦንድ ይጀመር !
እናሸንፋለን!
አንጠራጠርም !
ጉዟችን ረጅም : ግባችንም ሩቅ ነው !!!!
ዉቃው
ውሃ አጠጪ
ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1032
Joined: Sun Jan 07, 2007 2:48 am

Postby ደጉ » Sun Jun 26, 2011 8:22 am

ዉቃው wrote:... " እስክትደርስ ሚስትህ አዝግም በገረድህ !

...ሰላም ውቃው ወንድማችን .....በጣም አሪፍ ጥቅስ..ከአሪፍ ማስታወሻ ጋር ... :D
"STUPID IS AS STUPID DOES " :D
ደጉ
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 4412
Joined: Mon Dec 15, 2003 10:39 am
Location: afghanistan

Postby ዉቃው » Sat Jul 02, 2011 2:29 am

ጓድ ሊቀመንበር መንግስቱ ኃ/ማርያም
የአብዮታዊ ጦር ኃይሎች ዋና አዛዥ
የኢሠፓ ማዕከላዊ ኮሚቴ ዋና ጸሃፊ
እና የኢሕድሪ ፕሬዚድንት ...በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ ንግግር አርገዋል ::

http://www.ethiotube.net/video/14618/Me ... Days--1991
ጉዟችን ረጅም : ግባችንም ሩቅ ነው !!!!
ዉቃው
ውሃ አጠጪ
ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1032
Joined: Sun Jan 07, 2007 2:48 am

Postby ዉቃው » Sun Jan 01, 2012 7:33 pm

ሰላም ጓዶችና ጓዲት

ስማችሁን ብዝረዝረው........አያልቅም :: ግን ባጭሩ እንኳን አደረሳችሁ :: እኔ ደርሻለሁ .....እስኪ ብቅ ብቅ በሉና ጠጡልኝ ::
ጉዟችን ረጅም : ግባችንም ሩቅ ነው !!!!
ዉቃው
ውሃ አጠጪ
ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1032
Joined: Sun Jan 07, 2007 2:48 am

Postby ዋናው » Tue Jan 03, 2012 1:10 pm

እንኳን አብሮ አደረሠን ጓድ ውቃው
እነሆ በዋርካ ውስጥ አብዮታዊ ትግላችንን ስናፋፍም እኔና ጓድ ደጉ ባሳለፍነው ዲሴምበር ወር 8 ዓመታት አስቆጠርን አሁንም ትግላችንን ወደፊት እንቀጥላለን ጥቂት የቦርዱ አባላት የውስጥ ለውስጥ ግንኙነታቸዉን ቢቀጥሉም ከሰፊው ጭቁን ሕዝብ ጋር 'ምናደርገው ወዳጅነት ይቀጥል ዘንድ የርስዎ ዓይነት ቆራጥ የዋርካ ተሳታፊ ከዚህ አለመራቅ ትልቅ ሚና እንደሚጫወት አይካድም::

በዚህ አጋጣሚ ለመላው ዋርካዊያን/ያት እንኳን ለብረሐነ-ልደቱ በሠላም አደሳችሁ ብያለው::
ጥበብ ከእኔ የበለጠ ጠንካራ ናት እኔ እንደምፈልገው ሳይሆን እሷ እንደፈለገችው ታደርገኛለች::
ዋናው
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 2799
Joined: Tue Dec 16, 2003 5:29 pm
Location: ሕልም ዓለም

Postby ዉቃው » Sun Jan 08, 2012 3:51 pm

እንኳን ደረስን ..ጓድ ዋናው !

አብዮታዊ ማበራታቻህን ተቀብለናል :: በነገራችን ላይ ..በተደጋጋሚ ትግላችን ...ትግላችን ስትል ...ምናልባች ይህ ሰው ጓድ ሊቀመንበር ነው እንዴ ?....አስብሎኛል :: ቅጽ አንድ "ትግላችን" መጽሀፉ .... እኔ እንደጠበኩት አላገኘሁትም :: ምን ጠብቀህ ነበር ለሚለው የጓድ ሊቀመንበር ጥያቄ በሌላ አርዕስት ብመለስስ ::

እስከዛ አነ "በቀለ ገላግሌ " (አረቄ ) ወዲህ በል !

----------------------------------------------

በቀለ ገላግሌ የኢትዮጵያ ሰራዊት ከሶማሊያ ጋር ባደረገው ጦርነት ለ ቢ ኤም 23 ያወጣው ሰም እንደነበር ሊቀመንበሩ ገልጸዋል ::
ጉዟችን ረጅም : ግባችንም ሩቅ ነው !!!!
ዉቃው
ውሃ አጠጪ
ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1032
Joined: Sun Jan 07, 2007 2:48 am

Postby ዋናው » Tue Jan 10, 2012 3:12 pm

ሠላም ጓድ ውቃው
እስቲ ባክህ እመለሳለው ባልከው ቃልህ ተመለስና ስለጓድ ሊ/መንበሩ ጥያቄና መልስ አጫውተን ትግል ትግል ትላለህ ላልከው አዎ ኑሮ ራሷ ትግል አይደለችን'ዴ... በማንኛዉም ርዕዮተዓለም ውስጥ ምንኖር የየራሳችን ትግል ይኖረናል እኛም እዚችሁ ተዋውቀን የትግል ጉዙዋችንን እንደያዝን አንድ ቁና ዘመን ወይም አድአሪያህን እንደሚሉት decade ሊሞላን ምን ቀረን...
ለማንኛዉም በቀለ ገላግሌህን እየተጎነጨህ እቺን ዜማ ለትዝታ ልጋብዝህ
እዚችጋ ጠቅ <=
ጥበብ ከእኔ የበለጠ ጠንካራ ናት እኔ እንደምፈልገው ሳይሆን እሷ እንደፈለገችው ታደርገኛለች::
ዋናው
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 2799
Joined: Tue Dec 16, 2003 5:29 pm
Location: ሕልም ዓለም

Postby ጌታ » Tue Jan 10, 2012 3:14 pm

ዋንቾ እንኳን አደረሰህ!!! ተነሳ ተራመድን እየኮመኮምኩ ነው::
ኢትዮጵያ እጆቿን ወደ እግዚአብሄር ትዘረጋለች!!!
ጌታ
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 3029
Joined: Sun Apr 17, 2005 5:35 pm
Location: ዶሮ ተራ

Postby ፓን ሪዚኮ » Wed Jan 11, 2012 8:56 am

ጌታ wrote:ዋንቾ እንኳን አደረሰህ!!! ተነሳ ተራመድን እየኮመኮምኩ ነው::
መምሬ ....ተነሳ ተንፏቀቅ አይሻልህም???
ለማንኛውም መልካም ገና
ፓን
Imageኢትዮጲያ ትቅደም
ፓን ሪዚኮ
አለቃ
አለቃ
 
Posts: 2044
Joined: Tue Aug 03, 2004 3:35 am
Location: ጎሃ ጽዮን

Postby ጌታ » Wed Jan 11, 2012 2:51 pm

ፓን ሪዚኮ wrote:
ሰናይት25 wrote:
ፓን ሪዚኮ wrote:http://www.mereb.com.et/?mpid=5339593819

ጓዶች እስቲ በዚች ተዝናኑ

ፓኑ አባ ፈርዳ
የሀበሻ ጀምብዱ የሚባለውን መፅሀፍ ካነበብኩት 3 ሳምንታት አለፉ:: ተርጉዋሚው "ድርሳነ ሰላሌ" ቢለው ይቀላል :lol: ይሄንን መፅሀፍ ለማመን በጣም ይከብደኛል:: የመፅሀፉ አላማ የሰላሌ ሰዎች ብቻቸውን :lol: ጣሊያንን አርበደበዱ የሚል ነው:: ተርጉዋሚው የሰላሌ ሰው መሆኑን ስረዳም ግምቴ ግምት ብቻ ሳይሆን 100% ትክክል መሆኑን ተረዳሁ:: ሰላሌን የሚያውቅ ያውቀዋል :lol: ደም በዞረበት የማይዞረው ሰላሌ ጣሊያንን አርበደበደው :lol: :lol: ይለናል የሀበሻ ጀምዱ የሚባለው የትርጉም ስራ:: የሚገርመው ደሞ በዚያን ግዜ የሰላሌ ህዝብ ብዛት ራሱ በመፅሀፉ ላይ ከተጠቀሰው ቁጥር ለማነሱ ምንም ጥርጥር የለውም:: ለማንኛውም ያላነበባችሁት አንብቡትና ያልኩትን ለማየት ያብቃችሁ:: ጎንደር: ጎጃም: ወሎ: ሸዋ: አሩሲ: ወለጋ: ጉራጌ: ጋምቤላ: ሌላውም ሌላውም በኢትዩ-ኢጣሊያ ጦርነት ግዜ እቤቱ ቁጭ ብሎ ፀሎት እያረገ ነበር :lol: :lol: ጥሩ የተረት መፅሀፍ ናት ወድጃታለሁ :roll:
እናመሰግናለን ...እስቲ በቅጡ እንደገና ያንብቡት ....የዚህ መጽሀፍ ተርጓሚ ...ያቀረበው በተንቤን የራስ ካሳን የጦርሜዳ ውሎና ፍጻሜውን ነው ...ጥሩ አንባቢና ጠባብ ባይሆኑ ኖሮ ይህን ለማለት ባልበቁ ነበር

ለመንኛውም ስለ አስተያየቶ ሳላመሰግን አላልፍ
ጳኑ አባ ፈርዳ
ተርጓሚው


ይቺን አስተያየት እስከዛሬ አላየኋትም ነበር:: ሰናይት25 መጽሐፉን አላነበቡትም; ካነበቡት ደግሞ ኢትዮጵያዊ አይደሉም:: ሲጠቡ ሲጠቡ ዘርን ክፍለሐገርን ትትው በከተማ ይከፋፍሉን ገቡ:: አዶልፍ ፓርልሳክም የኢትዮጵያና የኢትዮጵያውያን ፍቅር ስላሰከረው ሰላሌያዊ ነው:: ሁላችንም ኢትዮጵያውያን ሰላሌዎች - ሲዳማዎች - ወለጋዎች - አድዋዎች ነን!!!
ኢትዮጵያ እጆቿን ወደ እግዚአብሄር ትዘረጋለች!!!
ጌታ
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 3029
Joined: Sun Apr 17, 2005 5:35 pm
Location: ዶሮ ተራ

Postby recho » Wed Jan 11, 2012 6:06 pm

ጌታ wrote: ሁላችንም ኢትዮጵያውያን ሰላሌዎች - ሲዳማዎች - ወለጋዎች

ሜይ ቢ ...
አድዋዎች ነን!!!
እ? እ? እ ??? ኖት ሚ !!! ሳቂቼ ሳቂቼ ጥርሴን አመመው አለ አማርኛ ለማጁ ... ራስህን ቻል ጌት ቅቅቅ

ሰላም
"ሰነፍ በልቡ። አምላክ የለም ይላል በሥራቸው ረከሱ ጐስቈሉ በጎ ነገርን የሚሠራ የለም " መዝሙረ ዳዊት ምእራፍ 14:1
recho
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 3171
Joined: Mon Sep 20, 2004 12:28 pm
Location: Earth

Postby ጌታ » Wed Jan 11, 2012 6:14 pm

recho wrote:
ጌታ wrote:
ሁላችንም ኢትዮጵያውያን ሰላሌዎች - ሲዳማዎች - ወለጋዎች

ሜይ ቢ ...
አድዋዎች ነን!!!
እ? እ? እ ??? ኖት ሚ !!! ሳቂቼ ሳቂቼ ጥርሴን አመመው አለ አማርኛ ለማጁ ... ራስህን ቻል ጌት ቅቅቅ

ሰላም


ሪቾ የጠፋሽ ልጅ ደህና ነሽ? ኑሮና ብልሃቱ እንዴት ይዞሻል? እኔ እንኳን ከመጽሐፉ ዓላማ ውጪ የሆነች ጠባብ አስተያየት ስላየው ነዶኝ እንጂ ሌላ የቦለቲካ ውይይት ልከፍት አላሰብኩም ነበር:: ለማንቻውም ፓስወርድሽን ሰው እንዳልሰረቀሽ ተሥፋዬ ነው :lol: :lol: :lol:
ኢትዮጵያ እጆቿን ወደ እግዚአብሄር ትዘረጋለች!!!
ጌታ
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 3029
Joined: Sun Apr 17, 2005 5:35 pm
Location: ዶሮ ተራ

Postby recho » Wed Jan 11, 2012 6:22 pm

ጌታ wrote:
ሪቾ የጠፋሽ ልጅ ደህና ነሽ? ኑሮና ብልሃቱ እንዴት ይዞሻል? እኔ እንኳን ከመጽሐፉ ዓላማ ውጪ የሆነች ጠባብ አስተያየት ስላየው ነዶኝ እንጂ ሌላ የቦለቲካ ውይይት ልከፍት አላሰብኩም ነበር:: ለማንቻውም ፓስወርድሽን ሰው እንዳልሰረቀሽ ተሥፋዬ ነው :lol: :lol: :lol:
ጌቾ ዚ ግሬት አለሁልህ... ቦተሊካው ይቅር ልክነው .. ደግሞ ያቀምሱኝና ተደባደብልኝ ብየ እንዳላስቸግርህ ቅቅቅ ማናባቱ ...ይሰርቀኛል ብለህ ነው ፓስዎርዴን ... እኔው የዋርካ ነገር ብቅት ብሎኝ ..ጠፋሁ እንጂ .. እየመጣሁ ማንበቤ አልቀረም ለነገሩ .. ዞሮ ዞሮ ከዋርካ አይጠፋ መቼም ... አንተሳ እንዴትነው ? አዲሱ አመት እንዴት ይዞሀል .. እኔጋር ቸበር ቻቻ ነው .. እንደጅምሩ ከሆነ በውነቱ አለም ዘጠኝ መሆኑ ቀርቶ አስር መሆኑን አስመስክሬ ነው የምጨርሰው :lol:
"ሰነፍ በልቡ። አምላክ የለም ይላል በሥራቸው ረከሱ ጐስቈሉ በጎ ነገርን የሚሠራ የለም " መዝሙረ ዳዊት ምእራፍ 14:1
recho
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 3171
Joined: Mon Sep 20, 2004 12:28 pm
Location: Earth

Postby ጌታ » Wed Jan 11, 2012 7:16 pm

recho wrote: ጌቾ ዚ ግሬት አለሁልህ... ቦተሊካው ይቅር ልክነው .. ደግሞ ያቀምሱኝና ተደባደብልኝ ብየ እንዳላስቸግርህ ቅቅቅ ማናባቱ ...ይሰርቀኛል ብለህ ነው ፓስዎርዴን ... እኔው የዋርካ ነገር ብቅት ብሎኝ ..ጠፋሁ እንጂ .. እየመጣሁ ማንበቤ አልቀረም ለነገሩ .. ዞሮ ዞሮ ከዋርካ አይጠፋ መቼም ... አንተሳ እንዴትነው ? አዲሱ አመት እንዴት ይዞሀል .. እኔጋር ቸበር ቻቻ ነው .. እንደጅምሩ ከሆነ በውነቱ አለም ዘጠኝ መሆኑ ቀርቶ አስር መሆኑን አስመስክሬ ነው የምጨርሰው :lol:


ድብድብ እንኳን ዋርካ ላይ የምችላቸው ሙዝና ጉዱ ካሳን ብቻ ነው :lol: :lol: :lol: ምናልባት ፓኑ ጨብ ያለ ቀን ባገኘው እዘርረው ይሆናል:: ከኔ ይልቅ የድሮ ጓደኛሽን አክየን ብትተማመኚ ያዋጣሻል :lol: :lol: ግን እውነት አክየ አልናፈቀሽም?? ከምር ጊዜ ሲያልፍ የተቧቀስሽውን ጓደኛ ሁሉ እኮ ሚስ ታደርጊያለሽ:: አሁን አኩሻን አግኝቼ የበደልኩትን ሁሉ ይቅርታ ጠይቄ እንደድሯችን ብናወጋ ደስ ይለኝ ነበር:: ሌላ ሚስ የማደርገው ወዳጄ ሽማግሌው ነው:: ኧረ እናንተዬ ሰው ከዋርካ ሲሰናበት ሄጃለሁም አይል??? ሀሪከንማ ከዛሬ ነገ በስልክ እናወራለን እንደተባባልን የውሃ ሽታ ሆነ:: ኧረ ስንቱን ላስታውስ?! ቢከፋም ቢለማም ቤተሰብ ነንና ባመት አንዴም ብቅ ብለን በሕይወት መኖራችንን ብናሳውቅ መልካም ነው::

አዲሱ ዓመት ብዙም ለውጥ ባላይበትም እስካሁም መልካም ነው:: ዊንተሩ ሞቅ ማለቱ አዝመራው ላይ ያለውን ተፅዕኖ ባላውቅም እኔ በረዶ መዛቁ ቀርቶልኝ በቲሸርት መሄዱ ተስማምቶኛል:: አንቺ ጋር ያለውን ቸበርቻቻ ያዝልቅልሽ!! አንቺን ደስስስ ሲልሽ እኔም ደስ ይለኛል:: የሽማግሌ ነገር አንድምጠይቅሽ ጥያቄ አለና እስቲ የግል ሳጥንሽን ተመልከቻት::

ውቃው የሚወቃ ይውቃህና ጥያቄ ስል ጆሮህ ቆመ አይደል?? ሜሴጁ ላይ ኮፒ አደርግሀለሁ :lol: :lol: :lol:
ኢትዮጵያ እጆቿን ወደ እግዚአብሄር ትዘረጋለች!!!
ጌታ
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 3029
Joined: Sun Apr 17, 2005 5:35 pm
Location: ዶሮ ተራ

PreviousNext

Return to Warka Intimate - ዋርካ ፍቅር

Who is online

Users browsing this forum: No registered users and 6 guests