ባልቻና መዶሻው ግሮሠር=> ተጠፋፋን

The Love Forum (love, relationship) (የኔ ቆንጆ እንተዋወቅ :-)

Postby recho » Wed Jan 11, 2012 8:19 pm

ቅቅቅ አክዬ ... አክዬ ጋር እኮ ሰላም ካወረድን ቆየን በሰፈራችን ሲያልፍ የቆርቆሮ አጥራችንን በድንጋይ ላይመታ ወይንም ሪቾቾቾ እያለ ላይጮህ ቃል አስገብቼው እኔም ደግሞ መንገድ ላይ ሳገኘው አንበርክኬ በኩርኩም ላልለው ( አልደርስበትማ ቁመትና ንፍጥ ልጅል ነው ሲባል አልሰማህም ? ቀውላላ ነው ተብሎ ይገመታል :lol: ) ቃል ገብቼለት እርቅ ሰላም አውርደን የጠላታችንን አይን ደም አስመሰለነዋል ቅቅቅ ግን ከምር ግን ለምን ይንበረከካል መጀመሪያ ጅል ካልሆነ :lol: እሱማ በዋርካ ድብድብ እንደዛ ደም በደም ሲሆን እኮ አረጋግጦልኛል ... አክክይይይይዬ አይዞህ በቃ ሁለተኛ ስምህን ላላነሳ ምዬልህ ነበር ለካ .. ጠላትህ በክፉ ይነሳና ...

የዌዘር ነገር ተወው ወዳጄ... ብራውን ክሪስመስ እያሉ ሲላቀሱብን ከረሙ .. ከምር ግን ሚስ አርጌዋለሁ .. ዛሬ ትንሽ ፍለሪ ነገር ባይ እኔዋ ደስ ደስ ሲለኝ እኮ እረ ይሄ ነገር ይጋባል .. ማለት ዊርድ መሆኑ ማለቴ ነው .. እያለኩ ነበር .. በቲሸርት መሄድ እንኩዋን ይቅርና ትላንትና በሸሚዝ ብቻ ያለ ጃኬት ስለሄድኩ ብርቅ ሆኖብኝ ዋለ .. ዛሬ ደግሞ እንኩዋን ጃኬት ያቺ ሸንተረርማዋን ብርድልስም ባገኝ ባደባባይ ለብሻት ከመሄድ ወደሁዋላ ማለቴን እንጃልኝ .. ይበርዳልልልልልልል !!! ሁህ ሁህ !!


ውቂቾ አለ በሂወት እንዴ? :) አይይ ማን ሪጮ ይበለኝ ቅቅቅ
"ሰነፍ በልቡ። አምላክ የለም ይላል በሥራቸው ረከሱ ጐስቈሉ በጎ ነገርን የሚሠራ የለም " መዝሙረ ዳዊት ምእራፍ 14:1
recho
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 3171
Joined: Mon Sep 20, 2004 12:28 pm
Location: Earth

Postby ጌታ » Wed Jan 11, 2012 9:36 pm

ሪጮ

ወደነአክየ ጉዳይ ልመለስና ሰዎች ዋርካ ላይ እንደዚያ ሲያጫውቱን ከርመው ለምን ድርግም ብለው ይጠፋሉ? አዎ አንዳንዶች አገርቤት ገብተው ምንም ዓይነት አክሰስ ስለሌላቸው ዋርካን ሳይወዱ በግድ የተሰናበቱ አሉ:: ለምሳሌ ቶታአው አንዲሁ ጠፍቶብን ስንጨነቅ ከወራት በፊት ብቅ ብሎ ሰላም ብሎና'ል (ና ትጥበቅ) ቅቅቅ:: አንዳንዶች ደግሞ ስድቡና ትርክምርኪው አንጀታቸውን ቆርጦት እርም ብለው ጠፍተዋል:: እነዚህ ፍቅር የማያውቁ ወረተኞች ይመስሉኛል:: በቃ አንድ ወቅት በእፍ እፍ ፍቅር ዋርካን ጥዋትና ማታ ተጥደውባት እንዳልነበር እስከዘላለሙ መፈጠሯን ረስተዋል:: እነዚህን እኛም አንፈልጋቸውም::

ነፍሳቸውን ይማርና እንደ ጌታባለው ወይም ወርቅሰው1/ልጁነኝ1/ቃኘው ይቺን ዓለም ተሰናብተውም የሄዱ ሌሎች ይኖራሉ ብዬ እገምታለሁ:: ገነትም ውስጥ ዋርካ ብሎክድ ነው ወይም ጸሎቱና መዝሙሩ ፋታ አይሰጥም መሰለኝ ብቅ ብለው አያውቁም::

አይገርምም እኔ አክየና ዲጎኔ እንኳን ዋርካ ላይ ከተወለድን 7 ዓመት ልንደፍን ወራት ቀሩን::
ኢትዮጵያ እጆቿን ወደ እግዚአብሄር ትዘረጋለች!!!
ጌታ
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 3029
Joined: Sun Apr 17, 2005 5:35 pm
Location: ዶሮ ተራ

Postby recho » Wed Jan 11, 2012 9:46 pm

ጌታ wrote:ሪጮ

ወደነአክየ ጉዳይ ልመለስና ሰዎች ዋርካ ላይ እንደዚያ ሲያጫውቱን ከርመው ለምን ድርግም ብለው ይጠፋሉ? አዎ አንዳንዶች አገርቤት ገብተው ምንም ዓይነት አክሰስ ስለሌላቸው ዋርካን ሳይወዱ በግድ የተሰናበቱ አሉ:: ለምሳሌ ቶታአው አንዲሁ ጠፍቶብን ስንጨነቅ ከወራት በፊት ብቅ ብሎ ሰላም ብሎና'ል (ና ትጥበቅ) ቅቅቅ:: አንዳንዶች ደግሞ ስድቡና ትርክምርኪው አንጀታቸውን ቆርጦት እርም ብለው ጠፍተዋል:: እነዚህ ፍቅር የማያውቁ ወረተኞች ይመስሉኛል:: በቃ አንድ ወቅት በእፍ እፍ ፍቅር ዋርካን ጥዋትና ማታ ተጥደውባት እንዳልነበር እስከዘላለሙ መፈጠሯን ረስተዋል:: እነዚህን እኛም አንፈልጋቸውም::
ወረት ነው ብለህ ነው ? እስቲ ዋርካን ተመልታት .. ድሮ ጥሩ ጊዜ ማሳለፊያ ..መረጃ መለዋወጫ .. መዝናኛ ነበር .. አሁን በተወሰኑ የፖለቲካና እምነት አራማጆች በቁጥጥር ስር የዋለ ሳይበሩ አፍጋኒስታን ከሆነ ቆየ እኮ... አክራሪነት በጣም በዝቶ ... ፍቅርና መተሳሰብ ጠፍቶ ዝምብሎ ስለ ትርኪምርኪ ፖለቲካ ወይንም አጸያፊ የሀይማኖት ስድድብ ሆነ ወሬው .. ከበዛም ወይምን ከተሻሻለ እንትንዋ በዚህ ያዝ በዛ ጥመድ አይነት የቁጭራ ሰፈር ጨዋታ :lol: ወይ እንደበፊቱ አንደር ኤጅ አትግቡ ብለው ማስታወቂያ ቢቴ በራቸው ላይ ሸብ ቢያደርጉ አሪፍ ነበር ..


ነፍሳቸውን ይማርና እንደ ጌታባለው ወይም ወርቅሰው1/ልጁነኝ1/ቃኘው ይቺን ዓለም ተሰናብተውም የሄዱ ሌሎች ይኖራሉ ብዬ እገምታለሁ:: ገነትም ውስጥ ዋርካ ብሎክድ ነው ወይም ጸሎቱና መዝሙሩ ፋታ አይሰጥም መሰለኝ ብቅ ብለው አያውቁም::

ምጽ ምጽ ትል ነበር ያቺ ሰኑቱ ናት መሰለኝ ... ከምር ስንቱ አለፈ .. የሚገርም ነው .. ጌታያለው .. አይቀር የሚለው ልጅ የምር ሞቶ ቀረ ማለት ነው .. ወርቅሰውም .. ግን እነዚህ ታወቁ እንጂ ስንቶች ሞተው እንደሆነ ማን ያውቃል ብለህ ነው .. አሁን ሪቾስ ሞታ ሞታ የዋርካ ነገር አላስችል ብልዋት መጥታስ እንደሆነ ማን ፈለጋትና ይታወቃል ብለህ ነው :( ግን የምር አንዳንዴ ስለሞት ሳስብ ትንሽ ፌር ያልሆነ ነገር አለ ከምር .. አሁን ለስከመጨረሻው መሄዳቸው ሳይገርም በምንም መልኩ ከኛ ጋር እንዳይገናኙ መሆኑ አያናድድም ? አንዳንዴ በስልክ ቢፈቀድ ምን ነበረበት . ኢሜል ደግሞ በቅርብ ለሞቱ... ለነገሩ ለዛኛው አለም እኮ ኢሜልና ስልክ ህልም ነው አሉ .. ለዛ ነው እነሱ በህልማችን እየመጡ ያናግሩናል ... ይጎበኙናል እኛ ደግሞ ኢሜል እና ቮይስ ሜል አልደረሰንም ብለን እነነጫነጫለን .. ሰው መቼም በቃን አያቅ ቅቅቅ እረ በህልም አታሳጣን ነው ሆ ሆ ...
አይገርምም እኔ አክየና ዲጎኔ እንኳን ዋርካ ላይ ከተወለድን

7 ዓመት ልንደፍን ወራት ቀሩን::


[/quote]ልጅ ጌታቸው እኔ ቀድማለሁ አንተ ለዋርካ በነገርህ ላይ ?
"ሰነፍ በልቡ። አምላክ የለም ይላል በሥራቸው ረከሱ ጐስቈሉ በጎ ነገርን የሚሠራ የለም " መዝሙረ ዳዊት ምእራፍ 14:1
recho
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 3171
Joined: Mon Sep 20, 2004 12:28 pm
Location: Earth

Postby ደጉ » Fri Jan 13, 2012 5:33 pm

recho wrote:....
አይገርምም እኔ አክየና ዲጎኔ እንኳን ዋርካ ላይ ከተወለድን

7 ዓመት ልንደፍን ወራት ቀሩን::


ልጅ ጌታቸው እኔ ቀድማለሁ አንተ ለዋርካ በነገርህ ላይ ?[/quote]
...ሪችዬ መልካም ልደት የኔ ክፉ :D
"STUPID IS AS STUPID DOES " :D
ደጉ
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 4426
Joined: Mon Dec 15, 2003 10:39 am
Location: afghanistan

Postby ዋናው » Sat Jan 14, 2012 3:52 am

ሠላም ሠላም ጌታ ርቾዬ አባፈረዳ እና ደጉሸት ...
ከምር ግን ዋርካ ላይ እንዲህ እየተመላለስን ዳግም እናወራለን የሚለው ተስፋዬ እየተመናመነ መጥቶ ነበር ... መቼም እኔም እንደሁላችሁም ብጠፋም አሁንም ዋርካ ኢንዴክስ ምትለዋ ከላይ ቱልባሩ ላይ ከፊት እንዳለ ነው... ታዲያ ኢ-ሜይሎች ተነበው ዞር ዞር ሲባል በየቀኑ ጠቅ አድርጌ መግባቴን አልተውኩትም ግን እናንተ እንዳላችሁት ዋርካ ውርክክ ብላለች ከራሱ አውጥቶ ሀሳቡን አንድ ገፅ ዪሚጥፍ'ንኳን ጠፍቷል በቀላሉ ሊንክ መለጠፊያ ሆናለች... ላለመዋሸት ሊንክ ለማፈላለግ ዋርካ አሁንም አንደኛ ነች ... እንደድሮው ማሕበራዊ ውይይቶች አሉ...? ተብሎ ከተጠየቀ ግን የፖለቲካና የስፖርቱን አምድ እንጃ እንጂ እነኚህ የኛዎቹ ሁለት ሰፍሮች ግን በነጦምኔው ቋንቋ ሾቋል ብል ይቀለኛል...

ጌታ አንት የተሰማህ ስሜት እኔም ይሰማኛል ለምን አንድ ሰሞን ስንጨዋወት ደስ ብሎን ከርመን በዛው እንደዘበት እንጠፋለን... ብዬ በርግጥ ላይፍ ከባድ ነው የዛሬ 6 እና 5 ኣመት የነበረን የዋርካ ሞራል ዛሬ ድረስ ይኑር ማለቱ ድፍረት ሁሉ ሊሆን ይችላል ግን እንዲህ በሳምንትና በ 10 ቀናት እንኳን ጥቂት ቧልት እና ቀልድ እያመጣን ባንጠፋፋ ጥሩ ነበር:: አንድ ሰሞን ጥሩንባ ነፍቼ ጃኬት ጎትቼ አሰባስቤ ነበር እንዳንጠፋ ብዬ ርዕስ እየፈጠርኩኝ ሁሉ እሪ እምቧ ሁሉ ብዬ ባሟሙቅ ወዲያው ሰዉ ሁሉ ላጥ ላጥ አለ አንድ ቀን ግን ከምር በጣም ደበረኝ በቃ ቲስ... ብዬ ነው ሎግ ኦፍ አድርጌ የወጣዉት...
በዚህ ላይ ዋርካ አልሻሻል አለች የድሮ የነተበ ፐርፕል ሸሚዟን ለብሳ በቃ... ምንም ዓይነት ለውጥ አላሳይ አለች ዛሬ ዘመኑ እንደውቃው ስካር ፍጥን ብሎ የት ደርሶ ፎረሞች HTML5 ሊጀምሩ ባሉበት ወቅት..... እስቲ ተዉት (ያቅማችንን እንተባብር ብሎኬት ሚያቀብል አይጠፋም ተዉ ዋርካን እናድሳት እንገንባት ብዬ የቮለንተሪ ወረቀት ባስገባ የጉዱሻን ቅንጥብጣቢ ጠቀለሉበት...

ለማንኛዉም ስላየዋችሁ ደስ ብሎኛል ሽርፍራፊ ጊዜ ሲገኝ 'ስቲ ኑና ቢያንስ እንትና እንደፃፈቸው ምትለዋን እንኳን ለጥፋችሁ መኖራችሁን ጠቆም አድርጉ...

ሪቾ የሙታኖቹ ኢሜይል ተመችቶኛል አይ ዊሽ ስካይፒም ኖሮ የናፈቁኝን ባየዋቸው በዚህ አጋጣሚ ዲሴምበር 21 እንቀላቀላቸዋለን ሚባለው ነገር እንዴት ነው እናንተዬ?
እስቲ በዚህ ርዕስ እናውራ እጄ አንድ መፀሀፍ አለ The End of Time The Maya Mystery of 2012 የሚል የነርሱ ካላንደር እንዳለ ሆኖ ከዓለም ምትተርፈው ጥግ ቦታ ኢስት አፍሪካ ብቻ ናት ይባላል... እንደዚያ ከሆነ የሰመር ሆሊዳዬን ለዲሴምበር ላስተላልፈው ይሆን...

እስቲ እተጎነጫችሁ አውሩ::
ጥበብ ከእኔ የበለጠ ጠንካራ ናት እኔ እንደምፈልገው ሳይሆን እሷ እንደፈለገችው ታደርገኛለች::
ዋናው
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 2801
Joined: Tue Dec 16, 2003 5:29 pm
Location: ሕልም ዓለም

(-:

Postby ደጉ » Sat Jan 14, 2012 11:14 pm

ዋናው ሰላም ሰላም ወንድማችን ...አንዱ ኮሚክ ወንድማችን ሎተሪ እንጂ ተስፋ አትቁረጥ ብሎ ሲመክር አለስማህም...:)
..ለነገሩ ዋርካን ብናድንም ብንገልም በ እኛ ተጠቃሚዎችዋ እጅ ያለ ነው እሚመስለው...እንዳልከው ብዙ ጊዜ እንደ በፊቱ ላይኖረን ይችላል....እኔ በበኩሌ ግን ትንሽ ግዜ እማጣ አይመስለኝም...ለ ኢሜል ጊዜ ካለኝ ዋርካ ገብቶ አዲስ ነገር አይቶ ለመውጣትም ትንሽ አይጠፋም...ለሁሉም አንጠፋፋ ላልከው ግን አይዞን አንጠፋፋም...:)

አሪፍ ዊኬንድ ይሁንልን :)
"STUPID IS AS STUPID DOES " :D
ደጉ
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 4426
Joined: Mon Dec 15, 2003 10:39 am
Location: afghanistan

Postby ዉቃው » Wed Jan 18, 2012 1:03 am

አዎ በህይወት አለሁ ወዳጆቼ .....መጠጥ ቤት ቁምነገር አልፎ አልፎ አልፎ ሲወራ መልካም ነው :: ጓድ ጌታችውም ከሁለት መስመር የአመታት ፖስቶች ወደ በርካታ አንቀጾች መተላለፋቸው በራሱ ትልቅ እመርታ ነው ::

እኔ እምለው ..የምር አንዲት እህቴ ...ከምር በዋርካ ተናዳ ሰው እንደሞተባት ያህል በምሬት መሰናበቷን በጓሮ አውግታኛለች :: ምክንያቷን ባትገልጽልኝም ..በዋርካ ያለው የፀረ-አብዮተኞች ቅጥ ያጣ የሀይማኖት ስድድበ-ንትርክ ሳይሆን እንዳልቀረ ገምቻለሁ :: በኔ እምነት ..ንትርኮች እየተነሱ የሚጋጋሉብት ምክንያት ....የአንኢምፕሎይመንት ቁጥር ከፍ ሲልና መላጦቹ ልክ እኛ በህይወት ጣጣ እንደተጠመድን እነሱም በጊዜ ማጣት ዋርካዋን መጎብኘት መቀነሳቸው ሲበዛ እንደሆነ መረጃዎች ያሳያሉ :: ይህ ደግሞ የዋርካዋን ረጅም አብዮታዊ ጉዞ በአጭር እንዳይቀጨው ከማስጋቱም በተጨማሪ ...ታሪክን ለመጻፍና መጪውን ትውልድ በሞራል ኮትኩተን ለማሳደግ የምንናደርገውን መራራ ትግል ያደናቅፋል:: ይህን ለመከላከል በዋርካ ጥቂት አብዮት ጠባቂዎችን መርጦ አብዮቱን ከቀልባሾች ማዳን ግድ ይላል ::

ይህ በዚህ እንዳለ ...ወደ ሌላው ጉዳይ ስንዘልቅ....በ2012 የእሙሙ ጉዳይ እንዴት ይዟችኍል ? ለኔ እንዳጀማመሩ ከሆነ .......ዝም ነው :: ይቀናኛል ነው የምላችሁ :: ፈጣሪው ይጠብቅልኝ ::
ጉዟችን ረጅም : ግባችንም ሩቅ ነው !!!!
ዉቃው
ውሃ አጠጪ
ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1032
Joined: Sun Jan 07, 2007 2:48 am

Postby አቡቲ » Sun Jan 29, 2012 2:34 am

ሰላም ለእናንተ ይሁን!

ይገርማል ከጊዜያት ቆይታ ዛሬ ለአፍታ ያህል ብቅ አልሁ

እንዴት ናችሁ ታዲያ? ይሄ በቅብጥርጥር የተሞላ ዐለም ይቀባጠርበት ይቀባጠርለት ዘንድ ቢቀባጠርም ዳሩ እኔ ግን እቀባጥርበታለሁ.....

ሰላም!
"With all its sham, drudgery, and broken dreams, it is still a beautiful world.
Be cheerful. Strive to be happy."


Desiderata
አቡቲ
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 138
Joined: Wed Mar 09, 2005 2:59 am
Location: ኢትዮጵያ

Postby ፓን ሪዚኮ » Mon Jan 30, 2012 8:23 am

ሰላም ጎበዝ ዛሬ መጠጣት የሚፈልግ ካለ ባልቻ ቤት እንገናኝ ...አሮጊት ይመስል የመንደር ወሬ አሉባልታ ምናምን ይዞ የሚመጣ ካለ ቅንድቡ ይቆረጣል ::
ፓኑ አባ ፈርዳ
Imageኢትዮጲያ ትቅደም
ፓን ሪዚኮ
አለቃ
አለቃ
 
Posts: 2044
Joined: Tue Aug 03, 2004 3:35 am
Location: ጎሃ ጽዮን

Postby ተድላ ሀይሉ » Tue Jan 31, 2012 2:05 am

ዋናው wrote: በዚህ አጋጣሚ ዲሴምበር 21 እንቀላቀላቸዋለን ሚባለው ነገር እንዴት ነው እናንተዬ?
እስቲ በዚህ ርዕስ እናውራ እጄ አንድ መፀሀፍ አለ The End of Time The Maya Mystery of 2012 የሚል የነርሱ ካላንደር እንዳለ ሆኖ ከዓለም ምትተርፈው ጥግ ቦታ ኢስት አፍሪካ ብቻ ናት ይባላል... እንደዚያ ከሆነ የሰመር ሆሊዳዬን ለዲሴምበር ላስተላልፈው ይሆን...

እስቲ እተጎነጫችሁ አውሩ::


ፓኑ በፒልስነር ቺርስ ብለሃል .... እኔ ደግሞ በአገሩ ቢራ (እንደ ፒልስነር ባይጥመኝም) ....

ጋሼ ዋናው :- ይኼ የ'Maya Calender' የዓለምን ፍጻሜ ይተነብያል የሚሉት ፈሊጥ የእኔ ቢጤ የዋሆችን ለማነሁለል የሚጠቀሙበት የቁጩ ትንበያ እንደሆነ እጠረጥራለሁ :: ባለፈው አንድ ሐሮልድ ካምፒንግ የተባለ የጃጀ አሜሪካዊ ሚሊዬኔር ገና ለገና ገንዘብ አለኝ ብሎ "ዓለም Octobe 21, 2010" ታልፋለችና ሐብታችሁን ሁሉ ሸጣችሁ ንሥሃ ግቡ እያለ ሲያምታታ ነበር :: የተታለሉት ተታለሉ : ዓለማችን ግን እንደርሱ ፍላጎት ሣይሆን አላለፈችም ይኼው አለች :: እና ወንድሜ ሆይ መጽሐፉም "በኋለኛው ዘመን የሚነሡ ሃሣይ መሢኃን ይበዛሉ" ይላልና ለእንዲህ ዓይነት ትንበያዎች ብዙም ልብህን ከፍተህ አትስጣቸው ::

ተድላ
የወያኔ ሕገ -አራዊት አንቀፅ 39 ኢትዮጵያን የመበታተኛ ፈንጂ ነው !
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር !!!
ተድላ ሀይሉ ዘብሔረ -ኢትዮጵያ ::
ተድላ ሀይሉ
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 4903
Joined: Fri Mar 17, 2006 2:45 pm
Location: ኢትዮጵያ

Postby ዋናው » Mon Feb 06, 2012 2:51 pm

ተድላ ሀይሉ wrote:

ጋሼ ዋናው :- ይኼ የ'Maya Calender' የዓለምን ፍጻሜ ይተነብያል የሚሉት ፈሊጥ የእኔ ቢጤ የዋሆችን ለማነሁለል የሚጠቀሙበት የቁጩ ትንበያ እንደሆነ እጠረጥራለሁ :: ባለፈው አንድ ሐሮልድ ካምፒንግ የተባለ የጃጀ አሜሪካዊ ሚሊዬኔር ገና ለገና ገንዘብ አለኝ ብሎ "ዓለም Octobe 21, 2010" ታልፋለችና ሐብታችሁን ሁሉ ሸጣችሁ ንሥሃ ግቡ እያለ ሲያምታታ ነበር :: የተታለሉት ተታለሉ : ዓለማችን ግን እንደርሱ ፍላጎት ሣይሆን አላለፈችም ይኼው አለች :: እና ወንድሜ ሆይ መጽሐፉም "በኋለኛው ዘመን የሚነሡ ሃሣይ መሢኃን ይበዛሉ" ይላልና ለእንዲህ ዓይነት ትንበያዎች ብዙም ልብህን ከፍተህ አትስጣቸው ::

ተድላ


ሠላም ተድላችን
'ሚናፈሱትን ወሬዎች ስሰማ እጀመንገዴን መፅሐፉን ቃኘት አደረግኩት'ንጂ አምኜው ሱባኤ ልግባ አላልኩም :lol: ግን የሆነ የሚገርም የራሳቸው ነገር ነበራቸው እነርሱ እንደሚሉት ለዓለማችን የተሰፈረላት መቁጠሪያ አልቆ 'ሚገለበጠው ዲሴምበር 21 2012 ነው ነው::
የተባለዉን ሁሉ ቢፈጸምማ ኖሮ የመጀመሪያዉን ትንበያ አልፈን እዚህኛው ላይ ባልደረስን... ለነገሩ በእምነታችንም ቢሆን በእምነቱ ለሚፀና እንደሚድን ይታወቃል, በሳይንሱ ኢቨሊዩሽንም ቢሆን መሬት ገና ወጣት የምትባልበት ደረጃ ላይ ያለች ነች እርግጥ ነው ምድራችን ስልጣኔ እየፈሳባት ግምባሯን መቋጠሯ ይታያል...


ጥበብ ከእኔ የበለጠ ጠንካራ ናት እኔ እንደምፈልገው ሳይሆን እሷ እንደፈለገችው ታደርገኛለች::
ዋናው
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 2801
Joined: Tue Dec 16, 2003 5:29 pm
Location: ሕልም ዓለም

Postby ዋናው » Mon Feb 06, 2012 3:06 pm

አቡቲ wrote:ሰላም ለእናንተ ይሁን!

ይገርማል ከጊዜያት ቆይታ ዛሬ ለአፍታ ያህል ብቅ አልሁ

እንዴት ናችሁ ታዲያ? ይሄ በቅብጥርጥር የተሞላ ዐለም ይቀባጠርበት ይቀባጠርለት ዘንድ ቢቀባጠርም ዳሩ እኔ ግን እቀባጥርበታለሁ.....

ሰላም!

ሠላም የኔታ አቡቲ እንኳን በዓይነ-ድር (on the web/ዋርካ) ለመተያየት አበቃን... ከተያየን የ'ድሜዎቻችን ዘለሎች ጨመሩ ልበል...?
በል ምትጎነጨው ያዝ
ጥበብ ከእኔ የበለጠ ጠንካራ ናት እኔ እንደምፈልገው ሳይሆን እሷ እንደፈለገችው ታደርገኛለች::
ዋናው
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 2801
Joined: Tue Dec 16, 2003 5:29 pm
Location: ሕልም ዓለም

Postby ዉቃው » Sun Mar 04, 2012 3:06 am

መኢጠማዎች

ዛሬ ያሰኘኝን ልንገራችሁ ....ጉርም'ርሜ

ያሆ ............ያሆ

ጉርም'ርሜ ና ጉርም'ርሜ
አሆ በሌ ..አሁ በሌ ..ጉርምርምርምርምርምርምርም


ፓ ! መች ይሆን ሰርግ ሳንጠብቅ ጉርምርም የምለው ?

ቤቲ... ጌታ ይባርክሽ ! ለክሪኤቲቪቲው
http://www.youtube.com/watch?v=9WUJ91cLmK8

ጋሽ ሰዩም ተፈራ ..አሪፍ ሽለላና ቀረርቶ..ሰላሳዩን ማርያም የጠየቀካትን አትንሳህ ::

ጠጡ !
ጉዟችን ረጅም : ግባችንም ሩቅ ነው !!!!
ዉቃው
ውሃ አጠጪ
ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1032
Joined: Sun Jan 07, 2007 2:48 am

Postby ፓን ሪዚኮ » Tue Mar 13, 2012 11:59 pm

ባልቻ ምነው ? ምነው? ኑሮ መወደዱ ሳያንስ ? ባዶ ቤት ለፈረሴ ብስ የሚያቀርብ ውርጋጥ ለኔ ቢራዬን ይምትቀዳ ጠንጋራም ብጤ ብትሆን አንዲት አሮጊት ማስገባት አቅቶህ ?ያቀናነው ስንት የደከምንበት ቤት የማንም መጫወቻ ኤት ሆኖ ሲቀር ዝም ትላለህ?ደብዚም አረጀች ...ሞኒካም መነነች ..ደጉም መነኮሰ...ጉዱ ካሳም ጥርሱን ጨረሰ ...ውቃውም ...ምን ሆነ? ቻ ይቅር በግዜ ፈረሴን ታክሲዬን ይዤ ወዳማረብኝ ወደምከበርበት ቢራ ቤቴ ልገስስ ...የዚህ ቤት ወዳጆች ብዙ የታዘብኳቸው ሰዎች አሉኝ ..ስም አልጠራም ...አንድ ቀን ጥሬው ሙዝ ይነግራቹህ ይሆናል..ማን ያውቃል ...ምርቃናን የበላውም ጅብ ከሾኸ.አመታት አልፈዋል ...ቻዎ...ከ ጥቂት ቢራዎች በኋላ የተጽፍ:;
ፓኑ አባ ፈርዳ
Imageኢትዮጲያ ትቅደም
ፓን ሪዚኮ
አለቃ
አለቃ
 
Posts: 2044
Joined: Tue Aug 03, 2004 3:35 am
Location: ጎሃ ጽዮን

Postby እምቢ ለሀገር » Wed Mar 14, 2012 2:55 pm

ፓን ሪዚኮ wrote:ባልቻ ምነው ? ምነው? ኑሮ መወደዱ ሳያንስ ? ባዶ ቤት ለፈረሴ ብስ የሚያቀርብ ውርጋጥ ለኔ ቢራዬን ይምትቀዳ ጠንጋራም ብጤ ብትሆን አንዲት አሮጊት ማስገባት አቅቶህ ?ያቀናነው ስንት የደከምንበት ቤት የማንም መጫወቻ ኤት ሆኖ ሲቀር ዝም ትላለህ?ደብዚም አረጀች ...ሞኒካም መነነች ..ደጉም መነኮሰ...ጉዱ ካሳም ጥርሱን ጨረሰ ...ውቃውም ...ምን ሆነ? ቻ ይቅር በግዜ ፈረሴን ታክሲዬን ይዤ ወዳማረብኝ ወደምከበርበት ቢራ ቤቴ ልገስስ ...የዚህ ቤት ወዳጆች ብዙ የታዘብኳቸው ሰዎች አሉኝ ..ስም አልጠራም ...አንድ ቀን ጥሬው ሙዝ ይነግራቹህ ይሆናል..ማን ያውቃል ...ምርቃናን የበላውም ጅብ ከሾኸ.አመታት አልፈዋል ...ቻዎ...ከ ጥቂት ቢራዎች በኋላ የተጽፍ:;
ፓኑ አባ ፈርዳ

ጌታ ፓኑ እንደምን አሉ? እኔም እኮ በታጠቅ ፈረሴ ወደ ዋርካ ፖለቲካ እየገሰገስኩ እያለሁ አስኪ ባልችሻ ቤት አንድ ሁለት ልበል ብየ ዱብ ብል ቤቱ ወና ሁኖ አገኘሁት! አሳላፊ የለ!ጠጁ የለ! ያዚህ ቤት ታርኩ ሞልቶ የተትረፈረፈ ነበር::ምን አባቴ ይሻለኛል? አንድ ሁለት ቀምሸ ካልሄድኩ እዛ ቦለቲካ ቤት መለጐሜም አይደል :?
እንዴው ጌታ ፓኑ ከቤቱ ዋና ባለቤት ጋር ቅርርብ ካልዎት እባክዎት ይምከሩት! አዳዲስ ደንበኞች እየመጡ ነውና ቤትዎትን ሞቅ ሞቅ ያድርጉት ይበሉልኝ አደራ :!: በተለይ በደባርቅ ገብስ የተጠመቀ የደሮ አይን የመሰለ ጠላ ካዘጋጁ እኔ ብቻ አንዷን ገንቦ ጭልል እንደማደርግላቸው ይገሩልኝ :idea: የፈረንጁን ውስኪ ሁሉ የሚያስንቀውን የግብጦ አረቂ ካወጡም ወንድሜ ሞንሟናው መምጣቱ አይቀርም! እንግዲህ ይምከሯቸው!
ጌታ ፓኑ ይኸ ፈረስዎት ቁጭ የአብቹን ፈረስ አይደል እንዴ የሚመስለው :!: ፓ... ፓ... ፓ..! እንዴው ከየት አገኙት? መቸም ከሰላሌ መሆን አለበት! ሰላሌ ስል...እ..አዎ! ከጐሀ ጽዮን ትንሽ ወደ አባይ በርሀ ወረድ እንዳሉ አንዲት የፍየል ግንባር የምታኽል ቄንጣ ከተማ አለች::ፍ-ል-ቅ-ል-ቅ ትሰኛለች::እሷ የጠመቀችውን የማሽላ ጠላ የጠጡ ግዜና እንዼው መ-ፍ-ለ-ቅ-ለ-ቅ ነው!
አይ የኔ ነገር በባዶ ሆድዎት! እስኪ ይችን የተፈተገች የገብስ ቆሎ ባፍዎት ያዙሩ..ይያዙ ጌታየ! ውሀም ታነሳለች! ይበሉ እንግዲህ ይቺ ቤት ስራ ከጀመረች እየተገናኘን እንጫወታለን! የርስዎ ጭዋታ አይጠገብ! እንኳን ፊት ለፊት አግኝቸዎት ያቺ መጥሀፍዎትም አፌን እንዳስከፈተችኝ ነው የቀረችው! የትልቅ ሰው ዘር እኮ ጭዋታ ያውቃሉ! ደህና ይዋሉ ጌታየ!
እምቢ ለሀገር
ከፍልቅልቅ
ETHIOPIA ETHIOPIA ETHIOPIA
እምቢ ለሀገር
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 262
Joined: Mon Feb 13, 2012 5:08 pm

PreviousNext

Return to Warka Intimate - ዋርካ ፍቅር

Who is online

Users browsing this forum: No registered users and 1 guest