እምቢ ለሀገር wrote:ጌታ ፓኑ እንደምን አሉ? እኔም እኮ በታጠቅ ፈረሴ ወደ ዋርካ ፖለቲካ እየገሰገስኩ እያለሁ አስኪ ባልችሻ ቤት አንድ ሁለት ልበል ብየ ዱብ ብል ቤቱ ወና ሁኖ አገኘሁት! አሳላፊ የለ!ጠጁ የለ! ያዚህ ቤት ታርኩ ሞልቶ የተትረፈረፈ ነበር::ምን አባቴ ይሻለኛል? አንድ ሁለት ቀምሸ ካልሄድኩ እዛ ቦለቲካ ቤት መለጐሜም አይደል :?
እንዴው ጌታ ፓኑ ከቤቱ ዋና ባለቤት ጋር ቅርርብ ካልዎት እባክዎት ይምከሩት! አዳዲስ ደንበኞች እየመጡ ነውና ቤትዎትን ሞቅ ሞቅ ያድርጉት ይበሉልኝ አደራ :!: በተለይ በደባርቅ ገብስ የተጠመቀ የደሮ አይን የመሰለ ጠላ ካዘጋጁ እኔ ብቻ አንዷን ገንቦ ጭልል እንደማደርግላቸው ይገሩልኝ :idea: የፈረንጁን ውስኪ ሁሉ የሚያስንቀውን የግብጦ አረቂ ካወጡም ወንድሜ ሞንሟናው መምጣቱ አይቀርም! እንግዲህ ይምከሯቸው!
ጌታ ፓኑ ይኸ ፈረስዎት ቁጭ የአብቹን ፈረስ አይደል እንዴ የሚመስለው :!: ፓ... ፓ... ፓ..! እንዴው ከየት አገኙት? መቸም ከሰላሌ መሆን አለበት! ሰላሌ ስል...እ..አዎ! ከጐሀ ጽዮን ትንሽ ወደ አባይ በርሀ ወረድ እንዳሉ አንዲት የፍየል ግንባር የምታኽል ቄንጣ ከተማ አለች::ፍ-ል-ቅ-ል-ቅ ትሰኛለች::እሷ የጠመቀችውን የማሽላ ጠላ የጠጡ ግዜና እንዼው መ-ፍ-ለ-ቅ-ለ-ቅ ነው!
አይ የኔ ነገር በባዶ ሆድዎት! እስኪ ይችን የተፈተገች የገብስ ቆሎ ባፍዎት ያዙሩ..ይያዙ ጌታየ! ውሀም ታነሳለች! ይበሉ እንግዲህ ይቺ ቤት ስራ ከጀመረች እየተገናኘን እንጫወታለን! የርስዎ ጭዋታ አይጠገብ! እንኳን ፊት ለፊት አግኝቸዎት ያቺ መጥሀፍዎትም አፌን እንዳስከፈተችኝ ነው የቀረችው! የትልቅ ሰው ዘር እኮ ጭዋታ ያውቃሉ! ደህና ይዋሉ ጌታየ!
እምቢ ለሀገር
ከፍልቅልቅ
ሠላም ብያለሁ እምቢ...
ወግህን ሳዳምጥ የ2012 ዋርካዊ አትመስልም አንተማ የሻይቦይ አብሮ አደግ መሆን አለብህ የዳቦ ግብር ፈርተህ እንጂ አብርህን ያረጀህ ሳትሆን አትቀርም... የሆነው ሆኖ በስማ በለው ከሚሆን እኔው ራሴ ምክርል ልሰማ መጥቼያለሁ አሁንማ ጠላ ጠማቂዉም ዛፍ ቆራጩም ጠጅ ቀጂዉም ቤቱ ከርችሞ ስለተመመ የዋርካን ቢዝነስ በሞኖፖል ለማያዝ እያሰብኩኝ ነው ፓኑ እንዳለው ጠንጋራና ሸፋፋ ሳይሆ ቅንድብ ምታደርቀዋን አንጓዋ ያማረ ቆንጆ አምጥቼ እንዲ አጥንቱ የወጣውን ቤቴ ላይ አምነሸንሻታለሁ... ድሮም ቢሆን ቤቴን ሚያደምቀው ተላካፊ'ኮ ነው::
የገብስ ቆሎህን ዘግኜያልሁ አመሰግናለሁ:: እስቲ ወደጓዳ ልግባና ጉሮሮ ሚያረጥብ ነገር ልፈልግ ደብዚቾ 50ኛ ዓመቷን ስታከብር ተከፍቶ የተጀመረ ወይን ጠጅ ነበር ለትዝታም ቢሆን እሱን ላምጣው::
አባፈረዳ ምን ላድርግ ሁሉም በቁሙ እየተመለሰ አስቸግሮኝ'ኮ ነው በል ና ፈረስህን መልሰህ እሰርና ስለጥንቱ እናውራ::
ያ ውቃው በር ላይ ሲዘፍን ሰማዉት ልበል...?