እስቲ የኳስሜዳ ልጆች አንድ በሉ

The Love Forum (love, relationship) (የኔ ቆንጆ እንተዋወቅ :-)

Postby ጦምኔው » Wed Aug 01, 2007 1:31 pm

በለውውውውውውው...............አወራረደው::..........አንተ ደሞ የመጬ ትገርማለህ:: የሐሮኒን ነገር አታንሳው ባክህ:: ሐሮኒ አፈቀረን ተፈቀርን ነው የሚባለው::....ቅቅቅቅ............ወይ ሐሮኒ ማታ ማታ ተማመን ነበር እኮ..........ቅቅቅቅቅ.......አሁንም ሐሮኒ እንደዛው ነው እንዴ??...........ስማ ደሞ የኔ ዘፈን የሚባለው የቱ ነበር እንኳ?

ይመችህ አቦ ከአውቶቡስ ተራ እስከ አድማስ ( ሐሮኒ) ድረስ አስቃኘኸን...........ስማ ጳውሎስ ሆቴል ያለው ማኪያቶ አቦ ድሮ ቀረ ባክህ........ገኒ ቤት ያለውስ ቅቅል ትዝ አይልህም?.........ኧረ እንደውም ጠዋት ጠዋት ዊክ ኤንድ ላይ ዱለት ተማመን ነበር ጳውሎስ......አየለ ሆቴልን ምነው ላሻ አልከው ታዲያ?...........ደሞ ከስጋ ቤቶቹ መደዳ የለማ ቤት ነበር ተማመን.............አይ ለማ እርሱ ራሱ እኮ ጸዳ ብሎ የሽንጥ ስጋ ነው የሚመስለው :lol: ........

ጸሀይ እብዷ..............በጣም ምስኪን ሴት ናት ከምር....አለች ይሆን ግን አሁን? ሰናይት እብዷስ?..........አስታወሳችዋት?.........ዝናጯ ቀዌ?.........ኧረ ስንቱ ቀረ እኛ ሰፈር.............

ስማ ፑል ቤቱ ማለት የነ ዮናስ ቤት ነው? ወይስ ትዝታ ግሮሰሪ አጠገብ ያለው?..........አቦ ዘነጋሁት መሰለኝ?..............ወይስ ትኩሱ ቪዲዮ ቤት (03)..........ኧረ ባክህ አስለፈለፍከኝ...........ተመቸኸኝ ግን ማርያምን::

:lol: :lol: ሚስተር ትሪ :lol: :lol: .........ቅቅቅቅ............አሁን እኔ እንደው በቡሌ ነገር እታማለሁ?............እንደው ብታማ እንኳ ባንተ እታማለሁ?.............አንተ እኮ ጀርባህ ሁሉ ሆድ ነው አሉ......ኧረ እንደውም ችኳንታ መች ሞተ አለ እንጂ የተባለው አንተን ካየን በኍላ አይደል :?:.......ቅቅቅ.........አንድ ጊዜ ስትጎርስ አንድ በያይነት እጅህ ላይ ያዘዝክ ነው የሚመስለው እያሉ ያሙሀል እነ ሀት... :lol: .......ለጭውቴ ነው ጀለሴ..........ቡሌ የጌጃ ነው ባክሽ..............ዘለልነው!!

SNS ተሰርቶ አለቀ እንዴ?..........ለዳሽን ባንክ አከራይተውት ነበር የበፊቱን ስቶራቸውን.............ከአጠገቡ ጊቢው ውስጥ ጂ ፕላስ እያሰሩ ነበር,...........አለቀ ይሆን?........ምን አገባኝ እስኪ አሁን?........ሰሙ ንጉስ እንኳን ይህንያህል አልጨነቀውም.............

ስማ ደሞ ምነው ጀምስ እና ሜክሲኮ ሻይቤቶችን ረሳሀቸው?............አሁን እንደው እዚያ ቤት ጥምዝምዙን ብስኩት ያልበላ አለ?..........ሁለቱ ወንድማማች ሻይ ቤቶች ከልጅነታችን ጀምሮ ነው ያሳደጉን...........እንደውም የሀት የልጅነት ፍቅረኛዋ መከመሪያ የጠበሳት በጀምስ ብስኩት ነው :lol:......ከቀስቴ አስፎርፎ................ቅቅቅ

ኧረ አብራራሁ በጣም ስልህ እንደ አብራር አብዶ..............ቅቅቅ

በሉ የሰፈር ልጆች ከች በሉና ቅደዱ..............ሰላም::
ጦምኔው
ዋና ውሃ አጠጪ
ዋና ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1529
Joined: Sun Jan 14, 2007 10:40 pm
Location: Right here

Postby ሰናም » Wed Aug 01, 2007 1:32 pm

አማን ናቹ ኳስ ሜዳዎች sarandem :lol: :lol: :lol: በጣም አሪፍ ነው በተለይ ስጋ-ቤቱ የጳውሎስ ማኪያቶ waw ነው የሚየስብለው እስኪ ሌሎቻቹም ቀጥሉበት
ሰናም
አዲስ
አዲስ
 
Posts: 17
Joined: Sat Sep 09, 2006 6:14 pm

Postby ጦምኔው » Sat Aug 04, 2007 4:03 pm

እሺ ባካችሁ የሰፈር ልጆች.......ሰላም ነው?

ምነው ምን ተገኘ ጠፋፋችሁሳ?........እንዴት ነው ስፖርት ሻይ ቤት ብስኩት በነጻ መታደል ተጀመረ እንዴ?.....ቅቅቅ........ወይስ ዋቢ ሸበሌ ዳቦ ቤት ወረፋ በዝቶባሁ ነው?................ስላችሁ ተጠፋፋን:: አቦ ብቅ ብቅ በሉና አጫውቱና.........

ኧረ አድዬ እየጠራኝ ነው መጣሁ ቆይ ................
ጦምኔው
ዋና ውሃ አጠጪ
ዋና ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1529
Joined: Sun Jan 14, 2007 10:40 pm
Location: Right here

Postby AAETV » Sat Aug 04, 2007 9:57 pm

እስፓርት ሻይ ቤት ቅቅቅቅቅቅቅ በከ ከፍተኛ 6 እስት አዳጋው ሻይ እይጠጥውኝ ነው>>>>> ከፈልክ ሂሩት ኬክ ቤት ሻይ እግብዝካላውኝ ጦምኔው..........


ጦምኔው አንተ ግን የ01 ቀበሌ ልጅ መስልክኝ አንድ ቀን ከበደ ወፍጮቤት ጋ 50 ሳንቲብ ተብድርክኝ ነበር መቼ ነው የምትክፍልኝ እኔ የ27ቱ ነኝ ኮቴ ተራ ጋ
AAETV
አዲስ
አዲስ
 
Posts: 13
Joined: Thu Apr 01, 2004 5:14 pm

Postby ጦምኔው » Sat Aug 11, 2007 3:24 pm

ሠላም የሰፈር ልጆች........

ምነው ተጠፋፋን? ሳራንደም, ሆት ማማ. AAETV, ሰናም,.........ሁልሽም ......አቦ ብቅ በሏ!...........

እስኪ ስለ ኳስ ሜዳ ሰፈር አንዳንድ ሰዎች ላስታውስ..........አሁን እስኪ ማን ይሙት የኳስ ሜዳ ልጅ ሆኖ ጫማውን "ቦግዬ" ጋር ያላሰፋ አለ?.........ቦግዬ እኮ ጫማ ሲሰፋ ተማመን ነበር......የተቦደሱ ስኒከሮችን ምናምን የልጅነት ወዘናቸውን ነው የሚጌቫቸው.........ቅቅቅቅ..........እንደውም adidas እና NIKE ካምፓኖዎቹ ጠይቀውት ነበር........ሊቀጥሩት......እሱ ግን ለሰፈር ልጆች ካለው ቀና ፍቅር ጥሎን ሊሄድ አልፈቀደም....አገልግሎቱን ስቲል እየሰጠ ይገኛል.......ቦግዬ ፍቅር የሆነ ልጅ ነው::

ቦግዬ ዲሪንዲሪሪን.........ቦጋለም ዲሪንዲሪሪም............. :lol: :lol: :lol:

አንተ ደሞ 50 ሳንቲሜን ስንግህን ቀቡ አድርጌህ ከች ታረጋታለህ..........10 ጀላቲ ከ አልጋነሽ ቤት ይገዛልኛል...........ስልህ የበሶ ጀላቲ :lol: :lol: :lol: .....የኛ ሰፈር አይስ ክሬም ልበልህ :lol:

ፒስ!!
ጦምኔው
ዋና ውሃ አጠጪ
ዋና ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1529
Joined: Sun Jan 14, 2007 10:40 pm
Location: Right here

Postby sarandem » Sun Aug 12, 2007 11:13 am

አረ አልጠፋንም አለን ...አለን ...ገና እንኖራለን
ጦምኔው wrote:?...........ስማ ደሞ የኔ ዘፈን የሚባለው የቱ ነበር እንኳ?


አሁን የራስህ ሲንግል ጠፍታህ ነው:: በል እኔ ሳላወጣ ራስህን አጋልጥ :wink:
ለቦግነት አሁን ከዘፈንካት ጋር ትመሳሰላለች::
ጦምኔው wrote:ይመችህ አቦ ከአውቶቡስ ተራ እስከ አድማስ ( ሐሮኒ) ድረስ አስቃኘኸን...........ስማ ጳውሎስ ሆቴል ያለው ማኪያቶ አቦ ድሮ ቀረ ባክህ........

ልክ ነህ በቅርቡ እንደድሮ መስሎኝ ጎራ ብዬ ነበር ማክያቶው እንደ ድሮ አይደለም አዛ ቤት ውስጥ እነዛ ካልካቸው መንትዮች ውስጥ አንዱን አግኝቼው (አሁን ፖሊስ የሆነውን) ብዙ ቀደድን ነው ሚባለው::

ጦምኔው wrote:?......አየለ ሆቴልን ምነው ላሻ አልከው ታዲያ?...........

በአሁኑ ሰአት አየለ ሆቴል የመጬ ገበያ ደርቶለታል:: ትሴ እና ግርግር ስለሚበዛ ላሻ ማለት ሲያንሰኝ ነው::


ጦምኔው wrote:ጸሀይ እብዷ..............በጣም ምስኪን ሴት ናት ከምር....አለች ይሆን ግን አሁን? ሰናይት እብዷስ?..........አስታወሳችዋት?.........ዝናጯ ቀዌ?.........ኧረ ስንቱ ቀረ እኛ ሰፈር.............ጸሀይ ቀዌዋን ካየኻት ቆየ:: ኢብሮ ግን እንደሞተ ሰምቻለሁኝ::

ጦምኔው wrote:ስማ ፑል ቤቱ ማለት የነ ዮናስ ቤት ነው? ወይስ ትዝታ ግሮሰሪ አጠገብ ያለው?..........አቦ ዘነጋሁት መሰለኝ?..............ወይስ ትኩሱ ቪዲዮ ቤት (03)..........ኧረ ባክህ አስለፈለፍከኝ....


ከዘኩ ምግብ ቤት ፊት ለፊት የተከፈተውን ነው የጠቀስኩት:: ያሁኑን አያረገውና ፑል ምንጫወተው ሞተራ(ሞቼ ተሟሙቼ ራቴን) ነበር::

ጦምኔው wrote: .........ቅቅቅቅ............አሁን እኔ እንደው በቡሌ ነገር እታማለሁ?............እንደው ብታማ እንኳ ባንተ እታማለሁ?.............አንተ እኮ ጀርባህ ሁሉ ሆድ ነው አሉ......ኧ :?:.......ቅቅቅ.........አንድ ጊዜ ስትጎርስ አንድ በያይነት እጅህ ላይ ያዘዝክ ነው የሚመስለው እያሉ ያሙሀል እነ ሀት... :lol: .......

:) :) :) በሳቅ ነው የገደልከኝ የመልስ ምት በሌላ ቀን ይሰጥሀል::
ጦምኔው wrote: SNS ተሰርቶ አለቀ እንዴ?..........ለዳሽን ባንክ አከራይተውት ነበር የበፊቱን ስቶራቸውን.............ከአጠገቡ ጊቢው ውስጥ ጂ ፕላስ እያሰሩ ነበር,...........አለቀ ይሆን?........ምን አገባኝ እስኪ አሁን?........ሰሙ ንጉስ እንኳን ይህንያህል አልጨነቀውም.............

አይገርምም ያንተ እንደዚህ ለነሱ ቤት ማለቅ መጨነቅ :?:
:) :) :) ይልቅ እነ ሰሙ በቅሎ ቤት ያለውን show room ወደ sport bar ቀይረውት ሄጄ አይቼው በጣም ያምራል::

ጦምኔው wrote:ስማ ደሞ ምነው ጀምስ እና ሜክሲኮ ሻይቤቶችን ረሳሀቸው?............አሁን እንደው እዚያ ቤት ጥምዝምዙን ብስኩት ያልበላ አለ?..........ሁለቱ ወንድማማች ሻይ ቤቶች ከልጅነታችን ጀምሮ ነው ያሳደጉን...........እንደውም የሀት የልጅነት ፍቅረኛዋ መከመሪያ የጠበሳት በጀምስ ብስኩት ነው :lol:......ከቀስቴ አስፎርፎ................ቅቅቅ

:) :) :)
ከጀምስ እና ሜክሲኮ አሁንም ትልቅ ከሆንም በኃላ ሳንቡሳ አስመጥተን እንበላ ነበር::
ጦምኔው wrote:ኧረ አብራራሁ በጣም ስልህ እንደ አብራር አብዶ..............ቅቅቅ

:D :D እንደ አብራር አብዶ ብቻ ሳይሆን እንደ ጛድ አብዱ ጭምር :D
sarandem
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 674
Joined: Tue Jul 11, 2006 8:59 am
Location: Nomad Cafe

Postby ጦምኔው » Sun Aug 19, 2007 2:04 pm

ኧረ የሰፈር ልጆች የት ገባችሁ? ሆያሆዬ ልትጨፍሩ ሄዳችሁ እንዴ?.......ቅቅቅቅ........አይ ሆያሆዬ :? .......ተጨፈረለት በደጉ ዘመን:: ትዝ ይላችኍል መሳለሚያ ያለው ግርግር?....የሀገር ሆያሆዬ ጨፋሪ ፈላ ሶስት አራት ሆኖ ዱላ እና ኪሽ ኪሽ ይዞ በየመደቡ ላይ ሲንጫጫ?.......ቅቅቅቅ.........ወይ ያ ዘመን!!.......ትዝ ይለኛል ሳንቲም የማይወጡ የመሴ ነጋዴዎች ሽንኩርት ድንች ምናምን ይሰጡንና ያንን ሰፈር ይዘን መጥተን እንቸበችበው ነበር..... :lol: ......ሆያሆዬ መሳለሚያ ቀረ ባክህ.......ትንሽ ደሞ ከፍ ስንል ስልህ በዕድሜ ወደ መርኬ እንሸጋገራለን መሴን ለፈላዎች ትተን........እንዲህ እንዲህ እያልን ነበር ሆያሆዬን ለዚህ ያበቃነው :lol: :lol: :lol:

አቦ ጠፋችሁሳ የሰፈር ልጆች.......እስኪ የቡሄ ገጠመኛችሁን ዱቅ ዱቅ አርጉና እንንፈርበት ወይም እንዘንበት....

አንዴ እኮ ነው ሆያሆዬ ልንጨፍር ወደ መሳለሚያ እየሄድን ሙላት ሆቴል ከዓሳ ቤቱ ጎን ማለት ከ 11 ቁጥር አውቶቡስ መጫኛው ጋር ያለው ጡጢ ቤት ገባን:: ኑ ጨፍሩ ብለውን ስንቀውጥ ቆየን./.....መዓት ሰዓት አስጨፈሩን አውጪው እየተቀያየረ ........መጨረሻ ላይ ምን አንዳሉን ታውቃለህ.....በሉ እስካሁን ለጨፈራችሁበት ሽልማት የሚሆን አንድ ሆያሆዬ ጨፍሩ!!........... :lol:

ኧረ በቡሄ ስንት ይወራል!!

እንኳን ለቡሄው አደረሳችሁ................!!
ጦምኔው
ዋና ውሃ አጠጪ
ዋና ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1529
Joined: Sun Jan 14, 2007 10:40 pm
Location: Right here

Postby sarandem » Thu Aug 23, 2007 12:17 pm

ኬፍ ኬፍ :!: :!:
ምነው ሰፈር ላይ መከሰት አቆማቹ :?:
እንደጉድ ተጠፋፋን ነው ሚባለው:: እኔ እንኳን ሰሞኑን በርበሬ ስለተወደደ መስቃን....አሊቾ ....ወሪሮ መለስ ቀለስ እያልኩ ነው::

ሽቀላ በሰሞኑ ያስፈልጋል:: ከቡሄ የተገኘችው ፍራንካ እንደሆ .... መግዣ አታልፍ::

ሰፈር ደውዬ ነበር:: AAETV ትሴዎችን በማስቸገር አልተቻለም::
ትሴ ከመውደዱ የተነሳ በኮቴ ተራ ሚያልፋ ሴቶችን ነጠላ ይቓጫል አሉኝ:: ሴቶች እኮ ገና ሲያገኙት በጣም ስለሚያስቸግር ነጠላቸውን ቓጭልን ብለው ይሰጡታል አሉ:: አሉ ነው እንግዲህ :lol: :lol: :lol: እባክህ AAETV እንደዚማ ትሴዎችን አታስቸግር::

በሰሞኑ ማይረባ ነገር ከተናገርሽ ጎመን በጤና ሚባል አባባል መጥቷል:: ይህ እንግዲህ ከጸሀዬ ዮሀንስ ካሴት ውስጥ አንዱ ዘፈን ላይ ጎመን በጤና ምናምን ሚላት ነገር አለ:: ብቻ የሱ ዘፈን ኮሚክ መሆን ተከትሎ የመጣ ቡጨቃ ነው አሉ:: አሉ ነው እንግዲህ:: ጫወታን ጫወታ ያነሳው የለም ከሰሞኑ ጎሳዬ ቲሸርት አወጣ አሉ:: የሱም ዘፈን ቢሆን ኮሚክ ነገር ነው አሉ:: በሀይለኛው ዝግ ቢዘጋም ዘፈኑ ግን የተጠበቀውን እና የተወራለትን ያህል አልሆነም:: እሱ ግን ድምፄ አሪፍ ነው ይላል አሉ::

ይልቅ ኢሳያስ ወደ ሰፈር ተመልሷል:: ገና እንደተመለሰ ጂን ናፍቆኛል ብሎ ለአንድ ቀን ብቻ ሀረር ግሮሰሪ ከሰት ብሎ ነበር:: እናንት አሜሪካ ያላቹት ላይ ብዙ ያጫወተባቹ ነገር አለ :: አሜሪካ ያሉት መጠጥ ያስጀምሩትና ዛሬ ገና ሚያጣጣኝ አገኘሁ ሲል በሁለተኛው ላይ ተቄ በማለት እንደተማረረ ለሰው ሁሉ ያወራል :: :evil: ::

በሉ ልሂድ ጎመን በጤና አበዛሁ መሰለኝ
sarandem
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 674
Joined: Tue Jul 11, 2006 8:59 am
Location: Nomad Cafe

Postby ሰናም » Thu Aug 23, 2007 1:56 pm

ሰላም የኳስሜዳ ግርፎች እንዴት ነው የአዲሱ አመት ዋዜማ ኳስሜዳ ግርግር ሁሉም ባቅሙ ሸቅሎ 2000 ለማክበር ደፋ ቀና ሲል የኑሮ ውድነት ጣራ ነካ ሲባል በርበሬ $1000 ብር ከገባ ዘንድሮ የዶሮ አልጫ ሳይሆ አይቀም የሚበላው :lol: :lol: :lol: በሉ እንግዲ መሰንበት ደግ ነው አለቸ ሜሪ አርምዴ :lol: :lol: :lol:
ሰናም
አዲስ
አዲስ
 
Posts: 17
Joined: Sat Sep 09, 2006 6:14 pm

Postby ጦምኔው » Sat Aug 25, 2007 10:36 pm

ዋዛፕ የሰፈር ልጆች.............

ስማ እንጂ ሳራንደም.........የ AAETV ነገርንማ አታንሳው........ :lol: የችኮችን ነጠላ ይቋጫል :lol: ........ኧረ እንደውም እየጀነጀናቸው ነው አሉ መንገድ ላይ የሚቋጨው.........ስልህ ዎክ እያረጉ ሁላ.......ቅቅቅ......ኧረ እንደውም ከቹኮች ጋር ብዙ ከመታየቱ የተነሳ የሴቶች ጉዳይ አማካሪ እንዲሆን የ27 ቀበሌ ሴቶች ጉዳይ ሀላፊ ለምናዋለች አሉ.......እኔ እንደሆነ ምን አውቄ..........አሉ ነው እንግዲህ.........

ስማ ሰናም.........የዶሮ አልጫ?............ቅቅቅቅቅ........ሳይሆን አይቀርም ባክህ.......ኑሮ ሀርድ ሆኗል አሉ ባክህ.........እሱ ያውቃል ነብሴ.....አንቺ ግን አማን ነሽ አይደል?/..........ሀት ማማ አንተን ተከትላ ነው የጠፋችው የሚባለው እውነት ነው?.....

ኧረ ጨዋታው ቀዝቅዟል እዚህ ሰፈር........አቦ ብቅ እንበላ........

ፒስ ደሞ.......ይመቸን.........
ጦምኔው
ዋና ውሃ አጠጪ
ዋና ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1529
Joined: Sun Jan 14, 2007 10:40 pm
Location: Right here

Postby AAETV » Sun Aug 26, 2007 6:27 pm

ስላም ስላም የስፈር ልጆች እንዲት ነው ኑሮ??
የ27 ቀበሌ?? ስማ እኔ ሶሬ ነኝ ወይስ ዋጋዬ?? የ27 ቀበሌ የሴቶች ለቅምብር የምትድርግኝ??

ስማ የአባዳማ እድርተኝ ጡርባ ነፋ ጦምኔው እንዲት ነህ??
ጦምኔው መቼ ነው የእኔን 1 ብር የምትክፍልኝ ክፍተኛ ሜዴ የብድርኩክን
AAETV
አዲስ
አዲስ
 
Posts: 13
Joined: Thu Apr 01, 2004 5:14 pm

Postby ቀብራራው ንጉሴ » Sun Aug 26, 2007 7:38 pm

ወንዱ የሳቱ ላንቃ ..እም ግራ አሳይቶ ቀኝ የሚማታ አንድ ብቻውን ለሺ የሚበቃ ወንዱ የሳቱ ላንቃ
ቀብራራው ንጉሴ
አዲስ
አዲስ
 
Posts: 29
Joined: Mon Aug 20, 2007 10:27 am

Postby ጦምኔው » Sun Aug 26, 2007 7:53 pm

AAETV... :lol: :lol: ስማ ደሞ አታፍርም..........ቅቅቅቅ.........ዋጋዬ?.......ስልህ አለ አይደል አንተም እኮ የመጬ አበዛኸው........እስኪ አሁን ነጠላ መቋጨት ሆቢህ ሆኖ.......

ስማ እንጂ እንዴት ነው ሰፈር? ኩሉ አማን ነው?......ሚሊኒየሙን ለመቀበል ያላችሁ ተነሳሽነትስ?......ሰፈር ውስጥ የርችት ፕሮግራም ከሸራተን አዲስ በቀጥታ ለመከታተል እንዲቻል የተደረገ ጥረት አለ?.....ስልህ እኛ ከእሪ በከንቱ ልጆች በምን እናንሳለን?........ጋራ ላይ ስላልሰፈርን ነው?.......ስልህ አለ አይደል......ሞቢልም ጋራ ነው!!.......

ደሞ ስለ ብድሩ.......1 ብር?.......እኔ እኮ የምለው ቆይ........ያንተ ብድር በስንት ፐርሰንት ነው ኢንተረስት ሬቱ የሚያድገው?.....ወይስ በ ኢንኩቤተር እያስፈለፈልከው ነው አንድ ብር የገባው?.......አንድ የበሶ ጀላቲ በ አስር ሳንቲም ገዛህልኝና ነው ኤካ አምጣ የምትለው...........ኧረ እፈር ባክህ......

እኔ የምልህ ምን አዲስ ነገር አለ ሰፈር?.....የወለደ ያገባ የሞተ.....የገደለ.....ጭውቴው ምን ይመስላል?......ተስፋዬ ሕንጻ ላይ ያለውን ንግድ ባንክ ለመዝረፍ ጥረት ታደርጋለህ አሉ ደሞ.......ወሬ አይደበቅ....

ስማ እንጂ 27 ቀበሌ ሲባል......ከአባይ ዳቦ ቤት ገባ ብሎ ያሉት እነዚያ ቆነጃጅት እህትማማቾት አሉ አሁንም?.......አንዷ ስሟ ዘላለም ነበር መሰለኝ......ወይ ውበት.......እስኪ የት እንደደረሱ አጫውተን.......ግን ምን አገባኝ የትስ ቢደርሱ?.....ያገባኝ ይሆን እንዴ???

ደሞ በአባ ዳማ እድር ብር ነው ከሀገር የወጣው እያልክ የምታስወራውን ወሬህን ሳራንደም ቢሰማ ዋ ብያለሁ.......ማላገጫህን እና ማላመጫህን ወደ ማዳመጫህ ነው የሚያጠጋጋው........እሱ እኮ ኤሊያስ ጋ ካራቴ ስልህ ውሹ ይሰራል አሉ........04 አዳራሽ........ቅቅቅቅ.............


አስለፈለፍከኝ ጃል............
ጦምኔው
ዋና ውሃ አጠጪ
ዋና ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1529
Joined: Sun Jan 14, 2007 10:40 pm
Location: Right here

Postby ጦምኔው » Sun Aug 26, 2007 7:56 pm

ቀብሬው.......ስልህ ንጉሴው....... :lol: :lol:

"ኧረ ጎራው" በዜማ ይጎለዋል ፉከራህ ከፊት ለፊቱ...........እና ከኍላው ደሞ........... :lol:

አማን ነው ጀለሴ?.......ይመችሽ......እስኪ የሰፈር ወግ ዱብ አርጊ.........

ፒስስስስስስስ
ጦምኔው
ዋና ውሃ አጠጪ
ዋና ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1529
Joined: Sun Jan 14, 2007 10:40 pm
Location: Right here

Postby ኮሊማ » Mon Aug 27, 2007 10:52 am

ስላም ኳስ ሜዳዎች

ጦምኔው ስለኳስ ሜዳ ብዙ ብዙ ትላለህ
ስማ ከሰፈራችሁ አሪፍ ቢገኝ አንድ ቴዲ አፍሮ ነው
ሚካኤልን በጣም ትገርማላችሁ እሺ!
.....የመጨረሻ ምላሳም ናችሁ ..... ግን ለምንድን ነው ከሰፈር ብዙም ማትወጡት ርቃችሁ ሄዳችሁ ከተባለ እስቴድየም ....::
ሁሌም የሚያሳዝነኝ ፉገራዎቻሁ ከአውቶብስ ተራ እስከ ፓስተር እንጂ የሌላ ሰፈር ልጆችን ፈጌ አለማስባሉ...... ቅቅቅቅቅቅ ለነገሩ
እኔና ጀለሶቼ ግን አዋጥተንም ቢሆን ፈጌ ማልታችን አልቀረም ......... :: ያን ደፍጣጣውን ልጅ ግን የት እንደገባ
አፈላልገህ ንገረኝ ቤታቸው ከ27 ሜዳ አጠገብ ነበር ምናልባት አሁን ኮንዶሚኒየም ተሰርቶበት ይሆናል ምን አሳውቅኝ:: ሜዳው ላይስ ሕንፃ ሲሰራ ዝም ብላችሁ የለ::
ለማንኛውም ምላሽህ በጉጉት ይጠበቃል.......ግን ትርፍ ንግግር ተረብ ምናምን ሞክራለሁ ብለህ ውየውልህ......መዛቴ አይደለም ለጥንቃቄ ቢረዳህ ብዬ.......ቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅ

ኮሊማ
ከጠቅላይ ቢሮ
ኮሊማ
መንገደኛ
መንገደኛ
 
Posts: 4
Joined: Fri Mar 26, 2004 12:30 am
Location: ethiopia

PreviousNext

Return to Warka Intimate - ዋርካ ፍቅር

Who is online

Users browsing this forum: No registered users and 2 guests