እስቲ የኳስሜዳ ልጆች አንድ በሉ

The Love Forum (love, relationship) (የኔ ቆንጆ እንተዋወቅ :-)

Postby sarandem » Mon Jul 23, 2007 1:21 pm

ሀይ ጦምኔው እንዴት ነህ ባያሌው ..ሙዚቃ...ቤት ማለትህ አይቀርም::

ሙሌጌታ መኪና ዘዋሪ ሆነ ነው ያልከኝ ? በደረሰኝ ዜና ፋይል መሰረት መኪና ሲነዳ ስጎ ከማብዛቱ የተነሳ ምራቁ ሲመጣ ሚተፋው የፊት መስታወት ላይ ነው አሉ::

የሞቢልን ፉገራዎች እስክትለቃቅም እኔ ማስታውሰውን ልበል::

አንዷ ኢሳያስ አ. የተባል ልጅ ጋር ትመጣና በጣም ቁሽሽ ያለ calculator ስራልኝ ትለዋለች:: እርሱም ሳይቀበላት አንቺ አር ነው እንዴ ምታባዢበት? ብሎ ቆሌዋን ገፏታል::

ሌላው የሞቢል ልጆች ሚታወቁበት ነገር ገና ንግግር ስትጅምር ከግራም ከቀኝም እየቀየሱ አፍህን ያሲዙሀል:: አሁን አሁንማ እዛ ሰፈር አንዳንድ ማዘሮችም ሲቀይሱ መስማት የተለመደ ነገር ነው::

አንዷ የሞቢል ልጅ ታክሲ ውስጥ ስታዛጋ አይቶ አንዱ ተሳፋሪ ለጠበሳ ቡና ነው ሲላት .... ገበያ ነዋ ምትለው ብላ ተሳፋሪው ላይ አስቃበታለች::

አንዴ ደሞ ከዚሁ ሰፈር ልጅ(ሌላ ጊዜ ጭምት የሆነ ) ጋር አብረን ጠጥተን መስከሬ እንዳይታወቅ ቀስ እያልኩ ርምጃዬን እየጠበቅኩኝ ስራመድ አይቶ:: ፍሬንድ በሬንጅ ላይ ነው እንዴ ምትሄጂው ያለኝን ሳስታውሰው ሁሌም ፈገግ ያደርገኛል::
አቦ እንቀጣጥል እንጂ!!!
sarandem
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 674
Joined: Tue Jul 11, 2006 8:59 am
Location: Nomad Cafe

Postby HotMama » Tue Jul 24, 2007 12:48 am

እንዴት ሰንብታቹሀል...............ጠፋሁ አይደል

ሳረንደም..... አይ ስም አመራረጥ የመጨረሻ ነው ባክህ በጉራጊኛ ደስ አለን ማለት ነው believe me i'm a first class Gurage. ኢሳያስ ስትል ምን እንዳስታወስከኝ ታውቃለህ
አንድ ጊዜ ኢሳያስ ወንድሜን ከርቀት አይቶት አላወቀውም ኖሯል ከዛ ትንሽ ቀረብ ሲል አወቀውና በጣም ስለወፈረበት "እንዴ አንተ ነክ እንዴ ብቻህን ግር ብለህ ምቴደው" ብሎ ያሳቀበት ትዝ ይለኛል

መጣሁ
HotMama
አዲስ
አዲስ
 
Posts: 30
Joined: Sat Jul 14, 2007 2:38 am

Postby AAETV » Tue Jul 24, 2007 3:58 am

በእናቱቹ እዚህ ስፈር በምንም የአውጣል ከእዚህ.
AAETV
አዲስ
አዲስ
 
Posts: 13
Joined: Thu Apr 01, 2004 5:14 pm

Postby sleepless girl » Tue Jul 24, 2007 4:07 am

AAETV wrote:በእናቱቹ እዚህ ስፈር በምንም የአውጣል ከእዚህ.


እኔ የምልህ .AAETV.......የጻፍከው ከላይ ወደታች.....ከታች ወደላ......ከግራ ወደ ቀኝ ባነበው ሊገባኝ አልቻለም.......እስኪ እንደገና በአማርኛ ጻፈውማ.. :wink: :wink:
Nothing is impossible!!
sleepless girl
ዋና ውሃ አጠጪ
ዋና ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1510
Joined: Sun Feb 19, 2006 3:56 am
Location: near u!

Postby HotMama » Tue Jul 24, 2007 4:42 am

Sleepppp እኔም እኮ ግራ ገባኝ አሁን አሁንማ በቃ ተጠራጠርኩት. በኤርትራዊኛ ይመስላል
HotMama
አዲስ
አዲስ
 
Posts: 30
Joined: Sat Jul 14, 2007 2:38 am

Postby ሰናም » Tue Jul 24, 2007 1:49 pm

ሰላም HotMama እስኪ የኔንም ስም በጉራግኛ ተርጉሚል :lol: :lol: :lol: በተረፈ እስኪ ኳስሜዳ ጨዋታዎች አምጡ መልካም ቀን ለሁላቹም
ሰናም
አዲስ
አዲስ
 
Posts: 17
Joined: Sat Sep 09, 2006 6:14 pm

Postby HotMama » Tue Jul 24, 2007 8:22 pm

ሰናም የኛው ነህ መሰለኝ ማለቴ ኢና ቃር ትመስር

ያንተ ስምማ ትርጉሙ ደረሰ ማለት ነው. ልክ አይደለሁም :?: ጉራጊኛ ማወቅ ከፈለክ "የጫሙት ሽካ" የሚባል መጽሀፍ አለ እሱን አንብብ እንዳልኩህ ከበድ ከበድ ያሉ ቃላቶች ካሉ ወደኔ ጎራ በል እተባበራለሁ. ምን አባቱ ፈረንጅኛ እምቢ ቢለኝ በዚ ልታወቅ እን[/b][/u]
HotMama
አዲስ
አዲስ
 
Posts: 30
Joined: Sat Jul 14, 2007 2:38 am

Postby ሰናም » Wed Jul 25, 2007 12:50 am

HotMama የተንቢ ብያለሁ ስሜን በትክክል ነው የተረጎምሽው Thank you
ሰናም
አዲስ
አዲስ
 
Posts: 17
Joined: Sat Sep 09, 2006 6:14 pm

Postby AAETV » Sat Jul 28, 2007 9:58 pm

ስላም ስላም የኔ ቆንጆ ወ/ሮ Sleepless girl አሁንም እኔ አማርኛ ላይ ነው የልሽው አንቺ ልጅ?? በእናትሽ ካሴሜዳ ኤኔታ ጋ ትምሮ አንድ ሰው እንዲት አማርኛ የቻል>>>

ስሜ አሁን እኮ የ27 ቀበሌ ልጅ ብቻ ነው የማውራው እዚህ ቤት>>>>>
AAETV
አዲስ
አዲስ
 
Posts: 13
Joined: Thu Apr 01, 2004 5:14 pm

Postby ጦምኔው » Sat Jul 28, 2007 10:32 pm

ሠላም የሰፈር ልጆች:: አማን ተኩም ብለናል:: ኩሉ አማን ኩሉ ተማም ነው?...........እዚህ እኛጋ ስታይል በስታይል ነው አልኩህ........ምነው ጠፋፋችሁሳ? አቦ በጎይታ እንጨዋወታ.........

ሀት ማማ በላለዴ ይምጣ ኧዲጨ ብለናል.........ባገረዲ ባየ ቋንቋ............ :lol: ........ከባነንን አንገደድም አይደል :?: :lol: ........አቦ ጭውቴውን አመጫጪዋ.........

ስማ AA ETV .........ሰላም ነው? የኔታ ጋር የተማርከው አሁን ካረጁ በኍላ ነው እንዴ?.......ቅቅቅቅ..........ስልህ አማርኛህ ትንሽ ከበድ ይላል............አብሽር ጀለሴ ለጭውቴ ነው.........እስኪ የኔታን ሰላም በይልኝ: ሳይሽ ሳይሽ ግን የማርፍሽ ይመስለኛል::........ይመችሽ አንድ ቀን የሆድ የሆዳችንን እናወራ ይሆናል.............ሆት ማማ ከፈቀደች :lol: ..........

ሰናም ወዘላ ፈያ?....እሚደ ባቢደ ፈያ?.............አመጣጣሁት .......ቅቅቅቅ..........ይመቸኝ አቦ:: ጥፍቶ በሰላም ነው? ቀደዳሽ ተመችቶኝ ነበር አነካክተሽን እልሞ አልሽ እንጂ አቦ የሞቢሉን ዱቅ አርጊዋ,.........ላንቺም ቅጂ ለኔም አምጪ አለ ታይገር :lol:

የካቲት 23 ትምሮ ቤት በር ላይ ሎሚ በልጅነቱ ያልበላ አለ አሁን?.......የ 5 ሳንቲም አስራ ሰባት ሎሚ ገዝተን በየ ክፍለ ጊዜው ሶስት ሶስት ሎሚ ከትምሮ ጋር አወራርደን ነበር ለዚህ የበቃነው........ቅቅቅቅ..........መክሳት ይነሰን?........ሎሚ አይስ ክሬማችን ነበር የዛሬን አያድርገው :lol:

እዚያ ትምሮ ቤቱ በር ላይ አጥሩን ጥግ ይዘው ሎሚ: ስኳር ድንች :ድንሽ: ቆሎ: ዳቦ ቆሎ: አጋም: አካት ( የድንጋይ ዳቦ ዘመን ተመልሶ የመጣበት አጋጣሚ ነበር :lol: ).......ኧረ ስንቱ ተበላ:: አሁን ያ ሁሉ ትዝ ይለኛል:: ሰዎቹ ራሳቸው ትዝ ይሉኛል:: አሁንም ዘመን ተቆጥሮ ያልተለወጡ ሰዎች አሉ:: እኛ በሎሚ መዝናናት ብናቆምም እነሱ ግን እንጀራቸው እዚያችው የካቲት 23 ትምሮ ቤት በር ላይ የተመሰረተ ነው:; ............እስኪ ያላችሁን አጋጣሚ አስታውሱን:;

ሰናም አንድ ጊዜ ጀላቲ ከአልጋነሽ ቤት (29 ቀበሌ ኳስ ሜዳው ጋር) ገዝቼ ስሄድ የመነጨከኝ አንተ ሳትሆን አትቀርም:; አንድ ቀን አስከፍልሀለሁ.......... :lol:

ይመቻችሁ ጥቂት ትዝታዎችን ይዤ ደሞ ብቅ እላለሁ.........ይመቸን::
ጦምኔው
ዋና ውሃ አጠጪ
ዋና ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1529
Joined: Sun Jan 14, 2007 10:40 pm
Location: Right here

Postby sarandem » Sun Jul 29, 2007 7:53 am

ኳስ ሜዳዎች እንዴት ናቹ ባባጃሌው::

ምንድን ነው ባባጃሌው :?: የሚል አንባቢ መቼም አይጠፋም:: :lol:

ኳስ ሜዳዎች በጣም የቆየ ቃል *** ስትጠቀሙ ምንድን ነው*** ይላሉ:: አናንተ ደሞ *** ምን እንደሆነ ልታስረዱ ስትሞክሩ የባሰ ይደከምባችኃል::

ጦምኔው ያራዳ ልጅ ! የካቲት 23 የመቼ ባች ነሽ ? የካቲት 23 ትምሮ ቤት ባንቺ ጊዜ ሌሚ የ 5 ሳንቲም 17 ከነበረ እውነትም የድንጋይ ዳቦ ዘመን ተመልሶ የመጣበት ዘመን ላይ ነበርሽ:: እኔ ካንቺ ምለየው ሎሚው ላይ ሜታ ከረሜላ እና ሥኳር እጠቀም ስለነበረ ብቻ ነው:: ደሞ ከረሳሻቸው ነገሮች ፓስቲ: ሰሊጥ እና እምቦቲቶ ይጠቀሳሉ:: ለእስክሪብቶ እና ለደብተር እያልን ከአባት : ከእናት እንዲሁም ከወንድም ሸውደን እየተቀበልን ምንበላውን እንዴት ይረሳል?----ተረሳሽ ወይ ሚለውን ዘፈን ተመርጦላችኃል:: ግን እኮ እስክሪብቶ እና ለደብተር በየሳምንቱ ነበር ሚያልቅብን: :wink:

HotMama እንዴት ነሽ ገዳዎ?
ስንትና ስንት የኢሳያስ ፉገራዎች ጨመር ጨመር እንደማረግ ስም ስትተረጉሚ ተገኘሽ:: ለማንኛውም ....ዳይ... ፑሽ አፕ 10 ጊዜ ውረጂ :wink: እስክስታም ቢሆን::

ለመሆኑ ቀበሪቾን አታውቁትም? ቀበሪቾ ድንኳን ሰበራ የተካነበት ሥራው ነበር:: ድንኳን ሰበራ ከመውደዱ የተነሳ ከእንቅልፉ ሲነሳ የመጀርያ ሥራው ጣራ ላይ ሆኖ የት የት ድንኳን እንደተጣለ ማረጋገጥ ነበር ለቀጣዩ ስራ:: በዚህ ተግባሩ ሚያውቀው ኢሳያስ አንድ ቀን ሌሊት ላይ ከቀበሪቾ ጋር ሰፈር ላይ ይገናኛሉ::

ቀበሪቾ ሆዬ ለኢሳያስ እንዲህ ይለዋል << ምነው ለማኝ ሳያራ በጠዋት ተነሳህ :?: ኢሳያስ ፈጠን ብሎ << እስካሁን አላራህም እንዴ ? ብሎ መልሶለታል::

AAETV የኔታ ስትል ምን ትዝ አለኝ መሰለህ ኳስ ሜዳው ፊት ለፊት ችኳንታ (የአድዬ ወንድም) የት ጠፋ? አሁን የት ነው ያለው? እስቲ ቀጣጥሉ
sarandem
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 674
Joined: Tue Jul 11, 2006 8:59 am
Location: Nomad Cafe

Postby HotMama » Sun Jul 29, 2007 6:01 pm

እንዴት ናችሁ...........አይገባም.........በግዚያር በግዚያር አይገባም ስል

ጦምኔው የተንቢ የተንቢ አማን ነሽ ውይ የመጬ ነው ጨዋታህ እኔ እንኩአ የቀስተዳመና ተማሪ ነበርኩ ግን የ 5 ሳንቲም 17 ሎሚ ነገር አጃኢብ ነው የሆነብኝ. ጦምዬ ባለ ላስቲኩን ጀላቲ የደረስክበት አይመስለኝም. አንድ አማን አባኮ የሚባሉ ሽማግሌ ነበሩ ጀላቲ እየዞሩ የሚሸጡ. የዘፈናቸው ግጥም
አማን ቤቢ አማን ጽጌሬዳ እ እ እ እ.......... ብለው ይሸከሽኩት

Sarendem ያንቺ ዘመን ሰው ሳልሆን አልቀርም (የ ሎሚ በ ደስታ ከረሜላ) ዘመን ማለቴ ነው. ጨዋታህ በጣም ይመቻል. ግን ምን አደረኩህ 10 ፑሽ አፕ የምትፈርድብኝ በየትኛው ወገቤ እችለዋለሁ ብለህ ነው. እመጫት ስለሆንኩ ይቀየርልኝ. በቃ ሰሞኑን የ ኢሳያስ ባች የሆነ ብራዘሬ ከች ስለሚል ጆክ በጆክ ነው የማደርግክ. ግን ኢሳያስ አሜሪካን እንደሆነ ታውቃለህ?

ስለያቹ በምባ
HotMama
አዲስ
አዲስ
 
Posts: 30
Joined: Sat Jul 14, 2007 2:38 am

Postby ጦምኔው » Mon Jul 30, 2007 5:30 pm

ሠላም የሰፈር ልጆች:: እንዴት ነው ***ባባጃሌው***........ቅቅቅቅቅ..........ከኩርጄ:;

የቀበርቾ ነገር አደከምከኝ ብሮ.....ቅቅቅ.......ከምር:; .......ጣራ ላይ ወጥቶ የት የት ሰፈር ድንኳን እንዳለ ማየት ነው የጠዋት ስራው?....ቅቅቅቅ............

ችኳንታ..........አድዬ ራሱ እሱን ለመተካት በሂደት ላይ ያለ ነው የሚመስለው....ቅቅቅ............የት ገባ ግን እሱ?........ሞተ ሲሉ ሰማሁ :?: ....

እስኪ ቀጣጥሉበት.........የሞቢል; ልጅ ለመቀጣጠል ማን ብሎት?.. :lol:......

የካቲት 23 ትምሮ ቤት 1988(ዓ.ም. በኢትዮጵያ ነው ታድያ) ባች ነኝ.............አንተስ ሳራንደም?........ሎሚ የ አምስት ሳንቲም 17 የነበረው እኮ የሚሸጡት የ 27 ቀበሌ ሴትዮ ናቸው.....ደሞ ሁሌማ 17 አይደለም አንዳንዴም 15 ብሎም 10 ሊሆን ይችላል እንደ ነዳጁ ዋጋ ነው.................አሁን ነፍሳቸውን ይማረውና ሁሌም ሳያቸው ያሳዝኑኝ ነበር:; ሌሎችም ሴቶች ነበሩ.........የከረሜላው ነገር ይገርማል አይደል?...ቅቅቅ...........መቼም ጠጠር ከረሜላ ወይም ደሞ ናህና ከረሜላ ነው እንጂ ደስታ ከረሜላማ የሀብታም ልጆች.........ስልህ የቀስቴ ተማሪዎች ናቸው አክሰሱ የነበራቸው........ቅቅቅ.............

አንድ ትዝ የሚሉኝ ሰው ደሞ 27 ቀበሌ ያሉት ናቸው.........ወይዘሮ ሙሉጌታን አታርፏቸውም?........ወንድም ሴትም ናቸው አሉ.........እኔ ምን አውቄ ሲሉ ሰምቼ ነው:: ቤታቸው ከዮናስ ሱቅ ገባ ብሎ ነው:: ወደ ምህረት ክሊኒክ በሚወስደው መንገድ:: ይሸምናሉ: ወጌሻ ናቸው......የኳስ ሜዳ ልጆች ሲሰበሩ የሚጠግኗቸው እርሳቸው ናቸው::.............

አንድ ጊዜ ዕቁብ ሰበሰቡና የሰዉን ብር በሉት:: ግራ የገባቸው የሰፈሩ ዕቁብተኞች ተሰበሰቡና ምን እንዳሏቸው ታውቃላችሁ?

ወይዘሮ ሙሉነሽ አቶ ሙሉጌታ
በፈጠረሽ አምላክ በፈጠረህ ጌታ
ብራችንን መልሽ ብራችንን አምጣ:;.............. :lol: :lol: :lol:

መጣሁ.......
ጦምኔው
ዋና ውሃ አጠጪ
ዋና ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1529
Joined: Sun Jan 14, 2007 10:40 pm
Location: Right here

Postby AAETV » Wed Aug 01, 2007 5:53 am

ስላም ስላም የስፈር ልጆች እንዲት ናቸዉ?? ሱሙ ለእኔ ኢሳያስ አይደልም ፋገሬ እዚህ ስፈር የህይሌ ካሴ ወንደም ጌሬ ነው>>> ግን የእሱ ፉገራ ለሌላ ስፈር ልጅ አይግባም ምክንያቱም የእዛን ስፈር አፍ ስልማይግባቸው
AAETV
አዲስ
አዲስ
 
Posts: 13
Joined: Thu Apr 01, 2004 5:14 pm

Postby sarandem » Wed Aug 01, 2007 9:25 am

ኬፍ ብለናል:: እዚህ ሰፈር የጠፋም ሰው አይፈለግ? ለነገሩ መኖርህን የሚያውቅ የለም እንደምትሉኝ መች አጣሁት::

ሰሞኑን ሰነድ ስለቃቅም ነው የቆየሁት: እንደጉድ የያንዳንድሽ ሰነድ ተገኝቷል ተጣርቶ ለህዝብ እይታ ይቀርባል::


ሆትማማ እንዴት ነው ፑሽ አፕ አደከመሽ እንዴ? አገኘሁ ብለሽ ይሄን ገንፎ ልፈሽ ልፈሽ የገንፎ ተራራ ሳታክዪ ደረስኩልሽ:: ስቴፓሽ እንደድሮ ተማመን እንዳልሆነ ገመቹ ነገረኝ:: ልጅሽ ግን ባልሽን ቁጭ... ለጊዜው አንድ ለዜሮ እየተመራሽ ነው:: እናም 10 ፑሽ አፕ ሲያንስ ነው::አትነጫነጪ:: እንደውም ሲት አፕ ከምግብ በፊት እና በኃላ 10 ብትጨምሪበት እሪፍ ነው::

ስማ ጦምኔው ስለ 23 እና ስለ ወይዘሮ ሙሉነሽ (አቶ ሙሉጌታ) ያስጫወትካት በጣሙን ይደላል ነው ሚባለው:: ሌላም ጨመር ጨመርመር አርግበት::
እኝህ ሰውዬ/ሴት ሲሄዱ ብቅ ጥልቅ ሚሉት ናቸው እንዴ?

ለዛሬም እኔም እንዳንቺ 23 ልውረድ:: :D

ከአለታት አንድ ቀን ( ይህ አጠቃቀም አሁንም አልቀረም እንዴ? :o ) ሞባይሌ አንዴ አንጫራ: ጸጥ አለች:: ያው እንደተለመደው ሚስኪን ኮል ያረገው ደረሰ ነበር :: ደረሰ ሚስኪን ኮል ማድረግ የሀብታም በር አንኳኩቶ ሽል እንደማለት ይቆጠራል የሚል አባባል አለችው:: መልሼ ስደውልለት እሱና ሌሎች ፍሬንዶች ብርሀኑ ሥጋ ቤት እንደሆኑና ቶሎ እንድመጣ ለመንገር ነበር የደወለልልኝ::

ፒያሳ ላይ ታክሲ ውስጥ ስሳፈር አብቶቢስ ተራ ተሻግሬ እንደምወርድ ተስማምቼ ነበር የገባሁት:: ነገር ግን አምባሰል ሙዚቃ ቤት ስንደርስ ወያላው ፍሬንድ ተባበሪን: እዚህ ጋር ልንሸበለል ነው አለኝ:: :evil: እየተነጫነጭኩ አዲስ ከተማ ት/ቤት ሳልደርስ ወረዱኩኝ::

የአብቶቢስ ተራን ግርግር እና ወከባ ከዜድ ሙዚቃ ቤት ሙዚቃ ጋር እያጣጣምኩኝ አስፓልቱን ተሻግሬ ወደ ቀጠሮ ቦታ አመራሁ::

ወደ ሥጋ ቤቶች መደዳ ጋር ስደርስ የት ነበር ያሉኝ? ብዬ ሥጋ ቤቶቹን ብዛት መቁጠር ያዝኩኝ:: ብዙም ሳለፋ ጨርጨርን አልፌ: ሀንገር ጥለፎ ሳይጥለኝ ብርሀኑ ቤት ከሰት አልኩኝ:: ብሬ ልክ እንደ ዶክተር ጸዳ ያለ ልብስ ለብሷል:: ፊቱ ደሞ ያበራል ጥይቱ ነው ሚባለው:: ብሬ ከሥጋ ቤቱ የ100 ሻማ አሞፖል ውብት ሚቸረው ይመስላል:: ብሬን ሰላም ብዬ :: ወደ ውስጥ ዘው ዘው አልኩኝ:: ዛሬ የደሞዝ ቀን ስለሆነ ይሆን ወይስ በሌላ አላቅም ማንም የሰፈር ሰው አልቀረም::

ፒፕሉን ቃኝት ቃኝት አደረኩት:: በሩ ላይ የጋራዥ ሰራተኛ የሆኑ 3 ልጆች አሉ:: ከእነርሱ ውስጥ አንዱ ጋር አብረን ከቴ ተምረናል:: ከፊት ለፊት ደሞ እነ ውቃው 4 ኪሎ ሥጋ ለሁለት ጥብስና ጥሬውን በአንቦ ውሀ እና በወይን እያደረጉ ይወቁታል::

ከእነርሱ መደዳ ደሞ እነ አቤል:ሀምሳለ: ....ዝልዝል አዘው..እየወረዱበት ነው:: አይ አቤል እንዴት ሚያምር እና አስቂኝ ልጅ ነበር:: ትምሮ ላይም ቢሆን ጎበዝ ልጅ ነበር:: አሁን ጋራዥ ሰራተኛ መሆኑ ሁሌም ግርም ይለኛል:: ከፊት ለፊት ደሞ ሰናም(ደረሰ ወጉ):AAETV(በቅጽል ስሙ ጋሜ) : ጦምኔው እና ሆትማማ ተስይመዋል:: መቀመጫ ቦታ ከመጥፋቱ የተነሳ:: የተመጋቢ ቤንቾች ነበሩ እነ ቦቸራ : እንቅልፍ የለሽ እና ሽሜ(ሽመክት) ቦታ አጥተው ጥግ ላይ ቆመዋል:: የእነርሱ ሥራ ስትጎርስ ያንተን ጉርሻ LIVE መከታተል ነው:: እነርሱን አልፌ እነ አቤልን በስሱ ሰላም ብዬ ከእነ ሀትማማ : ጦምኔው ጋር እና ደረሰ ጋር ተቀመጥኩኝ::

8 ሜትር አስመትረን ጥሬ እና ጥብስ ካስደረግን በሆአላ አንቦ ውሀ እና በአዋዜ አወራረድነው::

ያው እንደተለመደው በጳውሎስ ማክያቶ ምሳችንን ላይ ቸለስንበት:: ማክያቶው አሪፍ ስለነበረ ድጌ አዘዝን::

ከጳውሎስ ከወጣን በኃላ በፖሊስ ጣብያው አድርገን ስናልፍ ፖሉሶቹ ጦምኔውን በሀይለኛው ሰላም አሉት:: ያው ጦምኔው እኮ የዚህ ቤት የዘወትር ደንበኛ ናት:: ትንሽ ፑል ተጫወትንና በጦምኔው ጉትጎታ ወደ ሀሮኒ አዘገምን:: ሀሮኒ ብዙ ሰአት ተቀመጥን ነው ሚባለው አላፊ አግዳሚውን ስንለክፍ..ስናወጣ ስናወርድ...ኢብሮ አስሬ እየመጣ ረዝቅ ሲለን.... ጸሀይ እብዷ ስትጮህብንን...ሙዳችን ሲከነት..... :evil: ከዛ ተነስተን ወደ ፓስተር መንገድ ጉዞ ሆነ::

መንገድ ላይ እየሄድን እያለ ዮሴፍ መጥቶ ተቀላቀለን:: ዮሴፍ ስለ ኳስሜዳ ልጆች በሙሉ ሰነድ አለው:: ማን እና ማን የት እንደሚቅም...ማን ማንን እንዳወጣ....ማን ጨዋ( :?: ) እንደሆነ እስከተወለደበት ቀን ድረሥ መረጃ በሽ ነው:: ኢንፎ ለመጥለፍ ለዮሴፍ ጫት መግዛት በቂው ነው::

እኔም ይህንን አውቄ ልክ መስጊድ ጋር ስንደርስ ፌዴራል ጫት ገዛሁለትና ስለ ጦምኔው እስቲ ንገረኝ አልኩት::
ሚስስተር ትሪን ነው አለኝ? አዎ ፈጠን ብዬ::
ጦምኔው ሚስተር ትሪ በመባል ይታወቃል:: ጦምኔው ሁሌም ስለ ምግብ አውርቶ አይጠግብም ::

ጦምኔው የሚለውን ስም የወጣላት ጣእም ምትባል የሀሮኒ ኬክ ቤት ልጅ ወዶ: እንደሆነና መጀመርያ ላይ ከዚች ልጅ ጋር ሀይለኛ ፎንቃ እንደጠገረረው ሰው ሚያውቅበት አይመስለውም ነበር:: መጨረሻ ላይ በሀይለኛ ምላሱ ካሰመጣት በኃላ አንዱ ልጅ: ከምኔው ጣእምን ገቢ አደረጋት ብሎ ጦምኔው እንዳለው ነገረኝ:: የዛሬን አይርገው እና ቢያንስ 3 ጊዜ ሳያያት ቢውል እንደሚያብድ ነገረኝ:: ሌላው ዘይገርም ነገር እዛ ቤት መሄድ ከማብዛቱ የተነሳ "የጦምኔው" ሚባል ዘፈን አለው::

ብዙ ቀጣጠልኩኝ ሌላ ጊዜ ብመለስ ይሻላል::
ቸር ሰንብቱልኝ
sarandem
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 674
Joined: Tue Jul 11, 2006 8:59 am
Location: Nomad Cafe

PreviousNext

Return to Warka Intimate - ዋርካ ፍቅር

Who is online

Users browsing this forum: No registered users and 6 guests