እስቲ የኳስሜዳ ልጆች አንድ በሉ

The Love Forum (love, relationship) (የኔ ቆንጆ እንተዋወቅ :-)

Postby ጦምኔው » Sat Sep 01, 2007 9:29 pm

በለው የጠቅላይ ቢሮ አሪፎች ከች አሉ:: አማን ነው ? አሁን አንተ ራስህን ከኳስ ሜዳ ማራቅህ ነው? ሚኪያልን ትገርማለህ:: ስማ ደሞ አታስቁም ምናምን ያልከውን.....እያረፋችሁ አይደል እንዴ በፋሚሊ የምጽቁት በኛ ፉገራ.......ቅቅ......አሁን በኛ ሰፈር ጭውቴ ያልሳቀ አለ?......ይንመጭ አቦ

ያ ድፍጥጡ ልጅ ስሙ ማን ነበር......ነፍሱን ይማረውና ሞቷል ሲሉ ሰምቻለሁ.....ግን ለምን ፈለከው? ሙድ ለመያዣ ነው ወይስ ከምር ፈልገኸው ነው? ሶሪ መርዶ ካረዳውህ መቼም ከሞት የሚቀር የለምና ቻል ማረግ ነው::

ኧረ ነፍሴ እኛ ጭውቴ ነው እንጂ ሀርድ ምናምን አናርፍም.....ስልህ አካብዳለሁ ካልክ አለ አይደል........ይመ ህ ጀለሴ......


ሳራንደም እና ሰናም የት ገባችሁ ጀለሶች? ሀት እና AAETV አቦ ከች በሉና አጫውቱና:: ሚሊኒየም ምናምን........

ቺርስስስስስ
ጦምኔው
ዋና ውሃ አጠጪ
ዋና ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1529
Joined: Sun Jan 14, 2007 10:40 pm
Location: Right here

Postby sarandem » Sun Sep 02, 2007 6:22 am

ሀይ ፌሬንዶች እንዴት ናቹ::
ጦምኔው ለሚንየም 500 አበድረኝ ያልኩህን እዛ ቤት ወስደህ መላጫ ታደርገኛለህ :twisted: ቆይ ላግኝህ
አቦ ይሄ ሚልንየም እኮ ኑሮ አስወደደብን ነው ምልህ ሰው ደሞ ተጨካክኗል ነው ምልህ:: እሁን እኔ ለምሳሌ ማዘር ሰሞኑን ስትዝትብኝ ነበር:: ምን እንዳለች ታውቃለህ :?: በፈጣጤ አይኖርም ከዚህ ቤት ወይ እኔ ወይ አንተ መውጣት አለብን ያው በዲፕሎማሲ እኔን ከቤት ለማስወጣት ነው:: ይገርምሀል እንደውም የእርሷ ይሻላል :: እኔ ወደ ኢንተርኔት ካፌ ስመጣ ፋዘር ጠመንጃ እየወለወለ ነበር::
ሰው ደሞ በጣም ይሞታል ነው ሚባለው:: እንደ ድሮ ድንኳን በየቦታው መትከል ቀርቷል:: ከሚልንየም በኃላ ድንኳኖች ሽኩኔት እየተገጠመላቸው ሰው በሚሞትበት ቦታ ማንፏቀቅ ነው:: እዛው ለዛው ከሆነ ፎቶ ብቻ ነው ሚቀያየረው::
sarandem
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 674
Joined: Tue Jul 11, 2006 8:59 am
Location: Nomad Cafe

Postby ጦምኔው » Sun Sep 30, 2007 4:28 pm

:lol: :lol: ቅቅቅቅቅ.......ስማ እንጂ ረስቼው ሳልጠይቅህ....ቅቅ.....የዲፕሎማሲው ነገር የት ደረሰ? ጠረዙሽ እንዴ ከቤት?.....ቅቅቅ......የፋዘርህማ አነፈረኝ ነው የምልህ......ቅቅ.......ጠመንጃ ምናምን ያልከው.........ኑሮ ባክህ ዘንድሮ ሀርድ ሆኗል:: ፋዘርም ባለፈው እንዲሁ ደውዬለት ነበር እና ምን እንዳለኝ ታውቃለህ?.........ምንም አላለኝም:;

ሳራንደም ያቺን $500 ነገርማ አታንሳት......ቅቅቅቅ....ሚኪያልን ማቱሳላ አስመሰልከኝ እኮ:: ለ3000 እከፍልሀለሁ ትለኛለህ? ኧረ ትገርማለህ ከምር:;

ስማ ደሞ ስፈር ደውለህ ታውቃለህ? እንዴት ነው ፒፕሉ? እስኪ ሰሞኑን ጭርር ላድርጋ ጭውቴዎች ሰባስቤ ከች እላሉ:: ስላህ ጠፋፋችሁ እኮ::

ሀያ መስቀላዮ!!

ፈያ እደር::
ጦምኔው
ዋና ውሃ አጠጪ
ዋና ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1529
Joined: Sun Jan 14, 2007 10:40 pm
Location: Right here

Postby ቶድ » Fri Jan 04, 2008 4:31 pm

አቦ ወደኳስ ሜዳ ብቅ ስል ያ የማውቀው የአራዳ ልጆች ጫወታ ያለ መስሎኝ ነበረ:: ምነው እነጦምኔው እኔ ላጫውታችሁ እንዴ??? ያ ሰፈር እኮ የጫወታ ፕራይስ ሜከር ነው:: ብዙ የከተማው ፉገራ መፍለቂያ የሆነበት ሰፈር እኮ ነው!!!!!!!!!!!!! ደግሞም መርኬና ኳስ ሜዳ ኩታ ገጠም አይደሉም እንዴ?????????? ካልሆነ እኔ የማውቀውን እዘረዝርላችኌለሁ:: እስኪ የነኃይሌ ካሴን, የላ(ነፍስ ይማር), ጌራ, ጃምቦ, አሚቶ, ቶፊክ, ዑመር ቂጦ, ጀማል......እረ ስንቱን ልጥቀሰው???????? አቦ ጀባ በሉን እባካችሁ!!!!!!!!!!!!!
ቶድ
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 100
Joined: Fri May 04, 2007 5:33 pm

Postby ሰናም » Sat Jan 05, 2008 3:17 am

ሰላም ውድ የኳስ-ሜዳ ልጆች አማን ናቹ :lol: :lol: :lol: HAPPY NEW YEAR 2008. ዛሬ (ዋርካ) ስገባ ቶድ የረሳትን ስሞች አስታወሰኝ.ቅቅቅ ሌሎቻቹስ ምነው ጠፋቹ እስኪ ብቅ በሉና እንቅደድ :lol: :lol: :lol:
ሰናም
አዲስ
አዲስ
 
Posts: 17
Joined: Sat Sep 09, 2006 6:14 pm

Postby ቶድ » Sat Jan 05, 2008 2:47 pm

የኮልፌ ት/ቤት ዘበኛ የነበረ አንድ ሰው መሳለሚያ አካባቢ ስጋ ቤት ይከፍትና ድርጅቱን ለማስተዋወቅ ስፖርተኞችን እያፈላለገ እያለ...... በአጋጣሚ ኃይሌ ካሴንና ጃምቦን ያገኛቸዋል:: ከዛም እዛ ጋር ስጋ ቤት ስለከፈትኩ እባካችሁ እንዳትቀሩ ብሎ ይላቸዋል:: ከዛም ጃምቦ ፈጠን በማለት "በቃ ሽንጥ ቋንጣ ሲሆን ታርፈዋለህ" አለው:: እንግዲህ አስቡት.... ሽንጥ በጣም የሚፈለግና የሚበላ ስጋ ገዢ በማጣት ደርቆ ቋንጣ ሲሆን አስቡት::
ቶድ
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 100
Joined: Fri May 04, 2007 5:33 pm

Postby sarandem » Mon Jan 14, 2008 4:34 am

ቶድ wrote:አቦ ወደኳስ ሜዳ ብቅ ስል ያ የማውቀው የአራዳ ልጆች ጫወታ ያለ መስሎኝ ነበረ:: ምነው እነጦምኔው እኔ ላጫውታችሁ እንዴ??? ያ ሰፈር እኮ የጫወታ ፕራይስ ሜከር ነው:: ብዙ የከተማው ፉገራ መፍለቂያ የሆነበት ሰፈር እኮ ነው!!!!!!!!!!!!! ደግሞም መርኬና ኳስ ሜዳ ኩታ ገጠም አይደሉም እንዴ?????????? ካልሆነ እኔ የማውቀውን እዘረዝርላችኌለሁ:: እስኪ የነኃይሌ ካሴን, የላ(ነፍስ ይማር), ጌራ, ጃምቦ, አሚቶ, ቶፊክ, ዑመር ቂጦ, ጀማል......እረ ስንቱን ልጥቀሰው???????? አቦ ጀባ በሉን እባካችሁ!!!!!!!!!!!!!


ቶድ ዘ ሰፈረ አዲስ ከቴ ፐሮፌሽናል ልናረግሽ አስበናል:: ለማንኛውም ሥንቅ እና ትጥቅ አሟልተሽ አሸዋ ሜዳ ክስቶ በይ:: ለአንድ አመት ጆከር ብትሆኚ ምን ይልሻል? ወይስ በክንፍ ተመላላሽ እናርግሽ? ለማንኛውም አንቺ ትሬኒንግ ጀምሪ እኛ ደሞ እንቀጣጥላለን::
ችርስ
sarandem
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 674
Joined: Tue Jul 11, 2006 8:59 am
Location: Nomad Cafe

Postby ቶድ » Tue Jan 15, 2008 3:20 am

ወንደሜ ሳራንደም !!!!!!!!! ለግብዣህ በጣም ነው የማመሰግነው:: ነገር ግን በፕሮፌሽናልነት ከመርካቶ (ፍቅርና ብር ካለበት ቦታ) ተነስቼ አልሸጥም.... ነገር ግን በተውሶ መምጣት እችላለሁ:: ምክንያቱም ኳስ ሜዳ መሳለሚያና አካባቢው እጅግ በጣም የምወደው ሰፈርና እጅግ በጣም የምናፍቃቸው የውድ ጓደኞቼ ሰፈር ነው:: ነገር ግን........ እትብቴ የተቀበረበት ሰፈሬን የመርካቶን ባጄን እንደያዝኩት ወደኳስ ሜዳ ብጋበዝ እጅግ በጣም በኩራትና በመደሰት ነው:: የማይደሰትስ ማን ነው???? ወደኳስ ሜዳኮ... አሜሪካዎች እንኳ በዲቪ ነው የሚገቡት!! ያራዶች ሰፈር, የፍቅር ሰፈር, የመከባበር ሰፈር, የመረዳዳት ሰፈር, የቆንጆዎች ሰፈርና የሚመቹ ሰዎች መኖሪያ ሰፈር...... ሌላም ሌላም ብል እውነቴን ነው:: ለማንኛውም እስኪ ስለ ፉአድ (የቢራ ኳስ ተጫዋች ስለነበረው) አንድ ፉገራ.................:: ቢራ "Á" ከሰፈር ልጆች ጋር ለእግር ኳስ ምርጫ ሄደው በነበረበት ሰዓት ሌሎቹ ጓደኞቾ በአጥቂነት በተከላካይነትና በበረኛነት ተመረጡ:: እሱም ደግሞ በተመላላሽነት ተመርጠሀል ሲባል... ደሞዜ ስንት ነው አለ:: $1200 ነው አሉት:: የሌሎቹስ ብሎ ጠየቀ.. የሁሉም አንድ ነው...... ያው $1200 ነው የሚከፈለው ሲባል...... ፉዋድም በፍጥነት ..... ኖ ኖ አያዋጣኝም አለ:: ምነው ይሉታል?? እኔ ከሜዳ ጫፍ እስከ ሜዳ ጫፍ እየሮጥኩ.... ሌሎቹ ግን የተወሰነ ቦታ ቆመው እየዋሉ...... በፍጹም አያዋጣኝም አለ ይባላል::
ቶድ
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 100
Joined: Fri May 04, 2007 5:33 pm

Postby ጦምኔው » Sat Apr 19, 2008 5:51 pm

ቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅ..............ቶድ........ቅቅቅ.........ፉአድ....ቅቅቅቅ...አያዋጣኝም.......ከኮርና እስከኮርና.....ስልህ.....አነፈርከኝ ሜን

ሰላም ነው አባ? እንዴት ነው?....ሳራንደምማ እልሞ ምናምን አለ.....ሀት ማማ.....ሰልማ....እረ ሁልሽም.....በሰላም ነው?......ጭውቴ አለቀ እንዴ?........ኳስ መዳዎች ከች በሉ እንጂ........

እስኪ ጭውቴ ፈላልጌ ከች እላለሁ......

ፒስስስስስስስስስስ
ጦምኔው
ዋና ውሃ አጠጪ
ዋና ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1529
Joined: Sun Jan 14, 2007 10:40 pm
Location: Right here

Re: እስቲ የኳስሜዳ ልጆች አንድ በሉ

Postby ጦምኔው » Thu May 03, 2018 11:50 pm

ይህ ቤትማ ከፊት ፔጅ ንቅንቅ ........
ጦምኔው
ዋና ውሃ አጠጪ
ዋና ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1529
Joined: Sun Jan 14, 2007 10:40 pm
Location: Right here

Previous

Return to Warka Intimate - ዋርካ ፍቅር

Who is online

Users browsing this forum: No registered users and 6 guests

cron