by sarandem » Wed Aug 01, 2007 9:25 am
ኬፍ ብለናል:: እዚህ ሰፈር የጠፋም ሰው አይፈለግ? ለነገሩ መኖርህን የሚያውቅ የለም እንደምትሉኝ መች አጣሁት::
ሰሞኑን ሰነድ ስለቃቅም ነው የቆየሁት: እንደጉድ የያንዳንድሽ ሰነድ ተገኝቷል ተጣርቶ ለህዝብ እይታ ይቀርባል::
ሆትማማ እንዴት ነው ፑሽ አፕ አደከመሽ እንዴ? አገኘሁ ብለሽ ይሄን ገንፎ ልፈሽ ልፈሽ የገንፎ ተራራ ሳታክዪ ደረስኩልሽ:: ስቴፓሽ እንደድሮ ተማመን እንዳልሆነ ገመቹ ነገረኝ:: ልጅሽ ግን ባልሽን ቁጭ... ለጊዜው አንድ ለዜሮ እየተመራሽ ነው:: እናም 10 ፑሽ አፕ ሲያንስ ነው::አትነጫነጪ:: እንደውም ሲት አፕ ከምግብ በፊት እና በኃላ 10 ብትጨምሪበት እሪፍ ነው::
ስማ ጦምኔው ስለ 23 እና ስለ ወይዘሮ ሙሉነሽ (አቶ ሙሉጌታ) ያስጫወትካት በጣሙን ይደላል ነው ሚባለው:: ሌላም ጨመር ጨመርመር አርግበት::
እኝህ ሰውዬ/ሴት ሲሄዱ ብቅ ጥልቅ ሚሉት ናቸው እንዴ?
ለዛሬም እኔም እንዳንቺ 23 ልውረድ:: :D
ከአለታት አንድ ቀን ( ይህ አጠቃቀም አሁንም አልቀረም እንዴ? :o ) ሞባይሌ አንዴ አንጫራ: ጸጥ አለች:: ያው እንደተለመደው ሚስኪን ኮል ያረገው ደረሰ ነበር :: ደረሰ ሚስኪን ኮል ማድረግ የሀብታም በር አንኳኩቶ ሽል እንደማለት ይቆጠራል የሚል አባባል አለችው:: መልሼ ስደውልለት እሱና ሌሎች ፍሬንዶች ብርሀኑ ሥጋ ቤት እንደሆኑና ቶሎ እንድመጣ ለመንገር ነበር የደወለልልኝ::
ፒያሳ ላይ ታክሲ ውስጥ ስሳፈር አብቶቢስ ተራ ተሻግሬ እንደምወርድ ተስማምቼ ነበር የገባሁት:: ነገር ግን አምባሰል ሙዚቃ ቤት ስንደርስ ወያላው ፍሬንድ ተባበሪን: እዚህ ጋር ልንሸበለል ነው አለኝ:: :evil: እየተነጫነጭኩ አዲስ ከተማ ት/ቤት ሳልደርስ ወረዱኩኝ::
የአብቶቢስ ተራን ግርግር እና ወከባ ከዜድ ሙዚቃ ቤት ሙዚቃ ጋር እያጣጣምኩኝ አስፓልቱን ተሻግሬ ወደ ቀጠሮ ቦታ አመራሁ::
ወደ ሥጋ ቤቶች መደዳ ጋር ስደርስ የት ነበር ያሉኝ? ብዬ ሥጋ ቤቶቹን ብዛት መቁጠር ያዝኩኝ:: ብዙም ሳለፋ ጨርጨርን አልፌ: ሀንገር ጥለፎ ሳይጥለኝ ብርሀኑ ቤት ከሰት አልኩኝ:: ብሬ ልክ እንደ ዶክተር ጸዳ ያለ ልብስ ለብሷል:: ፊቱ ደሞ ያበራል ጥይቱ ነው ሚባለው:: ብሬ ከሥጋ ቤቱ የ100 ሻማ አሞፖል ውብት ሚቸረው ይመስላል:: ብሬን ሰላም ብዬ :: ወደ ውስጥ ዘው ዘው አልኩኝ:: ዛሬ የደሞዝ ቀን ስለሆነ ይሆን ወይስ በሌላ አላቅም ማንም የሰፈር ሰው አልቀረም::
ፒፕሉን ቃኝት ቃኝት አደረኩት:: በሩ ላይ የጋራዥ ሰራተኛ የሆኑ 3 ልጆች አሉ:: ከእነርሱ ውስጥ አንዱ ጋር አብረን ከቴ ተምረናል:: ከፊት ለፊት ደሞ እነ ውቃው 4 ኪሎ ሥጋ ለሁለት ጥብስና ጥሬውን በአንቦ ውሀ እና በወይን እያደረጉ ይወቁታል::
ከእነርሱ መደዳ ደሞ እነ አቤል:ሀምሳለ: ....ዝልዝል አዘው..እየወረዱበት ነው:: አይ አቤል እንዴት ሚያምር እና አስቂኝ ልጅ ነበር:: ትምሮ ላይም ቢሆን ጎበዝ ልጅ ነበር:: አሁን ጋራዥ ሰራተኛ መሆኑ ሁሌም ግርም ይለኛል:: ከፊት ለፊት ደሞ ሰናም(ደረሰ ወጉ):AAETV(በቅጽል ስሙ ጋሜ) : ጦምኔው እና ሆትማማ ተስይመዋል:: መቀመጫ ቦታ ከመጥፋቱ የተነሳ:: የተመጋቢ ቤንቾች ነበሩ እነ ቦቸራ : እንቅልፍ የለሽ እና ሽሜ(ሽመክት) ቦታ አጥተው ጥግ ላይ ቆመዋል:: የእነርሱ ሥራ ስትጎርስ ያንተን ጉርሻ LIVE መከታተል ነው:: እነርሱን አልፌ እነ አቤልን በስሱ ሰላም ብዬ ከእነ ሀትማማ : ጦምኔው ጋር እና ደረሰ ጋር ተቀመጥኩኝ::
8 ሜትር አስመትረን ጥሬ እና ጥብስ ካስደረግን በሆአላ አንቦ ውሀ እና በአዋዜ አወራረድነው::
ያው እንደተለመደው በጳውሎስ ማክያቶ ምሳችንን ላይ ቸለስንበት:: ማክያቶው አሪፍ ስለነበረ ድጌ አዘዝን::
ከጳውሎስ ከወጣን በኃላ በፖሊስ ጣብያው አድርገን ስናልፍ ፖሉሶቹ ጦምኔውን በሀይለኛው ሰላም አሉት:: ያው ጦምኔው እኮ የዚህ ቤት የዘወትር ደንበኛ ናት:: ትንሽ ፑል ተጫወትንና በጦምኔው ጉትጎታ ወደ ሀሮኒ አዘገምን:: ሀሮኒ ብዙ ሰአት ተቀመጥን ነው ሚባለው አላፊ አግዳሚውን ስንለክፍ..ስናወጣ ስናወርድ...ኢብሮ አስሬ እየመጣ ረዝቅ ሲለን.... ጸሀይ እብዷ ስትጮህብንን...ሙዳችን ሲከነት..... :evil: ከዛ ተነስተን ወደ ፓስተር መንገድ ጉዞ ሆነ::
መንገድ ላይ እየሄድን እያለ ዮሴፍ መጥቶ ተቀላቀለን:: ዮሴፍ ስለ ኳስሜዳ ልጆች በሙሉ ሰነድ አለው:: ማን እና ማን የት እንደሚቅም...ማን ማንን እንዳወጣ....ማን ጨዋ( :?: ) እንደሆነ እስከተወለደበት ቀን ድረሥ መረጃ በሽ ነው:: ኢንፎ ለመጥለፍ ለዮሴፍ ጫት መግዛት በቂው ነው::
እኔም ይህንን አውቄ ልክ መስጊድ ጋር ስንደርስ ፌዴራል ጫት ገዛሁለትና ስለ ጦምኔው እስቲ ንገረኝ አልኩት::
ሚስስተር ትሪን ነው አለኝ? አዎ ፈጠን ብዬ::
ጦምኔው ሚስተር ትሪ በመባል ይታወቃል:: ጦምኔው ሁሌም ስለ ምግብ አውርቶ አይጠግብም ::
ጦምኔው የሚለውን ስም የወጣላት ጣእም ምትባል የሀሮኒ ኬክ ቤት ልጅ ወዶ: እንደሆነና መጀመርያ ላይ ከዚች ልጅ ጋር ሀይለኛ ፎንቃ እንደጠገረረው ሰው ሚያውቅበት አይመስለውም ነበር:: መጨረሻ ላይ በሀይለኛ ምላሱ ካሰመጣት በኃላ አንዱ ልጅ: ከምኔው ጣእምን ገቢ አደረጋት ብሎ ጦምኔው እንዳለው ነገረኝ:: የዛሬን አይርገው እና ቢያንስ 3 ጊዜ ሳያያት ቢውል እንደሚያብድ ነገረኝ:: ሌላው ዘይገርም ነገር እዛ ቤት መሄድ ከማብዛቱ የተነሳ "የጦምኔው" ሚባል ዘፈን አለው::
ብዙ ቀጣጠልኩኝ ሌላ ጊዜ ብመለስ ይሻላል::
ቸር ሰንብቱልኝ