የአጎቴ ልጅ አርግዛ ቁጭ

The Love Forum (love, relationship) (የኔ ቆንጆ እንተዋወቅ :-)

Postby የኮካታ » Thu Sep 20, 2007 7:25 pm

ችሎ ማደር እንድግዲህ የሆነው ሆኗልና መፍትሄው ምን ይሁን ነው ጥያቄህ::
እኔ እንዳለዉበት አካባቢ ከሆነ ያላችዉት ብዙ single mothers ስለሞሉ አንዷን አግኝቶ ማናገር ለልጅቷ ትልቅ የሞራል ድጋፍ ይሰጣታል ምክንያቱም በተመሳሳይ ችግር ዉሥጥ ስላለፉ!

አጎትህ ፈላጭ ቆራጭነታቸውን አገር ቤት አልተዉትም ማለት ነው! ልጅቷ ከዚ በዋላ ከአባቷ ጋር የድሮው አይነት ግንኙነት ሊኖራት አይችልም.....ልጁን ወለደችም አወለደችም.... ስለዚህ ይህ ዉሳኔ የሷና የእናቷ ነው... የአባቷን ቁጣና ኩርፍያ መርሳትና አንተም ገንዘብ ካለህ ለጊዜው ስራ እስክታገኝ ድረስ ቤት ተከራይላትና ትቀመጥ...አባት አንድ ቀን ልቡ ይራራና ልጄ ማለቱ አይቀርም

የደነቀኝ ነገር በ 27 አመት ከቤተሰብ ጋ መቆየቷና የናነተ ቤት የዉሻ ስም.....!!
Lucky being kokata!
የኮካታ
ጀማሪ ኮትኳች
ጀማሪ ኮትኳች
 
Posts: 74
Joined: Fri Sep 14, 2007 3:41 am
Location: somewhere beautiful

Postby ችሎ_ማደር » Thu Sep 20, 2007 7:59 pm

የኮካታ wrote:አጎትህ ፈላጭ ቆራጭነታቸውን አገር ቤት አልተዉትም ማለት ነው! ልጅቷ ከዚ በዋላ ከአባቷ ጋር የድሮው አይነት ግንኙነት ሊኖራት አይችልም.....ልጁን ወለደችም አወለደችም.... ስለዚህ ይህ ዉሳኔ የሷና የእናቷ ነው... የአባቷን ቁጣና ኩርፍያ መርሳትና አንተም ገንዘብ ካለህ ለጊዜው ስራ እስክታገኝ ድረስ ቤት ተከራይላትና ትቀመጥ...አባት አንድ ቀን ልቡ ይራራና ልጄ ማለቱ አይቀርም

አሁን ገና ጨዋታ መጣ:: አስቲ የት ላይ ነው መፍለጡ መቁረጡ:: ሐላፊነት የለም አንዴ; ቤት አይከበርም አንዴ: ዞሮ ለቤተስቡ አንደመርዳት አርግዝ አርጎ ማረፍ:: የአጎቴ ጥፋት የቱ ላይ ነው??
ይህ ጉዳይ በማናችንም አህት ወይም ዘመድ ላይ ይደርስ ይሆናል መልክቱ ግን ትምህርት ነው:: ለምሆኑ የዋርካ ሴቶች አስተያየት ስጡበት አባካችሁ::
ችሎ_ማደር
ጀማሪ ኮትኳች
ጀማሪ ኮትኳች
 
Posts: 55
Joined: Wed Sep 12, 2007 4:16 pm

Postby የኮካታ » Thu Sep 20, 2007 8:47 pm

ችሎ ማደር!
አሁን ገና ጨዋታ መጣ :: አስቲ የት ላይ ነው መፍለጡ መቁረጡ :: ሐላፊነት የለም አንዴ ; ቤት አይከበርም አንዴ : ዞሮ ለቤተስቡ አንደመርዳት አርግዝ አርጎ ማረፍ :: የአጎቴ ጥፋት የቱ ላይ ነው


ልጅቷ ተሳስታ አንዴ አርግዛለች! በቃ! ከዚ ተነስና መፍትሄ ፈልግ! ወደዋላ ተመልሰህ ለምን አረግዝሽ ብትላት ብትዘል ብትፈርጥ የተጎዳዉን የልጅቷን ስሜት ጨምረህ ነው የምትጎዳው እንጂ ምንም የምታመጣው ነገር የለም::

አጎትህም ይህን መረዳት አለምቻላቸው ነው እንዲበሳጩና በግትርነት ልጅቷን ከቤት ዉጪልኝ የሚሉት! ረጋ ብለው ምን ላድግ ብለው ቢያስቡ ትልቅ ጥፋት ደግመው እየሰሩ ያሉት አጎትህ ናቸው! የሰውን (ያዉም የልጃቸውን) ችግር ተረድቶ እንደ መርዳት በችግሯ ላይ ሌላ ችግር መደረብ ትልቅ ሀጥያት ነው:: ለዚ ነው ፈላጭ ቆራጭ ያልኩት::


በተጨማሪም አንድ ቤተሰብ የሚመሰረተው 50% ባል 50% ሚስት ነው እንጂ እንደጃንሆይ ዘመን ትዳር ያዉም በሰለጠነው አለም ትሁኖ አያምርም! ባል ከቤት ዉጪ ስላሉ ብቻ የአጎትህ ሚስት ሀሳብ ምን እንደሆነ ሳይታወቅ ልጅቱ ትዉጣለች ማለት አይደለም! ሁለቱም ተነጋግረው ከቤት ትዉጣ ካሉ ok! ልጅቷም ትልቅ ናት ራስዋን መምራት ትችላለች!!!

የቤተሰብ ክብር የምትለው ነገር በጣም ያስቃል! ልጃቸው ተቸግራ ከቤት ዉጪልኝ እያሉ አባት ስለቤተሰብ ክብር ሲጨነቁ! ይህ ነው የአጎትህ ትልቅ ጥፋት! ከሁሉም የከፋው የሳቸው ትፋ ነው! ልጃቸውን እኔ አለዉልሽ ብሎ እንደአባት ተጋፍጦ እንደመመከት እራስን በቤተሰብ ክብር ስም ከልሎ ከችግሩ ማምለት ምን የሚሉት ነገር ነው::


እሳቸውስ በድሮው አስተሳአሰብ ሄደው ስለሆነ ለመፍረድ ያስቸግራል! ግን ያንተ ይገርማል! በዚ ሁኔታ ላይ ላለች ልጅ የቤተሰብ ክብር ብሎ ጣጣ ምፍትሄዋ አይሆንም!!!
Lucky being kokata!
የኮካታ
ጀማሪ ኮትኳች
ጀማሪ ኮትኳች
 
Posts: 74
Joined: Fri Sep 14, 2007 3:41 am
Location: somewhere beautiful

Postby ችሎ_ማደር » Thu Sep 20, 2007 9:26 pm

'የኮካታ' ለተስጠው ህሳብና አስተያየት ጥሩ ትምህርት ነው::
አኔም በጣም ልጅ ስለሆንኩ ብዙው ጠለቅ ብሎ አይገባኝም:: አጎቴ ግን የ44 አመት ዶክተር አና ዘመናዊ ናቸው::
የኮካታ wrote:
የቤተሰብ ክብር የምትለው ነገር በጣም ያስቃል! ልጃቸው ተቸግራ ከቤት ዉጪልኝ እያሉ አባት ስለቤተሰብ ክብር ሲጨነቁ! ይህ ነው የአጎትህ ትልቅ ጥፋት! ከሁሉም የከፋው የሳቸው ትፋ ነው! ልጃቸውን እኔ አለዉልሽ ብሎ እንደአባት ተጋፍጦ እንደመመከት እራስን በቤተሰብ ክብር ስም ከልሎ ከችግሩ ማምለት ምን የሚሉት ነገር ነው::
ግራ የሚያጋባ ነው አጎቴ ያሉበት ሁኔታ:: አኔን ስለሚያቀርቡኝ አንድ አንድ ሐሳብ መወርወሬ አልቀረም:: አስካአሁን ግን ጠንከር ያለና መስረት ያለው መፍትሔ ገና አልተገኘም::ነገ ትንቯ ልጃቸው ብትደግመውስ??
ችሎ_ማደር
ጀማሪ ኮትኳች
ጀማሪ ኮትኳች
 
Posts: 55
Joined: Wed Sep 12, 2007 4:16 pm

Postby Debzi » Thu Sep 20, 2007 10:15 pm

ችሎ_ማደር wrote: የዋርካ ሴቶች አስተያየት ስጡበት አባካችሁ::


እሺ:: ግና እኚህ የ44 አመቱ አጎትህ ሶስተኛ ልጃቸው 27 አመቷ ሲሆን.....የመጀመሪያ ልጃቸው ወደ 30 ገደማ መሆኑ ነው ቢያንስ ቢያንስ...እና ልል ያሰብኩት አጎትህና ያጎትህ ሚስት በ14 አመታቸው ልጅ ሲወልዱ ቤተ ሰቦቻቸው ረድተዋቸዋል ወይ? ሳይረዷቸው የቀሩ አይመስለኝም:: አጎትህም እንግዲህ ልጃቸውን እንደምንም ብለው ኩራታቸውን ዋጥ አርገው እስክምትቆናጠጥ ድረስ ቢረዷት ጥሩ ነው:: ነው እምልህ::
Ke akbrot selamta gar!!
Debzi
ዋና ውሃ አጠጪ
ዋና ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1918
Joined: Sun May 02, 2004 12:34 am
Location: Los Angeles, CA

Postby ፓን ሪዚኮ » Thu Sep 20, 2007 10:33 pm

ሙዝ1 wrote:ችሎ ማደር
በመጀመሪያ ይህ ስምህ የዉሻ ስም ነው
ጌታ እና ትትና ግን ታዘብኳችሁ... እንዴት ለመቻል ምክር አጸጡትም?
አንተ ቡችላ ...እስቲ አቅምህ አይደለምና ............እስቲ ነገሩን ለሀገር ሽማግሌዎች ተወው
ፓኑ አባ ፈርዳ
Last edited by ፓን ሪዚኮ on Thu Sep 20, 2007 11:01 pm, edited 1 time in total.
Imageኢትዮጲያ ትቅደም
ፓን ሪዚኮ
አለቃ
አለቃ
 
Posts: 2044
Joined: Tue Aug 03, 2004 3:35 am
Location: ጎሃ ጽዮን

Postby ችሎ_ማደር » Thu Sep 20, 2007 10:55 pm

Debzi wrote:
ችሎ_ማደር wrote: የዋርካ ሴቶች አስተያየት ስጡበት አባካችሁ::


እሺ:: ግና እኚህ የ44 አመቱ አጎትህ ሶስተኛ ልጃቸው 27 አመቷ ሲሆን.....የመጀመሪያ ልጃቸው ወደ 30 ገደማ መሆኑ ነው:

ይቅርታ በማደባለቄ አሷ የመጀመሪያዋ ነች:
ችሎ_ማደር
ጀማሪ ኮትኳች
ጀማሪ ኮትኳች
 
Posts: 55
Joined: Wed Sep 12, 2007 4:16 pm

Postby Debzi » Thu Sep 20, 2007 11:22 pm

ኦ...እሷ የመጀመሪያ ነች ለካ:: እሺ::
አባትና እናቷ እኩያሞች ናቸው ብንል....በ17 አመታቸው ነው የወለዷት ማለት ነው:: ያ ማለት ሀይስኩል እያሉ ነው ማለት ነው:: ያ ማለት እነሱም ሳያስቡት ነው ማለት ነው እቺ ልጅ የተረገዘችው:: ሳያስቡት ፕላን ሳያረጉት ልጅ ስለወለዱ ልጃቸውም እነሱ ያጠፉትን ስለደገመች ይሆን የተናደዱት? ጥያቄ ነው::

በተረፈ.....ትክክለኛ መልስ አንደኛው ገጽ ላይ በእህምም የተመለሰ ይመስለኛል:: እኔ እንደው የእድሜው ነገር ስላሳቀኝ ነው ዘው ያልኩት::

ችሎ_ማደር........ጥሩ መወያያ ክፍል ከፍተህ ሰዉን ስላወያየኸው ሽልማት ይገባሀል:: አጎትህም ጥንካሬውን ይስጣቸው:: አሜን::

ችሎ_ማደር wrote:ይቅርታ በማደባለቄ አሷ የመጀመሪያዋ ነች:
Ke akbrot selamta gar!!
Debzi
ዋና ውሃ አጠጪ
ዋና ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1918
Joined: Sun May 02, 2004 12:34 am
Location: Los Angeles, CA

Postby ችሎ_ማደር » Fri Sep 21, 2007 4:38 am

Debzi wrote:ችሎ_ማደር........ጥሩ መወያያ ክፍል ከፍተህ ሰዉን ስላወያየኸው ሽልማት ይገባሀል:: አጎትህም ጥንካሬውን ይስጣቸው:: አሜን::


አጅግ በጣም አመስግናለሁ:: ዛሬ ደግሞ አዲስ ነገር ሆኗልና ካጣራሁ በሁዋላ እነግራኍለሁ::

የአጎቴና የሚስታቸው የሕይወት ታሪክ ለወደፊት ታላቅ ፊልም የሚሆን ታሪክ ስላለ በዋርካ ስነጽሁፍ በኩል አሳዛኝ: አስቂኝ; ፍቅር: ፖለቲካ; አስር ቤትና ስደት ባጭሩ አቀርባለሁ:
ችሎ_ማደር
ጀማሪ ኮትኳች
ጀማሪ ኮትኳች
 
Posts: 55
Joined: Wed Sep 12, 2007 4:16 pm

Postby ትትና » Fri Sep 21, 2007 8:35 am

ሙዝ መፍትሄ ስትባል ስለስም የሰጠህው አስተያየት በሳቅ ገሎኛል!

ዴብዚ:- ያንቺ ነገር, ካልኩሌሽን ሀሪፍ ነሽ!

ችሎ ማደር በጣም ይቅርታ እነዚህ ሁለት ሰዎች አንተ ካሰፈርከው ችግር በተመጣጣኝ ሀሳቤን ስለሰረቁት ነው::

:D

ነገሩ እውነት ነው ብለሀል ከሆነ:- ብዙ ተብሎ በቂ መልስ ተሰጥቶበታል:: ሁለት ነገር ግን:-

1. አጎትህ:- ልጃቸው ልጅ ሳይሆን በሽታ አምጥታ በአጭር ጊዜ ውስጥ የምትለያቸው ቢሆን ምን ሊሆኑ ነበር? ልጅ ሲያድግ ዘመድ ይሆናል መሽታ ግን... " በፊት ነበር እንጂ አስቦ መደቆስ አሁን ምን ያደርጋል ድስት ጥዶ ማልቀስ ሲባል አልሰሙም::

2. ያንተ ለአጎትህ ክብር እንደዛ መሆንህ ነው የገረመኝ:- አንተ እራስህ እሳቸውን መስለህ ነው የታየህኝ የ 44 አመቱን አዛውንት:: ምን ሆነህ ነው ግን ስለክብር...... ያልከው?

አድራ እንዳትጣላኝ እንጂ: እንኳን አረገዘች! በ27 አመቷ ትምህርት ብላ..... ትደርስበታለች በሰላም ትገላገል እንጂ::

አክባሪህ
ትትና
ውሃ አጠጪ
ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1253
Joined: Wed Feb 23, 2005 11:26 am
Location: united states

Postby ችሎ_ማደር » Fri Sep 21, 2007 4:32 pm

ትትና wrote:1. አጎትህ:- ልጃቸው ልጅ ሳይሆን በሽታ አምጥታ በአጭር ጊዜ ውስጥ የምትለያቸው ቢሆን ምን ሊሆኑ ነበር? ልጅ ሲያድግ ዘመድ ይሆናል መሽታ ግን... " በፊት ነበር እንጂ አስቦ መደቆስ አሁን ምን ያደርጋል ድስት ጥዶ ማልቀስ ሲባል አልሰሙም::

2. ያንተ ለአጎትህ ክብር እንደዛ መሆንህ ነው የገረመኝ:- አንተ እራስህ እሳቸውን መስለህ ነው የታየህኝ የ 44 አመቱን አዛውንት:: ምን ሆነህ ነው ግን ስለክብር...... ያልከው?


አኔ አንኳ ለነገሩ ብዙ ማሰቤና አጎቴን ማማክሬ ባይቀርም; በበሰለ አስተያየቴ ተሰሚነት ለማግኘት ፍሬ ተርስኪ ወሬ አላወራም::
አንዴት አደርጎ ነው አስቦ የሚደቆሰው አስቲ? Boyfriend መኖሩን አለመቀበል ነው? ቀደም ብዬ አንዳልኩት አናቷ መክረዋል:: Birth control አስከማሳዘዝ ድረስ::
አኒህ ስው ምን ያድርጉ:: "በሰው ቁስል አንጨት ስደድበት' አይሁን ስታማከሩ: "ነግ በኔ" አለች ወ/ሮ ድንብላል::
ችሎ_ማደር
ጀማሪ ኮትኳች
ጀማሪ ኮትኳች
 
Posts: 55
Joined: Wed Sep 12, 2007 4:16 pm

Postby kiyora » Fri Sep 21, 2007 4:45 pm

ከምር ትትና ያለችው እውነት ነው. አጎትህ አንተ ራስህ ነህ. ቢ ኦነስት. anyway just take action i think u got enough information.
kiyora
ጀማሪ ኮትኳች
ጀማሪ ኮትኳች
 
Posts: 59
Joined: Wed Jun 29, 2005 4:51 pm

Postby ችሎ_ማደር » Fri Sep 21, 2007 4:57 pm

kiyora wrote:ከምር ትትና ያለችው እውነት ነው. አጎትህ አንተ ራስህ ነህ. ቢ ኦነስት. anyway just take action i think u got enough information.


አጎቴ አኔ አለመሆኔን አረጋግጥልሀ(ቫ)ለሁ:

ለነገሩ ይህ ብዙ ትምሕርት ያለው መልአክት ይመስለኛል አና ውይይቱን ቀጥሉበት::
ችሎ_ማደር
ጀማሪ ኮትኳች
ጀማሪ ኮትኳች
 
Posts: 55
Joined: Wed Sep 12, 2007 4:16 pm

Postby ትትና » Thu Sep 27, 2007 10:32 am

ችሎ ለካ እዚ ጋር ትንሽ ተበሳጭተሀል:: ወይ ጉድ መች አየሁትና የኔ ነገር ዋንስ ኢን ኤ ብሉ ሙን እየመጣሁ::

እልቅ birth control ስትል ምን ትዝ እንዳለኝ ታውቃለህ:: ድሮ ልጅ ሆኜ ቶንሲል የሚባል የልጆች ጠላት የሆነ በሽታ ያስቸግረኝ ነበር ታዲያ እንደልማዴ ታምሜ እናቴ ጤና ጣቢያ ወስዳኝ የጠዋቱ ብርድ ነገር አይወራ እንኳን ላመመው..... ከዛ እንደምንም ሰራተኞቹ ሰአት እስኪደርስ ብለው ጸሀይ ላይ ቆመው ታሽተው ሲበቃቸው ገቡ:: እኛ አይናችን ቁልጭ ቁልጭ እያለ ስንጠባበቅ ቆይተን ወደ 8:30 ጠዋት ላይ አንዷ ጠቆር ያለ ከለር ያላት ከወገቧ በላይ ደበልበል ያለች ታኮ ጫማ ያደረገች ጸጉራ እቤት ውስጥ በቢጎዲን ተጠቅልሎ በጸሀይ የደረቀ ይሚመስል የተፈጥሮ ቅንዷን አያስፈልግም ባል ልጭት አድርጋው በራሶ ከፍ አድርጋ በቀጭን ኩል የፊደል "በ" አስመስላ ያስቀመጠች ሴትዮ ወጥታ
" እንግዲህ ስሙ አትንጫጩ! በላ ሀርድ ከሰጠች በኃላ... የቤተሰብ ምጣኔ.... በሚል አርስት ላይ በመሽከርከር አላስፈላጊ እርግዝና......" እያለች እውቀቷን ተነተነችው ነው ይሚባለው:: እንዲሞቀኝ እናቴ ነጠላ ውስጥ ሆኜ ወሬውም እንዳይቀር በአንድ አይኔ አጮልቄ ግን ከትምህርቱ ይልቅ መልኳን ነበር በደንብ ያጠናሁት::
ግን ያጎትህ ሚስት የዛን ለት ነበሩ ማለት ነው? :D ሳሾፍብህ ነው!
ትትና
ውሃ አጠጪ
ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1253
Joined: Wed Feb 23, 2005 11:26 am
Location: united states

Re: የአጎቴ ልጅ አርግዛ ቁጭ

Postby ችሎ_ማደር » Thu Sep 22, 2016 12:00 pm

ዋርካ እና እኔ ጠፍተን ከረምን....

ይኸው የአጎቴ ልጅ ከወለደች ወደ 9 ዓመት ሆነ፡፡
የልጅዋ አባት ጎረምሳ ግን እንደተፈራው ሃላፊነት የጎደለውና አሳዳጊ የበደለው ምንም ያህል አይረዳም፤
.....
ልጅትዋ ግን የወርቅ ፍልቃቂ የምሰለ መልክና ጸባይ ተክናለች፤ አጎቴም በጣም ይውድዋታል፡

እናትዋ ማለትም ያጎቴ ልጅ እንደፈፋሁት ራሥዋን መቻል ከብድዋታል...
"The difference between stupidity and genius is that genius has its limits." Albert Einstein
ችሎ_ማደር
ጀማሪ ኮትኳች
ጀማሪ ኮትኳች
 
Posts: 55
Joined: Wed Sep 12, 2007 4:16 pm

Previous

Return to Warka Intimate - ዋርካ ፍቅር

Who is online

Users browsing this forum: No registered users and 4 guests