ራሑ አጠር ብትልም ጸጉሯና ፈገግታዋ ልብ ይሰርቃል:: 'ደጋን አግር አንላታለን' ፍቄ ሳይሰማ:: ከራሁ ጋራ ያደረ ለት, ቀኑን ሙሉ ደስ ብሎት ይዋል አንጂ ሲደክም አንዳደረ ያስታውቃል:: ራሑ ራሷን የቻለች ስልሆነች ከፍቄ ምንም አትፈልግም:: ዘወትር ቤቷ ምግብ አይጠፋም:: ራሑ ከታውቀ ኮሌጅ በሙያ በክብር ተመርቃለች:: ታድይ ባለም ላይ አንደፍቄ ያለ ወንድ ያለ አይመስላትም:: ይኸው ከተዋወቁ ወደ ሁለት አመት ገደማ ሆናቸው::
ስለሶፊ ግን ቢወራ, ቢወራ, ቢወራ የት ተጀምሮ የት አንደሚቆም ያስቸግራል:: አንዳው አምዬ ማርያምን ነው የምትመስል:: የመልኳ, የቁመቷ, የዳሌና የአግሯ, የጣቶችዋ አና, የፀጉርዋ: መለኪያ የለውም:: ፍቄ ዙረት በሔደበት ከጎኑ አትለይም:: በመኪና ውስጥ ሲንቨራቨሩ, ወይ በየ ሆቴል ያየ አቤት ሲያስቀኑ! ፍቄ ሶፍን በመጀመሪያ አይቶ ፈዞ የቀረው የራሑ ምርቃት ለት ነው:: ለራሁ የገዛውን
አበባ ለሶፊ ሲሰጥ አሷም ተከትልው ስትበን ነው::
ፍቄ ራሑንም ሶፊንም በጣም አድርጎ ይወዳቸዋል:: አንደ ፍቄማ ሁኔታማ ሁለቱም ቢተዋወቁና አብረው ቢኖሩ ያስደስተው ነበረ::
ዛሬ ሶፊ ወይ አንጋባ ወይም በቃን ብላ ያንድ ወር ጊዜ ሰጥታዋለች:: ይኸው ግራ ገብቶት ይነኍለላል:: በርግጥ ሁለቱንም በጣም ይውዳቸዋል
ዋርካዎች አስቲ ምከሩልኝ !!