የአክስቴ ልጅ ሁለት ወዶ ይነኍለላል

The Love Forum (love, relationship) (የኔ ቆንጆ እንተዋወቅ :-)

የአክስቴ ልጅ ሁለት ወዶ ይነኍለላል

Postby ችሎ_ማደር » Sun Sep 23, 2007 7:35 am

ራሑ አጠር ብትልም ጸጉሯና ፈገግታዋ ልብ ይሰርቃል:: 'ደጋን አግር አንላታለን' ፍቄ ሳይሰማ:: ከራሁ ጋራ ያደረ ለት, ቀኑን ሙሉ ደስ ብሎት ይዋል አንጂ ሲደክም አንዳደረ ያስታውቃል:: ራሑ ራሷን የቻለች ስልሆነች ከፍቄ ምንም አትፈልግም:: ዘወትር ቤቷ ምግብ አይጠፋም:: ራሑ ከታውቀ ኮሌጅ በሙያ በክብር ተመርቃለች:: ታድይ ባለም ላይ አንደፍቄ ያለ ወንድ ያለ አይመስላትም:: ይኸው ከተዋወቁ ወደ ሁለት አመት ገደማ ሆናቸው::
ስለሶፊ ግን ቢወራ, ቢወራ, ቢወራ የት ተጀምሮ የት አንደሚቆም ያስቸግራል:: አንዳው አምዬ ማርያምን ነው የምትመስል:: የመልኳ, የቁመቷ, የዳሌና የአግሯ, የጣቶችዋ አና, የፀጉርዋ: መለኪያ የለውም:: ፍቄ ዙረት በሔደበት ከጎኑ አትለይም:: በመኪና ውስጥ ሲንቨራቨሩ, ወይ በየ ሆቴል ያየ አቤት ሲያስቀኑ! ፍቄ ሶፍን በመጀመሪያ አይቶ ፈዞ የቀረው የራሑ ምርቃት ለት ነው:: ለራሁ የገዛውን

አበባ ለሶፊ ሲሰጥ አሷም ተከትልው ስትበን ነው::
ፍቄ ራሑንም ሶፊንም በጣም አድርጎ ይወዳቸዋል:: አንደ ፍቄማ ሁኔታማ ሁለቱም ቢተዋወቁና አብረው ቢኖሩ ያስደስተው ነበረ::

ዛሬ ሶፊ ወይ አንጋባ ወይም በቃን ብላ ያንድ ወር ጊዜ ሰጥታዋለች:: ይኸው ግራ ገብቶት ይነኍለላል:: በርግጥ ሁለቱንም በጣም ይውዳቸዋል

ዋርካዎች አስቲ ምከሩልኝ !!
ችሎ_ማደር
ጀማሪ ኮትኳች
ጀማሪ ኮትኳች
 
Posts: 56
Joined: Wed Sep 12, 2007 4:16 pm

Postby ሙዝ1 » Sun Sep 23, 2007 7:41 am

መቻል
ስለኔ ነዉ አይደል የምታወራ? :wink:
ሙዝ1
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 3128
Joined: Wed Feb 22, 2006 9:25 am

Postby እህምም » Sun Sep 23, 2007 4:33 pm

:lol: I say they should both leave him.
Homage to darkness : http://yekolotemari.blog.com/2010/02/09 ... -darkness/


"Is it stealing
if I take
the pains of others

and make it my healing?"
http://elicitbeauty.blogspot.com/
እህምም
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 2509
Joined: Mon Dec 19, 2005 10:36 pm
Location: on a small rock; between an ocean and a sea.

Postby የኮካታ » Sun Sep 23, 2007 4:47 pm

ልጅ ችሎ ማደር!!! በመጀመርያ ሹክ ያለ በላን ሰላም በልልኝ! ግን አንተ ምንድነው የፋሚሊህን ችግር ምክር ስጡኝ እያልክ ዋርካ ላይ መወያያ የምታደርገው?? ባለፈው የተመከርከዉን ምን አደረከው??? ያጎቴ ልጅ አርግዛ.... ምክር ስጡኝ አልክ! አሁን ያክስትህ ልጅ 2 ወደደ! አንድት የፋሚሊ ሽማግሌ ነህ ውይ ሁሉም ችግሩን የሚነግርህ??? እንደነገርከኝ ከሆነ ልጅ ነህ...ጨቅላ! ያለእድሜህ እየተጨነክ ነዉናያለእድሜህ ሳትሸብት በዚ ይብቃህ! ስምህ ችሎ ማደር አይደል? ችለው እንዲያድሩ ብትነግራቸው ምን ይልሀል!!!
Lucky being kokata!
የኮካታ
ጀማሪ ኮትኳች
ጀማሪ ኮትኳች
 
Posts: 74
Joined: Fri Sep 14, 2007 3:41 am
Location: somewhere beautiful

Postby Debzi » Sun Sep 23, 2007 5:05 pm

ሰላም ችሎ_ማደር,

ያክስትህ ልጅ ሶፊን ቢያገባ ደስ ይለኛል:: አቃለሁ...አቃለሁ ጥያቄው የኔ ደስታ አይደለም:: ቢሆንም...ቢሆንም....የፍቄን አይነት ሰዎች አውቃለሁ እና ከጥፋታቸው እሚያስተምራቸው ሰው ያስፈልጋቸዋል:: አየህ....ራሑ ጨዋና የምትፈልገውን የምታውቅ ረጋ ያለች ሴት ናት:: ፍቄ ለሷ ያንሳታል:: ሶፊ ግን ጩሉሌ መሳይ ዛሬ እሱን ለጥቅሟ ብላ የፈለገችው ነገ ደሞ ወደ ሌላ የምትሄድ አይነት ሴት ስለሆነች ትንሽ ቆይታ እንደ በርበሬ ስለምታቃጥለው ያግባትና ይቅመሰው:: ከዛ በኋላ እንዲህ በሴቶች መጫወቱን ያቆማል ባይ ነኝ::

አቤት አቤት! በሰንበቱ መጥፎ አሰብኩ መሰለኝ! ይቅር ይበለኝ:: አሜን::
Ke akbrot selamta gar!!
Debzi
ዋና ውሃ አጠጪ
ዋና ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1918
Joined: Sun May 02, 2004 12:34 am
Location: Los Angeles, CA

Postby ሰልማ1 » Sun Sep 23, 2007 5:10 pm

ወይ ደብዚ እስቲ አሁን የችሎ ማደር ልጅ ምን አደረገሽና ነው ይህን የምትመኝለት.......
senisebiyorom
ሰልማ1
ውሃ አጠጪ
ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1304
Joined: Sun Aug 05, 2007 2:11 am

Postby ችሎ_ማደር » Mon Sep 24, 2007 1:08 am

Debzi wrote:ሰላም ችሎ_ማደር,

ያክስትህ ልጅ ሶፊን ቢያገባ ደስ ይለኛል:: ............... ትንሽ ቆይታ እንደ በርበሬ ስለምታቃጥለው ያግባትና ይቅመሰው:: ከዛ በኋላ እንዲህ በሴቶች መጫወቱን ያቆማል ባይ ነኝ::

አቤት አቤት! በሰንበቱ መጥፎ አሰብኩ መሰለኝ! ይቅር ይበለኝ:: አሜን::

ወይ ጉዱ ....አቤት!!!!!!!!!!!!!!!!!!

ለነገሩ የራሑ ያልጋ መመቸት ጉዳይ ዋነኛ የትዳር ቁልፍ ሳይሁን ይቀራል ?? የአኛ ሕዝብ ስለዚሕ ጉዳይ በግልፅ አይነጋገርምና::
ስለ አስተያየቱ በጣም እያመስገንኩ አባካችሁ ቀጥሉብት !!!
ችሎ_ማደር
ጀማሪ ኮትኳች
ጀማሪ ኮትኳች
 
Posts: 56
Joined: Wed Sep 12, 2007 4:16 pm

Postby Debzi » Tue Sep 25, 2007 3:39 pm

ችሎ_ማደር wrote:ለነገሩ የራሑ ያልጋ መመቸት ጉዳይ ዋነኛ የትዳር ቁልፍ ሳይሁን ይቀራል ??


አይመስለኝም:: ሴቶች እርግጥ ይህንን እንደ ክራይተሪያ ሊወስዱት ይችላሉ:: ወንዶች ግን መልክ: የሰውነት ቅርጽ: ጠባይ..የመሳሰሉትን ነው የሚመርጡት::
Ke akbrot selamta gar!!
Debzi
ዋና ውሃ አጠጪ
ዋና ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1918
Joined: Sun May 02, 2004 12:34 am
Location: Los Angeles, CA

Postby ጩጉዳ » Tue Sep 25, 2007 5:14 pm

አይ ያንተ . . :lol: ነገር ያክስቴ ልጅ ያጎቴ ልጅ ያባቴ ልጅ እያልክ ያንተም የዘመዶችህም ጉድ ቢቆጠር አላልቅ አለ:: :lol: :lol: እኔ የምመክራችሁ ሁላችሁም ተሰብስባችሁ ወደ ጸባይ ማረሚያ በፈቃድኝነት ግቡ:: :lol: :lol: :lol: ካልታረማችሁም ማዕከላዊ ሄዳችሁ እጅ ስጡ::

ደብዚ :lol: :lol: :lol: :lol: ሰው ማጋባት ጀመርሽ እንዴ??? ጠንቀቅ ነው::
መታገስንና መቻልን የመሰለ ብቀላ የለም ::
ጩጉዳ
ውሃ አጠጪ
ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1267
Joined: Mon Jan 31, 2005 6:40 am
Location: Studio City, Wilson Republic

Postby Debzi » Tue Sep 25, 2007 10:44 pm

ጩጉዳ wrote:ደብዚ :lol: :lol: :lol: :lol: ሰው ማጋባት ጀመርሽ እንዴ??? ጠንቀቅ ነው::


ተው እንጂ ጩጉዳዬ!! እንዲህ የሳቅክብኝ ምህኛቱ ምንድ ነው? ገና አንተን ለማጋባት ትልቅ ፕላን አለኝ:: ::
ዋርካ ፍቅር ላይ ፍቅርን የሚመለከት አርስት ሲኖር አስደንግጦኝ ነው እዚህ ዘው ዘው ማለት ያበዛሁት!!
""ዋርካ ፍቅር....የኔ ቆንጆ እንተዋወቅ"" ይላል የፎረሙ ስም............... ለነገሩማ.......
Ke akbrot selamta gar!!
Debzi
ዋና ውሃ አጠጪ
ዋና ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1918
Joined: Sun May 02, 2004 12:34 am
Location: Los Angeles, CA

Postby ትትና » Thu Sep 27, 2007 10:13 am

ጨጉዳው :D :D :D ገደልከኝ ሙት!

እውነትም ጸባይ ማረሚያ አደራ እነዛ የ90 አመት አዛውንት ጋቢ ተከናንበው ሶፋ ላይ ቁጭ የሚሉ ያስመሰልካቸው አጎትህ እንዳይረሱ::

ችሎዬ ግን እውነቷን ተናገር ያንተ ታሪክ ናት አይደል? ነው ወይስ እንዲህ አጫጭር ልብ ወለድ ትሞካክራለህ? ወይ ትንሽ እረዘም አድርገውና እናንብብልህ::

ለማንኛውም ለአጎትህ ልጅ መፍትሄው ራሑን አስተዋውቀንና ልጁ ጸባይ ማረሚያ ሊገባነውና ይቅርብሽ እንበላት::
ትትና
ውሃ አጠጪ
ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1253
Joined: Wed Feb 23, 2005 11:26 am
Location: united states

Postby ችሎ_ማደር » Fri Sep 28, 2007 10:13 pm

ትትና wrote: ለአጎትህ ልጅ መፍትሄው ራሑን አስተዋውቀንና ልጁ ጸባይ ማረሚያ ሊገባ ነውና ይቅርብሽ እንበላት::


የአክስቴ ልጅ ነው::

ጨጉዳው! ተው ተው አያድርስብሕ ነው::
ችሎ_ማደር
ጀማሪ ኮትኳች
ጀማሪ ኮትኳች
 
Posts: 56
Joined: Wed Sep 12, 2007 4:16 pm

Postby ጩጉዳ » Mon Oct 01, 2007 9:42 am

ችሎ_ማደር wrote:የአክስቴ ልጅ ነው:: ጨጉዳው! ተው ተው አያድርስብሕ ነው::


ነፍሱ ...... ምን ላርግ ጉዳችሁ ቢቆጠር ኮ አላልቅ ስላለኝ ነው:: :lol: :lol: :lol: :lol: አይዞኝ ! ጸባይ ማረሚያ ነጻ ነው አሉ የምክር አገልግሎት ለዛውም እነ ዘርኦምና ግዳይ ደህና አርገው ያስተምሩሻል:: :lol: :lol:
መታገስንና መቻልን የመሰለ ብቀላ የለም ::
ጩጉዳ
ውሃ አጠጪ
ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1267
Joined: Mon Jan 31, 2005 6:40 am
Location: Studio City, Wilson Republic

Postby ጩጉዳ » Mon Oct 01, 2007 9:45 am

Debzi wrote:ተው እንጂ ጩጉዳዬ!! እንዲህ የሳቅክብኝ ምህኛቱ ምንድ ነው? ገና አንተን ለማጋባት ትልቅ ፕላን አለኝ:: ::
ዋርካ ፍቅር ላይ ፍቅርን የሚመለከት አርስት ሲኖር አስደንግጦኝ ነው እዚህ ዘው ዘው ማለት ያበዛሁት!!
""ዋርካ ፍቅር....የኔ ቆንጆ እንተዋወቅ"" ይላል የፎረሙ ስም............... ለነገሩማ.......


ቅቅቅቅ <ምህኛቱማ> ስታጣብሺ ስለሾፍኩሽ ነው:: ደግሞ እኔን ከማን ? እኮ ከማን? ቅቅቅቅ ያች ሠራተኛሽ ኮ ለዛ ነገር ቢሆን እንጂ ለትዳርማ አትሆንም:: እኔማ የማገባት .... አሪዞና ትሮሊ ስቴሺን የተቀበለች ባለሚሳይል ጡቷ ነች::
መታገስንና መቻልን የመሰለ ብቀላ የለም ::
ጩጉዳ
ውሃ አጠጪ
ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1267
Joined: Mon Jan 31, 2005 6:40 am
Location: Studio City, Wilson Republic

Postby ጩጉዳ » Mon Oct 01, 2007 9:48 am

ትትና wrote:ጨጉዳው :D :D :D ገደልከኝ ሙት!


ትትና ቅቅቅ ምን ላርግ ብለሽ ነው:: ጉዳቸው ቢቆጠር አላልቅ አለ ኮ:: :lol: እኔ የቀበሌያቸው ሊቀመንበር ብሆን ይሄኔ ከርቸሌ ከትቻቸዋለሁ:: :lol: :lol: እነሱን ለፍርድ ሳያቀርቡ ነው ማሰር::
መታገስንና መቻልን የመሰለ ብቀላ የለም ::
ጩጉዳ
ውሃ አጠጪ
ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1267
Joined: Mon Jan 31, 2005 6:40 am
Location: Studio City, Wilson Republic

Next

Return to Warka Intimate - ዋርካ ፍቅር

Who is online

Users browsing this forum: No registered users and 3 guests

cron