የኢትዮጵያ ቤ/ክ የጾታ ትምህርት- ማንበብ ለሚፈልግ

The Love Forum (love, relationship) (የኔ ቆንጆ እንተዋወቅ :-)

የኢትዮጵያ ቤ/ክ የጾታ ትምህርት- ማንበብ ለሚፈልግ

Postby ብርኃናዊት » Tue Oct 30, 2007 5:33 am

ሠላም ዋርካውያን እንደምናችሁ: እግዚአብሔር ይመስገን እኔ በጣም ደህና ነኝ::

በኛ ባህል ስለ ጾታ ግንኙነትና ስለ ሩካቤ ስጋ መወያየት ነውር በመሆኑ ለዘመናት የ"ተከድኖ ይብሰል' ጉዳይ ሆኖ ብዙ ባለትዳሮች ሲቸገሩበትና ከትዳራቸው ውጪ እንዲወሰልቱ ምክንያት እየሆናቸው ሲኖር ቆይቷል:: ዝሙት አዳሪዎችና እውነተኛ ፍቅርን የመመስረት ዐላማ የሌላቸው የወሲብ ሱሰኞች በሙያው በሚገባ ተክነውበትና የፍቅር ቃሉን ማዥጎድጎድ ችለውበት ወንዶችን ከትዳር ውጭ ሲያስኮበልሉ እናቶች/ሚስቶች ደግሞ ለባሎቻቸው እንዴት ሆነው መቅረብ እንዳለባቸውና ምን ዓይነት ስሜት ማሳየት እንዳለባቸው ባለማወቃቸው ባሎቻቸውን ሲያርቁና በአንጻሩ በድንገት እጁ ላይ የወደቁበትን ጎረቤትም ይሁን አሽከር በድብቅ ሲለማመጡና አብረው ሲባልጉ ይገኛሉ (ከውሽማቸው የሚያገኙትን ከባላቸው ጋር ማግኘት የማይችሉ ይመስል::) በአንጻሩ በውስጣቸው ባለ እውነተኛ ፍቅር ብቻ በመታገዝ አንዳቸው ለአንዳቸው ስሜት በመጨነቅ አስደሳች የሩካቤ ህይወት ለመኖር የቻሉ ባልና ሚስትም በቀድሞውም ዘመን ቢሆን ብዙዎች ነበሩ::

ይህን ርዕስ ለመክፈት ያነሳሳኝ ታድያ በዚህ መድረክ እንደሚስተዋለው ምዕራባውያንን የጾታ ግንኙነትና የባልና የሚስት ጠቅላላ ግንኙነት ምን ይመስላል የሚለውን ጥያቄ ለመመለስ እንደዋነኛ ዋቢዎች አድርጎ የመመልከቱ አዝማሚያ አግባብ መስሎ ስላልታየኝ ነው:: የዚህም ምክንያቴ ሶስት ናቸው:: አንዱ የኢትዮጵያውያንን መልካም ሥነ-ምግባርና መንፈሳዊ ሰላም እንዲሁም አካላዊ ጤና የሚያውኩ አጉል ልማዶችን ሊያስለምዱን ስለሚችሉ ሲሆን ሁለተኛው ምክንያት ደግሞ ለሁሉም ነገር እነርሱን እንደመምህር አድርጎ የመመልከቱ ነገር ከትምህርቱ: ከቴክኖሎጂው: ከፖለቲካው አልፎ አልጋችን ላይ መውጣቱ የጥገኝነታችንን ስነ-ልቦና ፈር ያስለቅቀዋል ብዬ ስለፈራሁ ነው:: ሶስተኛው ምክንያቴ ደግሞ ከነርሱ የምንወስዳቸው እጅግ ጠቃሚ ተራክቦንና የዕለት-ተዕለት ህይወትን የተመለከተ ሳይንሳዊና ስነ-ልቦናዊ ዕውቀቶች ቢኖሩም የነሱን የፍቅርና የወሲብ ሞዴል ለመከተል በጣም መመኘት ግን ከባህል: ከሀይማኖትና ከኢኮኖሚ ሁኔታችን ጋር ስለሚጋጭብን ውስጣዊ አለመረጋጋትስ: ራስን የመውቀስና በራስ ያለመርካት ስሜትን ሊያዳብርብን ይችላል በሚል ነው:: እስኪ አስቡት: እንደነሱ መቅበጥ አላስፈላጊ ነው ብዬ ባላምንም እንቅበጥ እንኩአ ቢባል ሌላው ቢቀር ኢኮኖሚያችን አይፈቅድልን እኮ ብዬ እገምታለሁ:: ለምሳሌ- የሻወር እንደልብ መገኘት: ፈር በለቀቁ ግንኙነቶች ወቅት የሚጠቀሟቸው ቅባቶችና ልዩ ድዮድራንቶች (ለምሳሌ- አፈ-ወሲብ የምንለውን አጸያፊ ተግባር ለመፈጸም አሜሪካውያን ሴቶች የተለየ ሽቶ የሴት አካላቸው ላይ ይጠቀማሉ: ይህ ደግሞ የተፈጥሮ የንጽህና መቆጣጠሪያ ፈሳሻቸውን ስለሚያዛባ እጅግ ጠንቀኛ እየሆነባቸው ጥያቄ አስነስቶባቸዋል:: አይገርምም?) : እንዲሁም ደግሞ የተራክቦ ህይወታቸውን ምንም ስለማይቆጣጠሩት ጨርሶ ከቁጥጥራቸው ውጭ በሚሆንበት ጊዜ የሚያማክሩት የተለየ ባለሙያ (ቴራፒስት): ወ. ዘ. ተ. አላቸው:: እኛ ለዚህ አቅሙ አለን? ምናልባት ውጭ ያለን ኢትይጵያውያን የፈለግነውን ለማግኘት የምንችል ቢመስለንም አብዛኛው ህዝባችን ግን በፊልም የሚመለከተውን ነገር በውን ለማድረግ በመመኘት ብቻ ተቃጥሎ ኢትዮጵያዊ ሆኖ መፈጠሩን ሲጠላ ብናይ ይህ መጥፎ ጉምጀታ ጎጂ መሆኑን እንረዳለን ብየ አስባለሁ::

ስለሆነም ከአሁን በኋላ በተቻለኝ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ በተክርስቲያን በሩካቤና በፍቅር ግንኙነት ዙርያ ምን ትላለች: ከመጽሀፍ ቅዱስስ በመነሳት እንዴት ታስተምራለች የሚለውን ለማካፈል እሞክራለሁ:: (በነገራችን ላይ ታስተምራለች ስል መድረክ ላይ ማለቴ አይደለም: ይልቁንም አቋሟ ምንድነው የሚለውን ማለቴ ነው::) ከኔ የተሻለ ዕውቀቱ ያላችሁ ትኖራላችሁ ብዬ ስለማምን እናንተም አዋጡ እላለሁ:: አዲስ አባል በመሆኔም በስድብና በጸያፍ ቃላት እንዳታስበረግጉኝ ስል በትህትና እጠይቃለሁ::

እህታችሁ ብርኃናዊት
ብርኃናዊት
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 3302
Joined: Sat Oct 27, 2007 3:57 am

Postby ብርኃናዊት » Mon Nov 12, 2007 10:18 pm

ሰላም ዋርካውያን:

እንግዲህ ቀደም ሲል ቃል በገባሁት መሰረት ለዛሬ የሚሆነንን መነሻ ይዤ መጥቼያለሁ::

ጥያቄ- ለመሆኑ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ-ክርስቲያን አስተምህሮና ቀኖና መሰረት ተቀባይነት የሌላቸው የሩካቤ ስጋ ገጽታዎች አሉ?-

መልስ- አዎን አሉ!!

ጥያቄ-ምን ምን ናቸው?

መልስ-1. ከጋብቻ በፊት የሚፈጸም ሩካቤ
2. በቅዱስ ቁርባን ለተጋቡ ሙሽሮች ከጋብቻ በፊት 2 ቀን እና ከጋብቻ በህዋላ 3 ቀን ባለው ጊዜ ውስጥ የሚፈጸም ሩካቤ
3. ከጋብቻ ውጭ የሚፈጸም ሩካቤ
4. ያለቦታው የሚፈጸም ሩካቤ
5. ያለጊዜው የሚፈጸም ሩካቤ
6. በባል ወይም በሚስት ፍላጎት ብቻ የሚፈጸም ሩካቤ
7. ልጅ ለመውለድ ካለመፈለግ የተነሳ በኮንዶም ወይም በሌላ ወሊድ መቆጣጠሪያ አጋዥነት የሚፈጸም ሩካቤ
8. በአበይት በአላት: በጾምና በሰንበት ቀን የሚፈጸም ሩካቤ
9. በወር አበባ ጊዜ የሚፈጸም ሩካቤ
10. በእርግዝና ጊዜ የሚፈጸም ሩካቤ
11. ባልና ሚስት ፊት ለፊት ተጋጥመው ከሚፈጽሙት ሩካቤ ውጭ በሌሎች አተኛኘት/አቀማመጥ አቅጣጫዎች የሚፈጸም ሩካቤ
12. የወንድ ዘር ከሴቷ ማህጸን ውጭ እንዲፈስ እየተደረገ የሚፈጸም ሩካቤ (ግብረ-አውናን)
13. አፈ-ወሲብ እና በመቀመጫ በኩል የሚደረግ ሩካቤ (oral and anal sex)
14. በተመሳሳይ ጾታ መሀል የሚደረግ ሩካቤ (Homosexuality)
15. ከግኡዝ አካላት ጋር የሚደረግ ሩካቤ (Dildos, vibrators, sex machines, etc.)
16. ከእንስሳት ጋር የሚደረግ ሩካቤ (bestiality)
17. በተቀደሰ ስፍራ (በቤተ-ክርስቲያን ወይም በገዳም ቅጥር ግቢ) የሚፈጸም ሩካቤ
18. ሌሎች ሰዎች እያዩ የሚፈጸም ሩካቤ
19. ራስ ከራስ ጋር የሚፈጸም ሩካቤ (masterbation)
20. የሰውነት አካልን በማቁሰል: በመጉዳት: እጅና እግርን በማሰር ወ ዘ ተ. የሚፈጸም ሩካቤ (BDSM)
:

ጥያቄ- ለምን ይሆን እነዚህ ሁሉ የሩካቤ ስጋ አፈጻጸም ገጽታዎች በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ-ክርስቲያን የሚከለከሉት?

መልስ- የፈጣሪን ቁጣ ስለሚያነሳሱ: ሰውን ከሰውነት ክብር ዝቅ ስለሚያደርጉ: ለቅድስናው ህይወቱ ደንታ እንዳይኖረው ስለሚያደርጉና ለጤናውም ቢሆን ጠቃሚ ስላልሆኑ ነዋ!!

ጥያቄ- ለመሆኑ በቀድሞው ዘመን የነበሩት /በመጽሀፍ ቅዱስ ላይ ታሪካቸው ከተጻፈላቸው ቅዱሳንም ይሁን ገድልና ድርሳናቸው ከተጻፈላቸው አባቶች እናቶች ቅዱሳን መሀል ይህንን ያህል ስለ ሩካቤ ህይወታቸው የሚጠነቀቁ ነበሩ እንዴ?

መልስ- አዎን! በሚገባ

ጥያቄ- እስቲ ከላይ ከተዘረዘሩት የሩካቤ ስጋ ገጽታዎች ጋር በተያያዘ መጽሀፍ ቅዱስና የቤተ-ክርስቲያናችን ቀኖና እንዲሁም የሌሎች ቅዱሳን ታሪክ ምን ይላል?

መልስ- በቀጣዩ ጽሁፌ እመለስበታለሁ::

ቸር ይግጠመን
ብርኃናዊት
ብርኃናዊት
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 3302
Joined: Sat Oct 27, 2007 3:57 am

Postby ቦዚ » Tue Nov 13, 2007 8:59 am

ሰላም ብርሓናዊት እነዚህ 10. በእርግዝና ጊዜ የሚፈጸም ሩካቤ
11. ባልና ሚስት ፊት ለፊት ተጋጥመው ከሚፈጽሙት ሩካቤ ውጭ በሌሎች አተኛኘት /አቀማመጥ አቅጣጫዎች የሚፈጸም ሩካቤ
በኦርቶዶክስ ተዋህዶ እይፈቀዱም መባሉ በጣም ገርሞኛል :!: :!: ለመሆኑ ሁሉም ኦርቶዶክስ ተዋህዶ አማኝ ፖሲስን አይጠቀምም ማለት ነው :?: :?:
ቦዚ
መንገደኛ
መንገደኛ
 
Posts: 1
Joined: Tue Nov 13, 2007 7:32 am

Postby ዲጎኔ » Tue Nov 13, 2007 10:36 am

የክርስቶስ ሰላም ከሁላችን ይሁን
ውድ ብርሀናዊት ከመጽሀፍ ቅዱስ ጋር የሚስማሙትን ሙሉ በሙሉ የምቀበል ስሆን ሌሎቹን በቅዱስ ቃሉ በቆሮንቶስና በእብራዊያን መልክቶች ላይ ለጸሎት ካልሆነ በቀር የወሲብ ፍላጎትን አትከላከሉ መኝታ ቅዱስ ጋብቻ ንጹህ የሚለውን ያልተከተለን በቅዱስ ተሀድሶ መተው እንደሚቻል አበክሬ አሳስባለሁ::በወር አበባ ጊዜና ወሊድ በተቃረበበት ጊዜ ከወሲብ መታቀቡ ለሀይጂን እንጂ ሀይማኖታዊ ዶግማ ሆኖ ሊወሰድ አይገባውም::ግብረሰዶም ከጋብቻ በፊት ወሲብ ልቅ ወሲብና የመሳሰሉትን ግን ያለማወላወል በቁርጠኛነት በቃሉ መቃወም ይቻላል::
ዲጎኔ ሞረቴው ከአንዲት ቅድስት ኦርቶድክስ ተሀድሶ ደብር

ብርኃናዊት wrote:ሰላም ዋርካውያን:
እንግዲህ ቀደም ሲል ቃል በገባሁት መሰረት ለዛሬ የሚሆነንን መነሻ ይዤ መጥቼያለሁ::
ጥያቄ- ለመሆኑ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ-ክርስቲያን አስተምህሮና ቀኖና መሰረት ተቀባይነት የሌላቸው የሩካቤ ስጋ ገጽታዎች አሉ?
መልስ- አዎን አሉ!!
ጥያቄ-ምን ምን ናቸው?
[color=red]ጥያቄ- ለምን ይሆን እነዚህ ሁሉ የሩካቤ ስጋ አፈጻጸም ገጽታዎች በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ-ክርስቲያን የሚከለከሉት?

መልስ- የፈጣሪን ቁጣ ስለሚያነሳሱ: ሰውን ከሰውነት ክብር ዝቅ ስለሚያደርጉ: ለቅድስናው ህይወቱ ደንታ እንዳይኖረው ስለሚያደርጉና ለጤናውም ቢሆን ጠቃሚ ስላልሆኑ ነዋ!!

ጥያቄ- ለመሆኑ በቀድሞው ዘመን የነበሩት /በመጽሀፍ ቅዱስ ላይ ታሪካቸው ከተጻፈላቸው ቅዱሳንም ይሁን ገድልና ድርሳናቸው ከተጻፈላቸው አባቶች እናቶች ቅዱሳን መሀል ይህንን ያህል ስለ ሩካቤ ህይወታቸው የሚጠነቀቁ ነበሩ እንዴ?

መልስ- አዎን! በሚገባ

ጥያቄ- እስቲ ከላይ ከተዘረዘሩት የሩካቤ ስጋ ገጽታዎች ጋር በተያያዘ መጽሀፍ ቅዱስና የቤተ-ክርስቲያናችን ቀኖና እንዲሁም የሌሎች ቅዱሳን ታሪክ ምን ይላል?

መልስ- በቀጣዩ ጽሁፌ እመለስበታለሁ::

ቸር ይግጠመን
ብርኃናዊት
ዲጎኔ
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 4752
Joined: Fri Aug 19, 2005 2:03 am
Location: united states

Postby HAHUHI » Tue Nov 13, 2007 3:05 pm

ሀይ ብርሀናዊት ሰላም ብለናል
የፃፍሻቸውን ነገሮች 90 በ100 ባምንባቸውም 11ኛው ግን ሊገባኝ አልቻለም ምክንያቱም ሰው እንደፈለገዉ እንደሚመቸው ቢያደርግ ማለት sex ቢፈፅም ምንድን ነው ችግሩ. ትንሽ ማብራሪያ ብትሰጭኝ በጣም ደስ ይለኛል.

መልካም ቀን ለሁላችሁ.
HAHUHI
አዲስ
አዲስ
 
Posts: 37
Joined: Tue Oct 23, 2007 4:22 pm
Location: canada

Postby ችሎ_ማደር » Tue Nov 13, 2007 4:29 pm

ብርኃናዊት wrote:ሰላም ዋርካውያን:

መልስ- በቀጣዩ ጽሁፌ እመለስበታለሁ::አስካሁን ድረስ ለምን ብዙው ስው ጠበቅ ያለ የኦርቶዶክስ ተከታይነት አንደሌለው ሣሥብ ነበረ:: አመሰግናለሁ ጎሽ አሁን ገና ገባኝ::

በጣም ከጥቂቶቹ በስትቀር አብዛኛው በዚህ ዘመን ሊሰራ የማይችል ያረጀና ያፈጀ ነው:: ባልና ሚስት አንዳፈጣጠራችው ሁኔታ ፍላጎታቸውን ለማርካት በተለያየ (POSITION) ቢገናኙ ህጥያቱ ለምንድነው::

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ አንደ ካቶሊክ ሊቃውንታት ዘመን የሚያሻሽላቸውን ጉዳዮች አብሮ ማስተካከል ካልቻሉ አብዛኛው ወደ ፔንጤ ማድላቱን አያባስው መሔዱን አንጠራጠር::

* ምን አለ ሚስቴን ሳጣ (MASTERBATE) ባደርግ ክምሽረሙጥ?
* ምን አለ (CONDUM) ባደርግ በማሰወረድ ከመግደል?
* ምን አለ በፈለግነው ቀን ብንገናኝ?
* መመሪያችን መፅሕፍ ቅዱሥ ነው ወይስ ምንድነው?

መነጋገሪያውን አረአስት በጣም ወድጀዋለሁና በርቺ(ታ)
"The difference between stupidity and genius is that genius has its limits." Albert Einstein
ችሎ_ማደር
ጀማሪ ኮትኳች
ጀማሪ ኮትኳች
 
Posts: 53
Joined: Wed Sep 12, 2007 4:16 pm

Postby wendu » Wed Nov 14, 2007 12:00 am

ችሎ ማደር አሥተያየትህን እጋራለሁ :: በተለይ ከመጽሀፍ ቅዱስ ውጭ ያሉ የቤ/ክ ህጎች ይሻሻሉ ማለት logical ነው::
wendu
መንገደኛ
መንገደኛ
 
Posts: 6
Joined: Thu Nov 08, 2007 7:48 pm

Postby ቢሊጮዋ » Wed Nov 14, 2007 2:01 am

ጋብቻ ከትመስረት በሃላ ልጅ ላልመውለድ መከላከያ መጠቅም ሀጥያቱ ምኑ ላይ ነው ?
ቢሊጮዋ
አዲስ
አዲስ
 
Posts: 13
Joined: Sun Jul 16, 2006 3:07 am

Postby sleepless girl » Wed Nov 14, 2007 4:33 am

5. ያለጊዜው የሚፈጸም ሩካቤ
6. በባል ወይም በሚስት ፍላጎት ብቻ የሚፈጸም ሩካቤ
7. ልጅ ለመውለድ ካለመፈለግ የተነሳ በኮንዶም ወይም በሌላ ወሊድ መቆጣጠሪያ አጋዥነት የሚፈጸም ሩካቤ

12. የወንድ ዘር ከሴቷ ማህጸን ውጭ እንዲፈስ እየተደረገ የሚፈጸም ሩካቤ (ግብረ -አውናን )ብርሀናዊት..........በጣም ቁምነገር ያለው ነገር ነው የምታስነብቢን ያለው............
ከዘረዘርሻቸው ውስጥ እነዚህ ከላይ ከጻፍኳቸው በስተቀር በሌሎቹ አምንበታለሁ........."ያለጊዜው የሚፈጸም ሩካቤ" ስትይ ምን ማለትሽ ነው? እንደኔ እንደገባኝ ከሆነ ሴክስ ጊዜ ጠብቆ የሚደረገግ አይመስለኝም.........ወይንም አባባሉን ሚስአንደርስቱድ አድርጌው ይሆናልና እስኪ አብራሪልኝ...............

ሌላው ጥያቄዬ ደግሞ ኮንዶም መጠቀም ሀጢአት ከሆነ ላለማርገዝ ሲባል የወንዱ ዘር ከሴቷ ማህጸን ውጪ ቢፈስ እንዳታረግዝ ይረዳታል........ሀጢአትነቱ ምኑ ላይ ነው? ነው ወይስ ልጅ በላይ በላይ እንድትወልድ ነው የሚፈለገው?................
Nothing is impossible!!
sleepless girl
ዋና ውሃ አጠጪ
ዋና ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1510
Joined: Sun Feb 19, 2006 3:56 am
Location: near u!

Postby ብርኃናዊት » Wed Nov 14, 2007 4:43 am

ሰላም ዋርካውያን:

እንደምናችሁ? አስተያየትና ተሳትፎዋችሁ በጣም አስደስቶኛል:: በርቱ:: ትንሽ ፈተና ቢጤ አሯሩጦኝ ነው ዝም ያልኩት እንጂ አንድ በአንድ ከመጽሀፍ ቅዱስ ጋር እያዛመድን እንተነትናቸዋለን:: በተለይ አጨቃጫቂ የሆኑትን (ለምሳሌ እንደ ወሊድ መቆጣጠሪያ እና እንደ አተኛኘት አቅጣጫዎች ያሉትን):: ነገር ግን መጽሀፍ ቅዱስ ስለ አተኛኘት አቅጣጫ ሳይቀር ቅኔያዊ በሆነ አገላለጽ ተገቢውን ነገር ገልጾልናል:: ምናልባት 'እዚህ ጋር መጽሀፉ እንዲህ ማለቱ ስለ አተኛኘት አቅጣጫ እያወራ ላይሆን ይችላል" ልንል እንችላለን:: የቤተ-ክርስቲያኗ የትርጓሜ ሊቃውንት ግን ስለ ሩካቤ የተነገሩ እንደሆኑ አስረግጠው የሚነግሩን ቃላት አሉ:: ተፈጥሮም የሚያስተምረን ነገር አለ:: ዲያቆን ህብረት የሺጥላ ክርስቲያናዊ ሩካቤን በተመለከተ ከጻፈው ትዳርና ተላጽቆ መጽሀፍ ላይ እና እንዲሁም በግሌ ከማውቃቸው ሌሎች ዋቢዎች ተነስቼ የቻልኩትን ያህል ማብራርያ እሰጣለሁ:: አሁንም ለተሳትፎዋችሁ እግዚአብሔር ይስጥልኝ::

ከመሰናበቴ በፊት ለዛሬ በሚከተለው የችሎ ማደር አስተያየት ላይ ትንሽ ልበል::


እስካሁን ድረስ ለምን ብዙው ስው ጠበቅ ያለ የኦርቶዶክስ ተከታይነት አንደሌለው ሣሥብ ነበረ :: አመሰግናለሁ ጎሽ አሁን ገና ገባኝ ::

በጣም ከጥቂቶቹ በስትቀር አብዛኛው በዚህ ዘመን ሊሰራ የማይችል ያረጀና ያፈጀ ነው ::


እዚህ ጋር ከመጽሀፍ ቅዱስ ውስጥ ስለ ሩካቤ ብቻ ሳይሆን ስለሌሎች ብዙ ብዙ "ያረጁና ያፈጁ" የሚመስሉ ቃለ-እግዚአብሔሮች ማሰብ እንችላለን:: ብዙ የመጽሀፍ ቅዱስ ቃላት በአሁኑ ዘመን ለመፈጸም አስቸጋሪዎች ናቸው:: ሩካቤ ከዚህ የተለየ አይለም:: ለምሳሌ: ምን ያህሎቻችን በዚህ ዘመን የሚከተሉት ቃላት ተፈጻሚነት አላቸው ብለን እናስባለን?

1. "አንዱን ጉንጭህን ሲመታህ ሌላኛው ጉንጭህን ስጠው"
".....ህምምምምም. ያውም በዚህ self-confidence እና assertiveness የሀይማኖት ያህል በገነነበት ዘመን???" ያስብለናል::

2. አይንህ ብታሰናክልህ አውጥተህ ጣላት" "
......... ሆ ሆ ሆ... በገዛ እጄ አካል ጎዶሎ ልሆን? እሱ በድሮው ዘመን ይሰራ ይሆናል:: አሁን ግን ልጄ መማር አለብኝ: ማንበብ አለብኝ: ዘመኑ የሳይንስና ቴክኖሎጂ ነው:.. ከኢንፎርሜሽን መራቅ የለብኝም: ወ ዘ ተ እንላለን:: (በነገራችን ላይ ይህንን ትእዛዝ ቃል በቃል የፈጸመ አባት አለ:: ያም ግብጻዊው ስምዖን ጫማ ሰፊው ነው:: እሱም በድንግልና የሚኖር ድሀ ጫማ ሰፊ ነበረ:: እናም አንዲት ሴት ባቷንና እግሯን እያሳየች ስትፈታተነው አይኑን ጫማ በሚሰፋበት ወስፌ ጎልጉሎ አውጥቶ ጥሎታል:: ይህም ታላቅ ሰማእትነት ሆኖለት በረከት አግኝቷል:: ኍላም የቅድስናው ፍሬ በግብጹ ፓትርያክ ታውቆ በወቅቱ ለነበረው አረማዊ ንጉስ ተራራን እስከማንቀሳቀስ ድረስ ታላቅ ሳይንስና ቴክኖሎጂ የማይሰራው ተአምር ሰርቷል:: ስምዖን በቅድስናው ብዛትና በጸሎቱ ያንቀሳቀሰው ግዙፍ ተራራ በአዲሱ ቦታው ላይ እስካሁን ቆሟል:: አያችሁ የቅድስና ፍሬ?)

3. አብርሀም እንግዳ መቀበልን ልማዱ በማድረጉ አብ ወልድ መንፈስ ቅዱስ በቤቱ በ 3 ሰዎች አምሳል ተገኙ የሚለውን ታሪክ ስንሰማ

"....ሆ ሆ ሆ.. ልጄ አብርሀም የኖረው ድንጋዩ ሁሉ ዳቦ በሆነበት ዘመን ነው:: አሁን ዳቦው ድንጋይ የሆነበት ችጋራም ዘመን ላይ ደርሰናል:: እና በዚህ ዘመን ይሄ አያዋጣም:: saving ባህላችንን ልናዳብር ይገባናል:: ፈረንጆች የሰለጠኑት እንደዚያ ነው::.. እንላለን:: እንጂ ልንፍፈጽመው የምንችለው: ልንፈጽመው የሚገባና ብንፈጽመው በረሀብ ፈንታ በረከት የሚያስገኝልን መሆኑን አናውቅም::

4. ስለዚህ እምነታችሁን በእግዚአብሔር ላይ አድርጉ: የእግዚአብሔርን ጸጋ አትከላከሉ:: እግዚአብሄር ለፈጠረው ፍጡር ካንተ/ካንቺ በላይ ያስባል:: እንደ አውናን ልጅ ላለመውለድ ዘራችሁን መሬት አታፍስሱ: እንደ አህዛብ ደርዝ የሌለው ግንኙነት አታድርጉ: እግዚአብሔርን አያስደስትምና...ስንባል

....ወቸው ጉድ! ደግሞ 12 ልጅ ወልጄ በፌስታል ላንጠለጥላቸው ነው ወይስ ምን ላደርጋቸው ነው? አንዱንም በትክክል ካሳደግሁ ይበቃኛል:: በዚያ ላይ በወጣትነቴ የብዙ ልጆች አባት/እናት ሆኜ መታሰር አልፈልግም: ገና ያላየሁት ብዙ ላይፍ አለ::... እንላለን:: እናም የምንወልዳቸው ልጆች ተጫውተውና አብረው ተካፍለው ያላደጉ: እግዚአብሔር ያልባረካቸው: እጅግ ራስ ወዳዶችና የሀገር ፍቅር የሌላቸው: በዚያ ላይ ሰበበኞችና አሁንም አሁንም የሚታመሙ ቀሽሞች ሆነው እርፍ ይላሏ!! የእግዚአብሔር በረከት በየዋህነትና በእምነት እንጂ በሰው ጥበብና ቀመር አትገኝምና::

እናም እንዲህ እንዲህ አይነት ብዙ ከመንፈሳዊነት ያራቁን የአስተሳሰብ ዘዬዎች ስላሉ እንዲህ አይነት ትምህርት ስንሰማ እንደነግጣለን:: ወይም '..ያረጀ ያፈጀ.." እንለዋለን:: ምክንያቱም ምን ያህል ከመንፈሳዊ ህይወት እንደራቅን ስለሚያሳስቡን ነው:: (በነገራችን ላይ ችሎ ማደር አንተን እየወቀስኩ አይደለም:: ሁላችንም እኔን ጨምሮ በአሁን ሰ'አት የምናስበው እንደዚያ ነው:: ጥሩ ነጥብ አንስተሀል::)

ሌላኛው በአእምሮዋችን ልናኖረው የሚገባን ነጥብ ደግሞ ቤተ-ክርስቲያኗ በህግጋት ብዛት በጣም የሚትጫነን ቢመስለንም በአንዳንድ ነገሮች ላይ ደግሞ እንደተጋቢዎቹ ሁኔታና ነፍስ አባታቸውን በማማከር የሚያገኙት የተለየ መብት አዘጋጅታለች:: እናም "ሙድ ይገባታል":: ለምሳሌ: በጫጉላ ሽርሽር ጾምም ይሁን: ወይም ሰንበትም ይሁን ወይም በአል ይሁን: ምንም ይሁን እስከ 40 ቀናት ድረስ ሙሽሮቹ እንደፈለጉ የመሆን መብት አላቸው:: እና ሶደሬ ሄዳችሁ አይን አይናችሁን ተያዩ አትልም- በአልም ቢሆን ሰንበትም ቢሆን ሻሩትና ይውጣላችሁ- ትላለች እንጂ:: በርግጥ ይህ ህግ የቱ ጋር እንደተጻፈ ለጊዜው አላስታውስም:: ሳገኘው እመለስበታለሁ:: ሌሎችም ሌሎችም መብቶች እንደየአግባብነቱ የሚፈቀዱ አሉ:: እና ለወደፊት እንወያያለን:: stay tuned ነው የሚባለው አይደል?!

ቸር ይግጠመን
ብርኃናዊት
ብርኃናዊት
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 3302
Joined: Sat Oct 27, 2007 3:57 am

Postby እናትዬ » Wed Nov 14, 2007 4:09 pm

ሰላም ብርኃናዊት የአምዱ መከፈት ጥሩ ነው... ብዙ እውቀቶችን ለመገብየት ይረዳል.... እኔ የምጠይቅሽ ጥያቄ የእስልምና እምነት ተከታይ እና የክርስትና እምነት ተከታይ ቢጋቡ ምን ችግር አለው?

አመሰግናለሁ
Image
እናትዬ
ውሃ አጠጪ
ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1286
Joined: Sat Jan 13, 2007 11:21 am
Location: ቀፊራ - ድሬደዋ

Postby ችሎ_ማደር » Wed Nov 14, 2007 6:40 pm

ብርኃናዊት wrote:
እስካሁን ድረስ ለምን ብዙው ስው ጠበቅ ያለ የኦርቶዶክስ ተከታይነት አንደሌለው ሣሥብ ነበረ :: አመሰግናለሁ ጎሽ አሁን ገና ገባኝ ::

በጣም ከጥቂቶቹ በስትቀር አብዛኛው በዚህ ዘመን ሊሰራ የማይችል ያረጀና ያፈጀ ነው ::


እናም እንዲህ እንዲህ አይነት ብዙ ከመንፈሳዊነት ያራቁን የአስተሳሰብ ዘዬዎች ስላሉ እንዲህ አይነት ትምህርት ስንሰማ እንደነግጣለን:: ወይም '..ያረጀ ያፈጀ.." እንለዋለን:: ምክንያቱም ምን ያህል ከመንፈሳዊ ህይወት እንደራቅን ስለሚያሳስቡን ነው:: (በነገራችን ላይ ችሎ ማደር አንተን እየወቀስኩ አይደለም:: ሁላችንም እኔን ጨምሮ በአሁን ሰ'አት የምናስበው እንደዚያ ነው:: ጥሩ ነጥብ አንስተሀል::)
ብርኃናዊት


ብርኃናዊት;

በመጀመሪያ አጅግ በጣም ላመሰግንሽ አወዳለሁ:: ለመጀመሪያ ጊዜ ድንቅ አስተማሪ አና የማብራራት ችሎታ የተሰጠው የሃይማኖት ምሁር በመሆንሽ አከብርሻለሁ::

ነገር ግን ይህን በቆምክበት ሒድ የሆኑትን ለይቶ ማስተካከል የሚያስፈልጋቸውን ሁኔታዎች መሰረቱን ጠብቆ ማስተካከል ነው አንጂ አንዳው ለመንፈስ አባትሕ ተናገር ከተሳሳትክ ብሎ መደምደም 'ጊዜው; ሁኔታውና; ቦታው" አይፈቅድም:: በተለይ አንዳንች ዘመናዊ ትምሕርትን የቀስሙ የመጣውን ሁሉ ተቀብለው አኛንም ተቀበሉ ማለት ባለፈው አንዳልኩት ወደ ሌላ ሃይማኖት ያባርራል::

ሌላ ብዙ የሚያነጋግሩ ልምዳዊ ነገሮች ስላሉ አንድ ባንድ ብንነጋገርባቸውና ሲሆን የሚስተካከሉትን ህሳብ አየሰጠን ብናልፍም; ይሕ አርአስት ከሁሉም ይክብዳል::

ጊዜ ሲኖርሽ ስለሚቀጥሉት በሰፊው አንነጋገር::
* ግብረ ሥጋ ግንኙነት ለመደሰት ነው? ልጅ ለመውለድ ነው? ወይስ ለመደስትና ከፈቀዱና ከተዘጋጁ ለመውለድ ነው?
* ስለ ግበረ ስጋ ግንኙንት (POSITION) ለመሆኑ ባል ከላይ ሚስት ከታች አይነት ነው? ይህ ጥያቄ ከላይኛው ጋራ የተዛመደ ሲሆን ከመልስሽ በኍላ (SOCIAL SCIENCE) ሃይማኖትን ሳይፃረር የሚለውን አቀርባለሁ::

ውድ ብርኃናዊት አግዚአብሔር ይባርክሽ!
"The difference between stupidity and genius is that genius has its limits." Albert Einstein
ችሎ_ማደር
ጀማሪ ኮትኳች
ጀማሪ ኮትኳች
 
Posts: 53
Joined: Wed Sep 12, 2007 4:16 pm

Postby ችሎ_ማደር » Wed Nov 14, 2007 6:41 pm

ብርኃናዊት wrote:
እስካሁን ድረስ ለምን ብዙው ስው ጠበቅ ያለ የኦርቶዶክስ ተከታይነት አንደሌለው ሣሥብ ነበረ :: አመሰግናለሁ ጎሽ አሁን ገና ገባኝ ::

በጣም ከጥቂቶቹ በስትቀር አብዛኛው በዚህ ዘመን ሊሰራ የማይችል ያረጀና ያፈጀ ነው ::


እናም እንዲህ እንዲህ አይነት ብዙ ከመንፈሳዊነት ያራቁን የአስተሳሰብ ዘዬዎች ስላሉ እንዲህ አይነት ትምህርት ስንሰማ እንደነግጣለን:: ወይም '..ያረጀ ያፈጀ.." እንለዋለን:: ምክንያቱም ምን ያህል ከመንፈሳዊ ህይወት እንደራቅን ስለሚያሳስቡን ነው:: (በነገራችን ላይ ችሎ ማደር አንተን እየወቀስኩ አይደለም:: ሁላችንም እኔን ጨምሮ በአሁን ሰ'አት የምናስበው እንደዚያ ነው:: ጥሩ ነጥብ አንስተሀል::)
ብርኃናዊት


ብርኃናዊት;

በመጀመሪያ አጅግ በጣም ላመሰግንሽ አወዳለሁ:: ለመጀመሪያ ጊዜ ድንቅ አስተማሪ አና የማብራራት ችሎታ የተሰጠው የሃይማኖት ምሁር በመሆንሽ አከብርሻለሁ::

ነገር ግን ይህን በቆምክበት ሒድ የሆኑትን ለይቶ ማስተካከል የሚያስፈልጋቸውን ሁኔታዎች መሰረቱን ጠብቆ ማስተካከል ነው አንጂ አንዳው ለመንፈስ አባትሕ ተናገር ከተሳሳትክ ብሎ መደምደም 'ጊዜው; ሁኔታውና; ቦታው" አይፈቅድም:: በተለይ አንዳንች ዘመናዊ ትምሕርትን የቀስሙ የመጣውን ሁሉ ተቀብለው አኛንም ተቀበሉ ማለት ባለፈው አንዳልኩት ወደ ሌላ ሃይማኖት ያባርራል::

ሌላ ብዙ የሚያነጋግሩ ልምዳዊ ነገሮች ስላሉ አንድ ባንድ ብንነጋገርባቸውና ሲሆን የሚስተካከሉትን ህሳብ አየሰጠን ብናልፍም; ይሕ አርአስት ከሁሉም ይክብዳል::

ጊዜ ሲኖርሽ ስለሚቀጥሉት በሰፊው አንነጋገር::
* ግብረ ሥጋ ግንኙነት ለመደሰት ነው? ልጅ ለመውለድ ነው? ወይስ ለመደስትና ከፈቀዱና ከተዘጋጁ ለመውለድ ነው?
* ስለ ግበረ ስጋ ግንኙንት (POSITION) ለመሆኑ ባል ከላይ ሚስት ከታች አይነት ነው? ይህ ጥያቄ ከላይኛው ጋራ የተዛመደ ሲሆን ከመልስሽ በኍላ (SOCIAL SCIENCE) ሃይማኖትን ሳይፃረር የሚለውን አቀርባለሁ::

ውድ ብርኃናዊት አግዚአብሔር ይባርክሽ!
"The difference between stupidity and genius is that genius has its limits." Albert Einstein
ችሎ_ማደር
ጀማሪ ኮትኳች
ጀማሪ ኮትኳች
 
Posts: 53
Joined: Wed Sep 12, 2007 4:16 pm

Postby ሙዝ1 » Thu Nov 15, 2007 12:51 pm

የቁጭ ተላጽቆ, የቁም ተላጽቆ, ከልቢ ተላጽቆ(ዶጊ ስታይል), ማይ ተላጽቆ(ሻወር ዉስጥ), አግባብ አይደሉም ቢባልም ከማድረግ ወደ ሗላ አልልም....
ሙዝ1
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 3128
Joined: Wed Feb 22, 2006 9:25 am

:-)

Postby ደጉ » Thu Nov 15, 2007 10:07 pm

... ብርህናዊት እኔን መቼም ከየ ህይማኖቱ እያማረረ እሚያስወጣኝ ነገር አንዱ ቢኖር ይህው ነው ....:( ደስ ያለኝ ነገር ግን የ ኦርቶዶክስ እምነት የኔን እምነት የሴክስ አጠቃቀም ሳይቃወመው ማለፉ .. :D በሁሉ ተስማምቼ ትንሽ ቅር ያለኝ ግን 20ኛው መከልከሉ ነው .... ስለ ሰሩት ህጢአት ቅጣት በዚህ መልክ ቢሰጣቸው ክፋቱ ምን ላይ ነው...? በነገራችን ላይ 18ኛው ቪዲዮን /በ ዲቪዲ/ ስራዬ ተብሎ የታተመውንም ይመለከታል..ወይስ ሌሎች ሰዎችን ላይፍ በቀዳዳ ማየት...?:D
... መጽህፍ ቅዱስ እሚፈቅደው ፓዝሽን ሚሽነሪ (ቴሌ ታቢ ሴክስ) ብዙ ሳንርቅ ምን ያህል መጥፎ ለመሆኑ ከዲጎኔ የተሻለ ኢግዚቢት እዚህ ማቅረብ እሚቻል አይመስለኝም...ከልቤ ነው አይታወቅም ከፖዝሽኑ ሳይሆን ወይ ከቦታው ይሆናል.....:(
"STUPID IS AS STUPID DOES " :D
ደጉ
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 4412
Joined: Mon Dec 15, 2003 10:39 am
Location: afghanistan

Next

Return to Warka Intimate - ዋርካ ፍቅር

Who is online

Users browsing this forum: No registered users and 6 guests