የኢትዮጵያ ቤ/ክ የጾታ ትምህርት- ማንበብ ለሚፈልግ

The Love Forum (love, relationship) (የኔ ቆንጆ እንተዋወቅ :-)

:-)

Postby ደጉ » Sun Jan 27, 2008 8:39 pm

ብርኃናዊት wrote:....የችግሩን አሳሳቢነት ለመረዳት እውነተኛ ቁርጠኝነቱና ትክክለኝ አተቆርቋሪነቱ ካለህ በPrivate ኢትዮጵያውያን የቤት-እመቤቶች: አባወራዎች: ወጣቶችና ልጆች: እንዲሁም ጎዳና ተዳዳሪዎች ላይ እየተደረገ ያለውን ጥናትና እስካሁን የተደረሰበትን ጆሮ አስይዞ የሚያስጮህ አሳፋሪ ውጤት እነግርሀለሁ::

.....እህታችን እስከምትልኪልኝ እጠብቃለሁ....
ሌላ መረጃ ደግሞ አንተው ራስህ ወረድ ብለህ የጻፍከውን ጽሁፍ አይተህ ራስህን መገምገምና የሌሎች ዋርካውያንን "በዚህ ነገር አትምጡብኝ" የሚለውን ደረቅ አቋም መመልከት በቂ ነው::

...ደረቅ አቁዋም አልሽው ቆንጆ.... እኔማ እንዲለሰልስ ያላደረኩት ጥረት አልነበረም.....ለሁሉም ግን ቆንጆ...እኔ በዚህ አትምጡብኝ ለማለት ሳይሆን..ያለውን እና የተሰማኝን ነው..ለነገሩ እኔ እምነቱ እንደማይመለከተኝ ሆኜ እርቄአለሁ....ውድ ቤተክርስቲያናችን ያንን ፈቀደችም አልፈቀደችም ማድረግ እምፈለገውን አደርጋለሁ.... እማይሆን ቢሆን ኖሮ እኮ ተፈጥሮ ነገሮችን ባላመቻቸች ነበር...ከላይ እግዚአብሄርን በስራው እሚያሙ ሰዎች የጻፉትን አይቼአለሁ...ለምሳሌ አፈ-ጉባኤ... እርግጠኛ ነኝ አፈ ጉባኤ ይሄን የመስራት እድል ቢያጋጥመው የት ጋ አድርጎ እንደሚሰራው አላውቅም... :lol: ከዛ ውጪ ግን ከላይ ያነሱዋቸው ነጥቦች አሉ....አንቺም እንዲህ ብለሻል...
በሙሉ በመጽሀፍ ቅዱስ የተጻፈው እኮ ኃጥያቱ ሳይሆን መከላከያ መንገዱና ፈውሱ ነው :: እነሱም "ንስሀ " እና "ህግጋተ -እግዚአብሄርን መጠበቅ " ይባላሉ :: ዳዊት በአብዛኛው መዝሙሮቹ የጻፈው ምን ያህል የሰው ሚስት በመተኛት : በመግደል : እና በሌሎችን ኃጥያቶች ምክንያት እንደታወከና እንዳለቀሰ ከእግዚአብሔር ምህረትን ለማግኘት ምን ያህል እንደለመነ ነው :: ጠቢቡ ሶሎሞንስ "ሁሉ ከንቱ ነው " በማለት ከ 1000 ከሚሆኑ ሴቶች ጋር የፈለገውን ለማድረግ እንደመቻሉና ሀብትና ስልጣን የሞሉት ቢሆንም ከክርስቶስ በቀር ምንም ደስታ እንደሌለ በመግለጽ በፍጹም የንስሀ ቃና መጽሀፈ -መክብብን እንደጻፈስ አላስተዋልክምን...
እኔ ደጉ እንደ ዳዊት መዝሙር እንደ ሰለሞን መጽህፍ መጻፍ ባልችልም...ማድረግ እምችለውን ልክ እንደ እነሱ አድርጌ መጨረሻ ላይ ዜማም ሆነ መጽህፍ በሰው አጽፌ ንስህ ብገባስ...? መቼም ይቅርታን አልነፈገም.. :D
ፌዘኛ ሰው ግን ትመስላለህ::

ፊቴን አይተሽ ነው...?

... ነገር ግን ከሩካቤ በኍላ ለ 3 ሰአት ያህል ሰውነት እረፍት የማይሰጠው ከሆነ ከጊዜ በኍላ ችግር የሚያመጣ መሆኑን የሚያትት ጽሁፍ ነው::

...ይሄ እምትይው አይነት እኮ ሴክስ ሳይሆን የቀን ስራ መሆን አለበት....እንዴ አንቺ አላጋጠመሽ ይሆናል እንጂ ትንሽ ጭሮ እሚጨርሰውም 3 ሰአት እረፍት...? አይበዛበትም ትያለሽ....? :wink:
...እና ሰውነቴ እንደፕላስቲክ ይሳባል ላልከው- አዎን! አደንዛዥ እጽ የሚጠቀሙ አትሌቶችም "ዕጽ በደንብ ያስሮጠኛል" ይላሉ:: ችግሩ የሚመጣው በኍላ ጉበት ሲነካ ነው::

....ቆንጆ ከ አደንዛዥ እስት ጋር እንኩዋን ምንም እሚያገናኝ ነገር የለውም..ካለው አንቺም ችግር ውስጥ ነሽ እህታችን ...;-) መቼም ሴክስ ማድረግ በጉበት እና በመሳሰሉት ላይ ችግር ይፈጥራል እምትይ ከሆነ...ቁጭ ብዬ ልስማሽ.. :D ለመሆኑ ትዳር ምናምን አለሽ...?
ይሄ ያሁኑ የኛ ትውልድም 24 ሰአት ስለዝሙት እያለመ ልብሱን በዘር ጭቃ እየለወሰ ትንፋሽ አጥሮት ሲሽመደመድ እየኖረ 40 አመት እንኳ ሳይሞላው የሚሞት ቀሽማዳ ትውልድ የሆነበት እንዱ ምክንያት ይሄ ሊሆን ይችላል::

.... እህታችን እዚህ ላይ ልንጣላ ነው...ዘርን እሚያክል ክብር ነገር ጭቃ ትያለሽ... :D ለሱ ከሚጋደሉት አንድዋ አንቺ አይደለሽ....? ደግነቱ እኔ 78 ነኝ ግን እንዳንቺ ህሳብ ቢሆን እኔ ገና ድሮ ሞቻለሁ... :shock:
የሚገርመው ደግሞ "ለማግባት እድሜዬ አልደረሰም: ገና ልጅ ነኝ" እያለ የሚያቀርበው የምክንያት መአት ነው:: አጉል ተግደርዳሪ!! ቀጣፊ ትውልድ!!

...አንቺን ያናደደሽ ነገር ባይገባኝም....እኔ በዚህ መልክ ልንገርሽ....እድሜዬ አልድረሰም እሚለው ወንድ ከሆነ..ትክክል ነው:: ሰት ልጅ በ 17 አመትዋ በደንብ የበሰለች ስትሆን ወንድ ልጅ በተመሳሳይ እድሜ ገና ስለ ኩዋስ ነው እሚያስበው....ለዚህም ይመስለኛል በሞዴሉ አለም ሴቶች ከ 16 እስከ አስራ ሰባት ባለው እድሜያቸው ተመልምለው በ 22 አመታቸው ጡረታ እሚወጡት..ያ ማለት እኮ 66 አመታቸው ነው ማለት ነው... :wink:
እንግዲያው ስትሞት ሳጥንህን ሰፋ አድርገህ ለስጋህ ሌሎች ክፍሎች አሰራለት:: ከምድር በታች ካንዱ ክፍል ወዳንዱ እየተዘዋወርክ እንድትኖር:: ፌዘኛ!!

...አብረሺኝ ትመጫለሽ...? ባለ 3 ክፍል እንዳደርገው.... :wink:
ከነፍሳቸው ሳይሆን ከስጋቸው ጋር ለመኖር እቅድ ላወጡ ሰዎች የሚሆን ምንም መልስ የለኝምና አታልፋኝ!!
ብርኃናዊት

.... እንዴ! እንዲህማ አትማረሪ ... ጀርባው እስኪላጥ የሰራ ሆዱ እስኪወጠር ይበላል ይባል የለ....ካለፋሽ እኮ የድካምሽን ዋጋ አታገኚም.. :wink: [/quote]
"STUPID IS AS STUPID DOES " :D
ደጉ
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 4413
Joined: Mon Dec 15, 2003 10:39 am
Location: afghanistan

Postby ብርኃናዊት » Sun Feb 10, 2008 6:36 pm

እንደምን ከረማችሁ የዚህ ቤት ተሳታፊዎች:

ጡሙሶ ዋርካ ጄኔራል ላይ ሰሞኑን ብዙ ጊዜ ያሳለፍን በመሆኑ ወደዚህ መጥተን ይህን ጠቃሚ ውይይት ሳንቀጥል ቀርተናል:: ቢሆንም አሁንም ለመቀጠል እንችላለን በሚል ተስፋ ካቆምኩበት እቀጥላለሁ::

ጡሙሶ እንደጻፈው:

ለምን ወሊድ መቆጣጠሪያ አንጠቀምም ?? ለሚለው

ሳይንስ በሕይወታችን ብዙ ጥሩ ነገር እንዳደረገ ባይካድም እንኩዋ ጉዳትም ሳያስከትልብን አይቀርም ;; ከአርስታችን ጋር የሚሄድ ለመጥቀስ ;

1. ወደ መረን የለቀቀ ስድነት መርቶናል ;; ምክንያቱም ወሊድ መቆጣጠሪያ ክኒን ትወስዳለች : ከዚያ ከማንም ጋር መጋደም ;; ወንዱም ኮንዶም እየተጠቀም መጋደም

2. ብዙ ሴቶች እህቶቻችንን ወሊድ መቆጣጠሪያ እንዳይወልዱ እንዳደረጋቸው ደግሞ ያለመዘንጋት

ስለዚ ሳይንስ ጥሩም መጥፎም ጥሩም ጎድን አለው ::

በሳይንስ ከመማራችን በፊት እግዚ /ር ሁሉን አዘጋጅቶታል ;; ይሄም ባህርያዊ ወሊድ መቆጣጠርያ ;; ሴት ልጅ በ 1 ወር ውስጥ መውለድ የምትችልባቸው ቀኖች ከ 8 አያልፉም ;; 22 ቀኖች መውለድ አትችልም ;; እሺ ለጥንቃቄና የወንዱ ዘር በሴትዋ ማህጸን ውስጥ ሁለት ቀን በህይወት የመኖር እድል ስላለው ብለን ከፊትና ከሁዋላ ሁለት ሁለት ቀኖች እንጨምርበት 18 ቀኖች ያለምንም መጠራጠር አትወልድም ;; ሴክስ ማድረግም ይቻላል ;; ስለዚህ እግዚ /ር ከምጀመርያ አዘጋጅቶታል ;; ስለዚህ ለባልና ለሚስት በወር 15 ቀን በቂ ሆኖ አይታያችሁም ;; በሁዋላ ደግሞ ያለምንም ችግር ; ማለት ከኪኒን ከሚመጣ አሉታዊ ጎን ነጻ ነው የምትሆነው ;;

ለምሳሌ አንድ የ 25 ዓመት ልጃ ገረድ ዓመት ዓመት ብትወልድ 15 ልጅ የመውለድ ችሎታ ቢኖራትም እንኩዋ እግዚር ግን የሰው ነገር ስለሚረዳው መከላከያውንም አድርጎላታል ;; ስለዚህ ሳይንስን ብቻ ሳይሆን እግዚ /ርንም መስማት ያስፈልጋል ;;

በተጨማሪ ደግሞ በክርስትና ሃይማኖት ሴክስ የራሱ ዓላማ አለው ;; መጀመርያ የእግዚ /ር ስራ ለመቀጠል (ልጅ መውለድ ነው );; ሆን ተብሎ ልጅ ላለመውለድ ተብሎ በወሊድ መቆጣጠርያ እየተጠቀሙ የሚደረግ ሀጢአት ነው ;; አቅምን አውቆ የእግዚ /ር መደብ ሳይቃወሙ መፈጸም ግን ሐጢአት አይደለም ;; ምክንያቱም በተፈጥሮ የተደረገ ነገር ሀጢአት አይድለም ;;

ለምሳሌ : ሁለት ባልና ሚስት <በተለይ ውጪ የሚኖሩ > ልጅ ማሳደግ ትንሽ ከበድ ስለሚል : ይዞታቸውን አይተው ከተወሰነ ዓመት በሁዋል እንወልዳለን ቢሉ ; ጊዜው እስከሚደርስ ድረስ እንደባልና ሚስት ባህርያዊ የመከላከያ ዘዴ እየተጠቀሙ ቢፈጽሙ ሐጢአት የሚያስብለው ነገር የለም ;; ከእግዚር መደብ አልወጡም ;; በቂ መተዳደርያ የሌላቸውን ባልና ሚስት ልጅ የግድ መውለድ አለባችሁ ብሎ ማስቸገር በችግር ላይ ችግር መጥራት ነው ;; ሐጢአት የሚያስብለው ግን እየቻሉ ሆን ብሎ ለመውለድ አለመፈለግ ነው ;;

ከጋብቻ በፊት የሚደረግ ማንኛውም ሴክስ ግን ሐጢአት ነው ;;

ቸር ሰንብቱ


እርግዝና መቆጣጠሪያን አስመልክቶ የጻፍከውን ይህን አሳብ በአመዛኙ እስማማበታለሁ:: ወሊድ መከላከያ ብዙ ኢ-ክርስቲያናዊ የሆኑ ነገሮችን እንድንፈጽም መንገድ ከፍቷል: የብዙ እናቶችን ጤና አዛብቷል: የሰውና የእግዚአብሔርን ፈቃድ በማለያየት አንዳንዶችን ለቅስፈት አብቅቷል (ለምሳሌ ለወንድሙ ሚስት ልጅ እንዲተካ ከሟች ወንድሙ ሚስት ጋር እንዲተኛ ህጉ ያዘዘው አውናን ልጅ ላለመውለድ በሚል እሳቤ ዘሩን ከሚስቱ ማህጸን ውጭ ሲያፈስ እግዚአብሄር በዚህ አዝኖ ቀስፎታል)::

ወሊድ መቆጣጠሪያን በአዎንታዊ መልክ ስናየው ደግሞ ጡሙሶ እንዳለው ኢኮኖሚያዊ ብቃቱ ሳይኖራቸው ልጅ ለመውለድ ላልፈለጉ ሰዎች ጥሩ መጠለያ ሆኗል::

ነገር ግን አሁንም በርዕሳችን እንደተመለከትነው ወሊድ መቆጣጠሪያን ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን አስተምህሮ አንጻር ነውና የምናየው እኛን ከተመቸንና ኑሮዋችንን ካደላደለ ምን ጨነቀን ማለት አንችልም:: ቤተክርስቲያኗ ወሊድ መከላከያ ከእግዚአብሔር ይልቅ የሰው ፈቃድ በሰው ህይወት ውስጥ እንዲሰለጥን ያደርጋል የሚል ጥብቅ ስጋት አላት:: ቤተክርስቲያን ሰውና እግዚአብሔርን ማገናኘትና የእግዚአብሄር ፈቃድ ከሰው ፈቃድ እንደሚበልጥ ማሳየት ነውና የሚጠበቅባት ሁሌም ለእግዚአብሔር ፈቃድ ታደላለች::

ነገር ግን ባሁኑ ወቅት ይህን ለመተግበር ጨርሶ የማይቻል እየመሰለ መጥቷል:: ማለትም ብዙዎች ያለምንም ወሊድ መቆጣጠሪያ የመጣውን ሁሉ በእግዚአብሔር ጸጋነት ለመቀበል መቻላቸውን ይጠራጠራሉ:: ይህ ከብዙ የተጠላለፈ የአለማችን ኢኮኖሚያዊ: ማህበራዊና ፖለቲካዊ አካሄድ ጋር የተሳሰረና በቀላሉ እንደዝሙት ወይም እንደሌላ ኃጥያት በአንድ ሰው የግል ጥረት ብቻ ሊታገሉት የሚችሉት ችግር አይደለም:: የክርስቲያኖችን ታላቅ መስዋዕትነት የሚጠይቅ ጉዳይ ነው::

በዚህ ጉዳይ ጠለቅ ያለ ጽሁፍ ከመጻፌ በፊት ዋርካውያን በሚከተለው ጥያቄ ዙሪያ አስተያየት ቢሰጡ ደስ ይለኛል::

እግዚአብሔር "ብዙ ተባዙ ምድርንም ሙሏት" ብሎናል:: ይህ ትዕዛዝ የእግዚአብሔር ቃል ነው:: አልተሻረም:: አላለፈም:: ያም ማለት የዛሬ 3700 አመት አካባቢ የታዘዝነው "አትስረቅ" የሚለው ህግ አሁንም እንደሚሰራው ሁሉ ያኔ የተናገረው "ብዙ ተባዙ ምድርንም ሙሏት" ትዕዛዝም አሁንም ህያው ነው ማለት ነው::

እናም ጥያቄዬ: "ለመሆኑ ምድር ሞልታለች (የሰው ልጆችን መሰረታዊ ፍላጎት ማሟላት የምትችልበት ሀይል ተሟጧል/አልቃለች/?)" የሚል ይሆናል::

ምን ትላላችሁ?
ብርኃናዊት
ብርኃናዊት
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 3302
Joined: Sat Oct 27, 2007 3:57 am

Postby ደጉ » Sun Feb 10, 2008 8:19 pm

ብርኃናዊት wrote:..... (ለምሳሌ ለወንድሙ ሚስት ልጅ እንዲተካ ከሟች ወንድሙ ሚስት ጋር እንዲተኛ ህጉ ያዘዘው አውናን ልጅ ላለመውለድ በሚል እሳቤ ዘሩን ከሚስቱ ማህጸን ውጭ ሲያፈስ እግዚአብሄር በዚህ አዝኖ ቀስፎታል)::.....

.... ተኝተው ሚያደርጉትን ሁሉ እግዚአብሄር ያያቸው ነበር.. :shock: :shock: :shock: ሁልጊዜ እንደዛ እሚያይ ከሆነ እኔ እንደዛሬ አፍሬ አላውቅም... :( እሱ ግን በሳቅ እሚሞት ይመስለኛል ሳስበው.. :D
"STUPID IS AS STUPID DOES " :D
ደጉ
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 4413
Joined: Mon Dec 15, 2003 10:39 am
Location: afghanistan

Postby ብርኃናዊት » Wed Jul 23, 2008 12:41 am

ዋርካ ፍቅር የነበረችኝ አንድ ቤት ይህች ብቻ ነበረች::

የመጨረቻዋን ጥያቄ የሚሞክራት ጠፍቶ በዚያው ደርቃ ቆማለች:: ጥያቄዋ "በእውኑ ምድር ሞልታለች ወይ?" የምትል ናት::

ከዚህ ጋር አብሮ አንድ ሰው "በዘመናችን የህዝብ ቁጥር አሳሳቢ የሆነበት ምክንያት እውነት ብዙ ሰዎች ስላሉ ነው ወይስ ብዙ ገብጋባ ሰዎች ስላሉ ነው?" የሚለውን ጥያቄ ራሱንና ሌላውን በመጠየቅ ብዙ ሊመራመር ይችላል!!

ደህና ሰንብቱ ዋርካ ፍቅሮች!!

ብርኃናዊት
ብርኃናዊት
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 3302
Joined: Sat Oct 27, 2007 3:57 am

ከለላ ሐይማኖት ጋር

Postby ሰላምለኩሉኩሙ » Sun Oct 21, 2012 10:15 pm

እናትዬ wrote:ሰላም ብርኃናዊት የአምዱ መከፈት ጥሩ ነው... ብዙ እውቀቶችን ለመገብየት ይረዳል.... እኔ የምጠይቅሽ ጥያቄ የእስልምና እምነት ተከታይ እና የክርስትና እምነት ተከታይ ቢጋቡ ምን ችግር አለው?

አመሰግናለሁ

ዉድ እናትዬ:
ከስርአተ ቤተ ክርስትያን ያነበብኩትን ላካፍል::
በሀይማኖት የማይመሳሰሉ ወንድ እና ሴት መጋባት እንደሌለባቸዉ ተከልክሏል:/ዘዳ. 7 ቁ 3-4/ ነገር ግን ወንድ የኦርቶዶክስ ተዋህዶ እምነት ተከታይ ሆኖ ሴትዋ የሌላ እምነት ተከታይ ብትሆን; የኦርቶዶክስ ተዋህዶ እምነት ተከታይ እንድትሆን አድርጎ ማግባት ይችላል::ሴትዋም እንዲሁ ወደ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ሀይማኖት መልሳ ማግባት ይገባታል:: /1 ቆሮ.7 ቁ 12-17; ፍት.ነገ.24: 912-915/
ለተጨማሪ ማብራሪያ ይህን መጽሀፍ ይመልከቱ: "ስርአተ-ቤተ ክርስትያን" በሊቀ ካህናት ክንፈ ገብርኤል አልታየ [/url]
for all the good reasons
ሰላምለኩሉኩሙ
መንገደኛ
መንገደኛ
 
Posts: 1
Joined: Sun Oct 21, 2012 9:39 pm

Postby ጉድ ታይም » Wed Nov 28, 2012 10:05 pm

ይሄን ትሬድ ከመጀመርያ እስከ መጨረሻው ቃል በቃል ግማሽ ቀን ሰውቼ አንበብኩት:: ቀላል ያስፈራል?? በተለይ እንደኔ አይነቱ ባለጌ አንድዬ ይቅር ካላለን ቦታ የለንም :( ስላካፈልሽን ስላስፈራራሽንም :oops: ጭምር ምስጋናዉ ይ ደረስሽ እህት ብርኃናዊት
ብርኃናዊት wrote:ሰላም ዋርካውያን:

እንግዲህ ቀደም ሲል ቃል በገባሁት መሰረት ለዛሬ የሚሆነንን መነሻ ይዤ መጥቼያለሁ::

ጥያቄ- ለመሆኑ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ-ክርስቲያን አስተምህሮና ቀኖና መሰረት ተቀባይነት የሌላቸው የሩካቤ ስጋ ገጽታዎች አሉ?-

መልስ- አዎን አሉ!!

ጥያቄ-ምን ምን ናቸው?

መልስ-1. ከጋብቻ በፊት የሚፈጸም ሩካቤ
2. በቅዱስ ቁርባን ለተጋቡ ሙሽሮች ከጋብቻ በፊት 2 ቀን እና ከጋብቻ በህዋላ 3 ቀን ባለው ጊዜ ውስጥ የሚፈጸም ሩካቤ
3. ከጋብቻ ውጭ የሚፈጸም ሩካቤ
4. ያለቦታው የሚፈጸም ሩካቤ
5. ያለጊዜው የሚፈጸም ሩካቤ
6. በባል ወይም በሚስት ፍላጎት ብቻ የሚፈጸም ሩካቤ
7. ልጅ ለመውለድ ካለመፈለግ የተነሳ በኮንዶም ወይም በሌላ ወሊድ መቆጣጠሪያ አጋዥነት የሚፈጸም ሩካቤ
8. በአበይት በአላት: በጾምና በሰንበት ቀን የሚፈጸም ሩካቤ
9. በወር አበባ ጊዜ የሚፈጸም ሩካቤ
10. በእርግዝና ጊዜ የሚፈጸም ሩካቤ
11. ባልና ሚስት ፊት ለፊት ተጋጥመው ከሚፈጽሙት ሩካቤ ውጭ በሌሎች አተኛኘት/አቀማመጥ አቅጣጫዎች የሚፈጸም ሩካቤ
12. የወንድ ዘር ከሴቷ ማህጸን ውጭ እንዲፈስ እየተደረገ የሚፈጸም ሩካቤ (ግብረ-አውናን)
13. አፈ-ወሲብ እና በመቀመጫ በኩል የሚደረግ ሩካቤ (oral and anal sex)
14. በተመሳሳይ ጾታ መሀል የሚደረግ ሩካቤ (Homosexuality)
15. ከግኡዝ አካላት ጋር የሚደረግ ሩካቤ (Dildos, vibrators, sex machines, etc.)
16. ከእንስሳት ጋር የሚደረግ ሩካቤ (bestiality)
17. በተቀደሰ ስፍራ (በቤተ-ክርስቲያን ወይም በገዳም ቅጥር ግቢ) የሚፈጸም ሩካቤ
18. ሌሎች ሰዎች እያዩ የሚፈጸም ሩካቤ
19. ራስ ከራስ ጋር የሚፈጸም ሩካቤ (masterbation)
20. የሰውነት አካልን በማቁሰል: በመጉዳት: እጅና እግርን በማሰር ወ ዘ ተ. የሚፈጸም ሩካቤ (BDSM)
:

ጥያቄ- ለምን ይሆን እነዚህ ሁሉ የሩካቤ ስጋ አፈጻጸም ገጽታዎች በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ-ክርስቲያን የሚከለከሉት?

መልስ- የፈጣሪን ቁጣ ስለሚያነሳሱ: ሰውን ከሰውነት ክብር ዝቅ ስለሚያደርጉ: ለቅድስናው ህይወቱ ደንታ እንዳይኖረው ስለሚያደርጉና ለጤናውም ቢሆን ጠቃሚ ስላልሆኑ ነዋ!!

ጥያቄ- ለመሆኑ በቀድሞው ዘመን የነበሩት /በመጽሀፍ ቅዱስ ላይ ታሪካቸው ከተጻፈላቸው ቅዱሳንም ይሁን ገድልና ድርሳናቸው ከተጻፈላቸው አባቶች እናቶች ቅዱሳን መሀል ይህንን ያህል ስለ ሩካቤ ህይወታቸው የሚጠነቀቁ ነበሩ እንዴ?

መልስ- አዎን! በሚገባ

ጥያቄ- እስቲ ከላይ ከተዘረዘሩት የሩካቤ ስጋ ገጽታዎች ጋር በተያያዘ መጽሀፍ ቅዱስና የቤተ-ክርስቲያናችን ቀኖና እንዲሁም የሌሎች ቅዱሳን ታሪክ ምን ይላል?

መልስ- በቀጣዩ ጽሁፌ እመለስበታለሁ::

ቸር ይግጠመን
ብርኃናዊት
ጉድ ታይም
አዲስ
አዲስ
 
Posts: 14
Joined: Fri Nov 12, 2010 11:19 pm
Location: Europe

Previous

Return to Warka Intimate - ዋርካ ፍቅር

Who is online

Users browsing this forum: No registered users and 2 guests