የኢትዮጵያ ቤ/ክ የጾታ ትምህርት- ማንበብ ለሚፈልግ

The Love Forum (love, relationship) (የኔ ቆንጆ እንተዋወቅ :-)

Postby ትትና » Sun Nov 18, 2007 9:22 am

ድንቅ ትምህርት ነው! እህታችን ብርሀናዊት ቶሎ ፈተናሽ አልቆ ተመልሰሽ ለያንዳንዱ ጥሩ ማብራሪያ እንደምትሰጪበትተስፋ አደርጋለሁ!!

ችሎ ማደር:- የቤተክርስቲያን ነገር እኔን እንደገባኝ ከሆነ ጊዜና ወቅት ጠብቃ የእግዚአብሔርን ቃል ማጣመም መብቷ አይመስለኝም:: ሀጢያት ባደገ ቁጥር ሰዎች ከቤተክርስቲያን እንዳይወጡ የቲፎዞ ስራ መስራት ያለባት አልመሰለኝም:: ጆሮ ያለው ይስማ ብላ ከመናገር በቀር.... ደሞ የእግዚአብሄር ቃል አያረጅም አያፈጅም! ያለ የነበረ የሚኖር ነውና ከለወጠውም እሱ ራሱ ያደርገዋል ልክ አዲስ ኪዳን ላይ ብዙ የብሉይ ስራቶች እንደተቀየሩ::
በሌሎች ሀይማኖቶች:- አንዴ የሰማሁትን ልንገርህ ለምሳሌ:- ሰውየው አንደኛው የዩናይትድ ቸርች ስራ አስፈጻሚ ነገር ነው (ኮሚቴ) ሲያጫውተኝ ስብሰባ አለን ለብዙ ጊዜ የተሰበሰብንበት ነው አከራካሪ ሆኖ እስካሁን መወሰን አቃተን አሁን ግን የመጨረሻ ነው አለኝ:: ስለምንድነው ስብሰባው ስለው ስለ አንዳይነት ጾታ ጋብቻ አለ:: ገና እንደመጣሁ ነበርና ክው አልኩ:: ምን ልትሉ ነው የምትሰበሰቡት ስለው:: በቤተክርስቲያናችን ልናጸድቀው ብሎኝ ቁጭ:: ቄሱ ምን ይላሉ ስለው? ምን አገባቸው! እኛ ኮሚቴዎች ከወሰንን......... ወይ ጉድ ብዬ ዝም አልኩ:: እና መጽሀፍ ቅዱስ ነው ወይስ የዘመኑ ሁኔታ የሚወስነው?
ትትና
ውሃ አጠጪ
ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1253
Joined: Wed Feb 23, 2005 11:26 am
Location: united states

Postby ፊሊፖስ » Sun Nov 18, 2007 6:36 pm

ግሩም ትምህርት:: እንደገባኝ ከሆነ ብርሃናዊት ከወገባችን በታች ባለው ሳይሆን ካንገታችን በላይ ባለው እናሰብ አውሬዎች አይደለንም ማለትዋ ይሆን? ትክክል ነው:: ግኑኝነት ያለፍቅር ዋጋ የለውም::
A QuEstion oF BalAnCe

Image
ፊሊፖስ
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 123
Joined: Thu Nov 08, 2007 12:16 pm

Postby ደባልቄ » Mon Nov 19, 2007 1:14 am

ጥያቄ - ለመሆኑ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ -ክርስቲያን አስተምህሮና ቀኖና መሰረት ተቀባይነት የሌላቸው የሩካቤ ስጋ ገጽታዎች አሉ ?-

መልስ - አዎን አሉ !!

ጥያቄ -ምን ምን ናቸው ?

መልስ -1. ከጋብቻ በፊት የሚፈጸም ሩካቤ
2. በቅዱስ ቁርባን ለተጋቡ ሙሽሮች ከጋብቻ በፊት 2 ቀን እና ከጋብቻ በህዋላ 3 ቀን ባለው ጊዜ ውስጥ የሚፈጸም ሩካቤ
3. ከጋብቻ ውጭ የሚፈጸም ሩካቤ
4. ያለቦታው የሚፈጸም ሩካቤ
5. ያለጊዜው የሚፈጸም ሩካቤ
6. በባል ወይም በሚስት ፍላጎት ብቻ የሚፈጸም ሩካቤ
7. ልጅ ለመውለድ ካለመፈለግ የተነሳ በኮንዶም ወይም በሌላ ወሊድ መቆጣጠሪያ አጋዥነት የሚፈጸም ሩካቤ
8. በአበይት በአላት : በጾምና በሰንበት ቀን የሚፈጸም ሩካቤ
9. በወር አበባ ጊዜ የሚፈጸም ሩካቤ
10. በእርግዝና ጊዜ የሚፈጸም ሩካቤ
11. ባልና ሚስት ፊት ለፊት ተጋጥመው ከሚፈጽሙት ሩካቤ ውጭ በሌሎች አተኛኘት /አቀማመጥ አቅጣጫዎች የሚፈጸም ሩካቤ
12. የወንድ ዘር ከሴቷ ማህጸን ውጭ እንዲፈስ እየተደረገ የሚፈጸም ሩካቤ (ግብረ -አውናን )
13. አፈ -ወሲብ እና በመቀመጫ በኩል የሚደረግ ሩካቤ (oral and anal sex)
14. በተመሳሳይ ጾታ መሀል የሚደረግ ሩካቤ (Homosexuality)
15. ከግኡዝ አካላት ጋር የሚደረግ ሩካቤ (Dildos, vibrators, sex machines, etc.)
16. ከእንስሳት ጋር የሚደረግ ሩካቤ (bestiality)
17. በተቀደሰ ስፍራ (በቤተ -ክርስቲያን ወይም በገዳም ቅጥር ግቢ ) የሚፈጸም ሩካቤ
18. ሌሎች ሰዎች እያዩ የሚፈጸም ሩካቤ
19. ራስ ከራስ ጋር የሚፈጸም ሩካቤ (masterbation)
20. የሰውነት አካልን በማቁሰል : በመጉዳት : እጅና እግርን በማሰር ወ ዘ ተ . የሚፈጸም ሩካቤ (BDSM):

ጥያቄ - ለምን ይሆን እነዚህ ሁሉ የሩካቤ ስጋ አፈጻጸም ገጽታዎች በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ -ክርስቲያን የሚከለከሉት ?

መልስ - የፈጣሪን ቁጣ ስለሚያነሳሱ : ሰውን ከሰውነት ክብር ዝቅ ስለሚያደርጉ : ለቅድስናው ህይወቱ ደንታ እንዳይኖረው ስለሚያደርጉና ለጤናውም ቢሆን ጠቃሚ ስላልሆኑ ነዋ !!


እና የኦርቶዶክስ ሀይማኖት እንዲህ ያዛል ?

እኔ ዝም ብዬ ኦርቶዶክስ ነኝ እንጅ : ብዙ ጣጣ አላቅም
እንዲህ አስቸጋሪ ግን አይመስለኝም

ለምሳሌ:

2. በቅዱስ ቁርባን ለተጋቡ ሙሽሮች ከጋብቻ በፊት 2 ቀን እና ከጋብቻ በህዋላ 3 ቀን ባለው ጊዜ ውስጥ የሚፈጸም ሩካቤ


እኔ ደግም አንድ የበተ ክርስቲና ሰርግ ላይ : አንድ ቄስ ሲያስተምሩ የሰማሁት

በፊት አንድ 1 በኋላ 1 በድምሩ ሶስት ቀን ሲባል ነው :: የአንቺው ደግሞ አዲስ ነው : ምናልባት ነገ ደግሞ ሌላ ቦታ ሌላ ቁጥር እንሰማ ይሆናል :: የመጣፍ ቅዱስ ማስረጃ የሌለው ነገር ግራ ያጋባል ::

4. ያለቦታው የሚፈጸም ሩካቤ


ይህም ግልጥ አይደለም ምናልባትም ከዚህ

7. በተቀደሰ ስፍራ (በቤተ -ክርስቲያን ወይም በገዳም ቅጥር ግቢ ) የሚፈጸም ሩካቤ


ከሚለው ጋር የሚስማማ ከሆነ ስቡቅ ነው :: ወይም ይብራራ ::

[/quote]5. ያለጊዜው የሚፈጸም ሩካቤ

ይህምቢሆን ግልጥ ያለ መገር አይደለም

[code]9. በወር አበባ ጊዜ የሚፈጸም ሩካቤ
10. በእርግዝና ጊዜ የሚፈጸም ሩካቤ

የሚለውን ለመጠቆም ከሆነ ድግግሞሽ ሆአልና ቁጥሩ እንደገና ይስተካከል

6. በባል ወይም በሚስት ፍላጎት ብቻ የሚፈጸም ሩካቤ

እኔ የሰማሁት ደግሞ ባልም ሚስትም ቢጠያየቁ (አንደኛው ባይፈልግም) እምቢ መባባል የለብቸውም ሲባል ነው ::
ሲጠይቅ እምቢ ከተባለማ ትኩሳቱን ላማብረድ ወደ ሌላ መከጀሉ አይቀሬ ነውና ሰውን ማባለግ ነው ::

11. ባልና ሚስት ፊት ለፊት ተጋጥመው ከሚፈጽሙት ሩካቤ ውጭ በሌሎች አተኛኘት /አቀማመጥ አቅጣጫዎች የሚፈጸም ሩካቤ

ይህ በጭራሽ ተቀባይነት የሌለው የራስ ፈጠራና የግል አስተያየት ይሆናል እንጅ : የፈጣሪ ህግ ሊሆን አይችልም : አምላክ እንዲህ አይነት ቢሮክራሲ የሚያበዛ ሳይሆን ቸርና የሰዎችን ችግር የሚያውቅ አምላክ ነው :

8. በአበይት በአላት : በጾምና በሰንበት ቀን የሚፈጸም ሩካቤ

ይህም በሚገባ መብራራት አለበት :
በአላት ሲባል የቱን ነው ? ስንት ናቸው ? ግልጥ አይደለም ::

7ኛ
9ኛ
10ኛ
12ኛ ብዙ የሚይነጋግሩን ቢሆኑም በኔ በኩል ብዙም ተቃውሞ የለኝም

በሌሎቹ በሙሉ እስማማለሁ :;

የእህታችን ቅን አሳቢነትሽ በጣም የሚበረታታ ቢሆንም
አንዳንድ ነገሮችን ግን ከራስሽ ባህርይ ጋር በማገናኘት የምታካባJ ይመስለኛልና ላላ ማድረጉ ጥሩ ነው

መጥሀፍ ቅዱስ ውስጥ ካለ It's OK

በግምትና በግል ፍላጎት ገፋ ገፋ እያደረጉ መጨማመር ከሆነ ግን :

ሀይማኖቱን ታስጠሉታላችሁ

እኔ የማያቸው አንድናድ ሰዎች ለሰዎች ሲያስተምሩ በጣም ጎበዝ ናቸው

እነሱ ግን ግን 10 % 100 እንኳን አያደርጉትም
ደባልቄ
መንገደኛ
መንገደኛ
 
Posts: 5
Joined: Mon Nov 05, 2007 7:24 pm

Postby ደባልቄ » Mon Nov 19, 2007 1:19 am

ጥያቄ - ለመሆኑ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ -ክርስቲያን አስተምህሮና ቀኖና መሰረት ተቀባይነት የሌላቸው የሩካቤ ስጋ ገጽታዎች አሉ ?-

መልስ - አዎን አሉ !!

ጥያቄ -ምን ምን ናቸው ?

መልስ -1. ከጋብቻ በፊት የሚፈጸም ሩካቤ
2. በቅዱስ ቁርባን ለተጋቡ ሙሽሮች ከጋብቻ በፊት 2 ቀን እና ከጋብቻ በህዋላ 3 ቀን ባለው ጊዜ ውስጥ የሚፈጸም ሩካቤ
3. ከጋብቻ ውጭ የሚፈጸም ሩካቤ
4. ያለቦታው የሚፈጸም ሩካቤ
5. ያለጊዜው የሚፈጸም ሩካቤ
6. በባል ወይም በሚስት ፍላጎት ብቻ የሚፈጸም ሩካቤ
7. ልጅ ለመውለድ ካለመፈለግ የተነሳ በኮንዶም ወይም በሌላ ወሊድ መቆጣጠሪያ አጋዥነት የሚፈጸም ሩካቤ
8. በአበይት በአላት : በጾምና በሰንበት ቀን የሚፈጸም ሩካቤ
9. በወር አበባ ጊዜ የሚፈጸም ሩካቤ
10. በእርግዝና ጊዜ የሚፈጸም ሩካቤ
11. ባልና ሚስት ፊት ለፊት ተጋጥመው ከሚፈጽሙት ሩካቤ ውጭ በሌሎች አተኛኘት /አቀማመጥ አቅጣጫዎች የሚፈጸም ሩካቤ
12. የወንድ ዘር ከሴቷ ማህጸን ውጭ እንዲፈስ እየተደረገ የሚፈጸም ሩካቤ (ግብረ -አውናን )
13. አፈ -ወሲብ እና በመቀመጫ በኩል የሚደረግ ሩካቤ (oral and anal sex)
14. በተመሳሳይ ጾታ መሀል የሚደረግ ሩካቤ (Homosexuality)
15. ከግኡዝ አካላት ጋር የሚደረግ ሩካቤ (Dildos, vibrators, sex machines, etc.)
16. ከእንስሳት ጋር የሚደረግ ሩካቤ (bestiality)
17. በተቀደሰ ስፍራ (በቤተ -ክርስቲያን ወይም በገዳም ቅጥር ግቢ ) የሚፈጸም ሩካቤ
18. ሌሎች ሰዎች እያዩ የሚፈጸም ሩካቤ
19. ራስ ከራስ ጋር የሚፈጸም ሩካቤ (masterbation)
20. የሰውነት አካልን በማቁሰል : በመጉዳት : እጅና እግርን በማሰር ወ ዘ ተ . የሚፈጸም ሩካቤ (BDSM):

ጥያቄ - ለምን ይሆን እነዚህ ሁሉ የሩካቤ ስጋ አፈጻጸም ገጽታዎች በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ -ክርስቲያን የሚከለከሉት ?

መልስ - የፈጣሪን ቁጣ ስለሚያነሳሱ : ሰውን ከሰውነት ክብር ዝቅ ስለሚያደርጉ : ለቅድስናው ህይወቱ ደንታ እንዳይኖረው ስለሚያደርጉና ለጤናውም ቢሆን ጠቃሚ ስላልሆኑ ነዋ !!


እና የኦርቶዶክስ ሀይማኖት እንዲህ ያዛል ?

እኔ ዝም ብዬ ኦርቶዶክስ ነኝ እንጅ : ብዙ ጣጣ አላቅም
እንዲህ አስቸጋሪ ግን አይመስለኝም

ለምሳሌ:

2. በቅዱስ ቁርባን ለተጋቡ ሙሽሮች ከጋብቻ በፊት 2 ቀን እና ከጋብቻ በህዋላ 3 ቀን ባለው ጊዜ ውስጥ የሚፈጸም ሩካቤ


እኔ ደግም አንድ የበተ ክርስቲና ሰርግ ላይ : አንድ ቄስ ሲያስተምሩ የሰማሁት

በፊት አንድ 1 በኋላ 1 በድምሩ ሶስት ቀን ሲባል ነው :: የአንቺው ደግሞ አዲስ ነው : ምናልባት ነገ ደግሞ ሌላ ቦታ ሌላ ቁጥር እንሰማ ይሆናል :: የመጣፍ ቅዱስ ማስረጃ የሌለው ነገር ግራ ያጋባል ::

4. ያለቦታው የሚፈጸም ሩካቤ


ይህም ግልጥ አይደለም ምናልባትም ከዚህ

7. በተቀደሰ ስፍራ (በቤተ -ክርስቲያን ወይም በገዳም ቅጥር ግቢ ) የሚፈጸም ሩካቤ


ከሚለው ጋር የሚስማማ ከሆነ ስቡቅ ነው :: ወይም ይብራራ

5. ያለጊዜው የሚፈጸም ሩካቤ


ይህም ቢሆን ግልጥ ያለ መገር አይደለም

9. በወር አበባ ጊዜ የሚፈጸም ሩካቤ

110. በእርግዝና ጊዜ የሚፈጸም ሩካቤ


የሚለውን ለመጠቆም ከሆነ ድግግሞሽ ሆአልና ቁጥሩ እንደገና ይስተካከል

6. በባል ወይም በሚስት ፍላጎት ብቻ የሚፈጸም ሩካቤ


እኔ የሰማሁት ደግሞ ባልም ሚስትም ቢጠያየቁ (አንደኛው ባይፈልግም) እምቢ መባባል የለብቸውም ሲባል ነው ::
ሲጠይቅ እምቢ ከተባለማ ትኩሳቱን ላማብረድ ወደ ሌላ መከጀሉ አይቀሬ ነውና ሰውን ማባለግ ነው ::

11. ባልና ሚስት ፊት ለፊት ተጋጥመው ከሚፈጽሙት ሩካቤ ውጭ በሌሎች አተኛኘት /አቀማመጥ አቅጣጫዎች የሚፈጸም ሩካቤ


ይህ በጭራሽ ተቀባይነት የሌለው የራስ ፈጠራና የግል አስተያየት ይሆናል እንጅ : የፈጣሪ ህግ ሊሆን አይችልም : አምላክ እንዲህ አይነት ቢሮክራሲ የሚያበዛ ሳይሆን ቸርና የሰዎችን ችግር የሚያውቅ አምላክ ነው :

8. በአበይት በአላት : በጾምና በሰንበት ቀን የሚፈጸም ሩካቤ


ይህም በሚገባ መብራራት አለበት :
በአላት ሲባል የቱን ነው ? ስንት ናቸው ? ግልጥ አይደለም

7ኛ
9ኛ
10ኛ
12ኛ ብዙ የሚይነጋግሩን ቢሆኑም በኔ በኩል ብዙም ተቃውሞ የለኝም

በሌሎቹ በሙሉ እስማማለሁ :;

የእህታችን ቅን አሳቢነትሽ በጣም የሚበረታታ ቢሆንም
አንዳንድ ነገሮችን ግን ከራስሽ ባህርይ ጋር በማገናኘት የምታካባጂው ይመስለኛልና ላላ ማድረጉ ጥሩ ነው

መጥሀፍ ቅዱስ ውስጥ ካለ It's OK

በግምትና በግል ፍላጎት ገፋ ገፋ እያደረጉ መጨማመር ከሆነ ግን :
ሀይማኖቱን ታስጠሉታላችሁ

እኔ የማያቸው አንድንድ ሰዎች ለሰዎች ሲያስተምሩ በጣም ጎበዝ ናቸው

እነሱ ግን 10 % 100 እንኳን አያደርጉትም
ደባልቄ
መንገደኛ
መንገደኛ
 
Posts: 5
Joined: Mon Nov 05, 2007 7:24 pm

Postby ShyBoy » Mon Nov 19, 2007 5:59 pm

ትትና wrote:ድንቅ ትምህርት ነው! እህታችን ብርሀናዊት ቶሎ ፈተናሽ አልቆ ተመልሰሽ ለያንዳንዱ ጥሩ ማብራሪያ እንደምትሰጪበትተስፋ አደርጋለሁ!!

ችሎ ማደር:- የቤተክርስቲያን ነገር እኔን እንደገባኝ ከሆነ ጊዜና ወቅት ጠብቃ የእግዚአብሔርን ቃል ማጣመም መብቷ አይመስለኝም:: ሀጢያት ባደገ ቁጥር ሰዎች ከቤተክርስቲያን እንዳይወጡ የቲፎዞ ስራ መስራት ያለባት አልመሰለኝም:: ጆሮ ያለው ይስማ ብላ ከመናገር በቀር.... ደሞ የእግዚአብሄር ቃል አያረጅም አያፈጅም! ያለ የነበረ የሚኖር ነውና ከለወጠውም እሱ ራሱ ያደርገዋል ልክ አዲስ ኪዳን ላይ ብዙ የብሉይ ስራቶች እንደተቀየሩ::
በሌሎች ሀይማኖቶች:- አንዴ የሰማሁትን ልንገርህ ለምሳሌ:- ሰውየው አንደኛው የዩናይትድ ቸርች ስራ አስፈጻሚ ነገር ነው (ኮሚቴ) ሲያጫውተኝ ስብሰባ አለን ለብዙ ጊዜ የተሰበሰብንበት ነው አከራካሪ ሆኖ እስካሁን መወሰን አቃተን አሁን ግን የመጨረሻ ነው አለኝ:: ስለምንድነው ስብሰባው ስለው ስለ አንዳይነት ጾታ ጋብቻ አለ:: ገና እንደመጣሁ ነበርና ክው አልኩ:: ምን ልትሉ ነው የምትሰበሰቡት ስለው:: በቤተክርስቲያናችን ልናጸድቀው ብሎኝ ቁጭ:: ቄሱ ምን ይላሉ ስለው? ምን አገባቸው! እኛ ኮሚቴዎች ከወሰንን......... ወይ ጉድ ብዬ ዝም አልኩ:: እና መጽሀፍ ቅዱስ ነው ወይስ የዘመኑ ሁኔታ የሚወስነው?


ትቴክስ እንዴት ነሽ ባያሌው? የምር በጣም አሪፍ መልስ ነው የሰጠሽው! አንች ልጅ ቀላል ጨምረሻል! ለነገሩ ድሮም የምታኮሪ ነበርሽ! በስነ-ጽሁፉ: በሀይማኖቱ: በሶሻል ላይፉ..............በቃ በሁሉ ነገር የምትሰጫቸው ሀሳቦች በጣም ደስ ይሉኛል!!! የምር በይ ቶሎ ሪዙሜሽን ላኪልኝ.........:lol: ካልሆነ እኔ ልላክ እንዴ? :lol:
ShyBoy
ውሃ አጠጪ
ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1118
Joined: Tue Apr 04, 2006 10:36 pm
Location: Gojjam

Postby ጌታ » Mon Nov 19, 2007 6:49 pm

ደባልቄ wrote:
2. በቅዱስ ቁርባን ለተጋቡ ሙሽሮች ከጋብቻ በፊት 2 ቀን እና ከጋብቻ በህዋላ 3 ቀን ባለው ጊዜ ውስጥ የሚፈጸም ሩካቤ


እኔ ደግም አንድ የቤተ ክርስቲያን ሰርግ ላይ : አንድ ቄስ ሲያስተምሩ የሰማሁት

በፊት አንድ 1 በኋላ 1 በድምሩ ሶስት ቀን ሲባል ነው :: የአንቺው ደግሞ አዲስ ነው : ምናልባት ነገ ደግሞ ሌላ ቦታ ሌላ ቁጥር እንሰማ ይሆናል :: የመጣፍ ቅዱስ ማስረጃ የሌለው ነገር ግራ ያጋባል ::


ደባልቅ ወንድሜ

እዚህ ጋ እንደሁለታችሁም አባባል በቅዱስ ቁርባን ለሚጋቡ ሙሽሮች ከጋብቻ በፊት ወሲብ ይፈቀዳል ማለት ነው:: ካልሆነ ሁለት ቀን ሆነ አንድ ሊያከራክር ባልተገባው ነበር:: እኔ እንደሰማሁት ብዙ እምነቶች (ክርስትና እስልምና ቡድሀም ጭምር) ከጋብቻ በፊት ወሲብን ይከለክላሉ::

የፀሀፊው የመሳሳት መብት እንደተጠበቀ ነው:: :lol:
ኢትዮጵያ እጆቿን ወደ እግዚአብሄር ትዘረጋለች!!!
ጌታ
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 3029
Joined: Sun Apr 17, 2005 5:35 pm
Location: ዶሮ ተራ

Postby ችሎ_ማደር » Mon Nov 19, 2007 7:43 pm

ትትና wrote: የቤተክርስቲያን ነገር እኔን እንደገባኝ ከሆነ ጊዜና ወቅት ጠብቃ የእግዚአብሔርን ቃል ማጣመም መብቷ አይመስለኝም:: ሀጢያት ባደገ ቁጥር ሰዎች ከቤተክርስቲያን እንዳይወጡ የቲፎዞ ስራ መስራት ያለባት አልመሰለኝም:: ጆሮ ያለው ይስማ ብላ ከመናገር በቀር.... ደሞ የእግዚአብሄር ቃል አያረጅም አያፈጅም! ያለ የነበረ የሚኖር ነውና ከለወጠውም እሱ ራሱ ያደርገዋል ልክ አዲስ ኪዳን ላይ ብዙ የብሉይ ስራቶች እንደተቀየሩ::
በሌሎች ሀይማኖቶች:- አንዴ የሰማሁትን ልንገርህ ለምሳሌ:- ሰውየው አንደኛው የዩናይትድ ቸርች ስራ አስፈጻሚ ነገር ነው (ኮሚቴ) ሲያጫውተኝ ስብሰባ አለን ለብዙ ጊዜ የተሰበሰብንበት ነው አከራካሪ ሆኖ እስካሁን መወሰን አቃተን አሁን ግን የመጨረሻ ነው አለኝ:: ስለምንድነው ስብሰባው ስለው ስለ አንዳይነት ጾታ ጋብቻ አለ:: ገና እንደመጣሁ ነበርና ክው አልኩ:: ምን ልትሉ ነው የምትሰበሰቡት ስለው:: በቤተክርስቲያናችን ልናጸድቀው ብሎኝ ቁጭ::


ትትና; ይህ መልስ ከኔ ጥያቄ ጋራ ብዙ ግንኙነት የለውም:: የምንነጋገረውም በመጽሀፍ ቅዱስ ላይ በተጻፈ ሕግጋት ውስጥ ያለ አይደለም:: በብዛት በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን የወጣ ሕግ ነው::
የኔም አስተያይት ከዚሁ ጋራ በተያያዘ የካቶሊክ ቤተ ክርስቲያንም አንዲሕ ያሉ ያረጁ ያፈጁ ባሕላዊ ሕግጋትን ባለው ዘመን አንደሚሰራ አስተካከለውታል::(አስታውሱ; መጽሀፍ ቅዱስን አሻሽሉ ወይም ያረጀ ያፈጀ አላልኩም::)
በተለይ የምንነጋገርበት መስመሮች በወንድና በሴት መሀል የግብረ ሥጋን ግንኙነት መጣጣም ጭልጥ ብሎ ስለሚያደናገር በግልፅ ማስተካክሉ; አንዳንዴም ከትዳር መፍርስና ከመሳሰሉት ሁሉ ያድናል:: ቄሶቹ የፃፉትን ሁሉ በጭፍን የመቀበሉ ጊዜ አልፏል::
አኔ የኦርቶዶክስ ኃይማኖት በጥብቅ አፍቃሪ ስሆን ኃይማኖቴን በትክክል የማወቅ የመማርና የማስተማር ግዴታም አለብኝ::
በመጽሐፍ ቅዱስ አንዳንድ ሕጎች ጥያቄ ቢኖረኝም; ስለ አመንኩበት ተቀብየዋለሁ:: አንግዲህ የመነኮሳትንና የዲያቆናትን አባባል አንደዘመኑ ያስተካክሉ ነው አንድንቀበላቸው ያልኩት::

ቤተ ክርስቲያንም "ጆሮ ያለው ይስማ" ብላ ዝም አትልም::

ስለ አስተያየትሽና ትችቱ በጣም አምሰግናለሁ::
"The difference between stupidity and genius is that genius has its limits." Albert Einstein
ችሎ_ማደር
ጀማሪ ኮትኳች
ጀማሪ ኮትኳች
 
Posts: 55
Joined: Wed Sep 12, 2007 4:16 pm

Postby ደባልቄ » Mon Nov 19, 2007 11:51 pm

ደባልቄ እንደጻፈ(ች)ው:


Quote:
2. በቅዱስ ቁርባን ለተጋቡ ሙሽሮች ከጋብቻ በፊት 2 ቀን እና ከጋብቻ በህዋላ 3 ቀን ባለው ጊዜ ውስጥ የሚፈጸም ሩካቤ


እኔ ደግም አንድ የቤተ ክርስቲያን ሰርግ ላይ : አንድ ቄስ ሲያስተምሩ የሰማሁት

በፊት አንድ 1 በኋላ 1 በድምሩ ሶስት ቀን ሲባል ነው :: የአንቺው ደግሞ አዲስ ነው : ምናልባት ነገ ደግሞ ሌላ ቦታ ሌላ ቁጥር እንሰማ ይሆናል :: የመጣፍ ቅዱስ ማስረጃ የሌለው ነገር ግራ ያጋባል ::


ደባልቅ ወንድሜ

እዚህ ጋ እንደሁለታችሁም አባባል በቅዱስ ቁርባን ለሚጋቡ ሙሽሮች ከጋብቻ በፊት ወሲብ ይፈቀዳል ማለት ነው :: ካልሆነ ሁለት ቀን ሆነ አንድ ሊያከራክር ባልተገባው ነበር :: እኔ እንደሰማሁት ብዙ እምነቶች (ክርስትና እስልምና ቡድሀም ጭምር ) ከጋብቻ በፊት ወሲብን ይከለክላሉ ::

የፀሀፊው የመሳሳት መብት እንደተጠበቀ ነው ::


የጣፊውን የመሳሳት መብት እኔም አከብራለሁ

እኔ እንኳን ማለት የፈለግሁት ከጋብቻ በፊት ወሲብ ይፈቀዳል ለማለት ሳይሆን
በአጠቃላዩ ስለተናገርሁ ነው : ማንም ባለትዳር መቁረብ ከፈለገ ህጉን ለማለት ነው

ለማንኝውም እኔም የሰማሁት ከጋብቻ በፊት ወሲብ እንደማይፈቀድ ነው

ግን ይቻላል ?
ደባልቄ
መንገደኛ
መንገደኛ
 
Posts: 5
Joined: Mon Nov 05, 2007 7:24 pm

Postby ብርኃናዊት » Tue Nov 20, 2007 1:29 am

ውድ ደባልቄ:

እዚህ ጋር ፈጠን ያለች ማስተካከያ ልሰጥ ነው የገባሁት:: ጸሀፊዋ አገላለጽ ላይ ተሳስቼያለሁ:: ልክ ነው:: በቁጥር አንድ ላይ እንደተጠቀሰው ከጋብቻ በፊት ሩካቤ አይፈቀድም:: ነገር ግን ከጋብቻ በፊት ሁሉን ነገር ጨርሰው (በግብረ-ስጋ ተዋውቀው) በመአስባን (በንስሀ) የሚጋቡ ሰዎች አሉ:: እነዚህ ሰዎች ከሰርጋቸው ቀን በፊት ከማንኛቸውም ሩካቤ መታቀብ አለባቸው:: ምክንያቱም ንስሀ ላይ ናቸውና::

እናም የተሰጠው ማስተካከያ ትክክል ነው:: ባልና ሚስት ቁርባን ከሚቀበሉበት ቀን በፊት 2 ቀን እና ከቁርባኑ በህዋላ 3 ቀን ነው ከሩካቤ የሚከለከሉት:: እና "ሙሽሮች" በሚለው ፈንታ "ቅዱስ ቁርባን የሚቀበሉ ባልና ሚስት ከሚቀበሉበት ቀን በፊትና በኍላ" ተብሎ ይነበብልኝ:: 2 ቁጥርን ስጽፍ በአእምሮዬ የነበሩት already የተጋቡት ባልና ሚስት ናቸው::

ቸር ይግጠመን
ብርኃናዊት
ብርኃናዊት
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 3302
Joined: Sat Oct 27, 2007 3:57 am

Postby ትትና » Mon Nov 26, 2007 7:06 am

ችሎ ማደር:- እኔ አንተን ልተች ብዬ አይደለም ሀሳቤን የገለጽኩት:: ባይሆን ያላልከውን ብዬ ከሆነ እስቲ ከታች ያለውን ተመልከተው:: ለማንኛውም ካበሳጨሁህ, ይቅርታ! ሌላው የማንም ሀይማኖት ተከታይ ሁን እሱ ያንተ ምርጫ ነው እኔ በማንም ሀይማኖት ላይ ነቀፋ የለኝም::
ያረጀ ያፈጀ መመሪያ አወጡ ያልካቸው ካህናቶች ከምን በመነሳትና መመሪያቸው ምን እንደነበረ ብርሀናዊት መብራሪያ ስትሰጥበት ጥያቄያችን ይመለሳል ብዬ ተስፋ አደርጋለሁ::


ከአክብሮት ጋር
ትትና


ችሎ_ማደር wrote:
ብርኃናዊት wrote:ሰላም ዋርካውያን:

መልስ- በቀጣዩ ጽሁፌ እመለስበታለሁ::አስካሁን ድረስ ለምን ብዙው ስው ጠበቅ ያለ የኦርቶዶክስ ተከታይነት አንደሌለው ሣሥብ ነበረ:: አመሰግናለሁ ጎሽ አሁን ገና ገባኝ::

በጣም ከጥቂቶቹ በስትቀር አብዛኛው በዚህ ዘመን ሊሰራ የማይችል ያረጀና ያፈጀ ነው:: ባልና ሚስት አንዳፈጣጠራችው ሁኔታ ፍላጎታቸውን ለማርካት በተለያየ (POSITION) ቢገናኙ ህጥያቱ ለምንድነው::

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ አንደ ካቶሊክ ሊቃውንታት ዘመን የሚያሻሽላቸውን ጉዳዮች አብሮ ማስተካከል ካልቻሉ አብዛኛው ወደ ፔንጤ ማድላቱን አያባስው መሔዱን አንጠራጠር::

* ምን አለ ሚስቴን ሳጣ (MASTERBATE) ባደርግ ክምሽረሙጥ?
* ምን አለ (CONDUM) ባደርግ በማሰወረድ ከመግደል?
* ምን አለ በፈለግነው ቀን ብንገናኝ?
* መመሪያችን መፅሕፍ ቅዱሥ ነው ወይስ ምንድነው?

መነጋገሪያውን አረአስት በጣም ወድጀዋለሁና በርቺ(ታ)
ትትና
ውሃ አጠጪ
ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1253
Joined: Wed Feb 23, 2005 11:26 am
Location: united states

Postby ብርኃናዊት » Sat Dec 01, 2007 8:15 pm

ሰላም ወገኖች:

በስተመጨረሻ ወደዚህ ቤት ብቅ አልኩኝ:: ብዙ ሀተታ ሳላበዛ ወደ ቁም ነገሩ እገባለሁ::

በቅድሚያ በቤተ ክርስቲያናችን የማይፈቀዱ የሩካቤ ገጽታዎችን ለማስታወስ ያህል መልሼ እዘረዝራቸውና በመቀጠል ከዋርካ ተሳታፊዎች እንደተገነዘብኩት አጨቃጫቂ የሆኑት ነጥቦች ላይ ከመጻፍት ያገኘሁትን ማብራሪያ እሰጣለሁ::

1. ከጋብቻ በፊት የሚፈጸም ሩካቤ
2. ቅዱስ ቁርባን ለሚቀበሉ ባልና ሚስት ከቁርባን በፊት 2 ቀን እና ከቁርባን በህዋላ 3 ቀን ባለው ጊዜ ውስጥ የሚፈጸም ሩካቤ
3. ከጋብቻ ውጭ የሚፈጸም ሩካቤ
4. ያለቦታው የሚፈጸም ሩካቤ
5. ያለጊዜው የሚፈጸም ሩካቤ
6. በባል ወይም በሚስት ፍላጎት ብቻ የሚፈጸም ሩካቤ
7. ልጅ ለመውለድ ካለመፈለግ የተነሳ በኮንዶም ወይም በሌላ ወሊድ መቆጣጠሪያ አጋዥነት የሚፈጸም ሩካቤ
8. በአበይት በአላት : በጾምና በሰንበት ቀን የሚፈጸም ሩካቤ
9. በወር አበባ ጊዜ የሚፈጸም ሩካቤ
10. በእርግዝና ጊዜ የሚፈጸም ሩካቤ
11. ባልና ሚስት ፊት ለፊት ተጋጥመው ከሚፈጽሙት ሩካቤ ውጭ በሌሎች አተኛኘት /አቀማመጥ አቅጣጫዎች የሚፈጸም ሩካቤ
12. የወንድ ዘር ከሴቷ ማህጸን ውጭ እንዲፈስ እየተደረገ የሚፈጸም ሩካቤ (ግብረ -አውናን )
13. አፈ -ወሲብ እና በመቀመጫ በኩል የሚደረግ ሩካቤ (oral and anal sex)
14. በተመሳሳይ ጾታ መሀል የሚደረግ ሩካቤ (Homosexuality)
15. ከግኡዝ አካላት ጋር የሚደረግ ሩካቤ (Dildos, vibrators, sex machines, etc.)
16. ከእንስሳት ጋር የሚደረግ ሩካቤ (bestiality)
17. በተቀደሰ ስፍራ (በቤተ -ክርስቲያን ወይም በገዳም ቅጥር ግቢ ) የሚፈጸም ሩካቤ
18. ሌሎች ሰዎች እያዩ የሚፈጸም ሩካቤ
19. ራስ ከራስ ጋር የሚፈጸም ሩካቤ (masterbation)
20. የሰውነት አካልን በማቁሰል : በመጉዳት : እጅና እግርን በማሰር ወ ዘ ተ . የሚፈጸም ሩካቤ (BDSM):


አጨቃጫቂ ከሆኑት ነጥቦች መሀል ለዛሬ ቁጥር አስራአንድን ላብራራ:

11. ባልና ሚስት ፊት ለፊት ተጋጥመው ከሚፈጽሙት ሩካቤ ውጭ በሌሎች አተኛኘት /አቀማመጥ አቅጣጫዎች የሚፈጸም ሩካቤ

ሩካቤ ስጋ ለመሆኑ በተለምዶ ከሚታወቀው ባልና ሚስት ፊት ለፊት ተጋጥመው ከሚፈጽሙት ሩካቤ ውጭ በሌሎች አቅጣጫዎችና እንቅስቃሴዎች የማይፈጸመው ለምንድነው? እውነት እናትና አባቶቻችን ሩካቤ ሲፈጽሙ በሌላ አቅጣጫ መፈጸም እንደሚችሉ ሳያውቁት ቀርተው ነው ወይስ ሀይማኖታዊ ምክንያት ስላላቸው ነው?

እስቲ ትንሽ ከመጽሀፍ ላይ ያገኘሁትን ላካፍል:

(በነገራችን ላይ አግባብ ያልሆኑ የሩካቤ አፈጻጸም አቅጣጫዎች ስንል በዚሁ በዋርካ ላይ እንደታዘብኩት የተለያየ ስም የወጣላቸው እነ Dogi (የፉ????) እነ በቁም ሩካቤ መፈጸም- እነ ካማሱትራ: እነ ወንበር እነጠረጴዛ ሁሉ ይጨምራል:: አልጋ የሰው ልጅ ክብር እንደሆነ መቼም እናጣዋለን ብዬ አልገምትም::

የእግዚአብሔር ነብይ ዳዊት "በልባብና በልጓም ጉንጫቸውን እንደሚለጉሟቸው ልብ እንደሌላቸው እንደ ፈረስና በቅሎ አትሁኑ:" መዝ 31:9: በማለት ሰውን ሁሉ ይመራል:: የሰው ልጅ በባህርየ ስጋ ምንም እንኳ እንስሳትን ቢመስልም በአንጻሩ ደግሞ መላእክትን የምታስመስለው ነፍስ በውስጡ ስለምትገኝ በኑሮው ሁሉ እንስሳትን መምሰል የለበትም:: [color=black]ለነገሩ አስተውላችሁታል?? አንዱ ስርአት አልባ የሩካቤ አፈጻጸም አቅጣጫ እኮ ከነስሙ እንኳን "ዶጊ" ነው:: ውሻ ነን እያልን ይሆን??እንሰሳት እንደተወለዱ ወዲያውኑ በእግራቸው ቀጥ ብሎ መቆምና መንቀሳቀስ ይችላሉ:: ይህም ለመወለዳቸው ምክንያት የሆነው ሩካቤ በቁም (በመቆም) መፈጸሙን ያመለክታል:: እንሰሳት ግንኙነታቸውን ቆሞ ለመፈጸም ምቹ ተፈጥሮ ስላላቸው ድርጊታቸውን የሚቃወም መጽሀፋዊና ተፈጥሯዊ ህግ የለም:: የሰው ልጅ ግን ሩካቤን በመቆምና በመቀመጥ እንዳይፈጽም ተፈጥሮው ምቹ ካለመሆኑም የተነሳ የእግዚአብሔርም ህግ አይፈቅድለትም::ለነገሩ አብዛኛው ጊዜም አስተውላችሁት እንደሆነ የወንድና የሴት ቁመት እንኳ እኩል ባለመሆኑ በቁም ሩካቤ መፈጸም የሚለው ፈሊጥ ምቹ ባለመሆኑ የዚህ ድርጊት አጨብጫቢዎች "ወንዱ የተለየ አካላዊ ጥንካሬ ያስፈልገዋል" ሲሉ ይደመጣሉ:: ምነው ቢተኙ? ምናልባት አንዳንዱ ወንድ ጠዋት ጠዋት እየተነሳ ጡንቻውን ለማፈርጠም ብሎ ብረት የሚያነሳው ለዚህ ይሆን?? ይህ ሲሆን እኛ ራሳችን የሩካቤ/ያውም አግባብ ያልሆነ ሩካቤ/ ባርያ መሆናችንን አያመለክትም ትላላችሁ? ለሌላ ነገር ይህን ያህል አንተጋማ?!!- ወደጽሁፉ ልመለስ:

የሰው ልጅ በተወለደ ጊዜ ወዲያውኑ እግሮቹ ቀጥ ብለው መቆምና መንቀሳቀስ አይችልም:: ይህም ለርሱ መወለድ ምክንያት የሆነው የናትና የአባቱ ግንኙነት በመተኛት እንደተፈጸመ (ወይም [እናትና አባቱ ህጉን ጥሰው ከሆነም] በመተኛት መፈጸም እንደነበረበት ) እንዲሁም የማንኛውም ባልና ሚስት ሩካቤ በመተኛት መፈጸም እንዳለበት ያመለክታል:: ይህ የራሳችን ተፈጥሮ ከሚያስተላልፍልን በተጨማሪ የአዳም ረድኤት ሄዋን ስትፈጠር እንዴት እንደነበር መጽሀፍ ቅዱስ ሲገልጽ "እግዚአብሔር አዳምን ከባድ እንቅልፍ ጣለበት አንቀላፋም: ከጊኑም አንዲት አጥንት ወስዶ ስፍራውን በስጋ ዘጋው:: እግዚአብሔር አምላክም የወሰዳትን አጥንት ሴት አድርጎ ሰራት:: ዘፍ 2:21" ይላል:: እግዚአብሔር አዳምን ካስተኛውና ከባድ እንቅልፍ ከጣለበት በኍላ ሔዋንን መፍጠሩ ግብራቸው (ግንኙነታቸው) በመተኛት መፈጸም እንዳለበት ሥርአት ለመስራት ነበር::


መጽሀፍ ቅዱስ "ሁለት ሰዎች በአንድ አልጋ ይሆናሉ አንዱ ይወሰዳል ሁለተኛውም ይቀራል" ሉቃ 17: 34 በማለት የባልና ሚስት በግብር መተዋወቅ የሚፈጸመው በመኝታ መሆኑን ገልጾ ነገር ግን ከሁለቱ አንዳቸው በድንገት በሞት መነጠቃቸው ለጌታችን መድሀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ መምጣት ምልክት እንደሚሆን ነግሮናል:: አስተውላችሁታል እዚህ ጋር? የጌታ መንጫው ሲቃረብ ባልና ሚስት ሩካቤ እየፈጸሙ እያለ በድንገት አንዱ ይሞታል? ምን አይነት መቅሰፍት ይሆን የሚጠብቀን? በሌላም ስፍራ ነብዩ ናታን ስለ ኦርዮ ሚስት በበግ እየመሰለ ለዳዊት በነገረው ጊዜ በብብቱም ትተኛ ነበር 2ኛ ሳሙ 12:5 በማለት ገልጿል::(በሩካቤ መተዋወቃቸውን ለመግለጽ ነው:: ይህ አገላለጽ ተገቢው የሩካቤ አፈጻጸም ምን መሆን እንዳለበት ያሳየናል::) በመጽሀፍ ቅዱስ በአንድም ስፍራ ሩካቤን እንደ እንሰሳት የፈጸሙ ሰዎች ታሪክ አናገኝም::

የሩካቤና የአምስቱ ህዋሳቶች ትይዩነት

ጌታችን መድሀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በአጭር ቁመት በጠባብ ደረት ተወስኖ በህቱም ድንግልና ተወልዶ ዐለምን ለማዳን የመጣ የአብ የባህሪ ልጅ መሆኑን በተለያየ ምክንያት ብዙዎች እንዳላመኑበት በምሳሌ ሲያስረዳ እንዲህ ብሏል:- አንድ ሰው ታላቅ እራት አድርጎ ብዙዎችን ጠራ: በእራትም ሰአት የታደሙትን አሁን ተዘጋጅቷልና ኑ እንዲላቸው ባርያውን ላከ: ሁላቸውም በአንድነት ያመካኙ ጀመር:: የፊተኛው መሬት ገዝቻለሁ ወጥቼም ላየው የግድ ያስፈልገኛል ይቅር እንድትለኝ እለምንሀለሁ አለው:: ሌላውም አምስት ጥማድ በሬዎች ገዝቻለሁ ልፈትናቸውም እሄዳለሁ ይቅር እንድትለኝ እለምንሀለሁ አለው:: ሌላውም ሚስት አግብቻለሁ ስለዚህም ልመጣ አልችልም አለው:: " ሉቃ 10: 16-20 በዚህ ታሪክ 'ታላቅ እራት ያደረገው ሰው" ጌታችን ኢየሱስ ሲሆን ታዳሚዎቹም በአለም ያሉ ሰዎች በሙሉ ናቸው:: "ታላቅ እራት" የተባለው ጥሪም ጌታችን ያለዘር ያለሩካቤ መወለዱን እንዲያምኑ መጠራታቸውን የሚያመለክት ነው:: ሆኖም ሁሉም በተለያየ ምክንያት ጥሪውን አክብረው አልተገኙም:: እንዲያውም አንደኛው በጥሪው ያልተገኘበትን ምክንያት ሲገልጽ "አምስት ጥማድ በሬዎች ገዝቻለሁ ልፈትናቸውም እሄዳለሁ" በማለት ነበር:: ይህም [ምስጢራዊ ትርጉሙ] ሲፈታ "አንተ ያለዘር ያለሩካቤ በህቱም ድንግልና ተጸነስኩ በድንግልናም ተወለድኩ እመኑብኝ ትላለህ: እኔ የማውቀው ደግሞ ፍሬ የሚገኘው ማሳ በጥማድ በሬዎች ታርሶ ዘር ተዘርቶ እንደሆነ ሁሉ የሰው ልጅም የሚገኘው በአምስቱ በሬዎች የሚመሰሉ የባልና ሚስት ህዋሳት ተጠምደው ተጋጥመው በሚፈጸም ሩካቤ ነውና ይቅር በለኝ በልደትህ አላምንም እንደማለት ነበር:: ...

አምስት ጥማድ በሬዎች ገዝቻለሁ የሚለው አረፍተ ነገር ፍቺ ልጅ ለመውለድ በባልና ሚስት መካከል ለሚፈጸም ተራክቦ ትክክለኛነት ምሳሌ አለው:: ይህንን ቃል በመናገር በጌታ እራት ላይ ላለመገኘቱ ምክንያት የሰጠው ሰው የተሳሳተው የጌታን ልደት እንደማንኛውም ሰው ልደት አድርጎ በመቁጠር ጌታን ያለዘር ያለሩካቤ በድንግልና መወለዱን ባለማመኑ ነው እንጂ "አምስት ጥማድ በሬዎች ገዝቻለሁ" በማለት ለሩካቤ ለሰጠው ምሳሌያዊ ገለጻ አይደለም::
[በነገራችን ላይ ይህን ገለጻ ጌታ ራሱ የሰጠው ነው እንጂ በዚያን ወቅት በአፉ ለእራት ጋባዡ እንደዚያ ያለ ሰው አልበነረም: በልቡ ግን አብዛኛው ሰው የጌታን በድንግልና መወለድ ይጠራጠር ነበር::] ይህ አረፍተ ነገር በወንድና በሴት መካከል ለሚደረግ የተፈጥሮ ህግንና የመጽሀፍ ስርአትን የጠበቀ ሩካቤን በትክክል መግለጽ የሚችል መንፈሳዊና ምሳሌያዊ አገላለጽ ነው:: ስለዚህ በዚህ ቃል መሰረት በባልና ሚስት መካከል ሩካቤ መፈጸም ያለበት ትይዩ በመሆንና አምስቱ ህዋሳቶቻቸውን አንድ በማድረግ ነው:: .... ማለትም አፍ ለአፍ: እጅ ከእጅ... ጋር አንድ ይሆናሉ (ይጋጠማሉ) ማለት ነው:: ከዚህ የወጣ ሩካቤ አፈጻጸም ግን ከሰይጣን የተገኘ ነው:: በነገራችን ላይ ምናልባት በስሜት መሀል እጃቸው ቢላቀቅ ወይም ቢገላበጡ ህግ ጣሱ ማለት አይደለም:: በማስመሪያ እየለካ 'ተላቃጭኍል' ብሎ የሚቀጣቸው መላክ አለ ብዬ አላምንም: ስሜታቸውን በነጻነት የመግለጽ መብት አላቸው: ሆኖም እንደእንስሳ የመሆን ባህሪ ሊያሳዩ አይገባም::]

እንሰሳት ሩካቤ ሲያደርጉ ፊትና ኍላ በመሆን ነው:: የሰው ልጅ ግን ከእንሰሳት ይለያልና ፊት ለፊት ሆኖ ሩካቤን ይፈጽማል:: ብዙ እንሰሳት እንደተወለዱ አይናቸውን አይገልጡም/አያዩም:: ይህም ለጽንሰታቸው ምክንያት የሆነው ሩካቤ ባለመተያየት (ፊትና ኍላ በመሆን) መፈጸሙን ሲያመለክት የሰው ልጅ ደግሞ እንደተወለደ ወዲያውኑ አይኑን መግለጡና ለማየት መቻሉ ምንም እንኳ የተፈጥሮ ነገር ሆኖ [በስሜት] አይንን መጨፈን ባይቀርም ሴትና ወንድ ትይዩ ሆነው ተራክቦ እንደሚያደርጉ ያመለክታል:: ለነገሩ ነገር በዐይን ይገባል አይደለም የሚባለው ? ፊት ለፊት ላለመተያየት መፈለግ በስነ ልቦናም ቢተነተን ንቀትን ወይም እውነተኛ ፍቅር ሳይኖር ሩካቤውን ብቻ መፈለግን ያሳያል :: (ልክ አንዳንድ ዋርካውያን cover the face, attack the base እንዳሉት ማለት ነው - ማንነቷን ወይም መልኳን ላለማየት : ይህ ደግሞ እንሰሳነት ነው ::

ምንጭ- ትዳርና ተላጽቆ- በ ዲያቆን ህብረት የሺጥላ

እና እንግዲህ ከላይ ከተሰጠው መጽሀፍ ቅዱሳዊ አተናተን ጋር በተያያዘ አንድ ትዝ ያለኝን ባህላዊ ግጥም ልጥቀስ:

ሙሽሪት ባንድ አልጋ ሙሽራው ባንድ አልጋ
ይመስላሉ መላክ ክንፉን የዘረጋ


ይህ ስለሩካቤና በአጠቃላይም አብሮ ስለመተኛት የተነገረ ቅኔ ነው:: በሌላ ከላይ በጠቀስናቸው አገላለጽ የተጠቀሱትን ስርአት አልባ አቅጣጫዎች እንሲ እናስባቸው? እንደዚያ የተኙ ባልና ሚስት ክንፉን የዘረጋ መላክ ሳይሆን የሚመስሉት ምናልባት አህያና ነጂዋ: ወይም ውሻ: ወይም ግመል: ወይም ጠረጴዛ ላይ የተኛ በሽተኛና መርማሪ ዶክተር ነው የሚመስሉት:: አባቶቻችንና እናቶቻችን ብዙ ነገር የሚያውቁ ሲሆን ሌሎች የአተኛኘት ዘዴዎችን የማያደርጉት (ቢያንስ አብዛኞቹ) አላዋቂ ስለሆኑ ወይም ሞኝ ስለሆኑ ወይም ማድረግ እንደሚችሉ ጠፍቷቸው ሳይሆን ከስርአት የወጣ በመሆኑ ነው:: እነሱ እንክዋን ይህን ቀርቶ የዝንብ ጠንጋራም ያውቃሉ::

ለዛሬ በዚሁ ይብቃኝና ከሌሎቹ ጥያቄዎች ጋር አብሬ ደግሞ ቀደም ሲል የተለያዩ ተሳታፊዎች ያነሷቸውን ጥያቄዎች በሚቀጥለው አብራራለሁ::

ሰላም!
ብርኃናዊት
ብርኃናዊት
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 3302
Joined: Sat Oct 27, 2007 3:57 am

Postby ዲያና » Wed Dec 05, 2007 6:22 pm

ውድ ብርሀናዊት ትምህርቱ መልካም ነው:: ጥያቄ ለመመለስም ደግሞ በቂ ዝግጅት አድርገሽና አስበሽበት ቢሆን ደስ ይለኛል:: ስለ መጽሀፍ ቅዱስ ስታወሪ ቆይተሽ ሌላ ደግሞ ስትቀላቅዪ አንባቢው ይደናገርና ቀለል አድርጎ ሊወስደው ይችላል:: ለምሳሌ
ሙሽሪት በአንድ አልጋ ሙሽራው በአንድ አልጋ
ይመስላሉ መልዐክ ክንፉን የዘረጋ

የሚለው ግጥም አለማዊ ስለሆነ ያንቺን (supportive explanation) ወይም ደግሞ ደጋፊ ገለጻ ያላላዋል:: ስለዚህ በተቻለሽ መጠን ከክርስትና ጋር የተያያዙ መረጃዎችን ብቻ ብታቀርቢ የተሻለ ይመስለኛል:: በተጨማሪ ደግሞ አምስቱም የስሜት ህዋሳት አንድ ይሆናሉ የሚለው በደንብ አልገባኝም:: እንዴት ነው ለምሳሌ በሚሳሳሙበት ጊዜ አይኖቻቸው የሚጋጠሙት? ወይም ጆሮዎቻቸው? ይቅርታ ስላልገባኝ ነው::

አክባሪሽ
ዲያና
Pray for Oneness!!!
ዲያና
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 364
Joined: Tue Mar 09, 2004 2:25 am

Postby ብርኃናዊት » Wed Dec 05, 2007 7:01 pm

እንደምነሽ ዲያና:

ሙሽሪት በአንድ አልጋ ሙሽራው በአንድ አልጋ
ይመስላሉ መልዐክ ክንፉን የዘረጋ

የሚለው ግጥም አለማዊ ስለሆነ ያንቺን (supportive explanation) ወይም ደግሞ ደጋፊ ገለጻ ያላላዋል :: ስለዚህ በተቻለሽ መጠን ከክርስትና ጋር የተያያዙ መረጃዎችን ብቻ ብታቀርቢ የተሻለ ይመስለኛል :: በተጨማሪ ደግሞ አምስቱም የስሜት ህዋሳት አንድ ይሆናሉ የሚለው በደንብ አልገባኝም :: እንዴት ነው ለምሳሌ በሚሳሳሙበት ጊዜ አይኖቻቸው የሚጋጠሙት ? ወይም ጆሮዎቻቸው ? ይቅርታ ስላልገባኝ ነው ::


ስለመልካም አስተያየቱ እግዚአብሔር ይስጥልኝ:: ጥያቄዎችን የአቅሜን ያህል ለመመለስ ዝግጁ ነኝ:: ከኔ አቅም ውጭ የሚሆኑትን ደግሞ ሌሎች እውቀቱ ያላቸው ሰዎች እየሞሉበት በትዳርና በሩካቤ ዙርያ ያሉትን የተሳሳቱ ግንዛቤዎች አብረን እንሞርዳቸዋለን ብዬ ነበር ይህን ቤት የከፈትኩት::

ወደጥያቄሽ ስገባ በቅድሚያ "አምስቱ ህዋሳት" የተባሉት እኛ በሳይንስ የምናውቃቸው አምስቱ የስሜት ህዋሳት አይደሉም:: የመጽሀፉ ጸሀፊ "አፍ ከአፍ: እጅ ከእጅ...." ብሎ ያቆመው የቀረውን እናንተው ጨርሱት ብሎ በጨዋ ደንብ መግለጹ ነው:: እና "አይንና አይን ትይዩ መሆናቸው: አፍና አፍ ትይዩ መሆናቸው: እጆች ትይዩ መሆናቸው: ከዚያም ያላለቁት ደግሞ ወረድ ስንል የምናገኛቸው ዋናዎቹን የስሜት አካላት ማለት ነው:: (chest/breast and genitals):: በተጨማሪም "ይገጥማሉ" የሚለው አባባል በአካል መገጣጠም ብቻ ሳይሆን ትይዩ መሆንንም ያመለክታል:: ለምሳሌ አይንና አይን በምንም ታሪክ በአካል አይገጥምም:: በዚህ አገላለጽግን ትይዩ ይሆናል ለማለት ነው::

ሌላው ጥያቄሽ አለማዊ ዘፈን ለምን እንደማስረጃ ታቀርቢያለሽ የሚል ነው:: ዘፈኑ እንደማስረጃነት የቀረበው ስለ አተኛኘት አቅጣጫው አግባብነት ሳይሆን በባህላችን ይህ መጽሀፍ ቅዱሳዊ የአተኛኘት አቅጣጫ የተለመደ መሆኑን ለማሳየት ነው:: በጽሁፉ መግቢያ ላይ እንዲህ የሚል ጽሁፍ አስፍሬ ነበር:

እውነት እናትና አባቶቻችን ሩካቤ ሲፈጽሙ በሌላ አቅጣጫ መፈጸም እንደሚችሉ ሳያውቁት ቀርተው ነው ወይስ ሀይማኖታዊ ምክንያት ስላላቸው ነው ?


ይህን አረፍተ-ነገር የተመለከት ሰው "እናትና አባቶቻችንስ ቢሆኑ በሌላ መልክ ሩካቤ ይፈጽሙ አይፈጽሙ ምን የምናውቀው ነገር አለ? አላየናቸው!" ብሎ ሊያስብ ይችላል:: ነገር ግን የሰርጉን ግጥም የጠቀስኩት በአንድ አልጋ ላይ ተቃቅፎ መተኛት የሚለው እሳቤ በብዙዎች ዘንድ የተለመደና ተቀባይነትን ያገኘ እንደነበረ ለማስረዳት ነው:: (ግጥሙ የአለማዊ ዘፈን ግጥም መሆኑ ጠፍቶኝ አይደለም ማለቴ ነው):: አንድ ስነ-ቃል በወቅቱ የነበሩትን ህዝቦች አስተሳሰብና ባህል የማንጸባረቅ ኃይል ስላለው ያንን እንደማስረጃ መጠቀሜ ነበር:: አጻጻፌ ላይ ግልጽ ባለመሆኑ ይቅርታ!!

ብርኃናዊት
ብርኃናዊት
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 3302
Joined: Sat Oct 27, 2007 3:57 am

Postby ብርኃናዊት » Wed Dec 05, 2007 7:48 pm

ሰላም አንባቢዎች:

ለዛሬ ደግሞ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ቀኖናና በመጽሀፍ ቅዱሳዊ አስተምህሮ የተከለከሉ የሩካቤ ስጋ ገጽታዎች መሀል ቁጥር 5 እና ከሱ ጋር የተያያዙትን ቁጥር 1, 8, 9 እና 10 አብረን እናያቸዋለን::

5. ያለጊዜው የሚፈጸም ሩካቤ (እግዚአብሔር በሰጠን 24 ሰአት ውስጥ ሩካቤ መፈጸም የሚገባው በሌሊቱ/በምሽቱ ክፍል ብቻ ነው እንጂ በቀን ብርኃን ሩካቤ መጽሀፍቅዱሳዊ አይደለም)
1. ከጋብቻ በፊት የሚፈጸም ሩካቤ
8. በአበይት በአላት: በጾምና በሰንበት ቀን የሚፈጸም ሩካቤ
9. በወር አበባ ጊዜ የሚፈጸም ሩካቤ
10. በርግዝና ጊዜ የሚፈጸም ሩካቤ1. ከጋብቻ በፊት የሚፈጸም ሩካቤ

ለመሆኑ ከጋብቻ በፊት ድንግልናን ማጣት ምን ችግር አለው?

ድንግልና ማለት ክብረ ስጋ: ማኅተመ ስጋ: ማኅተመ ህሊና ማለት ነው:: ከዚህ ትርጉም እንደምናየው ሁለት አይነት ድንግልና አለ:: የስጋ ድንግልና እና የኅሊና(የልቦና) ድንግልና:: የስጋ ድንግልና ብሩካቤ የሚፈርስ ሲሆን የልቡና/የኅሊና ድንግልና ግን በሀሳብ የሚፈርስ ነው:: ብዙዎቻችን ይህን ድንግልና በቀላሉ እናጣዋለን:: ለመጠበቅ እጂግ ከባድ ነው:: ምክንያቱም ስለሩካቤ የሚያሳስቡ ፊልሞች: ሰዎች: መጻህፍቶች: ድርጊቶች ወ ዘ ተ በአሁኑ ጊዜ እንደአሸን ስለፈሉ ነው:: (በነገራችን ላይ ስለሩካቤ ማወቅ/ማሰብ ማለትና የኅሊናን ድንግልና ማጣት ማለት የግድ አንድ አይነት አይደሉም:: የህሊና ድንግልና የሚጠፋው አንድ ሰው ለከት በሌለው ምኞት "እንዲህ ባደርግ" "እንዲህ ቢሆንልኝ" "ከእከሌ ጋር እንዲህ ብሆን" እያለ የሚመኘው ምኞት የሚወልደው የሀሳብ ሀጥያት ነው:: ስለሩካቤ በጤናማ መልክ ማሰብና ማወቅ ግን አግባብ ነው:: )

ሁለቱንም ድንግልና በመጠበቅ ቀደምት አርአያ የምትሆነን ቅድስት ድንግል ማርያም ናት:: እርሷ በሀሳቧም ድንግል ነች: በስጋዋም ድንግል ነች:: ነገር ግን ስለሩካቤ ጭራሽ አታውቅም ነበር ማለት አይደለም:: መላኩ ቅዱስ ገብሬል ልጅ እንደምትወልድ ሲያበስራት "ወንድ አላውቅምና ይህ እንዴት ይሆንልኛል?" ብላ መጠየቋ ሩካቤ በተቃራኒ ጾታ መሀል የሚፈጸምና ልጅ የሚያፈሩበት ምግባር እንደሆነ እንደምታውቅ ያሳየናል:: ነገር ግን በኅሊና ድንግል ናት ማለታችን ዝም ብላ ብቻ በምኞት ይህን እያሰበች የምትኖር አይደለችም ማለታችን ነው::

የስጋም ይሁን የነፍስ ድንግልናን እስከጋብቻ ድረስ መጠበቅ እጅግ በጣም ትልቅ መንፈሳዊ ጸጋን ያሰጣል:: እግዚአብሔር መንፈሳዊ ጸጋ ሲያበዛልንና ትዳራችንን ሲባርክልን በኛ አይን ላይታይ ይችላል:: ነገር ግን ድንግልናን እስከጋብቻ ድረስ መጠበቅ እኛ በማናውቀው መልኩ ከብዙ አይነት የአለም ፈተናና የሰይጣን ወጥመድ ከልሎ በእግዚአብሄር ቤት ሊያኖረን የሚያስችል ጸጋ አለው:: ድንግልናን መጠበቅ በራሱ ተጋድሎ ነው:: ሀይማኖታዊ ምግባር ነው:: ልክ አንድ ሰው ሩጫ ተወዳድሮ አሸንፎ ሲጨርስ ሜዳልያ እንደሚሰጠው ሁሉ በዚህ የወጣትነት የቤት ስራ አልፎ ጋብቻ ጋር መድረስ የቻለ ሰው በምድርም በሰማይም ሽልማት ይሰጠዋል:: በምድር በቤተክርስቲያን የተክሊል ስርአት ሲፈጸም አክሊል ይደረግለታል- ይህ አክሊል ሰማእታት አለምን ንቀው ለክርስቶስ ደማቸውን ሲያፈሱ የሚሰጣቸውን አይነት የድል አክሊል ይወክላል:: በሰማይ ደግሞ መላእክት በአካለ ነፍሱ ላይ የድል አክሊል ያቀዳጁታል:: ይህም ከእግዚአብሔር የሚሰጠው እሱን: ቤተሰቡንና የሚወልዳቸውን ልጆቹን የሚያስባርክበት ትልቅ ጸጋ ነው:: ድንግልናውን ያጣ ሰው ከልብ ንስሀ በመግባትና የንስሀ (የመአስባን) ጋብቻ በመፈጸም: አግብቶ ከሆነም ደግሞ ንስሀ ገብቶ ከባለቤቱ ጋር ሆኖ ስጋና ደሙን በመቀበል ያጣውን ጸጋ መልሶ እጁ ማስገባት ይችላል:: ለዚህ እንግዲህ ልክ እንደያዕቆብ መሽቀዳደም ይገባል!!!

ድንግልና የመንፈስ ጸጋ እንደሚያስገኝና እኛ ከማናውቀው ክፉ ነገር ሁሉ እግዚአብሄር እንዲጠብቀን እንደሚያስደርግልን የምታሳየን ዋናዋ ምሳሌያችን አሁንም እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ናት:: በዮሀንስ ራእይ መዕራፍ 12 ላይ እንዲህ የሚል ጽሁፍ እናገኛለን:

ታላቅ ምልክትም በሰማይ ታየ:: ጸሀይን ተጎናጽፋ ጨረቃ ከእግሮቿ በታች ያላት በራሷም ላይ 12 ከዋክብት አክሊል የሆነላት አንዲት ሴት ነበረች:: እርሷም ጸንሳ ነበር: ....

ይልና ወረድ ብሎ

ዘንዶውም ሴቲቱ በወለደች ጊዜ ሕጻንዋን እንዲበላ ልትወልድ ባላት ሴት ፊት ቆመ:: አህዛብን ሁሉ በብረት በትር ይገዛቸው ዘንድ ያለውን ልጅ ወንድ ልጅ ወለደች...

ከዚያም ወረድ ብሎ እንዲህ ይላል:

ዘንዶውም ወደምድር እንደተጣለ ባየ ጊዜ ወንድ ልጅ የወለደችውን ሴት አሳደዳት:: ከእባቡም ፊት ርቃ አንድ ዘመን: ዘመናትም የዘመንም እኩሌታ ወደምትመገብበት ወደስፍራዋ ወደበረሀ እንድትበር ለሴቲቱ ሁለት የታላቁ ንስር ክንፎች ተሰጣ:: .....ምድርም ሴቲቱን ረዳቻት: ምድሪቱም አፍዋን ከፍታ ዘንዶው ያፈሰሰውን ወንዝ ዋጠችው::...

ይለናል:: እንግዲህ ሴቲቱ የተባለችው ቅድስት ድንግል ማርያም በሰይጣን አነሳሽነት ልጇን ሊገድሉባት የፈለጉትን የሄሮድስ ሰራዊት ሸሽታ ወደግብጽ በርሀና ከዚያም ወደኢትዮጵያ መሰደዷን አስመልክቶ የተጻፈ ጽሁፍ ነው:: የተሰመረበት ቃል እንደሚነግረን ሁለቱ ክንፎች የተባሉት በሁለቱ ድንግልናዎቿ (በስጋና በነፍስ) ምክንያት ያገኘቻቸው የእግዚአብሔር ጸጋዎች ናቸው:: ይህ ጸጋዋ በስደቷ ጊዜ ሁሉ በየመንገዱ ከገጠማት ፈተና እየሰወረ በህይወት እንድትቆይ እንደረዳት የቃሉ ምስጢራዊ ትርጉም ያስረዳናል:: ስለዚህም ድንግልናን መጠበቅ በነፍሳችን እንዲህ ያለ በረከት ያስገኝልናል::

አለዚያ ግን ራሳችንን ለፈተና አመቻችተን እያቀረብን ሲሆን የተሰጠንን የወጣትነት የቤት ስራም መወጣት ባለመቻላችን የሚሰጠንን የድል አክሊል ያስቀርብናል::

ይቀጥላል::
ብርኃናዊት
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 3302
Joined: Sat Oct 27, 2007 3:57 am

Postby ብርኃናዊት » Wed Dec 05, 2007 8:56 pm

የቀጠለ...

5. ያለጊዜው የሚፈጸም ሩካቤ

ከላይ እንደተገለጸው እግዚአብሔር በሰጠን 24 ሰአት ውስጥ ሩካቤ መፈጸም የሚገባው በሌሊቱ /በምሽቱ ክፍል ብቻ ነው እንጂ በቀን ብርኃን ሩካቤ መፈጸም መጽሀፍቅዱሳዊ አይደለም:: ለመሆኑ ከመጽሀፍ ቅዱስ ምን እንማራለን?

ምንም እንኳ ጋብቻ ውስጥ ሩካቤ የተፈቀደ ቢሆንም አሁንም ቢሆን አፈጻጸሙ ጊዜ አለው:: በመጽሀፍ ቅዱስ ውስጥ በደጋግ (ጻድቃን) አባቶችና ሚስቶቻቸው መሀል ይደረጉ የነበሩ ሩካቤዎች በጨለማ (በስውር) የሚደረጉ ነበሩ:: ለምሳሌ ያዕቆብ ከህግ ባለቤቱ ከልያ ጋር ተኝቶ ልያ አምስተኛ ልጇን ይሳኮርን በጸነሰችበት ጊዜ ግንኙነታቸው በሌሊት እንደነበር በመጽሀፍ ቅዱስ ላይ በግልጽ ተጽፏል:: ዘፍ 30:15-16 በተጨማሪም ጻድቁ ኢዮብ መከራ በጸናበት ጊዜ የተወለደበትንና የተጸነሰበትን እለትና ሰአት ሲረግም "ያ የተወለድኩበት ሰአት ይጥፋ: ያም ወንድ ልጅ ተጸነሰ የተባለበት ሌሊት" በማለት ተናግሯል:: ኢዮ 3:3:: የኢዮብ እናትና አባት ኢዮብን ያገኙበት ሩካቤያቸው በምሽት እንደተፈጸመ የሚያስረዳን ሲሆን ኢዮብ ሩካቤ የሚፈጸምበት ሰአት ሌሊት እንደሆነ በውስጡ ያለውን ግንዛቤም ያሳየናል:: ኢዮብ ጻድቅ አባት ስለሆነ የርሱን አርአያነት መከተል መልካም ይሆናል:: ሌላው የያእቆብና የልያ ታሪክ የሚያሳየን ነገር አለ:: ያዕቆብ በጫጉላ ጊዜ ወደተዘጋጀለት መኝታ ሲገባ አብሯት ያደረው ራሔል መስላው ነበር:: ነገር ግን ሲነጋ ልያ ሆና ተገኘች::ዘፍ 29: 21-26 ይህ የተከሰተው ሩካቤው የተፈጸመው በምሽት ጊዜ ስለሆነና ልያን ተገላልጣ በቀን ብርሀን ስላልተመለከታት ነው::

ሩካቤ በሌሊት የሚፈጸመው ኃጥያት ስለሆነ ሳይሆን ሩካቤ የጋብቻ ምስጢር ስለሆነ ነው:: ከዚህ ጋር በተያያዘ በቅዱስ ዮሀንስ አፈወርቅ የተግሳጽ መጽሀፍ ውስጥ " ዳግመኛም ከሚስትህ ጋር ሁነህ በአንድነት የምትሰራውን ስራ ስጋዬ ናትና አስነቅፋታለሁ ብለህ ባደባባይና በገበያ አትሰራውም" የሚል ቃል እናገኛለን: ሩካቤ በተወሰነ መልኩ ስውርነቱን መጠበቅ ለሩካቤ ክብርን መስጠት ነው::

አዳም የምትረዳው ሄዋን ስትፈጠርለት እግዚአብሔር አዳም ላይ ከባድ እንቅልፍ እንዲወድቅበት ማድረጉ አዳምና ሔዋን ሩካቤያቸውን በምሽትና በስውር መፈጸም እንዳለባቸው የሚያሳይ ነው:: እንቅልፍ የምሽት ተግባር ነውና::

አዳምና ሄዋን በሰሩት ኃጥያት ምክንያት የጸጋ ልብሳቸው በተገፈፈ ጊዜ "ከኛ ሌላ የሚመለከተን ሰው በዙሪያችን የለም" በማለት እንደልባቸው አልሆኑም:: እርስ በርሳቸው እንኳ ተፋፍረው በአካላቸው ላይ ግልድም በማድረግ ኃፍረተ ስጋቸውን ሸፍነዋል እንጂ:: ስለዚህም ሌላ ሰው እንኳ በአጠገባቸው ባይኖር ባልና ሚስት እርቃናቸውን ሆነው እርስ በርስ እየተያዩ በቀን የሚፈጸሙት ሩካቤ ቢያንስ አዳምና ሄዋን እንኳ በልቦናቸው የተገለጠላቸውን እውቀት ማጣታቸውን ያመለክታልና መጽሀፍ ቅዱሳዊ አይደለም:: ባልና ሚስት እርቃናቸውን የተመለመለ ግንድ መስለው እንደፈለጉ እየተያዩ ሩካቤ ሲፈጸሙ ቆይተው ድርጊቱ ካለፈ በኍላ ግን ከባድ የስነ-ልቦና ሀፍረት ውስጥ ሊገቡ ይችላሉ:: በዚህ በኩል ራሳቸውን በደፋርነት ባለማመዱት መጠን ደግሞ ለራሳቸውና ለሰውነታቸው ያላቸው ክብር ቀንሶ ቀንሶ ይሄድና በኍላ የባሰበት ነገር ከመፈጸምና ብሎም ከትዳር ውጭ መሄድ ሁሉ ምንም አይመስላቸው ይጀምራል:: የሩካቤ ጋጠወጥ አፈጻጸምና የሀሽሽ ሱስ አንድ ነው:: ዛሬ ቆርኪ የምትሞላ ሀሽሽ የተጠቀመ ሰው ነገ የቆርኪዋ ያህል መጠን ምንም አያደርግለትም:: ስለዚህ በኩባያ መውሰድ ይጀምራል: ከዚያ በባልዲ: ከዚያ በበርሜል.... እያለ ይቀጥል ይሆናል: መቼም ሰው በመሆኑ በመሀል ተጎድቶ ከጥቅም ውጭ ስለሚሆን ማቆሙ አይቀርም እንጂ! ሩካቤም እንደዚያው ነው:: አንድ ጋጠወጥ ነገር ዛሬ ፈጸመን እንደሆነ ነገ በተመሳሳይ በርሱ ብቻ አንደሰትም: ሌላ የባሰበት ተጨማሪ አዲስ ነገር እንፈልጋለን:: በኍላ ጭራሽ ሁሉ ነገር በትዳራችን ውስጥ ይሰለቸንና ሌላ የባሰበት እብደት የሚያሳየን ሰው ፍለጋ ደግሞ እንሄዳለን:: ይህ እብደት ውስጥ ከመግባት በፊት በሁሉ ነገር ላይ የልክ ገደብ መጣል ይገባል::

በሙሉ ብርሀን ሁለንተናቸውን እየተያዩ ሩካቤን መፈጸም በስሜት ላይ የሚያስከትለው ችግር ሌላ ባልና ሚስት በተያዩ ቁጥር ሩካቤ ብቻ እንዲታወሳቸው በማድረግ ወደ እንሰሳዊ ተግባር ይዞዋቸው ከመሄዱም በተጨማሪ መሰለቻቸትን በመፍጠር "ለዚሁ ሴትነትሽ ነው?" "ለዚሁ ወንድነትህ ነው?" እስኪባባሉ ድረስ መናናቅን መሀከላቸው በማምጣት እንዳይነፋፈቁ ሊያደርጋቸው ይችላል:: ከዚህ በተጨማሪ በተለይ በሴት ልጅ ተክለ ቁመና ዙርያ ያሉትን perfectionistic ግንዛቤዎች በማስፋፋት ረገድ ሩካቤን በግላጭ እንደመፈጸም ያለ መጥፎ መንገድ የለም:: ለምሳሌ በውቅያኖስ ዳርቻ (Beach) በአጭርና ግልጽ የውስጥ ልብሶች ለመዝናናት እየፈለጉ ሰውነታቸው ላይ ባለው ጠባሳ: ቦርጭ: ወይም የሆነ ስጋዊ እንከን ምክንያት ያንን ሊያደርጉ ባለመቻላቸው
ከባድ የስነ-ልቦና ጫና የተፈጠረባቸው በሚልየን የሚቆጠሩ ሴቶች አሉ:: እነዚህ ሴቶች ቁመናቸው ሲታይ እንዲያምርና ሌላውን እንዲስብ በሚል ፍላጎት በጣም ውድና ጎጂ የሆኑ የፋት ማስወገጃ ህክምናዎች: የፕላስቲክ ቀዶ ጥገናዎች: የጠባሳ ማስወገጃ የጨረር ህክምናዎች ወዘተ ለመጠቀም እየተገደዱ መጥተው በስተመጨረሻ ያልጠበቁት ጣጣ ውስጥ በመግባት ለከባድ ጉዳት የተዳረጉ በጣም ብዙ ሴቶች አሉ (ይህ የአደባባይ ምስጢር ነው: በአሁን ጊዜም ብዙዎች እየተወያዩበት ነው:: የውበት ትርጉምም መረን ለቆአል: ወደቦታው ይመለስ የሚሉም ምሁራን ቁጥራቸው እየጨመረ ነው):: ይህን ነጥብ ያመጣሁበት ምክንያት በቀንና በግላጭ እየተያዩ ሩካቤን ለመፈጸም መፈለግና እርቃንን መተያየት እንዲህ ያለ አካላችን ላይ ያከ እንከን እንዳይታይ የምንፈልግበት አይነት ጫና በሴቶች ላይ ማምጣቱ ስለማይቀር ለራሳችን ያለን ግንዘቤና በሰውነታችን ለማፈር ያለንን ዝንባሌ ይጨምረዋል:: ይህ ነገር አሁን አሁን ለወንዶችም ቢሆን አልቀረላቸውም:: እነሱም ከዚህ ጫና እያመለጡ አይደለም:: ስለዚህ ለሰውነት የሚገባውን ክብር በመስጠት በሌሊት ሩካቤን መፈጸም እንዲህ ካለው መሸማቀቅና አጉል ቅብጠት ያድናል::

ከዚህ በተጨማሪ ሩካቤ ለእግዚአብሔር የሚቀርብ መባ ነው:: ሩካቤ ሀይማኖታዊ ገጽታ ያለው የስጋ ስራ ነው:: (ልክ ምግብ እንደመብላት ሁሉ) ሩካቤ ክቡር ነው:: ብሔረ ብጹአን በሚባል ቦታ በእግዚአብሔር ጠባቂነት ተከልለው የሚኖሩ ጻድቃን ሩካቤን የሚፈጽሙት በጋብቻቸው ሁለቴ ብቻ ሲሆን አንዱ ልጅ ለመውለድ ሲሆን አንዱ ደግሞ ለእግዚአብሔር መባ በማለት ነው:: ታሪኩን ተንተን አድርጌ ለማስረዳት- ብሔረ-ብጹአን የሚባል አለም አለ::ይህ አለም እኛ ከምንኖርባት ምድር እጅግ በጣም የጸዳ ነው:: እኛ ለምንኖርባት ምድርም በጣም ቅርብ ነው:: ነገር ግን በአይን አይታይም:: በሌላ የህልውና ርግብግቢት (vibration/spectrum) ነው ያለው:: ገነት ግን አይደለም:: ከገነት ሌላ ብሄረ-ህያዋን የሚባል እነ ሄኖክ: እነ ዮሀንስ: እነ ኤልያስ ተነጥቀው የተወሰዱበት ቦታ አለ:: በብሄረ-ብጹአን በመንፈሳዊ ተጋድሏቸው ምክንያት እግዚአብሔርን የሚያስደስት ኑሮ ያሳዩ የተወሰኑ ሰዎች በአንድ ወቅት ተነጥቀው ተወስደው እስካሁን ድረስ የሚኖሩበት ቦታ ነው:: ይህን ቦታ የግብጹ መነኩሴ ዞሲማስ እንዲገለጸለትና ሄዶ እንዲያያቸው 40 አመት ሙሉ ሱባኤ በመግባት እግዚአብሄርን ሲለምን ከኖረ በኍላ በ40ኛው አመት ጸሎቱ ሰምሮለት በደመና ተነጥቆ ወደዚያች ምድር ተወስዶ የሰዎቹን አኗኗር አይቶ ተመልሷል:: ይህ መነኩሴ ያየው ነገር በዚያ አለም የሚኖሩት ሰዎች ይጋባሉ: ይዋለዳሉ: ነገር ግን ኃጥያት የሚባል ነገር በመሀላቸው አይታወቅም:: ባልና ሚስትም ሩካቤን የሚያደርጉት ሁለቴ ብቻ ሲሆን ከላይ እንደተገለጸው አንዱ ዘር ለመተካት ሲሆን ሌላኛው ለእግዚአብሔር መባ ነው::

ወደዚህ ትንታኔ የገባሁት ሩካቤ በሌሊት ሲፈጸም በፍጹም ተመስጦና ሀሳብ ሳይበታተን መሆን እንዳለበት ለመግለጽ ነው:: ምክንያቱም የእግዚአብሔር መባ በቸልታ ሊደረግ አይገባውም:: ምግብን እየዘፈንን ወይም እየተንጎራደድን ወይም ሌላ ነገር እየሰራን መብላት የእህሉን ክብር ማሳነስ እንደሚሆንብን ሁሉ ማለት ነው:: አባቶች ሲያስረዱ "የቀን ልቦና ባካና ነው: የሌሊት ግን ክት ነው" ይላሉ:: ቀን ላይ "ሰው መጣ አልመጣ: ሰው አየኝ አላየኝ" እያሉ የሚፈጽሙት ሩካቤ የሩካቤውን ክብር የሚያሳጣና መባነቱን የሚያስቀር ነው:: በተጨማሪም ሳይንስ ሳይቀር እንዳረጋገጠው በተለይ ሴት በሩካቤ ጊዜ የምታስበውና የሚሰማት ስሜት የምትጸንሰው ልጅ ላይ ተጽእኖ እንደሚኖረው እየገለጹ ነው:: በዚህም ምክንያት "a fetus has a hidden/invisible antenna" ወይም "ጽንስ የማይታይ አንቴና አለው" ለማለት ተገደዋል:: ያም ማለት በእናቱና በአካባቢዋ ያለውን ስሜት ያጠናል: decode ያደርጋል: perceive ያደርጋል: ይቀርጻል ማለት ነው:: በዚህም ምክንያት በእንዲህ አይነት ብኩን ልቦና የሚፈጸም ሩካቤ የጽንሱን "ንድፍ" (ማለትም ሲያድግ ምን አይነት ልጅ እንደሚሆን የሚቀርጹትን እምቅ ሀይሎች) እንዲዛቡና ለአእምሮ በሽተኝነት ወይም ለሌላ የስሜት አለመረጋጋት የተጋለጠ ልጅ (ልብ በሉልኝ: የግድ ይጋለጣል ማለት አይደለም: ነገር ግን ለመጋለጥ ያለው እድል ሰፊ ነው ማለት ነው) እንዲጸነስ ያደርጋል::

ስለዚህ ሩካቤ የሚፈጸምበት የሌሊቱ (የምሽቱ) ክፍል መሆኑን ተረድተን ቅጥ ያጣ የሩካቤ ህይወት ውስጥ እንዳንገባ ራሳችንን ለመጠበቅ ይርዳን!

ይቀጥላል!
ብርኃናዊት
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 3302
Joined: Sat Oct 27, 2007 3:57 am

PreviousNext

Return to Warka Intimate - ዋርካ ፍቅር

Who is online

Users browsing this forum: No registered users and 2 guests