የኢትዮጵያ ቤ/ክ የጾታ ትምህርት- ማንበብ ለሚፈልግ

The Love Forum (love, relationship) (የኔ ቆንጆ እንተዋወቅ :-)

Postby ሀሁሁሁ » Wed Dec 05, 2007 10:00 pm

ከላይ እንደተገለጸው እግዚአብሔር በሰጠን 24 ሰአት ውስጥ ሩካቤ መፈጸም የሚገባው በሌሊቱ /በምሽቱ ክፍል ብቻ ነው እንጂ በቀን ብርኃን ሩካቤ መፈጸም መጽሀፍቅዱሳዊ አይደለም


መጽሀፍቅዱስ በቅድስና በትዳር ውስጥ የተፈቀደ መሆኑን ይናገራል እንጂ ስለ ቀን ለሊት የሚባል FORMULA አላወጣልንም ..በዘፍ 26 :8 ላይ አቤሜሌክ ይስሐቅ ሚስቱን ርብቃን ሲዳራ በመስኮት አየው ይላል..አልመሸም ነበር ማለት ነው

አዲስ ኪዳን ላይ ደግሞ 1ኛ ቆሮ 1-5 ላይ

" ለጸሎት ትተጉ ዘንድ ተስማምታችው [u] ለጊዜው[/u ካልሆነ በስተቀር እርስ በርሳችው አትከላከሉ "

የሚለው እንጂ ስለ ቀንና ለሊት አይናገርም

ማብራሪያውን ወድጄዋለሁ ግን መፅሀፍ ቅዱስ በለሊት ብቻ
ይደረግ ብላል የሚለው ማጠቃለያ መስመር የለቀቀ ስለመሰለኝ ነው ...
ሀሁሁሁ
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 308
Joined: Fri Jan 20, 2006 11:44 pm

Postby ብርኃናዊት » Wed Dec 05, 2007 10:15 pm

የቀጠለ:

8. በአበይት በአላት : በጾምና በሰንበት ቀን የሚፈጸም ሩካቤ


ትርጉም-

ሰንበት- ቅዳሜና እሁድ (እንዲሁም በቤተ-ክርስቲያኗ ወኖና መሰረት የእመቤታችን: የሚካኤልና የበአለወልድ (29) ቀን እንደእሁድ ሰንበት እንዲከበሩ ያዛል)
አበይት በአላት- የጌታ 9 በአላት (ብስራት: ልደት: ጥምቀት: ደብረ-ታቦር: ሆሳእና: ስቅለት: ትንሳኤ: እርገት እና ጰራቅሊጦስ ናቸው)

ጾም- ማንኛውም የአዋጅም ሆነ የግል ጾም (ሁዳዴ: ሮብና አርብ: የገና ጾም: የገሀድ ጾም /ወይም በተለምዶ ጾመ-ጋድ የሚባለው/: የነነዌ ጾም: የሰኔ ጾም: እና የፍልሰታ ጾም ናቸው)

**የጳጉሜና የጽጌ ጾሞች የፈቃድ ጾም ስለጾሙ ባልና ሚስት እነዚህን ጾሞች ለመጾም ከፈለጉ ከሩካቤ መታቀብ አለባቸው: ካልሆነ ግን ሩካቤ የመፈጸም መብታቸው የተጠበቀ ነው::

ለመሆኑ በሰንበት ቀን ከተጸነሱ ሰዎች መሀል ማንን ማንን እናውቃለን? (ልብ በሉ ከክርስቶስ ልደት በፊት ሰንበት ማለት ቅዳሜ ነበረች:: እሁድ የስራ ቀን ነበር:: ከክርስቶስ ልደት በኍላ ግን እሁድ ትልቋ ሰንበት ሆነችና ቅዳሜዋ "ቀዳሚት ሰንበት" ወይም "የበፊቷ ሰንበት" ተባለች:: ሁለቱም ግን በኢትዮጵያ ቤተክርስቲያን ቀኖና ሰንበት ተብለው ታውጀዋል:: ከክርስቶስ ልደት በፊት እመቤታችን የተጸነሰችው በእለተ-እሁድ ነበር- ያም ማለት እናትና አባቷ ሰንበት ሻሩ ማለት አይደለም- እሁድ ገና ሰንበት አልሆነችም ነበርና)

እና አንድ በእለተ ቀዳሚት (ሰንበት) የተጸነሰ ሁላችንም የምናውቀው ሰው አለ- ያም ሰው ይሁዳ ይባላል:: ይሁዳ በመጽሀፍ ቅዱስ "የጥፋት ልጅ" ተብሏል:: የጥፋት ልጅ የተባለው አንዱ ምክንያት ልጅነቱን/ውልደቱን ያስገኘችው ሩካቤ የተፈጸመችበት ሁኔታ ጥፋት በመሆኑ ነው:: ያም ማለት የተወለደው ከናት ካባቱ ከህግ ጋብቻ ነው:: ነገር ግን ሩካቤው የተፈጸመው በሰንበት እለት ነበር::

ለመሆኑ በሰንበትና በበአል ለምን ሩካቤ ይከለከላል?

የክርስቲያን ሰንበት ማለት በኦሪት ከነበረችው የአይሁዶች ሰንበት ፍጹም ትለያለች:: በኦሪቱ ሰንበት የሚታሰበው ምንም ስራ ሳይሰሩ እጅ እግርን አጣጥፎ በር እንኳ ሳይከፍቱ ሳይዘጉ በመዋል ሲሆን የክርስቲያን ሰንበት ግን የምትከበረው የነፍስን ስራ በመስራት ነው:: በሰንበት ልንሰራ የሚገቡን ብዙ የነፍስ ስራዎች ያሉ ሲሆን ከነዚህ መሀል ሩካቤን አናገኝም:: ሩካቤማ ከነስሙ እኮ "ግብረ-ስጋ" ነው የሚባለው- ግብረ ነፍስ አይደለም:: ለበአላትም ቢሆን እንደዚያ ነው:: በአላትና ሰንበታት የሰማዩን ኑሮ የምናስብባቸው እለታት ናቸው:: እግዚአብሔር የሰው ልጅ በዚህ ምድር ሲኖር ተስፋ መንግስተ-ሰማያትን እንዲያስብና ፈራሽ በስባሽ ብቻ ሳይሆን በትንሳኤ ተነስቶ ፍርድ የሚቀበል እንደሆነ እንዳይረሳ ለማድረግ የበአላትንና የሰንበትን ስርአት ሰርቶልናል:: ያም ማለት ሰው ከሰኞ እስከአርብ ምድራዊ ስራ ሲሰራ ቆይቶ ቅዳሜና እሁድ ሲደርሱ ግን (ቢያንስ ቢያንስ እሁድን) በፍጹም ተመስጦ ሰማያዊ ነገርን እያሰበና መንግስተ-ሰማያትን እያሰበ በቅዳሴ: በጸሎት: በምጽዋት: የታመመ በመጠየቅ: የታረዘ በማልበስ: የታሰረ በመጎብኘት: የተራበ በማብላት እንድናሳልፈው ይፈልጋል:: ይህ የሳምንት ኡደት እጅግ ጤናማ የሆነ የሰው ልጅ መንፈሳዊና ስነ-ልቦናዊ በረከት ያሰጠዋል:: ስለዚህ አንድ ሰው በአንዲት ሰንበት መላውን ሳምንት ማስባረክ ይችላል:: ታድያ በሰንበትና በአበይት በአላት የምናስበው መንግስተ-ሰማያትን ነው:: በመንግስተ-ሰማያት ደግሞ እንደመላእክት እያመሰገኑ መኖር እንጂ ማግባት መጋባት: ሩካቤ መፈጸም መዋለድ የሚባል ነገር የለም:: ይህን ጌታ ራሱ በወንጌል ነግሮናል:: በሰንበት ወደ ቤተ-ክርስቲያን መሄድና ከተቻለ ስጋ ወደሙ መቀበልም ተገቢ በመሆኑ ይህን ለማድረግ የሚፈልግ ክርስቲያን ስለቅዱስ ቁርባንና ስለ ቤተ-ክርስቲያን ክብር ሲል ከሩካቤ መታቀብ አለበት::

መጽሀፍ ቅዱሳችን ሰንበትን ከስጋ ስራ ተከልለን በፍጹም መንፈሳዊ ስራት እንድናከብረው የሚከተለውን ያዘናል:

"ፈቃድህን በተቀደሰው ቀኔ ከማድረግ እግርህን ከሰንበት ብትመልስ: ሰንበትንም ደስታ: እግዚአብሔር የቀደሰውንም "ክቡር" ብትለው: የገዛ ፈቃድህንም ከማግኘት ከንቱ ነገርም ከመናገር ተከልክለህ ብታከብረው: በዚያን ቀኔ በእግዚአብሔር ደስ ይልሀል: በምድር ከፍታዎች ላይ አወጣሀለሁ: የአባትህንም የያዕቆብ ርስት አበላሀለሁ: የእግዚአብሄር አፍ ተናግሯልና::" ኢሳ 58: 13-14

ስለዚህ በሰንበት ፈቃድህን ከማድረግ ተቆጠብ ማለቱ የመንግስተ-ሰማያት መግቢያ ጽድቅ እንዲሆነን ነው::

ሰንበት ማለት መንግስተ-ሰማያት የሚታሰብባት እለት ለመሆኗ ማስረጃ የሚሆን ከሰንበት ጋር በተያያዘ ሌላ አስደናቂ ነገር አለ:: እስቲ ለአንድ አፍታ ክርስቶስ በመጨረሻው ዘመን ተመልሶ መጥቶ ፍርድ ሰጥቶ ከዚያ ጻድቃን ወደመንግስተ-ሰማያት: ኃጣን ወደ ገሀነም ተጥለው ኑሯቸን የሚቀጥሉበት እለት ምንድነው ብለን እናስብ? መልሱ ሰንበት (እሁድ) ነው;: በፍርድ ቀንና ከዚያ በኍላ ያለው ጊዜ አሁን እንዳለንበት ጊዜ በእለታት የተከፋፈለ አይደለም:: ለሊትና ቀን የሚባል ነገር የለውም:: ነገር ግን ሁሌም እሁድ ይሆናል- የማይመሽ- የማይነጋ- የማያልፍ እሁድ ማለት ነው:: ለዚህ ማስረጃ የሚሆነን ምስጢራዊ ቃል በመጽሀፍ ቅዱስ የመጀመሪያ ክፍል ላይ ይገኛል::

"እግዚአብሔርም የሰራውን ስራ በሰባተኛው ቀን ፈጸመ: በሰባተኛውም ቀን ከሰራው ስራ ሁሉ አረፈ" ዘፍ 2:2

ይህ ቃል የሚያስረዳን የስነ-ፍጥረት መጀመሪያ በተከናወነበት መልኩ አስተላለቁም በዚያው መልክ እንደሚሆን ነው:: እግዚአብሔር በሰባተኛው ቀን ከሰራው ስራ ሁሉ አረፈ መባሉ ሰባተኛው ሺህ ባለቀ ጊዜ የተፈጠሩት ፍጥረታት ምድራዊ ኑሮ አብቅቶ ሰማይና ምድር እንደሚያልፉና ሰውም በፍርድ ጻድቁ ከኃጥኡ እንደሚለይ በትንቢት መልክ የተነገረው ቃል ነው:: እያንዳንዷ ቀን አንድ አንድ ሺህ አመትን ትወክላለች:: በዚህ አቆጣጠር ከሄድን ስምንተኛውን ሺህ እንደማንጨርሰው በግልጽ ያሳየናል::

የሰንበትን እለት የሚያከብሩ ነገር ግን በሌላው የኑሮ ገጽታቸው በጣም በኃጥያት የተነከሩ ሰዎች እንኳ በሰንበት ዕለት ከሲኦል እንደሚወጡና ሰኞ እንደሚመለሱ ድርሳነ ሰንበት የተባለው የቤተክርስቲያኗ መጽሀፍ ያስረዳናል:: እነዚህ ሰዎች በፍርድ ቀን በሰንበት ምክንያት ነጻነት ይሆንላቸዋል:: ከዚያን ቀን ጀምሮም ሰንበት ዘላለማዊ ሆና ሰፍና ስለምትኖር ተመልሰው ወደ ሲዖል አይወርዱም:: በዚያው ዳኑ ማለት ነው:: ይህ በሰንበት የመንፈስ ስራን መስራት ምን ያህል ክብር እንዳለው ያስረዳናል::

በበአላት በኩል ያለውም ስራት ተመሳሳይነት አለው:: በአላት ቃልኪዳን አላቸው:: ለሰው በረከትን የማሰጠት: ስለዚህ በነዚያ ቀን እለቱ የሚከበርበትን ምክንያት እያሰቡ ማክበር እንጂ የስጋ ግብር መፈጸም አይገባም::

በጾም ደግሞ ሩካቤ የሚከለከልበት ምክንያት ግልጽ ነው:: ጾም ምግባረ ነፍስ ስለሆነ ስጋን ከሚያስደስቱ ምቾት ከሚሰጡ ነገሮች ሁሉ መራቅ ስላለብን ነው:: በጾም ወቅት ባልና ሚስት መኝታ ለይተው ሲሆን ሱባኤውን ለማሰብ መሬት እያደሩ አምላካቸውን መማጸን አለባቸው:: ለዚህ ትልቅ ምሳሌ የሚሆኑን የእመቤታችን እናት ሀና እና ኢያቄም ናቸው:: በነገረ ማርያም እንደተጻፈው ሀና እና ኢዮአቄም መላክ መጥቶ ብስራት እስኪያበስራቸው ድረስ 7 ቀን መኝታ ለይተው መተኛታቸውን እናነባለን:: ይህ የሱባኤ አምሳል ነው:: ምክንያቱም ልጅ ከማጣት የተነሳ ኃዘን ላይ በነበሩበት ወቅት ያዩትን ህልም እግዚአብሔር እውን እንዲያደርግላቸውና ተአምሩን እንዲገልጽላቸው ከልብ እየተማጸኑት የነበረበት ወቅት ስለሆነ ነው::

ለዚህ አንድ መጽሀፍ ቅዱሳዊ ማስረጃ የሚሆነን "ለጸሎት ትተጉ ዘንድ ተስማምታችሁ ለጊዜው ካልሆነ በቀር እርስ በርሳችሁ አትከላከሉ: ራሳችሁን ስለአለማግዛት ሰይጣን እንዳይፈትናችሁ ደግሞ አብራችሁ ሁኑ" የሚለው የቅዱስ ጳውሎስ ቃል ነው:: 1ኛ ቆሮ 7:5 ይህ ቃል ልክ እንደሀናና ኢያቄም በጾም/በሱባኤ ያለንበት ጊዜ ላይ ከሩካቤ መከልከል እንዳለብን ይነግረናል:: እዚህ ላይ ሐዋርያው "ጸሎት" ያለው ከጾም ጋር ያለውን ሱባኤ ማለቱ ነው:: ምክንያቱም ጸሎት የሁል ጊዜም ተግባር ሲሆን "ለጊዜው" ማለቱ በተለየ የጾም ወቅት የምናደርገውን ሱባኤ ለማመልከት እንደሆነ መረዳት ይቻላል:: መጽሀፍ ቅዱስ በዚህ አይነት ወቅት "በጽዮን መለከትን ንፉ: ጾምንም ቀድሱ: ጉባኤውንም አውጁ" ካለ በኍላ ጨመር አድርጎ "ሙሽራው ከእልፍኙ ይውጣ: ሙሽሪትም ከጫጉላዋ ይውጡ" በማለት ከሩካቤ መታቀብ እንደሚገባ ይገልጻል:: ኢዩ 2: 15-16

ቅዱስ ዳዊትም ለእግዚአብሔር ማደርያ የሚሆን መቅደስ ለመስራት ባሰበ ጊዜ ሱባኤ እንደገባ መጽሀፍ ቅዱስ ይነግረናል:: በዚህ ወቅት ከሩካቤ ቀርቶ ምቹ አልጋ ላይ እንኳ ከመተኛት ራሱን እንዳገለለ ቅዱስ ዳዊት በመዝሙሩ ነግሮናል: "ወደ ምንጣፌም አልጋ አልወጣም" በማለት: መዝ 231:3

በጥቅሉ በጾም ህዋሶቻችን ሁሉ መጾም አለባቸው:: ስጋዊ ነገር ከማየት: ከመስማት: ከማድረግና ከማሰብ መቆጠብ አለብን::

ይቀጥላል!
ብርኃናዊት
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 3302
Joined: Sat Oct 27, 2007 3:57 am

Postby ብርኃናዊት » Wed Dec 05, 2007 10:24 pm

ውድ ሀሁሁሁ

እንደምን አለህ? ለተሳትፎህ በጣም እግዚአብሔር ይስጥልኝ::

መጽሀፍቅዱስ በቅድስና በትዳር ውስጥ የተፈቀደ መሆኑን ይናገራል እንጂ ስለ ቀን ለሊት የሚባል FORMULA አላወጣልንም ..በዘፍ 26 :8 ላይ አቤሜሌክ ይስሐቅ ሚስቱን ርብቃን ሲዳራ በመስኮት አየው ይላል ..አልመሸም ነበር ማለት ነው


ያው በማብራሪያው ላይ እንዳየኸው ቀንና ለሊት የሚለውን ፎርሙላ ያወጣልን ራሱ እግዚአብሔር ነው:: የአዳም እንቅልፍ ስለሌሊት የሚነግረን ነገር አለው:: አዳም በቀን በየሰአቱ ለእግዚአብሔር መባን ያቀርብ እንደነበር የስነ-ፍጥረት መጻህፍት ያስረዳሉ:: ከዚያም በተጨማሪ አዳምን "ገዢያችን ነህ" "አስተዳዳሪያችን ነህ" እያሉ እንሰሳት በሙሉ እጅ ይነሱት እንደነበረ እነመጽሀፈ አክሲማሮስን የመሳሰሉ የስነ-ፍጥረት መጻህፍት ይነግሩናል:: እግዚአብሄር በመሀል "አንድ ጊዜ" ብሎ መጥቶ አይደለም እለታዊ ምግባሩን አስትቶና የምስጋና መስዋእቱን አስጥሎ እንቅልፍ የለቀቀበት:: ምክንያቱም አዳም የተፈጠረው ለማመስገን ነውና:: እንቅልፍ የተለቀቀበት በእንቅልፍ ሰአቱ ነው:: በዚያ ሰአት ሄዋን ከጎኑ መፈጠሯ ሩካቤን የሚያመለክት ምስጢር አለው:: ሄዋን ከአዳም አጥንት እንደተገኘች ሁሉ ልጆችም ከወላጆቻቸው አብራክ የእንዲወጡ ምክንያት የሚሆነውን ሩካቤ የተባለውን ተፈጥሯዊ ጸጋ ተፈጥሯዊ ጸጋ በእንቅልፍ ሰአት የሚደረግ ምግባር እንደሆነ ሲነግረን ነው::

ብርኃናዊት
ብርኃናዊት
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 3302
Joined: Sat Oct 27, 2007 3:57 am

Postby ብርኃናዊት » Wed Dec 05, 2007 10:52 pm

ይቅርታ ሀሁሁሁ

ጥያቄውን ሙሉ ለሙሉ ሳልነካው ስላቆምኩ ተመልሼ ገባሁ::

ይስሀቅና ርብቃ ሲዳሩ አቤሜሌክ አያቸው ማለት ሩካቤ ሲፈጽሙ አያቸው ማለት አይደለም:: መዳራት ሩካቤ መፈጸምን አያመለክትም:: መዳራት - አብዛኛው ጊዜ መተቃቀፍ: መሳሳምና መደባበስን ነው የሚያመለክተው:: ለዚህ ደግሞ ልክ ነህ የሰአት ገደብ አልተበጀለትም:: ባልና ሚስት ዘና ባሉ ሰአት ሊያደርጉት ይችላሉ:: ሰው ፊት ግን ማድረግ ብዙም የሚመከር አይደለም::

ብርኃናዊት
ብርኃናዊት
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 3302
Joined: Sat Oct 27, 2007 3:57 am

Postby ሀሁሁሁ » Thu Dec 06, 2007 10:57 pm

እና አንድ በእለተ ቀዳሚት (ሰንበት ) የተጸነሰ ሁላችንም የምናውቀው ሰው አለ - ያም ሰው ይሁዳ ይባላል :: ይሁዳ በመጽሀፍ ቅዱስ "የጥፋት ልጅ " ተብሏል :: የጥፋት ልጅ የተባለው አንዱ ምክንያት ልጅነቱን /ውልደቱን ያስገኘችው ሩካቤ የተፈጸመችበት ሁኔታ ጥፋት በመሆኑ ነው :: ያም ማለት የተወለደው ከናት ካባቱ ከህግ ጋብቻ ነው :: ነገር ግን ሩካቤው የተፈጸመው በሰንበት እለት ነበር


ብርኃናዊት
በመፅሀፍ ቅዱስ ውስጥ ይሁዳ ቅዳሜ ነው የተፀነሰው ተብሎ ተጽፍዋል ወይ ?

ቅዳሜ የተጸነስ የጥፋት ልጅ ነው የሚለውስ ከወዴት መጣ ?


የመጸነስ ቀንና የሰውን ባህርይ ማገናኘት የኮከብ ቆጣሪ/የጠንቁዋይ / ወዘተ..ስራ ነው ..ከአጋንንት ነው.. የእግዚያብሔር ቃል አይደግፈውም !!!!!!!!!!!!!!
ሀሁሁሁ
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 308
Joined: Fri Jan 20, 2006 11:44 pm

Postby ብርኃናዊት » Fri Dec 07, 2007 1:42 am

ሰላም ሀሁሁሁ

ብርኃናዊት
በመፅሀፍ ቅዱስ ውስጥ ይሁዳ ቅዳሜ ነው የተፀነሰው ተብሎ ተጽፍዋል ወይ ?

ቅዳሜ የተጸነስ የጥፋት ልጅ ነው የሚለውስ ከወዴት መጣ ?


የመጸነስ ቀንና የሰውን ባህርይ ማገናኘት የኮከብ ቆጣሪ /የጠንቁዋይ / ወዘተ ..ስራ ነው ..ከአጋንንት ነው .. የእግዚያብሔር ቃል አይደግፈውም !!!!!!!!!!!!!!


አሁንም ተሳትፎህ አይለየን እያልኩ:

1. የይሁዳ ታሪክ ሙሉው መጽሀፍ ቅዱስ ላይ አልተጻፈም:: ሆኖም ከጽንሰቱ ጀምሮ እስከህልፈቱ ድረስ ያለው ታሪኩ በሌሎች የታሪክ መዛግብት ላይ ተጽፏል- ለሌሎች መማሪያ እንዲሆን በሚል::

2. ቅዳሜ የተጸነሰ የጥፋት ልጅ ነው የሚለው ከየት መጣ ላልከው መልሱ ከመጽሀፍ ቅዱስ የሚል ይሆናል:: ቅዳሜ ሰንበት ነች:: እሁድ ደግሞ አዲሷ የክርስቲያን ሰንበት ነች:: እግዚአብሔር "የሰንበትን ቀን ትጠብቀው ዘንድ አስብ" ብሎ ከአስርቱ ትዕዛዛት ሶስተኛውን የሰጠን ሰንበትን አለመጠበቅ ጥፋት ስለሆነ ነው:: ሰንበትን ብቻ ሳይሆን በአላትንና አጽዋማትን ከስጋ ስራ ተቆጥበን ማሳለፍ እንደሚገባን እግዚአብሔር ምንም በማያሻማ መልኩ በመጽሀፍ ቅዱስ ላይ ገልጾልናል::

"ፈቃድህን በተቀደሰው ቀኔ ከማድረግ እግርህን ከሰንበት ብትመልስ : ሰንበትንም ደስታ : እግዚአብሔር የቀደሰውንም "ክቡር " ብትለው : የገዛ ፈቃድህንም ከማግኘት ከንቱ ነገርም ከመናገር ተከልክለህ ብታከብረው : በዚያን ቀኔ በእግዚአብሔር ደስ ይልሀል : በምድር ከፍታዎች ላይ አወጣሀለሁ : የአባትህንም የያዕቆብ ርስት አበላሀለሁ : የእግዚአብሄር አፍ ተናግሯልና ::" ኢሳ 58: 13-14

"በጽዮን መለከትን ንፉ : ጾምንም ቀድሱ : ጉባኤውንም አውጁ " ካለ በኍላ ጨመር አድርጎ "ሙሽራው ከእልፍኙ ይውጣ : ሙሽሪትም ከጫጉላዋ ይውጡ " በማለት ከሩካቤ መታቀብ እንደሚገባ ይገልጻል :: ኢዩ 2: 15-16

ታድያ እንደዚህ አድርጎ ስለሰንበትና ስለጾም ጊዜያት ግልጽ የሆነ ትዕዛዝ የሰጠንን እግዚአብሔር በሰንበት ሩካቤ ብንፈጽም ጥፋት እንጂ ጽድቅ ይሆንልናል? የይሁዳ ቅዳሜ መጸነስ ብቻ ሳይሆን በጾምና በበአል ቀን ቢጸነስም እንኳ ያው የጥፋት ልጅ ከመሆን አይተርፍም:: በሰንበት በመጸነሱ የጥፋት ልጅ ቢሆንም ቤተሰቦቹም ሆኑ እሱ ግን በንስሀ ለመመለስ እድሉ ነበራቸው:: ያንን አለመጠቀማቸው ሌላው ጥፋት ነው:: ይሁዳን የጥፋት ልጅ ያሰኘውና ባህሪውም ሰይጣናዊ እንዲሆን ያደረገው ብዙ ነገሮች ተደራርበውና ነው እንጂ በሰንበት በመጸነሱ ብቻ አይደለም:: ያ እንዲያም በይበልጥ ጥፋቱ የሚሆነው የቤተ-ሰቦቹ ነው:: ነገር ግን ሰንበትን በሩካቤ መሻር ለሚወለደው ልጅ ትልቅ በረከት የሚያሳጣ ጥፋት ነው::

እናም ሰንበትን አትሻሩ ብሎ ትዕዛዝ የሰጠን ጌታ ሆኖ ሳለ በሰንበት የሚደረግ ሩካቤ የጥፋት ልጅነትን ሊያስከትል ይችላል ብሎ መናገር በምንም ተአምር ኮከብ ቆጣሪነት አይደለም:: እግዚአብሔር ህጉን የተላለፉትን ይረግማል:: ቢችሉ በንስሀ መመለስ አለባቸው: ካልሆነ ግን ዛሬም ነገም የጥፋት ልጆች ናቸው:: ይህ ኮከብ ቆጣሪነት ከሆነ እግዚአብሔርን ራሱ ነው ኮከብ ቆጣሪ እያልነው ያለነውና ድፍረት ይሆንብናል::
ብርኃናዊት
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 3302
Joined: Sat Oct 27, 2007 3:57 am

Postby ሀሁሁሁ » Fri Dec 07, 2007 5:39 pm

Sex between a husband and wife is a very holy. It is not a sin or a dirty work . It is not work either.

ፈቃድህን በተቀደሰው ቀኔ ከማድረግ እግርህን ከሰንበት ብትመልስ : ሰንበትንም ደስታ : እግዚአብሔር የቀደሰውንም "ክቡር " ብትለው : የገዛ ፈቃድህንም ከማግኘት ከንቱ ነገርም ከመናገር ተከልክለህ ብታከብረው : በዚያን ቀኔ በእግዚአብሔር ደስ ይልሀል : በምድር ከፍታዎች ላይ አወጣሀለሁ : የአባትህንም የያዕቆብ ርስት አበላሀለሁ : የእግዚአብሄር አፍ ተናግሯልና ::" ኢሳ 58: 13-14
ሀሁሁሁ
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 308
Joined: Fri Jan 20, 2006 11:44 pm

Postby ብርኃናዊት » Fri Dec 07, 2007 7:36 pm

ሰላም ሀሁሁሁ

Sex between a husband and wife is a very holy. It is not a sin or a dirty work . It is not work either.


ትክክል ብለሀል:: ህጋዊ ሩካቤ ኃጥያት አይደለም:: ቁሻሻ ነገርም አይደለም:: የተቀደሰ ነገር ነው:: ቅድስት ድንግል ማርያምን: ጻድቃንን: ቅዱሳንን: ሁሉ ያስገኘ ሩካቤ እንዴት ቁሻሻ ይሆናል? አይሆንም!!

ነገር ግን በጾም ወቅት ስጋ አንበላም ስንል ስጋ ርካሽ ስለሆነ አይደለም:: ወዪም ምግብ መብላት ኃጥያት ስለሆነ አይደለም:: እንዲያማ ቢሆን ኖሮ በፍስክ ጊዜም ቢሆን መብላት አይገባንም ነበር:: ነገር ግን ለሁሉ ጊዜ ስላለውና የሰው ልጅ በስርአት ስለተፈጠረ በህጉ መሄድ ስላለበት ነው እንጂ:: ህጉን ያወጣው እግዚአብሄር ነው:: እኛ እሱን "ስለምን እንዲህ አድረግህ?" ብለን የመክሰስ መብት የለንም:: በሰንበት ቀን ፈቃድህን አትፈጽም ማለት አትፈጽም ነው:: ሌላ ትርጉም የለውም::

ብርኃናዊት
ብርኃናዊት
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 3302
Joined: Sat Oct 27, 2007 3:57 am

Postby ሀሁሁሁ » Fri Dec 07, 2007 9:18 pm

እኔም እሱን "ስለምን እንዲህ አድረግህ ?" ለማለት ሀሳቡም ፈቃዱም መብቱም እንደሌለኝ አጥብቄ አውቃለሁ ..እግዚያብሔር ያላሸከመንን ሸክም እንዳንሸከም ብዬ ነው እንጂ ቃሉን ለመጣስ አይደለም ..1ኛ ቆሮ 1-5 ላይ
" ለጸሎት ትተጉ ዘንድ ተስማምታችው ለጊዜው ካልሆነ በስተቀር እርስ በርሳችው አትከላከሉ "

ሲል ባልና ሚስት ተነጋግረው ተማምነው ተስማምተው ማድረግም አለማድረግም እንደሚችሉ ነው የሚናገረው ..ጉዳዪ ከቀንና ከሰአት ጋር የሚገናኝ ቢሆን ኖሮ " የጾም ቀን ካልሆነ በስተቀር የስንበት ቀን ካልሆነ በስተቀር " ብሎ በመለሰላቸው ነበር . በምእራፉ መጀመሪያ ላይ " ስለ ሴት ጋር ስላለ ግኑኝነት ለጠየቁት መልስ እየሰጠ እንደሆነ ይናገራልና

ለሊት ብቻ በፍስክ ቀን ብቻ ...ወዘት ይደረግ የሚለው ትምህርት ትንሽ ከመፅሀፉ ዞር ያለ , የሩካቤ ግኑኝነትን ተፍጥሮዋዊ ሳይሆን mechanical የሚያደርግ ትምህርት ነው ብዬ ነው...
አክባሪሽ

ሀሁሁሁ.
ሀሁሁሁ
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 308
Joined: Fri Jan 20, 2006 11:44 pm

Postby ብርኃናዊት » Fri Dec 07, 2007 11:27 pm

ውድ ሀሁሁሁ :

አባባልህ በደንብ ገብቶኛል :: ሳልረዳው የቀረሁ እንዳይመስልህ:: እንዲህ አይነት ነገሮችን እናነብ የሁላችንም ጥያቄ እንደሚሆን እገምታለሁ:: ሆኖም እንዲህ ያሉ ስራቶች ሰው የሚያደርጋቸውን ነገሮች ሜካኒካል ለማድረግ የተሰሩ ሳይሆኑ ራሱን መግዛት እንዲችል ለማብቃት የተሰሩ ናቸው :: ለነገሩ ካሰብከው እኮ ማታ ከመተኛትና ጠዋት ከመነሳት የባሰ ሜካኒካል ነገር የለም :: እንዳንተ አባባል ከወሰድነው የተወሰነ የጊዜ ኡደትን ጠብቆ የሚደረግ ነገር በሙሉ ሜካኒካል ከሆነ ብዙው የስነ -ፍጥረት ህግ ሜካኒካል ነው የሚሆነው :: ለምሳሌ ጸሀይ በምስራቅ ወጥታ በምእራብ ትገባለች :: በሌላ ቀን በደቡብ አትወጣም :: ሰው ከናቱና ካባቱ ይወለዳል : ያድጋል : ያረጃል : ይሞታል :: ኡደቱ አይገለበጥም : ወይም አይለወጥም :: ሰው የህይወት ryhthm ሙን ጠብቆ እንዲኖር የእግዚአብሔር ፈቃዱ ነው :: "በዚህ ወቅት በብላት እችላለሁ :በዚህ ወቅት ግን አልበላም : በዚህ ወቅት ሩካቤ መፈጸም እችላለሁ : በዚህ ወቅት ግን አልፈጽምም " ብሎ ራሱ ላይ በስራቱ መሰረት ማዕቀብ መጣልና ማንሳት ከቻለ ራሱ የራሱ ጌታ ሆነ ማለት ነው :: ይህ የማንችለውን ሸክም መሸከም አይደለም :: ይህ ስጋን ለነፍስ ማስገዛት ነው :: ይህ የክርስትና አላማ ነው :: ለእግዚአብሄር ሲሉ የሳሱለትን ነገር መተው ከዚህ ይጀምራል :: ይልቅ የማንችለው ሸክም የሚባለውስ እንደይሁዳ አይነት ልጅ ወልደን በስጋም በነፍስም ሳንባረክ መኖር ነው :: ያንን አንችለውም :: ነገር ግን ሰንበትን በነፍስ ስራ ለማሳለፍ በመወሰን ከሩካቤ መከልከል ለእግዚአብሔር ስንል ልናደርጋቸው ከምንችላቸው ቀላል ነገሮች መሀል አንዱ ነው ::

ሰፋ አድርገን ካሰብነውም እኮ ለነገሩ በሰንበት ቀን አንድ ሰው ቤተክርስቲያን መሄድ አለበት :: ቤተ -ክርስቲያን ለመግባት የፈለገ ሰው ደግሞ ሰንበት ስለሆነ ብቻ ሳይሆን ቤተ -ክርስቲያን ስለሚገባ ብቻ ራሱ ከሩካቤ መቆጠብ አለበት :: ይህንን እስራኤላውያን ወደመገናኛው ድንኳን ለመጠጋት ሲያስቡ እንኳ ይጠብቁት ነበር :: ያኔ በድንኳኑ ታቦት ብቻ ነው ያለው :: በኛ ዘመን ግን ክቡር የሆነው የክርስቶስ ስጋና ደም ሳይቀር በቤተክርስቲያን አለ :: ታድያ ጥንቃቄያችን ከነሱ ሊበልጥ እንጂ ሊያንስ ይገባልን ? ደግሞም እኛ ራሳችንን ለመግዛት ጥረት ባደረግን መጠን እግዚአብሄር እጅግ ከፍ ያለ የነፍስ ጸጋ ሊሰጠን የታመነ ነው :: እኛ የምንችላትን ያህል መሞከር ይገባናል እንጂ "የማንችለው ሸክም ነው " ብለን መፍራትና ወደ ኍላ መመለስ አይገባንም :: እግዚአብሄር ለኛ ያዘጋጀውን የነፍስ ጸጋ ምን እናውቃለን ? አንተ ያነሳኸው የሀዋርያው ጥቅስም ቢሆን እኮ የሚለው "ለጸሎት ትተጉ ዘንድ እርስ በርሳችሁ ተስማምታችሁ ካልሆነ በቀር እርስ በርሳችሁ አትከላከሉ" ነው የሚለው:: ከበአላት: ከሰንበት እና ከአጽዋማት ጊዜ በላይ ለጸሎት የምንተጋበት ጊዜ የት አለ? የለም! እነዚህ ናቸው ለጸሎት የምንተጋባቸው ጊዜያት ማለት::

ቸር ይግጠመን !
ብርኃናዊት
ብርኃናዊት
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 3302
Joined: Sat Oct 27, 2007 3:57 am

Postby ብርኃናዊት » Sat Dec 08, 2007 3:40 am

የቀጠለ..

9. በወር አበባ ጊዜ የሚፈጸም ሩካቤ

ክርስቲያኖች ሴቷ በወር አበባ ላይ እያለች ሩካቤ ሊፈጽሙ አይገባም:: ምክንያቱ ምንድነው?

የሰው ልጅ ክቡር ነው:: ሴት ልጅ በወር አበባ ላይ ሳለች ሩካቤን መፈጸም ክቡር ዘርን (የወንድን ዘር) እዳሪ ከሆነ ደም ጋር መቀላቀል ነውና ትልቅ ኃጥያት ነው::

ንጉስ ዳዊት ከሰው ሚስት ጋር ድርጊቱን በመፈጸሙ ቢነቀፍም ከኦርዮ ሚስት ከቤርሳቤህ ጋር በተገናኘ ጊዜ ከወር አበባዋ ነጽታ እንደነበር መጽሀፍ ቅዱስ እንዲህ በማለት ይገልጻል:-

ዳዊትም መልክተኞችን ልኮ አስመጣት: ወደርሱም ገባች: ከርኩሰትዋም ነጽታ ነበርና ከርሷ ጋር ተኛ: ወደበትም ተመለሰች: ሴቲቱም አረገዘች

(** በኦሪት ጊዜ የወር አበባ እንደርኩሰት ይቆጠር ነበር:: ነገር ግን በሀዲስ ኪዳን የወር አበባ ይባላል እንጂ ርኩሰት አይደለም)

መጻፍ ቅዱስ ሴት ልጅ በወር አበባ ላይ እያለች የሚፈጸም ሩካቤን ሲከለክል እንዲህ ይላል:

እርሷም በመርገምም በርኩሰት ሳለች ኃፍረተ-ስጋዋን ትገልጽ ዘንድ ወደ ሴት አትቅረብ::" ዘሌ 18: 19 የወር አበባ ግዜ የሚፈጸም ሩካቤ በሀዲስ ኪዳንም ጊዜ ቢሆን ክልክል ነው::ክርስቶስ እንዳዲስ አልፈቀደውም::

በተጨማሪም እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ከዮሀንስ ጋር 15 አመት በኖረችበት ጊዜ ለሌሎች እንዲያስተምርና እንዲያስጠነቅቅ አበክራ ከነገረችው ነገሮች መሀል አንዱ በወር አበባ ጊዜ ሩካቤ መፈጸም እንደማይገባ ነው:: ይህም ማስጠንቀቂያዋ "ራእየ-ማርያም" በተባለው መጽሀፍ ላይ ተጽፏል::

10. በርግዝና ጊዜ የሚፈጸም ሩካቤ

ሴት ልጅ ርጉዝ ሆና ሳለ ሩካቤ መፈጸም በጣም አደገኛ ነው:: ምክንያቱም በጽንስ ወቅት የሚደረግ ሩካቤ የጽንሱን አቀማመጥ እንዲዛባ በማድረግ በጽንሱና በናቲቱ ላይ ከፍተኛ የሆነ የጠና መታወክ ሊያስከትል ስለሚችል ነው:: ከዚህም ሌላ በመንፈሳዊ አይን ለተመለከተው ሴቲቱ ጸንሳ እንደሆነ እናትና ልጅን በአንድ ጊዜ እንደመገናኘት ሲሆን ጽንሱ ወንድ ከሆነ ደግሞ ግብረ-ሰዶም እንደመፈጸም ነውና በጽንስ ጊዜ የሚፈጸም ሩካቤ በሀይማኖት ፈጸሞ የተወገዘ ነው:: (ለነገሩ ሳይንስም ቢሆን እምብዛም አይደግፈውም)

በመጽሀፍ ቅዱስ ላይ አንድም ቦታ ሚስቱ ርጉዝ ሆና ሩካቤን የፈጸመ ሰዉ አናገኝም:: እንዲያውም የኦርዮና የቤርሳቤህ ታሪክ እንደሚያሳየን እግዚአብሔር በረቂቅ መንገድ የዋሆችን ሚስታቸው ርጉዝ ሆና እንዳይተኙ እንደሚጠብቅ ማየት እንችላለን:: በርሳቤህ መጸነሷን እንዳወቀች ለንጉስ ዳዊት ብትልክበት ንጉስ ዳዊት "ጽንሱ ያንተ ነው" ለማለት እንዲመቸው ባሏን ኦርዮን ከጦር ሜዳ አስመጥቶ አብሯት እንዲሆን ቢያደርግም ኦርዮ ግን በልቡ ባለው መንፈሳዊነት ምክንያት (ርጉዝ መሆኗን ባያውቅም) "ሌሎች በጦር ሜዳ እየተዋደቁ እኔ በምቾት ከባለቤቴ ጋር አልተኛም" በማለት ከሚስቱ ጋር ሳይገኛኝ አድሯል::እግዚአብሔር በረቂቅ ጥበብ ብዙም ያልገፋ ጽንስ ከያዘችው ሚስቱ ጋር እንዳይተኛ እንዲህ ጠብቆታል:: እኛ ደግሞ እያወቅን ከማድረግ በይበልጥ መጠንቀቅ አለብን::

ከዚህም ሌላ ሴት ልጅ ከወለደች በህዋላ በአራስነት እያለች ሩካቤ መፈጸምም በሀይማኖት ክልክል ነው:: (አሁንም ሳይንሱ ሳይቀር በአራስነት ጊዜ የሚፈጸምን ሩካቤ አይደግፈውም):: በዚህ ጊዜ ሴት ለሩካቤ እምብዛም ስሜቱ አይኖራትም:: ሰውነቷም ወደ ቀድሞ ይዘቱ ገና አይመለስም:: ከላይ በጠቀስነው የራእየ-ማርያም መጽሀፍ ላይ በአራስነት ሩካቤ መፈጸም እንደማይገባ በሚገባ ተጠቅሷል::

ይቀጥላል
ብርኃናዊት
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 3302
Joined: Sat Oct 27, 2007 3:57 am

Postby ግርማዊነታቸው » Wed Dec 19, 2007 3:46 pm

የከበረ ሰላምታ: ውድ ብርሃናዊት:

ይህን ድንቅ ቤት እንዳልረሳሽው ተስፋ እያደረግኩ የሚቀጥሉትን ጥያቄዎች እንዳቀርብ ፍቀጅልኝ:

1. 'ማየት/መተያየት' ሲባል ሁለቱ ዓይኖቻችንን በመጠቀም ብቻ ነውን?

2. በሩካቤ ወቅት ከዓይኖቻችን ሌላ በይበልጥ እንድናይ የሚረዱን ሌሎች ነገሮች የሉምን?

3. እውሮች ወይም ዓይናቸው የደከመ ሰዎችሽ በምን መልክ ሩካቤን ማካሄድ ይችላሉ/ይኖርባቸዋል?

ከምስጋና ጋር


ብርኃናዊት wrote: የሩካቤና የአምስቱ ህዋሳቶች ትይዩነት

[color=darkblue]እንሰሳት ሩካቤ ሲያደርጉ ፊትና ኍላ በመሆን ነው:: የሰው ልጅ ግን ከእንሰሳት ይለያልና ፊት ለፊት ሆኖ ሩካቤን ይፈጽማል:: ብዙ እንሰሳት እንደተወለዱ አይናቸውን አይገልጡም/አያዩም:: ይህም ለጽንሰታቸው ምክንያት የሆነው ሩካቤ ባለመተያየት (ፊትና ኍላ በመሆን) መፈጸሙን ሲያመለክት የሰው ልጅ ደግሞ እንደተወለደ ወዲያውኑ አይኑን መግለጡና ለማየት መቻሉ ምንም እንኳ የተፈጥሮ ነገር ሆኖ [በስሜት] አይንን መጨፈን ባይቀርም ሴትና ወንድ ትይዩ ሆነው ተራክቦ እንደሚያደርጉ ያመለክታል::
ለነገሩ ነገር በዐይን ይገባል አይደለም የሚባለው ? ፊት ለፊት ላለመተያየት መፈለግ በስነ ልቦናም ቢተነተን ንቀትን ወይም እውነተኛ ፍቅር ሳይኖር ሩካቤውን ብቻ መፈለግን ያሳያል :: (ልክ አንዳንድ ዋርካውያን cover the face, attack the base እንዳሉት ማለት ነው - ማንነቷን ወይም መልኳን ላለማየት : ይህ ደግሞ እንሰሳነት ነው ::
The OriGinal is UnfaiThful To The TranSlation.
ግርማዊነታቸው
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 301
Joined: Fri Oct 27, 2006 2:01 pm
Location: Universe

Postby ቀልደኛ » Fri Dec 21, 2007 8:48 pm

9. በወር አበባ ጊዜ የሚፈጸም ሩካቤ

ክርስቲያኖች ሴቷ በወር አበባ ላይ እያለች ሩካቤ ሊፈጽሙ አይገባም :: ምክንያቱ ምንድነው ?

የሰው ልጅ ክቡር ነው :: ሴት ልጅ በወር አበባ ላይ ሳለች ሩካቤን መፈጸም ክቡር ዘርን (የወንድን ዘር ) እዳሪ ከሆነ ደም ጋር መቀላቀል ነውና ትልቅ ኃጥያት ነው ::

ንጉስ ዳዊት ከሰው ሚስት ጋር ድርጊቱን በመፈጸሙ ቢነቀፍም ከኦርዮ ሚስት ከቤርሳቤህ ጋር በተገናኘ ጊዜ ከወር አበባዋ ነጽታ እንደነበር መጽሀፍ ቅዱስ እንዲህ በማለት ይገልጻል :-

ዳዊትም መልክተኞችን ልኮ አስመጣት : ወደርሱም ገባች : ከርኩሰትዋም ነጽታ ነበርና ከርሷ ጋር ተኛ : ወደበትም ተመለሰች : ሴቲቱም አረገዘች

(** በኦሪት ጊዜ የወር አበባ እንደርኩሰት ይቆጠር ነበር :: ነገር ግን በሀዲስ ኪዳን የወር አበባ ይባላል እንጂ ርኩሰት አይደለም )

መጻፍ ቅዱስ ሴት ልጅ በወር አበባ ላይ እያለች የሚፈጸም ሩካቤን ሲከለክል እንዲህ ይላል :

እርሷም በመርገምም በርኩሰት ሳለች ኃፍረተ -ስጋዋን ትገልጽ ዘንድ ወደ ሴት አትቅረብ ::" ዘሌ 18: 19 የወር አበባ ግዜ የሚፈጸም ሩካቤ በሀዲስ ኪዳንም ጊዜ ቢሆን ክልክል ነው ::ክርስቶስ እንዳዲስ አልፈቀደውም ::

በተጨማሪም እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ከዮሀንስ ጋር 15 አመት በኖረችበት ጊዜ ለሌሎች እንዲያስተምርና እንዲያስጠነቅቅ አበክራ ከነገረችው ነገሮች መሀል አንዱ በወር አበባ ጊዜ ሩካቤ መፈጸም እንደማይገባ ነው :: ይህም ማስጠንቀቂያዋ "ራእየ -ማርያም " በተባለው መጽሀፍ ላይ ተጽፏል ::

10. በርግዝና ጊዜ የሚፈጸም ሩካቤ

ሴት ልጅ ርጉዝ ሆና ሳለ ሩካቤ መፈጸም በጣም አደገኛ ነው :: ምክንያቱም በጽንስ ወቅት የሚደረግ ሩካቤ የጽንሱን አቀማመጥ እንዲዛባ በማድረግ በጽንሱና በናቲቱ ላይ ከፍተኛ የሆነ የጠና መታወክ ሊያስከትል ስለሚችል ነው :: ከዚህም ሌላ በመንፈሳዊ አይን ለተመለከተው ሴቲቱ ጸንሳ እንደሆነ እናትና ልጅን በአንድ ጊዜ እንደመገናኘት ሲሆን ጽንሱ ወንድ ከሆነ ደግሞ ግብረ -ሰዶም እንደመፈጸም ነውና በጽንስ ጊዜ የሚፈጸም ሩካቤ በሀይማኖት ፈጸሞ የተወገዘ ነው :: (ለነገሩ ሳይንስም ቢሆን እምብዛም አይደግፈውም )

በመጽሀፍ ቅዱስ ላይ አንድም ቦታ ሚስቱ ርጉዝ ሆና ሩካቤን የፈጸመ ሰዉ አናገኝም :: እንዲያውም የኦርዮና የቤርሳቤህ ታሪክ እንደሚያሳየን እግዚአብሔር በረቂቅ መንገድ የዋሆችን ሚስታቸው ርጉዝ ሆና እንዳይተኙ እንደሚጠብቅ ማየት እንችላለን :: በርሳቤህ መጸነሷን እንዳወቀች ለንጉስ ዳዊት ብትልክበት ንጉስ ዳዊት "ጽንሱ ያንተ ነው " ለማለት እንዲመቸው ባሏን ኦርዮን ከጦር ሜዳ አስመጥቶ አብሯት እንዲሆን ቢያደርግም ኦርዮ ግን በልቡ ባለው መንፈሳዊነት ምክንያት (ርጉዝ መሆኗን ባያውቅም ) "ሌሎች በጦር ሜዳ እየተዋደቁ እኔ በምቾት ከባለቤቴ ጋር አልተኛም " በማለት ከሚስቱ ጋር ሳይገኛኝ አድሯል ::እግዚአብሔር በረቂቅ ጥበብ ብዙም ያልገፋ ጽንስ ከያዘችው ሚስቱ ጋር እንዳይተኛ እንዲህ ጠብቆታል :: እኛ ደግሞ እያወቅን ከማድረግ በይበልጥ መጠንቀቅ አለብን ::

ከዚህም ሌላ ሴት ልጅ ከወለደች በህዋላ በአራስነት እያለች ሩካቤ መፈጸምም በሀይማኖት ክልክል ነው :: (አሁንም ሳይንሱ ሳይቀር በአራስነት ጊዜ የሚፈጸምን ሩካቤ አይደግፈውም ):: በዚህ ጊዜ ሴት ለሩካቤ እምብዛም ስሜቱ አይኖራትም :: ሰውነቷም ወደ ቀድሞ ይዘቱ ገና አይመለስም :: ከላይ በጠቀስነው የራእየ -ማርያም መጽሀፍ ላይ በአራስነት ሩካቤ መፈጸም እንደማይገባ በሚገባ ተጠቅሷል ::

ይቀጥላል


ወይ ወ/ሮ ብርሃን!

በወር አበባ ጊዜ
በእርግዝና ጊዜ
በአራስነት ጊዜ
በጦም ጊዜ
በበአላት ጊዜ (ከግማሽ አመት በላይ የሚሆኑ ቀናት)
ወዘተ
ታዲያ ምኑን ተጋቡት

እኔ እምለው አንቺ አግብተሻል ? ወይስ ገናነሽ ?
መቸም ይህን ሁሉ የሚጠነቅቅ ጅል ወንድ አታገኝም
ሲያምረው እየሸወደሽ ካልሆነ በቀር ::

የኔ እህት : ሃይማኖት እንዲህ ከሆነስ በአፍንጫዬ ይውጣ

ምኑን ትዳር ሆነ እያዩ ምራቅን መዋጥ በይው እንጅ

አንቺ የኢትዮጳ መሪ ብትሆኚ : መንቀሳቀስ የምንችል አይመስለኝም ::

በይ ቻው

መጥኜውን ይስጥሽ

በቁም ነገር የማይቀልደው
ቀልደኛ ነኝ
ቀልደኛ
መንገደኛ
መንገደኛ
 
Posts: 9
Joined: Sun Nov 18, 2007 11:58 pm

Postby ብርኃናዊት » Sat Dec 22, 2007 12:19 am

ቀልደኛው እንደምነህ?

እውነትም ቀልደኛ! ከልቤ አስቀኸኛል!!

ግን ቀልድ አይደለም:: የተናገርከው እውነት ነው:: ለማናችንም ቢሆን ይሄ ከባድ እንደሚመስል በጣም ግልጽ ነው:: በተለይ ለመጀመሪያ ጊዜ ለሚያነበው ሰው "ታድያ እንዴት ነው ነገሩ? እንመንኩስ እንዴ?" እንደሚያስብል አልጠራጠርም:: ምክንያቱም እኔም እንደዚያ ብዬ ነበር::

ግን ልነግርህ የምፈልገው አንድ ትልቅ እውነታ አለ:: ያም በዚህ መመሪያ መሰረት ኑሮዋቸውን የሚመሩና በደስተኝነት: በጤንነት የሚኖሩ ብዙ ባለትዳሮች እንዳሉ ነው:: እኔ ይህን ስላነበብኩት ብቻ አይደለም ያመንኩበት:: በህይወት ኖረውበት በሚገርም ሁኔታ የተጠቀሙበት ሰዎች ስላሉ ነው እንጂ::

ሌላው ልነግርህ የምፈልገው እውነታ ደግሞ ሀይማኖት የሺዎች ዘመን ዕድሜ ያለው ክስተት ሲሆን ሩካቤ ደግሞ ሰው ከተፈጠረበት ጀምሮ የኖረ ቢሆንም በጣም ዝነኛ ከሆነና rising star መሆን ከጀመረ ግን 50 አመት እንኳ አይሞላውም:: በታሪክ ክስተት sexual revolution የሚባለው ክስተት ከተከሰተ 40 አመት አልሞላውም:: ነገር ግን ነገሮች በፍጥነት ተለዋውጠው አንድ ሀይማኖት ስለሩካቤ ያለውን አመለካከትና አቋም ከግምት ውስጥ አስገብቶና ገምግሞ ከተስማማን ብቻ የሀይማኖቱ ተከታይ እስከምንሆንበት ድረስ የደረሰ ለውጥ ተከስቷል:: ድሮ ድሮ "በዚህ ነገር የመጣብኝ ከሆነ ሁሉ ነገር ገደል ይግባ" ይሉ የነበሩት ዝሙት አዳሪዎች ብቻ ነበሩ:: እነሱም የኑሮ ነገር ይዞዋቸው ነው:: አሁን ግን የማንኛውም አማካይ ሰው አቋም ሆኗል:: ግብረ-ሥጋ ከግብረ-ሥጋ አልፋ ግብረ-ነፍስ: ግብረ-መንፈስ የሆነችበት ዘመን ላይ የደረስን ይመስላል:: እና ይሄ ጤነኛ ነው ወይ ብለን መጠየቅ አለብን::

በነገራችን ላይ እዚህ አምድ ስር የተጻፉትን ጽሁፎች በሀይማኖት ስም ስለተጻፉ ነው እንጂ የሳይንስ መጽሀፎችም ጭምር በጥናት ያረጋገጧቸው ናቸው:: ለምሳሌ ቀን ግንኙነት ፈጽሞ ወደ ሥራ መሰማራት: በአራስነት ጊዜ ሩካቤ: በርግዝና ጊዜ ሩካቤ... ለጤና ጠንቅ እንደሆኑ እየተናገሩ ነው:: ሳይንስስ ለጤና ጠንቅ ነው ሲለን የስጋ ጤንነታችንን ማለቱ ነው:: የነፍስን ጤንነት የሚያረጋግጥልን ዶክተር ደግሞ የለም:: እና ምናልባት ስጋችን እምብዛም ጤንነቱ ባይናጋ እንኳ ለነፍሳችን ጤንነት መጠንቀቅ የለብንም? መልሱን ላንተ!!

እና አይዞህ! እኔ የኢትዮጵያ መሪ ብሆን ጭራሽ ስለ ሩካቤ አዋጅ አላወጣም:: የማወጣው ህግ ሰው ሁሉ በታታሪነት ስራውን ቀን እንዲሰራና እሁድ እሁድ: የበአላት ቀንና የአጽዋማት ጊዜ ደግሞ ከቤተክርስቲያን እንዳይቀር ነው:: በተረፈ በሌሎቹ ቀናት ደግሞ ኬሚስቶቻችን ከጤናዳምና ከአሪቲ የተሰራ ሽቶ አምርተው በገፍ ለዜጎቼ እንዲሸጡ አድርግና ወላጆች ያን እያሸተቱ ምን የመሰሉ ሸጋ ልጆች በግዛቴ ይወልዱልኛል:: አይመስልህም???!!

አክባሪህ!
ብርኃናዊት
ብርኃናዊት
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 3302
Joined: Sat Oct 27, 2007 3:57 am

Postby ትትና » Mon Dec 24, 2007 11:13 am

ብርሀናዊት:- እንዴት ከርመሻል?

ትምህርትሽን እየተከታተልኩ ነው እስቲ ይቀጥል ለማለት ነው ብቅ ያልኩት::
ጥያቄ ጠያቂዎችም ጥሩ ውይይት እያደረጉ ነው::
ትትና
ውሃ አጠጪ
ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1253
Joined: Wed Feb 23, 2005 11:26 am
Location: united states

PreviousNext

Return to Warka Intimate - ዋርካ ፍቅር

Who is online

Users browsing this forum: No registered users and 6 guests