የኢትዮጵያ ቤ/ክ የጾታ ትምህርት- ማንበብ ለሚፈልግ

The Love Forum (love, relationship) (የኔ ቆንጆ እንተዋወቅ :-)

Postby ብርኃናዊት » Tue Dec 25, 2007 8:23 pm

ሰላም የዚህ ቤት ተሳታፊዎች:

ውድ ግርማዊ እንዴት እንደሆነ ባላውቅም ጥያቄህን አላየሁትም ነበር:: የቀልደኛን አስተያየት ብቻ ነበር ያየሁት:: የጻፍከውን ጥያቄ ገና ዛሬ ማየቴ ነው:: በጣም ይቅርታ ይደረግልኝ እያልኩ ይቅርታ እንደሚደረግልኝ በመተማመን ለጥያቄህ የሚመስለኝን አካፍላለሁ::

ትትና እንኳን ደህና ተመልስሽ ወደዚህ ቤት:: እኔማ ይሄ ጽሁፍ ሰዉን እያስደነበረው ይሆን እንዴ ብዬ ሁሉ ተጠራጥሬ ነበር:: እና መቼም ለማንበብ ፈቃደኛ የሆኑ እስካሉ ድረስ ማስነበቡ አይከፋምና እቀጥላለሁ:: ስለማነቃቂያውና ስለምክሮችሽ እግዚአብሔር ይስጥልኝ::

ወደግርማዊ ጥያቄዎች ስመጣ:

1. 'ማየት /መተያየት ' ሲባል ሁለቱ ዓይኖቻችንን በመጠቀም ብቻ ነውን ?


2. በሩካቤ ወቅት ከዓይኖቻችን ሌላ በይበልጥ እንድናይ የሚረዱን ሌሎች ነገሮች የሉምን ?


ሁለቱን ጥያቄዎች በትክክል ተረድቼህ እንደሆነ እርግጠኛ ባልሆንም አያይዤ ልሞክራቸው:: እዚህ ጋር ማየት ሲባል እኔ እንደተረዳሁት ከሆነ ብዙ ነገሮችን ያካትታል:: ለምሳሌ አንዱ የሌላውን ስሜት ማጤን መቻል: በትንፋሽና በላህይ(ወዘና ወይም በስሜት በተዋጠ መልክ መተያየት): መነጋገር (ምናልባት የፍቅር ቃላትን ሹክ መባባል) እና መሳሳም- እነዚህ ሁሉ በአካላዊ አይን ከመተያየት የበለጠ በመንፈሳዊ አይን ባልና ሚስቱ እንዲተያዩ ያደርጋቸዋል:: መደባበስ (ምናልባት passionate touching እንደሚባለው አይነት ድርጊት) በራሱ ትርጉም የሚኖረው ሁለቱ ሰዎች በዚህ አይነት መልክ ስሜታዊ ግንኙነት ሲኖራቸው ነው:: እዚህ ጋር መላ ሰውነትን በአይን ካላየሁ ብሎ የሚፎክርና ምናልባት ግልጥልጥ ባለ መልኩ ሁሉን ማየት የሚፈልጉ ተጋቢዎች መጥፎ ሴሰኞች ይሆናሉ ብዬ እገምታለሁ:: መተያየት ሲባል ግን እኔ እንደሚመስለኝ አእምሯዊ ስሜታዊና አካላዊ መገጣጠም ነው:: ይህ ነጥብ የተጠቀሰበት ክፍል እንደሚያትተው ከሆነም ሌሎች ጋጠወጥ የአስተኛኘት አቅጣጫዎች ይህንን ትልቅ ስሜታዊና መንፈሳዊ መተዋወቅና "መተያየት" ሊያግዱት ይችላሉ:: ምናልባት ተባራሪ ጽሁፎች ወይም የነጮችን የፍቅር ልቦለዶች አይተን እንደሆነ ሌሎች ሁሉን ነገር የመተያየትና አካልን አግባብ ባልሆነ መልኩ የመጠቀም ፍላጎቶች (genital manipulation) (ምናልባት oral sex, anal sex, sex from behind... ወዘተ የምንላቸው አይነት ስካሮች) በራሳቸው ከሰውየው ወይም ከሴትየዋ ማንነት ውጪ ሱስ የሚሆኑበት አጋጣሚ እጅግ ብዙ እንደሆነ እንረዳለን:: ያንን የምናደርግበት አጋጣሚ ከተገኘ ሴትዮዋ/ሰውየው ማንም ትሁን/ትሁን ማን ግድ እንደማይኖረንና ለዚያ ስንል ብቻ ግንኙነት ለመፈጸም እንደምንፈተንበት የነጮቹን ችግር ያየ መረዳት አይከብደውም:: ይህ እኔ እንደሚመስለኝ ፍጹም እንስሳነት ነው:: እንዲህ አይነቱ የጋጠ-ወጥ ወሲብ አብዮትም ሴቶችን እንደሙሉ ሰው- የራሷ ማንነት: ስብዕና: ነፍስ: መንፈስ: ስሜት ያላት ፍጥረት ሳትሆን እንደ (የነጮቹን አባባል ልጠቀመውና- Piece of ass ስለቃሉ ይቅርታ- በጣም ገላጭ መስሎ ስለታየኝ ነው) ብቻ ማየትን ያስከትላል:: አንዳንድ ዋርካውያንም ይህን አባባል ደግመውታል- cover the face, attack the base- ይሄ ለአጋራችን ስሜት: ማንነትና ምንነት ያለመጨነቅን ያሳያል::

እና ወደጥያቄህ ጠቅለል ባለ መልኩ ስመለስ- አዎን: ከአይን ውጭ ሌሎች ብዙ የስሜት ህዋሳት ፍቅርን በተሞላ የሩካቤ ስጋ ወቅት ይሳተፋሉ:: ጆሮ: አፍንጫ: ትንፋሽ: ከንፈር እጅ: ፊት: ወ ዘ ተ..... በነዚህ ሁሉ "የሚተያዩ" ባልና ሚስት ጥምረታቸው ልባዊ እና ሰብአዊ እንደሚሆን መረዳት ይቻላል:: እንዲያውም በሩካቤ ስጋ ወቅት አይን በስሜት የተነሳ አብዛኛው ጊዜ የሚከደን ስለሆነ የነዚህ ህዋሳት ተሳትፎ ምናልባት ከአይን ቢበልጥ እንጂ አያንስም::

3. እውሮች ወይም ዓይናቸው የደከመ ሰዎችሽ በምን መልክ ሩካቤን ማካሄድ ይችላሉ /ይኖርባቸዋል ?


እንግዲህ ከላይ ያልነውን ገለጻ ከግምት ውስጥ ካስገባን እውሮች አይን ስለሌላቸው ምናልባት በአካል መልክን መተያየት ላይችሉ ይችላሉ:: ነገር ግን ሩካቤን አስመልክቶ በተለየ ሁኔታ የሚያመልጣቸው ነገር አለ ብዬ አላምንም:: ቀድሞውኑ ነገር እነዚህ ሰዎች የሚተዋወቁት በድምጽ: በትንፋሽ: በዳበሳና በሰዉየው/ሴትየዋ ውስጣዊ ማንነት ስለሆነ እነዚህን አካላዊና መንፈሳዊ ሀብቶች መጠቀም ይችላሉ:: እነሱ እንዲያውም ከዚህ አይነቱ መንፈሳዊ ትስስርን ከሚያላብስ ሩካቤ ውጭ ሌሎች ጋጠ-ወጥ ሥርአቶች አይስማሙዋቸውም ብዬ አስባለሁ:: ይስማማናል ብለው ቢፎክሩ እንኳ ማየት ስለማይችሉ እንደው ሲፈላለጉ መኖር ነው የሚሆንባቸው::

እንግዲህ ከሞላ ጎደል ሀሳቤ ይህን ይመስላል:: ጥያቄህን በደንብ ተረድቼዋለሁ ብዬ እገምታለሁ:: ካልሆነም ብቅ ብለህ ማስተካከያ በመስጠት በሌላ ገጽታው እንወያይባቸዋለን::

ከቀጣዩ ክፍል ጋር ብቅ እላለሁ::

ብርኃናዊት
ብርኃናዊት
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 3302
Joined: Sat Oct 27, 2007 3:57 am

Postby ብርኃናዊት » Wed Dec 26, 2007 9:33 am

ሰላም አንባቢዎች:

ለዛሬ እስቲ ቁጥር 4 "ያለቦታው የሚፈጸም ሩካቤ" የሚለውንና ከርሱ ጋር የተያያዙትን ቁጥር 17 እና 18 (በተቀደሰ ሥፍራ/በቤተክርስቲያን የሚፈጸም ሩካቤ እና ሰው እያየ የሚፈጸም ሩካቤ) በሚሉት ላይ ትንሽ እንማማር::

4. ያለቦታው የሚፈጸም ሩካቤ
17. በተቀደሰ ሥፍራ/በቤተክርስቲያን የሚፈጸም ሩካቤ
18. ሌሎች ሰዎች እያዩ የሚፈጸም ሩካቤ

ያለቦታው ከሚፈጸሙ ሩካቤዎች ሁሉ ምናልባት እጅግ አስቀያሚውና ድፍረት የበዛበት የሚሆነው በቤተ-ክርስቲያን ቅጽር ግቢ ወይም በተቀደሱ ሥፍራዎች (ምሳሌ- ጸበል ቦታ: ነዋያተቅድሳት ያሉበት ግምጃ ቤት: በገዳማት ሥፍራ ወ ዘ ተ...) የሚደረገው ነው:: ይህ ድፍረት ብዙውን ጊዜ አስከፊ መቅሰፍትን የሚያስከትል ነው::

ለመሆኑ ሩካቤ በቤተክርስቲያን መፈጸም ለምን ትልቅ ኃጥያት ሆነ?

አዳምና ሔዋን ተፈጥረው በገነት ውስጥ ለሰባት አመት ከሁለት ወር ሲኖሩ አንድም ቀን እርስ በርስ በገነት ውስጥ ሩካቤ ፈጽመው አያውቁም ነበር:: ለዚህ ብዙ ምክንያቶች ቢኖሩትም አንዱና ዋነኛው ምክንያት ገነት የቤተክርስቲያን ምሳሌ በመሆኗ በየጊዜው የሚነሱ ሰዎች ቤተክርስቲያንን በማቃለል ፈቃደ-ሥጋቸውን ለመፈጸም እንዳይደፋፈሩ ትምህርት ለመስጠት ነው:: ቤተክርስቲያን አጸደ ነፍስ ናትና:: በነፍስ ደግሞ ፍትወተ-ሥጋ የለባትም:: በተጨማሪም በመንግስተ-ሰማያት ሰዎች እንደ መላዕክት ይሆናሉ እንጂ አያገቡም አይጋቡም (ማቴ 22:30) ቤተክርስቲያንም የመንግስተ-ሰማያት ምሳሌ ስለሆነች... ውስጧ በግብረ-ሥጋ መተዋወቅ አይገባም::

በመኝታችን ስናልም አድረን ህልመ-ሌሊት ሲያገኘን ወደ ቤተመቅደስ መግባት የማይፈቀድልን ከሆነ ሩካቤ ከቤተክርስቲያን ምን ያህል መራቅ እንዳለበት መገመት ይቻላል:: የኤሊ ልጆች አፍኒንና ፊንሀስ መቅደስ የሆነ ሰውነታቸውን ማሳደፋቸው አልበቃ ብሏቸው በመገናኛው ድንኳን ደጅ ከሚያገለግሉ ሴቶች ጋር በመተኛታቸው አባታቸው ኤሊ ይህን ርግማን ነገር ማድረጋቸውን እያወቀ እምቢ አላችሁ ልጆቼ ከማለት ብቻ በቀር የወሰደው ምንም አይነት ርምጃ ባለመኖሩ እግዚአብሔር በፍርድ ተነስቶ ታቦተ-ጽዮን እንድትማረክ ሲያደርግ አፍኒንና ፊንሀስም በአንድ ቀን ጦርነት እንዲወድቁ አድርጎአቸዋል:: ኃጥያታቸውን በቸልታ ያለፈ ኤሊም በዚያው እለት ወድቆ እንዲሞት አድርጎታል:: ከዚህ በተጨማሪም "የዔሊ ቤት ኃጥያት በመስዋዕትና በቁርባን ለዘላለም እንዳይሰረይለት ምያለሁ" (1ኛ ሳሙ 2:14 በማለት ራሱ እግዚአብሔር በመቅደስ ዙርያ የሚደረግ ዝሙት ምን ያህል ለቁጣ እንደሚያነሳሳ ገልጾልናል::.....

ጻድቁ ኖህ ወደ መርከብ በገባ ጊዜ ሌላው አለም የጠፋበትን የምንዝር ኃጥያት ልጆቹም እንዳይደግሙበት በመስጋት ወንዶች ልጆቹንና ሚስቶቻቸውን በአንድነት እንዳይሆኑ ለያይቷቸዋል:: ምንም እንኳ ሚስቶቻቸው ቢሆኑም የኖህ መርከብ የቤተክርቲያን አምሳል ናትና ልጆቹ በመርከቧ ውስጥ በሩካቤ እንዲተዋወቁ አልፈቀደም:::...

እስራኤላውያን በመተተኛው በለአም አቀናባሪነት በተዘጋጀው የተንኮል መረብ ተይዘው ለጣዖት በሰገዱና ከአህዛብም ጋር ባመነዘሩ ጊዜ ዘንበሪ የተባለ እስራኤላዊ ከስቢ የተባለች ምድያማዊትን ተሸክሞ ወደ መገናኛው ድንኳን ካገባት በኍላ ከርሷ ጋር ተኛ:: በዚህ ጊዜ ፊንሀስ የተባለ የካህኑ የአላዛር ልጅ የድንኳኑ አውታር ሲነቃነቅ አይቶ ተከትሏቸው ቢገባ ዘንበሪና ከስቢ እርስ በርስ ተያይዘው አገኛቸው:: ለእግዚአብሔር ፍጹም ቅናት ቀንቶ ወደ ቤተእግዚአብሔር በስእለት አማካኝነት በገባ ጦር በሚሰራሩበት አንድ አድርጎ ወጋቸው:: ዘዳ 25: 1-9:: እግዚአብሔር በፊንሀስ ስራ ፍጹም ደስ አለው:: ሰው እንደገደለም አልቆጠረበትም: የጠመመን እንደማቅናት የጎደለን እንደመሙላት አየለት እንጂ:: እግዚአብሄርም ከቁጣው ተመልሶ ለፊንሀስ ለዘላለም በክህነት ያገልግለኝ በማለት ቃል ኪዳን ሰጠው:: ...."


እንግዲህ በተቀደሰ ሥፍራ የሚደረግ ሩካቤ በእግዚአብሔር ዘንድ ፈጽሞ የተጠላ መሆኑን ከብዙ በጥቂቱ እንዲህ አየን:: እኔ የሰማሁት አንድ ታሪክ አለ:: ይህ ታሪክ በትንግርት መልክ በኢትዮጵያ ራድዮ መተላለፉን አስታውሳለሁ:: ቤተክርስቲያኑ ኢትዮጵያ ውስጥ ይሁን ውጭ ሀገር ባላስታውስም ነጥቡ ግን አንድ ወንድ እና አንዲት ሴት በቤተክርስቲያኑ ውስጥ ሰው በሌለበት ሰአት ሩካቤ ሲፈጸሙ አጠገባቸው የነበረው ግድግዳ ተደርምሶ ወንዱ ሞቶ ሴቷ ብትተርፍም እንደዚያው ላያቸው ላይ እንደወደቀ ቆይተው በማግስቱ ራሱ ከላያቸው ላይ ግድግዳው ማንም ሳይነካው ተነስቶ ተመልሶ ቆሟል:: ይህንን ሴቷ ራሷ ምስክርነት ሰጥታለች:: በቅርቡ ደግሞ ኢትዮጵያ ውስጥ በአንድ ቤተክርስቲያን አጸድ ተመሳሳይ ድርጊት የፈጸሙ ሁለት ወጣቶች ድርጊቱን እየፈጸሙ እያለ እዚያው ባሉበት ደርቀው በመቅረት ለተወሰኑ ቀናት የቆዩ ሲሆን የደብሩ ካህናት ልጆቹን ሸፍነውና ሰው እንዳይገባ አድርገው ምህላ በመያዝ በስተመጨረሻ ነፍሳቸውን አውቀው ሊላቀቁ በቅተዋል:: እንግዲህ ከዚህ የበለጠ ምስክርነት በዚህ ረገድ አያሻንም:: አንዳንድ ጊዜ ጠንቋዮች "በዚህ ሥፍራ ሄዳችሁ ብትገናኙ የተቀደሰ ልጅ ትጸንሳላችሁ" እያሉ እንደሚያታልሉም እንዳንረሳ:: በብተክርስቲያን ሩካቤን መፈጸም እኛንም ጽንሱንም ያስረግም ይሆናል እንጂ አያስባርክም::

ይቀጥላል!
ብርኃናዊት
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 3302
Joined: Sat Oct 27, 2007 3:57 am

Postby ብርኃናዊት » Wed Dec 26, 2007 10:48 am

ጥያቄ- ባልና ሚስት ሩካቤን የት ሊፈጽሙ ይገባል?

መልስ- በቤታቸው!!

ጥያቄ- ምናልባት ውጭ እየተናፈሱ ግንኙነት ማድረግ ቢፈልጉስ?

መልስ- ሰው ያያቸው እንደሆነስ? ሰው ሊያያቸው አይገባም!!

ጥያቄ- ሰው ቢያያቸው ታድያ ምን አለበት?

መስል- የኖህንና የልጁን ታሪክ አላነበብክም? ኖህ ከሚስቱ ጋር በስካር መንፈስ ግልጽና ጥንቃቄ የጎደለው ሩካቤ በመፈጸሙ ራሱን ጥሎ እርቃኑን በድንኳኑ ውስጥ እንደተንጋለለ ልጁ አይቶ ስለሳቀበት እንደረገመው መጽሀፍ ቅዱስ ይነግረናል:: የኖህ ልጅ ካም ለርግማን የበቃው በግልጽ በተደረገ ሩካቤ ምክንያት መሆኑን ልብ ማለት ይገባል:: ምንም እንኳ ኖህና ሚስቱ በተገቢው ቦታ ቢያደርጉትም እና እያደረጉት እያለ ባይታዩም ሰው ያየናል ብለው ግን አልተጨነቁም ነበርና ይህ ሁሉ መዘዝ መጣ::

ጥያቄ- ግን ማንም ሰው ሊያያቸው በማይችልበት- ለምሳሌ በቅጽረ-ግቢያቸው ጓሮ ወይም በአታክልት ሥፍራ ወይም በሌላ ቦታ ቢፈጽሙስ?

መልስ- አልጋ እኮ የሰው ልጅ ክብር መገለጫ ነው:: መተኛትም ሩካቤም በአስፈላጊው መንፈሳዊነት ከታጀበ ሀይማኖታዊ ምግባር ነው:: ታድያ ሰው እንዴት እንደተራ ውዳቂ ነገር መሬት ለመሬት ሩካቤ ይፈጽማል?

ጥያቄ- ግን እነሱ ከፈለጉስ?

መልስ- ምናልባት የፈለጉት ራሳቸውን ስላለማመዱት ይሆናል: ወይም በአልጋ ከሚፈጸመው ሩካቤ የተለየ ደስታ የሚሰጥ መስሏቸው ይሆናል: ወይም ለሌሎች ስለማይጠነቀቁ ይሆናል:: ለራሳቸውና ለለሎች የሚጠነቀቁ ግን እንደዚያ አያደርጉም:: ከዚህ ጋር የተያያዙ ሁለት ገጠመኞች ላጫውትህ:-

አንዱ 9ኛ ክፍል ተማሪ የሆኑ ሁለት ሴት ጓደኛሞች ከአንደኛዋ ቤት ቁጭ ብለው እያጠኑ እያለ ከአጠገባቸው ቤቱን ተከራይታ የምትኖር አንዲት ሴት ወንድ ጓደኛዋ ይመጣና ልፊያና ጭዋታ (መቆናጠጥ: መመታታት: መጫወት...) ይጀምራሉ:: ይህ ልማዳቸው ሆኖ ኖሮ ሴቲቱ በያንዳንዱ ድርጊት መሀል ትጮሀለች: ትስቃለች: ወ ዘ ተ... አብረው ከሚያጠኑት የ9ኛ ክፍል ተማሪዎች መሀል እንግዳይቱ እምብዛም ትኩረት ሳትሰጠው ስታጠና ቆይታ በኍላ ጩኸቱ እየበረከተ ሲመታ ይህ ነገር አዲስ ሆኖባትና የጥል መስሏት ደንግጣ "ወይኔ! ምን ሆነው ነው? ለምንድነው የሚጣሉት?" ብላ ጓደኛዋን ትጠይቃለች:: ጓደኛዋም አይኗን እንኳ ቀና ማድረግ አፍራ ትንፋሿ ቀጥ ብሎ እያንዳንዱን ድርጊታቸውን በአይነ-ህሊናዋ እየሳለች ስትከታተላቸው ቆይታ ኖሮ አንገቷን እንዳቀረቀረች የእፍረት ፈገግታ እየፈገገች "ተያቸው ባክሽ ሲጨማለቁ ነው" ብላት ጥናቷን ለመቀጠል ሞከረች:: ነገር ግን ሀሳቧ ፈጽሞ በመበተኑና እንግዳይቱም ነገሩ ገብቷት መሳቅ ስለጀመረች ማጥናታቸውን አቁመው ሌላ ወሬ ማውራት ቀጠሉ:: አሁን እዚህ ጋር በልጅቷ አእምሮ ውስጥ የሚቀረጸውን ነገር ልትነግረኝ ትችላለህ? ሰዎቹ ለልጆቹ ሥነ-ልቦና እንኳ አለመጠንቀቃችው አግባብ ነውን? በመስማት ብቻ ሰው ይህን ያህል ከታወከ በማየት ምን ያህል ይታወክ ይሆን? ካም የአባቱን ርቃን ሲያይ ምን ተሰማው ይሆን?


ጥያቄ- ምናልባት ልጆቹ በዕድሜ ትንሽ ስለሆኑ አግባብ ላይሆን ይችላል:: ነገር ግን ስለ ሩካቤ የሚያውቅ ሰው ባልና ሚስትን ሩካቤ ሲፈጽሙ ቢያያቸው ምን ችግር አለው?

መልስ- ችግርማ አለው!! ሰዎች ሩካቤ ሲፈጽሙ ማየት ሱስ ሊሆን እንደሚችል አታውቅም? ሰዎች ሩካቤ ሲፈጽሙ መታየትስ ሱስ ሊሆን እንደሚችል አልተረዳህም? ሰዎች እኮ ለፖርኖግራፊ ሱሰኝነት የሚጋለጡት ሰዎች ሩካቤ ሲፈጽሙ ማየት ከባድ ሱስ ስለሚሆንባቸው ነው:: ለነዚህ ሰዎች እኮ ሩካቤ መፈጸም ሩካቤ ሲፈጸም የማየትን ያህል ደስታ አይሰጣቸውም:: በዚህ ልማዳቸው የተነሳም በገዛ ትዳራቸው ወይም በገዛ ጓደኛችው መርካት ስለሚያቅታቸው ችግር ውስጥ የሚገቡ በርካቶች እንዳሉ ማወቅ ይገባል::

ከዚህም በተጨማሪ ራስን በፎቶ በቪድዮ ወ ዘ ተ እየቀረጹ የሚያዩና የሚያሳዩ "ጀብደኞች" አንዴ እንዲህ አይነት ህይወት ውስጥ ከገቡ በኍላ ጭራሽ ሊወጡት እንደማይችሉ መገንዘብ ይኖርብናል:: ሩካቤ ሲፈጸም ማየት: ሩካቤ ሲፈጽሙ መታየት እጅግ በጣም ከባድ ሴሰኝነትን ሊያዳብር ይችላል:: በመጽሀፍ ቅዱስ አንድም እንኳ በግልጽ ሩካቤን በመፈጸሙ "እሰየሁ" የተባለ ሰው አናይም:: ይህ ጸባይ የሶዶምና ጎሞራ ሰዎች ጸባይ እንጂ የእግዚአብሄር ሰዎች ጸባይ አይደለም:: የሰዶምና የጎሞራ ሰዎች ማንም ይሁን ማን በየመንገዱ ሩካቤን ይፈጽሙ ነበር:: እንዲሁም ደግሞ ሎጥ ጋር መጥተው የነበሩትን መላዕክት ሰዎች መስለዋቸው "ቤትህ ያሉትን እንግዶች ስጠን: ከነርሱ ጋር መተኛት እንፈልጋለን" ብለው ማለታቸው ራሱ አንዳቸው ሌላኛቸውን እያየ ዝሙትን ይፈጽሙ እንደነበር ማስረጃ ነው:: ይሄ የሶዶማውያን መገለጫ ነው::


ጥያቄ- ወደ አልጋው ጉዳይ እንመለስና አሁንም ሰው በአልጋ ነው እንጂ በሌላ ቦታ ሩካቤ መፈጸም የለበትም ያልከው ነገር አልተዋጠልኝም:: እንዴት ነው? በርግጥ ችግሩ ምንድነው?

መልስ- እንደተባለው አልጋ የሰው ልጅ ክብር ነው:: ሩካቤም ክቡር ነው:: የሚጸነሰውም ልጅ ክቡር ነው:: አብዛኛውን ጊዜ ከአልጋና ከቤት ውጭ ሩካቤ መፈጸም አይምሮን ለኃጥያት ለማለማመድ ቁርጠኝነቱ ላላቸው ሰዎች ነው እንጂ በመንፈሳዊ ቅንነት ለሚያስቡ ሰዎች አስቀያሚ ነገር ነው:: ከላይ ሁለት ገጠመኞች ብዬ የጀመርኩት ትረካ ሁለተናው ከዚህ ጋር ይያያዛል::

ልጅቷ የዩኒቨርሲቲ ተማሪ ስትሆን ከአንድ ወንድ ጓደኛዋ ጋር ምሽት ላይ ተገናኝታ ስታወራ ትቆይና ስሜት ውስጥ ገብተው በስተመጨረሻ ጥሻ ውስጥ መሬት ላይ እንዲህ ያለ ድርጊት ሲፈጽሙ የጥበቃ ሰራተኞች ይይዟቸዋል:: ድርጊቱ አግባብ ካለመሆኑም በላይ ሰአት እላፊ በመሆኑና ለወንዶች ባልተፈቀደ ቦታ ላይ ልጁ እንዲገኝ በመጋበዟ በሚል እሱም እሷም ተከሰው የበላይ ጋር ይቀርባሉ (መቼም የደረሰባቸውን የሀፍረት ስሜት በቀላሉ ለመንገር ያዳግታል):: እዚህ ጋር ስለልጆቹ ለመተንተን ሳይሆን ድርጊቱን የሰማች አንዲት የገጠር ወጣት የተናገረችው ትዝ ስላለኝ ነው:: ያች ልጅ "በስመ-አብ! አልጋ ለምናቸው ተሰራ? የሰውነታቸውስ ክብር? ልጆቹስ እንደፈለጉ ይሁኑ! ግን ቦታ ቢመርጡ ምናለ?" በማለት ነበር ስሜቷን የገለጸችው:: ይህ ተራው የአምሮዋችን ክፍልና ስሜታችን ሰው የመሆናችን መገለጫ ነው: ምንም አዋቂና ተፈላሳፊ መሆን አያስፈልገንም ይህን ለማወቅ:: የሚገርመው ነገር ድርጊቱን የፈጸመችው ልጅ ከዚያ በኍላ ተመሳሳይ ጥፋት ባትፈጽምም በተደጋጋሚ ከዚህ ጋር የተያያዙ ጥፋቶችን በመሥራት መወያያ ርዕስ ለመሆን በቅታ ነበር:: የበለጠ የሚገርመው ነገር ደግሞ ልጅቱ ከዚያ በፊት አይናፋርና በጨዋነት የምትታወቅ የነበረች መሆኗ ነው:: እዚህ ጋር ዋናው ነጥቤ አንድ ለአእምሮዋችን ሊከብደን የሚችልን ነገር (በተለይ ሩካቤን ከመሰለ sensitive ጉዳይ ጋር የተያያዘ ድርጊትን) አንዴ ጨክነን ከፈጸምነው በኍላ ከዚያ በኍላ እንደ አዳምና ሔዋን "ክፉና በጎው ተገልጦልን" ወይም ደግሞ አንዳንዶቻችን ጥሩ በሚመስል ቃል እንደምንገልጸው "አይነጥላችን ተገፎ" ከዚያ የባሱ እሾክና አሜኬላዎችን ስናበቅል እንደምንኖር ለማስረዳት ነው::


ጥያቄ- እሺ! ምናልባት የመሬቱ ወይም የውጭው ጉዳይ ላይ "ሰብአዊነት የጎደለው ነው" ብለን እንስማማ:: ነገር ግን ቤርጎ: ወይም መኪና: ወይም የመዋኛ/መታጠቢያ ገንዳ: ወይም ወዘተ የሚፈጸም ሩካቤን አብረን እንቃወመው ይሆን?

መልስ- አንድ ሰው በጉዞ ላይ እያለ እግዚአብሄር ሰላም እንዲያደርሰው በመመኘትና እግዚአብሄርን በማክበር እንዲሄድ ይገባል እንጂ በመኪና በአውሮፕላን በጀልባ በመርከብ ወ.ዘ.ተ ውስጥ የሚፈጸም ሩካቤ እምብዛም ተደጋፊነት አይኖረውም:: ምክንያታዊ ሆነን ካሰብነውም ብዙውን ጊዜ አመቺ አይደለም:: በሩጫ: በጥድፊያ: በሰው አየኝ አላየኝ የሚደረግ ሩካቤ በጥቅሉ ለሰው ሥነ-አእምሮም ተስማሚ አይደለም:: ይህ በቅዱሳት መጻህፍት በነጭና በጥቁር እስኪጻፍልን መጠበቅም የለብንም:: አብዛኛው የመጽሀፍ ቅዱስ የተቀደሱ ግንኙነቶች ሁሉ በረጋ መንፈስ በቤት ውስጥ የሚፈጸሙ ናቸው እንጂ በተልከሰከሰ አኳህዋን የተፈጸሙ አልነበሩም::

ስለቤርጎ ምን እንላልን? እኔንጃ! ሌላ የሚያግዳቸው ነገር እስከሌለ ድረስ ቤርጎ ውስጥ ሩካቤ ባልና ሚስት ቢፈጽሙ ችግር አለው? እኔ አይመስለኝም!!

ስለመዋኛ ቦታዎች ከሳይንሱም አንጻር ብንመለከተው እምብዛም ተደጋፊነት የለውም:: በፊልም የምንመለከታችው ቅብጠቶች አብዛኛው ጊዜ ጤነኛ ናቸው ማለት አይቻልም:: ብዙ የሩካቤ-ስጋ ተመራማሪዎች አጥብቀው እንደሚያስጠነቅቁት ውሀ ውስጥ የሚደረግ ሩካቤ ወደ ሴቷ ማህጸን በርከት ያለ ውሀ pump በማድረግ ከባድ የጤና መቃወስ ሊያስከትል ይችላል:: ነገር ግን በኃይማኖት አይን ከታየ ከመዋኛ ቦታዎች ወይም ከገንዳዎች ጋር በተያያዘ አብረው ሊታሰቡ የሚገባቸው ሌሎች ነገሮች ስላሉ (እነሱም ከላይ የተጠቀሱት ናቸው) በአብዛኛው እንዲህ ያለ ቅብጠት በንደዚህ ያሉ ቦታዎች ባይሞከሩ ይመረጣል::


ቸር ይግጠመን!!
ብርኃናዊት
ብርኃናዊት
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 3302
Joined: Sat Oct 27, 2007 3:57 am

Postby ዛዙ » Wed Dec 26, 2007 10:23 pm

ብርኃናዊት እንዴት ከራረምሽ? የምታቀርቢያቸውን ትምህርቶች ብስማማም ባልስማማበቸውም እንደማነብ ነግሬሻለሁ:: ስለጾታ ትምህርት አሁን መጨረሻ ላይ የጻፍሽውም ሁሉም ከግብረ-ገብ አንጻር የሚደገፍ ቢሆንም ያንቺ ደሞ ክርስቲያናዊ ትምህርት እሰከሆነ ድረስ በመጽሀፍ ቅዱስ መደገፍ አለበት:: ስትጠቅሺ ደሞ የራስሽን ሀሳብ ሳትጨምሪ መሆን አለበት:: ለምሳሌ
የኖህንና የልጁን ታሪክ አላነበብክም ? ኖህ ከሚስቱ ጋር በስካር መንፈስ ግልጽና ጥንቃቄ የጎደለው ሩካቤ በመፈጸሙ ራሱን ጥሎ እርቃኑን በድንኳኑ ውስጥ እንደተንጋለለ ልጁ አይቶ ስለሳቀበት እንደረገመው መጽሀፍ ቅዱስ ይነግረናል :: የኖህ ልጅ ካም ለርግማን የበቃው በግልጽ በተደረገ ሩካቤ ምክንያት መሆኑን ልብ ማለት ይገባል :: ምንም እንኳ ኖህና ሚስቱ በተገቢው ቦታ ቢያደርጉትም እና እያደረጉት እያለ ባይታዩም ሰው ያየናል ብለው ግን አልተጨነቁም ነበርና ይህ ሁሉ መዘዝ መጣ ::
ብለሻል:: ይህ ታሪክ ዘፍ 9:20-29 ያለ ሲሆን ኖህ እንኳን 'ጥንቃቄ የጎደለው ወሲብ' ሊፈጽም ይቅርና የሚስቱም ስም አይነሳም:: ምንጩ ከየት እንደሆነ ብትነግሪን ለኛ ትምህርት ይሆነናል:: ሌላው ደሞ
ጻድቁ ኖህ ወደ መርከብ በገባ ጊዜ ሌላው አለም የጠፋበትን የምንዝር ኃጥያት ልጆቹም እንዳይደግሙበት በመስጋት ወንዶች ልጆቹንና ሚስቶቻቸውን በአንድነት እንዳይሆኑ ለያይቷቸዋል :: ምንም እንኳ ሚስቶቻቸው ቢሆኑም የኖህ መርከብ የቤተክርቲያን አምሳል ናትና ልጆቹ በመርከቧ ውስጥ በሩካቤ እንዲተዋወቁ አልፈቀደም
ይህ ደግሞ ዘፍ 6:13 ጀምሮ እስከ ዘፍ 8 መጨረሻ ድረስ የተጻፈ ታሪክ ነው:: የትም ቦታ እግዚአብሄር ልጆቹን ከሚስቶቻቸው ለይቶ እንዲያስቀምጣቸው ሲያዘው ወይም እሱ ሲያዛቸው አናነብም:: ያንቺን ክርክር ለመቃወም ሳይሆን ለክርክርሽ የጠቀስሽው ማስረጃ የኖህ መርከብ በአዲስ ኪዳን ከክርስቶስ ጋር ባላት አናሎጂ ነው እንጂ የምታተወቀው ያን ጊዘ እኮ ከምድራዊ ጥፋት የማምለጫ መሳሪያ ነበረች:: ስለዚህ የተቀደስ ነበርና መርከቡ ላይ ወሲብ እንዳይፈጸም ለመልከልከሉ ምንም ማስረጃ የለንም:: Regardless, በተቀደሱ ቦታዎች ወሲብ መፈጸም ተገቢ ነው ማለቴ አይደለም:: ግን ምንድነው የተቀደሰ ቦታ? በአዲስ ኪዳን ሰውነታችንም የተቀደሰ የእግዚአብሄር ቤተ መቅደስ ነው:: ሌላው
አልጋ እኮ የሰው ልጅ ክብር መገለጫ ነው :: መተኛትም ሩካቤም በአስፈላጊው መንፈሳዊነት ከታጀበ ሀይማኖታዊ ምግባር ነው :: ታድያ ሰው እንዴት እንደተራ ውዳቂ ነገር መሬት ለመሬት ሩካቤ ይፈጽማል ?
ያልሺው በኔ አስተያየት ፍጹም መጽሀፍ ቅዱሳዊ መሰረት የሌለው ነው:: ለመሆኑ አዳምና ሄዋን አልጋ ላይ የተኙ ይመስልሻል? አንድ የሆነ ዛፍ ስር ነው የሚተኙ የነበረው ብዬ አስባለሁ:: አያቶቻችን ሁሉ እኛን በሀጢአት ነው የወለዱን ማለት ነው? ለመሆኑ የሰው ልጅ አልጋ ላይ መተኛት የጀመረው መቼ ነው? ሌላው
እስራኤላውያን በመተተኛው በለአም አቀናባሪነት በተዘጋጀው የተንኮል መረብ ተይዘው ለጣዖት በሰገዱና ከአህዛብም ጋር ባመነዘሩ ጊዜ ዘንበሪ የተባለ እስራኤላዊ ከስቢ የተባለች ምድያማዊትን ተሸክሞ ወደ መገናኛው ድንኳን ካገባት በኍላ ከርሷ ጋር ተኛ :: በዚህ ጊዜ ፊንሀስ የተባለ የካህኑ የአላዛር ልጅ የድንኳኑ አውታር ሲነቃነቅ አይቶ ተከትሏቸው ቢገባ ዘንበሪና ከስቢ እርስ በርስ ተያይዘው አገኛቸው :: ለእግዚአብሔር ፍጹም ቅናት ቀንቶ ወደ ቤተእግዚአብሔር በስእለት አማካኝነት በገባ ጦር በሚሰራሩበት አንድ አድርጎ ወጋቸው :: ዘዳ 25: 1-9:: እግዚአብሔር በፊንሀስ ስራ ፍጹም ደስ አለው :: ሰው እንደገደለም አልቆጠረበትም : የጠመመን እንደማቅናት የጎደለን እንደመሙላት አየለት እንጂ :: እግዚአብሄርም ከቁጣው ተመልሶ ለፊንሀስ ለዘላለም በክህነት ያገልግለኝ በማለት ቃል ኪዳን ሰጠው ::
ያልሽው ነው:: [ዘኍልቁ 25 ነው ዘዳግም አይደለም] ማወቅ ያለብን ነገር እስራኤል የበለዐም መተት አይደለም ከሞአብ ሴት ልጆች ጋር እንዲያመነዝሩ ያደረጋቸው:: እሱማ እንደማይሰራ ራሱ በለዐም 'በእስራኤል ላይ ሟርት አይሰራም በያዕቆብ ላይ አስማት የለም' ሲል መስክሯል:: የራሳቸው የልብ ሀሳብ ነው:: ግን በጣም ያሳቅሽኝ
የድንኳኑ አውታር ሲነቃነቅ አይቶ
በሚለው አባባልሽ ነው:: እዛ ክፍል ላይ ይሄ ነገር ስለሌለ መጽሀፍ ቅዱስ ስታነቢ ምናብሽን በጣም ትጠቀሚያለሽ ማለት ነው ብዬ ደምድሜያለሁ:: :lol: በአጠቃላይ ትምህርቶችሽ ከግብረ-ገብ አስተምህሮም አንጻር ተገቢነት አላቸው:: የመጽሀፍ ቅዱስ መሰረት ካላቸው ግን ተገቢውን ጥቅስ ወይም ክፍል ነው ማሳየት ያለብሽ እንጂ እንዲሁ 'ተገቢ አይደለም' ብለሽ ማለፍ ያለብሽ አይመስለኝም::

በመጨረሻ የምነግርሽ ነገር እኛ በአዲስ ኪዳን የምንኖረው በምህረቱ እንጂ ህግን በመጠበቅ አይመስለኝም:: ህግ ስላልበጀ እኮ ነው ጌታ መጥቶ መሰቀል ያስፈለገው:: የህግ ሁሉ መጨረሻ ፍቅር እንደሆነ የእግዚአብሄር ቃል ያስተምረናል ሮሜ 13:10:: እንኳን የሌለ ህግ ልናወጣ ይቅርና ያለውንም መጠበቅ በሰው ልጅ አቅም እንደማይቻል መቼም ላንቺ አላስተምርሽም:: ህግን በመጠበቅ አንድከም:: ፍቅርን ግን እንከታተል:: ያን ጊዜ የሚረባንን ከማይረባን እንድንለይ የሚረዳን መንፈስ ቅዱስ ይመራናል:: ከዛ ውጭ የሚመጣ ምሪት ሁሉ ከንቱ ነው:: ይሄ አባባል ልቅነትና እንደፈለጉ የመሆንን የሚያበረታታ ነው ብለሽ ልታስቢ ትችያለሽ::ነገር ግን የጌታ ፍቅር የገባውና በልቡ ያለ ሰው መቼም ቢሆን ልቅ ሊሆን አይችልም:: ውስጡ ያለው ፍቅር ያስገድደዋል:: መኖር ያለብን እግዚአብሄርን በመፍራት ቢሆንም ከዛ ይበልጥ ደግሞ እግዚአብሄርን መውደድ ነገሮችን ተገድደን ሳይሆን በፍቅር እንድናደርግ ያደርገናል:: ጌታም ያስተማረን ይሄንኑ ነው::

አክባሪሽ

ዛዙ
ዛዙ
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 199
Joined: Sat Oct 09, 2004 12:46 pm
Location: ethiopia

እግዜር ያላከበረውን ተዋህዶ ታከብረዋለች?

Postby አፈ-ጉባኤ » Sun Jan 06, 2008 7:28 pm

የወሲብ አፈጻጸምን አስመልክቶ ባረብ አገራቶች የተለያዩ አስቂኝ ህግጋት አሉ:: ኢራናዊው አያቶላ ሆሚኒ ሊትል ግሪን በተሰኘ መጽሀፉ እንደዘበዘበው በዝርዝር ያተተ የለም:: በመጽሀፉ "ከንሰሳት ጋር በሚፈጸም ተራክቦ ወንዱ ካፈሰሰ በኻላ እንሰሳው እንዲገደል አሊያም ወደ ሌላ መንደር ተወስዶ እንዲሸጥ" ያዛል::

የጥንት ግብጻውያን እንደጻፉት ነትገብ የተሰኙ የሰማይና ምድር አማልክቶቻቸው እጅግ ስለሚፋቀሩ ለአመታት አለማቋረጥ እየተዋሰቡ ሳለ የተሰኘው የአየር አምላክ በቅናት የገብን ብልት ረጋግጦ ጨፈላልቆበታል::

የሰው ልጆች ፈጣሪ ለምን ከወሲብ እሚገኘውን እርካታ የጥቂት ሰኮንዶች ብቻ አድርጎ እንዳሳጠረው አይገባኝም:: ግፍ ነው:: እጅግ ከሚገባው በላይ አሳጥሮታል:: ግብጻውያኑ ያየር አምላክ በቅናት ባያሳጥረው ኖሮ እኛም ያለማቋረጥ በወሲብ እየረካን መቀጠል እንችል ነበር ይላሉ-የጥንቶቹ:: ድንቅ ነበር!

ተዋህዶ የባለትዳሮችን አንሶላ ገፋ በዚህ አስገባ በዚያ አስወጣ ትላለች ብዬ አልጠበኩም ነበር:: አፈጣጠራችንን ካጤነው የሰው ልጆች ፈጣሪ ለወሲብ ክብር ያለው አይመስልም:: ክብርማ ቢሰጠው የደረቅና ፍሳሽ ቆሻሻ ማስወገጃዎችን አንድ ጋ የዘር መውጫን በሌላ ቀዳዳ አድርጎ ይሰራው ነበር:: ባለማድረጉም የተነሳ የሁሉም ሴት ብልት ጥሩ ጠረን የለውም::

ያይሁዳውያኑ አምላክ በዘሑልቅ 31:16 ላይ እስራኤላውያኑ ምድያማውያንን ሲጨፈጭፉ ሴቶችን ስላስተረፉ መቅሰፍቱን አወረደባቸው ይላል:: እሱ ያዘዛቸው ልጃገረዶቹን ብቻ እንዲያስተርፉ ስለነበር:: ወንድ የቀመሳቸው ሁሉ በፊቱ እርኩሰቶች ነበሩ!!

ብሉይ ኪዳንን ስናይ አብዛኞቹ የሀይማኖት አባቶች አተራማሾች ነበሩ:: ዳዊትና ልጁ ሰለሞንማ ያንን ሁሉ ሴት ሲያተራምሱ ባባለዘር በሽታ ሳይለከፉ አይቀርም:: ስላልኖሩበት ፍቅርና ታማኝነት ከሚጽፉ ይልቅ እንዴት በሽታውን በባህላዊ መድሀኒት መከላከል እንደሚቻል (ተከላክለውት ከሆነ) ካልሆነም ስለስቃዩ ቢጽፉ ድንቅ ነበር::

ካንቺው ብሶ ተቀንሶ እንዲሉ እግዜሩ የዘርና ፍሳሽ ቆሻሻ ማስወገጃን ማደበላለቁ የወሲብ እርካታን የአራትና አምስት ሰኮንዶች ማድረጉ ወንድ የደረሰባቸውን ሴቶች በማራከስ ለወሲብ ያለውን ዝቅተኛ ግምት በይፋ እያሳየ ሳለ ተዋህዶ አንሶላ ውስጥ ገብታ የስራ አፈጻጸም አመራር መስጠቷ "ከባለቤቱ ያወቀ ኢንጅነር ነው" ያሰኛታል::

በግሌ ሁሉንም ያጠቃቅ ስልቶች እጠቀማለሁ-ከምላስ በቀር እሱም ምክንያቱ ከላይ ተጠቅሷል::
አፈ-ጉባኤ
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 302
Joined: Tue Mar 15, 2005 5:20 pm
Location: united states

Postby ብርኃናዊት » Fri Jan 18, 2008 9:56 pm

[/quote]
ብርኃናዊት
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 3302
Joined: Sat Oct 27, 2007 3:57 am

Postby ብርኃናዊት » Fri Jan 18, 2008 9:59 pm

እንደምን ከርማችኍል ዋርካውያን:-

ከሳምንታት በኍላ ወደቤቴ ስለተመለስኩ እስቲ ያቆምኳቸውን ነገሮች ልቀጥል ብዬ ወደቤቴ ብገባ አንዳንድ አስተያየቶች ስለቆዩኝ በጣም ተደስቼያለሁ:: ብዘገይም አስተያየት ሰጭዎች ከማንበብ ወደኍላ አትሉም በሚል ተስፋ ለዛዙ እና ለአፈ-ጉባኤ የሚከተለውን ምላሽ ጽፌያለሁ:: ተሳትፎዋችሁ ይቀጥል!!

ውድ ዛዙ_ በቀጥታ ወደጥያቄህ ልግባና:

ስለኖህና ባለቤቱ: ስለ መርከቧ የቤተክርስቲያን ተምሳሌትነትና በወቅቱ የተቀደሰች የአምልኮ መፈጸሚያ ቦታ እንደነበረች: ስለ በለአም: እንዲሁም ስለዘንበሪና ከስቢ እና ስለድንኳኑ አውታር መነቃነቅ በሙሉ በጣም በተዘረዘረ ሁኔታ በብሉያት የአንድምታ መጻህፍት ተተንትኖ ተጽፏል:: በዚህ ረገድ በጣም ሰፊ አስተምህሮና በጣም ብዙ የሀገርህ ባህሎች ሳይቀሩ አሉ:: ምናልባት አልሰማህ ይሆናል እንጂ:: እኔ ከምናቤ የጨመርኩት ምንም ነገር የለም:: ቃል በቃል የጻፍኩትም የመጽሀፉ ጸሀፊ የተጠቀማቸውን ቃላት ነው::እሱ የጻፋቸው ቢሆኑም እኔም ግን 100% እስማማባቸዋለሁ:: ለዚያ ነው ለሌላው ያለምንም ጥርጥር ለማካፈል የተነሳሁት:: እና ሁሉም ነገር (ሌላው ቀርቶ ዘንበሪና ከስቢ በምን መልኩ እንደተወጉ ሳይቀር) አንድምታ መጻህፍቱ ላይ በትንታኔ የተጻፈ መሆኑን ልገልጽልህ እወዳለሁ:: አንድምታዎቹ በራሳቸው ከመጽሀፍ ቅዱስና ከሌሎች የቤተክርስቲያን መጻህፍት ጋር ተገናዝበው የሚጻፉና የቤተክርስቲያን አባቶችም በየዘመናቱ የራቀውን አቅርቦ የረቀቀውን አጉልቶ እንዲያሳያቸው እግዚአብሔርን እየተማጸኑ የጻፏቸውና ያስፋፋፏቸው መጽሀፍ ቅዱስን በቅዱስ መንፈስ መሪነት የተረዱበት ጠቃሚ የመንፈሳዊና አእምሯዊ ምርምራቸው ውጤት በመሆኑ አብዛኛው ኢትትዮጵያውያን ክርስቲያኖች ይጠቀሙባቸዋል: ዋቢ ያደርጎአቸዋል:: የዚህ መጽሀፍ ጸሀፊም ከዚህ የተለየ አይመስለኝም::

በመጨረሻ የምነግርሽ ነገር እኛ በአዲስ ኪዳን የምንኖረው በምህረቱ እንጂ ህግን በመጠበቅ አይመስለኝም

አልክና ከዚያ ደግሞ

የጌታ ፍቅር የገባውና በልቡ ያለ ሰው መቼም ቢሆን ልቅ ሊሆን አይችልም :: ውስጡ ያለው ፍቅር ያስገድደዋል [quote]

1. ታድያ ጌታ ስለህግ ለምን አስተማረ? መጽውቱ: ጹሙ" ጸልዩ: ወ ዘ ተ እኮ ህግጋት ናቸው? በወንጌል ግን በፍቅር ያለገደብ የሚሰሩና እንደአይሁድ በminimum requirement formula ብቻ የማይሰሩ ሆነው በክርስቶስ ታድሰዋል እንጂ አልተሻሩም:: (ጌታ "እኔ ኦሪትንና ነብያትን ላጸና እንጂ ልሽራቸው አልመጣሁም" ያለውን አስታወስክን? አዎ! በኦሪት ከአስር እጅ አንድ እጅ ገቢህን ለእግዚአብሔር መስጠት ህግ ነበር:: በወንጌል ግን "ያለህን በሙሉኡ ሸጠህ ለድሀ መጽውትና ተከተለኝ" ሆኗል ህጉ:: እና ህጉ እኮ ጸና እንጂ አልተሻረም?? እንዲህ አድርገህ በአቅምህ እየሰራህ እንጂ ባዶ ሜዳ ላይ ተቀምጠህ የጌታን ምህረት ብትጠባበቅ እንደይሁዳ ትከስራለህ)

2. "የጌታ ፍቅር በውስጤ እስኪያድር" ብለን ኃጥያት ለመስራት ራሳችንን ነጻ እንልቀቀው ይሆን? (ልቅነትን ሊያስፋፋ የሚችል ይመስልሽ ይሆናል ላልከው- ለኔ ብቻ ሳይሆን በማንኛውም ሰው ዘንድ ግልጽ ያለ እውነታ ነው እንጂ?!!)

3. እኔና አንተስ "ጌታን እናፈቅራለን" ስንል ሳለ ኃጥያት የምንሰራው ጌታን ስለማናፈቅረው ይሆን? ጌታን እያፈቀሩ ሳሉ ኃጥያት የሰሩ እነጴጥሮስ የጌታን ምህረት በመታመን ቢጠቀሙም ህግን ለመጣስ ግን ድፍረቱ ነበራቸውን? (የአይሁድን ህግ ከጌታ ህግ ለይ!! አታመንዝር የአይሁድ ህግ ነበረች:: በአይሁድ ጊዜም ቀላል ነበረች:: በጌታ ጊዜም ህግነቷ አልተሻረም:: የባሰውኑ ጥብቅ ሆነች እንጂ:: ስለዚህም 'ሴትን አይቶ የተመኛት በልቡ አመነዘረ" ተባልን::) ታድያ የጌታ ህግ እንዲህ በቀልድ ልናየው የሚገባ ነው? እስቲ አስበው: በዚህ ቤት የተጻፉት ነገሮች በድርጊት ከማድረግ መቆጠብ ያሉብንን ነገሮች የሚያመላክቱ ናቸው:: ጌታ እኮ ከዚያ አልፎ በልብ ጭምር መፈጸም የሌለብንን ነገር እኮ ነግሮናል???!!! "ሴትን አይተህ በልብህ አትመኝ ሲለን እኮ "የሌላ ሰው ሚስት" አልተባለም?? "ሴት" ማለት ያላገባሀት እስከሆነች ድረስ ማንንም በዚያ አይን ማየት የለብህም ነው ያለው ጌታ??!! ታድያ ከዚህ የበለጠ ጥብቅ ህግ አለ? ሌላው እንዴት ሊገርምህ ቻለ?)

4. ወንጌልስ ከህግ ሁሉ የበላይ በሆነችው በፍቅር ላይ በመመስረቷ "ከህግ በላይ" ተባለች እንጂ "ከህግ ውጭ" ተባለችን?

5. ሰው በመንፈሳዊ ህይወቱ የሚያድገው በህግ ውስጥ አልፎ በመንፈሳዊ ህይወቱ ሙሉ ጉልምስና ከደረሰ በኍላ (በምድራዊ እድሜው ማለት አይደለም) ወንጌልን ማየት እንደሚቀለው ረሳኸውን?

6. ጌታን ማፍቀር ማለትስ ጌታን መውደድ ወይም አለመውደድ ይመስልሀልን? ወይስ ጌታን ሰው በተረዳው እና በፈለገው መጠን መውደድ ይመስልሀል? አዎን! መልሱ ሁለተኛው ነው:: ሰው ጌታን የሚወድበት አቅሙ እንደመንፈሳዊ ህይወቱ እና እንደሀይማኖታዊ ቆራጥነቱና ብርታቱ ይለያያል:: ወንጌላዊ ዮሀንስና ያዕቆብ ከአነሳሳቸው ለጌታ የነበራቸው ፍቅር ይለያይ ነበር:: እናም አንተ ያልከውን "ህግ አያስፈልግም: በውስጤ ያለው የጌታ ፍቅር ብቻ ኃጥያት አያሰራኝም" የሚለው አይነት አቋም የሚሰራው ጌታን ያፈቀርክበት ፍቅር ፍጹም ፍቅር ሲሆን ብቻ ነው:: የፍቅርህ መጠን በራሱ እንደህጻን ቀስ እያለ ያድጋልና ነው:: ይህንን ጳውሎስም በህጻንነት ወደጉልምስና እድገት ባለው እየመሰለ በሚገባ በመልክቱ አስረድቶናል::

እና ውድ ዛዙ: በፍጹም ነፍሴ በፍጹም ኃይሌ በፍጹም ጉልበቴ ጌታን እወደዋለሁ ብለህ የምታስብ ከሆነና በውነትም እንደዚያ ከሆንክ ጌታ በወንጌል ያዘዘውን ትዕዛዝ ፈጽመሀልና ጻድቅ ነህ! ለስም አጠራርህም ምስጋና ይገባል!! እኛንም እዚያ እንዲያደርሰን ከፈጣሪህ ረድኤት በረከት ለምንልን:: አልደረስክ እንደሆነ ግን አሁንም ገና ከህግ በታች ነህና እንደኛው በተለያዩ ኃጥያቶችና በአለማዊ ሀሳብ ምክንያት ዘግይተሀል:: በወንጌል ህግ መሰረት ከህግ በላይ ለመሆንና በውስጥህ ያለውን ለጌታህ ያለህን ፍቅር ፍጹም ለማድረግ ሰይጣን በኃጥያት ወጥመድ እየያዘ ወደኍላ እንዳይስብህ እንደኛው ሁሉ በአንዱ የመከራ ዘርፍ በሆነው በዝሙት ተሰናክለህ እንዳትወድቅ ትምህርት ቅሰም እልሀለሁ::

አክባሪህ!
ብርኃናዊት
ብርኃናዊት
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 3302
Joined: Sat Oct 27, 2007 3:57 am

Postby ብርኃናዊት » Fri Jan 18, 2008 10:22 pm

ሰላም ውድ አፈ-ጉባኤ:

ግልጽነት የተሞላበትን አስተያየትህን አደንቃለሁ:: ሁሉን ለማድረግ እንድንችል (ከፈለግን ኃጥያትን ጭምር) ሙሉ መብትና ሥልጣን የሰጠንን እግዚአብሔር ለፍጹም ዲሞክራሲያዊ አመራሩ የምንሰጠው ምላሽ ፍቅርና በፍቅር መገዛት ሊሆን ይገባል እንጅ ህልውናውን መፈታተንና ህግጋቱን ማናናቅ ሊሆን አይገባም እላለሁ::

አጠር አጠር ያሉ ምላሾችን ለአንዳንድ ነጥቦችህ ለመስጠት እወዳለሁ::

ብሉይ ኪዳንን ስናይ አብዛኞቹ የሀይማኖት አባቶች አተራማሾች ነበሩ :: ዳዊትና ልጁ ሰለሞንማ ያንን ሁሉ ሴት ሲያተራምሱ ባባለዘር በሽታ ሳይለከፉ አይቀርም :: ስላልኖሩበት ፍቅርና ታማኝነት ከሚጽፉ ይልቅ እንዴት በሽታውን በባህላዊ መድሀኒት መከላከል እንደሚቻል (ተከላክለውት ከሆነ ) ካልሆነም ስለስቃዩ ቢጽፉ ድንቅ ነበር ::


በሙሉ በመጽሀፍ ቅዱስ የተጻፈው እኮ ኃጥያቱ ሳይሆን መከላከያ መንገዱና ፈውሱ ነው:: እነሱም "ንስሀ" እና "ህግጋተ-እግዚአብሄርን መጠበቅ" ይባላሉ:: ዳዊት በአብዛኛው መዝሙሮቹ የጻፈው ምን ያህል የሰው ሚስት በመተኛት: በመግደል: እና በሌሎችን ኃጥያቶች ምክንያት እንደታወከና እንዳለቀሰ ከእግዚአብሔር ምህረትን ለማግኘት ምን ያህል እንደለመነ ነው:: ጠቢቡ ሶሎሞንስ "ሁሉ ከንቱ ነው" በማለት ከ1000 ከሚሆኑ ሴቶች ጋር የፈለገውን ለማድረግ እንደመቻሉና ሀብትና ስልጣን የሞሉት ቢሆንም ከክርስቶስ በቀር ምንም ደስታ እንደሌለ በመግለጽ በፍጹም የንስሀ ቃና መጽሀፈ-መክብብን እንደጻፈስ አላስተዋልክምን? አብርሀም- ከሌላ በወለደው ልጅ በእስማኤል ምክንያት ትዳሩና ባለቤቱ በጥቂቱም ቢሆን ተረብሸው እንደነበረ አላነበብክም? እነሶዶምና ጎሞራ እና በጥፋት ውሀ ጊዜ የነበሩትማ ምን እንደደረሰባቸው አልነግርህም::

እና "ያተረማመሱበትን" ብቻ ሳይሆን በአተራማሽ ባህሪያቸው ምክንያት ራሳቸው "የተተረማመሱበትን" ክፍል ጭምር እያነበቡ ትምህርት መውሰድ ይገባል እላለሁ::

ተዋህዶ የባለትዳሮችን አንሶላ ገፋ በዚህ አስገባ በዚያ አስወጣ ትላለች ብዬ አልጠበኩም ነበር ::


ተዋህዶ ክርስቶስ ነው:: ተዋህዶም የምጸብከው ክርስቶስን ነው:: ክርስቶስ ደግሞ ከሰጠኸው ላይቀር ሁለንተናህን እንድጸጠው ይፈልጋል እንጂ "አንተ ሥራዬ ላይ እርዳኝ; የአልጋውን ጉዳይ ለኔ ተወው" እንድትለው አይፈልግም:: ተዋህዶ እኮ እንኳን ከህግ ባለቤትህ ጋር እንዴት ተራክብፕ መፈጸም እንዳለብህ ቀርቶ ሌሎችን በምን አይን እንደምትመለከታቸውና በዕለተለት ኑሮህ ውስጥ እንዴት ልታስብ እንደሚገባህ ጭምር አመራር መስጠት ከጀመረች ቆይታለች? ሩካቤ እኮ በጣም ውጪያዊ ነው:: ውስጣዊ አስተሳሰብህ ላይ ሳይቀር ተዋህዶ አመራር እየሰጠች አይደል እንዴ? አመራሩን ለመቀበል ነው እኮ የተዋህዶ ተከታይ የሆነው?!!

እና እግዚአብሔር ለሥጋ የሚያስደስቱ ብዙ ነገሮችን ቢፈቅድልንም ከርሱ አስበልጠን ስንወዳቸው ግን ይከፋዋል:: ስለዚህ:

ለምግብ- ጹሙ ይለናል
ለእንቅልፍ- በጸሎት ትጉ ይለናል
ለገንዘብ-መጽውቱ ይለናል
ለመልክና ቁመና- ስገዱ ይለናል
ለፍትወት- በአንድ ተወስናችሁ ባግባቡ አድርጉት ይለናል

በዚህ ውስጥ ግን በምንም ተአምር ከምንም ነገር ጋር የማይወዳደር ፍጹም ደስታንና ዘላለማዊ ህይወትን ያጎናጽፈናል:: በሰው ፊትም ግርማ ሞገስንና ልዩ ልዩ ጸጋን ይሰጠናል:: ምንም ሙሉ ለሙሉ የነፈገን መብትም የለም:: ገደብ አበጀለት እንጂ:: ቅዱሳን እኮ እንኳንስ ህግ ተሰርቶላቸው ለመገደብ ቀርቶ በፈቃዳቸው ብዙ ነገሮችን ርግፍ አድርገው ትተው ተከትለውታል:: ምን አገኙ? ላንተ አልነግርህም:: ግን እጂግ አተረፉ::

እናም እንምሰላቸዋ?!!

አክባሪህ
ብርሀናዊት
ብርኃናዊት
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 3302
Joined: Sat Oct 27, 2007 3:57 am

Postby ፌዴራል » Sat Jan 19, 2008 7:40 am

ውድ ብርሀኃናዊት እንደምናለሽ/ህ

ጽሁፉን በጽሞና እየተከታተልኩ ነበር ::አሁን ሳይንስ ደረስኩበት ከሚለው ዘመናዊ ድንቁርና አንጻር የሩካቤ ስጋ ጉዳይ መረን ለቆ የ እንስሳት ባህሪ መያዙ እጅግ በጣም የሚያሳዝን እና የብዙ ሚሊዮኖችን እርካታ ዜሮ ማድረጉ የምንጊዜም ጠበሳ መሆኑ አይካድም::ጥቂት የማይባሉ ኢትዮጵያውያንም የፈረንጆችን የብልግና ዘይቤ ተከትለው መጨማለቅ ከለመዱ ቆይተዋል::ይህም ከ እሳት ወደ እረመጥ ጨምሯቸው ኑሯቸውን የምድር ላይ ገሀነም ስላደረገባቸው ለ እነሱ የሚሆን ባል ወይም ሚስት አውሮፓ ወይም, አሜሪካ ያጡበት እና ከሀገር ቤት ሚኢስት ወይም ባል እንደሽሮ እና በርበሬ ማስመጣት ከተለመደ ቆይቷል::ከዚህ አንጻር ሲታይ የአንች አካሄድ 100% ጨዋነት የተሞላበት በመሆኑ እንዲህ አይነት ኢትዮጵያዊ መኖሩ በግሌ ነኔ ኩራቴ ነው::
ነገር ግን ከላይ እስከተራቁጥር 20 ድረስ ከጠቀስሻቸው ነጥቦች ውስጥ መካከል ቅደም ተከተሉን ባላስታውሰውም
1ኛ በ እርግዝና ጊዜ ክልክል መሆኑ ገርሞኛል::እስኪ አስቢው 9 ወር ሙሉ አንድ ሰው ከህግ ሚስቱ ታቅቦ እንደ ድመት ናዝሮ የሚሞትበት ምክንያት ስለማይኖር ለውስልትና ሰፊ በር የሚከፍት አይመስልሽም?
2ኛ ሊሊት ብቻ መሆኑ ደግሞ መግረም ሳይሆን አስቆኛል::ለምን መሰለሽ ስሜት አማክሮ የሚመጣ ነገር አይደለም:: እንኳን እስኪመሽ ይቅርና 10 ደቂቃ መጠበቅ አቅቷቸው በንዴት የቤት እቃ ሳይቀር የሚሰብሩ መቸም እብዶች ልንላቸው አንችልም:: በሰመመን ልቦለድ ላይ የዮናታን ሚስት ባሏን ጠርታው እሱ በንባብ ተጠምዶ ትንሽ ቢዘገይ ሊሰበር የሚችል እቃ ሁሉ አልቆ ነው የጠበቀው::ታዲያ ለምን ስሜት እያለ የግድ ሌሊቱ እስኪመሽ ተብሎ 12 ሰአት ሙሉ እንቀጣለን? ይህ ነገር በፍጹም ከሀይማኖት ሊሆን አይችልም ብየ እገምታለሁ::ነው ከተባለ ደግሞ እኔ አላምንበትም::
3ኛ የቦታው ጉዳይ የግድ እቤት እና ከዚያም አልጋ ላይ ብቻ መባሉ ደግሞ ገርሞ ገርሞ የሚገርም ነው::
ሰው እንዳያያችሁ :ወይም የሰው ስሜት ጠብቁ ማለት ጥሩ እና የአስተዋይ ምክር ነው::በተረፈ ሰው እንደማያይ እርግጠኛ ከተሆነ የቦታው ሁኔታ የግድ አልጋ መሆን አለበት? ፍጹም አይመስለኝም::
4ኛ ይህ ፖዝሽን የሚባለውን ነገር እኮ አፈርድሜ አበላሽው::ሰዎች ተራቀቅን ብለው ስንት አስቀያሚ ነገር እየሰሩ ባሉበት ዘመን (ከተፈጥሮ የግንኙነት አካል ውጭ) እስካልወጡ እና ለተራክቦ የተፈቀደውን አካል እስከተጠቀሙ ድረስ በጥንታዊ የጋርዮሽ ስርአት እንኳ የሌለ ተራክቦ (አንድ አይነት መንገድ) ብቻ ነው የተፈቀደ መባሉ ሸም ነው::የአንች/ተ ሀሳብ ቢሆን ኢሎጅካል ነው ብየ አልፈው ነበር ::ነገር ግን ከሀይማኖት ጋር ስለተቆራኘ ሱሪ አውሶ አትቀመጡበት ነገር ሆነብኝ ::ምክንያቱም ተራክቦ በራሱ የትዳር ቅመም ነው::ከተፈጥሮ ምግባር ካልወጡ ባል እና ሚስት ተመካክረው ቢቀምሙት ምናለበት?

በተረፈ ግን አሁን በአለም ላይ ከሚታየው ጋጠወጥነት ግን አንች ባልሽው መንገድ ብቻ ተወሰኑ የሚል ህግ ቢወጣም በግሌ እስማማለሁ ::ምክንያቱም ዘር እየጠፋ ንጽህና ገደል እየገባ እርካታም ከነአካቴው እየተሰናበት ሰው ዘመናዊ አውሬ ከሚሆን አንች/ተ እንዳልሽው በአንዷ መንገድም ቢሆን ቆዝሞ ህይወትን መግፋቱ መረን ከለቀቀው ስቱፒድነት 100% ይመረጣል::
ስለ ቃላት አመራረጥሽ/ህ እና ስለ ምጡቅ ምግባርሽ/ህ ሳላመስግን አላልፍም::
Image
ፌዴራል
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 137
Joined: Sun Sep 12, 2004 8:10 am
Location: ethiopia

Postby ብርኃናዊት » Mon Jan 21, 2008 8:59 pm

ውድ ፌዴራል እንደምን አለህ?

እንኳን ለብርኃነ-ጥምቀቱ አደረሰህ!! ስለመልካም አስተያየቶችህ ሁሉ እግዚአብሔር ይስጥልኝ::

ጽሁፉን በጽሞና እየተከታተልክ መሆኑ አስደስቶኛል:: በአምዱ ከአንባብቢነት ወደተሳታፊነት በሸጋገርህም የበለጠ አስደስቶኛል::

አንተው ራስህ እንደገለጽከው መጽሀፍ ቅዱሳዊ ማብራሪያዎቹን ቀደም ብለህ አንብበሀቸዋል:: ስለዚህ አልደግማቸውም:: ነገር ግን አንዳንድ የሎጂክ ጥያቄዎችን በመጠየቅ ባነሳሀቸው ነጥቦች ላይ መልሰህ እንድታስብበት እጠይቅሀለሁ::

በቅድሚያ ሁላችንም እንድንረዳው የምፈልገው የዚህ ቤት ጽሁፍ ዋና አላማ ሩካቤ ባሁኑ ዘመን አለማችን የምትንጫጫውን ያህልና እኛም የመሰለንን ያህል እንደምግብ እንደውሀ እንደአየር ለነፍስ ለስጋ ለመንፈስ አስፈላጊ የደም ሥር የሆነ አድርጎ የማየት ዝንባሌያችንን እንድናስወግድ ለማሳሰብ ነው:: ሰው ከሩካቤ በላይ ነው:: ሌላው ቀርቶ ሰው ያለሩካቤ ተወልዶ እንኳን ያውቃል:: የዛሬ 2000 አመት ኢየሱስ የሚባል አንድ ሰው ያለሩካቤ ተጸንሶ ተወልዷል:: ሩካቤ የተፈቀደ ክቡር ነገር ቢሆንም (ልክ እንደእህል ሁሉ) የቅድስናችንና የህልውናችን መሰረት ግን አይደለም:: ሚዲያ: ዘፈኑ: ፊልሙና ሰዉ ሊያሳምነን እንደሚሞክረው ሩካቤ "የአለማችን ኃያል የስነ-ልቦና ገዢ" አይደለም:: ሩካቤን ልቅ ያደረግነውና ያለቦታው ቦታ የሰጠነው እኛ ነን:: እኛ በቀደድነው ደግሞ ሰይጣን ገባበትና አሰፋልን:: ከሩካቤና በሩካቤ ከመደሰት በላይ ሊያሳስበን የሚገባ ብዙ ነገር አለ:: ብዙ የቤት ሥራ አለብን:: በተለይ እኛ ኢትዮጵያውያን ብዙ ሥራ ይጠብቀናል:: 24 ሰአት ስለሩካቤ የምናስብበት ጊዜ ላይ አይደለንም:: ሩካቤን ክርስቲያናዊ በሆነ መልክ በተገቢው ቦታ: በተገቢው መንገድ: ከተገቢው ሰው ጋር: በተገቢው ጊዜ ባልተሳከረና በልቅ ፍትወት ምኞት ብዛት ባልናወዘ አእምሮ: ቀልባችንን ሳናጣ ልናደርገውና ልንደሰትበት የሚገባ ድርጊት ነው:: እና የሰውነታችን ጌቶች ነን እንጂ ሰውነታችን የኛ ጌታ አይደለም:: ይህችን ፌዴራል በሚገባ የተረዳሀት ይመስለኛል:: ሌላውም አንባቢ እንዲገነዘባት በማለት ነው ያካተትኳት::

ወደ አስተያየትህ ስመጣ:

1ኛ በ እርግዝና ጊዜ ክልክል መሆኑ ገርሞኛል ::እስኪ አስቢው 9 ወር ሙሉ አንድ ሰው ከህግ ሚስቱ ታቅቦ እንደ ድመት ናዝሮ የሚሞትበት ምክንያት ስለማይኖር ለውስልትና ሰፊ በር የሚከፍት አይመስልሽም ?


ሊሆን ይችላል:: ይህን መካድ አልችልም:: አይገባምም!! ነገር ግን ሰውየው እኮ ከማግባቱ በፊት ለዘመናት ከሩካቤ ራሱን ከልክሎ ነበር?!! ተሳስቶ የወደቀ ቢሆንም እንኳን እኮ ራሱን አበረታትቶ አልቀጠለበትም?!! ምናልባት ንስሀ ገብቶ እንደገና ራሱን መግታት ችሎ ነበር:: ታድያ ለ9 ወር ምን ያቅተዋል? ራሱን መጎሸም ለምን አይሞክርም? ለናቲቱ ጤናም እምብዛም የሚመከር እንዳልሆነ ሳይንስ እንኳ ነግሮናል እኮ? በሀይማኖትም በእርግዝና ሩካቤ እንደማይደገፍ: በርግዝና ወቅትም ሩካቤ የፈጸሙ ደጋግ አባቶች እንዳልነበሩ ተማምረናል:: ታድያ መንፈስን ጠንከር አድርጎና ወገቡን አስሮ ለልጁ የሚሆን ማስተማሪያ መጻህፍት: ሽንት ጨቆችን: አሻንጉሊት: መጫወቻ በመሰብሰብ: እንዴት እንደሚያሳድገው በማሰብና እቅድም በማውጣት: እናቲቱንም እንዳታስብና እንዳትጨነቅ ከጎኗ በመሆን በማሳሳቅና መንፈሷን በማዝናናት: የምትታረስበትን ገብስ በመውቀጥና ልጅን የመሰለ ታላቅ የእግዚአብሄር አደራ ተቀብሎ በሀይማኖት በምግባር ኮትኩቶ እንዴት እንደሚያሳድግ በማሰብ ጊዜውን ሊጠቀምበት ይገባል እንጂ ማስተንፈሻ ፍለጋ ሌላ ሴት ሲፈልግ: የሚስቱንም ስሜት ሲያደፈርስ መክረም የለበትም:: በዚህ ወቅት የሚጥለው የስሜትና የኢኮኖሚ እንዲሁም የመንፈሳዊ ትምህርት መሰረት ላይ ነው ልጁ የሚያድገው:: ይህ ታላቅ የሥራ ጊዜ ነው እንጂ ከሰውነቱ ጋር የሩካቤ ናፍቆት ወግ እያወጋ የሚቆዝምበት ጊዜ አይደለም:: ሰው ሊወለድ ነው!! ይህ ሰው ጳጳስም ንጉስም ጀግና ወታደርም ታላቅ መምህርም ሳይንቲስትም ሊሆን ይችላል:: ክብርና ዝግጅት ይገባዋል!! የእግዚአብሄር አደራም ነው:: ምናልባት ከእመቤታችን ከቅድስት ድንግል ማርያም ታላቅ ትምህርት ልንማር ይገባናል ብዬ አስባለሁ:: ጾመ-ማርያም ተብሎ የሚጠራውን የገና ጾም እኮ እመቤታችን ጾማዋለች?!! ሀብታም ሆና እንደዘመኑ ምግብና ልብስ: ደብተርና መጻህፍት ገዝታ ልጇን ለመቀበል መዘጋጀት ባትችልም: ምን እንደምታደርግ የምታማክረው ሰው ባይኖራትም (ምክንያቱም የሚወለደው ማን እንደሆነ ለመናገርና ያለጊዜው ነገር ለማበላሸት ባለመፈለግዋ- ሉቃስ እንዳለን ሁሉን በልቧ ትጠብቀው ነበር እንጂ) - ልጇን ለመቀበልና ለዚህ ታላቅ ጸጋ ለመዘጋጀት እመቤታችን ጌታን ጸንሳ ሳለ ለዝግጅቱና ለክብሩ ብላ ጾም ጾማ ነበረ:: አዎን!! ከእናትም እናት ናት እኮ!! ታድያ እናቶች እርጉዝ እያሉ እንዲጾሙ ቤተ-ክርስቲያን ባታዝም አባት ግን ሱባኤ ሊይዝ ይችላል:: የሳሙኤል እናት ሀና እና የአባታችን የተክለሀይማኖት እናት እግዚአሐረያ "አንተን የማያገለግል ልጅ ከሆነ ባልወልደው ይሻለኛል:: ልጄን ባርክልኝ" እያሉ ሲጸልዩ ኖረዋል:: የጸሎታቸውን ውጤት አይተናል:: ቤተክርስቲያን በአንድ የተወሰነ ወቅት አንድን ነገር አታድርጉ የምትለው በዚያን ወቅት መደረግ ያለበት ሌላ አስፈላጊ ሥራ ስላለ ነው:: ከዚህ ጋር የተያያዘ ነጥብ ለሌላው ጥያቄህም አነሳለሁ:: ከ9 ወሩ የባል ተአቅቦ ጋር በተያያዘ ግን እስቲ የሚከተለውን እናስበው:-

እናቲቱ ምናልባት ለአንድ አመት ለትምህርት ሌላ ሀገር ብትሄድስ? ባል ራሱን ማቀብ የለበትም?

እናቲቱ በህመም ምክንያት ቢያንስ ለ6 ወር ከሩካቤ እንድትታቀብ ዶክተር ቢያዛትስ? ባል ከሩካቤ መታቀብ አቃተኝ ብሎ ለውስልትና መሸነፍ አለበት?

ባልታወቀ ምክንያት ከቤቱ ውጭ ታፍኖ ቢወሰድ: ቢታሰር: ቢዘምት: ወዘተስ? ሚስት ቢያንስ ቁርጡን እስክታውቅ ለወራትም ሆነ ለተወሰኑ አመታት መታገስ የለባትም?

አተኩረን ብናስበው እኮ ከእርግዝና: ከአጽዋማት: ከበአላት ወዘተ ውጭ በጣም ብዙ ሩካቤን የሚያደናቅፉና የባልን ወይም የሚስትን ትዕግስት የሚጠይቁ አጋጣሚዎች በህይወታችን ይከሰታሉ:: የብዙ ባለትዳሮችን ገጠመኝም እንሰማለን:: በዚህ ሁሉ አጋጣሚ እንዴት ልናደርግ ነው? ራሳችንን መግታት መቻል እኮ ከማግባት በፊትም ሆነ ካገባን በኍላ የሚያስፈልገን ትልቅ መሳሪያ ነው?!! ለዚያ እኮ ነው ሩካቤ እኛ የሚመስለንን ያህል የህልውናችን መሰረት አይደለም ብለን ማመን ያለብን?!!

2ኛ ሊሊት ብቻ መሆኑ ደግሞ መግረም ሳይሆን አስቆኛል ::ለምን መሰለሽ ስሜት አማክሮ የሚመጣ ነገር አይደለም :: እንኳን እስኪመሽ ይቅርና 10 ደቂቃ መጠበቅ አቅቷቸው በንዴት የቤት እቃ ሳይቀር የሚሰብሩ መቸም እብዶች ልንላቸው አንችልም ::


እኔም ይህ ነገር ሳነበው መጀመሪያ ገርሞኝ ነበር!! ነገር ግን እስቲ ከዚህ ጋር የተያያዘ ጥያቄ ልጠይቅህ-

ስሜት ሲመጣ አማክሮ አይደለም:: ቤተክርስቲያን እያስቀደስን እያለ ሊመጣብን ይችላል: ባል ሌላ ሴት እያየ እያለ ሊመጣበት ይችላል: በግብዣ መሀል ስሜት ይመጣል: በቴሌቪዥን ማስታወቂያ ምክንያት ስሜት ይነሳል: በጆሮዋችን በምንሰማው Dirty joke ምክንያት ስሜት ሊመጣ ይችላል:: ታድያ በመጣ ቁጥር እናስተናግደው? በእውነተኛው መልክ ስናስበው እኮ ይህ አይቻልም? አይገባምም? ምናልባት ያ ሰው ሥራ ፈት ካልሆነ በቀር:: ቅድም ያልኩህን ነጥብ እዚህ ጋር ላመጣው እገደዳለሁ:: ቤተክርስቲያን በአንድ የተወሰነ ወቅት አንድን ነገር አታድርጉ የምትለው በዚያን ወቅት መደረግ ያለበት ሌላ አስፈላጊ ሥራ ስላለ ነው:: በቀን ብርሀን የምንሰራው የቀኑን ሥራ ነው:: የመስሪያ ቤት ሥራችንን በአግባቡ ሰርተናል? ላውንደሪ የሚገባ ልብስ አስገብተናል? ቤቱን አጽድተናል? ሆስፒታል የተኛ ዘመድ ጠይቀናል? የታሰረ የሀገራችንን ሰው ሄደን አጽናንተናል? የምናነበው መጽሀፍ ካለ አንብበን ጨርሰነዋል? ቤተክርስቲያን አገልግሎት ወይም ስብሰባ ካለብን ሄደን አገልግለን መጥተናል? ይህን ሁሉ አድርገን ጨርሰን ከሆነ በውነቱ ቀኑን ባግባቡ ተጠቅመናልና በጊዜ አልጋችን ላይ ልንተኛና ልንዝናና እንችላለን:: ግን አብዛኞቻችን ይህን አልጨረስንም:: አንጨርሰውምም: "መከሩ ብዙ ነው: ሰራተኛው ግን ትንሽ ነው" እንዳለው ጌታ:: በቀን የምንሰራው መከሩን ማጨድ ነው:: ከባለቤታችን ጋር የምንገናኘው (ያውም በዚህ ዘመን - ትምህርትንና ሥራ ጠፍሮ በያዘን ጊዜ) ምሽት አልጋችን ላይ ነው:: ሩካቤ በአግባቡ ከተፈጸመና ምንም አይነት የአእምሮ ጸጸት ከሌለበት (ማለትም ከሌላ ሰው ጋር በማይገባ ሁኔታ እስካልተፈጸመ ድረስ) ስጋን ብቻ ሳይሆን አእምሮና መንፈስን የሚያድስ እንደሆነ መጽሀፍ ቅዱስም ሳይንስም የመሰከረው ሀቅ ነው:: ታድያ ባልና ሚስት በመኝታቸው ሰአት ከሚገናኙት ተገቢው ሰአት ውጭ ስሜታቸው በቀን በማናቸውም ሰአት በመጣ ጊዜ እንዲያስተናግዱት የክርስቶስ ፈቃድ ቢሆን ኖሮና ለኛም የሚበጀን ቢሆን ኖሮ በቀንም ጭምር አብረው የሚውሉበትን (ምናልባት በቀራጭነትም ሆነ በገበሬነት አብረው አንድ ቦታ አንዲቀመጡና አንድ መስክ እንዲውሉ) ህግ አውጥቶልን ያርግ ነበር:: በዚህ በኩል ምንም ጥርጥር አይግባህ! ክርስቶስ የሚበጀንን እንጂ የማይበጀንን ስራት አይሰራልንም:: ያቺ የዮናታን ሚስት ያልካትን ግን ጸበል ብትጠመቅ ጥሩ ነበር ብዬ እገምታለሁ:: ስሜት እንደህጻን ነው:: ይህን ያህል ፊት ካሳዩት ይጨማለቃል:: ለባሏ ያላት ግልጽነት ሊደነቅ ቢችልም እቃ መሰባበር ድረስ ከደረሰች ግን ምናልባት "ሥነስራት የላትም" ለማለት ያስደፍር ይሆናል::

የቦታው ጉዳይ የግድ እቤት እና ከዚያም አልጋ ላይ ብቻ መባሉ ደግሞ ገርሞ ገርሞ የሚገርም ነው ::


ሩካቤን አልጋ ላይ እንፈጽመው ማለት ሩካቤን መተኛችን በሆነው ቦታ ላይ እንፈጽመው ማለት ነው:: ምናልባት ባልና ሚስት የሚተኙት ሶፋ ላይ ከሆነ ባልና ሚስቱ እዚያ ሊፈጽሙት ይችላሉ:: ምናልባት መሬት ፍራሽ አንጥፈው የሚተኙም ከሆነ ሩካቤን እዚያ ሊፈጽሙት ይችላሉ:: አልጋን የምንተረጉመው "አራት እግር ያለው ከእንጨት ወይም ከብረትና ከፍራሽ የተሰራ: ሁለት አንሶላ አንድ ብርድልብስ; አንድ አልጋ ልብስ ያለውና ራስጌ መብራት ያለውና ከመሬት ከፍ ያለ" ብለን በጠባቡ የምንተረጉመው ከሆነ ተሳስተናል:: እንዲያ ቢሆን ኖሮ አልጋ ያልገዙ ባልና ሚስት እኮ አልጋ እስኪገዙ ሩካቤ አይፈጽሙ ልንል ነው:: ነገር ግን አልጋ ማለት ማንኛውም በምሽት ጊዜ ሰውነታችንን በሥራቱ ለማሳረፍ ንጹህ ልብስ አንጥፈን የምንተኛበት ሥፍራ ነው:: ከጭቃ የተሰራ መደብ ሊሆን ይችላል: ፍራሽ ሊሆን ይችላል- ነገር ግን ቁም ነገሩ ስለተመቸን የምንተኛበት ቦታ ብቻ ሳይሆን ክቡር የሰው ልጅ ሰውነት የሚያርፍበት ቦታ በመሆኑ በንጽህና ጠብቀን የምናዘጋጀው ጎናችንን የምናሳርፍበት ቦታ ማለት ነው:: ቤትን በተመለከተ ቀደም ባሉት ጽሁፎች እንደገለጽኩት ምናልባት በንግድነት ለተወሰኑ ቀናት በምናርፍበት ቦታ- በሰው ቤት: በሆቴል ወ ዘ ተ ቤታችን ስላልሆነ ሩካቤን አንፈጽምም የሚል ህግ የለም:: እዚህ ጋር ዋናው ነጥብ አልጋ ላይ እንታሰር: ከቤት አንውጣ አይደለም:: እዚህ ጋር ነጥቡ- ተልካሻ ቦታ አንፈጽም: አንዝረክረክ: ለሰውነታችን የሚገባውን ክብር እንስጠው የሚል ነው:: በሁሉም በኩል- ማለትም በሰው ፊት ባለመጋለጥ: ተልካሻ ጸባይን እንድናዳብር ባለማድረግ (ምክንያቱም የምናደርገው ከአእምሮዋችን ጋር ስለሚያያዝ): ለሰውነታችን ምቾትን በመስጠትና በተለይ ለሴቶች አእምሯዊና ሰውነታዊ ምቾትን በመስጠት ጥሩ ሩካቤን እንዲፈጽሙ በማገዝ ነቀፌታ የሌለበት ቦታችን ቢኖር አልጋችን ነው:: ሻወር ውስጥ እንኳ ሩካቤ ባይፈጸም እንደማይመርጡ የሚናገሩ ጠበብት ገጥመውህ አያውቁም? እኔ ገጥመውኛል:: የተለያየ ምክንያት አላቸው:: እግዚአብሄር ታድያ ሀሳቡና ሥራቱ ከነዚህ ጠበብት የሚያንስ ይሆን? አያንስም!! ታድያ ጢሻ ለጢሻ: ሰው ፊት: መኪና ውስጥ: ወ ዘ ተ የሚፈጸም ሩካቤ ምን ያህል አጸያፊ ይሆን? እንግዲህ ልባችን ይፍረደው!!

ተራክቦ (አንድ አይነት መንገድ ) ብቻ ነው የተፈቀደ መባሉ ሸም ነው :


ለዝህች አንድ ጥያቄ ብቻ ጥዬ አልፋለሁ-

ምናልባት ባልና ሚስት ተራክቦ ሲፈጽሙ ፊት ለፊት መሆን አለባቸው መባሉ እኮ አንድ አይነት አቅጣጫ ይጠቀሙ ማለት አይደለም:: ፊት ለፊት በአግባቡ ባልጋቸው ላይ ሆነው ሊፈጽሙት የሚችሉት ብዙ አቅጣጫ አለ እኮ?! ስሜትም ያስገድዳቸዋል:: ስሜትም ራሱን የቻለ ነጻነት አለው:: እስቲ አስተውለህ አስበው?!!

በተረፈ ግን አሁን በአለም ላይ ከሚታየው ጋጠወጥነት ግን አንች ባልሽው መንገድ ብቻ ተወሰኑ የሚል ህግ ቢወጣም በግሌ እስማማለሁ ::ምክንያቱም ዘር እየጠፋ ንጽህና ገደል እየገባ እርካታም ከነአካቴው እየተሰናበት ሰው ዘመናዊ አውሬ ከሚሆን አንች /ተ እንዳልሽው በአንዷ መንገድም ቢሆን ቆዝሞ ህይወትን መግፋቱ መረን ከለቀቀው ስቱፒድነት 100% ይመረጣል
::

ትክክል!! ይህን አስተሳሰብ በዚህ ርዕስ ብቻ ሳይሆን በማናቸውም የህይወት ክፍላችን ልናዳብረው ይገባል:: ከእግዚአብሄር ስራት ከሚያወጣኝ "የቀረ ይቅር" የሚል ድፍረት ሊኖረን ይገባል!!

ከአክብሮት ጋር!
ብርኃናዊት
ብርኃናዊት
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 3302
Joined: Sat Oct 27, 2007 3:57 am

Postby ደጉ » Mon Jan 21, 2008 9:16 pm

ብርኃናዊት wrote:..... እንግዲህ በተቀደሰ ሥፍራ የሚደረግ ሩካቤ በእግዚአብሔር ዘንድ ፈጽሞ የተጠላ መሆኑን ከብዙ በጥቂቱ እንዲህ አየን:: እኔ የሰማሁት አንድ ታሪክ አለ:: ይህ ታሪክ በትንግርት መልክ በኢትዮጵያ ራድዮ መተላለፉን አስታውሳለሁ:: ቤተክርስቲያኑ ኢትዮጵያ ውስጥ ይሁን ውጭ ሀገር ባላስታውስም ነጥቡ ግን አንድ ወንድ እና አንዲት ሴት በቤተክርስቲያኑ ውስጥ ሰው በሌለበት ሰአት ሩካቤ ሲፈጸሙ አጠገባቸው የነበረው ግድግዳ ተደርምሶ ወንዱ ሞቶ ሴቷ ብትተርፍም እንደዚያው ላያቸው ላይ እንደወደቀ ቆይተው በማግስቱ ራሱ ከላያቸው ላይ ግድግዳው ማንም ሳይነካው ተነስቶ ተመልሶ ቆሟል:: ይህንን ሴቷ ራሷ ምስክርነት ሰጥታለች:: ....

...ይሄን ታሪክ እንደው አንድ የተረገመ ጉዋደኛ አለኝ እሱ ባነበበልኝ..ከምር አንደኛ ቦታ አይመርጥም ..ሁለተኛ እኔ ይሄን ግድግዳ ረግጠህ እምትሰራውን ስድ ስራ ተው ብለው አልሰማ ብሎኛል..እንዲህ አንድ ቀን የረገጠው ግድግዳ ከ እግሩ አሻራ አልፎ ወድቆበት እስኪገለው ...እርግጠኛ ነኝ እሱ ላይ የወደቀ ግድግዳ መቼም ራሱን ችሎ አይቆምም....;)
"STUPID IS AS STUPID DOES " :D
ደጉ
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 4416
Joined: Mon Dec 15, 2003 10:39 am
Location: afghanistan

Postby ደጉ » Fri Jan 25, 2008 8:48 pm

ብርኃናዊት wrote:..... ድሮ ድሮ "በዚህ ነገር የመጣብኝ ከሆነ ሁሉ ነገር ገደል ይግባ" ይሉ የነበሩት ዝሙት አዳሪዎች ብቻ ነበሩ::


:wink:
.... አሁን ግን የማንኛውም አማካይ ሰው አቋም ሆኗል::

:?

ግብረ-ሥጋ ከግብረ-ሥጋ አልፋ ግብረ-ነፍስ: ግብረ-መንፈስ የሆነችበት ዘመን ላይ የደረስን ይመስላል:: እና ይሄ ጤነኛ ነው ወይ ብለን መጠየቅ አለብን::

..ማንን እንጠይቅ እመቤት...? :?

...ለምሳሌ ቀን ግንኙነት ፈጽሞ ወደ ሥራ መሰማራት:

... :shock: .. እመቤት! ይሄ ደግሞ ችግሩ ምኑ ላይ ነው..እስኪ ያገኘሽውን መረጃ እዚህ አቅርቢሊኝ:: እንደውም ብዙ ጊዜ በተለይ ስፖርተኞች ከውድድር በፊት ሴክስ ያደረጉ በውድድር መልካም ውጤት እንደሚያመጡ ነው እኔ የሰማሁት ..ለምሳሌ እግር ኩዋስ ተጫዋቾች... እኔም ራሴ በግሌ እስከማውቀው ከሴክስ በሁዋላ እምሰራው ስፖርት ከሌላው ቀን በጣም ይለያል...ሰውነቴ እንደ ላስቲክ ነው እሚሳበው.. :D
በአራስነት ጊዜ ሩካቤ:

... ይሄ እንኩዋን ይደብራል...
በርግዝና ጊዜ ሩካቤ...

... ይሄም ያው ነው.....
እና ምናልባት ስጋችን እምብዛም ጤንነቱ ባይናጋ እንኳ ለነፍሳችን ጤንነት መጠንቀቅ የለብንም? መልሱን ላንተ!!

...ነፍሳችንንማ ካስደስትናት ራስዋ ጤንነትዋ ይስተካከላል....እህታችን ከኛ ጋ ቀሪው እኮ ስጋችን ነው ..ነፍሳችንማ በችግር ጊዜ ትታን ነው እምትሄደው...ታዲያ ትቶ ለሚሄድ ምን አስጨነቀን...?

ከጤናዳምና ከአሪቲ የተሰራ ሽቶ አምርተው በገፍ ለዜጎቼ እንዲሸጡ አድርግና ወላጆች ያን እያሸተቱ ምን የመሰሉ ሸጋ ልጆች በግዛቴ ይወልዱልኛል:: አይመስልህም???!!

..ስለ ሽቶ ጥቆማሽን እኔም ከልብ አመሰግናለሁ.... እያሸተቱ እሚወልዱዋቸው ልጆች ግን ቡራቡሬ እሚሆኑ ይመስለኛል....ብዙ ጊዜ "ሽታ" አለባቸው እሚባሉ ልጆች ስላየሁ.. :D
.....እዚህ ግን ብዙ እሚጠየቅ ጥያቄ ይኖረኛል...አብዛኛው ህግ ከስነስርአት የወጣ ነው....ማስተካከል ያለብን...
"STUPID IS AS STUPID DOES " :D
ደጉ
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 4416
Joined: Mon Dec 15, 2003 10:39 am
Location: afghanistan

Postby ብርኃናዊት » Fri Jan 25, 2008 10:40 pm

ደጉ:

.
.ማንን እንጠይቅ እመቤት ...?


የችግሩን አሳሳቢነት ለመረዳት እውነተኛ ቁርጠኝነቱና ትክክለኝ አተቆርቋሪነቱ ካለህ በPrivate ኢትዮጵያውያን የቤት-እመቤቶች: አባወራዎች: ወጣቶችና ልጆች: እንዲሁም ጎዳና ተዳዳሪዎች ላይ እየተደረገ ያለውን ጥናትና እስካሁን የተደረሰበትን ጆሮ አስይዞ የሚያስጮህ አሳፋሪ ውጤት እነግርሀለሁ:: (ስለ ኤድስ ምናምን አይደለም:: ምን ያህል እንደሚወሰልቱና ከማን ጋር እንደሚወሰልቱ እንዲሁም እንዴት እንደሚወሰልቱ የሚያትት ጥናት ነው) ሌላ መረጃ ደግሞ አንተው ራስህ ወረድ ብለህ የጻፍከውን ጽሁፍ አይተህ ራስህን መገምገምና የሌሎች ዋርካውያንን "በዚህ ነገር አትምጡብኝ" የሚለውን ደረቅ አቋም መመልከት በቂ ነው:: ይሄ ጠፍቶሀል ብዬ አላስብም:: ፌዘኛ ሰው ግን ትመስላለህ::

.. እመቤት ! ይሄ ደግሞ ችግሩ ምኑ ላይ ነው ..እስኪ ያገኘሽውን መረጃ እዚህ አቅርቢሊኝ :: እንደውም ብዙ ጊዜ በተለይ ስፖርተኞች ከውድድር በፊት ሴክስ ያደረጉ በውድድር መልካም ውጤት እንደሚያመጡ ነው እኔ የሰማሁት ..ለምሳሌ እግር ኩዋስ ተጫዋቾች ... እኔም ራሴ በግሌ እስከማውቀው ከሴክስ በሁዋላ እምሰራው ስፖርት ከሌላው ቀን በጣም ይለያል ...ሰውነቴ እንደ ላስቲክ ነው እሚሳበው ..


የጤና አምድ ላይ ታገኘዋለህ:: ለጊዜው ፈላልጌ አጣኍት:: ነገር ግን ከሩካቤ በኍላ ለ 3 ሰአት ያህል ሰውነት እረፍት የማይሰጠው ከሆነ ከጊዜ በኍላ ችግር የሚያመጣ መሆኑን የሚያትት ጽሁፍ ነው:: እና ሰውነቴ እንደፕላስቲክ ይሳባል ላልከው- አዎን! አደንዛዥ እጽ የሚጠቀሙ አትሌቶችም "ዕጽ በደንብ ያስሮጠኛል" ይላሉ:: ችግሩ የሚመጣው በኍላ ጉበት ሲነካ ነው:: ይሄ ያሁኑ የኛ ትውልድም 24 ሰአት ስለዝሙት እያለመ ልብሱን በዘር ጭቃ እየለወሰ ትንፋሽ አጥሮት ሲሽመደመድ እየኖረ 40 አመት እንኳ ሳይሞላው የሚሞት ቀሽማዳ ትውልድ የሆነበት እንዱ ምክንያት ይሄ ሊሆን ይችላል:: የሚገርመው ደግሞ "ለማግባት እድሜዬ አልደረሰም: ገና ልጅ ነኝ" እያለ የሚያቀርበው የምክንያት መአት ነው:: አጉል ተግደርዳሪ!! ቀጣፊ ትውልድ!!

ነፍሳችንማ በችግር ጊዜ ትታን ነው እምትሄደው ...ታዲያ ትቶ ለሚሄድ ምን አስጨነቀን ...?


እንግዲያው ስትሞት ሳጥንህን ሰፋ አድርገህ ለስጋህ ሌሎች ክፍሎች አሰራለት:: ከምድር በታች ካንዱ ክፍል ወዳንዱ እየተዘዋወርክ እንድትኖር:: ፌዘኛ!!

..ስለ ሽቶ ጥቆማሽን እኔም ከልብ አመሰግናለሁ .... እያሸተቱ እሚወልዱዋቸው ልጆች ግን ቡራቡሬ እሚሆኑ ይመስለኛል ....ብዙ ጊዜ "ሽታ " አለባቸው እሚባሉ ልጆች ስላየሁ ..


የዚህ ጽሁፌ አንድምታ ከውጪ ሁሉን ነገር ማስመጣትና መማር (አጉል ባህልን ጨምሮ) አይልመድብን: የራሳችን ቤተክርስቲያን በአጽዋማትና በበአላት ያወታችልንን ህግ እንከተል ለማለት ነው: እንጂ ስለሽታ ለማውራት አልነበረም::

.....እዚህ ግን ብዙ እሚጠየቅ ጥያቄ ይኖረኛል .....


ከነፍሳቸው ሳይሆን ከስጋቸው ጋር ለመኖር እቅድ ላወጡ ሰዎች የሚሆን ምንም መልስ የለኝምና አታልፋኝ!!

ብርኃናዊት
ብርኃናዊት
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 3302
Joined: Sat Oct 27, 2007 3:57 am

ለብርሀናዊት

Postby ጡሙሶ » Sat Jan 26, 2008 12:33 am

መቼም ለዚህ አርስት እንግዳ ነኝና እንኩዋን ደህና መጣህ ብለሽ እንደምትቀበይኝ አልጠራጠርም

ብርሀናዊት ይህንን አርስት መርጠሽ ለውይይት መጋበዝሽና በማስተማርሽ ሳትመሰገኚ አታልፊም;; በተቻለ መጠን ለማስረዳት ሞክረሻል;; በቂ ነው ባይ ነኝ እኔ በበኩሌ;; አንድ ግን እየተደጋገመ የሚጠየቅ ጥያቄ ግን አለ;; ይሄም ደግሞ እንደዚህ ባደርግ ምናለበት? . . . ምናለበት? በአጭሩ ለምናለበት መልስ የለውም;; የቤተክርስትያን ትምህርት የእግዚአብሔር ትምህርት ነው;; <አታመንዝር> የሚለውን የእግዚ/ር ትእዛዝ ምን ማለት እንደሆነ ቤተክርስትያን ትተረጉመዋለች;; ግልጽ ነው? ስለዚህ የጥያቄ ማብዛትና: ምክንያት መደርደር: ምናለበት እያሉ መጠየቅ የእግዚ/ር ትእዛዝ ሊያስቀይር አይችልም;; ጥያቄው ለማወቅና ለመማማር ከሆነ ግን አይጠላም;; ሀጢያትን እንደ ተፈቀደ አድርጎ ለመውሰድና ለመፈጸም ከሆነ ግን ተሳስተናል ያለነው;; መንገዳችንን መሳታችንን አውቀን ወራጅ ብለን ትክክለኛ መንገዳችንን እንያዝ;;

ግልጽ መሆን ያለበት ነገር
መጽሐፍ ቅዱስን ካነበብን እግዚ/ር መጀመርያ ሕጉን ሲሰጥ (10 ቃላት) የግድ ይሄን መፈጸም አለባችሁ ብሎ ያስገደደው ሰው የለም;; እሱ ያለው <የሰጥሁዋችሁን ሕግ ከፈጸማችሁ እኔ አምላካችሁ እናንት ደግሞ ሕዝቦቼ ትሆናላችሁ>; ያልፈለገ በራሱ መንገድ መጓዝ መብቱን አልነፈገውም;;
ክርስቶስም ልክ እንደ አባቱ ነው ያደረገው;; የምትወዱኝ ከሆነ ትእዛዜን ጠብቁ: ይኸው ጠባቡና ሰፊው በር በመረጣችሁት መግባት ትችላላችሁ;; ክርስቶስም ማንንም አላስገደደም;; እግዚ/ር ለሰው ልጅ በተፈጥሮው ሙሉ ነጻነትን ሰጥቶናል: አሁንም ቢሆን ነጻነታችንን አይነካብንም;; የኛ የራሳችን ምርጫ ነው;;

ስለዚህ አንድ ክርስትያን ነኝ የሚል: በክርስቶስ ስም የሚጠራ ክርስቶስ ባሳየው መንገድ መጓዝ ግዴታው ነው;; ይሄ ደግሞ የውዴታ ግዴታ ማለት ነው;; ወድጄ ፈልጌ ነው ክርስትያን የሆኑኩት ስለዚህ እንደክርስትያን መኖር ደግሞ ግዴታዬ ነው;; ሁለት አይነት መንገድ የለም;; ማለት ቤተክርስትያን ውስጥ ክርስትያን ከቤተክርስትያን ውጪ ደግሞ ሌላ ሰው እንደመሆን;; ይሄ ደግሞ አይሆንም;; ከሰኞ እስክ እሁድ ከጠዋት እስከ ማታ ክርስትያን መሆን ነው ክርስትና;;

ሰለዚህ የውይይቱ ተሳታፊዎች እኛ ክርስትያን ከመሆናችን በፊት ሰዎች ነን;; ሰው ደግሞ በእግዚ/ር አርአያና አምሳል የተፈጠረ ክቡር ነው;; ስለዚህ ክቡነታችንን አንርሳ;; ከእንስሳ የሚለየን ደግሞ የምናደርገውን የማመዛዘን የመፍረድ ችሎታ ስላለን ነው;; ስለዚህ የሚያምርብንና የሚያስጠላብንን: የሚጠቅመንንና የሚጎዳንን; የሰው ስራና የእንስሳ ስራ ከለየን ክርስትያን መሆን አይከብደንም;; ለመሆኑ እንስሳ ነው ወደ ሰው የተቀየረው ወይስ ሰው ነው ወደ እንድሳ የተቀየረው ብለን ራሳችንን ጠይቀን እናውቃለን? ካልጠየቅን ዛሬ እንጠይቅ;;

በደንብ ከተረዳን በክርስትና መንገድ መጓዝ ሕይወት ነው;; ለስጋዊ ሆነ ለመንፈሳዊ ሕይወታችን;; አዎ በሰለጠነው አለም እየተቀመጡ: ሀጢአቱና የጽድቁ ስራ የማይለይበት እንደክርስትያን ሆኖ መኖሩ ሊከብድ ይችላል;; ግን <ከአንጀት ካለቀሱ> እንደሚባለው እኛ በቁርጠኝነት ብቻ እንነሳ እንጂ የተቀረውን እግዚ/ር በጸጋው ይረዳናል;;

ተኝተህ ያለህ ንቃ!
በወጣትነት ጊዜህ አምላክህን አስብ:
አንተና አምላክህ ብቻ የምትገናኙበትን ጊዜ ወስንና ከሱ ጋር ተነጋገር; እሱም ይረዳሀል;;

ማስታወሻ: - ብርሀናዊት ያልገባኝ ነገር አለ;; ባልና ሚስት ከቃል ኪዳን በሁዋላ ለሁለት ቀን የሚሆን መገናኘት አይችሉም የሚለው ግን ግልጽ አልሆነልኝም;; ከቃል ኪዳን በፊት ያለውን ዝሙት ነው;; ከተጋቡ በሁዋላ ግን የሚሰጠው ምክንያት አጥጋቢ ሆኖ አልታየኝም;; በደንብ አድርገሽ ብታብራሪው;; በሁዋላ ደግሞ ለሙሽሮቹ ከባድ ነው;;

ለዛሬ በዚህ ይብቃኝ
ebakacihu sele selam enenegager
ጡሙሶ
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 170
Joined: Thu Nov 08, 2007 12:06 pm
Location: Eritrea

ለወጣቱ

Postby ጡሙሶ » Sat Jan 26, 2008 4:24 pm

ለምን ወሊድ መቆጣጠሪያ አንጠቀምም?? ለሚለው

ሳይንስ በሕይወታችን ብዙ ጥሩ ነገር እንዳደረገ ባይካድም እንኩዋ ጉዳትም ሳያስከትልብን አይቀርም;; ከአርስታችን ጋር የሚሄድ ለመጥቀስ;

1. ወደ መረን የለቀቀ ስድነት መርቶናል;; ምክንያቱም ወሊድ መቆጣጠሪያ ክኒን ትወስዳለች: ከዚያ ከማንም ጋር መጋደም;; ወንዱም ኮንዶም እየተጠቀም መጋደም

2. ብዙ ሴቶች እህቶቻችንን ወሊድ መቆጣጠሪያ እንዳይወልዱ እንዳደረጋቸው ደግሞ ያለመዘንጋት

ስለዚ ሳይንስ ጥሩም መጥፎም ጥሩም ጎድን አለው::

በሳይንስ ከመማራችን በፊት እግዚ/ር ሁሉን አዘጋጅቶታል;; ይሄም ባህርያዊ ወሊድ መቆጣጠርያ;; ሴት ልጅ በ1 ወር ውስጥ መውለድ የምትችልባቸው ቀኖች ከ8 አያልፉም;; 22 ቀኖች መውለድ አትችልም;; እሺ ለጥንቃቄና የወንዱ ዘር በሴትዋ ማህጸን ውስጥ ሁለት ቀን በህይወት የመኖር እድል ስላለው ብለን ከፊትና ከሁዋላ ሁለት ሁለት ቀኖች እንጨምርበት 18 ቀኖች ያለምንም መጠራጠር አትወልድም;; ሴክስ ማድረግም ይቻላል;; ስለዚህ እግዚ/ር ከምጀመርያ አዘጋጅቶታል;; ስለዚህ ለባልና ለሚስት በወር 15 ቀን በቂ ሆኖ አይታያችሁም;; በሁዋላ ደግሞ ያለምንም ችግር; ማለት ከኪኒን ከሚመጣ አሉታዊ ጎን ነጻ ነው የምትሆነው;;

ለምሳሌ አንድ የ25 ዓመት ልጃ ገረድ ዓመት ዓመት ብትወልድ 15 ልጅ የመውለድ ችሎታ ቢኖራትም እንኩዋ እግዚር ግን የሰው ነገር ስለሚረዳው መከላከያውንም አድርጎላታል;; ስለዚህ ሳይንስን ብቻ ሳይሆን እግዚ/ርንም መስማት ያስፈልጋል;;

በተጨማሪ ደግሞ በክርስትና ሃይማኖት ሴክስ የራሱ ዓላማ አለው;; መጀመርያ የእግዚ/ር ስራ ለመቀጠል (ልጅ መውለድ ነው);; ሆን ተብሎ ልጅ ላለመውለድ ተብሎ በወሊድ መቆጣጠርያ እየተጠቀሙ የሚደረግ ሀጢአት ነው;; አቅምን አውቆ የእግዚ/ር መደብ ሳይቃወሙ መፈጸም ግን ሐጢአት አይደለም;; ምክንያቱም በተፈጥሮ የተደረገ ነገር ሀጢአት አይድለም;;

ለምሳሌ: ሁለት ባልና ሚስት <በተለይ ውጪ የሚኖሩ> ልጅ ማሳደግ ትንሽ ከበድ ስለሚል: ይዞታቸውን አይተው ከተወሰነ ዓመት በሁዋል እንወልዳለን ቢሉ; ጊዜው እስከሚደርስ ድረስ እንደባልና ሚስት ባህርያዊ የመከላከያ ዘዴ እየተጠቀሙ ቢፈጽሙ ሐጢአት የሚያስብለው ነገር የለም;; ከእግዚር መደብ አልወጡም;; በቂ መተዳደርያ የሌላቸውን ባልና ሚስት ልጅ የግድ መውለድ አለባችሁ ብሎ ማስቸገር በችግር ላይ ችግር መጥራት ነው;; ሐጢአት የሚያስብለው ግን እየቻሉ ሆን ብሎ ለመውለድ አለመፈለግ ነው;;

ከጋብቻ በፊት የሚደረግ ማንኛውም ሴክስ ግን ሐጢአት ነው;;

ቸር ሰንብቱ
ebakacihu sele selam enenegager
ጡሙሶ
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 170
Joined: Thu Nov 08, 2007 12:06 pm
Location: Eritrea

PreviousNext

Return to Warka Intimate - ዋርካ ፍቅር

Who is online

Users browsing this forum: No registered users and 4 guests