የጃማ ልጆች ካላችሁ

The Love Forum (love, relationship) (የኔ ቆንጆ እንተዋወቅ :-)

Postby ባለሱቅ » Fri Feb 08, 2008 9:57 am

አንቺዬ
እኔ ያገርሽ ልጅ እያለሁ ወዴት ወዴት ጦስኝ አሰኘሽ?
ህምምምምምምምምምም

በይ ተመለሽ ወደሰፈርሽ

አገርሽን ግን ለማየት ጉጉትትትትትትትት እንዳልኩ ነው ምነግርሽ
ምን
አንዴ ስህን
አንዴ ደሴ
አንዴ ሮቢት
አንዴ ጃማ
አንዴ ጦስኝ

የት ሄደን እንፈልግሽ

እግራችን ቀጠነ

ወልዲያ አንድ መላ ሊፈጥር ይገባል
ህምምምምምምምምምምም
ባለሱቅ
ውሃ አጠጪ
ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1288
Joined: Mon Sep 27, 2004 6:20 am
Location: ethiopia

Postby የጃማ ጦስኝ » Mon Feb 11, 2008 4:56 pm

ሰላምታዬ ለሁሉም ይድረስ እንደምን አላችሁልኝ

ሰሞኑን ቤቴ ቀዝቀዝ ብሏል እዳልተመቻችሁ አሰብኩኝ

ብተረፈ በየካቲት 10/2000 የነነዊ ጾም ይገባል:: ማለት ሰኞ ገብቶ ሐሙስ ይሚፈታው ማለት ነው:: እንደገናም በዚሁ ወር ማለት በየካቲት 24/2000 ዋናው የዓብይ ጾም ይገባል ማለት ነው:: ከሀገር ውጭ ርቃችሁ ላላችሁ እና በየአካባቢያችሁ ቤ/እግዚአብሄር ለሌለ ሁሉ ይጠቅማል በማለት ይህችን ላበረክት ብዬ ነው በተረፈ መልካም ሁኑልኝ
በቅንነት ፈራጅ ሕዝብ እንዳይጐዳ:
ማን ይሆን ትልቅ ሰው ሃቅን የተረዳ :?:

Image
http://www.cyberethiopia.com/warka5/vie ... hp?t=26693
የጃማ ጦስኝ
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 338
Joined: Sun Sep 02, 2007 12:02 am
Location: ጃማ

Re: የጃማ ልጆች ካላችሁ

Postby መስሜ » Wed Feb 13, 2008 12:29 am

የጃማ ጦስኝ wrote:ብቅ ብቅ በሉ መልካም ስራ ለመስራት
ምን ሊሰራ ታስቦ ነው? ንገረኝና በፉጨት ልጥራቸው ቅቅቅ ከምር ግን የጃማ ጦስኝ ሲባል እሰማ ነበር:: ግን ግን ካልጠፋ ነገር ጦስኝ ምን ሊሰራ እኔ እንደሁ ሻይ አልወድ ቃቃቃ አሁን ደሞ አንተ እዚህ ከች ብለህ ሳይ ጀማ የት ነው ብየ ሳስብ ውቃው ጀማማ መሬ አጠገብ ነው ሲለኝ በቃ ልቤ ድው ድው ድው አለልሀ::

ጀማው ይፍረደኛ የምትል ዘፈን ልልቀቅባችሁ

http://www.youtube.com/watch?v=2nqLuy7Rkq0
DON"T BAN ME
መስሜ
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 186
Joined: Fri Aug 17, 2007 10:58 pm

የከንፈር ወዳጅ

Postby ወልዲያ » Wed Feb 13, 2008 7:36 am

ሠላም!
ኧረ ተው አንተ ልጅ መስሜ ያገሬ ልጅ:
እሷ ተይዛለች በዛ የየጁ እጅ::===:-)

Image

ጦስኝን አይተህ ለምን ታልፋታለህ:
ቢሆንም ባይሆንም ባይንህ ታልፋታለህ:---:-)
ባለሱቅ ብቻ ነው ትጠረጥራለህ::---:-)

የከንፈር ወዳጄን አይቼ እና አፍቅሬ:
አበት ላይ ወጣሁኝ በሷ ተጠርጥሬ::

ጥላሁን ታምራት (ቀይ እና ጠይም ናት)
http://www.youtube.com/watch?v=t3QEgSYxDR8ፍቅር የሠላም ገጽታ ነው
ወልዲያ
ወልዲያ
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 679
Joined: Tue Apr 17, 2007 11:55 am
Location: የጁ - ወሎ

በውሉ

Postby ወልዲያ » Sun Feb 17, 2008 10:15 am

ሠላም!Image
የሚጠጣ ውኃ ሳናገኝ በውሉ:
ከቶ ለምንድን ነው እንዲህ መብጠልጠሉ???

ጃማን ካርታ ላይ ማገኘት አልቻልኩም:
ሳል ሳል አድርገሽ አሳዪኝ በሠላም::


መልካም ሰንበት
ወልዲያ - የጁ
ወልዲያ
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 679
Joined: Tue Apr 17, 2007 11:55 am
Location: የጁ - ወሎ

Postby የጃማ ጦስኝ » Wed Mar 05, 2008 10:56 am

ሰላምታዬ ይድረሳችሁ::
ሰሞኑን ባለመኖሬ ቤቴ ቀዝቅዣል ምነው እናንተም ጠፋችሁ
በሉ እንግዲህ ጾሙን የበረከትና የሰላም ያድርግልን
አንጠፋፋ
በቅንነት ፈራጅ ሕዝብ እንዳይጐዳ:
ማን ይሆን ትልቅ ሰው ሃቅን የተረዳ :?:

Image
http://www.cyberethiopia.com/warka5/vie ... hp?t=26693
የጃማ ጦስኝ
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 338
Joined: Sun Sep 02, 2007 12:02 am
Location: ጃማ

Postby የጃማ ጦስኝ » Thu Jan 15, 2009 7:01 pm

ሰላም ለዚህ ቤት ታዳሚዎች በሙሉ እንዴምን ከረማችሁ ::

በደረሰብኝ የሰራ ውጥረት ምክንያት ቤቱ ለረጂም ጊዜ የቀዘቀዘ ቢሆንም, ቤቱ ለተነሳበት አላማ ወደኋላ ስለማይል አሁንም በድጋሚ የጃማ ልጆች በየትኛውም የዓለም ክልል የምትገኙ ሁሉ ቤቱን እየጎበኛችሁ ለተቀደሰ አላማ እንድንንነሳ መልዕክቴ ይድረሳችሁ
በቅንነት ፈራጅ ሕዝብ እንዳይጐዳ:
ማን ይሆን ትልቅ ሰው ሃቅን የተረዳ :?:

Image
http://www.cyberethiopia.com/warka5/vie ... hp?t=26693
የጃማ ጦስኝ
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 338
Joined: Sun Sep 02, 2007 12:02 am
Location: ጃማ

Postby ENGEDA1967 » Fri Jan 16, 2009 2:52 pm

ሰላም ወሎዬዎች
ወሎን አይቻት አላውቅም እንዲሁ በዝና ነው እንጂ ደግሞ አንድ እሸቱ የሚባል ነባር የደርግ ወታደር የነበረ አውቃለሁ የወሎ ልጅ ነው በተለይ የእያዩ ማን ያዘዋልን [ ዐይናማ እያለ የሚጫወተውን ዘፈን ሲሰማ ማበድ ነበር የሚቀረው አንድ ይመር የሚባል ልጅም አውቃለሁ ጉዋደኛየ ነበረ [ የአንድ ቅጥር ነን ] .
ለፍቅር ቆንጆ ናቸው ይባልላቸዋል ቆንጆዎችም ናቸው ሲባል እሰማ ነበር እኔ ግን አንዲት ፉንጋ ወሎየ አግኝቼ አብጄ ነበር የእስራኤል አምላክ ነው የገላገለን አመለጥኳት ቅቅቅቅቅ
ከውነት ወሎየ ሲባል ሲባሉ እወዳቸዋለሁ ለምን ብትሉኝ እንጃ ነው መልሴ ለነገሩ የምጠላው ሰውም የለኝ እስኪ ለሁሉም አንድ የምወደው ዘፈን ልጋብዛችሁ.
የወሎ ልጅ ናት የቦረና
የደጋጎቹ መልከ ቀና
የወሎ ልጅ ናት ያምባሰል
አቤት ውበትዋ ሲያማልል
//////////////////////
እሙች የፍራንስዋ ቆንጆ ወሎየ ነሽ መሰል ጠርጥሬሻለሁ
እስኪ ንገሪኝ ለምን እንምደወደድኩሽ ?
www.youtube.com/watch?v=5ftz117okl8&nr=1
engda ነኝ የጥንቱ
ENGEDA1967
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 475
Joined: Fri Aug 27, 2004 11:09 pm
Location: united states

እንኳን ለጥምቀት በዓል በሰላም አደረሰን!!!!

Postby የጃማ ጦስኝ » Fri Jan 16, 2009 3:51 pm

ሰላም ለዚህ ቤት ታዳሚዎች በሙሉ

የቤቷ ዓላማ እንደነገርኳችሁ ለተቀደሰ ዓላማ ነው በመሆኑም የተቀደሰ አስተያየታችሁ እንዳይለየን እንጋብዛችሗለን
እንኳን ለጥምቀት በዓል በሰላም አደረሰን:::
በቅንነት ፈራጅ ሕዝብ እንዳይጐዳ:
ማን ይሆን ትልቅ ሰው ሃቅን የተረዳ :?:

Image
http://www.cyberethiopia.com/warka5/vie ... hp?t=26693
የጃማ ጦስኝ
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 338
Joined: Sun Sep 02, 2007 12:02 am
Location: ጃማ

ማን ይሆን ትልቅ ሰው?

Postby የጃማ ጦስኝ » Fri Jan 16, 2009 11:41 pm

ለሌሎች በማሰብ አብዝቶ የሚጨነቅ;
ማን ይሆን ትልቅ ሰው ከሰዎች የሰው ሊቅ::
በቅንነት ፈርቅጂ ህዝብ እንዳይጎዳ:
ማን ይሆን ትልቅ ሰው ሀቅን የተረዳ::
ብዙ ጥበብ ያለው የውቀት አስተማሪ:
ቢበደል ቢጎዳም ሰዎችን መሀሪ::
ማን ይሆን ባለም ላይ ጥበብ የበዛለት:
የተጎዳን አይቶ ፈራጂ በቅንነት::
መንገዱ የቀናች በፍቅር የተሞላ :
በውነት የታመነ ጠባቂ መሀላ::
ማን ይሆን ይኸ ሰው ትልቅ የከበረ
በሰዎች መካከል ፍቅሩን ያዳበረ::
ኧረ ማን ነው ይኽ ሰው እጂጉን የላቀ:
ፍርድ እማያዛባ የተጠነቀቀ::
ሁሉ ሀብታም ድሀው
ሲፈልግ ይኽን ሰው:
የሰማይ መላዕክት አሰሙ ምስጋና;
እረኞች ቀደሙ ለመስማት ውብ ዜና::
የዚህ ዓለም ሁሉ ጌታ :
የመላው ፍጥረት ባለቤት:
ምንም እንደሌለው ንብረት:
ተወለደ አሉ በበረት!!
ከብቶቹን ሊያድን ከጥፋት!!


በመጭው ሰኞ የሚውለውን የጥምቀት በዓል ምክንያት በማድረግ ለመላው ታዳሚ የሚቀጥለውን መንፈሳዊ መዝሙር እጋብዛለሁ


http://uk.youtube.com/watch?v=9YxuNRQAc2c
በቅንነት ፈራጅ ሕዝብ እንዳይጐዳ:
ማን ይሆን ትልቅ ሰው ሃቅን የተረዳ :?:

Image
http://www.cyberethiopia.com/warka5/vie ... hp?t=26693
የጃማ ጦስኝ
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 338
Joined: Sun Sep 02, 2007 12:02 am
Location: ጃማ

Postby yodit » Sat Jan 17, 2009 10:17 am

ጃማ?? ሰምቼም አላወቅም አገራችን ተቆራርሳ ተሽጠች እያልን ስንል የገዛነውም አለ ይሆን እንዴ ያማላውቀው አገር ነው ይሄ ደሞ እስኪ የት እንዳለ አስረዱኝ ጉድ እኮ ነው
መልካም ቆይታ
yodit
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 360
Joined: Sat Oct 25, 2003 9:43 pm

ጀማ ወይስ ጃማ

Postby መራን » Sat Jan 17, 2009 1:05 pm

ጀማ መሰለኝ ለማለት የተፈለገው የጀማ ወንዝን የማያውቅ የአማራ ጠላት ነው አንሳሮ መሬ ወዘተ የጀማ ልጆች ናቸው
i just want comment new things
መራን
መንገደኛ
መንገደኛ
 
Posts: 5
Joined: Tue Jan 13, 2009 2:39 pm

Postby የጃማ ጦስኝ » Sat Jan 17, 2009 2:49 pm

ሰላም ዬዲት ሰላምታዬ ይድረስ

ሀገርን ለመገንጣጠል አይደለም አላማው ሁሉም በኢትዬጵያዊነቱ የማያምን ያለ አይመስለኝም :: ነገር ግን እያንዳንዳችን በተለያዬ አካባቢ መወለዳችን ደግሞ ሀቅ ነው
ስለዚህ የቤቱ ዓላማ ሀገር ለመገነጣጠል ወይም ችግር ለመፍጠር አይደለም ሳይሆን ባንድ አካባቢ በአንድ ት/ቤት የልጂነት ትዝታችንን ላሳለፍን እና በስራም ሆነ በተለያየ ምክንያት ከሀገርም ውጭ ወይም በሌላ ክ/ሀገር ላለን አብሮ አደጎች የመገናኛ ዘዴ ለመፍጠር ነው::

ሰለዚህ ሀገሪቱ ከኢትዬጵያ ውጭም አይደለችም ተገንጥላ የተሸጠችም አይደለችም::

አባባላህ/ሽ/ ክርክር ለመፍጠር እንዳይሆን አደራዬ የጠበቀ ነው
በቅንነት ፈራጅ ሕዝብ እንዳይጐዳ:
ማን ይሆን ትልቅ ሰው ሃቅን የተረዳ :?:

Image
http://www.cyberethiopia.com/warka5/vie ... hp?t=26693
የጃማ ጦስኝ
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 338
Joined: Sun Sep 02, 2007 12:02 am
Location: ጃማ

Postby ድርሰት » Mon Jan 19, 2009 12:44 pm

ስላም ለበቱ

እኔም እግር ጥሎኝ ዋርካው ስር ስቀመጥ የጃማ ልጆችን እይቼ ዱቅ አልኩታ ጥሩ መሆናቸውን ሰምቼ እንጂ ከዚያ ተወልጄ አዶለም

የጃማ ጦስኝ እባክዎ ቤቱን ሞቅ ሞቅ ያርጉት
There is always a small beginning for every thing that we should not despise!!!!!!!!!!!
ድርሰት
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 101
Joined: Mon Jan 19, 2004 6:16 pm
Location: united states

Postby የጃማ ጦስኝ » Mon Jan 19, 2009 4:45 pm

ሰላም ድርሰት እንኳን ደህና መጣህ :D በዋርካ ስር አንዳንድ ጊዜ አረፍ ማለትህ መልካም ነው ::
ታዲያ እንደስምህ እባክህን ድርሰትህንም ጣል ጣል አድርግልን::
እንዳልኩት ቤቷ የሰላም ቤት ናት ያለንን ሀሳብም ሆነ መልካም ነገር እኛን የሚጠቅመውን ሁሉ ጣል ጣል እንድታደርጉልን እናበረታታለን::
በቅንነት ፈራጅ ሕዝብ እንዳይጐዳ:
ማን ይሆን ትልቅ ሰው ሃቅን የተረዳ :?:

Image
http://www.cyberethiopia.com/warka5/vie ... hp?t=26693
የጃማ ጦስኝ
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 338
Joined: Sun Sep 02, 2007 12:02 am
Location: ጃማ

PreviousNext

Return to Warka Intimate - ዋርካ ፍቅር

Who is online

Users browsing this forum: No registered users and 2 guests