የጃማ ልጆች ካላችሁ

The Love Forum (love, relationship) (የኔ ቆንጆ እንተዋወቅ :-)

Postby የጃማ ጦስኝ » Wed Jun 23, 2010 6:34 pm

ለጃማ ጦስኝ ቤት ታዳሚዎቸ ሰላምታዬ ይድረሳችሁ::
እንዲሁም አዲሱ እንግዳዬ እንሳሮ እንኳን ደህና መጣህ!
ቤቱን ሞቅ ደመቅ ስላደረጋችሁት በጣም ደስ ብሎኛል::
ሾትል አንተ አለህ ወይ ባገሩ? ለመሆኑ የት እልም ብለህ ጠፍተህ ነው? ለነገሩ የኔም ጥያቄ ጅብ ክሄደ ውሻ ጮኸ ሆነ::
እስኪ አትጥፋ::
አንፈራራዬ እንደምን አለህ /ሽ/ መልካም ምኞትህን/ሽን/ደግሞም ጸሎትህ/ሽ/ አይለየኝ::
በተረፈ የቤቱ ዘበኛ የተጻፍትን እያየ እንዲያደንቅ እንጂ መልስ ለመስጠት ፈቃድ ገና ስላላገኘ እሱ የሚያደርገውን መኮረጅ በቤቱ ህግ ያስቀጣል::
አንድ ሲራራ ነጋዴ ወዳጂ ነበረኝ ! ባለሱቅ የሚባል ከስሮ ይሁን ትርፍ በዝቶበት አይታወቅም
ድምጹ ጠፋ::
ለገሂዳ ! በጣም ነው የማመሰግነው: ;
ስለትህን ለማድረስ ብቻህን እንዳትደክም ባይሆን አብረን እንጓዛለን :: ለማንኛውም ዘበኛው ቤቱን በደንብ መጠበቁን እየተከታተልክ አደራየ የጠበቀ ነው::

እህታችሁ የጃማ ጣስኝ
በቅንነት ፈራጅ ሕዝብ እንዳይጐዳ:
ማን ይሆን ትልቅ ሰው ሃቅን የተረዳ :?:

Image
http://www.cyberethiopia.com/warka5/vie ... hp?t=26693
የጃማ ጦስኝ
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 338
Joined: Sun Sep 02, 2007 12:02 am
Location: ጃማ

ለገሂዳ ተሾመ!!!

Postby ድርሰት » Thu Jun 24, 2010 11:12 am

እንክዋን ዴሰ ያለህ ወዳጀ ለገሂዳ!

ይህ ቤት አንድ ዘበኛ ነበረው በስራው የተመሰከረለት:: ትናንትና በወጣው አዋጅ አንተ ዘበኛውን እንድትቆጣጠር መሾምህን ሳነብ ደስ አለኝ:: ካያያዝህ ብዙ የስራ ልምድ ቢኖርህ ነው ይህ ዱብ እጣ የደረሰህ ደስ ይበልህ:: ግን ማንነው ለቀጣሪው አጃንሳ የክቡር ዘበኛ እንደነበርክ የነገረልህ እባክህ? ጥሩ ወዳጅ ነው ያገኘከው! ምናልባት ያ ማን ነው የሚሉት ወሬ አቀባይ ነው አሉ እሱ ሊሆን ይችላል:: ሾተል የሚባለው ሊሆን ይችላል:: እንደሱ አይነት ሰው ማስገባት ሲጀምሩ እኔም አብዮት አስነሳሁ:: ግን እሳቸው ገና አላወቁም::

በል ድህና ዋል ............... በአብዮታዊነት ምክንያት በስራ ቦታው ላይ (በዘበኝነት ላይ ያመጠ ወዳጅህ ነኝ)

ዴግ ዋልልኝ
There is always a small beginning for every thing that we should not despise!!!!!!!!!!!
ድርሰት
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 101
Joined: Mon Jan 19, 2004 6:16 pm
Location: united states

Re: በውሉ

Postby ውልጮ » Thu Jun 24, 2010 2:56 pm

የሚጠጣ ውሀ ስላነሳህብኝ
ትዝታ ተጭኖ ሆዴንም ቢብሰው
የሚከተለውን ልበለው ለዚህ ሰው
ጀማ(ዠማ) ወረዳዋን ካርታ ላይ ብታጣት
ዘመኑ ሲበላሽ ይሆን ሰርዘዋት
ወንዝን ጨምርና እስኪ አሁን ፈልጋት
ጊዜ ተላዋውጦ ቀን ቢጨልምባት
አትቀርም ተረስታ ዉለታ ብዙ ነች
ለጥቁር ነፃነት::

ወልዲያ wrote:ሠላም!Image
የሚጠጣ ውኃ ሳናገኝ በውሉ:
ከቶ ለምንድን ነው እንዲህ መብጠልጠሉ???

ጃማን ካርታ ላይ ማገኘት አልቻልኩም:
ሳል ሳል አድርገሽ አሳዪኝ በሠላም::


መልካም ሰንበት
ወልዲያ - የጁ
ውልጮ
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 361
Joined: Wed Feb 04, 2004 4:03 pm

Postby ባለሱቅ » Fri Jun 25, 2010 6:32 am

ሰላም ጃሚቲ
እንካን ለቤትሽ በቃሽ

ምን በሽታ በሽታ ብለሽ አስፈራሽኝ እኮ.. ቤትሽ ለመምጣት

እንዳይጋባብኝ

እኔ በሽታ ፈራለሁ ሙች
ቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅ

ሰላም ብያቹዋለሁ ለሁላቹም የዚህ ቤት ታዳሚዎች

ቺርስ ከጋና ጋር
ነገ አሜሪካን ቅጥትትትት እናደራለን ብለናል
ኢንሻላህ
ባለሱቅ
ውሃ አጠጪ
ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1288
Joined: Mon Sep 27, 2004 6:20 am
Location: ethiopia

Postby የጃማ ጦስኝ » Fri Jun 25, 2010 9:37 pm

ሰላም ለጃማ ቤት ታዳሚዎቸ እንደምን አላችሁ?

ባለሱቅ እንኳን ደህና መጣህ ! በጣም ገረምከኝ; እንዳይጋባብኝ?
ለመሆኑ የታመምኩት ካንተው ሱቅ በተገዛው ስኳር ነው መባሉን አልሰማህም?
ባለፈው ከኢትዮጵያ ስትመለስ ያስጫንከው ስኳር ከየት እንደሆነ ገና በምርመራ ላይ ነው :: እርግጠኛ ነኝ የመተሀራ አይደለም:: ከሀሰብ ከሆነ ችግር ላይ መውደቅህ ነው :: ምክንያቱም ፕሬዝዳንቱ ወደ እኛ የሚገባውን ማንኛውንም ነገር በሚያጠራጥር ሁኔታ እየመረዘው ነው ይባላል:: ለማንኛውም ; ሰውን ሲወዱ ከነንፍጡ ነው ይላል ያገሬ ሰው ; ስለዚህ ወደ ቤታችን የሚመጡ ሁሉ ያለመጠራጠር እንዲገቡ እናሳስባለን::
ለገሂዳ ወንድሜ አለህ ወይ ?
ምነው ሽታህ ጠፋ::

መልካም ሰንበት
እህታችሁ የጃማ ጦስኝ
በቅንነት ፈራጅ ሕዝብ እንዳይጐዳ:
ማን ይሆን ትልቅ ሰው ሃቅን የተረዳ :?:

Image
http://www.cyberethiopia.com/warka5/vie ... hp?t=26693
የጃማ ጦስኝ
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 338
Joined: Sun Sep 02, 2007 12:02 am
Location: ጃማ

Postby ለገሂዳ » Fri Jun 25, 2010 11:37 pm

ድርሰት:

እኔም ሹመቱን በድንገት ነው የሰማሁት:: የማመጽህን ጉዳይ በሚስጥር ብታትጫውተኝ መልካም ነበር:: ለማንኛውም ከእመቤትህ ቀጣሪዋ ላማልድህ እሞክራለሁ:: በስራህም አትለግም:: የእኔም የክቡር ዘበኛ ልምድ: የኮንጎና የኮሪያ ልምድ ይጠቅምሀል:: ከተስማማን:: ተግባባን::

የወልድያ ጠቀሱም ውልጮ:

የሚጠጣ ውሀ ጃማ ካጣ ሰው:
ተሰብሮ ይሆናል መያዣ አፎሌው:
ነጻነት ወዳድ ነው: ሕዝቡም ሰርቶ በላ:
ከወደደ አይጣላም: ከማለም መሀላ:
ከካርታ ካጣኸው: ከውስጥህ ፈለገው:
የጃማ መገኛ: ማደሪያው ልብ ነው::
ጃማ ጠፋች ብለህ: አትባዝን ፍለጋ:
ከልብ ተስላልች: እዚሁ ከእኛ ጋ::
ጊዜ ተለውጦ: ሊያጨልማት ቢሻ:
ጃማ ትወልዳለች: ለዚህም ማርከሻ::

ድርሰት:

እንግዲህ የሹመቴን እንኩዋን ደስ ያለህ ባይነት እጠብቃለሁ!

ባለሱቅንም በቤቱ ስላሰራጨው በሽታ የወጣበትን የእስር ማዘዣ ስራ ላይ ማዋልህን እንዳትረሳ:: በሳምንት ውስጥ ተይዞ ደጎሎ ፍርድ ቤት እንዲቅርብ አዘናል::
ለገሂዳ
አዲስ
አዲስ
 
Posts: 31
Joined: Fri Jan 25, 2008 1:41 am

Postby ባለሱቅ » Wed Jun 30, 2010 8:01 am

ባለሱቅንም በቤቱ ስላሰራጨው በሽታ የወጣበትን የእስር ማዘዣ ስራ ላይ ማዋልህን እንዳትረሳ :: በሳምንት ውስጥ ተይዞ ደጎሎ ፍርድ ቤት እንዲቅርብ አዘናል ::

ቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅ
እንዴት ነው ጃሚቲን ሰረቃት እንዴ ይሄ ሱቅ ሻጭ..... ለማሰር ተረባረባቹበት

ለምን ለኔ አትነግሩኝም... እንዲተውላቹ አስጠነቅቀዋለሁ... እንጂ ውዴን አትሰሩብኝ
በሽታና እስር አይወድም ባለሱቅ
ቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅ

ደህና ናቹ ግን ወጣቶቹ
ያገሬ ልጆች.. ጣፋጮቹ
በጃማ ውኃ ያደጋቹ
ካትክልቱ ስፍራ ከገባቹ
"ያንን" ተዉልኝ እባካቹ....
(ያንን እኔና እናንተ ብቻ ምናውቀውን ጣፋች ፍሬ)
አደራ
ተቀኝቼ ሞቻለሁ
ድንቄም እቴ አለች... ያይጦ እናት

ሰላም ሁኑልኝ...
ከፍቅር ጋር
ፊርማ የማይነበብ
ባለሱቅ
ውሃ አጠጪ
ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1288
Joined: Mon Sep 27, 2004 6:20 am
Location: ethiopia

Postby የጃማ ጦስኝ » Fri Jul 02, 2010 12:36 pm

ሰላም ለእናንተ ይሁን የጃማ ጦስኝ ቤት ታዳሚዎቸ::
ወይ ጉድ!
ደሞ ባለሱቅ ምን እያልክ ነው?
እንዲህ የፍቅር ጨው ጨምሬ በልቸ;
ትዝታው ገሎኛል ከሱቁ ገብቸ::ቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅ ገደለኝ ሸተተኝ አመሉ; ደሞ አገረሸብኝ;
ያን የወዬ ወተት ማነው የናጠብኝ;
ትቻለሁ ;ትቻለሁ; እኔ ቅቤ አልበላም ;
የወዬዎች ነገር አያስተማምንምምም ቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅ
ወገኖቸ ለጨዋታ ያህል ነው::
ባለሱቅዬ አለህ ? ጠፋህ እኮ :: ደሞ የምን ውሰዷት ነው
ዋ! አንዱ ወሎዬ እንዳይመነጥቅህ!ቅቅቅቅቅ
ለመሆኑ የት እየገባህ ነው አመጣጥህ ባመት የሆነው?

ለገሂዳ የት ነህ?
ጠፋህ እኮ የቤቱ ሀላፊነት ሙሉ በሙሉ ላንተ እንደተሰጠ እያወቅክ መጥፋትህ ተገቢ አይደለም::
አደራ ጠባቂ እንባዬን አብሶ;
እንዳንተ ያለ ሰው የሚያድነኝ ደርሶ;
አገኘሁኝ ብዬ አጥብቄ ስመካ;
ጥላህ ገሸሽ አይበል ያንተም እንደ; ዋርካ!!
እስኪ ሰላም ሁኑልኝ ::
መልካም ሰንበት በያላችሁበት::
እህታችሁ የጃማ ጦስኝ::
በቅንነት ፈራጅ ሕዝብ እንዳይጐዳ:
ማን ይሆን ትልቅ ሰው ሃቅን የተረዳ :?:

Image
http://www.cyberethiopia.com/warka5/vie ... hp?t=26693
የጃማ ጦስኝ
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 338
Joined: Sun Sep 02, 2007 12:02 am
Location: ጃማ

Postby ለገሂዳ » Thu Jul 08, 2010 11:19 pm

ሰላምታ ለጃማና ለቤቱ ታዳሚዎች:: ባለሙሉ ስልጣን የዘበኛ አለቃነት ሹመቴን በድንገት ባገኘው አንድም ሰው እንኩዋን ደስ ያለህ ያለኝ የለም:: ወዳጄ ዘበኛው እንኩዋ ችል ብሎኛል:: የጃሞም የሰው ወሬ አትስሚ ስለእንባ ጠባቂነቴ::

እንባሽን አልሻም አንዲትም ጠብታ
ሁልዬም አለሁኝ ጡዋትም ሆነ ማታ
ዘበኛ ሲጠብ ዝናሩን ሳይፈታ
በአለቃነቴ ባለብኝ አደራ
አንቺ ጋ ነኝ 'ኔ ምንም ሌላ አልሰራ
ለገሂዳ
አዲስ
አዲስ
 
Posts: 31
Joined: Fri Jan 25, 2008 1:41 am

Postby የጃማ ጦስኝ » Sun Jul 11, 2010 12:41 am

ሰላም የጃማ ጦስኝ ቤት ታዳሚዎቸ
ለገሂዳ እመለሳለሁ ድንገት የሆነ ጉዳይ ገጥሞኝን ነው::
ሾተልን የበላው አልታወቀም ?
በቅንነት ፈራጅ ሕዝብ እንዳይጐዳ:
ማን ይሆን ትልቅ ሰው ሃቅን የተረዳ :?:

Image
http://www.cyberethiopia.com/warka5/vie ... hp?t=26693
የጃማ ጦስኝ
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 338
Joined: Sun Sep 02, 2007 12:02 am
Location: ጃማ

Postby የጃማ ጦስኝ » Sun Jul 11, 2010 1:02 am

አንድ ነገር ከጎረቤት ልሰርቅ ሄጀ ነው::
የሰረቅኩትም ለሁላችንም የሚጠቅም ስለሆነ ነው::
htt://www.youtube.com/watch?v=c3AalquW5a0
ለጥልዬ ነፍስ ይማር እያልን:-
እኔም እንዲህ አሰኘኝ:-

ምድርና ሰማይን የሰራህ ፈጣሪ;
የዘላለም ንጉስ የሁሉ አሳዳር;
ኪሩቤል ለክብርህ የሚንቀጠቀጡ;
እልፍ አዕላፍ መላዕክት ምስጋና የሚያመጡ;
ከእሳተ ገሞራ ግርማህ የሚያስፈራ;
ከብዙ ውሗች ድምጽ ይልቅ ድምጽህ የሚያስፈራ;
ምን ዓይነት መሐጸን አንተን ተሸከመች!!!!!!!!!!!!!
በምንስ ልግለጽህ ለሰው እንዲገባው ለሰሚስ እንዲመች????

ልጄ ብሎ አቀፈኝ ሳለሁ በደለኛ!!
የዋለው ውለታ አለኝ አላስተኛ
የዋለው ውለታ አለኝ አላስተኝኝኝኝኝኝኝኝኝኝኝኝኛ
መልካም ሰንበት ለሁላችንም

እህታችሁ የጃማ ጦስኝ
በቅንነት ፈራጅ ሕዝብ እንዳይጐዳ:
ማን ይሆን ትልቅ ሰው ሃቅን የተረዳ :?:

Image
http://www.cyberethiopia.com/warka5/vie ... hp?t=26693
የጃማ ጦስኝ
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 338
Joined: Sun Sep 02, 2007 12:02 am
Location: ጃማ

Postby የጃማ ጦስኝ » Sun Jul 11, 2010 1:09 am

ይቅርታ:- የሌባ ነገር አንዱን ጥሎ አንዱን አንጠልጥሎ ነንዲሉ; ያሰብኩትን ሳላነሳ ባለሱቅ ደርሶብኝ ሳመልጥ ነው ያሰብኩትን ያላገኘሁት:ቅቅቅቅቅ
http:/www.youtube.com/watch?v=c3AaIquW5a0
በቅንነት ፈራጅ ሕዝብ እንዳይጐዳ:
ማን ይሆን ትልቅ ሰው ሃቅን የተረዳ :?:

Image
http://www.cyberethiopia.com/warka5/vie ... hp?t=26693
የጃማ ጦስኝ
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 338
Joined: Sun Sep 02, 2007 12:02 am
Location: ጃማ

Postby ለገሂዳ » Sun Jul 11, 2010 11:08 pm

ጃማ: በዘበኛ አለቃነቴ ሀላፊነት ሰላለብኝ የስርቆቱ ነገር አሳሳቢ ነው:: ደግሞ ያ ዘበኛው ሰምዎትን በማጥፋት ሊጠቀም ይችላል:: [/url][/code]
ለገሂዳ
አዲስ
አዲስ
 
Posts: 31
Joined: Fri Jan 25, 2008 1:41 am

Postby ድርሰት » Mon Jul 12, 2010 9:48 am

ወይ አንተ ..........................
There is always a small beginning for every thing that we should not despise!!!!!!!!!!!
ድርሰት
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 101
Joined: Mon Jan 19, 2004 6:16 pm
Location: united states

Postby ለገሂዳ » Tue Jul 13, 2010 12:32 am

ድርሰት - አዎ እንዳልከው ሁሉም ነገር ቸል ብለን ልናልፈው የማይገባ መጀመሪያ አለውና በስራህ ላይ ያገኘከው መረጃ ካለ ትንሽ ነው ብለህ ሳትንቅ ሪፖርት እንዲታደርግ ይሁን::

የዘበኛ አለቃ ቢሮ
ለገሂዳ
አዲስ
አዲስ
 
Posts: 31
Joined: Fri Jan 25, 2008 1:41 am

PreviousNext

Return to Warka Intimate - ዋርካ ፍቅር

Who is online

Users browsing this forum: No registered users and 7 guests