የጃማ ልጆች ካላችሁ

The Love Forum (love, relationship) (የኔ ቆንጆ እንተዋወቅ :-)

Postby ባለሱቅ » Wed Sep 15, 2010 10:09 pm

ጃሚቲ
የጃማዋ
እና የዚህ ቤት ደንበኞች
እንኳን ለ2003 በሰላም አደረሳቹ
አዲሱ አመት የሰላም የፍቅር የመተሳሰብ ይሁንላቹ
እንደገናም ለሚቀጥለው አዲስ አመት በሰላም ያድርሳቹ
ወጨቱ ይሙላ
ፍየሉ ይርከስ
ዶሮ ግቢአቹን ይሙላ

መጥተናል ባመቱ
እንደምን ሰነበቱ
እየተባለ ሁሌም ይዘፈንላቹ
ሰላም
ፍቅር
እምነት
ያብዛላቹ የአዲሱ አመት ጌታ

ሰላምምምምምምምምም
ባለሱቅ
ውሃ አጠጪ
ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1288
Joined: Mon Sep 27, 2004 6:20 am
Location: ethiopia

Postby ናይክ » Thu Sep 16, 2010 3:37 am

ከመስመር ወጣህ አትበሉኝእና...........

ጂማ ለመሆኑ የታካባቢ ነው.....??አክባሪያቹህ!!
Senef Gebere Be sene yemotal !!!!
ናይክ
አዲስ
አዲስ
 
Posts: 34
Joined: Thu Sep 23, 2004 6:11 pm
Location: united states

Postby የጃማ ጦስኝ » Thu Sep 16, 2010 5:06 pm

ናይክ wrote:ከመስመር ወጣህ አትበሉኝእና...........

ጂማ ለመሆኑ የታካባቢ ነው.....??አክባሪያቹህ!!


ሰላም ለጃማ ጦስኝ ቤት ታዛቢዎችም ታዳሚዎችም

የሰው ዘር መፍለቂያ የስልጣኔ ፍንጭ;
የክብር ዘውድ ያላት:- የጥቁር ኩራት ምንጭ;
ውበቷ እየሳበ ሁሉ የሚመኛት;
የደመናው ግርማ የፀሃይዋ ሙቀት;
የቡቃያው ተስፋ የዝናቡም ጥምቀት;
የአበቦቹም ጠረን ባየር የሚናኘው;
ጃማ ስትኖር ነው ትርጉም የሚያገኘው::ቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅ

ሰላም ናይክ እንኳን ደህና መጣህ/ሽ
ማንም ከመስመር ወጣህ አይልም ::ያላወቁትን መጠየቅ ብልህነት እንጂ አጉራ ዘለልነት አይደለም :: ለማንኛውም ጃማ በሰሜን ሸዋ እና በደቡብ ወሎ መሀል የምትገኝ; ሁሉንም የእህል አይነት የምታበቅልና የአየሯም ፀባይ ወይና ደጋ ሲሆን ሕዝቧም ትሁት; በጣም ደግና እንግዳ ተቀባይ ነው:: የቁንጅናቸውንም ነገር ጎረቤት ብትጠይቅ ከእኔ ይልቅ የበለጠ መረጃ ታገኛለህ/ሽ :: ለዚሁም የቅርብ ወዳጃችን ባለሱቅ ለመረጃው ይቅርባል::

ባለሱቅ በጣም ነው ደስ ያለኝ ሳይህ:: በቃ አንተ የቅዱስ ዮሐንስ ቀን ብቻ ነው ሰው ትዝ የሚልህ?
ለመሆኑ አለህ?
እጂሽ አመድ አፋሽ መቼስ ምን ታደርጊ;
እስቲ ወደ እግዚአብሔር እጆችሽን ዘርጊ::
እንዳትለኝ ብቻ ይኸን እፈራለሁ;
ሁል ጊዜ እንቁጣጣሽ ;ሁል ጊዜ ደስታ እመኝልሀለሁ::
እንዳንተ ያለ ወዳጂ መቸም የሚግኘው ከሩቅ ነው ከራያ
ጠላት ግን ከብብት ይፈላል ከጉያ ቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅ

ሰላም የምመኝላችሁ የጃማ ጦስኝ
በቅንነት ፈራጅ ሕዝብ እንዳይጐዳ:
ማን ይሆን ትልቅ ሰው ሃቅን የተረዳ :?:

Image
http://www.cyberethiopia.com/warka5/vie ... hp?t=26693
የጃማ ጦስኝ
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 338
Joined: Sun Sep 02, 2007 12:02 am
Location: ጃማ

Postby የጃማ ጦስኝ » Wed Sep 22, 2010 12:31 am

ሰላም ለጃማ ጦስኝ ቤት ታዳሚዎች እንደምን አላችሁ::
ሰሞኑን በተለያዬ ሳይቶች ስለ ነብዩ ሙሴና ህዝቡን ከግብፅ ምድር ስላወጣበት ተዓምር ሲናገሩ:- በዘመኑ በነበረ ሀይለኛ ነፋስ እንጂ የእግዚአብሔር ክንድ እንዳልነበረ ለማስተባበል ያላሰለሰ ጥረት እያደረጉ ሳይ በእውነትም በጣም;በጣም ያለቀ ጊዜ ላይ አለን:: ለመሆኑ የነፋስስ ሀይል የማን ይሆን?መቸስ ነው የስው ልጅ ከአምላክ ጋር የሚታረቀው?
https://www2.ucar.edu/news/parting-wate ... cape-route
htt://www.plosone.org/article/info%3Adoi%2Flo.1371%Fjournal.pone.0012481
በቅንነት ፈራጅ ሕዝብ እንዳይጐዳ:
ማን ይሆን ትልቅ ሰው ሃቅን የተረዳ :?:

Image
http://www.cyberethiopia.com/warka5/vie ... hp?t=26693
የጃማ ጦስኝ
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 338
Joined: Sun Sep 02, 2007 12:02 am
Location: ጃማ

Postby የጃማ ጦስኝ » Mon Sep 27, 2010 12:17 am

እንኳን ለብርሃነ መስቀሉ በሰላም አደረሳችሁ!!!

ግማደ መስቀሉ:-
በዐፄ ዳዊት ዘመነ መንግስት የገባው ግማደ መስቀል:
በታላቁ ቆስጠንጢኖስ እናት እሌኒ ንግሥት የተባለች ደግ ሴት የጌታችንን እና የመድሃኒታችንን መስቀል መስከረም 17 ቀን በ320ዓ.ም በእጣን ጢስ ምልክት ቁፋሮ አስጀምራ መጋቢተ 10 ቀን አግኝታ በማስወጣት ታላቅ ቤተ መቅደስ ጎልጎታ ላይ አሰርታ በክብር አስቀመጠችው:: ይህ መስቀልም ከዚያ እዕለት ጀምሮ እንዴ ፀሐይ እያበራ; ድውይ እየፈወሰ; አጋንንትን እያባረረ; ልዩ ልዩ ተአምራትን እየሰራ ሙት እያስነሳ; እውራንን እያበራ; ተአምራቱን ቀጠለ::
ይህንን ያየው የፋርስ መንግስት መስቀሉን ማርኮ ፋርስ ወስዶ አስቀመጠው:: በዚህን ጊዜ የኢየሩሳሌም ምእመናን የሮማው ንጉስ ሕርቃንን እርዳታ በመጠየቅ እንዲመለስ አድርገው በኢየሩሳሌም ብዙ ዘመን ሲኖር እንደገና ኃያላን ነገሥታት ይኽን መስቀል እኔ እወስድ እኔ እወስድ እያሉ ጦርነት ፈጠሩ; በዚህን ጊዜ የኢየሩሳሌም; የቁስጥንጥንያ;የአንጾክያ; የኦፌሶን; የአርመኒያ; የግሪክ;የእስክንድርያ የሃይማኖት መሪዎች በሽምግልና ጠቡን አበረዱት ከዚህም አያይዘው ኢየሩሳሌም የሚገኘውን የክርስቶስን መስቀል ለ4 ከፍለው በዕጣ አድርገው በስምምነት ተካፈሉ:: ከሌሎች ንዋዬ ቅድሳት ጋር በየአገራቸው ወስደው በክብር አስቀመጡት:: የቀኝ እጁ የተቸነከረበት የደረሰው ለአፍሪካ ሲሆን ከታሪካዊ ቅድሳት ጋር በግብጽ የሚገኘው የእስክንድርያ ፓትርያርክ
ተረክቦ ወስዶ በክብር አስቀመጠው::ይህ ግማደ መስቀል
ለብዙ ዘመን በእስክንድርያ ሲኖር በዐፄ ዳዊት ዘመን ወደ ኢትዮጵያ ገብቷል:: ስለዚህ ግማደ መስቀል ወደ ኢትዮጵያ መግባት ሁለት ዓይነት የተለያዩ የታሪክ ምንጮች አሉን::
1. ይህ ግማደ መስቀል ለብዙ ዘመን በእስክንድርያ ሲኖር በግብፅ እስላሞች እየበዙ ኃይላቸው እየጠነከረ ሔደ:: ከእስክንድርያም የሚኖሩ ክርስቲያኖች ለመስቀል አትስገዱ የክርስትናን እምነት አጥፉ ግብር ክፈሉ እያሉ እስላሞች አገዛዝ አጸኑባቸው:: በግብጽ የሚኖሩ ክርስቲያኖችም ስለሚድርስባቸው ግፍ አንድ ሆነው መክረው ለኢትጵያ ንጉሥ ለዳግማዊ ዐፄ ዳዊት እንዲህ የሚል መለዕክት ላኩበት:- ""ንጉሥ ሆይ በዚህ በግብጽ ያሉ እስላሞች ለክርስቶስ መስቀል ክብር አትስጡ ክርስትናን አጥፉ ግብር ክፈሉ እያሉ መከራ እያጸኑብን ስለሆነ 10ሽህ ወቄት ወርቅ እንሰጥሀለን አስታግስልን"" ብለው ጠየቁት:: በዚህ መሰረት ዐፄ ዳዊት ለሃይማኖቱ ቀንቶ 20ሺ ሠራዊት አስከትሎ ወደ ግብጽ ለመዝመት ሲዘጋጅ በሌላ በኩል ደግሞ የአባይን ወንዝ ለመገደብ ሙከራ ያደርግ ጀመር:: በዚህ ጊዜ በግብጽ ያሉ እስላሞች ፈሩ:: ከዚህ የተነሳ በግብጽ ያሉ እስላሞች በግብጻዊያን ክርስቲያኖች ላይ ያደርሱት የነበረውን ግፍና መከራ ወዲያው አቆሙ::
የግብጽ ክርስቲያኖችም በዚህ ተደስተው 12ሺ ወቄት ወርቅ
ለዳግማዊት ዳዊት ላኩላቸው:: ንጉሡም መልሰው ""እንኳን ደስ ያላችሁ የላካችሁትን ወርቅ ልኬአለሁ የእኔ አላማ ወርቅ ፍለጋ አይደለም የክርስቶስ ፍቅር አስገድዶኝ በተቻለኝ መጠን ችግራችሁን አስወግጃለሁ አሁን የምለምናችሁ በአገሬ ኢትዩጵያ ረሀብ ;ቸነፈር; ድርቅ ስለወረደብኝ መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ተሰቅሎበት የነበረውን መስቀልና የቅዱሳንን አፅም ከሌሎች ነዋየ ቅድሳት ጋር ለበረከት እንድትልኩልኝ"" ብለው ላኩባቸው::
እስክንድርያ ያሉ ምዕመናን ይህ መልእክት እንደደረሳቸው ከሊቃነ ጳጳሳቱና ከኤጲስ ቆጶሳቱ ጋር ውይይት በማድረግ ይህ ንጉስ ታላቅ ክርስቲያን ነው::
ስለዚህ ልቡ ደስ እንዲለው የፈለገውን የጌታችንን ግማደ መስቀል ከቅዱሳኑ አፅምና ከንዋየ ቅድሳቱ ጋር አሁን በመለሰው 12 ወቄት ወርቅ የብርና የነሀስ የወርቅ ሳጥን አዘጋጅተን እንላክለት ብለው ትስማምተው በክብር በሥነ ሥርዓት በሰረገላ በግመል አስጭነው ስናር ድረስ አምጥተው በአስረከቧቸው ጊዜ እያሸበሸቡ በግንባራቸው እየሰገዱ በክብር በደስታ ተቀበሏቸው:: ይህ የሆነው መስከረም 21 ነው::
ይቀጥላል
በቅንነት ፈራጅ ሕዝብ እንዳይጐዳ:
ማን ይሆን ትልቅ ሰው ሃቅን የተረዳ :?:

Image
http://www.cyberethiopia.com/warka5/vie ... hp?t=26693
የጃማ ጦስኝ
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 338
Joined: Sun Sep 02, 2007 12:02 am
Location: ጃማ

Postby menzewu » Mon Sep 27, 2010 1:41 am

እንዴ እኔ እኮ ስለ ጂማ ከፋ የሚወራ መስሎኝ ነፍጠኛ መጣ ብላችሁ እንዳትደነግጡ ብየ ዝም ብያለሁ!! ለካ ስለጃማ መርሀቤቴ ነው ጫወታው!! እንግዲያማ

የናቴ አገር ገርን. እንሳሮ ያባቴ. የኔ መርሀቤቴ
ዠማ ተጣጥቤ ልገባ ነው ቤቴ

ተብሉአልና እስኪ የጫወታ ምንሽሩን አቀባብሉት. እንደ እዉነት ለመናገር ግን መርሀቤቴን ከኮላሽ እስከ ፌጥራ ከእንሳሮ እስከ ደራና ሚዳ አውቃለሁ የምል ሰው ጃማን አላውቅም... ቢጣቢለው ወረዳ ውስጥ መሆኑ ነው...ወደ ጀጎሎ? ለማንኛውም እስኪ ወደ ወንጭት ብቅ በሉና እናውጋ
menzewu
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 377
Joined: Fri Dec 25, 2009 4:40 am

Postby menzewu » Mon Sep 27, 2010 1:56 am

በሉ ተውት በቤቱ የተጻፈውን መልሼ ሳነበው ግጥም, ጸሎት, ሰላም ፍቅር ምናም ን ልስልስ ነገር የበዛበታል.

ዘሀርመስጌን! መሬ እንዲህ ያለ ነገር የለም . ጃማ ወሎ መሆን አለበት
menzewu
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 377
Joined: Fri Dec 25, 2009 4:40 am

Postby የጃማ ጦስኝ » Wed Oct 06, 2010 9:46 pm

ሰላም ለጃማ ጦስኝ ቤት ታዳሚዎቸ::
መንዜው እንኳን ደህና መጣህ/ሽ ::
ቤቱ የፍቅር እና የሰላም የፀሎት እንዲሁም የመንፈሳዊ ግጥሞች ስብስብ የሚቀርብበት ነው::
ከዚህ ውጭ ምንም ነገር አናቀርብም:: ቤቷን ስለጎበኘሃት/ሻት ከልብ ምስጋናዬን አቀርባለሁ::

እህታችሁ የጃማ ጦስኝ
በቅንነት ፈራጅ ሕዝብ እንዳይጐዳ:
ማን ይሆን ትልቅ ሰው ሃቅን የተረዳ :?:

Image
http://www.cyberethiopia.com/warka5/vie ... hp?t=26693
የጃማ ጦስኝ
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 338
Joined: Sun Sep 02, 2007 12:02 am
Location: ጃማ

Postby የጃማ ጦስኝ » Mon Oct 18, 2010 1:09 pm

ሰላም ለጃማ ጦስኝ ቤት እንደምን አላችሁ?
ተጠፋፋን::
ብቅ እላለሁ::
እናንተም አትጥፉ::
በቅንነት ፈራጅ ሕዝብ እንዳይጐዳ:
ማን ይሆን ትልቅ ሰው ሃቅን የተረዳ :?:

Image
http://www.cyberethiopia.com/warka5/vie ... hp?t=26693
የጃማ ጦስኝ
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 338
Joined: Sun Sep 02, 2007 12:02 am
Location: ጃማ

Postby የጃማ ጦስኝ » Sun Oct 31, 2010 11:59 pm

በስማም እንዴት የሚያስደነግጥ ነበር!!

ሕግ ያግድውውውውውውውውውውውውው
ወንድማማቾቹ አዋሽና አባይ;
ሁለቱም አኩራፊ ተበደልኩ ባይ;
በተለይም አባይ ቅጥ ስላጣ ስድቡ;
አዋሽ ገራገሩ አምርሮ ከልቡ;
ፍርድ ለመጠየቅ ከዳኛ ቀረቡ!!
አዋሽ ሽቁጥቁጡ ምንም ሳይኩራራ;
ፍትህን ልማግኘት ወደ ዳኛ አመራ;;

ይቀጥላል:-
እንኳን ደስስስስስስስስስስስ
አለን::
በቅንነት ፈራጅ ሕዝብ እንዳይጐዳ:
ማን ይሆን ትልቅ ሰው ሃቅን የተረዳ :?:

Image
http://www.cyberethiopia.com/warka5/vie ... hp?t=26693
የጃማ ጦስኝ
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 338
Joined: Sun Sep 02, 2007 12:02 am
Location: ጃማ

Postby ባለሱቅ » Wed Nov 10, 2010 5:07 pm

ሰላም ጃሚቲ
እንደምን አለሽልኝ ቆንጅት

ስራ በዛና.... ጊዜ ጠፋና

ቤትሽ መጥቼ አላውቅም

ሙሽሪትም ሺሻ መሸጥ አቆመች

እስኪ ቅጠሪኝ ስራ ካለሽ አንቺ ቤት
የቤት ኪራይ መክፈል አቃተኝ እኮ

ሰላምታዬ ይድረስሽ በጅምላ እና ችርቻሮ
ቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅ
ባለሱቅ
ውሃ አጠጪ
ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1288
Joined: Mon Sep 27, 2004 6:20 am
Location: ethiopia

Postby የጃማ ጦስኝ » Wed Nov 17, 2010 10:48 pm

ሰላም የጃማ ጦስኝ ቤት ታዳሚዎቸ እንደምን ከረማችሁ::
ባለ ሱቅዬ እንኳን ደህና ምጣህ!!
ድሮስ ሙሽሪት አሳምራ እንደማትካድምህ አስቀድሜ ነግሬህ አልንበረም?
ለማንኛውም ጊዜ የማይለውጠው የለም ጊዜ ስጣት::
እስኪ ካነበብኩት ትንሽ ላካፍላችሁ:-

ምጥ!

ሰማይ ምድርን ሰርቶ አጠናቀቀና;
አፈር ስላገኘ;
እስትንፋሱን እፍ ሲልበት;
አዳም ከውስጡ ተገኘ::
ያዳምን ጎድን በመበርበር;
ሔዋንን ፈጠረ;
ምጥ የተባለው አበሳ ያኔ ተጀመረ::
የሰው ልጅ ቢደሰት ምንም ቢደላደል;
ማሰብ መጨነቁ መጠበቡ አይቀር::
ደራሲው ምናቡን ;ቋንቋና ታሪኩን;
ሼኩ ቄሳውስቱ ዝማሬ ፀሎቱን;
ነጋዴውም ትርፉን ሴቷም ዘጠኝ ወሯን;
እንዳረጋገዛቸው;
እንደቢጠታቸው:
ዑደቱን ጠብቀው ሁሉም ያምጣሉ;
ወይም በዝምታ ወይ እያቃሰቱ::
የሰው ዘር ያራዊት;
የእንስሳ ሠራዊት;
ዛሬ የበላውን
የቀበተተውን;
እህ!! ሲል የሆዱን;
አንጀቱን በመጭመቅ......
ፊቱን በመከስከስ.....
አጎንብሶ ያምጣል ዘርግፎት ሊያበቃ;
ደግሞ ነገ አለና ስለሚያሻን እቃ:::::::::::

ይቀጥላል>>>>>>>>>>>

እህታችሁ የጃማ ጦስኝ
በቅንነት ፈራጅ ሕዝብ እንዳይጐዳ:
ማን ይሆን ትልቅ ሰው ሃቅን የተረዳ :?:

Image
http://www.cyberethiopia.com/warka5/vie ... hp?t=26693
የጃማ ጦስኝ
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 338
Joined: Sun Sep 02, 2007 12:02 am
Location: ጃማ

Postby የጃማ ጦስኝ » Wed Dec 15, 2010 4:48 pm

ሰላም ለጃማ ጦስኝ ቤት ታዳሚዎቸ; አንባቢዎቸና ወዳጅ ዘመዶቸ በሙሉ ሰላምታዬ በያላችሁበት ይድረሳችሁ::
ለቤቷ ያላችሁን ፍቅር ሳይ ልቤ የሚንካውን ያህል : ትንሽም አዝኛለሁ::
ቤቷን ከገጽ ገጽ እየፈለጋችሁ እንደምታነቧት ሁሉ ግን ተሽቀንጥራ ስትጠፋ ጎትታችሁ ባለማምጣታችሁ ታዘብኳችሁ::
ለመሆኑ ;_ ባለሱቅ ባገር አለህ?
ሾትልስ በደህና ነው?
ሌሎቻችሁስ?
እህታችሁ የጃማ ጦስኝ
በቅንነት ፈራጅ ሕዝብ እንዳይጐዳ:
ማን ይሆን ትልቅ ሰው ሃቅን የተረዳ :?:

Image
http://www.cyberethiopia.com/warka5/vie ... hp?t=26693
የጃማ ጦስኝ
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 338
Joined: Sun Sep 02, 2007 12:02 am
Location: ጃማ

Postby ባለሱቅ » Thu Dec 16, 2010 6:57 pm

ጃሚቲ
አቤትትትትትትትትት ለወቀሳ አቸኳኮልሽሽሽሽሽ
ሰው ታሞ ልሂን ይችላል
ዘመድ ሞቶበት ሊሆን ይችላል
ከፈተና ወድቆ ሊሆን ይችላል
ፍቅረኛው ዳምፕ አድርጋው ሊሆን ይችላል
የቤት ኪራይ ኮሮንቲ ስልክና ውሀ ናላውኝ አጡዘውት ሊሆን ይችላል
ባገናት በሁለተኛው ቀን አረገዝኩ ብላው ሊሆን ይችላል
የስደተኛነት ጥያቄው ፍቃድ ተከልክሎ ይሆናል
ሰፈራቸው ያለው ኢንተርኔት ካፌ ከስሮ ተዘግቶ ልሆን ይችላል
ያለው አንድ እግር ካልሲ ጠፍቶበት ሊሆን ይችላል
የሆነ ነገር ገጥሞት ሊሆን ይችላል....
አይባልም?
ዝም ብሎ ወቀሳ አለ?
ህምምምምምምምምምምምም
ታዘብኩሽ ቂጤ አለ... ሳያስበው ፈሳና.... መለስ ዜናዊ.. ፓርላማ ውስጥ.............

ደህና ነሽ ዎይ ግን አንቺ ቆጆ ልጅ
አዲሳባ አትመጪም ወይ... እንገናኝማ እንወያይ... ስለዚች ቤት
ለገና ሸገር ነኝ ብያለሁ አላህ ከፈቀደ
አንቺስ እና ያንቺ ቤት ታዳሚዎች የት ናቹ
ሸገር ጫት ተራ እንገናኝ... ለገና
ዮሀንስ ካዛንቺስ.... ጫት ተራ
በለጬን ይዘን እንፈርሻለን.... ሪንግ ሮዱ ላይ

የዛ ሰው ይበለን
ባለሱቅ
ውሃ አጠጪ
ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1288
Joined: Mon Sep 27, 2004 6:20 am
Location: ethiopia

Postby የጃማ ጦስኝ » Fri Dec 17, 2010 12:35 am

ሰላም ለጃማ ጦስኝ ቤት ታዳሚዎቸ በሙሉ!!

htt://www.ethiotube.net/video/11907/Rom ... dent-Yamal

ያማል??

ሽህ ጊዜ ቢያሳምም ባይመችም ዓለም;
ተፈጥሮን መሳደብ የሚገባ አይደለም::

ጨረቃም የለችም?? ሆሆይይይይይይ
ምን ጊዜ ናፈቅካት ደግሞ በደቂቃ?
አይይይይ
ያንተ ነገር ለዚችው ነው በቃ?
ምነው በቀመስከው ፍቅርን በጨረቃ:: ቂቂቂቅ

እና እንደነገርኩሽሽሽ?

ምንም አትንገረኝ አልሰማህም በቃ!
ፍቅርህን ለመግለጽ ምንድናት ጨረቃ?
ይኸን ሁሉ ምሬት ውስጥህ ከተሞላ;
አይመስለኝም ልብህ ለፍቅር የሚላላ::
እናማ ነገርኩህ !
አበባህ ይጠውልግ ይድረቅ እንደቅጠል;
ተፈጥሮን ሰድበሀል;
ስለማትሆነኝ ልብህ አይንጠልጠል::
አበቃ ነገርኩህ አርቲ ቡርቲ አታብዛ;
ፍቅር በፍቅር እንጂ በቀል አይገዛ::ቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅ
ገደለኝ ይኸ ልጅ ከሰማ ጉዴ ነው::

ባለሱቅዬ የኔ ወዳጅ የት ጠፍተህብኝ ነው እንዲህ ኡ ኡ ኡ
እስከምል የምትጠብቀው?
በቅንነት ፈራጅ ሕዝብ እንዳይጐዳ:
ማን ይሆን ትልቅ ሰው ሃቅን የተረዳ :?:

Image
http://www.cyberethiopia.com/warka5/vie ... hp?t=26693
የጃማ ጦስኝ
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 338
Joined: Sun Sep 02, 2007 12:02 am
Location: ጃማ

PreviousNext

Return to Warka Intimate - ዋርካ ፍቅር

Who is online

Users browsing this forum: Bing [Bot] and 1 guest