የጃማ ልጆች ካላችሁ

The Love Forum (love, relationship) (የኔ ቆንጆ እንተዋወቅ :-)

Postby የጃማ ጦስኝ » Mon Dec 20, 2010 12:48 am

ሰላም የጃማ ጦስኝ ቤት ታዳሚዎቸ::
መቸም ዓመት በዓል ሲቃረብ ሽር ጉዱ መከራ ነው:: የስጦታ እቃ ለመግዛት የሚደረገው ውጣ ውረድ ከሱቅ ሱቅ መንከራተቱ አይጣል:: እኛማ እጥፍ እጥፍ ዓመት በዓል ነው የምናከብረው::
እኔም ለእናንተ ለወዳጆቸ የማቀረበውን ስጦታ ለማቅረብ ከሱቅ ሱቅ ተንከራትቸ በስንት መከራ ትሆናለች ያልኳትን ሽምቸላችሁ ብቅ:-
ልጂቷ ከቻይና ጓደኛዋ አርግዛ ትወልዳለች:: የተፍለቀለቀችው ድንቡሽቡሽ ከአንድ ዓመት በኋላ በጠና ትታመምና ሳትድንላት ቀርታ ሞተቸባት ::
አንጀቷ የተቃጠለው እናት :- ልጄ ልጄ ልጄ; እኔ እኮ ገና ስትረገዢ አውቄዋለሁ እንደማታድጊልኝ አውቄዋልሁ እያለች አብዝታ ስታለቅስ ግራ የገባቸው ወዳጅ ዘመዶች እንዴ እንዴት አርገሽ ነው ገና ስታረግዥ እንደማታድግ ያወቅሽው? ቢሏት :-
ምን ድሮስ የቻይና እቃ ለጊዜው ነው እንጅ መች ይበረክታል :: ብላ እርፍ::

በሉ ቸር ይግጠመን::
እህታችሁ የጃማ ጦስኝ
በቅንነት ፈራጅ ሕዝብ እንዳይጐዳ:
ማን ይሆን ትልቅ ሰው ሃቅን የተረዳ :?:

Image
http://www.cyberethiopia.com/warka5/vie ... hp?t=26693
የጃማ ጦስኝ
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 338
Joined: Sun Sep 02, 2007 12:02 am
Location: ጃማ

Postby ባለሱቅ » Mon Dec 20, 2010 9:19 pm

ምን ድሮስ የቻይና እቃ ለጊዜው ነው እንጅ መች ይበረክታል ::

ኡ ኡ ኡ ኡ
በሳቅ ነው የገደለኝ ይሄ ቀልድች
በቃ የቻይና ሴት/እቃ እዲህ ኖኖ ቀር እማለት ነው
ቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅ
አደራ ነገር እንዳታጣምሚ.... ስለምወድሽ ነው እንደመጣልኝ ምዘባርቀው..............
እንደጋዘጠኛ
ነገረኛ
መሆን ስለማልችል
ብቻ ነው
ባለሱቅ
ውሃ አጠጪ
ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1288
Joined: Mon Sep 27, 2004 6:20 am
Location: ethiopia

Postby የጃማ ጦስኝ » Tue Dec 21, 2010 1:21 am

ቅቅቅቅቅቅቅቅቅ
እንኳንም እንደፈለክ ሆንክ ደሞ በእህትህ ቤት ምን አስጨነቀህ::

ሌላው ጉጉ ደሞ ;ከጓደኛው ጋር ምግብ ሊበሉ ይገቡና አዘው እስከሚመጣላቸው እየጠበቁ እያለ ;ፊት ለፊታቸው ሌሎች ጥሬ ሥጋ እዬበሉ ሲያይ በአምሮት ፍጥጥ ብሎ ሲመለከት ጥሬ ሥጋ ጎራሹ ወሬ ይዞ በትልቁ የጎረደውን ሊጎርስ ሲል ይከታተለው የነበረው ሰው አዋዜውን እረሳህ ብሎት እርፍ:: አሁንም አንተ ፍሬ ነገሩን ብትረሳውም አስቀኽኛል እንደ ባለ አዋዜው ቅቅቅ
ገደልከኝ
እህታችሁ የጃማ ጦስኝ
ግን መሄድህን ስሰማ ሆዴን ባር ባር አለኝ ሙት::
ትላንትና እናንተ ቤት ገብቸ ስስቅ ስላመሽሁ ሆዴን በጣም ነው ያመመኝ :: አንፈራራ በጣምምምምምምምም ነው ያሳቀኝኝኝኝኝኝኝኝኝኝ
ያቺ ደሞ አሁን ልስጥህ ያለችው እንቢ ይለኛል ብላ ነው?
ሞኝ በላት ::
አንተ ብትሆን እኮ ግን እንቢ ነው የምትለው:: ሙት እሽ አትልም!! ቅቅቅቅቅቅቅቅቅ
ገደልከኝ
በቅንነት ፈራጅ ሕዝብ እንዳይጐዳ:
ማን ይሆን ትልቅ ሰው ሃቅን የተረዳ :?:

Image
http://www.cyberethiopia.com/warka5/vie ... hp?t=26693
የጃማ ጦስኝ
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 338
Joined: Sun Sep 02, 2007 12:02 am
Location: ጃማ

Postby ባለሱቅ » Tue Dec 21, 2010 8:42 am

አንቺ ባለጌ
አንተ ብትሆን እኮ ግን እንቢ ነው የምትለው :: ሙት እሽ አትልም !! ቅቅቅቅቅቅቅቅቅ

እስኪ ማን ይሙት ዝም ተብሎ ልስጥህ ሲባል እሺ ሚል አለ?
ቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅ
እንዴት ብትገምቺኝ ነው ግን እንደሱ ያልሽኝ

ለነገሩ አንዴ ጠይቄ ድጋሚ መጠየቅ አልወድም
እራሳቸው ከጠየቁኝ ግን.... ግጥም አርጌ መራርቄ ነው ምቀበል
ማን ሞኝ አለ እንዳንቺ አይነት ቆንጆ ተገኝቶ እምቢ ሚል
ሞኝሽን ፈልጊ
ቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅ
እስኪ ጠይቂኝና እዪው.... አገር ቤት መጥተሽ ለገና
ቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅ
ገደለኝ ባልሽ
ባለሱቅ
ውሃ አጠጪ
ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1288
Joined: Mon Sep 27, 2004 6:20 am
Location: ethiopia

Postby የጃማ ጦስኝ » Sun Jan 16, 2011 11:45 pm

ስላም የጃማ ጦስኝ ቤት ታዳሚዎቸ እንደምን ከረማችሁ:: ዓመት በአሉ እንዴት አለፈ::
ባለፈው ወንድሜ አንድ ነገር ነግሮኝ በሳቅ ልሞት ነበር::
የጠፋሁትም ለዚህ ነው::
አ.አ ካመት በዓሉ በፊት ይደውልና ሶፋ ላመትባል እንድትቀይሩ እስኪ ስንት እንደሚገኝ ጠይቂና ዋጋውን ንገሪኝ ገንዘብ እልካለሁ ይላታለ:: በሳምንቱ ደውሎ የሶፋው ዋጋ ስንት እንደሆነ ሲጠይቃት; ''ቆንጆ እቃ በጣም የሚያምር አይቸ መርጨ አስቀምጡልኝ ብዩ ትንሽ ገንዘብ ቀብድ ሰጥቸ መጥቻለሁ :: አሁን ገንዘቡን ቶሎ ላክልኝ'':: ትለዋለች:: ጥሩ የምትፈልጉትን አገኘሽ'' አላት
''አዎ''
''በስንት ተገኘ''
''ውይ ብታይ ስንት ዞሬ ዞሬ መስለህ ያገኘሁት''
''ታዲያ ስንት አገኘሽ?''
'' ብቻ ደህና ነው::75 ሽህ ብር '' ስትለው ግራ ገብቶት
''እንዴ ምንድን ነው ግዚ ያልኩሽ ? መኪና ነው እንዴ? አለ ሁል ጊዜ መኪና ግዙ እያለች ስለምታስቸግር::
''እንዴ መኪናማ ካልከኝ እስከ 500 መቶ ሽህ ነው ትቀልዳለህ እንዴ ኑሮ እንደ ውጭ ሀገር እርካሽ መሰለህ'' ብላው እርፍ::
ለካስ ውጭ የሚኖር ሰው የኑሮ ችግር ያለበት አይመስላቸውም::
አይ ጥፋት !
በሉ ቸር ሰንብቱ
እህታችሁ የጃማ ጦስኝ
በቅንነት ፈራጅ ሕዝብ እንዳይጐዳ:
ማን ይሆን ትልቅ ሰው ሃቅን የተረዳ :?:

Image
http://www.cyberethiopia.com/warka5/vie ... hp?t=26693
የጃማ ጦስኝ
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 338
Joined: Sun Sep 02, 2007 12:02 am
Location: ጃማ

Postby anferara » Sun Apr 24, 2011 10:28 am

ለጃማ ጦስኝ ታዳሚዎች

እንክዋን ለብርሀነ ትንሳኤው በሰላም አደረሳችሁ::

ለሁላችሁም መልካም በዓል::
anferara
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 445
Joined: Wed Sep 27, 2006 5:06 pm

Postby የጃማ ጦስኝ » Wed Nov 09, 2011 5:46 pm

ሁሉም ነገር ቀርቶ ዓይኗን አትከልክሉኝ
በምወደው ነገር ወጋግታ ትግደለኝ!!
እኔ ለተወጋሁ ለቆሰልኩ ወድጄ
አሁን ምን አመጣው ፖሊሱን ከዴጄ::
መካሪም አያሻኝ ወድጃለሁ! በቃ ወድጃለሁ
እንኳንስ ስጋዬን ነፍሴን እሰጣለሁ::
እያለ ሲፎክር የሰማችው ጅልልልል የጂል መጨረሻ
የዚህ ስንኝ መጨረሻው በሚቀጥለው ቢሆን ምን ይመስላችኳል?
የቤቴ ታዳሚዎች በሌለሁበት ሳይቀር ቤቴን እዬጎበኛሁ
ከፔጅ ፔጅ እየሄዳችሁ ለምታነቡልኝ ሁሉ ምስጋናዬ ከፍ ያለ ነው::
መቸም የወለዱትን ሲስሙለት አይደል ነገሩ ::
ቸር ይግጠመን አክባሪያችሁ
የጃማ ጦስኝ
በቅንነት ፈራጅ ሕዝብ እንዳይጐዳ:
ማን ይሆን ትልቅ ሰው ሃቅን የተረዳ :?:

Image
http://www.cyberethiopia.com/warka5/vie ... hp?t=26693
የጃማ ጦስኝ
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 338
Joined: Sun Sep 02, 2007 12:02 am
Location: ጃማ

Postby ባለሱቅ » Sat Nov 19, 2011 3:24 am

መካሪም አያሻኝ ወድጃለሁ ! በቃ ወድጃለሁ
እንኳንስ ስጋዬን ነፍሴን እሰጣለሁ ::
እያለ ሲፎክር የሰማችው ጅልልልል የጂል መጨረሻ

ጨርሽው እንጂ የዚህን የጅል መጨረሻ
ሆነን ቀርተንልሻል ጃማ ሆደባሻ

እንካን ደህና መጣሸ
እስኪበነካካ እጅሽ ደባብሰሽ ጨርሽው ግጥሙን
ባለሱቅ
ውሃ አጠጪ
ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1288
Joined: Mon Sep 27, 2004 6:20 am
Location: ethiopia

Re: የጃማ ልጆች ካላችሁ

Postby MeronZG » Sun Nov 20, 2011 8:13 am

የጃማ ጦስኝ wrote:ሰላም


Image

ብቅ ብቅ በሉ መልካም ሥራ ለመሥራት::


እህታችሁ
የጃማ ጦስኝ - ከጃማ


Jimma or Jamma ... I was born in Jimma and left when I was 6, always wanted to go back - one of my last dreams :)
Ethiopian Music (7000+) http://www.hubesha.com/audio.php
MeronZG
አዲስ
አዲስ
 
Posts: 35
Joined: Sat Nov 12, 2011 11:26 pm
Location: Seattle

Postby የጃማ ጦስኝ » Tue Dec 13, 2011 11:41 am

ባለሱቅ wrote:
መካሪም አያሻኝ ወድጃለሁ ! በቃ ወድጃለሁ
እንኳንስ ስጋዬን ነፍሴን እሰጣለሁ ::
እያለ ሲፎክር የሰማችው ጅልልልል የጂል መጨረሻ

ጨርሽው እንጂ የዚህን የጅል መጨረሻ
ሆነን ቀርተንልሻል ጃማ ሆደባሻ

እንካን ደህና መጣሸ
እስኪበነካካ እጅሽ ደባብሰሽ ጨርሽው ግጥሙን


ስላም ለጃማ ጦስኘ ቤት አንባቢዎቸ ! እንደምን አላችሁ?
ባለሱቅዬ አለህ እንዴ እባክህ?
ምን አለች መሰለህ:--
ነፍሴን ከነፍሱ ጋር ስላቆራኘብኝ;
ሸሽጌ እኖራለሁ ማንም ሳያይብኝ::
ምን አለች አትበሉኝ ውስጤን ለመፈልፈል
የሚያጽናናኝ የለም ፈልቶ ቢገነፍል::
መልካም ጊዜ
እህታችሁ የጃማ ጦስኝ::
በቅንነት ፈራጅ ሕዝብ እንዳይጐዳ:
ማን ይሆን ትልቅ ሰው ሃቅን የተረዳ :?:

Image
http://www.cyberethiopia.com/warka5/vie ... hp?t=26693
የጃማ ጦስኝ
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 338
Joined: Sun Sep 02, 2007 12:02 am
Location: ጃማ

Postby የጃማ ጦስኝ » Tue Apr 16, 2013 5:07 pm

ሰላም ለጃማ ጦስኝ ቤት ታዳሚዎቸ እንደምን ከረማችሁ::
ከቤቱ ላልተወሰነ ጊዜ ብሰወርም ታዳሚዎቸ ግን ከልቤ አልጠፋችሁም ነበር:: እናንተም ቤቴን ካገር ሀገር እየተንከራተታችሁ የተመልካቹን ቁጥር ባልጠበቅሁት ሁኔታ አባዝታችሁ ስለጠበቃችሁኝ ደስታዬ የላቀ ነው::
እስኪ እጂሽ ከምን እንዳትሉኝ አንዲት ግጥም ልካብዛችሁ
ሊንኵን ተመልከቱት::
http://youtu.be/WTMZyphw4YM
በቅርብ እመለሳለሁ
የናንተው የጃማ ጦስኝ
በቅንነት ፈራጅ ሕዝብ እንዳይጐዳ:
ማን ይሆን ትልቅ ሰው ሃቅን የተረዳ :?:

Image
http://www.cyberethiopia.com/warka5/vie ... hp?t=26693
የጃማ ጦስኝ
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 338
Joined: Sun Sep 02, 2007 12:02 am
Location: ጃማ

Postby ብሩክ ቀን » Sat Apr 20, 2013 10:26 am

ሰላም የጃማ ጦስኝ

መቸም ይገርማል ፡፡ በቅርቡ ጃማ ነበርኩ፡፡

ጃማና ደጎሎ ወረኢሉ ካቤ
የጠጁ የጮማው አይጠፋም ከልቤ

የሚለውን ዘፈን እያንጎራጎርኩ 11፡00 ሰአት መርካቶ ደረስኩ፡፡ አቤት ያለው ወከባ፡፡ የረዳቶቹ ጩኽት ናላ ያዞራል፡፡ ጃማ ደጎሎ ! ጃማ ደጎሎ! ደጋግሞ ይጣራል፡፡ ጃማ ነኝ አልኩት፡፡ ተከተለኝ ብሎኝ እያጣደፈ ይዞኝ ትልቁ መናኽሪያ ይዞኝ ገባ፡፡ መኪናው ሞልቷል፡፡ ወዴ ሁለተኛው ይዞኝ ሄዴ እየተጣደፍኩ ገባሁ፡፡ መኪናው ወዳው ሞላ፡፡ሹፌሩ ሞተሩን አስነስቶ ከመሀል አዲስ አባባ ወዴ እንጦጦ አቅጣጫ ጉዞ ተጀመረ፡፡ ጫንጮን፣ ሙከ ጡሪን አልፈን ለሚ አፋፍ ብቅ ስንል አንዳች ነገር ተሰማኝ፡፡ ታች የጀማ ወንዝ እንዴ ዘነዶ ተጋድሟል አሻግሬ ሳማትር አለም ከተማን ወዴ ምስራቅ ስቃኝ ጅሩ ይታየኛል፡፡ እረዳቱ ስለ ገብርኤል ሲል ከሰጠምኩበት የሀሳብ ባህር ወጣሁ፡፡ ከለሚ አፋፍ እስከ ጀማ ወንዝ ያለው ጭው ያለ ገደልና ቁልቁለት ነው፡፡ ልክ ቁልቁለቱን ስንጀምር ውላ ገብርኤል የሚባል ቤተ_ክርስቲያን አለ፡፡ጸለይኩ፡፡ ሁላችንም አዋጥተን ለረዳቱ ሰጠነው፡፡ ያንን ነፍስና ስጋ የሚለያይ ገደላማ መንገድ እንዴ ዔሊ እተተጎተትን ተያያዝነው፡፡

ጊዜ ካለኝ በሚቀጥለው ከጀማ ወንዝ እስከ ወንጪት ከዛም ስለ መልከ ፀድቅ ገዳም እንድሁም ጃማና ደጎሎ እሞነጫጭር ይሆናል፡፡

መልካም ጊዜ ለሁላችን
የጃማ ጦስኝ wrote:ሰላም ለጃማ ጦስኝ ቤት ታዳሚዎቸ እንደምን ከረማችሁ::
ከቤቱ ላልተወሰነ ጊዜ ብሰወርም ታዳሚዎቸ ግን ከልቤ አልጠፋችሁም ነበር:: እናንተም ቤቴን ካገር ሀገር እየተንከራተታችሁ የተመልካቹን ቁጥር ባልጠበቅሁት ሁኔታ አባዝታችሁ ስለጠበቃችሁኝ ደስታዬ የላቀ ነው::
እስኪ እጂሽ ከምን እንዳትሉኝ አንዲት ግጥም ልካብዛችሁ
ሊንኵን ተመልከቱት::
http://youtu.be/WTMZyphw4YM
በቅርብ እመለሳለሁ
የናንተው የጃማ ጦስኝ
ብሩክ ቀን
አዲስ
አዲስ
 
Posts: 25
Joined: Mon May 28, 2012 11:13 am

Postby የጃማ ጦስኝ » Wed Apr 24, 2013 6:42 pm

ሰላም የቤቱ ታዳሚዎቸ; እንዲሁም ትልቁ እንግዳዬ ብሩክ ቀን :: እንደምን ከረማችሁ::
የፋሲካ ጦም መገባደጃው ስለሆነ ሁሉም ደከም ከም ማለቱ አይቀሬ ነው ለማንኛውም መልካም ፋሲካ ከወዲሁ እየተመኘሁ : ብሩክ ከጃማ በሰላም ሲመለስ የጃማን የማር ጠጂ ምን ከመሰለ የዶሮ ፍትፍት ጋር የዘን ለመቅረብ ቃል እገባለሁ:: ብሩክ ቀን እንግዲህ ወደ ስንደው ግራር አረፍ ብለህ ጠጁን እንዳትጨርሰው አደራ::
በቅንነት ፈራጅ ሕዝብ እንዳይጐዳ:
ማን ይሆን ትልቅ ሰው ሃቅን የተረዳ :?:

Image
http://www.cyberethiopia.com/warka5/vie ... hp?t=26693
የጃማ ጦስኝ
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 338
Joined: Sun Sep 02, 2007 12:02 am
Location: ጃማ

Postby የጃማ ጦስኝ » Tue Jun 25, 2013 2:31 pm

ሰላም የቤቱ ታዳሚዎች እንደምን አላችሁልኝ
ብቅ እላለሁ
በቅንነት ፈራጅ ሕዝብ እንዳይጐዳ:
ማን ይሆን ትልቅ ሰው ሃቅን የተረዳ :?:

Image
http://www.cyberethiopia.com/warka5/vie ... hp?t=26693
የጃማ ጦስኝ
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 338
Joined: Sun Sep 02, 2007 12:02 am
Location: ጃማ

Postby የጃማ ጦስኝ » Fri Aug 23, 2013 7:29 pm

ሰላም የጃማ ጦስኝ ቤት ታዳሚዎቸ እንደምን አላችሁ?
እስኪ ይቺን ብሎግ ጎብኙልኝ
www.ayalseyoum.com


መልካም ሰንበት
እህታችሁ የጃማ ጦስኝ
በቅንነት ፈራጅ ሕዝብ እንዳይጐዳ:
ማን ይሆን ትልቅ ሰው ሃቅን የተረዳ :?:

Image
http://www.cyberethiopia.com/warka5/vie ... hp?t=26693
የጃማ ጦስኝ
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 338
Joined: Sun Sep 02, 2007 12:02 am
Location: ጃማ

PreviousNext

Return to Warka Intimate - ዋርካ ፍቅር

Who is online

Users browsing this forum: MSN [Bot] and 1 guest