የጃማ ልጆች ካላችሁ

The Love Forum (love, relationship) (የኔ ቆንጆ እንተዋወቅ :-)

ቆንጆ ነው

Postby ወልዲያ » Fri Jan 30, 2009 12:59 pm

ሠላም ለቤቱ!


አለሽ ወይ ባገሩ?

የጀመርሽው ልብ ወለድ ቆንጆ ነው:: በዚሁ ቀጥይ:: ረዘም ያለ ትረካ እንደሚሆን እገምታለሁ:: ትረካው ሲያልቅ የተሰማኝን ሃሳብ ለመስጠት ተዘጋጅቻለሁ::

መልካም ጁማ
ወልዲያ - የጁ
ወልዲያ
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 679
Joined: Tue Apr 17, 2007 11:55 am
Location: የጁ - ወሎ

Postby የጃማ ጦስኝ » Fri Jan 30, 2009 4:44 pm

የቤቷን ስራ አጠናቀቀችና ወደ መኝታ ቤቷ ገብታ አረፍ አለች:: ያሳለፈቻቸውን የድካም አመታቶች ስታስባቸው; ዛሬ ያለችበት ሁኔታ እጂግ ደስ ይሚያሰኝ እንደሆነላት ገምታም አታውቅም ነበር:: ታሪኩን ከማግኝቷ በፊት የነበረውን የብቸኝነት እና የልፋት ጊዜ ዛሬ ላይ ሆና ጭራሽ ማሰብ አትፈልግም:: ትሪኩ ለእሷ ትልቅ የአምላክ ስጦታ ነው ከማንም ከምንም በላይ ትወደዋለች እጂግም ታምነዋለች:: ደጋግሞ በዓይነ ሕሊናዋ የሚመጣው የሰርጋቸው ቀን ምን እንደሚመስል ነው; አዎ ስድስት ወር ሳይሞላኝ በፊት ሰርጉ መሆን አለበት ለሙሽራ ልብሴ እንዳልቸገር; ለነገሩ ግን ዛሬ ጊዜ ምን ችግር አለ አርግዞ መጋባት እንደሆነ የተለመደ ሆኗል; '' ሁለቱ አንድ ይሆናሉ የሚለው የመ/ቅዱስ አነጋገር ቀርቶ ሶስቱ አንድ ይሆናሉ መባል ከተጀመረ ቆየ '' አለችና ለራሷ አንድ ጊዜ እርጉዝ ሆነው ስለተጋቡ ሰዎች የሰማችውን ጨዋታ አስታወሰች::
ስዓቱን ደጋግማ ብታይም የዛሬው የጉድ ነው ካለበትም ንቅንቅ አይልም:: እንደምንም አልጋዋ ላይ እየተገላበጠች የቤቷ ስልክ ደጋግሞ ጮኸ; ቀስ ብላ ካልጋው ወረደችና ስልኩን አንስታ ''ሀሎ ''አለች
''ሀሎ ሀና እንደት ዋልሽ '' አለች አስቴር ከወዲያ
''ውይ አስቱዬ እንደት ዋልሽ?
''ደህና ነኝ ! ምን እየሰራሽ ነው ?''
''ኧረ ምንም አልሰራም እንዲሁ ጋደም ብየ ነው የደወልሽው በዚህ ላይ ስዓቱ አልሄድ ብሎኝ እየታገልኩ ነው:: ዛሬ ታሪኩን የምስራች ለመንገር ተዘጋጂቻለሁ''
''ትላንት ሳትነግሪው ለምን ቀረሽ ?''
''ትላንት እቤት አላደረም የሚያስረክበው ስራ ስለነበረው ከጓደኞቹ ጋር ነው ያደረው''
''እኔ ምልሽ ወንድ ልጅ ደጋግሞ ውጭ ሲያድር ጥሩ እንዳልሆነ እወቂ በዚህ ላይ እነማናቸው ጓደኞችህ ብለሽም አትጠይቂም ለማንኛውም በጣም ነፃነት ለወንድ ልጅ መስጠት እንድሚያበላሽ እወቂ ''አለቻት
''ወይ ጉድ ይኸም አለ እንዴ ? እረባክሽ ዬኔ ታርኩ እንዲህ ላለው ነገር ጊዜም የለው:: ደግሞስ አመል ካለበት የኔ ጭቅጭቅ ምን ሊያስጥለው ብለሽ::'' አለች በልቧ ግን ድንገት ፍርሀት እንደበረዶ ሲረጭ ተሰማት; ለመሆኑ አንቺስ እንዴት ነሽ ? ለምን ብቅ አትይም እና ቡና አንጠጣም ?አለቻት '' ወይ ሀንዬ መቸ ታደልኩ ብለሽ ነው እኔ ለማረፍ ይኸ መከረኛ ሰውዬ ብር ካላክሽ ብሎ ወጥሮ ይዞኛል ያለኝን ሰብስቤ ልልክ ስቶክዊል እንዳመጣብኝ መሄደ ነው ስመለስም ይመሽብኛል በባስ ነው የምሄደው በይ እንዴት እንደዋልሽ ልጠይቅሽ ብየ ነው ከቻልኩ ነገ ብቅ ብየ አይሻለሁ :: '' ተባባሉና ስልኩ ቢዘጋም ሀና እዚያው እስልኩ አጠገብ እንደተቀመጠች ከአስቴር ጋር የተባባሉትን እያሰበች በሀሳብ ጭው ብላ ሄደች
'' ወይ ሰው የሰማው ነገር እቴ መቸም ጤና አያገኝ አሁን ምን አቅለብልቦኝ ነው እውጭ አደረ ብየ ያልኩት ሰው መቸም በሰው ኑሮ መግባት ይወዳል ;; ለመሆኑስ አሁን ሰው መልካም መልካሙን ይመክራል እንጂ ኤጭ ''
አለችና በአስቴር አነጋገር የተሰማትን ስሜት ወዲያ አውጥታ ወረወረችውና እሱ መቸ ሞላለት እናቴ ሌት ከቀን ከወረቀት ጋር እየታገለ ; መቸም ሰው ሲባል ጤና የለውም ያልታሰበውን ያሳስባል ሁለተኛም አይለምደኝ የቤቴን ሚስጥር እኔው ካልቻልኩ ማንም አይችልልኝም አለችና ብድግ ብላ ወደ ኪችን ልትገባ ስትል አንድ ነገር ፊቷ ድቅን አለባት ባለፈው ወር የተጋቡ ልጆች ቤት ልትጠይቅ ሄዳ ከሳሎናቸው መግቢያ ኮሪደር ላይ የተሰቀለውን የሰርጋቸውን ፎቶ ስታይ በልቧ የተመኘችውን አስታወሰችና የሷንም የሰርግ ፎቶ እንዴት እንደምትሰቅላቸው ከዚያም ስትወልድ ከልጃቸው ጋር ሶስት ሆነው ተነስተው የምትሰቅለውን በሀሳቧ አዘጋጀች
በቅንነት ፈራጅ ሕዝብ እንዳይጐዳ:
ማን ይሆን ትልቅ ሰው ሃቅን የተረዳ :?:

Image
http://www.cyberethiopia.com/warka5/vie ... hp?t=26693
የጃማ ጦስኝ
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 338
Joined: Sun Sep 02, 2007 12:02 am
Location: ጃማ

Postby ብርቄነህ » Fri Jan 30, 2009 7:11 pm

አምባሰል ብሎ ሀይቅ ካለ
ወረኢሉ ብሎ ምን ይላል?


መልስ ..............................ጃማ
ብርቄነህ
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 605
Joined: Thu Jan 22, 2009 5:30 pm

Postby የጃማ ጦስኝ » Sat Jan 31, 2009 1:01 pm

ሰላም ወርቄነህ እንደምን አልህ/ሽ
እንኳን ደህና መጣህ/ሽ ::
ለተጠየቅሁት ጥያቄ መልሱን እንዲህ እላለሁ
ከወረኢሉ በታች ከታሪ,ፋጂ;ደብረጉራቻ እና ጃማ /ደጎሎ ከተማ ናቸው:: እንግዲህ ውስጥ ውስጡን ትንንሽ ቀበሌዎችም አሉ እንሱን ደግሞ ስጠየቅ እመልሳለሁ ብየ ነው::
አደራ አትጥፋ/ፊ
በቅንነት ፈራጅ ሕዝብ እንዳይጐዳ:
ማን ይሆን ትልቅ ሰው ሃቅን የተረዳ :?:

Image
http://www.cyberethiopia.com/warka5/vie ... hp?t=26693
የጃማ ጦስኝ
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 338
Joined: Sun Sep 02, 2007 12:02 am
Location: ጃማ

አየር ሁኔታው የሰውየውን አመለካከት ሊለውጠው ይችላል ወይስ ያት

Postby ድርሰት » Tue Feb 03, 2009 1:22 pm

()()()()()()()()()()((((((((((((((((((((((((((())))))))))))
Last edited by ድርሰት on Thu Apr 16, 2009 1:00 pm, edited 1 time in total.
There is always a small beginning for every thing that we should not despise!!!!!!!!!!!
ድርሰት
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 101
Joined: Mon Jan 19, 2004 6:16 pm
Location: united states

Postby ጅብገደል » Wed Feb 04, 2009 8:15 am

ሰማ የጃማ ጦሥኝ እንዴት ነህ ?/
ስንት ነው የጃማ ህዝብ ብዛት ከ100 ትበልጣላችኁ ወይ ?
ከወሎ አጠገብ ከሆነ ሀገራችሁ ለምን የውሎ ልጆች የሚለው ክፍል ውሥጥ ደባል አትገባም ነበር ወይ አኔም ሩም ሜት እፈልግልህ ነበር
እኔም የዳውዶ ልጆች የማጀቴ ልጆች የሚል ቤት ልከፍት ነው :::;
ጅብገደል
ውሃ አጠጪ
ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1144
Joined: Wed Jan 14, 2009 3:23 am
Location: BULGA ENBUR GEBYAW GA

Postby ድርሰት » Wed Feb 04, 2009 10:08 am

**************************************************
Last edited by ድርሰት on Thu Apr 16, 2009 1:02 pm, edited 1 time in total.
There is always a small beginning for every thing that we should not despise!!!!!!!!!!!
ድርሰት
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 101
Joined: Mon Jan 19, 2004 6:16 pm
Location: united states

Postby ለገሂዳ » Thu Feb 05, 2009 1:20 am

ወዳጄ ድርሰት:

ምነው በጅብ ገደል ላይ ይህን የመሰለ እርግማን አወረድክበት - ጅብ ገደል ግባ ብለህ:: ባይሆን ደብረ-ጉራቻ ገደል ገባ ብትለው አይሻልም, በዚያውም ጃማን ያየው ዘንድ::

ጅብገደልስ ብትሆን ዋናው ነገር ጥራት ነው, ብዛት ዋጋ የለውም;; ፍቅር በራስ ቤት ሲሆን ነው እንጅ በደባልነት አያምርም:: ስለጃማ ወርቂቱ እረኞች ያሉትን ልንገራቸሁና ላብቃ:

የጃማ ማርና ቅቤው ዋጋው ውድ
ከለከፈ አይለቅም የሀድራው መውደድ
ሼሁም አበዱላት መነኩሴው ጭምር
ለጃማዋ እመቤት ለልእልት አምበርብር
ወደ ጃማ እሚጉዋዝ ምእመናኑ በዝቶ
የሌላው ቤተስኪያን አረፈው ተዘግቶ
ለገሂዳ
አዲስ
አዲስ
 
Posts: 31
Joined: Fri Jan 25, 2008 1:41 am

.....ባንቺው መጀን........

Postby ወልዲያ » Thu Feb 05, 2009 7:41 am

ሠላም ለቤቱ!


ሠው ለሠው አሥቦ ወንዝ ከተሻገረ:
ምንድን ነው ችግሩ ካልተንቀባረረ :?:

ጃማን አትንኩብኝ የእኔ ልብ ናት:
አቋቋም ባልችልም ቅኔ ክህኖት::

ድጓ ጀማምሬ ዋዜማ ደርሼ:
በፍቅር አለኩኝ ጃማን ጠቃቅሼ::

ባንቺው መጀን (ደርብ ዘነበ)
http://www.youtube.com/watch?v=Nk0xPpUsjDQ


መልካም ሓሙሥ
ወልዲያ - የጁ
ወልዲያ
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 679
Joined: Tue Apr 17, 2007 11:55 am
Location: የጁ - ወሎ

Postby ጅብገደል » Thu Feb 05, 2009 10:42 am

ታዲያ ድርሰትና ለገሂዳ ሁላታቹ ሳስበው እየታናጫቹ ይመስላል ያላችሁት ስትጨርሱ ንገሩኝ በጻፋችሁት ላይ በቅርቡ እንነጋገርበታልን
እስከዛው ቀበና ያለው ገደል ግብ
ጅብገደል
ውሃ አጠጪ
ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1144
Joined: Wed Jan 14, 2009 3:23 am
Location: BULGA ENBUR GEBYAW GA

Postby ድርሰት » Thu Feb 05, 2009 12:28 pm

**********************************
Last edited by ድርሰት on Thu Apr 16, 2009 1:03 pm, edited 1 time in total.
There is always a small beginning for every thing that we should not despise!!!!!!!!!!!
ድርሰት
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 101
Joined: Mon Jan 19, 2004 6:16 pm
Location: united states

Postby የጃማ ጦስኝ » Fri Feb 06, 2009 5:01 pm

ሰላም ለዚህ ቤት ታዳሚዎች ! እንደምን ከረማችሁ :: ቤታችን አምሮበታል እንዲህ ነው ትብብር እስኪ በርቱ ::
የጅብ ገደል ባመጣው ጣጣ መነኩሴው ሁሉ ቆቡን ጣለ ሲባል ሰምቸ ወይ ጊዜ አስባለኝ

በቋፍ ቁጭ ያለ ቆብ ወይ ያልጠበቀው ትጥቅ;
ልውጣ ልውረድ ብሎ ከራስ ጋር ትንቅንቅ::
በማር በቅቤ አድጋ በአሽከር በገረድ;
መነኩሴና ሸኩን አጣምራ ለውድ;
እንዲህ እየዘጋች የሰማይ መንገድ;
ምነው ምዕመን በዛ ጃማ የሚሄድ::
ውዱ ባለቤቴ የጁ ላይ ተወልዶ;
ቅኔ ጠፍቶት አየሁ ወይ ነዶ ወይ ነዶ::
የጁ ላይ ተወልደህ ላሊበላ አድገህ;
ቅኔ ድጓ ላንተ መቸ ሊከብድህ::
አቋቋም ባትችልም እንደካህናቱ;
ቆሞ ለማስቀደስ ጠንካራ ነህ ብርቱ::::::

መልካም ሰንበት
በቅንነት ፈራጅ ሕዝብ እንዳይጐዳ:
ማን ይሆን ትልቅ ሰው ሃቅን የተረዳ :?:

Image
http://www.cyberethiopia.com/warka5/vie ... hp?t=26693
የጃማ ጦስኝ
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 338
Joined: Sun Sep 02, 2007 12:02 am
Location: ጃማ

Postby ለገሂዳ » Sat Feb 07, 2009 7:40 pm

ቄሱ ቆብ ቢጥሉ,
ቀሚስም አውልቀው
ጥምጣሙን ቢፈቱ
ሽሁ ጡዋሂር ሆነው
አረዳ ፍርድ ስጥ
ጥፋቱ የማነው?
የውበት እመቤት እሱዋን ካደረጋት
እሱው በሰራቸው አይኖች ሲያስተውሉዋት
ልባቸው ተነድፎ ምርኮ ቢወድቁላት
ምንድነው ወንጀሉ, ምን ሀጢአት አለበት?
የአፍቅርን ትእዛዝ ነው'ኮ ያከበሩት!
ለገሂዳ
አዲስ
አዲስ
 
Posts: 31
Joined: Fri Jan 25, 2008 1:41 am

Postby የጃማ ጦስኝ » Mon Feb 09, 2009 4:43 pm

ሰላም ለዚህ ቤት ታዳሚዎች እንዴት ከረማችሁ እስኪ ወደ ጀመርነው ልብ ወለድ ልመልሳችሁ

ቤቷን በሚገባ ካዘጋጀች በኋላ የተሰራውን ምግብ ከያይነቱ ለመቀማመስ ብትሞክርም ለብቻዋ መብላቱን እንደሀጢያት ስለቆጠረችው ርሀቡን ታግሳ ታሪኩን መጠበቅ ጀመረች::
የለበሰቻትን ሳሳ ያለች ሸሚዝ ወደ መስታወቱ ጠጋ አለችና ስትመለከታት ጡቶቿ ከወትሮው በተለየ ሁኔታ ተወጥረዋል :: ታሪኩ ባለማስተዋሉ እንጂ በእርግጥም እርግዝናዋ መታየት ጅምሯል '' ወይ አምላኬ ላንተ ምን ይከፈልሀል '' አለችና ዓይኖቿ በእንባ ተሞልተው አምላኳን ስታመሰግን የቤቱ መጥሪያ ጮኸ; መጥሪያውን አነሳችና ''ሀሎ '' አለች
''እኔ ነኝ ክፈችልኝ'' አላት ከፈተችለትና '' ታሪክየ እንዴት ዋልክ ቁልፍህስ ጠፋብህ እንዴ '' አለችው ''የምን ቁልፍ'' አላት ''የበሩ ቁልፍ '' ''እ.. ለካ ቁልፍ አለኝ እረስቸው ነው'' አላትና አልፏት ቁጭ አለ '' የኔ ጌታ ደከመህ ? በል መጀመሪያ ታጠብና አረፍ ትላለህ '' አለች
''አይ አልታጠብም ምሳ በደንብ አልበላሁም የሚቀመስ ካለሽ '' እኔን እኔም አንተን ስጠብቅ አልበላሁም ''
አለችና ምግቡን በያይነቱ መደርደር ስትጀምር አሻግሮ ጠረንጴዛውን ተመለከተው ቤቱ በተለየ ሁኔታ ደመቅ ብሏል የሚያምር አበባ መሀል ጠረጴዛው ላይ ጉብ ብሏል የተጠቀለለ ጠርሙስም ይታያል ምንም ስሜት አልሰጠውም ምግቡን አቀራረበችና ቁጭ ብላ መብላት እንደጀመሩ ልታጎርሰው እጇን ስትዘረጋ '' ዝም ብለሽ ለራስሽ ብይ'' አላት ቀናም ብሎ ሳያያት ''እንዴ ከመች ወዲህ ነው ሳላጎርስህ በልቸ የማውቀው'' አለችና ትኩር ብላ አየችው ምንም መልስ ሳይሰጥ እህ ህ ብሎ ትንፋሹን በረጂሙ ሳበና ያንጠለጠለችውን ማንኪያ የመመንጨቅ ያህል ተቀበላትና '' እኔምለው እኔ ራሴን መመገብ እችላለሁ አላስፈላጊ ነገር አልፈልግም አለ '' እንዴ ከመቸ ወዲህ ነው ማጉረሴ አላስፈላጊ የሆነው ለነገሩ የሚናፍቅህ ጊዜ እሩቅ አይሆንም እኔም ሌላ የምንከባከበው አግኝቻለሁ '' አለችና ቀስ ብላ በግራ እጇ ሆዷን መደባበስ ጀመረች ''ምን ማለት ነው''? አላት ቀና ብሎ የሚጎርሰውን እንዳንጠለጠለ '' እሱን እማ አትቸኩል ከዛሬ አያልፍም እንጫወታለን ቀስ ብለን'' አለች '' ምንድን ነው እሱ'' አለ ቆጣ ብሎ ; ታሪኩ ከትንሽ ጊዜ ወዲህ ያቅበጠብጠዋል አልታወቀለትም እንጂ እሱንም እንደርጉዝ ሴት አድርጎታል ''ምንድነው ልትነግሪኝ የፈለግሽው?'' አላት ደገመና
''እንዴ ይደርሳል አልኩህ አኮ በልተን እንጨርስ '' አለች ፈገግ ብላ ''አልችልም ምንድነው ንገሪኝ አለና ያዘጋጀውን ሳይጎርስ እንድትነግረአ አፈጠጠባት ''አቤት አንተ አሁን ምን አስቸኮለህ ያው ያንተው ነው የምን መጣደፍ ነው ብላ እርሀቧን ለማጥፋት ጎረስ ጎረስ ማድረግ ጀመረች ''ሀና ታውቂያለሽ እኔ እንደማልችል እንዲህ ያለ ነገር አልወድም ንገሪኝ አለና ውጥር አደረጋት
''አቤት አንተስ እንኪ እረጋ በል ሻምፓኙም ይከፈት ሻማውም ይለኮስ አለችና ብድግ ስትል
በቅንነት ፈራጅ ሕዝብ እንዳይጐዳ:
ማን ይሆን ትልቅ ሰው ሃቅን የተረዳ :?:

Image
http://www.cyberethiopia.com/warka5/vie ... hp?t=26693
የጃማ ጦስኝ
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 338
Joined: Sun Sep 02, 2007 12:02 am
Location: ጃማ

Postby የጃማ ጦስኝ » Mon Feb 09, 2009 5:33 pm

ዛሬ የነነዊ ጾም ገብቷል ለሶስት ቀን ማለት ነው ሀሙስ ይፈታል:: ዋናው ያብይ ጾም የሚገባውም የካቲት 16 ነው በሀበሻ አቆጣጠር ማለት ነው:: በቤተክርስቲያንም ይችን ሶስት ቀን ቲቪ እንኳን ሳንከፍት በጾም በጸሎት እንድንቆይ ተነግሯል:: ያው ጸሎቱም ሀገራችንን በማሰብ እ/ር ምድሪቷን እንዲጎበኛት እና አፋችንን በሳቅ እንዲሞላው ነው::


:D እንኪ አስቀን አንዴ
ይከፈት አፋችን;
ተረት ተረት ይሁን
ያ ድህነታችን::

ተርፎን እንበሽብሽ;
እስኪ አስቀን አንዴ;
ልጅ እና እንጀራ ልጂ አንተም አለህ እንዴ?

ሁሉም ጠግቦ ይደር
እስኪ አስቀን አንዴ
የታረሰው መሬት ያብቅል ጤፍ ከስንዴ

እስኪ አስቀን አንዴ
አርግልን ዘ ጸ አ ት
ህዝብህ ከግብጽ ሀገር እንደተላቀቁት

እስኪ አስቀን አንዴ
ልጆች ምግብ ይብሉ በቀን ሶስት ጊዜ
እናትም በጓዳ ይቅርባት ትካዜ

መልካም ጾም ጸሎት
እህታችሁ የጃማ ጦስኝ
በቅንነት ፈራጅ ሕዝብ እንዳይጐዳ:
ማን ይሆን ትልቅ ሰው ሃቅን የተረዳ :?:

Image
http://www.cyberethiopia.com/warka5/vie ... hp?t=26693
የጃማ ጦስኝ
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 338
Joined: Sun Sep 02, 2007 12:02 am
Location: ጃማ

PreviousNext

Return to Warka Intimate - ዋርካ ፍቅር

Who is online

Users browsing this forum: Google [Bot] and 2 guests