የጃማ ልጆች ካላችሁ

The Love Forum (love, relationship) (የኔ ቆንጆ እንተዋወቅ :-)

ፆመ ነነዌ

Postby ድርሰት » Tue Feb 10, 2009 2:54 pm

=============================
Last edited by ድርሰት on Thu Apr 16, 2009 1:04 pm, edited 1 time in total.
There is always a small beginning for every thing that we should not despise!!!!!!!!!!!
ድርሰት
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 101
Joined: Mon Jan 19, 2004 6:16 pm
Location: united states

Postby የጃማ ጦስኝ » Tue Feb 10, 2009 6:22 pm

''እንቆቅልሹን አቁመሽ ለመናገር የምትፈልጊውን ለምን አትናገሪም''
'' ምን ነካህ ታሪክዬ የምን እንቆቅልሽ ተረት ተረት አመጣህ እኔስ የምነግርህ ፍጹም ድስታ ያለበት እውነት ነው''
''ታዲያ ምን ዙሪያውን ያዞርሻል? ለምን አትነግሪኝም?''
'' እኔማ ከመናገር አልቀርም የተሰራ ሳይታይ ; የተረገዘም ሳይወለድ መች ይቀራል''
''ማለት?''
''በቃ ደስ ይበልህ ''
''በምኑ ነው ደስታዬ?''
''አንትም አባት እኔም እናት ልንሆን ነው !!''
''ምን? ምንአልሽ''
''አርግዛለሁ''
''አርግ አርግዛለሁ? ማን አንቺ?''
''እንዴ አዎ እኔ '' አለች ከመቀመጫው ዘሎ በመነሳት እንደነብር ሲያፈጥባት ደንግጣ '' አዎ እርጉዝ ነኝ ምነው ደስታ ነው ወይስ ምንድነው ግራ አጋባኸኝሳ ''
''ደስታ ምንድነው እየሰራሽ ያለሽው ? ህይወቴን ለማበላሸት ነው ማለት ነው ዓላማሽ''
''አልገባኝም ምን ማለትህ ነው ማርገዜ አላስደሰተህም''
አለች ግራ እንደተጋባች '' በጭራሽ በጭራሽ የማይሆን እና የማይታሰብ ነው ደግሞም ተነጋግረናል ልጅ እንደማያስፈልገን'' አለ እንዳፈጠጠ
''ልጅ አያስፈልገንም ? እስከመቸ?
''እስከመቸም ቢሆን ልጅ አልፈልግም''
''ልጅ አልፈልግም?''
''ልጅ አልፈልግም አዎ አልፈልግም አሁንም እንደምንም ብለሽ የሚቻለውን ሁሉ አድርጊ ''
''እንዴት ማለት ምን ላድርግ?
''ከአስቴር ተመካከሪና አስወጭ እኔ በጭራሽ የማልቀበለው ነገር ነው ''
''አስዎጭ? አስወርጂ ማለትህ ነው? ''
''እንደፈለግሽ በይው ግን እኔ አልፈልግም ማስወጣት አለብሽ ''
''እኮ አስወርጂ ነው የምትለኝ?
''አዎ አስወርጂው''
''እግዚኦ !!! '' አለችና ደንግጣ እራሷን በሁለቱም እጆቿ ግጥማ አድርጋ ይዛ ባለችበት እንደድንጋይ ቆማ ቀረች
''ምነው ምን አጠፋሁ ? የኔ ጌታ አለችና እንደምንም ራሷን ተቆጣጥራ ልታነጋግረው ስትሞክር ገፍትሯት ወደ መኝታ ቤት ገባ :: ሀና እንደምንም ብላ ሶፋው ላይ አርፍ አለችና ስቅስቅ ብላ ማልቀስ ጀመረች ምን አልባት ለቅሶየን ሲሰማ ይመጣል ብላም ስላሰበች የለቅሶዋን ድምጽ ትንሽ ጨመር አደረገችው ምንም መልስ የለም ብቅም ብሎ ለቅሶው እንዲቆም ገላጋይ አላገኘችም :: የሚበቃትን ያህል ካነባች በኋላ ወደ መታጠቢያ ቤት ገብታ ተጣጠበችና ለመተኛት መኝታ ቤቱን ቀስ ብላ ከፈት አደረገች ስለተኛ እንዳልቀሰቅሰው ብላ :
''ኧረ እግዚኦ!!!!!! ምንድነው ጉዱ ''አለች በጩኸት የበለጠ ተደናግጣ '' ምን እያደረክ ነው ምንድነው ችግሩ ምን ይሁን ብለህ ነው?''
ምንም መልስ አልሰጣትም ብቻ በያለበት የተበታተነው እቃና ልብስ መኝታ ቤቱን የእብድ ቤት አስመስሎታል
''ለመሆኑ በጤናህ ነው ? ወይስ ሌላ እኔ የማላውቀው ችግር አለ? ለምን አታናግረኝም ? ኧረ ሰለመድሀኒዓለም ብለህ '' ምንም መልስ የለም ብቻ ሳይነጋበት እንደሚሮጥ ጅብ ይጣደፋል '' እና ምን እያደረክ እንደሆነ ለምን አትነግረኝም እያለች ስትለምነው ያለየሌለ ሀይሉን አሰባስቦ ሶስት ሻንጣ ሙሉ እያንዘፋዘፈ ከሶስት ወር በፊት በሰባት ሽህ ፓውንድ በገዛችለት መኪና እቃውን ጠቅልሎ በቆመችበት ጥላት ውልቅ አለ
በቅንነት ፈራጅ ሕዝብ እንዳይጐዳ:
ማን ይሆን ትልቅ ሰው ሃቅን የተረዳ :?:

Image
http://www.cyberethiopia.com/warka5/vie ... hp?t=26693
የጃማ ጦስኝ
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 338
Joined: Sun Sep 02, 2007 12:02 am
Location: ጃማ

አመሉን ቅጡለት

Postby የጃማ ጦስኝ » Wed Feb 11, 2009 3:20 pm

አመሉን ቅጡለት ;
እሱ ነው ጠላቱ
እንዳይታይ ማንነቱ;
እንዳይወጣ ውበቱ;
ጋረደበት::

እንዳይከበር በክብር;
እንዳይሞገስ ባዝማሪ;
እንዳይጋበዝ በምልጃ;
እንዳያወሩ ስለሱ ;
እውቀቱን እያነሱ;

አመሉ ጥሎት ከሜዳ;
ያ ሰው እጂግ ተጎዳ::
እንዳያዝኑለት ቅጥ የለው;
እንዳያቀርቡት እሬት ነው ;
አቤት የሱስ የጉድ ነው::

አደገ ብሏል ወላጂ ;
እሱስ ለማንም አይበጂ;;

በትቢት ተወጥሮ ;
ልብ አይገዛም ውሎ አድሮ;
እያወቀ ካላወቀ;
እያስተማረ ካልተማረ;
ታዲያ ምኑን አዋቂ ተባለ::

ከዚህ ያድናችሁ
በቅንነት ፈራጅ ሕዝብ እንዳይጐዳ:
ማን ይሆን ትልቅ ሰው ሃቅን የተረዳ :?:

Image
http://www.cyberethiopia.com/warka5/vie ... hp?t=26693
የጃማ ጦስኝ
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 338
Joined: Sun Sep 02, 2007 12:02 am
Location: ጃማ

Postby ድርሰት » Wed Feb 11, 2009 4:35 pm

====================
Last edited by ድርሰት on Thu Apr 16, 2009 1:04 pm, edited 1 time in total.
There is always a small beginning for every thing that we should not despise!!!!!!!!!!!
ድርሰት
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 101
Joined: Mon Jan 19, 2004 6:16 pm
Location: united states

Postby የጃማ ጦስኝ » Wed Feb 11, 2009 4:54 pm

ተካታታይ..........

ምድር ሰማይ ስለዞረባት ተንገዳግዳ አልጋው ላይ ተዘረረች::
ከዚያች ቀን ጀምሮ ከአልጋ ላይ አልተነሳችም; በህመም እንደተሰቃየች የመውለጃዋ ቀን ደረሰ::

''ሀንዬ በርቺ አሁን ይመጣሉ በሰላሳ ደቂቃ እንደርሳለን በለዋል'' አለች አስቴር ቤቷን ትታ እሷጋ ከተቀመጠች አንድ ሳምንት ሆኗታል:ታሪኩ ጥሏት ከወጣ ጀምሮ እንደ እናትም እንደ እህትም የምታስታምማትም የምታጽናናትም እሷ ነች;
''እኔምልሽ አስትዬ ሽንት ውሀው መፍሰሱን ነገርሻቸው ?'' አንቺ ደሞ በምን ቋንቋ ነው ይኸን ሁሉ የማወራው'' ታዲያ ማን ሊያስተረጉምልን ነው ? ያልቸገረሽን አታስቢ ደግሞስ ለምጥ ምን አስተርጓሚ ያስፈልጋል; ዝም ብሎ ማርያም ማርያም ማለት ነው እንጂ; ወይ አንቺ ማርያምንማ ያውቋታል ብለሽ ነው; አንድ ሰው ማርያም ማርያም ካለ መች አነሰ ;ስለዚህ ማርያም ማርያም ለማለቱ እኔ አለሁ ማማጡን አንቺ ነሽ የምታምጪው እነሱምኮ ብዙ ይገባቸዋል ችግራችን ስለዚህ አይዞሽ ወሬ አያበዙብንም ካልሆነም አስተርጓሚ ያመጡልናል'' እያለች ስታበረታታት አቡላንሱ ደርሶ የቤቱ መጥሪያ ተደወለ;
''ሀሎ'' አለችና በሩን ስትከፍት አዋላጆቹ እየተሯሯጡ ገቡ; '' ሀው ኢዝ ሽ ? ኢዝ ዘ ወተር ብሮክን አለች ነርሷ;መልስ የለም; ግራ ስለገባቸው ሁለቱ ሴቶች ሲተያዬ ነርሷ ሀናን ጠጋ አለችና በተኛችበት ዳበሰቻት ሽንት ውሀው መፍሰሱ ብቻ ሳይሆን ሀና ለመውለድ ለካ በጣም ተቃርባለች ''ኦ ማይ ጎድ ዜር ኢዝ ኖ ታይም ቱ ቴክ ኸር ቱዘ ሆስፒታል ዘ ቤቢ ኢዝ ዱ ስትላቸው ጓደኞቿ እየተሯሯጡ የሚያስፈልገውን መሳሪያ ማቀራረብ ሲቸምሩ ሀናን አስተካከለችና ነርሷ ፑሽ አለቻት ያለ የሌለ ሀይሏን አሰባስባ ሀና ማማጥ ጀመረች የሚገርም እድል ነው በአምስት ደቂቃ ውስጥ ሴት ልጂ ተገላገለች;; ኢዝ ኤ ገርል ኤ ቢውቲፉል ገርል አለችና ለሀና ስታስታቅፋት አስቴርም ጠጋ ብላ የሀናን እራስ ያዝ አድርጋ ሁለቱ የክፉ ቀን ወዳጆች ተላቀሱ :: ''ኖ ሞር ክራይ ኢትስ ፊኒሽድ ቢ ሀፒ'' አለችና የቀረውን ሲሰራሩ ''አስቴርዬ ምነው መንታ ሆነው ቢሆን ; ወንድና ሴት ምነው በሆኑልኝ ኖሮ'' አለቻት
ይኸማ እመቤቴን ማሳዘን ነው ተመስገን ነው እንጂ ደግሞስ ወንዱን ትወልጂዋለሽ ምን አስጨነቀሽ''
''ካሁን በኋላ ? ካሁን በኋላማ ወንድ የሚባል በአይኔም አላይም :: ብቻ አምላክ ይቺኑ ሽ ያርግልኝ ለኔም ጤናየን ይስጠኝ ''
''አይዞሽ እርግዝናው እኮ ነው እንጂ ሌላማ ምን ትሆኛለሽ ሀንዬ እዚህ ሀገር እንደሆነ ሰዎቹ የተባረኩ ናቸው ሴትና ልጂ በጣም ነው የሚያከብሩት ምን ይጎልብኛል ብለሽ ነው ዝም ብለሽ እማያስጨንቀው አያስጨንቅሽ ስትላት ትክዝ አለችና ልጇን ወደ ደረቷ በጣም አስጠግታ አቀፈችና እንደገና ስቅስቅ ብላ አለቀሰች::
በቅንነት ፈራጅ ሕዝብ እንዳይጐዳ:
ማን ይሆን ትልቅ ሰው ሃቅን የተረዳ :?:

Image
http://www.cyberethiopia.com/warka5/vie ... hp?t=26693
የጃማ ጦስኝ
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 338
Joined: Sun Sep 02, 2007 12:02 am
Location: ጃማ

Postby የጃማ ጦስኝ » Sat Feb 14, 2009 1:45 pm

ሰላም ወገኖች የት ገባችሁ ? የበላችሁ ጅብ አልጮህ አለኮ አቦ ;; ለማንኛውም መልካም የፍቅር ሰንበት ለሁላችሁ


ፍቅርን ላንድ ቀን አውርቶ;
ሻምፓኝ አበባን ተራጭቶ
ይውላል አሉ ሰው ሞኝ;
እኔስ እሱን አያርግኝ::
በቅንነት ፈራጅ ሕዝብ እንዳይጐዳ:
ማን ይሆን ትልቅ ሰው ሃቅን የተረዳ :?:

Image
http://www.cyberethiopia.com/warka5/vie ... hp?t=26693
የጃማ ጦስኝ
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 338
Joined: Sun Sep 02, 2007 12:02 am
Location: ጃማ

Postby የጃማ ጦስኝ » Mon Feb 16, 2009 1:19 pm

ሰላም ያገር ልጆች የት ገባችሁ ድምጻችሁን ለማሰማት ጊዜ ጠፋ ? መቸም ያው የዘመኑ ኑሮ እያባተለን መሆን አለበት ::


እጣ ስንጣጣል

እጣዬ ሲወጣ የማይረባ አንስቸ;
በኢትዮጵያዊነቴም ይሉኝታ ፈርቸ;
ወይ የማይበላ ወይ የማይጠጣ;
ግራ የሚያጋባ ከሁሉም የወጣ;
የድህነት የለው ወይ የሀብታም ሽታ
ዝብርቅርቅ ያለበት እጅግ የተምታታ
እጂ እጂ ያለ ነገር የነካው ሰው ሁሉ;
ብሞትም አልቀምሰው ያሉትን ይበሉ!!
ልዋል ጾሜን ልደር አልነካም በጭራሽ;
በሱ አልሰደብም በጣለው ቁርስራሽ;;
ድሀው ድሀ ብሎ ድሀውን ሰደበው;
ድሀው ተሰዳቢ ድሀውን ታዝቦ;
ዝም ብሎ እያየው ሲሄድ ቂጡን ገልቦ;
እሱ እንዲህ የረሳው ለካስ ድህነቱን
ያረጋት ጥብቆ አጣብቃው ደረቱን;
የለበሰ መስሎት ከግር እስከራሱ;
ሰዎች ሲስቁበት እሱን እያነሱ;
ያወደሱት መስሎት የድሆቹ አለቃ;
ድሆች በማስለቀስ በሜዳ ሲብቃቃ;
በቅንነት ፈራጅ ሕዝብ እንዳይጐዳ:
ማን ይሆን ትልቅ ሰው ሃቅን የተረዳ :?:

Image
http://www.cyberethiopia.com/warka5/vie ... hp?t=26693
የጃማ ጦስኝ
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 338
Joined: Sun Sep 02, 2007 12:02 am
Location: ጃማ

Postby የጃማ ጦስኝ » Mon Feb 16, 2009 1:21 pm

ለካስ የዕውቀት መምህር አንቱ የተባለው
ከሁሉም የከፋ ደካማ ጎን አለው
በቅንነት ፈራጅ ሕዝብ እንዳይጐዳ:
ማን ይሆን ትልቅ ሰው ሃቅን የተረዳ :?:

Image
http://www.cyberethiopia.com/warka5/vie ... hp?t=26693
የጃማ ጦስኝ
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 338
Joined: Sun Sep 02, 2007 12:02 am
Location: ጃማ

Postby ድርሰት » Tue Feb 17, 2009 11:27 pm

<<<<<<<<<<<<>>>>>>>>>>>>>>
Last edited by ድርሰት on Thu Apr 16, 2009 1:06 pm, edited 1 time in total.
There is always a small beginning for every thing that we should not despise!!!!!!!!!!!
ድርሰት
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 101
Joined: Mon Jan 19, 2004 6:16 pm
Location: united states

Postby የጃማ ጦስኝ » Fri Feb 20, 2009 3:54 pm

ሰላም ያገር ልጆች እንደምን አላችሁ ::

እኔምለው በቃ እናንተ ካልጎተጎቷችሁ ብቅ አትሉም ማለት ነው ? እኔስ በጣም እያሳዘናችሁኝ ነው :: ዝምድና በልመና ሆነኮ::

ለነገሩ የዛሬ ጊዜ ዝምድናም እሱስ ተለምኖም አልሰነበተም እኔ መቸም ያው የጥንት ሰው ሆኘ ነው እንጂ ምን ይደረግ እስኪ ለማንኛውን አንጠፋፋ::
በቅንነት ፈራጅ ሕዝብ እንዳይጐዳ:
ማን ይሆን ትልቅ ሰው ሃቅን የተረዳ :?:

Image
http://www.cyberethiopia.com/warka5/vie ... hp?t=26693
የጃማ ጦስኝ
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 338
Joined: Sun Sep 02, 2007 12:02 am
Location: ጃማ

Postby ድርሰት » Wed Feb 25, 2009 6:46 pm

))))))))))))))))))))))))))((((((((((((((((((((((((((((((((
Last edited by ድርሰት on Thu Apr 16, 2009 1:05 pm, edited 1 time in total.
There is always a small beginning for every thing that we should not despise!!!!!!!!!!!
ድርሰት
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 101
Joined: Mon Jan 19, 2004 6:16 pm
Location: united states

Postby የጃማ ጦስኝ » Thu Feb 26, 2009 4:58 pm

ሰላም ለዚህ ቤት ታዳሚዎች እንደምን ከረማችሁ :; እስኪ ወዴ ልብ ወለዳችን ልመልሳችሁ::

'' ሀንዬ ይኸ ስራሽ የማይገባ ነገር ነው :: ምንም የሚያስለቅስ ነገር የለም ;ምነው አንቺ ብቻ አይደለሽም ያለአባት ልጅ ወልደሽ የምታሳድጊው ; ምን አድስ ነገር አድርገሽ እራስሽን ያስጎዳሻል:: ማን ያውቃል ወይ አንድ ቀን ይገባውና ጥፋቱ ይመለሳል:: የእግዜር ነገር አይታወቅም ::'' አለቻት; ሀና ዓይኗን ከልጇ ላይ እንደተከለች '' አይ አስትዬ ምነው አዲስ ነገር በሆነማ እኔም ሆድ አይብሰኝም ነበር :: ግን እኔም ልጀም አንድ መሆናችን እየገረመኝ ነው'' አለችና ታሪኳን እንዲህ ስትል አጫዎተቻት:-

እናቴ የወሎ ሰው ነበረች ; ቤተሰቦቿ ችግረኞች በመሆናቸው እንደአካባቢው ልጆች ትዳር ይዞ ለመኖር እድል አላጋጠማትም ነበር; አቅም ስታወጣ ከነጋዴ ጋር ጠፍታ አዲስ አበባ ገባች; መቸም አዲስ አበባ ደግ ሀገር ነው አንዲት የወሎ /ያገሯን ሴት / አግኝታ እሳቸውጋ ሀገሩን እስክትለምድ ከተቀመጠች በኍላ ስራ አፈላልገው እሰው ቤት ተቀጠረች; የተቀጠረችበት ቤት ባለቤት ጎረምሳ ወንድማቸው እናቴን ደፈራትና እናቴ አረገዘች; እናቴም ልጀ ነበረችና ምንም ሳትጠረጥር ደፋ ቀና እያለች ስራዋን ስትስራ እርግዝናው እየገፋ መጣና አሰሪዎቿ ከቤት አባረሯት እሷም ለጎረምሳው እርግዝናው የሱ እንደሆነና ሌላ ሰው እንደማታውቅ ስትነግረው እንደት ተደፈርኩ ብሎ እናቴን ሁለተኛ እንዲህ አይነት ወሬ ስታወራ ቢሰማ እንደሚገላት አስጠንቅቆ ነግሮ አባረራት እናቴም ከመሞት መሰንበትን መርጣ ለማንም ሳትተነፍስ የቀን ስራ እየሰራች እኔን እስከምትወልድ እኛኑ ያገሯን ሴት ተጠግታ ቆየች:: ከወለደችኝም ወዲህ ለድሀ ልጅ መወለድስ ማን ቁም ነገር ሊለው ያባትን ነገር እኔን ለሴትየዋ የክርስትና ልጂ ሰጠችኝ : እሳቸውም መሀን ስለነበሩ እናቴን እና እኔን እንደልጅ አድርገው እናቴ የቀን ስራ እየሰራች እዛው ኖረች :: እኔም ማደግ አይቀርምና እንደምንም አደግሁ::

አንድ ቀን እናቴ ሰራ ውላ ስትመጣ የክርስትና እናቴ እንድ የምስራች ነገሩን;- ''ለሀና ጥሩ ስራ አገኘሁላት ጥሩ የተከበሩ ሰዎች ናቸው :: የተከበሩ የመንግስት ሰራተኞች በራቸው በዘበኛ የሚጠበቅ መቸም እግዜር አያልቅበት'':: አሏት እናት እንዴት እንደደነገጠች እስካሁን አልረሳውም::#
'' አይ ምነው አንቺ ደግሞ ምን ያስደነግጥሻል እሷም እኮ እንግዲህ ልጅ አይደለችም ለምን ነው እቤት ከኔ ጋር መዋሏ ትንሽም ቢሆን እንዳቅሟ ትስራና ታግዝሽ ምን ትሆናለች ብለሽ ነው አትሟሟ: '' አሏት::
''የት ነው እሱ እማማ ? ደግሞስ አሁን እሷ ምን ስራ ትሰራለች ብለው ነው?''
'' እንዳቅሟ ነው የተገኘው ስራውም :: ከባድም አይደለም ልጅ መጠበቅ ነው::''
''እስዎ ካሉ እኔም ምን እላለሁ እማማ''
'' አዎ ግድ የለሽም ማን ያውቃል እንጀራ ይወጣላታል '' አሉና የተከበሩ ጥሩ ሰዎች ቤት ልጅ ጠባቂተት ስራ ገባሁ; ባለበቶቹም ሆኑ ልጆቹ ወደዱኝ ከሰዎቹ ጋር አምስት አመት ከቆየሁ በኍላ እናቴንም ለቤት ሰራተኝነት ቀጠሯት:: የሚገርመው ነገር ሰዎቹ እናቴ እንደገባች ብዙም ሳይቆዬ የእንግሎዝ አምባሳደር ሆነው ተሾሙና ወደ እንግሊዝ ሲመጡ እናቴን አስፈቅደው እኔን እንግሊዝ ሀገር ይዘው ሲመጡ ለእናቴም የምትጽናናበት ትንሽ ገዘብ ሰጧት የዛን ቀን ያለቀሰችውን እንባ ሳስበው በህይወት እያለሁ አልረሳውም ; የክርስትና እናቴም በእድሌ በደሰቱም ከአይናቸው በመራቄ የእናቴን ያህል አዘኑ :: የዝግጂቱ ቀን ደረሰና ሰዎቹ እቃቸውን እና ቤተሰቡን በሙሉ አግበስብሰው እንግሊዝ ገባን::
በቅንነት ፈራጅ ሕዝብ እንዳይጐዳ:
ማን ይሆን ትልቅ ሰው ሃቅን የተረዳ :?:

Image
http://www.cyberethiopia.com/warka5/vie ... hp?t=26693
የጃማ ጦስኝ
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 338
Joined: Sun Sep 02, 2007 12:02 am
Location: ጃማ

ከላይ እስከ ታች

Postby ወልዲያ » Sun Mar 01, 2009 10:09 pm

ሠላም ለቤቱ!


ሉም ነገር ያምራል ከላይ እሥከ ታች:
ግም አሥታወሥሽኝ - ትረካው - የማይሠለች:
ሴ ላይ ብቅ በይ - ቡና - ልጋብዝሽ::መልካም ሰንበት
ወልዲያ - የጁ
ወልዲያ
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 679
Joined: Tue Apr 17, 2007 11:55 am
Location: የጁ - ወሎ

Postby ድርሰት » Tue Mar 03, 2009 2:15 pm

<><><><<>>>>>>>>>>>>>>>>>>>>>>>>>
Last edited by ድርሰት on Thu Apr 16, 2009 1:06 pm, edited 1 time in total.
There is always a small beginning for every thing that we should not despise!!!!!!!!!!!
ድርሰት
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 101
Joined: Mon Jan 19, 2004 6:16 pm
Location: united states

Postby የጃማ ጦስኝ » Tue Mar 03, 2009 3:45 pm

ሆሆሆሆሆይይይይይይይይ

የሚገርም ግብዣ ነው ያውም በሁዳዴ ጾም እንዲህ ያለውን ነገር መቀበል ይከብዳል::

ልለምን ተንበርክኬ;
እንዲሰጠኝ በልኬ::
እቃውን ለመቀበል;
ልዘጋጂ ሳልታለል::
ወርቅ መስሎ ነሀሱ;
ለገበያ መቅረቡን አትርሱ::
ወርቁን ጠጋ ወደሳቱ;
እንዲለይ ማንነቱ
ታዲያ ያን ጊዜ የጋባዡም ሆነ የተጋባዡ ማንነት ይለያል ለማንኛውም እስኪ ጊዜ ይፍታው::
ወንድሜ ድርሰት ሰለግብዣው እናመሰግናለን::
በቅንነት ፈራጅ ሕዝብ እንዳይጐዳ:
ማን ይሆን ትልቅ ሰው ሃቅን የተረዳ :?:

Image
http://www.cyberethiopia.com/warka5/vie ... hp?t=26693
የጃማ ጦስኝ
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 338
Joined: Sun Sep 02, 2007 12:02 am
Location: ጃማ

PreviousNext

Return to Warka Intimate - ዋርካ ፍቅር

Who is online

Users browsing this forum: No registered users and 4 guests