ለ ENGEDA1967 ከኢየሩሳሌም...ይሁዲዎች የሚሰሩትን እይ

The Love Forum (love, relationship) (የኔ ቆንጆ እንተዋወቅ :-)

ለ ENGEDA1967 ከኢየሩሳሌም...ይሁዲዎች የሚሰሩትን እይ

Postby 1234ጭልጥ » Mon Apr 27, 2009 8:28 pm

ይሁዲ ነኝ ባዩ ኢትዮጵያዊው በጥቁርነቱ በነጭ ይሁዲዎች ጥቃት ሲደርስበት...............ምን ትላለህ እንገዳ ?

http://ecadforum.com/blog/2009/04/22/is ... trackback/

ተርጉምና ንገረን እስኪ
YOU WILL NOT LIVE FOR EVER. HAVE YOU EVER ASKED YOURSELF HOW MANY MORE YEARS YOU GOT LEFT ?
1234ጭልጥ
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 119
Joined: Fri Mar 20, 2009 5:56 am

Postby ጩጉዳ » Tue Apr 28, 2009 12:46 pm

በጣም ያሳዝናል:: ኤሥራኤሎች በእግዚአብሄር ቃል መሰረት ለዘለዐለም ተባርከዋል ነቀፋ የለለባቸው የተስፋ ምድር የወረሱ ብጹአን ናቸው እየተባለላቸው ሚስኪን ያገሬ ሕዝብ ኦርቶዶክሱ ሁሉ ሀይማኖቱን እየቀየረ ወድዛች ምድር ጎረፈ:: የጠበቃቸው ግን ይህን የመሳሰለ ባርባሪክ ድርጊት ነው::

ኤስራኤሎች በነሱ ላይ የሆነውን ሆሊኮስት እንኳን ረስተውት በገዛ ወንድማቸው ጂው ላይ እንዲህ ዐይነት አሰቃቂ ድርጊት መፈጸማቸው እጅግ ያሳዝናል::

እኔ ራሴ ለነሱ ያለኝ አመለካከትና ድጋፍ ከፍተኛ ነበር:: ከእንግዲህ ግን በጥንቃቄ እንዳያቸው እገደዳለሁ::
መታገስንና መቻልን የመሰለ ብቀላ የለም ::
ጩጉዳ
ውሃ አጠጪ
ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1267
Joined: Mon Jan 31, 2005 6:40 am
Location: Studio City, Wilson Republic

ኢትዮጲያዊው በእስራኤል

Postby ቆንጂት08 » Wed Apr 29, 2009 10:34 am

ይህ ነገር የተፈጸመው በኦጉስት2007 ነው እኔ ያየሁት አሁን እናንተ በላካችሑት ሰአት ነው .ምን እንደነበረ ከምን እንደደረሰ ለጊዜው አላቅም ለማንኛውም ሁኔታው በጣም ያሳዝናል የልጁን ሁኔታና የፍርዱ ሁኔታ ከምን እንድድረሰ አጣርቼ ለማወቅ እሞክራለሁ .በዜናው እንደተረጎምኩት የሚለው ኢትዮጵያዊው ፓሊስና በዛ ምሽት ከሌሊቱ 2 ሰአት በሲቪል ልብስ ሲዘዋወር እንደነበር የተዝዋወረበት ቦታ ሰካራሞችና ሀሽሽ ተጠቃሚዎች ያሉበት ሲሆን በግሩፕ ተሰብስበው በመጠጣት ያሉ ጎረምሶች መሀል አንዱ ጋዜጣ አበሻው ላይ ይወረውርበታል አበሻውም ለምን ወረወርክ ብኝ በማለት ሲጠጋቸው ተሰብስበው ደበደቡት ፌንት ሆኖ ከመውደቁም በላይ የጭንቅላቱ አጥንት ተስብሯል ከጀርባውም አጥንት ተሰብሯል ለገሩ በስራኤል ፖሊሲ ዘረኝነት ፍጹም አይደገፍም ሆኖም ግን አልፎ አልፎ ዘርኝነት በግለሰቦች ዘንድ መከሰቱ አይቀርም .በዘረኝነት አበሻ የበደለ ሰው ባገሪቱ ህግ ፊት እየቀርቡ ከስራ የተባረሩ የግንዘብና አስራት ቅጣት የሚደርስባቸው ነጮች ብዙ ናቸው ማወቅ የሚገባው ግን የዛኑ ያህል ለኢትዮጵያ ይሁዲዎች ፍቅርና አቅብሮት ያላቸው እስራኤላውያኖች ብዙ ናቸው በኑሮ ደርጃና ትምህርት ከፍተኛ ደርጃ የደረሱ ከንጮች ኑሮ በልጠው የሚገኙ ኢትዮጵያዊያኖች ቁጥር አነስተኛ አደለም በኔ አስተሳሰብ በፈለገው ሀይማኖት ቢያምንም ሰው ኢትዮጲ ያዊ ምንግዜም ኢቶጵያዊ ነው.....
ቆንጂት08
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 887
Joined: Wed Dec 19, 2007 3:49 pm

Postby ENGEDA1967 » Wed Apr 29, 2009 6:38 pm

ሰላም እንደምን አላችሁ
ትርጉሙን በሚገባ ቆንጂት አስቀምጣዋለች የምጨምረው ነገር ቢኖር ይህ በዘረኞች ይሁን በሰካራሞች ጥቃት የደረሰበት እትዮፒያዊ ፖሊስ ስራውን መቀጠሉን ነው
እኛ ይሁዳውያን ብዙ ስቃይና መከራ አሳልፈናል አሁንም በአንዳንድ ሰካራሞች ወይም ዘረኞች ጥቃት እየደረሰብን ነው ግንንንንን //// አሁን ያለንበት ሀገራችን ህግና ፍትህ ከሁሉም በላይ የሆነበት ስለሆነ በቀላሉ እየተቋቋምነው ከሁሉም እኩል እየሆን ነው በነገራችን ላይ ከየመን የመጡ ይሁዳውያንም ከሩሲያ የመጡትም ተመሳሳይ ችግሮች አሉባቸው እኛ ግን ጥቁሮች በመሆናችን ብቻ ነገሩ ይገናል
እኔ በበኩሌ እስካሁን የማይረሳኝ ተወልጄ ያደኩባት ሀገሬ ህዝብ የበደለኝን ነው . እንዴ ? እበላለሁ እንዴ እንዴት ይሆን ሰው የምበላ ? እያልኩ ራሴን እስከመጠየቅ እደርስ ነበር የሚገርመው ነገር ውትድርና ሳለሁ ሁለት እንደወንድም የምንተያይ ጓደኞች ነበሩን ከሁለቱ አንዱ የቀጥቃጭ ልጅ ቡዳ ብሎ ሌላውን ሲሳደብ ሰምቼ ታዝቤ አልፌዋለሁ
እንግዳ ከእየሩሳሌም
ENGEDA1967
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 475
Joined: Fri Aug 27, 2004 11:09 pm
Location: united states

Postby ifa » Wed Apr 29, 2009 10:52 pm

ይቅርታ እንግዳ በጣም ለማወቅ ጉዋጉቼ ነው...የእትዮጵያ ህዝብ አንተንና ሌሎች ይሁዲወችን ለይቶ በድላል ወይስ ባገራችን በተለያዩ አካባቢዎች የሚደርሰውን በደል ባጠቃላይ ነው የምታወራው...ማለትም በይሁዲነትህ የደረሰብህን ነው ወይስ? እባክህ አብራራልኝ
Ethiopians are: " THE BLAMELESS RACE "

Homer (Greek poet of the 8th century B.C.)
ifa
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 135
Joined: Mon Jul 09, 2007 6:24 am

Postby 1234ጭልጥ » Fri May 01, 2009 9:02 pm

ifa wrote:ይቅርታ እንግዳ በጣም ለማወቅ ጉዋጉቼ ነው...የእትዮጵያ ህዝብ አንተንና ሌሎች ይሁዲወችን ለይቶ በድላል ወይስ ባገራችን በተለያዩ አካባቢዎች የሚደርሰውን በደል ባጠቃላይ ነው የምታወራው...ማለትም በይሁዲነትህ የደረሰብህን ነው ወይስ? እባክህ አብራራልኝ

ifa ምን ባክህ ENGEDA1967 ደርግ ከገበሬ ማህበር ሚሊሺያ ጋር ኤርትራ አዝምቶት ቡዳ ጠይብ እየተባባሉ የሚሳደቡት ቅስሙን ሰብሮታል :: በዚህም ድፍን የኢትዮጵያን ሕዝብ ተቀይሟል::

ፈላሻ ስለሆነ ቡዳ/ጠይብ የሚለው ቃል ያስበረግገዋል :: ያልተረዳው ግን በኢትዮጵያ የማያውቁት ወይም ካካባቢው ውጪ የመጣ ሰው ሁሉ ቡዳ ነው::እንደ ENGEDA1967 ቢሆን ድፍን ጎጃምና ሞረቴ ሀገሩን ባኮረፈ ነበር :: ጓደኛሞች እንኳን አንዱ ሲበላ ሌላው ያየው እንደሆን አትየኝ በቡዳ ትበላኛለህ ይላል:: የማያውቁት እንግዳ ሲመጣ ተሯሩጦ ህጻናትን ከዓይን ለመጠበቅ መደበቅ/መሸፈን ልማድ ነው ::

ENGEDA1967 ግን ምህረትየለሽ የመሀይም ሚሊሺያ ቡዳ/ጠይብ እየተባባሉ መዘላለፍ የማይሽር የህሊና ጠባሳ ስለሰጠው እስካሁን የቡዳ ነገር ያንገሸግሸዋል :: በዚህም እትብቱ የተቀበረባትን ሀገሩን አኩርፏል ::

የኔ ምክር ለENGEDA1967 ለቀቅ አድርገው::

አንደኛ በዚህ ነገር የሚያምነው መሀይሙ ነው::

ሁለተኛ በዚህ መሀይም ባህል የማያውቁት ሁሉ ቡዳ ነው ስለዚህ ባንተ ብቻ የመጣ አይደለም::

ሶስተኛ ጎጃሜዎች እንደሚሉት "ጎጃሜ ቡዳ ነው ብሎ ያለሽ ማነው : ሰውን ሰው ሲበላ የታባሽ አይተሽ ነው" ከነሱ ተማርና ይህን የሚያስጨንቅህን አስተሳሰብ ከአዕምሮህ አስወጣ::
YOU WILL NOT LIVE FOR EVER. HAVE YOU EVER ASKED YOURSELF HOW MANY MORE YEARS YOU GOT LEFT ?
1234ጭልጥ
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 119
Joined: Fri Mar 20, 2009 5:56 am

Postby ifa » Fri May 01, 2009 10:47 pm

ዋይ ወንድማለም "ቡዳ" ተብሎ መሰደብ እኮ ያረጀ ያፈጀ ነው ...ጥንት ያልተማሩ/ያላወቁ በሙሉ....ጎጃሜ እና ሎላውም የእትዮጵያ ክፍል ቡዳ ነውአሉ ከዚያም ሞረቴዋች ቡዳ ናቸው እርግጠኛ አይደሉሁም በሁሉም አካባቢ ደግሞ ቀጥቃጭ በሙሉ ቡዳ ነው ይባላል...እና ይህ የተረሳ ህዝባችን ሳያውቅ የሚናገረው እንጅ ሆን ተብሎ ፈላሻን ለማሳዘን አይደለም....የትም አካባቢ ስትሄድ አዲስ ከሆንክ ወይ ራቅ ካለ አካባቢ ከመጣህ ቡዳ ትሆናለህ ሰለሚባል በተለይ ህፃናትን እንዳታይ ትልቅ ጥንቃቄ የደረጋል
ምሳሌ ልንገርህ...አባቴ ጎጃሜ ነው ...የተውለደውም ያደገውም...እና ከ40 አመታት ቦሀላ ህይወት በሲዳሞ ክ/ሀገር ውስጥ በነገሌ ቦረና አካባቢ ሴትል እንዲያደግ ታስገድድና ወልዶ ከብሮ አገሬውን መስሎ የአገሩን አናናር ተላምዶ ከህዝቡ ተፋቂሮ ሲኖር...ሁሉም አባብዬ ጋሽዬ እያለው አገር አስታራቕ ሽማግሌ ሆኖ ተዋልዶ ተጋብቶ ሲኖር .......ከእለታት አንድ ቀን ወንድሙ(የጎጃምን መሬ ት ለቆ የማያውቅ )አባቴ ቢጠፋበት አፈላልጎ ነገሌ ቦረና ከነጠባብ ሱረው ብቕ ቢል ሰፈሩ ውስጥ ውር የሚል ህጻን ጠፋ ሁሉም ሴት እኛ ቤት ቡና ሲጠራ ህጻን በጀርባው አልያም በደረቱ አስቀምጦ የሚያጠባው ሁሉ ክትት አለ ቤቱ .....ለምን ቢባል የአባቴ ወንድም አጎቴ ህጻናቱን እንዳያይና እንዳይታመሙ በመስጋት ነው...እና ታዲያ አጎቴ ቡዳ ከሆነ አባቴስ ቡዳ መሆን የለበትም....የአካባቢው ሰው አባቴን እንደእንግዳ ማየት ካቆመ ቆይት ነበር.....እና የትም ብትህድ አማራም ትግሬም ጉራጌ ኦሮሞ ብትሆን በእንግድነትህ ሁሉም ይፈራሀል ...በተልይ ትንንሽ የገጠሪቱ እትዮጵያ ውስጥ...
እና እንግዳ ያንተን ፐርሰናል አታድርገው ...የእትዮፕያ ህዝብ የሚዋደድ የሚከባበር(ከፖለቲካ ጥቅመኞች ውጭ) ለወገኑ ደራሽ ነውና ...እንደዚህ አትማረር ወንድም

ደህና ሁን እንግዲህ
አይፋ
Ethiopians are: " THE BLAMELESS RACE "

Homer (Greek poet of the 8th century B.C.)
ifa
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 135
Joined: Mon Jul 09, 2007 6:24 am

Postby ሾተል » Fri May 01, 2009 11:17 pm

123ጭልጥና ኢፋ..

ከላይ የጻፋችሁትን መላምት አይቼ ግርም አለኝ::ምነው ኢትዮዽያ ነው ተወልዳችሁ ያደጋችሁት ወይስ ለላ አገር ተወልዳችሁ የተዛባ ነገር ስለኢትዮዽያ ተነግሯችሁ አመናችሁ?እባካችን እውነትን አንደባብቅ::እውነት ብናወራ ምንም አይለንም::ከእውነት ነው ሰው የሚማረው::እየዋሹ መማማርና ልዩነትን ማጥበብ አይቻልም::

አገራችን ያሉት ብሄረሰቦች ሳይናናቁ በፍቅር አንድ ሆነው እንደኖሩ አደረጋችሁዋቸው እኮ ጃል?

አሁንም ድረስ እንደኛ አገር ያለ ዘረኛና የራሱን ህብረተሰብ የሚንቅ አልፎም የለላ አፍሪካ አገሮችን የሚንቅ አገር ይኖር ይሆን?

እንዴ ኢፋ እስቲ አንተ ከጋምቤላ የተወለደች የቆዳዋ ቀለም በጣም የጠቆረ ለአንድ ቀን አብረኽ ለማደር እራስኽን አሳልፈኽ ትሰጣለኽ?እሱ ይቅርና አንተ የአዲስ አበባ ልጅ ከሆንክ ከጎጃም ጎንደር ወሎ የመጣች አክሰንት እንደጉድ ያላት የአለም ቆንጆ የሆነች ልጅ ለሴት ጉዋደኝነት ትይዛታለኽ?ይቺ ፋራ አለሌ ገጠር ፋራ ወዘተ እያልክ አይደለም እንዴ የምትንቃት?ስሜት ከወጠረኽ ጨለማን ተከናንበኽ ነው የምታወጣት....ወንድ ከሆነ ግን ከንቀትኽም አልፎ ድብን አድርገኽ ጸድበዋለኽ እንጂ ጉዋደኛ አታደርገውም::

ወደ እንግዳ ወዳለው ብመጣ.....ቅማንት ወይጦ ሺናሻ ፈላሻ የሚባሉት ያገራችን ብሄረሰቦች ፋቂ ቀጥቃጭ ቡዳ ሰይጣን ሳቢ ወዘተ እየተባሉ አይደለም እንዴ በህብረተሰቡ የሚሰደቡትና የሚገለሉት?ጎጃመ ያልሆነ ሰው አንድ ሰው ጎጃሜ ነኝ ብሎ ቢተዋወቅ መጀመርያ ያ ጎጃመ ያልሆነው ሰው በአይምሮው ምንድነው የሚመጣው?"ቡዳ" አይደለም እንዴ?ኢፋ መልሱን እራስኽ መለስከው እኮ::አባትኽ በመቆየት ተላመዱና ጎጃመነታቸው ተረሳ ነገር ግን አካባቢው የማያውቀው ጎጃመ ከመጣ ለህብረተሰቡ ጎጃሜ ቡዳ ነው ማለት ነው::ታድያ ያ ዘመዳችሁን ያካባቢው ሰዎች ሲፈሩት ሲንቁት ልጃቸውን እንዳያያቸው ሲደብቁበት በዛች ጊዘ ምን ይሰማዋል ብለን አስበን ይሆን?በገዛ አገሩ በእምዬ ኢትዮዽያ መሬት ጎጃሜ ስለሆነ ብቻ ሰዎች ቡዳ ነው ብለው ልጃቸውን ሲደብቁበት::

እንግዳ እንደዚህ ያለ ነገር ካንዴም ሚሊየን ጊዜ ደርሶበት ቢሆንስ?እንደዛ ህብረተሰቡ አግሎት ያደገ ቢሆንስ?ፈላሻዎች ሆኑ ሌሎች ቡዳ ፋቂ ወዘተ የሚባሉትና የተገለሉት እኮ ለላ አገር ሄደው አይደለም እዛው ተወልደው ባደጉበት ጎንደር ወይም ጎጃም ውስጥ ነው ::

እና ለመፍረድና ልክ ተፋቅረን እንዳደግንና እንደኖርን አንዋሽ...ባይሆን ለእርቅና አንድ ለመሆን ይጠቅመን ዘንድ ስህተታችንን አውቀን ግልጥልጥ አድርገን አውጥተን ተወያይተን ይቅር መባባል ካለብን ይቅር ተባብለን መጪው ትውልድን እንደኛ እንዳይሆኑ አስተምረን ልዩነታችንን አጥብበን አንድ ለመሆን መጣር እንጂ የተደረገን ነገር አልተደረገም እያልን እየዋሸን የተበደሉትን ሰዎች ወይም ህብረተሰቦች ድሮም በህብረተሰባቸው ተበድለዋን አሁንም በደላቸውን ሸምጥጠን እየዋሸን አናስቆጣቸው::

እድሜ ለደርግ ትንሽ ይሄንን ነገር አርግቦት ነበር::ቢሆንም በልባችን ውስጥ ያ መናናቅ ነበር...ህጉን ፈርተን በስውር እናደርገው ነበር እንጂ::

እኛ አንድ ሆነን ተፋቅረን ኖረን አናውቅም::በዘረኝነትና መናናቅ ያደግን ዘረኞች ነን::ስትናናቅ ባታድግ ኖሮ አዳሜ በአፍሪካነትህና በጥቁርነትኽ አምነኽ ሁሉንም አፍሪካኖች እንደአንድ አድርገኽ ባየኽ ነበር::እስቲ ናይጄርያ አግብታ የፈታች ልጅ ገቱ ኖሮኽ አግባት?እስቲ ጋምቢያ አግባና ኑር?

ብቻ ይቅር::ስለጉዳችን ብዙ ማለት ይቻላል::ለመማማር የተፈጠረ ትውልድ ስላይደል ስህተቱ ሲነገረው ያዙኝ ልቀቁኝ ይላል::

እነ እንግዳ የሚለውን ሙሉ ለሙሉ እቀበላለሁ::ጥላቻ ቢኖርበትም በፈላሻነቱ በደል ደርሶበት አድጎ ይሆናልና ........

ሾተል ነን...ልቦና ይስጠን....ለእውነት ያቁመን
እሰይ ተመስጌን አምላኬ ለካስ በክብርነቴ እራሴን ሆኜ እኔነቴን ፈልጌ አግኝቼዋለሁ !?
ሾተል
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 9644
Joined: Thu Jan 13, 2005 9:42 pm
Location: Vienna-Austria

Postby ተድላ ሀይሉ » Sat May 02, 2009 2:44 am

---
Last edited by ተድላ ሀይሉ on Sat May 02, 2009 2:49 am, edited 1 time in total.
ተድላ ሀይሉ
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 4903
Joined: Fri Mar 17, 2006 2:45 pm
Location: ኢትዮጵያ

Postby ተድላ ሀይሉ » Sat May 02, 2009 2:47 am

ሾተል wrote:123ጭልጥና ኢፋ..

ሾተል እውነት ብለሃል :: ነገር ግን በቀይ ያቀለምኩትን ደግመህ ራስህ ለመጻፍህ አንብበው :: እንዲህ ዓይነቱ መናናቅ በኢትዮጵያ ውስጥ ብቻ ነው ያለው ? በሌሎች የአፍሪቃም ሆነ የዓለም ክፍሎች አልነበረም : አሁንም የለም ብለህ አፍህን ሞልተህ መናገር ትችላለህ ? በነካ እጅህ ሁሉንም ማዬትና 'አሃ እንዲህ ያለው አስተሣሠብ ለካ እዚያም አለ !' ብለህ ብትፈርድ ይሻላል ::

ያም ሆነ ይህ ግን ከላይ ያነሣሁልህ ነጥብ ኢትዮጵያ ውስጥ ሰውን በተወለደበት አካባቢ : ወይም በዘሩ ወይም በዕምነቱ ወይም በቋንቋው ወይም በሙያው ወይም በፆታው ወዘተርፈ ምክንያት ማግለሉና ዝቅ አድርጎ ማዬቱ ትክክል ያለመሆኑን ሃቅ አይሽረውም ::

ተድላ
ተድላ ሀይሉ
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 4903
Joined: Fri Mar 17, 2006 2:45 pm
Location: ኢትዮጵያ

Postby ሾተል » Sat May 02, 2009 3:20 am

ተድላ ሀይሉ wrote:
ሾተል wrote:123ጭልጥና ኢፋ..

ከላይ የጻፋችሁትን መላምት አይቼ ግርም አለኝ::ምነው ኢትዮዽያ ነው ተወልዳችሁ ያደጋችሁት ወይስ ለላ አገር ተወልዳችሁ የተዛባ ነገር ስለኢትዮዽያ ተነግሯችሁ አመናችሁ?እባካችን እውነትን አንደባብቅ::እውነት ብናወራ ምንም አይለንም::ከእውነት ነው ሰው የሚማረው::እየዋሹ መማማርና ልዩነትን ማጥበብ አይቻልም::

አገራችን ያሉት ብሄረሰቦች ሳይናናቁ በፍቅር አንድ ሆነው እንደኖሩ አደረጋችሁዋቸው እኮ ጃል?

አሁንም ድረስ እንደኛ አገር ያለ ዘረኛና የራሱን ህብረተሰብ የሚንቅ አልፎም የለላ አፍሪካ አገሮችን የሚንቅ አገር ይኖር ይሆን?
እኛሾተል እውነት ብለሃል :: ነገር ግን በቀይ ያቀለምኩትን ደግመህ ራስህ ለመጻፍህ አንብበው :: እንዲህ ዓይነቱ መናናቅ በኢትዮጵያ ውስጥ ብቻ ነው ያለው ? በሌሎች የአፍሪቃም ሆነ የዓለም ክፍሎች አልነበረም : አሁንም የለም ብለህ አፍህን ሞልተህ መናገር ትችላለህ ? በነካ እጅህ ሁሉንም ማዬትና 'አሃ እንዲህ ያለው አስተሣሠብ ለካ እዚያም አለ !' ብለህ ብትፈርድ ይሻላል ::

ያም ሆነ ይህ ግን ከላይ ያነሣሁልህ ነጥብ ኢትዮጵያ ውስጥ ሰውን በተወለደበት አካባቢ : ወይም በዘሩ ወይም በዕምነቱ ወይም በቋንቋው ወይም በሙያው ወይም በፆታው ወዘተርፈ ምክንያት ማግለሉና ዝቅ አድርጎ ማዬቱ ትክክል ያለመሆኑን ሃቅ አይሽረውም ::

ተድላ

ሰላም ተድላ::

ከላይ በቀይ ቀለም ያቀለምከውን እነ የጻፍኩትን ደግመኽ አንብበው:;እርግጠኛ ሆኜ አለ ሳይሆን ያልኩት ይኖር ይሆን?ነው::ያ ማለት ባለም አንደኛ ዘረኞች ለመሆናችን ወይም አለመሆናችን እርግጠኛ ስላልሆንኩ ነው ከጥያቄ ጋር ይኖር ይሆን ያልኩት::

ዘረኝነትና መናናቅማ በያገሩ አለ::ግን እኛ ዘረኝነታችንን አለማወቃችን ነው የምናደደው::አዲስ የመጣ ቋንቋ አብረን በልተን አብረን ጠጥተን ተዋልደን የሚባለው ቋንቋ ነው ሊገባኝ ያልቻለው::ኢትዮዽያ ተወልጄ ኢትዮድያ ያደኩ ሁሉ አልመስል አለኝ ውሸታችን:;ወላሞ ኦሮሞ ቁላ ቆራጭ ጉጂ ቡዳ ጎጃሜ ቆማጣ አማራ ጠባሳ ወላሞ ፋቂ ሺናሻ ወዘተ እያለ ተናንቆ በግልጽም ሆነ በድብቅ እየተሳደበ አንዱ አንዱን እያገለለና እየናቀ ኖሮ ዛሬ ልክ ጉዳችንን የማናውቀው ይመስል እኛ ተፋቅረን ተጋብተን አንድ ሆነን ኖርን የምንለው ነገር ነው ሊገባኝ ያልቻለው::ስንቱ የማይሽር ቁስል አለበት::ፖለቲካ ሩም ጀምሬው የነበረው ጽሁፍ እንደዚህ ያሉትን ነገር ለመጻፍ ነበር::እና ብዙ ጉድ አለን::ታድያ ያንን ማወቅ ስራችንን ማስታወስ እንዴት እንርሳ?በቀላሉ የከተማ ልጆች የሆንነው እንኩዋን ከከተማ ከተማ እንለያይ የለ እንዴ...ለጉዋደኝነትም እንደዛው::

ይሄ የሀረር ልጅ ነው ይሄ የክፍለሀገር ልጅ ነው ይሄ የአዱ ገነት ልጅ ነው ወዘተ::

አይ መላም የለሽ ገንዘቤን መልሽ አለ::

እና በቀይ ያቀለምከው እርግጠኛ ስላልሆንኩ ማነጻጸሬን በጥርጥር አንጠልጥዬ የተውኩት እርግጠኛ ስላልሆንኩ ነው::

መልካም ጊዜ

ሾተል
እሰይ ተመስጌን አምላኬ ለካስ በክብርነቴ እራሴን ሆኜ እኔነቴን ፈልጌ አግኝቼዋለሁ !?
ሾተል
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 9644
Joined: Thu Jan 13, 2005 9:42 pm
Location: Vienna-Austria

Postby ተድላ ሀይሉ » Sat May 02, 2009 8:04 am

ሰላም ሾተል :-

ጥሩ ነው : ገብቶኛል :: በዓለም ዙሪያ ይኼ አለ :: እኛ በራሣችን ላይ ያለውን ድክመት የምንቀበልበት መንገድ እና ሌላው የዓለም ማኅበረሰብ የሚቀበልበት ሥልት ሊለያይ ይችላል :: ነገር ግን አትጠራጠር በሁሉም የዓለም ክፍል አለ :: አንተ በምትኖርበት አገር ኦስትርያ ያሉ ጀርመኖች ሂትለር ከእነርሱ እንዳልወጣ የናዚ ወንጀል የጀርመኖች እንጂ የእነርሱ የኦስትሪያውያን ያለመሆኑን ለማሣመን ይሞክሩ የለም ? ለማንኛውም እኛም ድክመታችንን በሠንካላ ምክንያቶችና እርባና-ቢስ መሸፋፈኛዎች በመጠቀም መደበቁ አልጠቀመንም : አይጠቅመንምም ::

ተድላ
ተድላ ሀይሉ
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 4903
Joined: Fri Mar 17, 2006 2:45 pm
Location: ኢትዮጵያ

Postby 1234ጭልጥ » Sat May 02, 2009 11:48 pm

እና ሾተልና ተድላ ሀይሉ እንግዳ ቡዳ ተብሎ ስለተሰደበ ድፍን ኢትዮጵያን ሊቀየምና ሊያኮርፍ ብሎም ሊክድ ይገባዋል ነው የምትሉት ?

እኔ አለመማር ነው ብሎ ሊያልፈው ይገባል ባይ ነኝ ::
በኢትዮጵያ የተሰደቡና የተገለሉ ያንን ችግር አልፈው አገሪቷን ለማስተዳደር የበቁ አሉ::ከነሱ መማር አለበት::

ምሳሌ
አጼ ቴዎድሮስ..............................................የኮሶ ሻጭ የእጀኛ/ጠይብ/ቡዳ ተብዬ ልጅ
መንግስቱ ኃ/ማርያም.....................................የባሪያ ተብዬ ልጅ
መለስ ዜናዊ...................................................የአጋሜ/ደሀ/ለማኝ ተብዬ ልጅ

እነዚህ ትልቅ ደረጃ የደረሱ ሰዎች እናንተ እንደምትሉት አገር አኩርፈው አገር ጥለው ቢሄዱ ኖሮ የአገር/የብሄር ቁንጮ ባልሆኑ ነበር
YOU WILL NOT LIVE FOR EVER. HAVE YOU EVER ASKED YOURSELF HOW MANY MORE YEARS YOU GOT LEFT ?
1234ጭልጥ
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 119
Joined: Fri Mar 20, 2009 5:56 am

Postby ተድላ ሀይሉ » Sun May 03, 2009 12:22 am

1234ጭልጥ wrote:እና ሾተልና ተድላ ሀይሉ እንግዳ ቡዳ ተብሎ ስለተሰደበ ድፍን ኢትዮጵያን ሊቀየምና ሊያኮርፍ ብሎም ሊክድ ይገባዋል ነው የምትሉት ?

እኔ አለመማር ነው ብሎ ሊያልፈው ይገባል ባይ ነኝ ::
በኢትዮጵያ የተሰደቡና የተገለሉ ያንን ችግር አልፈው አገሪቷን ለማስተዳደር የበቁ አሉ::ከነሱ መማር አለበት::

ምሳሌ
አጼ ቴዎድሮስ..............................................የኮሶ ሻጭ የእጀኛ/ጠይብ/ቡዳ ተብዬ ልጅ
መንግስቱ ኃ/ማርያም.....................................የባሪያ ተብዬ ልጅ
መለስ ዜናዊ...................................................የአጋሜ/ደሀ/ለማኝ ተብዬ ልጅ

እነዚህ ትልቅ ደረጃ የደረሱ ሰዎች እናንተ እንደምትሉት አገር አኩርፈው አገር ጥለው ቢሄዱ ኖሮ የአገር/የብሄር ቁንጮ ባልሆኑ ነበር

ሾተል የራሱን አስተያዬት ይሰጥሃል ::

የእኔ አቀራረብ አንተ ባልከው መንገድ አይደለም :: እኔ ኢትዮጵያ ውስጥ ድሮም ሆነ አሁን ዜጎችን በተለያዩ ምክንያቶች ዝቅ አድርጎ የማየት እና የመብት ረገጣ ነበረ : አሁንም አለ ነው አቋሜ :: ይህ ማለት ግን ተሣዳቢዎቹ እና አግላዮቹ ልክ ያልሆኑትን ያህል በጅምላ ኢትዮጵያውያንን የፈረጀው ሁሉ ትክክል አይሆንም :: ሁልጊዜም ጥፋት በጥፋት : ሥህተት በሥህተት አይታረምም ::

ተድላ
ተድላ ሀይሉ
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 4903
Joined: Fri Mar 17, 2006 2:45 pm
Location: ኢትዮጵያ

:-)

Postby ደጉ » Sun May 03, 2009 5:58 pm

ሾተል wrote:....ወላሞ ኦሮሞ ቁላ ቆራጭ ጉጂ ቡዳ ጎጃሜ ቆማጣ አማራ ጠባሳ ወላሞ ፋቂ ሺናሻ ወዘተ ....

:D .... ወላሞ ....ጠባሳ ወላሞ (ወላይታ) መለያ እንጂ ስድብ አይደለም....ልክ እሱ /እሱዋ አማራ ነች...ትግሬ ወይ ኦሮሞ ነች እንደሚባለው....እሚጠበሱትም ለአይን ህክምና ነው...ባይሰራም...ትግሬም ባይነሪ ቁጥሮች አሉት....ቁላ ቆራጭ (ጉጂ) ...ጉጂ አሁን አሁን ትቶ እንደሆን አላውቅም..እነሱ ይሄን ለጋብቻ የመቁረጥ (የመስለብ) ባህል እንዲያቆሙ በደርግ ግዜ በአጉል በህል ማስወገድ አይነት ፕሮግራም ሲነገራቸው ነበር ...ሁሉም ጉጂ አይሰልብም....ግን ያው ጆሮም ሆነ ቁላ ቆራጭ እስከሆነ ድረስ ነው ቢባል መለያው ነው..እስካደረገው ድረስ.. :D ቡዳ ...ድሮ ድሮ ጎጃሜ ሁሉ ቡዳ ይመስለኝ ነበር ... :) ወደ ጎጃም ስሄድ እማላደርገው መከላከያ አልነበረም...;) ለነገሩ "ቡዳ" አለ..ካለ ደግሞ "ቡዳ" ("ኢቭል አይ") ቢባል መለያው ነው...ያልሆነው ሰው ከተባለ ስድብ ሊሆን ይችላል.....ቆማጣ ወይም በአካል መጉደል እሚደረግ ግን ማንኛውም ስድብ አጸያፊ ነው....ዛሬ ደህና የሆነ ነገ ሊደርስበት ይችላል...ፋቂ ..ቀጥቃጭ ..ሸክላ ሰሪ የ እነ እንግዳ ዘሮች ደግሞ በዚህ እሚታወቁበት የ እጅ ሙያ ነው....እዚህ ሂትለር እና ህዝቡ ሲነሱባቸው በአራጣ አበዳሪነት ህዝቡን በዘበዙት እሚለው አንድ መነሻ ነበር ...ቀጥቃጭ ፋቂ ..ሸክላ ሰሪ መባላቸው ድሮ ድሮ ያሳዝነኝ ነበር....አሁን አሁን ግን ለምን እንዳዘንኩ ይገርመኛል..እዚህ አገር የፋሚሊ ስም ሁሉ ...ጫማ ሰሪ ..ዳቦጋጋሪ...ቀጥቃጭ ...ወዘተ ሲሆን...በዛ ስማቸው መጠራታቸው ዛሬ ማንም በሙያው እንደሚጠራው ነው.... ስም መጠሪያ ነው እስከሆነም ድረስ ለመለየት በሱ ከሚጠሩዋቸው አንዱ ነኝ... :D
...እንግዳ ኢትዮጵያ ውስጥ እንደዛ አሉኝ ብሎ ብስጭትህ ጭራሽ አይገባኝም...ማን ብለው እንዲጠሩህ ነበር ፍላጎትህ....መቼም በሙያ ዶክተር ሆነህም ቀጥቃጭ አይሉህም....;)ክሊፑ ላይ ግን ወገናችን ሲደበደብ ከምር ምነው እዛ ቦታ በዛ ሰአት በኖርኩ ነው ያልኩት ከምር::
"STUPID IS AS STUPID DOES " :D
ደጉ
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 4416
Joined: Mon Dec 15, 2003 10:39 am
Location: afghanistan

Next

Return to Warka Intimate - ዋርካ ፍቅር

Who is online

Users browsing this forum: No registered users and 4 guests