ETHIOPIAN FUN & ( .) ( .)

The Love Forum (love, relationship) (የኔ ቆንጆ እንተዋወቅ :-)

Postby Gosa » Thu Dec 13, 2012 7:05 pm

ደጉ ያገሬ ልጅ!
እንደው አንድ እንድትመልስልኝ የማልፈልገውን ጥያቄ ልጠይቅህ...ለመሆኑ ምን አይነት ስራ ነበር እንዲህ እንደ ጥንት ታማኝ ሐዋርያት(እነ ጴጥሮስ) ካገር አገር የሚያንከራትትህ? የዘመኑ ወንጌላዊ "ሂድ እና ደጉ የዞረባቸውን ቦታ ሁሉ እየዞርክ ወንጌልን ስበክ" የሚል የፕራይቬት መልዕክት ከላይ ቢመጣለት እራሱ ድሊት አድርጎ ጭጭ የሚል ነው የሚመስለኝ እንጂ እንዳንተ ይዞራል ብዬ አልገምትም:: ቦሬ ውስጥማ ከርመሀል ነው የሚባለው::
ጎሳ እነማንን ታውቃለህ? እነ ንጉሴ ኡዴሳን እነ ንጋቷ ማሞን ታውቅ ይሆን? ንጉሴን ካወቅከው እኔንም ሳታውቀኝ አትቀርም:: እስቲ ደግሞ ስለ ጎሳ ትንሽ ነካካልኝ::
.አሁን ስሙ ጠፋኝ በጎሳ በኩል የግበሬ ማህበሩ ሱቅ በነበረበት ወደ ግራ 10 ወንዶችና 1 ሴ እሚማሩበትን ትምህርት ቤት አለፈህ 40 ክሜ አንድ ወንዝ ተሻግረህ ያለ ቦታ አሁን ስሙ ጭራሽ ሊመጣልኝ አልቻለም ካስታወስከው ንገረኝ ....ሱኬ አይደለም ያን በእግር 3ሰአት የሄድኩበትን መቼም አረሳውም ...እኔ የከተማው ልጅ መጎተት ሲገባኝ የገጠሮቹን ልጆች እየጎተትኩ የጨረስኩት ተራራ ...


:D :D እንደው ባጠቃላይ አስራ አንድ ተማሪዎች ብቻ ነበሩ ማለት ነው በት/ቤቱ ውስጥ? ያቺ አንዷ ሴት ልጅ አሁን የወረዳው የሴቶች ጉዳይ ሀላፊ ሆናለች አሉ :D ወደዚያ አካባቢ ያሉት ት/ቤቶች ካራ: ሙሪ: ቃሌ ኩኩ ናቸው:: የትኛው ይሆን ታዲያ?
ቦሬ አንድ ክረምት ክረምት ወደ እናት ምግብ ቤት ስሄድ እምወዳት ስልክ እንጨት ነበረች አሁን መቼም የከተማ እድገት አንስቱዋት ይሆናል ከቦታዋ ...እሱዋ ስልክ እንጨት ክረምት ላይ ሁሌ አቅፋት ነበር ....ከስሩዋ እሚያዳልጥ ቦታ ስላላት ጭቃና ውህ ለብሶ ሰው እየረገጠው እሚያልፈውን ድንጋይ ማታ በደንብ ማየት ስለማይቻል ስልክ እንጨትዋን እያቀፍኩዋት ነበር ተሽከርክሬ እማልፈው ...አሁን አሁን ክረምት አገር ቤት ገባ ሲባል እንደ ጥሩ ጉዋደኛ ትዝ ትለኛለች ...

:D :D :D ገደልከኝ:: በጣም የሚገርመው የሳታላይት ስልክ ገብቶ ቴሌዎች የተተከሉትን የስልክ እንጨቶች ማንሳት ሲጀምሩ ያቺ እንጨት እንዳትነካ ህዝቡ ሰልፍ ወጥቶ ነው ያዳናት:: ብቻዋን ቆማለች አሁንም :D የማንም ባለውለታ እንጨት::
ለጊዜው ትዝ ያለኝ ግን አንድ ጊዜ አንድ ጊዜ የከተማው መስመር ኤሌትሪክ እሳት ፈጥሮ ችግር ነበር የመብራት ህይሉን ሰውዬ በየጠጅ ቤቱ ሲፈለግ ቆይቶ ቴትራ ሳይክል ጠጅ ቤት ነው መሰልኝ ተገኘቶ እሳቱን ከማከፋፈያው አጥፍቶልን ሰላም ያገኘንበት ጊዜ ነበር ...ቦሬ ሰው ከጠፋ ከጠጅ ቤት ሌላ እሚገኝበት ያለ አይመስለኝም

ተው የቴትራሳይክሉን ቤት ወሬ አታውራ:: በሆነ ወቅትማ በጣም ታዋቂ ሆኖ ነበር ያ ቤት:: የዚያ ቤት ልጅ በጣም ጥሩ ጸባይ ስለነበራት ጠጁ እንኳ ጥሩ ባይሆን ቤቱ እንደሞላ ነበር:: በጣም የሚያሳዝነው አግብታ ሁለት ልጆችን ወልዳ በልብ ህመም ማረፏን ሳልሰማ ቆይቼ ባለፈው ባለቤቷን አግኝቼው ስለጤንነቷ ስጠይቀው ነው የነገረኝ:: የምታምር እና ምርጥ ጸባይ ያላት ልጅ:: "ደህና ሰው አይበረክትም" ይል ነበር ሞፊቲ የጠጅ ሳንቲም ሲከለከል::ያ ያልከኝ የኤልፓው ሰውዬ ማን እንደሆነ ማወቅ አልቻልኩም:: እሱም ምን ያርግ...ብርዱ ነው እዚያ የሚያስቀረው:: በል እስቲ ስለጎሳ አውራልኝ::
We must learn to live together as brothers or perish together as fools.
Martin Luther King, Jr.
Gosa
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 377
Joined: Mon Nov 21, 2011 2:43 pm
Location: ethiopia

(-:

Postby ደጉ » Fri Dec 14, 2012 4:45 pm

ሰላም ሰላም ጎሳ,

Gosa wrote:ደጉ ያገሬ ልጅ!
እንደው አንድ እንድትመልስልኝ የማልፈልገውን ጥያቄ ልጠይቅህ...ለመሆኑ ምን አይነት ስራ ነበር እንዲህ እንደ ጥንት ታማኝ ሐዋርያት(እነ ጴጥሮስ) ካገር አገር የሚያንከራትትህ? የዘመኑ ወንጌላዊ "ሂድ እና ደጉ የዞረባቸውን ቦታ ሁሉ እየዞርክ ወንጌልን ስበክ" የሚል የፕራይቬት መልዕክት ከላይ ቢመጣለት እራሱ ድሊት አድርጎ ጭጭ የሚል ነው የሚመስለኝ እንጂ እንዳንተ ይዞራል ብዬ አልገምትም::

....በቅድሚያ አመሰግናለሁ ለመልስህ ....እሺ ጥያቄውን እንዳልመልስልህ ስለፈለክ አልመልስልህም በደፈናው ግን በወቅቱ ከነበረ የግብርና ፕሮግራም ጋር በተገናኘ ነበር::
...ልክ ነህ ሰባኪም ብሆን ወንጌል ያልደርሰበት እየገባህ መስበክ አለብህ ....ክፋቱ ግን ቡዲሂዝምን ለማስፋፋት ጊዜ ላገኘሁም... :D
ጎሳ እነማንን ታውቃለህ? እነ ንጉሴ ኡዴሳን እነ ንጋቷ ማሞን ታውቅ ይሆን? ንጉሴን ካወቅከው እኔንም ሳታውቀኝ አትቀርም:: እስቲ ደግሞ ስለ ጎሳ ትንሽ ነካካልኝ::

...ጎሳ የተቀስካቸውን ሰዎች ጨምሮ አውቃቸዋለሁ ንጉሴ ኡዴሳን ግን አሁን መልኩ ሊመጣልኝ አልቻለም ...ንጋትዋን ግን ቅላትዋን እጥረትዋን እና ሳቅዋን ጭምር አስታውሳልሁ... ጎሳ ባጋጣሚ ክሊኒክ ይዣቸው ለምሄደው በሽተኞች ቶሎ ተቀብላ እምታስተናግደን ነበረች..እሱዋ ብቻ ሳትሆን እህቶችዋም ...የ ንጉሴ ግን ፒክቸሩ ሊመጣልኝ አልቻለም..ምናልባት ብዙ ቅርበት ስለሌለኝ ይሆናል....ጎሳ ካቶሊኮቹ የሰሩት ት/ቤት መቼም አሁን ትልቅ ሳይሆን አይቀርም....እዛ የነበሩትን ሲስተሮች እና ፋዘሮች አውቃቸዋለሁ ...ብራዘር ጆን እሚባሉት ጎበዝ መካኒክ ነበሩ እዛ መስመር ለገጠመን የቴክኒክ ችግር በጣም ነበር የረዱን::ከዛ አንድ ማፊያ ነገር ጥቁር ፋዘር መጥቶ ነበር...እሱ አንድ ቻይናዊ አስቀያሚ ገጣጣ ሲስተር ነበረች በጣም ይላፉ ነበር ፈጣሪ ፈቅዶላቸው ነበር መሰለኝ...;)
:D :D እንደው ባጠቃላይ አስራ አንድ ተማሪዎች ብቻ ነበሩ ማለት ነው በት/ቤቱ ውስጥ? ያቺ አንዷ ሴት ልጅ አሁን የወረዳው የሴቶች ጉዳይ ሀላፊ ሆናለች አሉ :D

ቅቅቅቅቅ...ብትሆን እንዴት አሪፍ ነበር ....እሚገርመው እዛ አገር ጠለፋ በጣም የተስፋፋበት አገር ስለነበር ሴት ልጆችን ወደ ት/ቤት አይልኩም ነበር አሁን አሁን አላውቅም....በዛ የተነሳ ሴት ተማሪዎች ማየት በጣም ቀላል አልነበረም ወይ ለጠለፋ ያልደረሱ መሆን አለባቸው...የትኛው ት/ቤ እንደነበር አሁን በጭራሽ አላስታውስም ....እማስታውሰው ግን ከጎሳ ብዙ ሩቅ አይደለም...ካራ ራቅ ያለው ይመስለኛል እርግጠኛ አይደለሁም::
....ተው የቴትራሳይክሉን ቤት ወሬ አታውራ:: በሆነ ወቅትማ በጣም ታዋቂ ሆኖ ነበር ያ ቤት:: የዚያ ቤት ልጅ በጣም ጥሩ ጸባይ ስለነበራት ጠጁ እንኳ ጥሩ ባይሆን ቤቱ እንደሞላ ነበር::

....ጠጁ ይሄን ያክል ባይሆንም የሰው መብዛት አይገርመኝም...;) የቦሬ ሴቶች በጣም ቆንጆዎች ናቸው...ከሁሉ እማረሳው የፊታቸው ቆዳ ጥራቱን ነው ...ከማር መስሎኝ ስንት ላስቲክ ነጭ ማር ጨርሼ ነበር...አልሆነም..... :D ይልቅ አንድ በጣም እምታምር ቆንጆ ልጅ ነበረች አንድ ስታውት መኪና የነበራቸው ሰውዬ ልጅ...;)
በጣም የሚያሳዝነው አግብታ ሁለት ልጆችን ወልዳ በልብ ህመም ማረፏን ሳልሰማ ቆይቼ ባለፈው ባለቤቷን አግኝቼው ስለጤንነቷ ስጠይቀው ነው የነገረኝ::

ኦ! በጣም አሳዝናል ፈጣሪ ነፍሱዋን ይማረው
ያ ያልከኝ የኤልፓው ሰውዬ ማን እንደሆነ ማወቅ አልቻልኩም:: እሱም ምን ያርግ...ብርዱ ነው እዚያ የሚያስቀረው:: በል እስቲ ስለጎሳ አውራልኝ::

.....እዚህ መሳያ ቢኖር ስዬ አሳይህ ነበር ከምር ሰውየው እሚያስቸግር መልክ አልነበረውም ..አጠር ያለ ካኪ እሚለብስና ክረምት ፊት ነገር ነው እስኪ አስታውሰው... :D [/quote]
"STUPID IS AS STUPID DOES " :D
ደጉ
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 4413
Joined: Mon Dec 15, 2003 10:39 am
Location: afghanistan

Postby Gosa » Mon Dec 17, 2012 11:01 am

ሰላም ሰላም ደጉ ወንድሜ!
ክፋቱ ግን ቡዲሂዝምን ለማስፋፋት ጊዜ ላገኘሁም
:lol: :lol:
ያው ግን ብትሰብክም ባትሰብክም የሆነ ፍጡር ሆነህ መመለስህ አይቀርም አይደል? ገሀነም አላቸው እንዴ እነሱም :? ከምር ከሌላቸው የሚታሰብበት ጉዳይ ነው:: ለማንኛውም ደህና ነገር ከሰማህ አትርሳኝ :D
...ጎሳ የተቀስካቸውን ሰዎች ጨምሮ አውቃቸዋለሁ ንጉሴ ኡዴሳን ግን አሁን መልኩ ሊመጣልኝ አልቻለም ...

ንጉሴ ማለት ከጀልዶ በስተቀር በጥቁርነት ማንም እዚያ ከተማ ውስጥ አይበልጠውም:: ጀልዶን እንኳ ሳታውቅ አትቀርም: የታምራት ሐኪሙ (ኬላ ሰፈር ያለው ፋርማሲ ባለቤት) ወንድም ወይም ዘመድ ነው መሰለኝ:: ጎሳን ያን ያህል የምታውቅ ከሆነ ንጉሴንም እንደምታውቀው እርግጠኛ መሆን እችላለሁ::
ጎሳ ካቶሊኮቹ የሰሩት ት /ቤት መቼም አሁን ትልቅ ሳይሆን አይቀርም ....እዛ የነበሩትን ሲስተሮች እና ፋዘሮች አውቃቸዋለሁ ...ብራዘር ጆን እሚባሉት ጎበዝ መካኒክ ነበሩ እዛ መስመር ለገጠመን የቴክኒክ ችግር በጣም ነበር የረዱን ::

አንተ በጣም በጣም ነዋ የምታውቃቸው:: የብራዘር ጆን ጥርስስ ተነቃቃይ መሆኑን ታውቅ ነበር? :lol: እዚህ አገር መጥተን የዴንቸር አይነቶችን ከማየታችን በፊት የጥርሱ ጉዳይ ትልቅ ተአምር ይመስለን ነበር:: እሱ በጣም ጎበዝ መካኒክ ነበር:: ዛሬ ደግሞ ስለ አባ ጆ (ዮሴፍ) የጻፍከውን አንብቤ ስንት ነገር አስታወስከኝ:: መቼም እሳቸው የሰጡህ መዝገበቃላቱ እስካሁን ድረስ አይኖርም አይደል? በተለይ የዚያን አካባቢ ባህል አስመልክቶ ትልቅ መጽሀፍ ጽፈው ነበር:: ያላስፈለኩት ቦታ የለም:: ግን ላገኝ አልቻልኩም::
ከዛ አንድ ማፊያ ነገር ጥቁር ፋዘር መጥቶ ነበር ...
:D :D ቀላል ማፊያ! የሱ አይወራም:: በዚያን ወቅት እኔም እዚያ ስለነበርኩ ምናልባት ሳንተያይ አንቀርም አቦ::

ሰሞኑን ያንተን ጽፉፎች ፌስቡክ ላይ ፖስት አድርጌ ስንት ሰው ላይክ እና ሼር አደረገ መሰለህ:: ቆንጆ ኮመንት ነው የሰጡህ:: ይድረስህ::

በል ይመችህ ወንድሜ:: በቅርቡ እመለሳለሁ::
We must learn to live together as brothers or perish together as fools.
Martin Luther King, Jr.
Gosa
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 377
Joined: Mon Nov 21, 2011 2:43 pm
Location: ethiopia

:-)

Postby ደጉ » Mon Dec 17, 2012 10:21 pm

ሰላም ጎሳ :)
Gosa wrote:...ንጉሴ ማለት ከጀልዶ በስተቀር በጥቁርነት ማንም እዚያ ከተማ ውስጥ አይበልጠውም:: ጀልዶን እንኳ ሳታውቅ አትቀርም: የታምራት ሐኪሙ (ኬላ ሰፈር ያለው ፋርማሲ ባለቤት) ወንድም ወይም ዘመድ ነው መሰለኝ:: ጎሳን ያን ያህል የምታውቅ ከሆነ ንጉሴንም እንደምታውቀው እርግጠኛ መሆን እችላለሁ::

....ታምራት ፋርማሲስቱ ኦ! አወኩት....እሱ ሰውዬ እኮ ሲበዛ ንፋሳም ነበር....አንበሳ አድን ነበር ብሎ ሲያስቀኝ ነበር ... :D ከ አውራሪስ አዳኙ ጋ ተመሳሳይ የሆነ ታሪክ ነበር ...አዳኙ ጎበዙ ሰውዬ አውራሪስ ሊያድኑ ሄደው ...አውራሪሱ ድንገት ሲመጣባቸው አንድ ቁዋጥኝ ድንጋይ ጋ ሮተው ሲደበቁ....አውራሪሱ ከነ ቁዋጥኙ ወደ ሰማይ ሲያጎናቸው...ቅቅቅቅ ሰውየው በአየር ላይ እንዳሉ አቀባብለው ከላይ ሆነው አውራሪሱን ወደ ታች አነጣጥረው አናቱን መተው የገደሉት አይነት ታሪክ ወተት እየጠጣሁ ነበር የሰማሁት...ዛሬ ላይ ሆኘ ይቅር ብየዋለሁ... :D ወንድሙን ግን ላስታውሰው አልቻልኩም...ብዙ ጥቁዋቁር ስላየሁ ተምታታብኝ...ቅቅቅቅ ግን ከምር እሱ ግ ለመትከም ከምሄድ እዛ አንድ ቆንጆ የከብት ህኪም ነበረች ..እሱዋ ጋ ብሄድ ቶሎ እድናለሁ ብዬ አምናለሁ... :lol:
..አንተ በጣም በጣም ነዋ የምታውቃቸው:: የብራዘር ጆን ጥርስስ ተነቃቃይ መሆኑን ታውቅ ነበር?

...ጥርስ እንዳላቸውም አሁን ነው ትዝ ያለኝ :)
: ዛሬ ደግሞ ስለ አባ ጆ (ዮሴፍ) የጻፍከውን አንብቤ ስንት ነገር አስታወስከኝ:: መቼም እሳቸው የሰጡህ መዝገበቃላቱ እስካሁን ድረስ አይኖርም አይደል? በተለይ የዚያን አካባቢ ባህል አስመልክቶ ትልቅ መጽሀፍ ጽፈው ነበር:: ያላስፈለኩት ቦታ የለም:: ግን ላገኝ አልቻልኩም::

...ዲክሽነሪው አለ ግን አዲስ አበባ ነው ያለው ....የጻፉትን መጽህፍ ግን ማግኘት እምችል ይመስለኛል....እስኪ እሞክራለሁ...ከዛ እጠቁምህለሁ የት እንደምታገኘው::
...ሰሞኑን ያንተን ጽፉፎች ፌስቡክ ላይ ፖስት አድርጌ ስንት ሰው ላይክ እና ሼር አደረገ መሰለህ:: ቆንጆ ኮመንት ነው የሰጡህ:: ይድረስህ::

...ኦ! አመሰግናለሁ ...ለ ጻፉትም አመሰግናለሁ ብሉዋል በልልኝ...:)

በል ይመችህ ወንድሜ:: በቅርቡ እመለሳለሁ::

...በል አትቆይ :)
"STUPID IS AS STUPID DOES " :D
ደጉ
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 4413
Joined: Mon Dec 15, 2003 10:39 am
Location: afghanistan

(-:

Postby ደጉ » Tue Dec 18, 2012 2:55 pm

... ድሮ ድሮ አሉ ነው ነገሩ ድሮ በድንጋይ ዘመን ጊዜ እርግጠኛ ነኝ እናንተ አልነበራችሁም...ሾው እሚደርገው ማለት እኛ ወንዶቹ ሴቶቹን እንፕሬስ ለማድረግ እምንጠቀመው አደን ነበር ...በቃ አሉ የተባሉትን ትልልቅ የዱር እንስሳት እንገድልና ሌላ ወንድም ገድሎ ታይትላችንን እስኪወስድ ሴቶቻችንን የገዳይ ሚስት ስም አስጥተን ቀይ ምንጣፍ ላይ ባትሄድም ...በባዶ እግሩዋ ሄዳ ውህ ለምትቀዳበት ምንጭ ግን ቅድሚያ ነበራት...:) ዛሬ ዛሬ እንዳናድን እና ሴቶቻችንን ኢምፕሬስ እንዳናደረግ መንግስት ተብዬዎች ጠበንጃ እንዳንጠቀም ከለከሉ...እኛ ግን ሞኝ አይደለንም ሌላ ዘዴ ፈለገን....ባለን ነገር መሞከር ....መኪናም ካለን በተቻለ ከሌላው የበለጠ ቢሆን እንመርጣለን....ቤትም ከሆነ እንደዛው ...ጡንቻም ከሆነ እንደዛው ...በቃ አለ የተባለውን ነገር በሙሉ በዚህ መልኩ ለማሳየት እማንቆፍረው ጉድጉዋድ ልንገፋ እማንሞክረው ተራራ የለም...ይሄ ደግሞ በ እድሜም ይወሰናል....በ ወጣትነት ደረጃ ...መኪና ካለን ጭስ መውጫውን ...ሞቶር ቱን ብማድረግ ድምጹን ቀይረን አገሩናን ምድሩን ቀውጢ ማድረግ....ብስክሌትም ከሆነ የፊት ጎማዎቹ አክስ ላይ የላስቲክ አበባ ...ፎር ቼላው ላይ ዲኮረትድ የሆነ ነገር ...ከለር ፕላስተር ...ቴለያዮም ላይ እንዲሁ አንዳንድ እሚለጠፉ ነገሮችን የሁዋላ ራጅ ላይ የፍሬኑን ሽቦ ወደ ራጅ በማጠፍ የሆነ ድምጽ እንዲሰጥ ማድረግ..እና ሌላም ሌላም ወዘተ...;)
...ይሄን ሁሉ አለፍንና ዛሬ የኢንተር ኔት ሸዋዬ ሆነን አረፍነው.. :D
....ኢንተርኔት ላይ እምናሳየው ነገር ከሌለ አቴንሽንና ያው በዛውም ያሉትን እንስቶች ኢንፕሬስ ለማድረግ ... እንንጣጣለን በየትኛውም አቅጣጫ ሰዎች እንዲያዩን ከ ምስኪንዋ ኮምፒውተራችን ጋ ሆነን ሰው እማያይልንን ስቃይ እናያለን....አንድ ቀን አእምሯችን አዙሮ ይሄን ሁሉ ምንም ለማግኘት ነው እንዲህ መከራህን እምትበላው ብሎ አይጠይቀንም...እሱም አላበደም.. :D
....እስካሁን ብዙ ሰዎችን በ ሳይበሩ አለም አይቻለሁ....ልምድ ከሌለው ዶክተርና ልምድ ከሌለው ጸጉር አስተካካይ ይሰውራችሁ እንጂ በሳይበሩ አለም እማታዩት አይነት ታሪክ የለም...
..... የሳይበር ኢትዮጵያን እዚሁ በግልጽ እምታዩት ስለሆነ ለናንተ በመንገር ጊዜ አላጠፋም ....ሌሎች የፐብሊክ ሚዲያ ላይ ግን እንዴት ነው እሚገልጹት ....
....መቼም ሁልጊዜ ብዙ ምግብ በመብላት ጠንካራ ....ሁልጊዜም ያለ የሌለ መጽህፍም በማንበብ አዋቂ መሆን አይቻልም....ቢቻል ስንት ሰዎች አዋቂ በሆኑ ነበር ... :D
.....እሚቻል መስሎኝ ግን ሞክሬ ነበር....አልሆነም እንጂ ...:(
...እንደ ፓል ቶክ ያሉ ሩሞች ውስጥ እሚያወሩ ሰዎችን ልብ ብላችሁ ሁልጊዜም ባይሆን አልፎ አልፎ ሳትሰሙ አትቀሩም.... አንዳንዱ ሩም ጆይን ሲያደርግ ሰላም ያለው ሳይበቃው ...ማይክራፎን ሲይዝ ደገሞ የሰው ስም ከላይ አንስቶ እስከታች ...አንዳንዴ ወደ ሩ,ኡ ሊገባ በሆዱ ገና በማስብ ላይ ያለውንም ጨምሮ ሰላም ሳይል እሚቀር አይመስልም....ወሬ ወይም ቶፒክ ብለው የጀመሩት በሰላምታው ብዛት መስመሩን እሚቀይርበትም ጊዜ አለ....አንዳንዱ ደግሞ ...እጁን ማውጣት ሳለለበት እንጂ ስለሚወራው ነገር ምንም ነገሩም ህሳቡም የለውም....እንደነዚህ አይነቶቹ ማይክራፎኑን ሲይዙ መጀምሪያ እሚናገሩት እኔ እንኩዋን በቶፒኩ ላይ ምንም እምለው የለም ሰላም ልላችሁ ነው ይላሉ....ቅቅቅቅቅ በቴክስት እሚገላገለውን ያን ሁሉ ሰአት እጁን አውጥቶ ጠብቆ ...ሰላም ይላችሁዋል...ከምር የኛ ህዝብ እኮ የዋህ ነው.. :D
.....ብዙ ጊዜ በወንዶቹ ላይ ደግሞ እማየው ...መቼም አንድ ቀን ቴክኖሎጂ በምንገዛው ኮምፒውተር ውስጥ ስውር ካም አድርጎ ሰዎች ሳያዩን እምናይበት ቀን ያመጣልን ይሆናል....ራሳቸውን በጣም ከተፈላጊ ሰዎች (ሚሊየነር) በሉትዋቸው....ፑማ ጫማ ሁሉ በ ካም እያሳዩ ሲላጡ እሚውሉ እንበላቸው አሉ....እነዚህኞቹ ያው እንግዲህ ኢምፕሬስድ የሆኑ ሴቶች በጀርባ እሚጎርፉላቸውን እነሱና አንድ ፈጣሪ ንው መቁጠር እሚችሉት.. :lol: ካሉ ነው ...ግን እዛ ላይ ሰው ብልጥ የሆነ ይመስላል...እንደ እኛ ካሉት የዋሆች በስተቀር እሚነገረው ሁሉ እውነት ነው እያልን ቁጭ ብለን ማስታወሻ ከምንይዘው በስተቀር.. :D
....አንዳዱ ደግሞ ካም በከፈተ ቁጥር መኪና ሲነዳ ነው ....ይሄኛው በምን መልኩ ፍላጎቱን እንድሚገልጽ ለማወቅ ችግር ነው ....ፖስተኛ ነኝ ይሆን....ታክሲ ሹፌር ነኝ ይሁን ...የፒዛ ዴሊቨሪ ነኝ ይሁን አይታወቅም....በቡድህ ስም መልካም እድል ነው እምመኝለት... :D
....አንዱ ደግሞ ማይክራፎን ሲይዝ በህይለ ቃል ነው እሚጀምረው ....በቃ ያለው ህይለኛ ተደባዳቢ እኔ ነኝ ይላል ....በዱላ አለም ያለ ሰው ቀስ ያለ ምላስና ፈጣን አይን ይስጥህ እሚባልው እዚህ ሰውዬ ጋ አይሰራም....ፈጣን ምላስና ዘገምተኛ አይን ነው የሰጠው ...ዱላ በአፍ ተጀምሮ በአፍ እሚያልቅበት ቀን አደረስን ....ከልቤ ነው ካራቴ ለመማር ያጠፋሁዋቸውን አመታት ሁሉ ሳስብ በጣም እየቆጨኝ በቀን አንድ ጊዜ ማታ ከመኝታ በፊት በረንዳ ላይ እየወጣሁ እዬዬ ነው እምለው...
.....ፓል አሁን ሳየው የሆነ እራሱን የቻለ ከተማ ነው....ከቀብር በስተቀር ሁሉ ነገር አለ...ህሜት....ደስታ ..ጨዋታ ..መጠባበስ....ሰርግ....የጫጉላ ሩም...ወዘተ...እስካሁን ያላጋጠመኝ ሰው ሞቶ የቀብር ሩም ብቻ ነው.. :D
.....ፓል ላይ እናንተም ሰምታችሁ ይሆናል አንዳንድ ወንዶች ሴቶችን ኢምፕሬስ ለማደረግ እሚጠቀሙበት ዘዴ አለ...ፕሊስ እናንተ ይሄን ዘዴ እንዳትጠቀሙ....ወንድ ነው ይተዋወቃሉ ፕራይቬት ሲያወሩ ...ዋው ድምጽሽ ከዛ ካም ራቁቱን ሆኖ ይክፍታል....ሴቶቹ እሚሉት እወንት ከሆነ ....አንዳንዶቹ ከ እነ ፒሲ ሲዘጉ አንዳንዶቹ ወዲያው ብሎክ እንድሚያደርጉ ይናገራሉ...ያ ማለት ይሄ ዘዴ የትም አያደርስም...:(
.....አንዳንድ ወንዶች ደግሞ ከሴትቹ ጋ ተከባብረው እያወሩ ይቆዩና ..በመህል ምንድነው የለበሽው ብለው ኖርምል ጠይቀው ...ወዲያው ፓንት አሳይኝ እሚሉም አሉ.. :lol: አሁን እውነት ጎረቤታቸው ካሉ ሴት ነዋሪዎች አንድ የተሰጣ ፓንት ማየት አቅቱዋቸው በኢንተርኔት...?? :D እንደ እነዚህ አይነት ሰዎች ጤነኞች ናቸው..?
....አንዳንዱ ደገሞ ዛሬ ይተዋወቅና ልጅትዋ እምትኖርበትን አገር ካወቀ ..በነጋታው ቲኬት ኮርጫለሁ ነገ ልመጣ ነው ብሎ ኢምፕሬስ ለማድረግ ያስደነገጡዋቸው ብዙ አሉ....ከምር አዛ ያሉ ወንዶች ለዚህ ጉዳይ ሻንጣ ፓል አድርገው በተጠንቀቅ እሚጠባበቁ አሉ ማለት ነው.. :D
....ሴቶቹስ እምፕሬስ ለማድረግ ምን ይጠቀማሉ....;) ወደ ሴቶቹ ስንመጣ ቀላል አይደለም....ፕራይቬታቸውን የዘጉ ሁሉንም ማለቴ አይደለም አብዛኞቹ ማለት ግን እችላለሁ ....እነዚህ ሴቶች እሚጠይቃቸውን ወንድ አድ አያደርጉም....ሎቢ ላይ ያን በማድረጋቸው በሌላው ሪስፔክት እንዲደርጉ እሚፈልጉ ሲሆኑ ....ያን ሰው የዛኑ ቀን አድም ሊያደርጉ ወይ ላያደርጉም ይችላሉ....ግን እንደነዚህ አይነት ሴቶች ብዙ ጊዜ ...ራሳቸውን እማያውቁና እሚፈልጉትንም እሚያውቁ አይደሉም....ብዙ ጊዜ እነዚህን ሴቶች የብዙ ወንዶችን ስም እየጠሩ በ ወንዶቹ ዙሪያ ሲሽከረከሩ ታያላችሁ...ቴክስታቸውም ደማቅ ይሆንና በጣም ትልልቅ ያደርጉታል...አለዛ አቴንሺን አያገኙማ....ምን ያደርጋሉ ሌላ ጊዜ ኒካቸውን ይቀይሩና ...ፕራይቬታችሁ ካልተዘጋ ድንገት መተው ያስደንግጣሉ...:D አለዛም ደግሞ ኒክ ቀይረው ሳይለን አፕሮች ያደርጋሉ....;)
... እንደዚህ አይነት ቻት ሩምዎች ውስጥ ከ 10 ሰው 1 ችግር ይሌለበት ከተገኘ ተአምር ነው ማለት ነው....በዚህም ይሁን በዛ መንገድ ችግር የሌለበት የለም....
....አልፎ አልፎ ከወንዱም ከሴቱም በጣም አግሬሲቭ የሆኑ ያጋጥሙዋችሁዋል....እንደ እነዛ አይነቶቹ ለህክምና ፓል ላይ የመጡ ናቸው...ማን የምክር አገልግሎት እንድሚሰጥ አይታወቅም..ፓል ቶክ ገንዘብ ለመቆጠብና የሳይኮሎጂ እርዳታ ለማግኘት ብዙ ሰው እንደሚመጣ ሰምቻለሁ... :D
...ሚሊየኔር መሆን ከፈለጋችሁ እና ገንዘብ በሳህን ለኛ ለማሳየት ከፈለጋችሁ ጆይን ፓል ቶክ :lol:
.....እመለሳለሁ....:)
"STUPID IS AS STUPID DOES " :D
ደጉ
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 4413
Joined: Mon Dec 15, 2003 10:39 am
Location: afghanistan

(-:

Postby ደጉ » Tue Dec 18, 2012 11:33 pm

Men are born between a woman's legs and spend the rest of their lives trying to get back in them. Why?
Because there's no place like home.


Lenin :D

...አባት ለልጁ ስለ አልኮል መጠጥ መጥፎነት ለማስተማር ፈልጎ ልጁን ይጠራውና በተግባር ሊያሳየው ...በ 1 ብርጭቆ ውስኪ .....በ 1 ብርጭቆ ውህ ካደረገ በሁዋላ ሁለት ትሎች ያመጣና ...አንዱን ውስኪ ውስት አንዱን ውህ ውስጥ ይጨምራቸዋል.... ውስኪው ውስጥ ያለው ትል ወዲያውኑ ጥቅቅል ብሎ ሲሞት ውህው ውስጥ ያለው ግን እየተወራጨ ለመውጣት ይሞክር ነበር....
....አባትም ለልጁ አየህ አይደል የሆነውን...? አሁን ከዚህ ምንድነው የተማርከው ይለዋል...?
..ልጁም ከዚህ የተማርኩት አልኮል ከጠጣን ሆዳችን ውስጥ ያሉትን ትሎች እንዴት እንደሚገድልልን ነው....:)
"STUPID IS AS STUPID DOES " :D
ደጉ
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 4413
Joined: Mon Dec 15, 2003 10:39 am
Location: afghanistan

(-:

Postby ደጉ » Wed Dec 19, 2012 4:48 pm

"STUPID IS AS STUPID DOES " :D
ደጉ
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 4413
Joined: Mon Dec 15, 2003 10:39 am
Location: afghanistan

Postby *ማህደረ* » Wed Dec 19, 2012 8:52 pm

ሰላም ደጉ ወዳጄ እንዴት ነህ ባክህ?

ስለ ፓል የጻፍከውን አንብቤ አዝናናከኝ ነው የሚባለው :lol: የመጀመሪያው ጥያቄዪ ፓል የሚባለው የወሬ መቃረሚያ ቦታ አሁንም አለ? :D ድሮ የዋርካ ሩም ተክፍቶ በነበረበት ሰአት እኔም እሄድ ነበር እንደማስታውሰው ከሆነ ያ ክፍል ጥሩ ነበር በጥባጭ ባይበተነው :cry:

እስኪ በነካካ እግሬ ዋርካን ዞር ዞር ብዪ ልመልከታት...

ሰላም

ማህደረ
*ማህደረ*
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 419
Joined: Fri Aug 05, 2005 12:56 am
Location: ethiopia

Postby ደጉ » Wed Dec 19, 2012 10:47 pm

*ማህደረ* wrote:ሰላም ደጉ ወዳጄ እንዴት ነህ ባክህ?

....ማህዲዬ ሰላም ሰላም የኔ ቆንጆ እንደምን አለሽልኝ...አንቺ ልጅ ግን ጠፋሽ እኮ...እንደ ድሮ ቶሎ ቶሎ አትመጪም...ዘበኞቹን ሁሌ ስጠይቃቸው ..ቆየን ካየናት ነው እሚሉት...:)
ስለ ፓል የጻፍከውን አንብቤ አዝናናከኝ ነው የሚባለው :lol: የመጀመሪያው ጥያቄዪ ፓል የሚባለው የወሬ መቃረሚያ ቦታ አሁንም አለ? :D

....አዎ አለ ...ከ 50 በላይ በሚሆኑ ሩሞች ተደራጅቶ ...ማይክ ከያዙ 24 ሰአት መለፍለፍ ይችላሉ በሚባሉ አድሚኖች ታግዞ በተለያዩ ባለ ከለርና ከለር አልባ በሆኑ ኒኮች ደንበኞች ታጅቦ እና ደምቆበት....አለ:: ኢንቬስተር መሆንም ከፈለግሽ ሩም ላይ ኢንቬስት ማድረግ ትችያለሽ....ግን ያው ልክ እንደ ቡናቤት አንቺ ሩም ምጥተው ነገር በሳህን ሳይሆን በማይክ ይደፋሉ.. :D
...ግን በቁም ነገር ስለ እኛ ህዝብ ማወቅ ከፈለግሽ የዛን አይነት እድል አታገኚም...ከ 1ሺህ ህዝብ በላይ አንድ ላይ የት ታገኛለሽ ...? :D

እስኪ በነካካ እግሬ ዋርካን ዞር ዞር ብዪ ልመልከታት...

...አይደል ለ አንድ 6 ወር ደግሞ እሚሆንሽን...:) በይ አትጥፊ ደግሞ ...:)
"STUPID IS AS STUPID DOES " :D
ደጉ
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 4413
Joined: Mon Dec 15, 2003 10:39 am
Location: afghanistan

(-:

Postby ደጉ » Thu Dec 20, 2012 5:14 pm

...አንድ ጊዜ ከ አንዲት ከገርል ፍሬንዴ ጋ ተጣላንና በጣም ስለተበሳጨች ...ካሁን በሁዋላ ጉዋደኝነታችንን ማቆም አለብን ብላ ወሰነች....በዛም አላቆመችም ....የሰጠህኝን በሙሉ እመልሳለሁ አለች....እኔ ከልብሽ ነው ትቀልጃለሽ ..? ስላት ከልቤ ነው አለች....በቃ ከልብሽ ከሆነ ከንፈርሽን ከሳምኩት ጀምረሽ ሁሉንም መልሽልኝ አልኩዋት...ከዛ መጣላታችን ቀረ.. :D
....ፓልን ለመጀምሪያ ጊዜ ጆይን ያደርኩት በዋናው ሩም እዛ መክፈት ምክንያት ነበር...አላስታውስM አንድ 3 ዊኬንዶች እንደ ተገናኘን ነው መሰልኝ ሁሉም ነገር ቀረ ..
...ሰዎች ፓል በጣም አደገኛ ቦታ የሆነውን ያክል ብዙ እሚያስቁ አጋጣሚዎችንም ታያላችሁ....በሴት ኒክ ሆነው ሴት እሚያባርሩ ወንዶች....በወንድ ኒክ ሆነው ሴት እሚያባርሩ ሴቶች ወዘተ....ዛሬ ዛሬማ እዛ ላይ ሰው አይደለም ሌላውን ጥላውን እማያምንበት ደረጃ ላይ ደርሱዋል....
....ደርሼ ልምጣ ....:)
"STUPID IS AS STUPID DOES " :D
ደጉ
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 4413
Joined: Mon Dec 15, 2003 10:39 am
Location: afghanistan

Re: (-:

Postby recho » Thu Dec 20, 2012 5:32 pm

ደጉ wrote:...አንድ ጊዜ ከ አንዲት ከገርል ፍሬንዴ ጋ ተጣላንና በጣም ስለተበሳጨች ...ካሁን በሁዋላ ጉዋደኝነታችንን ማቆም አለብን ብላ ወሰነች....በዛም አላቆመችም ....የሰጠህኝን በሙሉ እመልሳለሁ አለች....እኔ ከልብሽ ነው ትቀልጃለሽ ..? ስላት ከልቤ ነው አለች....በቃ ከልብሽ ከሆነ ከንፈርሽን ከሳምኩት ጀምረሽ ሁሉንም መልሽልኝ አልኩዋት...ከዛ መጣላታችን ቀረ.. :D
....ፓልን ለመጀምሪያ ጊዜ ጆይን ያደርኩት በዋናው ሩም እዛ መክፈት ምክንያት ነበር...አላስታውስM አንድ 3 ዊኬንዶች እንደ ተገናኘን ነው መሰልኝ ሁሉም ነገር ቀረ . .
...ሰዎች ፓል በጣም አደገኛ ቦታ የሆነውን ያክል ብዙ እሚያስቁ አጋጣሚዎችንም ታያላችሁ....በሴት ኒክ ሆነው ሴት እሚያባርሩ ወንዶች....በወንድ ኒክ ሆነው ሴት እሚያባርሩ ሴቶች ወዘተ....ዛሬ ዛሬማ እዛ ላይ ሰው አይደለም ሌላውን ጥላውን እማያምንበት ደረጃ ላይ ደርሱዋል....
....ደርሼ ልምጣ ....:)
ከኦንላይን ላይ አክቲቪቲዎች በሙሉ ፓልቶክ የሚባል ቦታ ደርሼ ስለማላውቅ የሚሰማኝን ደስታ ልነገርህ አልችልም .. አንድ ጊዜ አንድ ጉዋደኛዬ ፓልቶክ አበሻ ሩሞች ምናምን የሚባል ቧት ላሰማሽማ ሰው እንዴት እንደሚባልግ ብላ የሆነ ሩም ገብታ በሂወቴ ሰምቼ የማላውቃቸው ስድቦች እና ብልግናዎች ሰምቼ :shock: ብያለሁ .. ሰው በጤናው መቼም ምንም ቢሆን እንደዛ አይባልግም ! ቁምነገር የሚሰራባቸው አገር የሚገነባባቸው ጦርነት የሚታወጅባችው ሩሞች እንዳሉም ሰምቻለሁ :lol: :lol: ያንን ቦታ ጤነኛ ጭንቅላት እስካለኝ ደርስ ግን ፈጽሞ አልረግጠውም :lol:
"ሰነፍ በልቡ። አምላክ የለም ይላል በሥራቸው ረከሱ ጐስቈሉ በጎ ነገርን የሚሠራ የለም " መዝሙረ ዳዊት ምእራፍ 14:1
recho
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 3171
Joined: Mon Sep 20, 2004 12:28 pm
Location: Earth

(-:

Postby ደጉ » Sat Dec 22, 2012 2:09 pm

...ሰላም ሰላም አለም እንደ ተጠበቀችው አልጠፋችም ይገርማል...ስንት ነገር ጠብቀን ከስራ ቀርተን ላይፍ በቲቪ ፕሮግራሙን እናያለን ብለን ጉዋጉተን እንደ ገና ለሁድ ተላለፈ እሚባል ወሬ ሰማሁ...ለሁሉም ግን ትናንት የነበረው የእለቱ ፕሮግራም ለነገ 23ም አልተቀየረም....

ፕሮግራም :-

ጠዋት 05:00 ላይ የ ማያ ተወላጆች በስፍራው ይገኛሉ...
ጠዋት 06:00 ኤሊያኖች ይደርሳሉ እተመደበላቸውም ቦታ ይይዛሉ....
ጠዋት 07:00 የG8 መሪዎች በስፍራው ይገኛሉ
>> 08:00 መላእክቶች ቦታው ይደርሳሉ
>> 09:00 ፖፕ ቤኔዲክት አጭር ንግግር ያደርጋሉ...
ከዛም The HIGH WAY TO HELL እሚለው ዘፈን በ ዝነኛ የአለም አርቲስቶች በህብረት ከተዘፈነ በሁዋላ...የ ፕሮግራሙ ፍጻሜ ይሆናል
ማታ 17:00 የማያ ነዋሪዎች ወደ ቀድሞ ሂዎታቸው ይመለሳሉ....

..የፕሮግራም ለውጥ ካለ ከማሳወቅ ወደ ሁዋላ አልልም.. :D
"STUPID IS AS STUPID DOES " :D
ደጉ
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 4413
Joined: Mon Dec 15, 2003 10:39 am
Location: afghanistan

Re: (-:

Postby ተድላ ሀይሉ » Sat Dec 22, 2012 5:35 pm

ደጉ wrote:...ሰላም ሰላም አለም እንደ ተጠበቀችው አልጠፋችም ይገርማል...ስንት ነገር ጠብቀን ከስራ ቀርተን ላይፍ በቲቪ ፕሮግራሙን እናያለን ብለን ጉዋጉተን እንደ ገና ለሁድ ተላለፈ እሚባል ወሬ ሰማሁ...ለሁሉም ግን ትናንት የነበረው የእለቱ ፕሮግራም ለነገ 23ም አልተቀየረም....

ፕሮግራም :-

ጠዋት 05:00 ላይ የ ማያ ተወላጆች በስፍራው ይገኛሉ...
ጠዋት 06:00 ኤሊያኖች ይደርሳሉ እተመደበላቸውም ቦታ ይይዛሉ....
ጠዋት 07:00 የG8 መሪዎች በስፍራው ይገኛሉ
>> 08:00 መላእክቶች ቦታው ይደርሳሉ
>> 09:00 ፖፕ ቤኔዲክት አጭር ንግግር ያደርጋሉ...
ከዛም The HIGH WAY TO HELL እሚለው ዘፈን በ ዝነኛ የአለም አርቲስቶች በህብረት ከተዘፈነ በሁዋላ...የ ፕሮግራሙ ፍጻሜ ይሆናል
ማታ 17:00 የማያ ነዋሪዎች ወደ ቀድሞ ሂዎታቸው ይመለሳሉ....

..የፕሮግራም ለውጥ ካለ ከማሳወቅ ወደ ሁዋላ አልልም.. :D

ሰላም ደጉ:-

'ወይ ፍንክች የአባ ቢላዎ ልጅ' :lol: እኛ አለን:: ለወደፊቱም እንደ ፈጣሪ ፈቃድ እንኖራለን 8)

ተድላ
የወያኔ ሕገ -አራዊት አንቀፅ 39 ኢትዮጵያን የመበታተኛ ፈንጂ ነው !
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር !!!
ተድላ ሀይሉ ዘብሔረ -ኢትዮጵያ ::
ተድላ ሀይሉ
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 4903
Joined: Fri Mar 17, 2006 2:45 pm
Location: ኢትዮጵያ

Re: (-:

Postby ደጉ » Sat Dec 22, 2012 8:53 pm

recho wrote:.... ከኦንላይን ላይ አክቲቪቲዎች በሙሉ ፓልቶክ የሚባል ቦታ ደርሼ ስለማላውቅ የሚሰማኝን ደስታ ልነገርህ አልችልም ..

ቅቅቅቅቅ...ሪች ደስታሽ ትክክል ነው....እውነቱ ለመናገር መድረስም የሌለብሽ ቦታ..... ምን ትመክራለህ ብባል እኔም አትግቡ እንጂ ግቡ አልልም ወይ ሁሉም እንደሚለው አጠቃቀም ካወቅክ ወይም ካወቅሽ እሚል አባባል አልቀበልም... ይኔ ምክር መግባት መብታችሁ ነው...ባትገቡ ግን ይመረጣል ነው...:)
...አንድ ጊዜ አንድ ጉዋደኛዬ ፓልቶክ አበሻ ሩሞች ምናምን የሚባል ቧት ላሰማሽማ ሰው እንዴት እንደሚባልግ ብላ የሆነ ሩም ገብታ በሂወቴ ሰምቼ የማላውቃቸው ስድቦች እና ብልግናዎች ሰምቼ :shock: ብያለሁ ..

...ትክክል ከሩም ሩም ይለያያል ....ጸጥ ብለው ከሙዚቃ ውጪ ምንም እማትሰሚባቸው ሩሞች አሉ...ወሬ 24 ሙሉ እሚወራባቸው አሉ....እንደዚሁም እንደ ኢትዮ ላቭ....ቆንጆዎችና ሲንግል....ፍሪ ዩር ማይንድ...ኑና እና እንናጭ እሚል ሩምም ነበር .... የጴንጤም ሆነው ስፔሻል (ልሳን) ቁዋንቁዎች እሚነግርባቸውም አሉ...ትርጉሙን የት እንድማገኝ እስካሁን ተቸግሬአለሁ...ሌሎችም ሌሎችም...
...በጣም እሚገርምሽ እንደነዚህ አይነት የብልግና ሩሞች ውስጥ እና ፖለቲካ ሩሞች ውስጥ እሚገባው ሰው በጣም ብዙ ነው....ሳስበው ፖለቲካና ብልግና የሆነ ኮመን የሆነ ነገር ሳይኖራቸው አይቀርም...ወይ እዛም ስድብ እዛም ስድብ ስለሆነ ይሆናል... :D
....ሰው በጤናው መቼም ምንም ቢሆን እንደዛ አይባልግም ! ቁምነገር የሚሰራባቸው አገር የሚገነባባቸው ጦርነት የሚታወጅባችው ሩሞች እንዳሉም ሰምቻለሁ :lol: :lol: ያንን ቦታ ጤነኛ ጭንቅላት እስካለኝ ደርስ ግን ፈጽሞ አልረግጠውም :lol:

....ቅቅቅቅቅ...ጤናማ ቢሆን እማ ልክ ነሽ ..ችግሩ ግን ከጤነኛው በሽተኛው ይበልጣል...በሽታቸው ያብዛኞቹ የበታችነት ስሜት ሲሆን...ሌላው የተፈጥሮ ደደብነት ያለበት የ አእምሮ ድህ ነው....ሌላው ደግሞ በተለያዩ አገሮች በመንግስት ድጎማ እሚኖሩና ፈረንጅ አስቀምጦ በማጀዘብ እሚያሰለጥንልን ህብረተሰብ ነው... አፋቸውንም ሲከፍቱ ብሶታቸውን ትሰሚያለሽ....
...የዛኑ ያክል ደግሞ ጥሩ ሩሞች ውስጥ ጆይን እሚያደርጉ ጥሩ አስተሳሰብ ያላቸው የራሳቸውን ስራ እሚሰሩ ከወንድም ከሴትም ያጋጠሙኝ አሉ...እነዚህ ሰዎች ግን ከላይ የጠቀሻቸው የብልግና ሩሞች ውስጥ ጆይን እንደማያደርጉ መገመት ይቻላል...

መልካም በአል ይሁንልሽ
እኔ እንኩዋን በአሉ አይመለከተኝም. :D [/quote]
"STUPID IS AS STUPID DOES " :D
ደጉ
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 4413
Joined: Mon Dec 15, 2003 10:39 am
Location: afghanistan

Re: :-)

Postby Gosa » Thu Dec 27, 2012 9:11 am

ደጉ wrote:ሰላም ጎሳ :)
Gosa wrote:...ንጉሴ ማለት ከጀልዶ በስተቀር በጥቁርነት ማንም እዚያ ከተማ ውስጥ አይበልጠውም:: ጀልዶን እንኳ ሳታውቅ አትቀርም: የታምራት ሐኪሙ (ኬላ ሰፈር ያለው ፋርማሲ ባለቤት) ወንድም ወይም ዘመድ ነው መሰለኝ:: ጎሳን ያን ያህል የምታውቅ ከሆነ ንጉሴንም እንደምታውቀው እርግጠኛ መሆን እችላለሁ::

....ታምራት ፋርማሲስቱ ኦ! አወኩት....እሱ ሰውዬ እኮ ሲበዛ ንፋሳም ነበር....አንበሳ አድን ነበር ብሎ ሲያስቀኝ ነበር ... :D ከ አውራሪስ አዳኙ ጋ ተመሳሳይ የሆነ ታሪክ ነበር ...አዳኙ ጎበዙ ሰውዬ አውራሪስ ሊያድኑ ሄደው ...አውራሪሱ ድንገት ሲመጣባቸው አንድ ቁዋጥኝ ድንጋይ ጋ ሮተው ሲደበቁ....አውራሪሱ ከነ ቁዋጥኙ ወደ ሰማይ ሲያጎናቸው...ቅቅቅቅ ሰውየው በአየር ላይ እንዳሉ አቀባብለው ከላይ ሆነው አውራሪሱን ወደ ታች አነጣጥረው አናቱን መተው የገደሉት አይነት ታሪክ ወተት እየጠጣሁ ነበር የሰማሁት...ዛሬ ላይ ሆኘ ይቅር ብየዋለሁ... :D ወንድሙን ግን ላስታውሰው አልቻልኩም...ብዙ ጥቁዋቁር ስላየሁ ተምታታብኝ...ቅቅቅቅ ግን ከምር እሱ ግ ለመትከም ከምሄድ እዛ አንድ ቆንጆ የከብት ህኪም ነበረች ..እሱዋ ጋ ብሄድ ቶሎ እድናለሁ ብዬ አምናለሁ... :lol:
..አንተ በጣም በጣም ነዋ የምታውቃቸው:: የብራዘር ጆን ጥርስስ ተነቃቃይ መሆኑን ታውቅ ነበር?

...ጥርስ እንዳላቸውም አሁን ነው ትዝ ያለኝ :)
: ዛሬ ደግሞ ስለ አባ ጆ (ዮሴፍ) የጻፍከውን አንብቤ ስንት ነገር አስታወስከኝ:: መቼም እሳቸው የሰጡህ መዝገበቃላቱ እስካሁን ድረስ አይኖርም አይደል? በተለይ የዚያን አካባቢ ባህል አስመልክቶ ትልቅ መጽሀፍ ጽፈው ነበር:: ያላስፈለኩት ቦታ የለም:: ግን ላገኝ አልቻልኩም::

...ዲክሽነሪው አለ ግን አዲስ አበባ ነው ያለው ....የጻፉትን መጽህፍ ግን ማግኘት እምችል ይመስለኛል....እስኪ እሞክራለሁ...ከዛ እጠቁምህለሁ የት እንደምታገኘው::
...ሰሞኑን ያንተን ጽፉፎች ፌስቡክ ላይ ፖስት አድርጌ ስንት ሰው ላይክ እና ሼር አደረገ መሰለህ:: ቆንጆ ኮመንት ነው የሰጡህ:: ይድረስህ::

...ኦ! አመሰግናለሁ ...ለ ጻፉትም አመሰግናለሁ ብሉዋል በልልኝ...:)

በል ይመችህ ወንድሜ:: በቅርቡ እመለሳለሁ::

...በል አትቆይ :)

ሰላም ደጉ ሰው!
"ንፋሳም " ያልከው በጣም ነበር ያሳቀኝ:: በነገራችን ላይ ሰውየው አሁን በሕይወት የሉም:: ሲበዛ "ተጫዋች "ነበሩ:: ስለ እሳቸው ትዝ የምለኝ ነገር የከለር ምርጫቸው ነው:: ቢራ ሲጠጡ እንደ ስፕራይት ጠርሙስ ባለ አረንጓዴ ቀለም ካልቀረበላቸው አይጠጡም ይባላል::
ግን ከምር እሱ ግ ለመትከም ከምሄድ እዛ አንድ ቆንጆ የከብት ህኪም ነበረች ..እሱዋ ጋ ብሄድ ቶሎ እድናለሁ ብዬ አምናለሁ ...
:D :D ማን ትሆን እንዲህ ሰፍ ያልክላት? ለነገሩ ካመንክባት ያለመድሀኒት በግል ምክር ብቻም ልታድንህ ትችል ይሆናል :D ታምራት ግን በዚያ ምላሳቸው ብዙ ሰው ስለሚያሳምኑ ፋርማሲያቸው ደህና ገበያ ነበረው:: ወንድም ከመሰለኝ ጥቁሩ ጀልዶ ጋር ደግሞ ምንም የቅርብ ዝምድና እንደሌላቸው በቅርቡ ሰማሁ:: እስከዛሬ ተሸውጃለሁ ማለት ነው :(

ብራዘር ጆን ጥርስ እንደነበራቸውም ዛሬ ነው የሰማሁ አልከኝ :D :D ይቅር ይበልህ::
ስለ አባ ጆ መጽሀፍ ፍንጩን ካገኘህ በተለይ " Guji Oromo culture in southern Ethiopia " እንደምትጠቁመኝ እተማመናለሁ:: እኔ ጉግል አድርጌ አርእስቱን ባገኝም መጽሀፉን ማግኘት አልቻልኩም::
ሰላም ሁንልን
We must learn to live together as brothers or perish together as fools.
Martin Luther King, Jr.
Gosa
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 377
Joined: Mon Nov 21, 2011 2:43 pm
Location: ethiopia

PreviousNext

Return to Warka Intimate - ዋርካ ፍቅር

Who is online

Users browsing this forum: No registered users and 4 guests